እንተዋወስ(entewawes)
164 subscribers
56 photos
23 videos
12 files
144 links
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Download Telegram
Forwarded from Towards Allah (Amal Abubeker)
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ርዕስ፦ በአሁን ሰዐት ትኩረታችን ምን ላይ ነው ?

የአደም ልጆች ድክመታችን ብዙ ቦታ ነው። ብዙ ነገሮች ያሳስቡናል፣ ያስጨንቁናል እንዲሁም ይፈታተኑናል በተለያየ ጊዜ በተለያየ ቦታ። በዛውም ልክ ደስታ ሲመጣ፣ ሲሳካልን፣ የጎደለን ሲሟላ ጊዜም በደስታ መግቢያ መውጫው ይጠፋናል። በቃ 24 ሰዐት ስለዛ ነገር ማሰብ ነው፤ ማውጣት ማውረድ
📌 አልሃምዱሊሏህ አላ ኩሊ ሃል ስለተደሰትንበት ነገርም ይሁን ስለተከፋንበት፣ ስለተሰበርንበት ሀዘን ምንም ቢሆን ከጀርባው ሂክማ አለው። አሁን ግን ላወራ የፈለኩት ውዶቼ ይሄ ሁሉ ጡዘት( መደሰት፣መቦረቅ፣መከፋት፣ማዘን ወ.ዘ.ተ) ውስጥ አሏህን ምኑ ጋር ነው ያስቀመጥነው (ለአሏህ በልባችን የሰጠነው ቦታ ምን ያህል ነው?)፤ በእነዚህ ስሜት ውስጥ ስንናወጥ ለደቂቃ አሏህ ምን ይለኛል?፤ ይህን አይነት reaction በማሳየቴ አሏህን አስከፋዋለው ? ወይስ አስደስተዋለው ? ብለን እራሳችንን ጠይቀናል ?

