🌹አል ፋሩቅ የሙፍቲዬ ትውልድ💚
6.04K subscribers
1.23K photos
143 videos
18 files
924 links
አሰላሙ አለይኩም ውድ የአል- ፍሩቅ ቤተሰቦች
ይህ ቻናል እስላማዊ ትምህርቶች ላይ ይሰራል
ሀሳብ አስተያየት ስህተት
ካለብንም አርሙን
👇👇👇
@zennfalaye
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌹🤍አንተዬ እሱን ይዘን የምን ወደ ሆላ
ሲይደምቀው እያየን የፈዘዘን ሁላ
እናምራለን እንጂ በጣም በቀን ለይላ
ሙሀመድ እያልን  አንዴት እናስጠላ ♥️



@limugenet
Audio
#ወዮዉላቹሁ (ከባድ ቅጣት ይጠብቃቹዋል )
አሏህን በውሳኔው ላይ የሚሟገቱ ሰዎች።
#ዐቁደቱ አጦሓዊያህ
#በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
#ክፍል 4⃣2⃣

#በጥሩ ኒያ ያዳምጡ ይጠቀሙበታል ለወዳጅ ዘመድ ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩን ተካፋይ እንሁን።


@limugenet
Audio
#አሏህ ከዐርሽም ሆነ ከሌሎችም ፍጡሮቹ ባጠቃላይ የተብቃቃው ነው።

#ዐቂደቱ አጦሓዊያህ
#በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
#ክፍል 4⃣3⃣

#በጥሩ ኒያ ያዳምጡ ይጠቀሙበታል ለወዳጅ ዘመድ ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩን ተካፋይ እንሁን።


@limugenet
Forwarded from 🍁 ኑራሪያ🌴የፍቅሮት🌿ምርኮኛ 💞 (🍂ÝÆÑTŲ 🍁ÑÆfÃķÌ🍁)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀሳብህን አስተውል …

• ሀሳቦቻችሁ የእናንተ ቃላት ስለሆኑ ይጠንቀቁ።

• ቃላቶችዎ ተግባር ስለሚሆኑ ይጠንቀቁ።

• ድርጊቶችዎ ልማድ ስለሚሆኑ ይጠንቀቁ።

• ባህሪዎን ስለሚቀርጹ ለልማዶችዎ ትኩረት ይስጡ።

• ለባህሪዎ ትኩረት ይስጡ, እጣ ፈንታዎን ይወስናል.

በውጪ ያለው የተሳካ ህይወት በእውነቱ ከውስጥ ስኬታማ እና ጤናማ ሀሳቦች ይጀምራል።

https://t.me/ketberiyoch
https://t.me/ketberiyoch
Audio
#አሏህ በዕውቀቱ ሁሉንም ነገር ያካበበ ነው።
#ዐቂደቱ አጦሓዊያህ
#በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
#ክፍል 4⃣4⃣

#በጥሩ ኒያ ያዳምጡ ይጠቀሙበታል ለወዳጅ ዘመድ ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩን ተካፋይ እንሁን።

@limugenet
Forwarded from جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية (😍سعادة عبدرية😘)
Forwarded from جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية (😍سعادة عبدرية😘)
ሂጅራ መልከ ብዙው
የቅኔ ውቅያኖስ፣ የሰም ወርቅ ማዕበል
ትግሉ ማይሸሸግ፣ ፈድሉ ማይታበል
ሂጅራ የድል ፍልቂት፣ የፅናት ኮረብታ
  የፍቅር መስታዎት፣ የመስዋት ጎታ
የገድል ነጸብራቅ፣ የኢማን ወገግታ
ሂጅራ የኑር አሊፍ፣ ቀስት መሰል ዳና
መሬተ ትግስቱ፣ መቅድመ ልዕቅና
   
ለመመለስ መውጣት፣ ለመልበስ እርዛት
ለማረፍ መባተል፣ ለመብዛት መነዛት
ብዙ ገድል ለድል፣
ለከፍታ መውረድ፣ ለመጋልም መብረድ 
የድል ንጋት ጮራ፣ ላይጠልቅ ሊያበራ
ማይታበይ ገድልን፣ ያስቃኘናል ሂጅራ

