መንፈሳዊ ህይወት
4.01K subscribers
437 photos
5 videos
8 files
62 links
✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇

https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን
Download Telegram
​​አይናችን ነሽ ማርያም
TewodrosYosef (ሊቀመዘምራን)

አይናችን ነሽ ማርያም አንችን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሃሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
አዝ
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
ባሸዋ ላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
አዝ
ገብተሻል አትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነዉ ባንች ነው የጠፋው ተገኝቶ
አዝ
ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሃረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራኒዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
አዝ
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ጸዋሪተ ፍሬ ያዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
አዝ
ከሃገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
ካደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጅ
ለጻድቃን አይደለም ለሃጥአን አማል
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

“ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደኾነ እንዲኹ ጸሎትን የማታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
እናት አለኝ የምታስብ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ምህረት
አንባ መጠጊያ ናት
✥ ------------- ✥
ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
✥ ------------- ✥
ለዘለዓለም ንጽህት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሃዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
✥ ------------- ✥
ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
✥ ------------- ✥
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬን በልጅሽ ጣፈጠ
✥ ------------- ✥
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር
እቴ ሙሽራዬ ሰለሞን ያለሽ (2x)
እኔም ልበልሽ እናቴ እመአምላክ ግቢ ከቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ ማርያም ግቢ ከቤቴ

 ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበሲዘረጋ
የክብር ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና ( 4x ) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና


አዝማች…
ወርቀዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሀርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና


አዝማች …
አሳድጎሽ ሳለ መላኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መላክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህርይተ ህሊና

አዝ…
የባሪያዉን ዉርደት ተመልክቷልና
ለወለድሽዉ ንጉስ ይድረሰዉ ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጅ ከቱዉን አይደለም
ብፅዕት እንላለን እኛም ለዘለዓለም
ነይ በደመና /4/
እመቤታችን እርህርይተ ህሊና

🕊🕊🕊አብረን እንዘምር🎤🎤🎤🕊🕊🕊
"እናንተ ደካሞች…"
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- “እናንተ ኃጢአት ሸክም
የሆነችባችሁ፣ እናንተ ጭንቀት አላኖር አላስቀምጥ ያላችሁ፣
እናንተ ሐዘን የደቆሳችሁ፣ እናንተ ትእዛዛቴን በመተላለፍ
ቅስማችሁ የተሰበራችሁ፣ እናንተ በሐፍረት ካባ ተከናንባችሁ
የምቆዝሙ፣ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ አበቃልኝ በቃኝ ብላችሁ ያንገሸገሻችሁ፣ እናንተ
ለመናገር እንኳን ድፍረት ያጣችሁ ምንም እንኳን ዝሙት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን
ዋሽታችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን ሰርቃችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን መናገር የማትችሉት
ከባድ የምትሉት ኃጢአት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን “ከእንግዲህ ወዲህ በቃ እግዚአብሔር
ይቅር አይለኝም” ብትሉም የእኔ ፍቅር፣ የእኔ ቸርነት ይህን ሁሉ ኃጢአታችሁ ይህን ሁሉ
ሸክማችሁ ይህን ሁሉ ሐዘናችሁ ይህን ሁሉ ከባድ የምትሉትን ነገራችሁ መደምሰስ የሚችል
ነውና ኑ፡፡
ኑና ላሳርፋችሁ፤ ኑና ስለ እናንተ የቆሰለውን እጄን ተደገፉ፤ ኑና ፍቅሬን ቅመሱ፤ ኑና ቸርነቴን
አጣጥሙ፤ ኑና ሸክማችሁን ሁሉ በእኔ ላይ አራግፉ፡፡ ብቻ እናንተ ፈቅዳችሁ ኑ እንጂ ከእኔ
ዓቅም በላይ የሆነ ሸክም የለባችሁምና አትስጉ፡፡ ኑና ሥርየተ ኃጢአትን ልስጣችሁ፤ ኑና
ዕረፍተ ነፍስን ሰጥቼ ላሳርፋችሁ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንኳ እንደ አመዳይ
አነጻላችኋለሁ፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ አጠራላችኋለሁ፡፡
ስለዚህ ኃጢአታችሁን እየቆጠራችሁ ከምትቆዝሙ ቀና በሉና ወደ እኔ ኑ፡፡ እኔ የዋህ
በልቤም ትሑት ነኝና ልጆቼ ወደ እኔ ቅረቡ፡፡ እኔም ልቅረባችሁ፡፡ “ቀንበሬን ተሸከሙ”
ስላችሁ በሩቁ አትፍሩኝ፡፡ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፡፡ ደግሞም ይህ ቀንበር
አንገታችሁን ለማለዘብ (ለመላጥ) ሳይሆን በቀጭኒቱ መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትሉ
እኔ ወዳዘጋጀሁላችሁ ርስት መንግሥት የምታደርስ ናትና በሩቁ አትፍሯት፡፡ ስለዚህ እናንተ
ደካሞች፣ እናንተ ዓቅመ ቢሶች፣ እናንተ ከእኔ ውጪ ምንም ማድረግ የማትችሉ በገዛ ደሜም
የገዛኋችሁ ልጆቼ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ማዳን ብቻ ሳይሆን አሳርፋችኋለሁ፡፡
እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው
የተሰበረውንም ያድናቸዋል::
(መዝ 34:18)
Channel name was changed to «መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)»
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 119)
----------
34፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።