📌 ዱንያ ወንድም እህቶቼ ምንም ያህል ብታምር፣ ብታብለጨልጭ በጣም አጭር ናት። ማዘናጊያ ናት። እንደው አታስደንቅም እኮ! ምከንያቱም ዛሬ በጣም ሀብታም የሆነው ሰው መሽቶ ሲነጋ ደህይቶ ልናይ እንችላለን፤ በጣም ጤነኛ የነበረ በደቂቃዎች ውስጥ ታሞ ሀኪም ቤት ገብቶ እናያለን። በተቃራኒው ደሞ በጣም በትንሽ ሰበብ ሀብት በሀብት ሆኖ ተቀይሮ እናያለን የታመመውም ድኖ። ዞሮ ዞሮ አሏህ ነው ሁሉን አድራጊ። ልብ አርጉልኝ!! ሂወታችን እንዲሻሻል ጥረት ማረግ(ሰበብ ማድረስ) የለብንም ሳይሆን በደምብ እንሞክራለን ውጤቱን ለአሏህ እንሰጣለን ምክንያቱም ነገሮችን ፈፃሚ፣ ገለባባጭ፣ቀያያሪ አሏህ ብቻ ነው።
﴿وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ﴾
آل عمران: 189]
📌 ብዙ ሰርተን፣ ደክመን ላናገኝ እንችላለን፤ ትንሽ ሰበብ አድርሰን ደሞ ያልታሰበ ርዝቅን ልናገኝ እንችላለን። የሆነ ነገር በጣም ጓግተንለት ላይሳካ ይችላል፤ እስከዚህም የሆንበት ጉዳይ ደሞ ተሳክቶ፣ ሰምሮ ልናይ እንችላለን። የምንወደውን ልናጣ እንችላለን፤ እገሌን በቃ አጣውት ብለን ተስፋ ቆርጠን ደግሞ ሊመለስ ይችላል። ግን በአጠቃላይ በዙህ ዑደት ውስጥ ከኛ ምንድነው የተፈለገው ?
﴿أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُتْرَكُوا أَن يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ﴾
العنكبوت: 2]
📌 የእኛ ምላሽ(reaction) ነው የተፈለገው። እንዴት ነው ነገሮችን የምናስተናግደው? አብዝተን ተደስተን እንዘነጋለን? ወይስ አመስጋኞች እንሆናለን? ወይም በተቃራኒው በጣም አዝነን ሰብር አተን አማፂያን እንሆናለን? ወይስ ሰብር አርገን ወደ አሏህ ዱዐ በማድረግ እንፅናናለን?
📌 እሺ መሀል ላይ ከሆንስ? በጣም የሚያስደስት ነገርም በጣም የሚያሳዝን ነገር ያልገጠመን ሰዎችስ (neutral) የሆነ ስሜት ውስጥ ያለን እኛስ ትኩረታችን የት ነው ? social media ላይ? ሀራም የሆነ relationship ውስጥ ነው ? ሱስ ውስጥ? game ላይ? ወይ እገሊት ምን ለበሰች፣ ምን ተቀባች ነው? ወይስ ከአሏህ ጋር ነን ? ሰላታችንን የምናቆም(በሰዐቱ የምንሰግድ)? አዝካር የምናበዛ ነን? ቁርአንን የምንቀራ ነን በ24 ሰዐት ውስጥ? ከፀሀፊው እስከ አንባቢው እራሳችንን እንጠይቅ
﴿ اعْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ ۖ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الْكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا ۖ وَفِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ ۚ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ﴾
الحديد: 20]
📌 ህይወታችን ላይ ምን እየሰራንበት ነው ? focus ያደረግነው ምን ላይ ነው? ትኩረት የሰጠነው ነገርስ ለዱንያም ለአኼራም ይጠቅማል? ከጠቀመ ኸይር እንቀጥልበት ካልሆነ ግን ሳይረፍድብን ቶሎ ማስተካከል ያለብንን ብናስተካክል መልካም ነው።
📌 በጣም ብዙ ውጥረት ውስጥ ጭንቀት ውስጥ ያላችሁ ትኖራላችሁ። በብዙ ነገሮች ተከባችሁ ያላችሁ። አሏህ አዛችሁን ሁሉ ያንሳላችሁ 🤲። የምትችሉትን ሰበብ አድርሱ ከዛ ጉዳያችሁን ሁሉ ለአሏህ አሳልፋችሁ ስጡ።
﴿ اللَّهُ وَلِيُّ الَّذِينَ آمَنُوا يُخْرِجُهُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَوْلِيَاؤُهُمُ الطَّاغُوتُ يُخْرِجُونَهُم مِّنَ النُّورِ إِلَى الظُّلُمَاتِ ۗ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ﴾
البقرة: 257]
﴿ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ﴾
البقرة: 186]
📌 ውስጣችሁን ይቅለላችሁ። ምንም ቢሆን ዱንያ ናት። ወሏሂ ሱመ ወሏሂ ነገ አሏህ ፊት ስንቆም ማናችን ለማናችን የምንሰጠው ቦታ፤ አሁን እያስጨነቀን ያለው የዱንያ ሀም ገም ከየድራሹ ነው ሚጠፋው በቃ እናት አባቴ የለ፤ የትዳር አጋሬ፣ ልጆቼ የለ ጓደኛዬ የለ። ብቻ የሚያሳስበን ወይ ጀሀነም መወርወራችን ወይ ጀነተል ፊርደውስ መግባታችን ነው። ስለዚህ ከአሁኑ ለአኼራችን ልዩ ትኩረት መስጠት ግድ ይለናል። አሏህ ብሎ በጀነተል ፊርደውስ የምንሰበሰብ ያርገን 🤲 አሚንንን።
﴿أَلَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ﴾
يونس: 62]
﴿الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ﴾
يونس: 63]
﴿لَهُمُ الْبُشْرَىٰ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۚ لَا تَبْدِيلَ لِكَلِمَاتِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ﴾
يونس: 64]

