መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
ሥርዓተ ጸሎት

ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” /የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን/ ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡-ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🔴1.በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል

በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/

🔴2.በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል

በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል፡፡ ልባችንን የቂም በቀልና የክፋት ምሽግ አድርገን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ “ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመዘርዕ ዘወድቀ ማእከለ አሥዋክ” /የቂመኛ ሰው ጸሎት በእሾህ መካል እንደ ወደቀ ዘርዕ ነው/ /መጽሐፈ መነኮሳት/፡፡

🔴3.ሀሳባችንን ሰብስበን አንድ ልብ በመሆን መጸለይ ይገባል

ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የጰራቅሊጦስ ዕለት አንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ /የሐ. ሥራ 2፡1-4/

🔴4.በመፍራት ማለት ንስሐ በመግባት ከልብ በመጸጸት መጸለይ ይገባል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

ነቢዩ ሕዝቅያስ በመፍራትና ከልብ በመጸጸት ሆኖ ስለጸለየ በዕድሜው ላይ አሥራ አምስት ዓመት ተጨምሮለታል፡፡ /2ኛ ነገሥት 20፡1-6/ /ኢሳ. 38፡1-5/

🔴5.በጸሎት ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ተሠርቷል

“በጽባሕ እቀውም ቅድሜከ ወአስተርኢ ለከ”

/በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እታይሀለሁም/ /መዝ. 5፡3/

🔴6.ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ይገለጽ ዘንድ የተነገረለት ነውና ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

🔴7.በጸሎት ጊዜ መስገድ ይገባል

ይኸውም ጸሎቱን ስንጀምርና ስንጨርስ እንዲሁም በጸሎት ጊዜ ስግደትን ከሚያነሳ አንቀጽ ስንደርስ መስገድ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

🔴8.ጸሎት ስንጀምር በትእምርተ መስቀል /በመስቀል ምልክት/ ማማተብ ይገባል

ስናማትብም ከላይ ወደታች ከግራ ወደ ቀኝ ነው፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፡፡ ከላይ ወደታች የምናማትብበት ምክንያት የሰላም አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት የመውረዱ ምሳሌ ነው፡፡ ከግራ ወደቀኝ የምናማትብበት ምክንያት ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ስለእኛ ሞቶ ከሞት ወደ ሕይወት ከኀሣር ወደ ክብር፣ ከሲኦል ወደገነት የመመለሱ ምሳሌ ነው፡፡ በቀኝ ገነት፣ በግራ ሲኦል ይመሰላልና፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

በመስቀል አምሳል የምናማትብባቸው ጊዜያቶችም ጸሎት ሲጀመርና መስቀሉን ከሚያነሳ አንቀጽ ሲደረስ ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

🔴9.ዐይኖችን ወደላይ አቅንቶ መጸለይ ይገባል

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ባስነሳው ጊዜ ዐይኖቹን ወደላይ አቅንቶ እንደጸለየ ሁሉ የሚጸልይ ሰው ዓይኖቹን ወደ ላይ ማንሳት እንዲገባ ነው፡፡ /ዮሐ. 11፡41/

🔴10.ለሌሎችም መጸለይ ይገባል

ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን፤ ለሌሎችም መጸለይ ይገባል፡፡ ኤርምያስ ለሀገር ሰላም መጸለይ እንደሚገባ ‹‹በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ ስለእርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ›› /ት.ኤር. 29፡7/፡፡ ታመው በየሆስፒታሉ፣ በየቤቱ ለሚገኙ ወገኖቻችን፣ በየማረሚያ ቤቱ ላሉ በአጠቃላይ በተለያየ ችግር ለሚንገላቱ ሁሉ መጸለይ ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአገር መጸለይ ይገባል፡፡ “ትድኑም ዘንድ እያንዳንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ” /ያዕ. 5፡16/


Share share share አድርጉት

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
መንፈሳዊ ህይወት pinned «🔴1.በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/ 🔴2.በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን…»
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ሼር እናድርግ
Forwarded from Deleted Account
#ጾም ፍስለታ_ከመግባቱ_በፊት_ይቅርታ_እንባባል እኔ ጾም ፍስለታ ከመግባቱ በፊት ይቅርታ ለመጠየቅ እፈልጋለው
#ይቅርታ_የመንግስተ_ስማያት_በር_መክፈቻ_ነው ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያስቀየምኳአችሁ ካላቹ ከልቤ ይቅርታ 🙏እጠይቃችኋለሁ 🙏🙏🙏 እባካችሁን እርሶም ጾም ከመግባቱ በፊት ይቅርታ ተጠያየቁ
መጸሐፍ እንዲ ይላል

