መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
“የቤተክርስቲያን ሕይወት መስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠንክሩ፡፡”
ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ

@linkortodoxe21

“የረቡዕ ምግብ ለሐሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረቡዕ አይጠቅምም የሐሙስ ምግብም ለአርብ አይሆንም የነፍስና የሥጋ ነገርም እንዲሁ ነው፡፡”
አባ ጴሜን

@linkortodoxe21

“ሐዋርያት በልሳን የመናገር ጸጋ የተሰጣቸው በዓለም ዞረው ወንጌልን እንዲያስተምሩ ነው፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@linkortodoxe21

ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንደውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምሮ ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር፡፡
አንዲት ቀዳዳ አንድን ትልቅ መርከብ ታሰምጠዋለች አንዲት ኃጢአት አንድን ትልቅ ሰው ለውርደት ልታበቃው ትችላለች፡፡
ኃጢአትን መደበቅ ራሱ ኃጢአት ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ንስሐ ሥጋዊውን ፍላጎት በመንፈሳዊ ፍላጎት መተካት ነው፡፡
በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሸመነ የደጋ ልብሳችን፣ የእርቃናችን መሸፈኛ፣ ጌጥ እና ክብራችን፣ ሊጡ አእምሮ የቦካበት አዲሱ እርሾ፣ አልጫውን ያጣፈጠ ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

@linkortodoxe21

/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/
በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡

@linkortodoxe21

/ቅዱስ አውጉስጢን/
ሥጋን በንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለትና እንዲሁ  ነፍሱም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች፡፡ ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት በጾታ መፈላለግንና ይህን በመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርባታል የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋን ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል፡፡

☺️ @linkortodoxe21
☺️ @linkortodoxe21
☺️ @linkortodoxe21
🌼🌼🌼እንካን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🌼🌼🌼

@linkortodoxe21
🌼ምን ይጎለብታል 🌼
👉መላእክት በሰማይ ያመሰግናታል ቀና ጎንበስ ብለው ያገለግላታል
🌷ሀዋርያት መሪያችን ስንቃችን ይሏታል
🌷ሰማዕታት አክሊል መከታ ያደርጋታል
🌷ነብያት ትንቢታችን ቃላችን ይሏታል
🌷ደናግል መመኪያ አለኝታ ያረጋታል
፦ሁሉም እንደ ቋንቋው ያመሰግናታል የአምላክ እናት ሆና ምን ይጎልባታል?
@linkortodoxe21
🌷ዘማውያን በእሷ ነጽተናል እያሉ
ያመሰግናታል ደስታ እየተሞሉ ዕውራን በእሳ በርትተናል ብለው ያመሰግናታል ከፊቷ ላይ ቆመው 🌷አንካሶች ዘለሉ ተሞልተው በደስታ በእሳ ዳንን ብለው ከእስራት በሽታ
🌷ሄሮድስ የፈጃቸው ሕጻናት በሙሉ እሷን በማመስገን ያሸብሽባሉ ሁሉም በየቋንቋው ያመሰግናቷል
🌷የአምላክ እናት ሆና ምን ይጎልባታል???