ወላሁ ተዓላ አዕለም

ጠቃሚና አስተማሪ ፅሁፎችን ለማግኘት 👇👇
https://t.me/remembarance
🌹ጥንቃቄ ለሴቶች 🌹
➲የአባትሽ ወንድም ልጅኦች
➲የእናትሽ ወንድም ልጅኦች
➲የአባትሽ እህት ልጅኦች
➲የእናትሽ እህት ልጅኦች
➲ የባልሽ ወንድም
➲ የእህትሸ ባል
➲የባልሽ አጎት
➽አጅነብይሽ ናቸውና ሊጨብጡሽ፤ሊያዩሽና ካንቺ ጋር ሊቀመጡ አይፈቀድም።እጅሽን፣እግርሽን፣ፊትሽንና ፀጉርሽን እንዳይመለከቱ በነሱ ፊት ሙሉ ሂጃብሽን በመልበስ ልትሰተሪ ይገባል።
ህይወት ቀላል ቢሆን ኖሮ
የታጋሾች ምንዳ ትልቅ ባልሆነ ነበር https://t.me/leihte/280
ሁሉም ነገር ለኸይር ነው
🤲የለመንከው ነገር ከሰጠህ ⁻ምስጋናን ሊያስተምርህ ነው።
🤲የለመንከው ነገር ከዘገየ ⁻ሶብርን ሊያስተምርህ ነዉ ።
🤲ለምነህ ምንም ካልመለሰልህ ⁻ ከዛ የተሻለ ያዘጋጀልህ ነገር አለ ማለት ነዉ ።
በየትኛውም አይነት ሁኔታ ላይ አላህ አላህ ላንተ ጥሩን እንደሚያስብልህ እወቅ።

▸አላህን በኸይር ጠሪጥረው
ሒጃብ ክፍል⓶
🌹ልብስንና ሒጃብን የሚመለከቱ ህግጋቶች #ሀ,ሸርያዊ የሙስሊም ሴት አለባበስ
⓵የሙስሊም ሴት ልብስ ወፍራም እና የተጎዘጎዘ ........👆ክፍል 1.
⓶ እይታን የሚከለክል እና እና ስስ ያልሆነ ከበስተጀርባው የሰውነቷን መልክ የማያሳይ መሆን የለበት ...
⓷ጠባብ ሆኖየሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ መሆን የለበትም.....👆ክፈል 1.
⓸ሴት ልጅ በአለባበስዋ ወንድን መምሰል የለባትም ፦ነብዩ ሰ.ዐ.ወ በወንድ የሚመሳሰሉ እና የወንዶችን መለያ የሚያደርጎ ሴቶችን ተራግመዋል።
#ለ አል-ሒጃብ
ሂጃብ ማለት ትርጉሙ የቅርብ ዘመጆቿ ካልሆኑ ወንዶች ሰውነቷን መሸፈን መለት ነዉ ።አላህ እንዲህ ይላል፦

وَلَا يُبْدِينَ زِيَنَتَهُنَّ إلَّا مَاظَهَرَ مِنْهَا وَلْيَضْرِبْنَّ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِنَّ وَلَايُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلًّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ ءَابَاءِهِنَّ أًوْ ءَابَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أو أبْنَاءِهَنَّ أو أبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أو إِخْوَنِهِنّ..(.النور: ٣١
....(የውስጥ) ጌጣቸውንም ከርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፤ጉፋታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ የጣፉ፤(የውስጥ )ጌጦቻቸውንም ለባሎቻቸው ፣ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ፣ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ፣ ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች፣ወይም ለወንድሞቸቸው...ካልሆነ በስተቀር አይግለጡ ። አን-ኑር ፡31