ይኸን ሁላ ጉዳይ፣ ስንቱን ስንት ቅኔ
ባንድ ሚያጠራቅም፣ ታሪኩን ሚለቅም 
የሂጅራው መፅሀፍ 
እንኳንስ ተነቦ ፣ ተገልጦም አያልቅም

እንደሳቸው ቅዋ
ደፋር፣ ጀግና፣ ብርቱ እንደመሆናቸው
ሙሽሪኮችን ማጥፋት መቼ ሊያቅታቸው
ግን ታጋሹ ነቢ፣
የጌታን ትዕዛዝ መቀበል መረጡ
ሚወዷትን አገር፣ መካን ጥለው ወጡ

በጉዟቸው ማግስት፣ ሙሽሪኮች በማታ
ነቢዩን ለመግደል በተኙበት ቦታ
ሆነዋል ከባቢ
ግን በሳቸው ቦታ ዓሊይን አድርገው
በፊት ለፊታቸው ወጡ ጀግናው ነቢ

አጀብ ፍቅር ጉዱ፣ ገጹ መበርከቱ
ለሞት አስተኝቶ፣ ረፍትን መስጠቱ
ዓሊይ አንድ ለታ
ከቶ እንዴት ነበረች ያች ሌሊት ላንተ
ተብሎ ሲጠየቅም
እንደዚያች ሌሊት፣
ረፍት ያለው እንቅልፍ፣ ተኝቼም አላውቅም።

ብቻ ደጉ ነቢይ፣ ጉዞውን ቀጠሉ
ሲዲቅ ግን ፈርተዋል
ለነፍሳቸው ሳይሆን ለውዳቸው ሲሉ

ዋሻው ጋር ደረሱ፤ ሲዲቁ ባከኑ
ጨርቃቸውን ቀደው፣ ሽንቁሩን ደፈኑ
ከዚያም አረፍ አሉ፣ ታፋቸው ላይ ዘይኑ።

አንድ ሽንቁር ቀርታ
ሲዘጓት በግራቸው፣ እባብ ነደፋቸው፤
ብቻ ነቢ ደህና፣
ዋናው ኑሩ ደህና
የርሱ ደህንነት ነው፣ ደህና ሚያደርጋቸው

እንዳይረበሹ የተኙት ትልቅ ሰው
ህመሙን ቢውጡም
አይን ጉድ አመጣ፣ እንባ እየፈሰሰው

ተነሱ ንጉሱ፤
ህመምን ከእንባ ባንድ አብረው አበሱ

ሲዲቅ እንደ ሰጉ፣ ነቢ እንዳስታገሱ
ሲዲቅ እንዳነቡ፣ ነቢም እንዳበሱ
ከመካ ተነስተው መዲና ደረሱ

እንኳን ሰው እንስሳው
ጦለዐ አለ ምድሩ፣ ጦለዐ አለ ሰማይ
የዓለሙ ጀንበር፣ ጦይባ መድረሱን ቢያይ
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
አስታዬት👇
@Seadtu
ሒጅራ: The Greatest Historical Shift 🤎

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው የ13 አመት የመካ ላይ ስቃይ እና እንግልትን የሚቀይር ህልም ተመለከቱ! በህልማቸው ከመካ ተነስተው ልክ እንደ 'የማማህ' የተምር ዛፎች የሚበዙበትን ከተማ ሲገቡ ተመለከቱ። ያ ቦታ የስሪብ(መዲና) ነበር። አላህን በሰላም የሚገዙበትን አዲስ ማህበረሰብ በመፍጠር እስልምናን ከፍ ወደሚያደርጉበት መዲና እንዲሰደዱ ጌታዬ አዘዛቸው! ሂጅራ የኢማን መንገድ ነው። 🤎

