Forwarded from 📚ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የዕውቀት ቁንጮ ነው!!📚📚 (️ (مَنْ عَمِلَ صَالِحًا فلِنَفْسِه) 𝑨𝒍𝒍𝒂𝒉 𝑰𝒔 𝑶𝒏𝒍𝒚 𝑶𝒏𝒆)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም ጁሙዓ ይሁንላቹ
ባለትዳር ወንድሞች አላህን ፍሩ አላህን ፍሩ ኢተቂላህ!!
በተለይ በተለይ ጫት ቃሚዎች አላህ ጫቱን ታች ወደላይ ያድርግባቹና አላህን ፍሩ!!
ጠዋት ትወጣለህ ትሰራለህ በስራ ቦታህ ታሳልፋለህ ሲመሽ ደሞ ጓደኛዬ ምኔ እያልክ እዛ ጫት ስቀመቅም ታመሻለህ።
ዉድዋ ሚስትክ ግን ቀን ሙሉቀን ብቻዋን : ሲመሽም በር በር እያየች በዛዉ ትተኛለች!! አታሳዝንክም ግን!!
ልጆችክስ እ አይናፍቁህም አንተ እስትገባ ይጠብቃሉ በናፍቆት ስታመሸ ልጅ ናቸዉ ይተኛሉ ።
አንተ አሁን አባት ነኝ ባል ነኝ ትላለክ!?ቢላሂ አለይክ?? እስቲ ለራስህ ጠይቀዉ በአላህ ወንድሜ ትዳር ማለት እኮ እንጨትና ከሰል መግዛት አደለም!! የቤት አስቤዛ ማስገባት አደለም!!
ትዳር ማለት መቻቻል ትዳር ማለት መከባበር ትዳር ማለት መፈቃቀር ትዳር ማለት መነፋፈቅ ትዳር ማለት መግባባት ነዉ።
እንጂ ትዳር መሰለቻቸት መኮራረፍ መራራቅ አይደለም ወላሂ።
ትዳር እኮ የዱንያ ጀነት ነዉ አደለም እንዴ ሁለቱ ሰዎች ከተግባቡ ከተዋደዱ ትዳር ማለት የዱንያ ጀነት ነዉ ላወቀበት!!
ስለዚ አኺ አደራህን የሚስትህን ልብ አትስበር ከናት ካባትዋ ቤት አመጣሀት አደል ኸላስ ፍቅር ስጣት ብቸኛ አታርጋት ትርፍ ግዜህን ከዉድዋ ሚስትህ ጋር አሳልዉ!!

✨እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉትን እሳትን ብቻ ነው ።እሳትንም በርግጥ ይገባሉ ።
(ሱረቱል ኒሳዕ መራፍ 10)
https://t.me/leihte/291
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
(ሱረቱል ኒሳዕ መራፍ 10)
https://t.me/leihte/291
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
✨እውነተኛ የሆኑ ጓደኞችን ፈልጋችሁ ያዙ ,እነሱ በሰላም ግዜ ጌጥ በችግር ግዜ አለኝታ ናቸው
🌺ረሱል ሰ.ዐ.ወ https://t.me/leihte/296
#وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
🌺ረሱል ሰ.ዐ.ወ https://t.me/leihte/296
#وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
✨የተኛ ሰው ህልም እያየ እንደነበረ ከተነሳ ቦኋላ እጂአያውቀውም ከአኺራ ዝንጉ የሆነ ሰው ሞቶ ከተነሳ ቦኋላ እንጂ ብዙ የከሰራቸውን ነገሮች አያውቅም።
🌺እህት ወንድሞቼ ሳይረፍድብን ነፍሳችንን እንመርምር .......
አላህ ካተረፉት እንጂ ከከሳሪዎች ተርታ አይመድበን
🤲 አሚን🤲
https://t.me/leihte/297
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
🌺እህት ወንድሞቼ ሳይረፍድብን ነፍሳችንን እንመርምር .......
አላህ ካተረፉት እንጂ ከከሳሪዎች ተርታ አይመድበን
🤲 አሚን🤲
https://t.me/leihte/297
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
✨ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ፦
إِنَّ اللهَّ لَا يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ،
وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَا لِكُمْ
አላህ ወደ መልካችሁ እና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ።ነገር ግን ወደ ልቦናችሁና ተግባራችሁ ይመለከታል።
https://t.me/leihte/298

