አይናችን ነሽ ማርያም
TewodrosYosef (ሊቀመዘምራን)
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አይናችን ነሽ ማርያም አንችን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሃሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
አዝ
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
ባሸዋ ላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
አዝ
ገብተሻል አትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነዉ ባንች ነው የጠፋው ተገኝቶ
አዝ
ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሃረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራኒዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
አዝ
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ጸዋሪተ ፍሬ ያዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
አዝ
ከሃገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
ካደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጅ
ለጻድቃን አይደለም ለሃጥአን አማልጅ
TewodrosYosef (ሊቀመዘምራን)
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አይናችን ነሽ ማርያም አንችን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሃሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
አዝ
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
ባሸዋ ላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
አዝ
ገብተሻል አትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነዉ ባንች ነው የጠፋው ተገኝቶ
አዝ
ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሃረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራኒዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
አዝ
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ጸዋሪተ ፍሬ ያዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
አዝ
ከሃገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
ካደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጅ
ለጻድቃን አይደለም ለሃጥአን አማልጅ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
“ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደኾነ እንዲኹ ጸሎትን የማታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
“ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደኾነ እንዲኹ ጸሎትን የማታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
እናት አለኝ የምታስብ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ምህረት
አንባ መጠጊያ ናት
✥ ------------- ✥
ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
✥ ------------- ✥
ለዘለዓለም ንጽህት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሃዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
✥ ------------- ✥
ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
✥ ------------- ✥
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬን በልጅሽ ጣፈጠ
✥ ------------- ✥
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ምህረት
አንባ መጠጊያ ናት
✥ ------------- ✥
ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
✥ ------------- ✥
ለዘለዓለም ንጽህት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሃዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
✥ ------------- ✥
ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
✥ ------------- ✥
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬን በልጅሽ ጣፈጠ
✥ ------------- ✥
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር
እቴ ሙሽራዬ ሰለሞን ያለሽ (2x)
እኔም ልበልሽ እናቴ እመአምላክ ግቢ ከቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ ማርያም ግቢ ከቤቴ
ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበሲዘረጋ
የክብር ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና ( 4x ) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና
አዝማች…
ወርቀዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሀርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና
አዝማች …