ሒጅራ ታላቅ ክስተታችን ነው። በህይወታችን ብዙ ሂጅራዎች ያስፈልጉናል። ሂጅራ ማለት ከአንድ ነገር (ሀገር: ሰዎች) ተለይቶ መሄድ የሚለውን ያመለክተናል! አሁን ላይ ከሀገር መሰደድ ላይኖርብን ይችል ይሆናል፤ ከእንቶ ፈንቶ ወሬዎች ሂጅራ ማድረግ ግን አለብን። አደብ ከጎደላቸው ንግግሮች፤ ድፍረት ከተሞላባቸው አጀንዳዎች ሂጅራ ማድረግ ይኖርብናል። አዲስ ማህበረሰብና መንደር ለመፍጠር ላንገደድ እንችል ይሆናል የራሳችንን አለም፤ ሀሳባችን ከሚገባቸው እና መልካም ስራዎችን አብረን ከምንሰራቸው ሰዎች ጋር ፍሬያማ ስብስብ በመፍጠር ሒጅራ ማድረግ ግን እንችላለን። 🤎

በሙሐረም ወር የረሱለላህን ﷺ ሒጅራ በስፋት እናነሳለን! የብዙ ለውጦች መነሻ የሆነውን ጉዞ አብረን እንመለከታለን። ከነገ ጀምሮ ስለ ታላቁ የኢማን መንገድ ያዘጋጀሁትን ተከታታይ ፅሁፍ ወደ እናንተ የማደርስ ይሆናል ኢንሻአላህ 😊🤎

እንኳን አደረሰን! አላህ መልካም ስራዎችን የምናበዛበት፤ ብዙ መልካም ለውጦችን የምናይበት ያድርግልን 🤲🏽

@limugenet
የሙሐረም ወር ልቅና እና የወሩ ታሪካዊ ክስተቶች
****

የሙሐረም ወር በኢስላማዊው የሂጅራ አቆጣጠር መጀመረያ ላይ የሚገኝ’ና በውስጡ አያሌ የአላህ ስጦታ እና በረከቶችን የያዘ ወር ነው ።

ወሩ አሏህ (ሱብሐነሁ ወተዐላ) በ‘ተውባ’ ምዕራፍ አንቀጽ  36 ላይ ...

إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ ..."

" የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ..."

በማለት ከገለጻቸው የተከበሩ 4 ወራቶች መሀከል የሚመደብ የአሏህ ወር ነው ።

ወሩ " ሙሐረም " ተብሎ መሰየሙ  የወሩን ልቅና ለመግለፅ’ና በውስጡ እርም የሆኑ ነገሮችን መስራት ከሌላው ጊዜ በበለጠ ወንጀልነቱ የሚገዝፍ መሆኑን ለመጠቆም እንደሆነ ዑለሞቻችን ይናገራሉ ። ኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) ከላይ የሰፈረውን የቁርአን አንቀጽ ሲያብራሩ ...

        " فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسكم "
" በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ " ሲል...
"በእነርሱ ውስጥ..."
የምትለው ቃል ሁሉንም ወራቶች የምትወክል ሲሆን በመቀጠል አራቱን የተከበሩ ወራቶች ነጥሎ በማውጣት መጥቀሱ በእነዚህ ወራቶች ውስጥ ወንጀልን መዳፈር ከሌላው ወራቶች በበለጠ እርምነቱ እንደሚጠብቅ ለመጠቆም እንደሆነ ያስረዳሉ ። 

ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ሲናገሩም...

" ምንም እንኳን በማንኛውም ጊዜያት ወንጀልን መስራት አስከፊ ቢሆንም በተከበሩ ወራቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ግን በሌላው ጊዜ ከሚፈፀሙት በበለጠ ወንጀልነታቸው በአሏህ ዘንድ ይከፋል " ይላሉ ።

ሐሰን አል–በስሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ...
" አሏህ (ሱብሐነሁ ወተዐላ) የወራቶቹን መጀመሪያ በተከበረ ወር (በሙሐረም) ሲያደርግ  የመዝጊያውንም ወር  በተከበረ ወር (ዙልሒጃህ) አድርጓል ። ከዓመቱ ወራቶች ውስጥ ከረመዳን ውጭ የሙሐረምን ያህል  በአላህ ዘንድ የተላቀ ወር የለም " ይላሉ ። 