ማቴዎስ 5
²³ እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥
²⁴ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ ። ወንድሞቼ ፣መባችን ፣ጸሎታችን ፣ጾማችን ከንቱ እንዳይሆንብን።
ወዳጆቼ ‼️ ከስጋ ብቻ ሳይሆን
#ከዝሙት_ከመጠጥ_ከሃሜት_እራሳችንን_እንጠብቅ ያለዚያ ጾማችን ዋጋ አይኖረዉም የበደልኳቹ ሁላችሁንም ይሄን ፅሁፋ ያነበባችሁ በሙሉ ከዚ በፊት ያረኩትን ደግሜ ላላደርገዉ ከልብ ይቅር እንድትሉኝ እጠይቃችኋለሁ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
እርሶም ይሄን ጹፍ #ሼር በማድረግ
ይቅርታ ጠይቁ
እኔ የበኩሌን ተወጥቻለሁ
እናተስ??

የፍስለታ ጾም ሁላችንም በይቅርታ እንጀምር

ይቀላቀሉ 👉 @hiyaw_qal
ይቀላቀሉ 👉 @hiyaw_qal
ይቀላቀሉ 👉 @hiyaw_qal
share💯share💯share💯
" የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።"
(መዝሙረ ዳዊት 45:9)

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 99)
----------
1፤ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።

2፤ እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

3፤ ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ።

4፤ የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።

5፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

🙏 @linkortodoxe21
🔵የጸሎት ጊዜያት

“ስብዐ ለዕለትየ እሴብሐከ” /በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ/ /መዝ. 118፡164/ ሲል ነቢዩ ዳዊት በተናገረው መሠረት በቀን ሰባት ጊዜ መጸለይ እንደሚገባ ታዟል፡፡

ይህም እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

1.ሰው ከእንቅልፍ ነቅቶ ከመኝታው ተነስቶ ገና ሥራ ሳይጀምር የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ /በነግህ/

2.በ3 ሰዓት

3.በ6 ሰዓት

4.በ9 ሰዓት

5.በ11 ሰዓት /በሠርክ/

6.በመኝታ ጊዜ

7.በመንፈቀ ሌሊት /ከሌሊቱ በ6 ሰዓት/

7ቱ የጸሎት ጊዜያት ከላይ የተገለጹት ሲሆኑ በተለይ የጧትና የሠርክ ጸሎት በቤተክርስቲያን መሆን እንዲገባው ታዟል፡፡

የሦስት ሰዓትና የሌሎች ጊዜያት ጸሎት ግን በቤትም ቢሆን በሌላ ቦታ ቢጸለይ አይከለከልም፡፡ ከነዚህ ጊዜያቶች የአንዱ የመጸለያ ጊዜ ቢደርስና የሚጸልየው ሰው ለመጸለይ ከማይችልበት ቦታ ቢሆን በልቡ የሕሊና ጸሎት ማድረስ እንዲገባው ታዟል፡፡

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ሀሳበ ልቡናችንን እንዲፈጽምልንና እንዲሁም ከልዩ ልዩ ፈተናና መከራ እንዲያድነን ሁልጊዜ መጸለይ ይገባል፡፡ ሰው ፈተና፣ መከራ ሲገጥመው ይጨነቃል እንቅልፍ ያጣል እንቅልፉ ጭንቀት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጭንቀት ምንም የሚገኝ ነገር የለም፡፡ ይህንንም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው” /ማቴ. 6፡27/ ሲል ተናግሯል፡፡

ፈተና፣ መከራ ሲገጥመን ተግተን መጸለይ እንጂ መጨነቅ አይገባም፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ “በምንም አትጨነቁ ነገር ግን ጸልዩ እያመሰገናችሁ ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ” /ፊልጵ. 4፡6/ ሲል ተናግሯል፡፡

ይህ ዓለም የፈተና፣ የመከራ ዓለም ነው፡፡ እንደውም በዚህ ዓለም ስንኖር ከደስታው ይልቅ የሚያመዝነው ፈተናው፣ መከራው ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የምንቋቋመው በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር በመነጋገር ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተግተን በመጸለይ ከፈተና እንደምንድን ሲገልጽ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት” /ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ/ /ማቴ. 26፡41/፡፡

በዚህ መሠረት አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከፈተና፣ ከመከራ እንዲያድነን ተግተን እንጸልይ፡፡

ንስሓ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲሁም በቅዱሳን አማላጅነት ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ልዑል እግዚአብሔር ወሰን በሌለው ቸርነቱ ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ የአምላክን እናት እናወድስ ከፍቅራ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ "

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21