አሳድጎሽ ሳለ መላኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መላክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና
አዝ…
የባሪያዉን ዉርደት ተመልክቷልና
ለወለድሽዉ ንጉስ ይድረሰዉ ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጅ ከቱዉን አይደለም
ብፅዕት እንላለን እኛም ለዘለዓለም
ነይ በደመና /4/
እመቤታችን እርህርይተ ህሊና
🕊🕊🕊አብረን እንዘምር🎤🎤🎤🕊🕊🕊
እኔም ልበልሽ እናቴ እመአምላክ ግቢ ከቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ ማርያም ግቢ ከቤቴ
ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበሲዘረጋ
የክብር ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና ( 4x ) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና
አዝማች…
ወርቀዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሀርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና
አዝማች …
አሳድጎሽ ሳለ መላኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መላክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና
አዝ…
የባሪያዉን ዉርደት ተመልክቷልና
ለወለድሽዉ ንጉስ ይድረሰዉ ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጅ ከቱዉን አይደለም
ብፅዕት እንላለን እኛም ለዘለዓለም
ነይ በደመና /4/
እመቤታችን እርህርይተ ህሊና
🕊🕊🕊አብረን እንዘምር🎤🎤🎤🕊🕊🕊
"እናንተ ደካሞች…"
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- “እናንተ ኃጢአት ሸክም
የሆነችባችሁ፣ እናንተ ጭንቀት አላኖር አላስቀምጥ ያላችሁ፣
እናንተ ሐዘን የደቆሳችሁ፣ እናንተ ትእዛዛቴን በመተላለፍ
ቅስማችሁ የተሰበራችሁ፣ እናንተ በሐፍረት ካባ ተከናንባችሁ
የምቆዝሙ፣ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ አበቃልኝ በቃኝ ብላችሁ ያንገሸገሻችሁ፣ እናንተ
ለመናገር እንኳን ድፍረት ያጣችሁ ምንም እንኳን ዝሙት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን
ዋሽታችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን ሰርቃችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን መናገር የማትችሉት
ከባድ የምትሉት ኃጢአት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን “ከእንግዲህ ወዲህ በቃ እግዚአብሔር
ይቅር አይለኝም” ብትሉም የእኔ ፍቅር፣ የእኔ ቸርነት ይህን ሁሉ ኃጢአታችሁ ይህን ሁሉ
ሸክማችሁ ይህን ሁሉ ሐዘናችሁ ይህን ሁሉ ከባድ የምትሉትን ነገራችሁ መደምሰስ የሚችል
ነውና ኑ፡፡
ኑና ላሳርፋችሁ፤ ኑና ስለ እናንተ የቆሰለውን እጄን ተደገፉ፤ ኑና ፍቅሬን ቅመሱ፤ ኑና ቸርነቴን
አጣጥሙ፤ ኑና ሸክማችሁን ሁሉ በእኔ ላይ አራግፉ፡፡ ብቻ እናንተ ፈቅዳችሁ ኑ እንጂ ከእኔ
ዓቅም በላይ የሆነ ሸክም የለባችሁምና አትስጉ፡፡ ኑና ሥርየተ ኃጢአትን ልስጣችሁ፤ ኑና
ዕረፍተ ነፍስን ሰጥቼ ላሳርፋችሁ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንኳ እንደ አመዳይ
አነጻላችኋለሁ፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ አጠራላችኋለሁ፡፡
ስለዚህ ኃጢአታችሁን እየቆጠራችሁ ከምትቆዝሙ ቀና በሉና ወደ እኔ ኑ፡፡ እኔ የዋህ
በልቤም ትሑት ነኝና ልጆቼ ወደ እኔ ቅረቡ፡፡ እኔም ልቅረባችሁ፡፡ “ቀንበሬን ተሸከሙ”
ስላችሁ በሩቁ አትፍሩኝ፡፡ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፡፡ ደግሞም ይህ ቀንበር
አንገታችሁን ለማለዘብ (ለመላጥ) ሳይሆን በቀጭኒቱ መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትሉ
እኔ ወዳዘጋጀሁላችሁ ርስት መንግሥት የምታደርስ ናትና በሩቁ አትፍሯት፡፡ ስለዚህ እናንተ
ደካሞች፣ እናንተ ዓቅመ ቢሶች፣ እናንተ ከእኔ ውጪ ምንም ማድረግ የማትችሉ በገዛ ደሜም
የገዛኋችሁ ልጆቼ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ማዳን ብቻ ሳይሆን አሳርፋችኋለሁ፡፡

✝መንፈሳዊ ህይወት✝ via @like
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 119)
----------
34፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።
35፤ እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
----------
34፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።
35፤ እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
[ - - - "#የህይወት_ህጎች" - - - ]
🌸🌸🌸🌼🌼🌼🌸🌸🌸🌼🌼
👉 ከመናገርህ በፊት | ☞ አስብ
👉 ከመፈረምህ በፊት | ☞ አንብብ
👉 ከማስተማርህ በፊት | ☞ ተማር
👉 ከመምከርህ በፊት | ☞ ተግብር
👉 ከመቁረጥህ በፊት| ☞ ለካ
👉 ከማጉደልህ በፊት | ☞ ተካ
👉 ከመዋጥህ በፊት | ☞ አላምጥ
👉 ከመገንዘብህ በፊት | ☞ አድምጥ
👉 ከማመንህ በፊት | ☞ አረጋግጥ
👉 ከመረከብህ በፊት | ☞ ቁጠር
👉 ከመወሰንህ በፊት | ☞ መርምር
👉 ከመስራትህ በፊት | ☞ አቅድ
👉 ከመተኮስህ በፊት | ☞ አልም
👉 ከመተቸትህ በፊት | ☞ አጣራ
👉 ከመብላትህ በፊት | ☞ ስራ
👉 ከመሞትህ በፊት | ☞ ነሰሃ ግባ
👉 ከመሄድህ በፊት | ☞ተስፋ ሰንቅ
👉 ስትወያይ-----☞ ሁን አስተዋይ
👉 ስትናደድ---- ☞ ቶሎ ብረድ
👉 ስትናገር---- ☞ በቁምነገር
👉 ስትቸገር---- ☞ መላ ፍጠር
👉 ስትቀመጥ---- ☞ ቦታ ምረጥ
👉 ስትወስን---- ☞ ቆራጥ ሁን!!