ኢብኑ ረጀብ ከተከበሩ 4 ወራቶች መሀከል በላጭነት ያለው የትኛው ወር ነው በሚለው ላይ ዑለሞች የተለያየ አቋም እንደያዙ ሲናገሩ ሐሰንን ጨምሮ ሌሎች የዒልም ባለቤቶች ብልጫ ያለው ወር የሙሐረም ወር ነው ማለታቸውን ተናግረዋል ።


የሙሐረም ወር የ‘ነስር’ ወር ነው ። አሏህ የተለያዩ ባሮቹን ከጭንቀት ያወጣበት ፣ የተለያዩ አማፂና አምባገነኖችን ያጠፋበት ወር ነው ። ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)  ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ እዚያ የነበሩ አይሁዶች የሙሐረም ወር 10ኛውን ቀን ሲጾሙ አገኟቸው ፣ ምክኒያታቸውን ሲጠይቁም " ቀኑ አሏህ በኒ ኢስራኢሎችን ከፊርዐውን ጭቆና ያዳነበት’ና ፊርዐውንንም በባህር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ነው "  የሚል መልስ አገኙ ። ነብዩም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) "  እኛ ከእናነተ በተሻለ ለሙሳ የተገባን ነን " ካሉ በኋላ ሙስሊሞች ቀኑን በጾም እንዲያሳልፉ አበረታቱ ።

የሙሐረም ወር ጾም
****

አቡ ሑረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት እና ሙስሊም በዘገቡት ሶሒህ ሐዲስ ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ተናግረዋል
" أفضل الصيام بعد رمضان شهر الله المحرم "
" ከረመዳን በኋላ በላጭ ጾም የሙሐረም ወር ጾም ነው "

የሙሐረም ወር እና የነብዩ ስደት

ይቀጥላል ...
Audio
#አሏህ በልቅና እንዲሁም ሁሉን በመቆጣጠር የበላይ ነው።
#ዐቂደቱ ጦሓዊያህ
#በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
#ክፍል 4⃣5⃣

#በጥሩ ኒያ ያዳምጡ ይጠቀሙበታል ለወዳጅ ዘመድ ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩን ተካፋይ እንሁን።


@limugenet
🟢ከአብሬት ሸህ ከቀሩ ትልልቅ ዑለሞች (ኪታበኞች) ነው ያደግነው። ከሙሪዶቻቸው ተለይተንም አናውቅም አልሐምዱ ሊላህ። ከሀገር ወጥተንም ረጀብ አብሬት መሐደራችን የማይቀር ነው።

🔰ከአብሬትዮች ሲፋ፡ ሰላት የማይሰግድ ሰው የሰራው ምግብ አይበሉም። ሰላት የማትሰግድ ሴት ያፈላቹ ቡና አይጠጡም። ይህ አባባ ላይ የቀሩ ኪታበኞች ላይ ከየሁት ሲፋ አንዱ ነው።

🟢አብሬት የተውሒድ ማብራት የሱና ህይወት የተዘረጋበት ሐድራ ነው።
🍁 @limugen
🍁 @limugenet
ለ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች መልካም ፈተና ይሁንላችሁ
كان الله معكم
ዘይኑል አቢዲን
<unknown>
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
አስታዬት👇
@Seadtu
Forwarded from جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية (😍سعادة عبدرية😘)
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

እስልምና በጥሩ ያዘናል ከመጥፎም ነገርም ይከለክለናል።

ከነገራቶችም ትምህርት እንድንወስድ   ያበረታታናል ።

      ✍️ እውን እስልምናችን ስለ ቤተሰብ ምስረታ ምን መምሰል እንዳለበት አይናገርምን?  የትዳር አጋሮች(ጥንዶች) መዋደድ እንዳለባቸው  ስለ አንድነት አያውጅምን?  ብዙ ጊዜ ደርሶች ላይ ስለዚህ ነገር ሲወሱ አይታይም እናም አስተማሪ ይሆናል ተብሎ የተዘጋጀውን «የፈቲ ባል» ተብሎ የተዘጋጀውን ታሪክ እነሆ ብለናል። 