Share share share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዐበይት እና ንዑሳን በዓላት መካከል አንዱ በዓለ መስቀል ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወርኃ መስከረም ብቻ በዓለ መስቀልን አራት ጊዜ ታከብራለች፡፡ የመጀመሪያው ምክንያተ ክብረ በዓል፣ በኢትዮጵያ ነግሦ የነበረው ዓፄ ዳዊት ከግብፅ ንጉሥና ሊቃነጳጳሳት የተላከለትን በቅዱስ ሉቃስ እጅ የተሳለችውን ስዕለ ማርያምን፣ በወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የተሳለውን ኩርዓተ ርእሱን ፣ ሌሎች ንዋያተ ቅድሳትን እና የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል የግብፅ እና ኢትዮጵያ ድንበር ከነበረችው አስዋን ከተባለችው ቦታ ተረክቧል፡፡
ንጉሡ የያዘውን በረከት ወደኢትዮጵያ ሳያደርስ ስናር በተባለው ቦታ ዐረፈ፡፡ ከጊዜ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ  ተቀብሎ በደብረ ብርሃን፣ በየረር፣ በመናገሻ እና በልዩ ልዩ ተራራማ ቦታዎች ሲዘዋወር ቆይቶ “መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አኑር”  የሚል ራእይ ተገልጦለት ቅዱስ መስቀሉን በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ በግሸን ደብረ ከርቤ አስቀምጦታል፡፡ መጋቢት ዐሥር ቀን ደብረ ብርሃን ሲገባ ብርሃን ስለወረደና ዐፄ ዳዊት ከግብፃውያን ጳጳሳት እና ንጉሥ እጅ መስቀሉን የተረከቡበትን ቀን በማዘከር የአድባራት እና የገዳማት ሊቃውንት ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው የብር መቋሚያ እና ጸናጽል  ይዘው ወደ ነገሥታቱ ሔደው ተቀጸል ጽጌ እያሉ  እያሸበሸቡ ጸሎተ ወንጌል  ያደርሱ ስለነበር መስከረም ዐሥር ቀን የዓፄ መስቀል በዓል ተብሎ ይከበራል፡፡


🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
መንፈሳዊ ህይወት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዐበይት እና ንዑሳን በዓላት መካከል አንዱ በዓለ መስቀል ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወርኃ መስከረም ብቻ በዓለ መስቀልን አራት ጊዜ ታከብራለች፡፡ የመጀመሪያው ምክንያተ ክብረ በዓል፣ በኢትዮጵያ ነግሦ የነበረው ዓፄ ዳዊት ከግብፅ ንጉሥና ሊቃነጳጳሳት የተላከለትን በቅዱስ ሉቃስ እጅ የተሳለችውን ስዕለ ማርያምን፣ በወንጌላዊው ቅዱስ…
መስቀሉ እንዴት ተገኘ?
አይሁድ መድኃኔዓለም እውር አበራ፣ ለምጽ አነጻ፣ አጋንንት አወጣ፣ ሙታንን አስነሳ፣ በሽተኞችን ፈወሰ፣ ብለው በሰይጣናዊ ቅንዓት ሰቅለው ከገደሉት በኋላ ከሙታን ተለይቶ መነሳቱ ሲገርማቸው የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ዕውር ሲያበራ፣ ሙት ሲያስነሳ፣ ልዩ ልዩ ደዌያትን ሲፈውስ አይተው የክርስቶስ መስቀል እንዲቀበርና ደብዛው እንዲጠፋ 300 ዓመታት ያህል በከርሠ ምድር ቀበሩት፡፡ አይሁድ የክርስቶስን መስቀል ለማጥፋት በጉድጓድ ጥለው የኢየሩሳሌም ነዋሪ ሁሉ ጉድፍ እንዲጥሉበት አደረጉ፡፡ ማንኛውም ቤተሰብ የቤቱን ጥራጊ እያመጣ መቃብሩ ላይ እንዲቆለል ተደረጎ ጥራጊ ሲጣልበት በመኖሩ ቦታው ኮረብታ ሆኖ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ለማውጣት ባይችሉ ክርስቲያኖቹ ቦታውን ያውቁት ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ጀኔራሎች በአስቫስያንና ጥጦስ ወረራ በ70 ዓ.ም ክርስቲያኖቹ ኢየሩሳሌምን ለቀው ስለወጡ መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ወዴት እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ዕሌኒ ንግሥት ልጇ ቆስጠንጢኖስ የክርስትና እምነት ፍቅርና ተቆርቋሪነቱ ቢኖረውም ገና አልተጠመቀም ነበርና አምኖ ተጠምቆ ወደ ክርስትና ሃይማኖት የገባልኝ እንደሆነ ወደ ኢየሩሳሌም ሄጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሳንፃለህ የተቀበረውን ቅዱስ መስቀሉን ፍለጋ አስፈላጊውን ሁሉ ራሴ አሟላለሁ ስትል ብፅዕት አድርጋ ስለነበር በአራተኛው መ/ክ/ዘ 337 ዓ.ም ከብዙ ሠራዊት እና መኳንንት ጋር ሆና ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች፡፡
ልጅዋ ቆስጠንጢኖስ ቅዱስ መስቀልን ከተቀበረበት ለማውጣት አስቦ ስለነበር እናቱ ከመንፈሳዊ ሃሳቡ ጋር በመተባበሩዋና ቅዱስ መስቀልን ለማስወጣት የነበሩትን ብፅዓት ለመፈጸም በማሰብ ተደሰቱ፡፡ አስቀድማ ሂዳ መስቀል ያለበትን ስፍራ እንድታጠና ሠራዊት ገንዘብ አሲዞ ላካት ዕሌኒም ኢየሩሳሌም ደርሳ ኮረብታ የሆነውን ሁሉ ብታስቆፍርም መስቀሉ ያለበትን ማግኘት አልቻለችም፡፡ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ የጎልጎታን ተራራ እንዲጠርጉ አዘዘች፡፡ በምንም ሁኔታ መስቀሉ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ከነሐሴ ወር ጀምራ ምሕላ ያዘች፣ ሱባኤ ገባች፡፡ ጊዮርጊስ ወልድ አሚድ ዕሌኒ ንግሥት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ ኤጲስ ቆጶስ አባ መቃርስን አገኘችውና መስቀሉ የተቀበረበት ስፍራ ጠየቀችው አባ መቃርስም ከሃዲዎቹ በላይ ብዙ አፈር አፍሰውበታል አፈሩም ትልቅ ተራራ አስከ መሆን ደርሷል ብሎ አስረዳት ይላል፡፡ ኪራኮስ የተባለም ሽማግሌ ወደ ንግሥቲቱ ቀርቦ መስቀሉ ያለበት ስፍራ ቀራንዮ መሆኑን አባቴ ነግሮኛል ተራራው ያ ነው፡፡ ብሎ ጎልጎታን አመልክቷል፡፡ በያዘችው ሱባኤ መልአከ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ መስቀሉን በእጣን ጢስ ታገኚዋለሽ ብሎ ነግሮአት ስለነበር ኅሊናዋ አልተጠራጠረም፡፡
የመላእኩንና የሽማግሌውን ቃል መሠረት አድርጋ በምድረ ይሁዳና ኢየሩሳሌም የነበሩትን ሕዝብ በጎልጎታ የሚደመር እንጨት እየያዛችሁ ኑ ብላ አዘዘቻቸው፡፡ መስከረም 16 ቀን ከየመንደራቸው እንጨት እየያዙ በጎለጎታ ተራራ ልይ ተደመሩ፡፡ ተደመሩትም እንጨቶች በእሳት አስለኮሰች፡፡ ብዙ ጊዜም የዕጣኑ ጢስ በተአምራት ከላይ ወደ ታች ተመልሶ መስቀሉ በተቀበረበት ሥፍራ ላይ ተተክሎ ታየ፡፡ የኢትዮጵያ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዕጣን የመስቀልን ሥፍራ አመለከተ፣ ጢስም ለመስቀሉ ሰገደ እያለ የዘመረው ለዚህ ነው፡፡ /ምዕራፍ ዘአርያም/ ንግሥት ዕሌኒ የዕጣን ጢስ ያመለከተውን ስፍራ ወዲያው መስከረም 16 ቀን ማስቆፈር ጀመረች፡፡ በብዙ ድካም በብዙ ጥረት በተፋጠነ ቁፋሮ መስቀሉ መጋቢት 10 ቀን ተገኘ

🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
መንፈሳዊ ህይወት
መስቀሉ እንዴት ተገኘ? አይሁድ መድኃኔዓለም እውር አበራ፣ ለምጽ አነጻ፣ አጋንንት አወጣ፣ ሙታንን አስነሳ፣ በሽተኞችን ፈወሰ፣ ብለው በሰይጣናዊ ቅንዓት ሰቅለው ከገደሉት በኋላ ከሙታን ተለይቶ መነሳቱ ሲገርማቸው የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ዕውር ሲያበራ፣ ሙት ሲያስነሳ፣ ልዩ ልዩ ደዌያትን ሲፈውስ አይተው የክርስቶስ መስቀል እንዲቀበርና ደብዛው እንዲጠፋ 300 ዓመታት ያህል በከርሠ ምድር ቀበሩት፡፡ አይሁድ…
ንግሥት ዕሌኒ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና ሁለቱ ወንወበዴዎች ጥጦስና ዳክርስ የተሰቀሉባቸው መስቀሎች በተገኘ ጊዜ ከእነዚህ ሁለቱ መስቀሎች ጌታችን የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል በምንአውቀዋለሁ ብላ ለኤጲስ ቆጶስ አባ መቃርስን ጠየቀችው አባ መቃርስም የጌታ መስቀል እንደ ልማዱ ሙት ላይ ሲያኖሩት ሙት ያስነሳልና በዚህ ለይተሽ ታውዋለሽ ብሎ ምልክት ነገራት፡፡ ወዲያው የጌታ መስቀል ሙት ላይ ቢያኖሩት ሙት ማስነሳቱ፣ ደዌ ቢያቀርቡለት ፈወሰ፡፡ ይህ የጌታችን የኢየሱስ መስቀል ብለው አመኑ፡፡ መስቀል እንዲው ችቦ አብርተው አበባ ይዘው እንዲህ አበራ፣ እንዲህም አበበ አብቦም ፍሬ ክብርን አፈራ እያሉ አሸበሸቡ፡፡
የምስራችንም የቆስጠንጢኖስ ዙፋን እስከነበረበት ቆስጠንጢንያ ድረስ አስተላለፈ፡፡ ከኢየሩሳሌም እስከ ቆስጠንጢኖስ ድረስ አስተላለፈ፡፡ ከኢየሩሳሌም እስከ ቆስጠንጢኖስ ድረስ የነበሩ ሕዝቦች ችቦ በማብራት በየደጁ ተሰብስቦ የደመራ እሳት ወጋገን በማሳየት አበባ ይዞ በመዘመር እልል በማለት ደስታውን በሕብረት ገለጡ፡፡
ዕሌኒ ንግሥት የጌታን መስቀል በማግኘቷ ስለተደሰተች ጌታ በተወለደበት ቤቴልሔም ጌታ በተቀበረበት ጎለጎታ ላይ አብያተ ክርስቲያናት ማሳነጽ ጀመረች፡፡ በዕንቍ በወርቅ በብር አስጌጠች አሠራች፡፡ ቆስጠንጢኖስም በገንዘብና በንዋየ ቅድሳት ረዳት፡፡ ቅዳሴ ቤተክርስቲያኑ መስከረም 17 ቀን የእስክንድርያ፣ የአንጾኪያ፣ የቆስጥንጥንያ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ኤጵስ ቆጶሳት መጥተው በዋዜማው መስቀል 16 ቀን ባረኩ፡፡ ቅዳሴ ቤቱንም አከበሩ፡፡ መስቀል ጥንዓ ይዘው ቅዱሳት መካናት ሁሉ ዞሩ ሥርዓተ ዑደት አደረጉ፡፡ የዕጣን ጢስ አመልክቶ ቁፈራ የተጀመረበትና ቅዳሴ  ቤቱ የተከበረበት አንድ ዕለት ሆነ በዚህም ዕለት ሆነ በዚያም ዕለት የዓለም ሕዝብ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም እየተሰበሰቡ በዓሉን በድምቀት ያከብሩት ነበር፡፡ ይህም መስቀል በኢየሩሳሌም ካስቀመጠችው በኋላ ዘረፉና ምርኮ አጋጥሟታል፡፡
ኢየሩሳሌም በየጊዜው ከጦርነት ከምርኮ ያላረፈች ሃገር በመሆኗ ቅዱስ መስቀልን በአሕዛብ እጅ እየተማረከ ቅዱስ ካንዱ ወዳንዱ መዘዋወሩ አልቀረም ነበር፡፡ የክርስቲያን ነገሥታትም በዚህ ነገር እየተናደዱ እየተቆጡ ጦራቸውን መስቀል ወደ ሔደበት ቦታ ሁሉ ከማዝመት አልተገዙም፡፡ ከዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው የሮም ንጉሥ ሕርቃል ነው፡፡ ሕርቃል በተንባላት ተማርኮ ወደ ፋርስ /ኢራቅ/ የሔደውን መስቀል በጦርነት አስመልሷል፡፡ የመስቀል ዘመቻና ጦርነት እየተባለ ብዙ ክርስቲያን ደም ፈሶበታል፡፡