🌸🌸🌸🌼🌼🌼🌸🌸🌸🌼🌼
👉 ከመናገርህ በፊት | ☞ አስብ
👉 ከመፈረምህ በፊት | ☞ አንብብ
👉 ከማስተማርህ በፊት | ☞ ተማር
👉 ከመምከርህ በፊት | ☞ ተግብር
👉 ከመቁረጥህ በፊት| ☞ ለካ
👉 ከማጉደልህ በፊት | ☞ ተካ
👉 ከመዋጥህ በፊት | ☞ አላምጥ
👉 ከመገንዘብህ በፊት | ☞ አድምጥ
👉 ከማመንህ በፊት | ☞ አረጋግጥ
👉 ከመረከብህ በፊት | ☞ ቁጠር
👉 ከመወሰንህ በፊት | ☞ መርምር
👉 ከመስራትህ በፊት | ☞ አቅድ
👉 ከመተኮስህ በፊት | ☞ አልም
👉 ከመተቸትህ በፊት | ☞ አጣራ
👉 ከመብላትህ በፊት | ☞ ስራ
👉 ከመሞትህ በፊት | ☞ ነሰሃ ግባ
👉 ከመሄድህ በፊት | ☞ተስፋ ሰንቅ
👉 ስትወያይ-----☞ ሁን አስተዋይ
👉 ስትናደድ---- ☞ ቶሎ ብረድ
👉 ስትናገር---- ☞ በቁምነገር
👉 ስትቸገር---- ☞ መላ ፍጠር
👉 ስትቀመጥ---- ☞ ቦታ ምረጥ
👉 ስትወስን---- ☞ ቆራጥ ሁን!!
✝መንፈሳዊ ህይወት✝ via @like
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እንኳን ለቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)፣ ለቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት፣ ለአባ ቅፍሮንያ ጻድቅ፣ ለቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል) እንዲኹም ለቅድስት እግዚእ ክብራ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ዳግመኛም ዛሬ ኅዳር 8 ቀን ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት፣ አባ ብሶይ (ቢሾይ)፣ አቡነ ኪሮስ፣ አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን እንዲኹም ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!
"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯
🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼

❤️ክርስቶስ ፍቅር ነው❤️
ሰው ሲያፈቅር አፍቃሪ ይባላል
ሰው ሲያከብር አክባሪ ይባላል
ሰው ጸባይ ሲኖረው ፀባየኛ ይባላል
ሰው ሲታዘዝ ታዛዥ ይባላል
ሰው ሲታገስ ታጋሽ
ትእግስት ሲኖረው ትእግስተኛ
ሲታትር ታታሪ
ሲያስብ አሳቢ
ለሰው ሲራራ ሩህሩህ
ይባላል። ይሆን እንጂ ሁሉንም የሚያሟላ ይኖራልን?አይኖርም፡ሃጥያት ሳይሰራ የማይኖር የለምና።
በፍጹም አምላክነቱ ፍጹም ሰው የሆነው ጌታችን መድሃኒታችን ክርስቶስ እየሱስ ሁሉን አሟልቶ ነጥብ እንኳ እንከን ሳይገኝበት የተገኘውስ??????
