መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንፁህ
ብትሆንም እንኳን አትፍረድበት።ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድ ብሏልና ።አባ ቴዎዶር
እግዚአብሔር ለሃጢኣተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል።አባ አርሳኒ
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (Mentesenhot)
#ጽጌ #ጾምን #በተመለከተ
ክርስቲያን ሲጾም ውሎ ሥጋ የሚበላ መሆን የለበትም። ጽጌ ጾም የፈቃድ ጾም ነው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ካህናት ሥጋ ሲበሉ ስታይ እንደ ይሁዳ እንደ ከሃድያን አድርጎ መቁጠር እና ማግለል ትልቅ ነውር ነው። እንዳውም አንዳንዶች የጽጌን ጾም አለመጾም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዳለመውደድና እንዳለማክበር አድርገው ሲቆጥሩም አይቻለሁ። ይሄም አንደኛው ችግር ነው። የፈቃድ ጾም ከበዓለ ፶ ውጭ ማንም ሰው መጾም ይችላል። ከ7ቱ የአዋጅ አጽዋማት ውጭ ባሉት በፍትሐ ነገሥት እንዳይጾምባቸው ከተደነገጉት እለታት ውጭ ደግሞ ማንኛውም ሰው መጾምም አለመጾምም ይችላል። ጽጌን ጾም ስትጾም ውለህ ካህን ለምን ሥጋ ይበላል ብለህ ሐሜት ካማህ ምኑን ጾምከው?

በዚህ ዙሪያ የጽጌን ጾም የሚጾሙ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን አሉ። እንደገና ቅዳሴ እንኳ ጠዋት የሚቀደስባቸው ደብሮች ጠዋት ይቀድሳሉ። የፈቃድ ጾም ስለሆነ ላይጾሙ ይችላሉ። ጠዋት ቀድሰው ወጥተው ጳጳሳትም ካህናትም ሊቃውንትም ሊበሉ ይችላሉ። አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ፣ እንዘ ተሐቅፊዮ እያሉ ማሕሌት አድረው ጠዋት ሥጋ ሊበሉ ይችላሉ። ምንም ወቀሳ የለባቸውም። እኔ የጾምኩትን የፈቃድ ጾም ሌላውም ካልጾመ ብሎ ድርቅ ማለት አገባብ አይደለም። ጾም ኃያል ነው። የቻለ ሰው ከዓመት እስከ ዓመት እንዳይጾምባቸው ከተደነገጉት እለታት ውጭ መጾም ይችላል። በዚህም በረከት ያገኝበታል። ነገር ግን እኔ ከዓመት እስከ ዓመት እንደጾምኩ ሌላውም ለምን አይጾምም ብሎ ሙግት አያስኬድም።

የጽጌ ጾም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደት እያሰብን የምንጾመው እንዲሁም ሊቃውንቱ "ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን" እያሉ በማሕሌት ነገረ ስደቷን እያወሱ የሚቆሙበት እለት ነው። ስለዚህ ጽጌን ጾም የሚጾመውም የማይጾመውም በመተማማት በመተቻቸት ሳይሆን፣ ዓይንና አፈር ሆነው ሳይሆን በፍቅር ሊያሳልፉት ይገባል።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷ አማላጅነቷ አይለየን።
#join or #share
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
🔵አንድ ቅዱስ አባት ማርያም ፊደል ናት አለ፤ ለምን ፊደል መማሪያ እንደ ሆነ እኛም በእርሷ ነገረ መለኮትን፣ ምስጢረ ተዋህዶን ተምረንባታል አውቀንባታል፤ አምላክ አስቀድሞ በሠማይ በልዕልና ሲኖር ተገልጾ አንድስ እንኳን ሠው ያየው አልነበረም አንድ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ተረከው እንጂ፤ ይህን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች ደግሞ ማን ናት? እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት እርሷ ከሴቶች ሁሉ ትለያለች ለምን የነፍሳችን መዳኛ የሆነውን ለነፍሳችን ረሃብ እውነተኛ ምግባችን፣ ለጥማችን ዘለዓለም የማንጠማበትን (ፍቅር፣ ክብር፣ ውዳሴ፣ አምልኮ ለእርሱ ይሁንና) ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደችልን፤ እመቤታችንን የወደድናትም ያወቅናትም ከመልዐኩ ብስራት ፤ከጌታችንም ሰው የሆነባት ቅጽበት በኋላ ነው፤ በእግዚአብሔር ሕሊና ግን ትታሰብ ነበር፤ ለነገሩ የአምላክ እናት አይደለችም እኛም በእርሱ ስለታሰብን የሚያስደንቅ አይደለም፤ እርሷ ግን ለድሕነት በልዩ ሁኔታ ትታሰብ ነበር፡፡