ደመራ ማለት ምን ማለት ነው???????
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
😍የፍቅር እናት 😍
@linkortodoxe21
ምስለ ፍቁር ወልዳ
@linkortodoxe21
😍እንካን ለፆመ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ
ከመስከረም 26እስከ ህዳር 6ድረስ ለ40ቀን ይጾማል የእመቤታችን ስደት በማሰብ የእመቤታችን ረድኤት በረከት አማላጅነት አይለየን አሜን!!!

" እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 2:13)

@linkortodoxe19
🟡አገልግሎት ምንድን ነው🟡

🗣 አገልግሎት ማለት በፍቃደኝነት በተሰጠን ጸጋ(ስጦታ ) ልዑል እግዚአብሔርን ማገልገል ማለት ነው፡፡ለዚህ ደግሞ ሁሉም ተጠርቷል ፡፡
🗣አገልግሎት በእግዚአብሔር ጥሪ የሚጀመር መንፈሳዊ ተልዕኮ ነው፡፤እግዚአብሔር ሰዎችን ያገለግሉት ዘንድና የፍቅሩ ተሳታፊዎች ይሆኑ ዘንድ ይጠራል፡፡
🗣 አግልግሎት በእግዚአብሔር በሰው ልጆች መካከል ያለ የፍቅር መግለጫ ነው፡፡
🗣አግልግሎት ከእግዚአብሔር የተደረገልንን ውለታ ማሰብ ነው፡፡
🗣 አንድ አባት” ቤተ ክርስቲያን አምጥታናለች ፤ አስተምራናለች ለጌታችንም አንድንገዛ አድርጋናለች “ ብለዋል፡፡
🗣አገልግሎት ማለት ያዩትንእና የሰሙትን የእግዚአብሔርን ቸርነት መመስከር፡ያወቁትን መንፈሳዊ ዕውቀት ላላወቀ ማሳወቅ ማለት ነው፡፡
🗣የቤተ ክርስቲያን አገለግሎት ዋና ዓላማው የጠፋውን የሰው ልጅ ለድኀነት ማብቃት ነው፡፡ ሰው ለድኀነት የሚበቃው አዕማደ ምሥጢራትን አምኖ ሲፈጽም በአመነበት እምነት ጸንቶ ከኃጢአት በመጠበቅ እግዚአብሔርን ሲያገልግል ነው፡" የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።"
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:15)

🌷 @linkortodoxe21
🌷 @linkortodoxe21
🌷 @linkortodoxe21
ብዙ ወጣቶች በዚህ ጊዜ በዝሙት (በግለ ወሲብ)እሰቃያሉ