       እንዲህ ይላል

"የፈቲ ባል" - ክፍል አራት (4⃣)

የማሜ ሰላምታ ድምፁ ከማማሩ የተነሳ ጆሮዋ ስር ተጠግቶ እያንሾካሾከ " እወድሻለሁም" ያላት ይመስል ሰላምታዉን ከመመለሷ ቀድማ "ማሜ..........." አለችዉ፡፡ "ወዓለይከ ሰላም" ስትለዉ ... እሷን አልፎ ፊቱን ወደ ቤቱ ዉስጥ አዙሮ በአይኖቹ ፈቲን እየፈለገ... "ሰላም ነሽ ጀሚላ?" አላት፡፡ እሷም "አልሐምዱሊላህ ሰላም ነህ ማሜ... ስራ እንዴት ነዉ?" አለችዉ፡፡
ማሜ ብላ እያቆላመጠች ስጠራዉ ለሷም አልታወቃትም እሱም አላስተዋላትም፡፡ "አሪፍ ነዉ አልሐምዱሊላህ ደሞ ወጣቱን አባትሽን ሰላም በይልኝ...ሃሃ..." እያለ ወደ ቤቱ ዉስጥ ሲዘልቅ ሁለቱም ተሳሳቁ በተለይ ጀሚላ ዉስጧን በደስታ አስፈደቃት፡፡ ሲቀልዳት በሀሴት ተፍነከነከች ወዲያዉ ግን ፊቷ ክስስስም አለ፡፡ ለካ ሳትነግረዉ ነዉ በቆመችበት ትቷት ወደ ዉስጥ የገባዉ፡፡
በጣም ተበሳጨች ልትከተለዉም ፈልጋ ነበር...
.
......... ማሜ ዉድ ባለቤቱን እየተጣራ ወደ ዉስጥ እየገባ ነዉ፡፡ "ፈቲዬ  የት ነሽ?"
....ፈቲ "ወዬ ማሜ እዚህ ነኝኝ" እያለች ከእቃ ቤት ወጣች፡፡
...."አሰላሙ ዓለይኪ የኔ ወድ..." ግንባሯን ሳም እያረጋት
..... "ወዓለይከሰላም ሀቢቢ እንዴት ዋልክልኝ?"
...... "አልሐምዱሊላህ ማሬ ምን ነዉ? ዛሬ ስራ አልጨረሺምዴ?"
......" አዎ አልጨረስኩም ጀሚላ መጣችና ስላንተ እያወራኃት ስራዬን እርስት አላረገዉም መሰለህ ደሞ አረፍ በል ትንሽ ነዉ የቀረኝ መጣሁ..." ብላዉ ወደ ስራዋ ስትሄድ እሱም ስራዉን ሊያግዛት እየተከተላት...
...."ቆይ እኔም ልገዝሽ አንቺን ብቻ ማን ልፊ አለሽ የኔ ዉድ" ብሏት ተከተላት፡፡
.
...ጊዜዎች እየነጎዱ ነዉ፡፡ ጀሚላም ፍቅሯን ዛሬ ነገ እነግረዋለሁ እያለች አንዴ ሳታገኘዉ ሌላ ጊዜ ደሞ ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ስፈራ አንድ ወር አለፋት፡፡
አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቡ የሚባሉበት ቀን እየደረሰ ነዉ፡፡ እሷም ፍቅሯን አልነገረችዉም ማንም ሳያዉቅላት ትወደዋለች ግልፅ ሳታወጣ ታፈቅረዋለች፡፡ አንድ ነገር ደሞ ጠርጥራለች ፈቲ መዉለድ አትችልም የሚል...፡፡ አንድ ቀን እሷና ፈቲ እያወሩ...
.. ፈቲ "እኔና ማሜ ከተጋባን አራት አመታችንን ይዘናል" ስትላት ጀሚም "እንዴት እስካሁን ሳትወልዱ?" ብላ ጠየቀቻት
.."አላህ አልፈቀደዉም ልጅ አልሰጠንም" ብላ መልሳላት ነበር፡፡ በሃሳቧ የመጣላት ፈቲ የመዉለድ ችግር እንዳለባት ነዉ፡፡ "ስለዚህ ለማሜ እንደማፈቅረዉ ብነግረዉ ፈቲን ፈትቶ ያገባኛል ወይም ሁለተኛ..." ብላ አሰበች፡፡ እንደገና መለስ ብላ "ኧረረረ ሁለተኛስ ይቅርብኝ" እያለች እራሷ ከሃሳቧ ጋር ትሟገታለች፡፡
.