          🔹ለእኛ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? የእርሱን ክብር ከተረዳን የእመቤታችንን ክብር ማየት ቀላል ነው፤ የጌታችን የማዳኑ ስራን ከተረዳን እንሱ የማዳኑን ስራ ሲፈጽም ከውልደቱ እስከ ስቅለቱ የአዲስ ኪዳንን ሰማዕትነት ከሐዋርያትም ከማንም ክርስቲያኖች በፊት ሰይፍ በአንገቷ ያይደለ በልቧ ውስጥ አልፎ በስንት መከራና ተጋድሎ ያሳለፈች ድንቅ እናታችን እንረዳታለን እናውቃታለን፤ ወዳጆቼ! አምላክን ወልዶ መስጠት እንዲህ ቀላል ነገር አይደለም፤ ዛሬ ጭንቅላታቸውን እንደስንደዶ አሹለው እኛም ለመመረጥ ብቁ ነን የሚሉና ወደ ሰማይ ያለ አቅማቸው እንደሚንጠራሩት ሴቶች ጌታን መውለድ ለምድራዊ ክብርና ጉራ አይደለም፤ ጌታን ለመውለድ ሴት መሆን ብቻ በቂ አይደለም ከሴቶች ሁሉ መለየት እንዲሁም በዚያ በጨለማው ዘመን እነ ኢሳያስና ኤልያስ ጻድቅ ብጹዕ ባልተባሉበት ዘመን በጸጋ ተመልቶ ከሰው ተለይቶ በተለየ ክብር መገኘት ያስፈልግ ነበር፤ አንድ ጥይቄ ልጠይቅ፡- ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበስራት  ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ የከበርሽ ነሽ ያላት መቼ ነበር? ጌታን ጸንሳ ወይስ ከመጸነሷ በፊት? ወዳጄ! እመቤታችን ቀዳማዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በማህጸኗ ገና ሳያድን እነ ማኑሄን የገሰጸ መልዓክ ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ብላ እመቤታችን እስክትገረምና እስክትደነቅ ድረስ ለቀደሙት አባቶች ያልተሰጠው ክብርን ለዚያውም ከታላቅ መላዕክ አግኝታለች፤ ሁላችን ከጸጋ ጎድለን በነበረበት ጊዜ ላይ ጸጋን ጸሞልጋ የተገኘች እርሷ ናት፤  እመቤታችን አክብሩኝ አምላክን ካልወለድኩት ያለችው እርሷ ሳትሆን የመረጣት ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው እርሱ የወደደውንና የመረጠውን ደግሞ ማንም ሊያዋርደው ሊንቀው ክብሩንም ሊቀንስ አይችልም፤ ነገር ግን አምላክ ራሱ ትህትናዋን አይቶ ከሰዎች ሁሉ አከበራት፡፡

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ለዚህ ክብር ያብቃን
@linkortodoxe21
መልካም እለተ ሰንበት
@linkortodoxe21
አጋዕዝት ዓለም ሥላሴ
@linkortodoxe21
🔺የዕለቱ መልዕክት

(1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ 4)
----------
16፤ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።

17፤ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።

18፤ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።

20፤ ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

21፤ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ተግሳጽ

🗣ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ።

🗣ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል።

🗣የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል።

🗣 የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል።

🗣በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ።

🗣በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3
join join join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"እኛ እንዘምራለን ጠላት ይጨነቃል የደስታቸው ምንጩ ከወዴት ነው ይላል የሰላም መፍሰሻ አንቺ ነሽ ተስፋችን የመስቀል ስር ስነድ ማርያም እናታችን"
@linkortodoxe21
"ወዳጄ ሆይ!

👉መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡

👉 ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡

👉እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡

👉 እነዚህ በርግጥ አንተ ገንዘብ አድርገሃቸው እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥምህ ነውና፡፡

👉 ስለዚህ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡"

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21