በሌላም አንቀፅ ፡እንዲህ ይላል ፡
.
..وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنّ مَتَعا فسْئَلُونَّ مِن وَرَآءِ حِجَابٍ.......
الأحزاب:٥٣
..........ዕቃንም ( ለመዋስ) በጠየቃችኀቸው ጌዜ ከመጋረጃው ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው ፤..አል -አሕዛብ:53

https://t.me/leihَte
https://t.me/leihte/279
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
በድቅድቅ ጨለማ
በጥልቅ ጉድጓድ ውሰጥ ያለችን ትንሽ ጉንዳን የሚንከባከብ አላህ አንተን የሚረሳ ይመስልሀል ?https://t.me/leihte/288
🌹ኢላህዬ🌹
ሚስጥሬን አዋቂ
ስህተቴን ደባቂ
ጥሪዬን ተቀባይ
ወንጀሌን ይቅር ባይ
ስወድቅ ምታነሳኝ አንተ ነህና
ሸክሙ በዝቶብኛል አግዘኝ ረበና
እያወቅክ ካንተ ውጪ እንደሌላኝ
የሚረዳኝ
እኔን ለራሴ ላፍታ አትተወኝ
ኢላሂዬ እኔን ለኔ አትተወኝ....

https://t.me/leihte/289
ታጋሽ ሰዉ ሁሌም አሸናፊ ነዉ

ማንኛዉም መከራ በዉስጡ መልካም ነገር ይዟል። ወይ ብርታት ይሠጥሃል፣ ወይ ልምድ ያወርስሃል፣ ወይ ዱዓ ያስለምድሃል፣ ወይ ዕውቀት ይገልጥልሃል። ሸይጧን ግን ይህን ሁሉ የመከራን በጎ ክፍል ይደብቅና ጨለማዉን ጎን ያሳይሃል። በጨለማ ተደብቀው የሚመጡ ብርሃን የየያዙ መከራዎች አሉ። አላህ የእዝነት ብርሃኑን ያሳየን።
منقول
t.me/https_Asselefya1
ከሞትክ በኋላ ሰዎች እንዴት
በፍጥነት እንደሚረሱህ ብታውቅ ኖሮ
በሂወትህ ከ አላህ ውጭ ማንንም
ለማስደሰት ብለህ አትኖርም ነበር
https://t.me/leihte/290
Forwarded from 📚ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የዕውቀት ቁንጮ ነው!!📚📚 (️ (مَنْ عَمِلَ صَالِحًا فلِنَفْسِه) 𝑨𝒍𝒍𝒂𝒉 𝑰𝒔 𝑶𝒏𝒍𝒚 𝑶𝒏𝒆)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም ጁሙዓ ይሁንላቹ
ባለትዳር ወንድሞች አላህን ፍሩ አላህን ፍሩ ኢተቂላህ!!
በተለይ በተለይ ጫት ቃሚዎች አላህ ጫቱን ታች ወደላይ ያድርግባቹና አላህን ፍሩ!!

ጠዋት ትወጣለህ ትሰራለህ በስራ ቦታህ ታሳልፋለህ ሲመሽ ደሞ ጓደኛዬ ምኔ እያልክ እዛ ጫት ስቀመቅም ታመሻለህ።

ዉድዋ ሚስትክ ግን ቀን ሙሉቀን ብቻዋን : ሲመሽም በር በር እያየች በዛዉ ትተኛለች!! አታሳዝንክም ግን!!

ልጆችክስ እ አይናፍቁህም አንተ እስትገባ ይጠብቃሉ በናፍቆት ስታመሸ ልጅ ናቸዉ ይተኛሉ ።
አንተ አሁን አባት ነኝ ባል ነኝ ትላለክ!?ቢላሂ አለይክ?? እስቲ ለራስህ ጠይቀዉ በአላህ ወንድሜ ትዳር ማለት እኮ እንጨትና ከሰል መግዛት አደለም!! የቤት አስቤዛ ማስገባት አደለም!!