.... የፈቲ ስልክ እየጠራ ነበር፡፡ ስልኳ ላይ የተደወለዉ የማታዉቀዉ ቁጥር ነዉ "ፊለይለቲ ሚነ ለያል ለስቱ አድሪ ማተራ......" የሚለዉ ነሽዳ ነበር የስልኳ መጥሪያ፡፡ ፈቲም ስልኩን አነሳችዉና
"ሄሎ"
"አሰላሙዓለይኩም.." ጎርነን ያለ የወንድ ድምፅ ነበር፡፡ ፈቲ ስልክ ስታወራ ጀሚላ የቤታቸዉ በር ላይ ቁጭ ብላ መፅሃፍ እያነበበች ነበር፡፡
"ወዓለይከ ሰላም ማን ልበል?
"ትናንት ሙሃመድ በዚህ ቁጥር ደዉሎልኝ ነበር፡፡ የሱ ስልክ አይደለምዴ?" ድምፁ ማስፈራራቱ ኮስተር ያለ ነዉ፡፡
"አይይ የመሃመድ አይደለም ግን የሱን ስልክ ቁጥር ልሰጥህ እችላለሁ" በዚህ ግዜ ጠላት እንደመጣባት የጥንቸል ጆሮ ጀሚላ አንገቷን ሰገግ አድርጋ ... ማዳመጥ ጀመረች፡፡
"እባክሽን ተባበሪኝ ለስራ ጉዳይ ፈልጌዉ ነበር"
"እሺ ፃፍ 09.. " ስትል ጀሚላ ከሰዉየዉ ቀድማ ቁጥሩን መፃፍ ተያያዘችዉ፡፡
" 09 21 79...." ፈቲ ለደዋዩ ቁጥሩን ነግራ ስጨርስ ጀሚላም እኩል ነበር የፃፈችዉ፡፡
.
ጀሚላ ምንም ጊዜ ሳታጠፋ ለማሜ መልዕክት ፃፈች ..."ማሜ አሰላሙዓለይኩም ካየሁህ ጊዜ ጀምሮ በጣም ነዉ የወደድኩህ!" ብላ ከፃፈች ቡኃላ send የሚለዉን ተጫነችዉ፡፡አቤት ድፍረቷ ...ለራሷም አስገርሟታል፡፡ የወራት ሸክሟን ያራገፈች መሰላት፡፡
አሁን ያስጨነቃት የሱ ምላሽ ምን እንደሚሆን ነዉ፡፡
ነገር ግን መልዕክቱ አልደረሰዉም "Dear Customer, your balance is insufficient for this service. Please recharge your account. ethio telecom" የሚል ሜሴጅ ስልኳ ላይ ገባ፡፡ ለካስ ስልኳ መልዕክት ሊያስልክ የሚችል ባላንስ አልነበረዉም፡፡
ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ዉስጥ እየሮጠች ገባች፡፡
"እማዬ ስልክሽ የት ነዉ?" ብላ እማማ ነፊሳን ጠየቀቻቸዉ፡፡ "እንቺ..." ብለዉ እናቷ ስልካቸዉን አቃበሏት፡፡ ወደነበረችበት ቦታ ተመልሳ ተቀመጠችና መልእክቱን መፃፍ ጀመረች "አሰላሙአለይኩም ማሜ በጣም እወድሀለሀሁ!" አይ...አለችና መልእክቱን አጠፋችዉና ሌላ መልእክት ፃፈች "አሰላሙአለይኩም ማሜ ካየሁህ ጊዜ ጀምሮ ላንተ ያለኝ ስሜት ልዩ ነዉ፡፡ ሳልወድህ አልቀረሁም!" ብላ ፃፈች፡፡ በማታዉቀዉ ሃይል ተገፍታ እጇ እስኪከዳት ድረስ send የሚለዉን ነካችዉ፡፡ እፎይታ ተሰማት ከማሜ "እሺ" እንጂ ሌላ መልዕክትን አጠብቅም፡፡
ምናልባት የሱ መልስ እምቢታ ቢሆን ብላ ማሰብም አልፈለገችም፡፡
.... መልእክቱ ማሜ ስልክ ላይ ገባ "ጢጥ ጢጥ" የሚለዉን የሞባይሉን የመልእክት ድምፅ ሲሰማ ስልኩን ከኪሱ አወጣ... የመልእክቱ ላኪ ... እማማ ነፊሳ ይላል...ፈገግ አለ፡፡ደንገጥም አለ ፡፡ "ፈቲ ምን ሁና ነዉ?" "አመማትዴ?" "ምን ብለዉ ልከዉ ይሆን?" በሚል ጥያቄ ራሱን አፋጠጠ፡፡ ሜሴጁን ሲከፍት ግን ያልገመተዉና ያላሰበዉ ነገር፡፡ ....