አፍቃሪ ያንስበታል እንጂ፡ እርሱ ❤️ፍቅር❤️ ነውና
በክርስቶስ ፍቅር ተዋደን እንኑር

የሚጠብቀኝ አይተኛም
ዝማሬ ዳዊት
#የሚጠብቀኝ_አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም
ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ
አዝ
መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
አዝ
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
አዝ
የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ
አዝ
እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም
መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ
"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4
"ክርስቲያን ወገኖቼ እኛን የሚጠብቅ
አይተኛም እና አትፍሩ"
የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም
ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ
አዝ
መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
አዝ
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
አዝ
የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ
አዝ
እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም
መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ
"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4
"ክርስቲያን ወገኖቼ እኛን የሚጠብቅ
አይተኛም እና አትፍሩ"
ቅዱሳን አባቶቻችን "ስለ ምጽዋት" እንዲህ አሉ :–
★ "አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው"
(ቅዱስ ባስልዮስ)
★ "አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) (paraphrased)
★ "ወንድምህ ዕርቃኑን ወድቆ እያለቀሰ ነው ፣ አንተ ግን የሚያምር የወለል ንጣፍ ለመምረጥ ተቸግረህ ቆመሃል"
ቅዱስ አምብሮስ
★ "ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም"
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
★ "አባት ሆይ ወጪውን ሳናሰላ እንድንመጸውት አስተምረን"
(ቅዱስ አግናጥዮስ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
🌻🌼🌸🌺💐🌹🌷🍁🌻🌹
የልኡሉ እግዚአብሄር ቤተሰቦች
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆት ሆይ ይህንን አጭር መልእክት ታነቡልኝ ዘንድ በእናታችን ስም እጠይቃችኋለው።🌸🌸🌸🌸🌸🌸
❤️" ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።"❤️
💛(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5:12)💛
🔸ይህን ጥቅስ አባታችን በመልእክቱ ሲጽፍ ምን እንዳለን በስፋት እንመልከት።
🔸ልጁ ያለው ህይወት አለው ማለት የእግዚአብሄርን ልጅ(ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ)ያለው(እርሱ በውኑ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ የሚያምን)ሁሉ የዘለአለም ህይወትን ይወርሳል።
🔹የእግዚአብሄር ልጅ የሌለው ግን ህይወት የለውም ሲል ደግሞ ከዛ በተቃራኒው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ የማያምን የዘለአለም ህይወት የለውም ማለት ነው።ይህንንም ክርስቶስ ስለሱ ስለማያምኑት ሲናገር
" በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
"
💙(የዮሐንስ ወንጌል 3:36)💙
♦️የዘለአለም ህይወትን መውረስ እንፈልጋለን?
🔶 ይህን የዘለአለም ህይወት ለመውረስ የእግዚአብሄር ልጅ ሊኖረን እንደሚገባ አስረግጦ አባታችን ዮሃንስ አስቀምጦልናል።
🔹የእግዚአብሄር ልጅ አለኝ ለማለት ማመናችን ብቻ በቂ ነውን?
🔴ቢሆን ኖሮማ ሃጥያተኞች ቀራጮች እና ገዳዮችም በምስክርነታቸው ይድናሉ ማለት ነዋ።
🔹ይህ ደግሞ ፍጹም ስህተት ነው።እምነት ያለ ስራ ባዶ ነውና።
🔴ክርስቶስ የሚኖረን ታድያ ሃያሉ አምላካችን ከፊታችን ቀድሞ የሚዋጋልን ምን ስናደርግ ይሁን?
🔸መጽሃፍ ቅዱስ እንደሚለው ክርስቶስን እንዲገባ ስንፈቅድለት በሩን ስንከፍትለት ነው።አለምን አጥፍተን መንፈስ ቅዱስን ስንቀበል፡ስናነግስም ነው።
🙂ይህንን አሁን እያነበበ ያለ ሰው
❓አንተ ወይም አንች ለክርስቶስ በሩን ለመክፈት ዝግጁ ነህ/ነሽ?