ትዳር ማለት መቻቻል ትዳር ማለት መከባበር ትዳር ማለት መፈቃቀር ትዳር ማለት መነፋፈቅ ትዳር ማለት መግባባት ነዉ።

እንጂ ትዳር መሰለቻቸት መኮራረፍ መራራቅ አይደለም ወላሂ።
ትዳር እኮ የዱንያ ጀነት ነዉ አደለም እንዴ ሁለቱ ሰዎች ከተግባቡ ከተዋደዱ ትዳር ማለት የዱንያ ጀነት ነዉ ላወቀበት!!


ስለዚ አኺ አደራህን የሚስትህን ልብ አትስበር ከናት ካባትዋ ቤት አመጣሀት አደል ኸላስ ፍቅር ስጣት ብቸኛ አታርጋት ትርፍ ግዜህን ከዉድዋ ሚስትህ ጋር አሳልዉ!!
4 ወርቃማ ንግግሮች ከዉዱ ነብያችን "ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም"

ረሱል "ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም" እንዲህ አሉ፦

¹የበደለህን ሰዉ ይቅር በል

²(ዝምድናን) የቆረጠህን ቀጥል

³ወዳንተ መጥፎ የሰራብህን መልካም ዋልለት

በራስህ ላይ እንኳ ቢሆን ሐቅን ተናገር

صحيح الترغيب2467

📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚

منقول
እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉትን እሳትን ብቻ ነው ።እሳትንም በርግጥ ይገባሉ ።
(ሱረቱል ኒሳዕ መራፍ 10)

https://t.me/leihte/291
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
እውነተኛ የሆኑ ጓደኞችን ፈልጋችሁ ያዙ ,እነሱ በሰላም ግዜ ጌጥ በችግር ግዜ አለኝታ ናቸው
🌺ረሱል ሰ.ዐ.ወ https://t.me/leihte/296
#وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
የተኛ ሰው ህልም እያየ እንደነበረ ከተነሳ ቦኋላ እጂአያውቀውም ከአኺራ ዝንጉ የሆነ ሰው ሞቶ ከተነሳ ቦኋላ እንጂ ብዙ የከሰራቸውን ነገሮች አያውቅም።

🌺እህት ወንድሞቼ ሳይረፍድብን ነፍሳችንን እንመርምር .......
አላህ ካተረፉት እንጂ ከከሳሪዎች ተርታ አይመድበን
🤲 አሚን🤲
https://t.me/leihte/297
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ፦
إِنَّ اللهَّ لَا يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ،
وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَا لِكُمْ
አላህ ወደ መልካችሁ እና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ።ነገር ግን ወደ ልቦናችሁና ተግባራችሁ ይመለከታል።

https://t.me/leihte/298
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from ليطمئن قلبي🤍 (. .,)
🌙በለሊቱ ክፈለ-ግዜ "ቁምና ጌታህን 🤲ተማፀን ።ከዛም መስገጃህን በምትጠቀልለው መልኩ ጭንቀትህንም ጠቅለል አድርገው ጌታህ በርግጥም የማያሳፍር ነው ።ጥያቄህን መላሽ ነው ።
https://t.me/alabizikrilahitemeinelkulubb
copy
ምናልባት እጅህ ላይ ሰዓት ልታደርግ ትችላለህ ፣ከእጅህ ላይ የሚያነሳው ወራሽህ ሊሆንል ይችላል ፣የመኪናህን በር ልትዘጋው ትችላለህ ፣የሚከፍተው የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ሊሆን ይችላል፣የሸሚዝህን ቁልፎች ልትዘጋ ትችላለህ ፣ጀናዛ አታቢ ሊፈታቸው ይችላል፣ስትተኛ አይኖችህ ወደ ቤትህ ጣሪያ ከተመለከቱ ቦኋላ ትከድናቸዋለህ ከዚያም የሰማያትና የምድርአምላክ ስር ልትከፍታቸው ትችላለህ ።
🤲ያ አላህ ኻቱማችንን አሳመርልን

https://t.me/leihte/296
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)