መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 138)
----------
2፤ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3፤ በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት።

4፤ አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።

5፤ በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ፤ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና።

@linkortodoxe21
" ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13)

@linkortodoxe21
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 42)
----------
1፤ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።

2፤ ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?

3፤ ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።

4፤ ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።

@linkortodoxe21
✟✟✟ሰላም በክርስቶስ ይብዛላችሁ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በቀን በቀን እናንተን ያስተምራሉ በሚል በቀን በቀን ከ1እስከ 3ጥያቄ አዘጋጅተናል ከእናንተ የሚጠበቀው መሳተፍ ብቻ ነው።
ለማንኛውም ነገር @Eyasues በዚ ያናግሩኝ
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 3)
----------
14፤ አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤

15፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።

16-17፤ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
" አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፤ አሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።"
(መዝሙረ ዳዊት 144:9)

🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” እንዳለ /2ኛ ጢሞ.3፥16/፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው ቅዱሳን አባቶቻችን ከጻፉት መጻሕፍት ጠቃሚ ምክሮችን እነሆ ብለናል
የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትሥራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት ዕወቅ”

📚መጽሐፈ ምክር
@linkortodoxe21
"የቤተክርስቲያን ሕይወት መስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠንክሩ፡፡”

ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ
@linkortodoxe21
“የቤተክርስቲያን ሕይወት መስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠንክሩ፡፡”
ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ

@linkortodoxe21

“የረቡዕ ምግብ ለሐሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረቡዕ አይጠቅምም የሐሙስ ምግብም ለአርብ አይሆንም የነፍስና የሥጋ ነገርም እንዲሁ ነው፡፡”
አባ ጴሜን

@linkortodoxe21

“ሐዋርያት በልሳን የመናገር ጸጋ የተሰጣቸው በዓለም ዞረው ወንጌልን እንዲያስተምሩ ነው፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@linkortodoxe21

ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንደውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምሮ ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር፡፡
አንዲት ቀዳዳ አንድን ትልቅ መርከብ ታሰምጠዋለች አንዲት ኃጢአት አንድን ትልቅ ሰው ለውርደት ልታበቃው ትችላለች፡፡
ኃጢአትን መደበቅ ራሱ ኃጢአት ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ንስሐ ሥጋዊውን ፍላጎት በመንፈሳዊ ፍላጎት መተካት ነው፡፡
በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሸመነ የደጋ ልብሳችን፣ የእርቃናችን መሸፈኛ፣ ጌጥ እና ክብራችን፣ ሊጡ አእምሮ የቦካበት አዲሱ እርሾ፣ አልጫውን ያጣፈጠ ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

@linkortodoxe21

/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/
በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡

@linkortodoxe21

/ቅዱስ አውጉስጢን/
ሥጋን በንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለትና እንዲሁ  ነፍሱም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች፡፡ ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት በጾታ መፈላለግንና ይህን በመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርባታል የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋን ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል፡፡

☺️ @linkortodoxe21
☺️ @linkortodoxe21
☺️ @linkortodoxe21
🌼🌼🌼እንካን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🌼🌼🌼

@linkortodoxe21
🌼ምን ይጎለብታል 🌼
👉መላእክት በሰማይ ያመሰግናታል ቀና ጎንበስ ብለው ያገለግላታል
🌷ሀዋርያት መሪያችን ስንቃችን ይሏታል
🌷ሰማዕታት አክሊል መከታ ያደርጋታል
🌷ነብያት ትንቢታችን ቃላችን ይሏታል
🌷ደናግል መመኪያ አለኝታ ያረጋታል
፦ሁሉም እንደ ቋንቋው ያመሰግናታል የአምላክ እናት ሆና ምን ይጎልባታል?
@linkortodoxe21
🌷ዘማውያን በእሷ ነጽተናል እያሉ
ያመሰግናታል ደስታ እየተሞሉ ዕውራን በእሳ በርትተናል ብለው ያመሰግናታል ከፊቷ ላይ ቆመው 🌷አንካሶች ዘለሉ ተሞልተው በደስታ በእሳ ዳንን ብለው ከእስራት በሽታ
🌷ሄሮድስ የፈጃቸው ሕጻናት በሙሉ እሷን በማመስገን ያሸብሽባሉ ሁሉም በየቋንቋው ያመሰግናቷል
🌷የአምላክ እናት ሆና ምን ይጎልባታል???

Share share share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዐበይት እና ንዑሳን በዓላት መካከል አንዱ በዓለ መስቀል ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወርኃ መስከረም ብቻ በዓለ መስቀልን አራት ጊዜ ታከብራለች፡፡ የመጀመሪያው ምክንያተ ክብረ በዓል፣ በኢትዮጵያ ነግሦ የነበረው ዓፄ ዳዊት ከግብፅ ንጉሥና ሊቃነጳጳሳት የተላከለትን በቅዱስ ሉቃስ እጅ የተሳለችውን ስዕለ ማርያምን፣ በወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የተሳለውን ኩርዓተ ርእሱን ፣ ሌሎች ንዋያተ ቅድሳትን እና የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል የግብፅ እና ኢትዮጵያ ድንበር ከነበረችው አስዋን ከተባለችው ቦታ ተረክቧል፡፡
ንጉሡ የያዘውን በረከት ወደኢትዮጵያ ሳያደርስ ስናር በተባለው ቦታ ዐረፈ፡፡ ከጊዜ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ  ተቀብሎ በደብረ ብርሃን፣ በየረር፣ በመናገሻ እና በልዩ ልዩ ተራራማ ቦታዎች ሲዘዋወር ቆይቶ “መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አኑር”  የሚል ራእይ ተገልጦለት ቅዱስ መስቀሉን በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ በግሸን ደብረ ከርቤ አስቀምጦታል፡፡ መጋቢት ዐሥር ቀን ደብረ ብርሃን ሲገባ ብርሃን ስለወረደና ዐፄ ዳዊት ከግብፃውያን ጳጳሳት እና ንጉሥ እጅ መስቀሉን የተረከቡበትን ቀን በማዘከር የአድባራት እና የገዳማት ሊቃውንት ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው የብር መቋሚያ እና ጸናጽል  ይዘው ወደ ነገሥታቱ ሔደው ተቀጸል ጽጌ እያሉ  እያሸበሸቡ ጸሎተ ወንጌል  ያደርሱ ስለነበር መስከረም ዐሥር ቀን የዓፄ መስቀል በዓል ተብሎ ይከበራል፡፡


🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷
🌷 @linkortodoxe21 🌷