ግለ ወሲብ በማድረግ ለተቸገራችሁ በሙሉ መፍትሄ፥

በመጀመሪያ፦
፠ ከማንኛውም ስሜት ቀስቃሽና ዝሙትን ከሚያሳስቡ ድርጊቶች መራቅ
፠ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም የመሳሰሉ ማህበራዊ ድህረ ገፆች መመልከት ማቆም።
፠ በቴሌግራምም ላይ ያልተገቡ ግሩፕ ወይም ፔጅ ላይ አለመገኘት።
፠ በስልካችን ጎግል ስንጠቀም ለአዋቂዎች መተግበሪያዎችን በማንሳት ወይም safe browsing ON በማድረግ ማንኛውም አላስፈላጊ ውጤቶች እንዳይመጡ ማድረግ
፠ እጅን በሀፍረተ ስጋ አከባቢ አለማኖር
፠ በስልክ ሆነ በአካል ከተቃራኒ ፆታዎች ጋር የሚደረጉ አላስፈላጊ ንግግሮችንም ሆነ ልፊያ ማቆም።
፠ የዝሙት ፊልሞችን፣ የሩካቤ ትዕይንት ያለባቸውን ፊልሞች፣ መገላለጥ የበዛባቸውን የሙዚቃ ክሊፖችና በጠቅላላው ስሜት አነቃቂ ምስሎችን ማየት ማቆም።
፠ ራሴን መቆጣጠር እችላለሁ ብሎ አለመደፋፈር።

ሁለተኛ፦
፠ አበዝቶና በየቀኑ ዘለግ ያለ የአምልኮት ስግደት መስገድ፤ መንፈሱ በሥጋ ላይ ስለሚቀመጥ እንዲሁም በፀሎት ሰዓት የተለያየ ምስል በአይምሮ ላይ ስለሚከስትና ሀሳብ ስለሚበታትን፣ በተቻላችሁ መጠን ዝም ብሎ ላብ እስኪወጣ ድረስ መስገድ
፠ ፀሎት ጠዋትና ማታ ማድረግ፤ በዋንኛነት ድርሳነ ማህየዊ፣ ትምህርተ ህቡአት፣ ሰይፈ ስላሴ ዘዘወትር፣ ሰኔ ጎሎጎታ እና መልክአ ሩፋኤልን መፀለይ
፠ ትንሽ ፀሎት ብዙ ስግደት አድርጉት፤ ከአልጋ ስትወርዱና ወደ መኝታ ስትሄዱ ተግብሩት፤ የዝሙት መንፈስ በአይምሮ፣ በእጅ፣ በሃፍረተ ሥጋ ላይ ስለሚቀመጥ የስግደት ላባችሁ ያቃጥለዋል።
፠ ፀሎት ስታደርጉ በሳምንት እና በዕለታት ከፋፍላችሁ የጠቀስኳቸውን ፀሎቶች እየሰበዙ መፀለይ፤ በነገራችን ላይ ርኩስ መንፈስ ፀሎት ይለምዳል። መልክአ ሩፋኤልን ማታ ሁሌም ልንተኛ ስንል መፀለይ።
፠ መዝሙር ማዳመጥ፣ ስበከትና ገድላት መስማት፣ ጉባኤ መካፈል፣ ቅዳሴ ማስቀደስ፤ በኤርፎን እያደረጋችሁ ማዳመጥ፣ መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ
፠ ፆም የተባለ በሙሉ አፍ እስኪመር ድረስ መፆም