ክፍል አምስት (➎)


ይቀጥላል......

ወደ ቴሌግራም አካውንታችን ለመቀላቀል 👇👇
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
አስታዬት👇
@Seadtu
Audio
#ንግግር የሚለው የአሏህ ባህሪ ትንታኔ
#ዐቂደቱ ጦሓዊያህ

#በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
#ክፍል 4⃣6⃣

#በጥሩ ኒያ ያዳምጡ ይጠቀሙበታል ለወዳጅ ዘመድ ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩን ተካፋይ እንሁን።


@limugenet
Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up: https://telega.io/c/limugenet

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!
የዐሪፎች መጠጥ ሳይጠጡ መኖር
እንዴት ያለ እጣ ነው ሳይሞት መቀበር!

የሸኾችን መንገድ ልታደናቅፍ እስካሁን ድረስ መረብ እየዘረጋህ እድሜህን ፈጀህ።
በራስህ ገመድ ተጠልፈህ እየወደቅክ መነሻውም ራቀህ!
እንኳን ልትጎዳቸው በጥሩም ብትመጣ እጃቸውን መንካት አልቻልክም!😎

ሻላቸውን በረካ አድርጎ ከኒፋቅህ ያላቅህ ለዲንም ለሀገርም የማትበጅ ከሆንክ አሏህ ይንቀልህ!

@limugenet
«ታማሚዎች ሁሉ ከህመማቸው መዳንን ይመኛሉ።በፍቅር ህመም የተጠቁት ህመምተኞች ግን ህመማቸው ሁሌ እንዲጨምር ይጠይቃሉ።የህመሙንና የናፍቆቱን መደራረብም አጥብቀው ይወዱታል።እኔም ከዚህ መርዝ የበለጠ ጣፋጭ መጠጥ፣ ከዚህ ህመም የተሻለም ጤንነት አልተመለከትኩም!።»

(መውላና ጀላሉዲን አል–ሩሚይ)

@limugenet
Audio
#በነብያት ባህሪ ዙሪያ የዑለሞች ንግግር።

#ዐቂደቱ ጦሓዊያህ

#በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
#ክፍል 4⃣7⃣

#በጥሩ ኒያ ያዳምጡ ይጠቀሙበታል ለወዳጅ ዘመድ ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩን ተካፋይ እንሁን።

@limugenet
የኔ ነቢይ ጨዋታቸው ለዛ ነበረው
<unknown>
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية
https://t.me/+R_QhFIbufEC65ol6
አስታዬት👇
@Seadtu