35፤ እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
​[ - - - "#የህይወት_ህጎች" - - - ]
🌸🌸🌸🌼🌼🌼🌸🌸🌸🌼🌼

👉 ከመናገርህ በፊት | ☞ አስብ
👉 ከመፈረምህ በፊት | ☞ አንብብ
👉 ከማስተማርህ በፊት | ☞ ተማር
👉 ከመምከርህ በፊት | ☞ ተግብር
👉 ከመቁረጥህ በፊት| ☞ ለካ
👉 ከማጉደልህ በፊት | ☞ ተካ
👉 ከመዋጥህ በፊት | ☞ አላምጥ
👉 ከመገንዘብህ በፊት | ☞ አድምጥ
👉 ከማመንህ በፊት | ☞ አረጋግጥ
👉 ከመረከብህ በፊት | ☞ ቁጠር
👉 ከመወሰንህ በፊት | ☞ መርምር
👉 ከመስራትህ በፊት | ☞ አቅድ
👉 ከመተኮስህ በፊት | ☞ አልም
👉 ከመተቸትህ በፊት | ☞ አጣራ
👉 ከመብላትህ በፊት | ☞ ስራ
👉 ከመሞትህ በፊት | ☞ ነሰሃ ግባ
👉 ከመሄድህ በፊት | ☞ተስፋ ሰንቅ
👉 ስትወያይ-----☞ ሁን አስተዋይ
👉 ስትናደድ---- ☞ ቶሎ ብረድ
👉 ስትናገር---- ☞ በቁምነገር
👉 ስትቸገር---- ☞ መላ ፍጠር
👉 ስትቀመጥ---- ☞ ቦታ ምረጥ
👉 ስትወስን---- ☞ ቆራጥ ሁን!!


እንኳን ለቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)፣ ለቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት፣ ለአባ ቅፍሮንያ ጻድቅ፣ ለቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል) እንዲኹም ለቅድስት እግዚእ ክብራ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

ዳግመኛም ዛሬ ኅዳር 8 ቀን ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት፣ አባ ብሶይ (ቢሾይ)፣ አቡነ ኪሮስ፣ አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን እንዲኹም ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯

🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
<<እውቀት ማለት አንብቦ መያዝ
ሳይሆን አንብቦ መተግበር ነው>>
<<በጥቅሶች ለመለወጥ እንጂ በጥቅሶች መገጣጠም አትገረም>>
❤️ክርስቶስ ፍቅር ነው❤️

ሰው ሲያፈቅር አፍቃሪ ይባላል
ሰው ሲያከብር አክባሪ ይባላል
ሰው ጸባይ ሲኖረው ፀባየኛ ይባላል
ሰው ሲታዘዝ ታዛዥ ይባላል
ሰው ሲታገስ ታጋሽ
ትእግስት ሲኖረው ትእግስተኛ
ሲታትር ታታሪ
ሲያስብ አሳቢ
ለሰው ሲራራ ሩህሩህ
ይባላል። ይሆን እንጂ ሁሉንም የሚያሟላ ይኖራልን?አይኖርም፡ሃጥያት ሳይሰራ የማይኖር የለምና።
በፍጹም አምላክነቱ ፍጹም ሰው የሆነው ጌታችን መድሃኒታችን ክርስቶስ እየሱስ ሁሉን አሟልቶ ነጥብ እንኳ እንከን ሳይገኝበት የተገኘውስ??????
አፍቃሪ ያንስበታል እንጂ፡ እርሱ ❤️ፍቅር❤️ ነውና
በክርስቶስ ፍቅር ተዋደን እንኑር