ሥስተኛ፦
፠ ይህን ስታደርጉ እንደናንተ ብርታት ሆነ እንደ መንፈሱ አይነት ሌሊት በተኛችሁበት ይመጣል፤ ይህ ማለት ዝንየት ሊመታችሁ ይችላል። በህልማችሁ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ሩካቤ እንድትፈፅሙ እያደረገ ያስቸግራችኋል።
፠ በነገራችን ላይ ማንኛውም የዝሙት ወይም የሩካቤ ህልም ከእግዚአብሄር አይደለም። የገዛ ባለቤታችሁም ሆነ ፍቅረኞቻችሁም ቢሆኑ፤ በአጭሩ የእነርሱን መልክ ይዞ በህልም ይመጣል እንጂ፣ ያ የምትወዱት ሰው በህልማችሁ መጥቶ እንዳልሆነ ተገንዘቡ።
፠ በአብዛኛው በህልም፣ ወሲብ ሳይሆን ራቁት ገላ ያሳያችኋል፣ ፍላጎታችሁን ያነሳሳል። ከዛ እንዳማራችሁ አድርጎ ከህልማችሁ ያነቃችኋል። ቀኑን ሙሉ ስለዛ ሰው እንድታስቡ፣ ያለ አግባብ በስሜት እንድትቃጠሉ ያደርጋል።
፠ እየበረታችሁ ስትሄዱ፣ አልጋችሁ ላይ ሌሊት እንደሚከብድ ነገር ሆኖ ሊመጣም ሆነ እንደ ድምፅ ሊሰማችሁ ይችላል፤ በተደጋጋሚ ትባትታላችሁ። በነገራችን ላይ መንፈስ ሊገባም ሲል ሆነ ሊወጣ ወይም ሊያዝ ሲል በተደጋጋሚ መቃዠትና መባተት ምልክቱ ነው።
፠ ሌላው በጣም ከበረታችሁና መቆጣጠር ስትጀምሩ በህልማችሁ የምትመጣውን ሴት ወይም መንፈስ፤ አንተ ሰይጣን ዞር በል በሉት፣ መልኩን ይቀይራል። ሴቶች ደግሞ የሚያሳያችሁን ወንድ አንቺ ሴት ሰይጣን ዞር በይ በሏት።
፠ መንፈስ ሲነቃበት ይጋለጣል፣ ስራው ይከሽፋል። ፆታ ኖሮት ሳይሆን ወንድ ላይ ሴት፣ ሴት ላይ ደግሞ ወንድ ሆኖ ስለሚገለጥ ነው። ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ሆኖ ከታያችሁ የግብረ ሰዶም መንፈስ ነው ማለት ነው።

አራተኛ፦
፠ ለምትወዱት ታቦት እንዲረዳችሁ ስዕለት ተሳሉ
፠ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ፀበል መጠመቅ ነው፤ ፀበል መጠመቅ መጨረሻ የመጣው። ሰይጣን ሞኝ አይደለም አንድ ቦታ አይቀመጥም፤ ቤተመቅደስ ስትገቡ አይገባም። ፀበል ስትጠመቁ አይጠመቅም። ፀሎት ስታደርጉ አያደርግም። በተለይ አብሮ የተወለደ የዛር መንፈስ ማለትም አይነጥላ ከሆነ በደንብ ያቃችኋል አሁንም እደግመዋለሁ በደንብ አድርጎ ጠንቅቆ ያቃችኋል። ነገር ግን ማደሪያና ማረፊያ ስለሌለው ተመልሶ ይገባል።ቤቴ ነው ብሎ ስለሚያስብ ነው። ከተነቃበት እና ከታሰረ ግን የትም አይሄድም።

በመጨረሻም፦
፠ ትግሉ ሊከብዳችሁ፣ እልህ አስጨራሽ ሊሆን ይችላል በተለይ ሊጋለጥ ሲል ትግሉ እጅግ ይበረታል። በየዕለቱ ብትወድቁ፣ ሳምንቱን በሙሉ ብትሰናከሉ፣ ወሩን በሙሉ በኃጢያት ብትወድቁ፤ መውደቅ ሁሌም ያለ የሚኖር ነው፤ አቧራችሁን አራግፋችሁ መነሳትና ለታላቅ ተጋድሎ መበርታት ነው።

ለማወቅ ያህል፤ ዛር አይነጥላ፣ ቡዳ አይነጥላ፣ ቡዳ፣ ሳጥናኤል፣ ሉሲፈር፣ ራሄሎ፣ ሮሃንያ ይባላሉ ይህን ግለ ወሲብ የሚያስፈፅሙት መንፈሶች።

በርቱ። አምላከ ተክለሃይማኖት ከእናንተ ጋር ይሁን። ይቆየን። shere በማድረግ የእግዚአብሔርን ህዝብ እናድን 🙏🙏🙏🙏
👍1
ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንፁህ
ብትሆንም እንኳን አትፍረድበት።ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድ ብሏልና ።አባ ቴዎዶር