🔸ሁኔታችንን እንመልከት።በእርግጥ ከልጅነታችን ጌታነቱን አምነን ተጠምቀን ክቡር መስቀሉን አስረን በማእተባችን የእርሱ እንደሆንን እናሳያለን።
🔊ውስጣችን ለመኖሩ ግን አለምን መጥላታችን ዋነኛ ነገር ነው።አለም ደግሞ ለገንዘብ ተገዢ ናትና።
🔸አለም ለይ ገንዘብ ከሌለ ህይወት የለም፡መንፈሳዊነት ለይ ግን ክርስቶስ ውስጣችን ከሌለ ህይወት የለም።
❓ውድ ቤተሰቦቼ ሆይ እስከመቼ ለሁለት ጌቶች እንገዛለን❔
🔸ሁላችንም አንመነው እንጂ
በአንድ ለእግዚአብሄር በአንድ ደግሞ ለገንዘብ ተገዚዎች ነን።
☑️ይህንን ማድረግ እንድናቆም፡በፍጹም እንዳንችል ደግሞ ጌታችን እንዲህ አስጠንቅቆናል።
" ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።"
❤️(የማቴዎስ ወንጌል 6:24)❤️
♦️እርሱ በኛ መኖሩን ታድያ በዚህ ሰአት የምናደርጋቸው አለማዊ ነገሮች እያየን እርግጠኛ መሆን እንችላለን?
🔘ያለፈው ያባከነው ጊዜ ሁሉ አልፏል።
⚫️ከዚህ በኋላ ላለው ግን ቅዱስ ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ተረድተን በአባቶቻችን ታግዘን በማንበብ ክርስቶስን በውስጣችን እናንግስ።
⚫️ህግጋቱን እና ትእዛዛቱን ሁሉ በማክበር እርሱን ተስፋችን አድርገን በፍቅሩ እየኖርን በጽናት እንጠብቀው።
✔️ይህንን ካደረግን በእርሱ እንደምንኖር እንዲህ ብሎ አረጋግጦልናልና።
✔️አንዴ በስጋ ከአባቱ አብ ለምኖ በሰጠን መንፈስቅዱስ እንደሚያኖረንም እንዲህ ብሎ ተናግሯል።
💛(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 14)💛
15-16፤ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
17፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
18፤ ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች 💜አልተዋችሁም፤💜 ወደ እናንተ እመጣለሁ።
19፤ ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ 💛እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ💛።
20፤ እኔ በአባቴ 💙እንዳለሁ 💙እናንተም በእኔ🖤 እንዳላችሁ🖤 እኔም በእናንተ ❤️እንዳለሁ ❤️በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።
21፤ ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም💛 የሚወደኝ እርሱ ነው💛፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ💚 ራሴንም እገልጥለታለሁ💚።
ስለዚህ ወገኖቼ ሁላችንም የመጨረሻ♦️ው ዘመን ነዋሪዎች ነንና፡የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቅርብ ነውና፡እስካሁን በሞኝነት ያጠፋነውን ጊዜ ረስተን በክርስቶስ አዲስ ፍጡር መሆናችንን ዳግም እንመስክር።
♦️በእርሱ የዘለአለምን ህይወት የምንጠብቅ ሁሉ እርሱ ንጹህ እንደሆነም እራሳችንን እናንጻ።
" በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።"
💙(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:3)💙
❤️💙💜🖤❤️💛💚💜🖤❤️💛
💜https://t.me//linkortodoxe21 💚
💛 https://t.me/linkortodoxe21 💜
💙💜❤️🖤💛💚🖤💜❤️💙💛
አስተያየት ካለ👉@mentesnhot

Telegram
✝መንፈሳዊ ህይወት✝
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟
መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇
https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟
መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇
https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን