መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 99)
----------
1፤ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።

2፤ እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

3፤ ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ።

4፤ የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።

5፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

🙏 @linkortodoxe21
🔵የጸሎት ጊዜያት

“ስብዐ ለዕለትየ እሴብሐከ” /በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ/ /መዝ. 118፡164/ ሲል ነቢዩ ዳዊት በተናገረው መሠረት በቀን ሰባት ጊዜ መጸለይ እንደሚገባ ታዟል፡፡

ይህም እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

1.ሰው ከእንቅልፍ ነቅቶ ከመኝታው ተነስቶ ገና ሥራ ሳይጀምር የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ /በነግህ/

2.በ3 ሰዓት

3.በ6 ሰዓት

4.በ9 ሰዓት

5.በ11 ሰዓት /በሠርክ/

6.በመኝታ ጊዜ

7.በመንፈቀ ሌሊት /ከሌሊቱ በ6 ሰዓት/

7ቱ የጸሎት ጊዜያት ከላይ የተገለጹት ሲሆኑ በተለይ የጧትና የሠርክ ጸሎት በቤተክርስቲያን መሆን እንዲገባው ታዟል፡፡

የሦስት ሰዓትና የሌሎች ጊዜያት ጸሎት ግን በቤትም ቢሆን በሌላ ቦታ ቢጸለይ አይከለከልም፡፡ ከነዚህ ጊዜያቶች የአንዱ የመጸለያ ጊዜ ቢደርስና የሚጸልየው ሰው ለመጸለይ ከማይችልበት ቦታ ቢሆን በልቡ የሕሊና ጸሎት ማድረስ እንዲገባው ታዟል፡፡

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ሀሳበ ልቡናችንን እንዲፈጽምልንና እንዲሁም ከልዩ ልዩ ፈተናና መከራ እንዲያድነን ሁልጊዜ መጸለይ ይገባል፡፡ ሰው ፈተና፣ መከራ ሲገጥመው ይጨነቃል እንቅልፍ ያጣል እንቅልፉ ጭንቀት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጭንቀት ምንም የሚገኝ ነገር የለም፡፡ ይህንንም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው” /ማቴ. 6፡27/ ሲል ተናግሯል፡፡

ፈተና፣ መከራ ሲገጥመን ተግተን መጸለይ እንጂ መጨነቅ አይገባም፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ “በምንም አትጨነቁ ነገር ግን ጸልዩ እያመሰገናችሁ ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ” /ፊልጵ. 4፡6/ ሲል ተናግሯል፡፡

ይህ ዓለም የፈተና፣ የመከራ ዓለም ነው፡፡ እንደውም በዚህ ዓለም ስንኖር ከደስታው ይልቅ የሚያመዝነው ፈተናው፣ መከራው ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የምንቋቋመው በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር በመነጋገር ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተግተን በመጸለይ ከፈተና እንደምንድን ሲገልጽ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት” /ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ/ /ማቴ. 26፡41/፡፡

በዚህ መሠረት አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከፈተና፣ ከመከራ እንዲያድነን ተግተን እንጸልይ፡፡

ንስሓ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲሁም በቅዱሳን አማላጅነት ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ልዑል እግዚአብሔር ወሰን በሌለው ቸርነቱ ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ የአምላክን እናት እናወድስ ከፍቅራ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ "

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 138)
----------
2፤ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3፤ በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት።

4፤ አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።

5፤ በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ፤ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና።

@linkortodoxe21
" ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13)

@linkortodoxe21