መንፈሳዊ ህይወት
4.02K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 138)
----------
2፤ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3፤ በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት።

4፤ አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።

5፤ በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ፤ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና።

@linkortodoxe21
" ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13)

@linkortodoxe21
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 42)
----------
1፤ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።

2፤ ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?

3፤ ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።

4፤ ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።

@linkortodoxe21
✟✟✟ሰላም በክርስቶስ ይብዛላችሁ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በቀን በቀን እናንተን ያስተምራሉ በሚል በቀን በቀን ከ1እስከ 3ጥያቄ አዘጋጅተናል ከእናንተ የሚጠበቀው መሳተፍ ብቻ ነው።
ለማንኛውም ነገር @Eyasues በዚ ያናግሩኝ
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 3)
----------
14፤ አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤

15፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።

16-17፤ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
" አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፤ አሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።"
(መዝሙረ ዳዊት 144:9)

🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
🌼 @linkortodoxe21
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” እንዳለ /2ኛ ጢሞ.3፥16/፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው ቅዱሳን አባቶቻችን ከጻፉት መጻሕፍት ጠቃሚ ምክሮችን እነሆ ብለናል
የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትሥራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት ዕወቅ”

📚መጽሐፈ ምክር
@linkortodoxe21
"የቤተክርስቲያን ሕይወት መስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠንክሩ፡፡”

ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ
@linkortodoxe21
“የቤተክርስቲያን ሕይወት መስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠንክሩ፡፡”
ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ

@linkortodoxe21

“የረቡዕ ምግብ ለሐሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረቡዕ አይጠቅምም የሐሙስ ምግብም ለአርብ አይሆንም የነፍስና የሥጋ ነገርም እንዲሁ ነው፡፡”
አባ ጴሜን

@linkortodoxe21

“ሐዋርያት በልሳን የመናገር ጸጋ የተሰጣቸው በዓለም ዞረው ወንጌልን እንዲያስተምሩ ነው፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@linkortodoxe21

ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንደውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምሮ ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር፡፡
አንዲት ቀዳዳ አንድን ትልቅ መርከብ ታሰምጠዋለች አንዲት ኃጢአት አንድን ትልቅ ሰው ለውርደት ልታበቃው ትችላለች፡፡
ኃጢአትን መደበቅ ራሱ ኃጢአት ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ንስሐ ሥጋዊውን ፍላጎት በመንፈሳዊ ፍላጎት መተካት ነው፡፡
በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሸመነ የደጋ ልብሳችን፣ የእርቃናችን መሸፈኛ፣ ጌጥ እና ክብራችን፣ ሊጡ አእምሮ የቦካበት አዲሱ እርሾ፣ አልጫውን ያጣፈጠ ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

@linkortodoxe21

/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/
በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡

@linkortodoxe21

/ቅዱስ አውጉስጢን/
ሥጋን በንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለትና እንዲሁ  ነፍሱም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች፡፡ ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት በጾታ መፈላለግንና ይህን በመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርባታል የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋን ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል፡፡

☺️ @linkortodoxe21
☺️ @linkortodoxe21
☺️ @linkortodoxe21
🌼🌼🌼እንካን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🌼🌼🌼

@linkortodoxe21