Forwarded from ليطمئن قلبي🤍 (. .,)
🌙በለሊቱ ክፈለ-ግዜ "ቁምና ጌታህን 🤲ተማፀን ።ከዛም መስገጃህን በምትጠቀልለው መልኩ ጭንቀትህንም ጠቅለል አድርገው ጌታህ በርግጥም የማያሳፍር ነው ።ጥያቄህን መላሽ ነው ።
https://t.me/alabizikrilahitemeinelkulubb

copy
✨ምናልባት እጅህ ላይ ሰዓት ልታደርግ ትችላለህ ፣ከእጅህ ላይ የሚያነሳው ወራሽህ ሊሆንል ይችላል ፣የመኪናህን በር ልትዘጋው ትችላለህ ፣የሚከፍተው የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ሊሆን ይችላል፣የሸሚዝህን ቁልፎች ልትዘጋ ትችላለህ ፣ጀናዛ አታቢ ሊፈታቸው ይችላል፣ስትተኛ አይኖችህ ወደ ቤትህ ጣሪያ ከተመለከቱ ቦኋላ ትከድናቸዋለህ ከዚያም የሰማያትና የምድርአምላክ ስር ልትከፍታቸው ትችላለህ ።
🤲ያ አላህ ኻቱማችንን አሳመርልን
https://t.me/leihte/296
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
✨ምናልባት እጅህ ላይ ሰዓት ልታደርግ ትችላለህ ፣ከእጅህ ላይ የሚያነሳው ወራሽህ ሊሆንል ይችላል ፣የመኪናህን በር ልትዘጋው ትችላለህ ፣የሚከፍተው የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ሊሆን ይችላል፣የሸሚዝህን ቁልፎች ልትዘጋ ትችላለህ ፣ጀናዛ አታቢ ሊፈታቸው ይችላል፣ስትተኛ አይኖችህ ወደ ቤትህ ጣሪያ ከተመለከቱ ቦኋላ ትከድናቸዋለህ ከዚያም የሰማያትና የምድርአምላክ ስር ልትከፍታቸው ትችላለህ ።
🤲ያ አላህ ኻቱማችንን አሳመርልን
https://t.me/leihte/296
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
🥀እህቴ 🥀
🍁ልብስሽ ሰፊ ነው ለፋሽን አይመችም ሲሉሽ....የናንተ ጠባብ ነው ለጀነት አይመችም በያቸው።
🍂ሰፊ ልብስና ሰፊ አስተሳሰብ ነፃነት አለው።
https://t.me/leihte/297
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
🍁ልብስሽ ሰፊ ነው ለፋሽን አይመችም ሲሉሽ....የናንተ ጠባብ ነው ለጀነት አይመችም በያቸው።
https://t.me/leihte/297
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
✍🏻 ከሷሊህ ሰዎች አንዱ :-
(አንዲት ሴት ከሸሪዐ ውጪ የሆነ የተራቆተ ልብስ መልበሷ በራሱ የአላህ ቁጣ በእሷ ላይ እንዳለ ምልክት ነው ا
➡️ምክንያቱም አላህ አደምና ሀዋእ
ላይ በተቆጣ ጊዜ ልብሳቸው
እንዲገፈፍ አድርጎ ሀፍታቸው
እንዲታይ አድርጎ ነበርና ይላሉ።)
አዎ አላህ ዱንያ ላይ አግዝፎ እርም ያደረገውን ኸምር (መጠጥን) ጀነት ውስጥ ተፈቃጅ አድርጎታልኮ መገላለጥን ግን ዱንያም ላይ አኺራም ላይ እርም ያደረገው ከባድ ወንጀል ነው።
👉አረ እንደውም ከጀነት ፀጋዎች ውስጥ ጭማሪ የሆነ መሰተር እንደሆነም ተነግሯል
ለዚህም ሱረቱ ጠሀ ላይ አላህ ለአደም "አንተኮ ጀነት ውስጥ አትራብምም አትራቆትምም ብሎታል።)
አላህ ሴቶቻችንን ያስተካክልልን
@bin_Husseynfurii
ــــــــــــــــــ 👑 ــــــــــــــــــ

Forwarded from ليطمئن قلبي🤍 (اكرام🍂)
ዓለም ከእነዚህ ልብሶች በላይ
ክብርን የሚያጎናፅፍ ልብስ
አይታ አታውቅም ወደፊትም አታይም.....
ኒቃቤ💜
ክብርን የሚያጎናፅፍ ልብስ
አይታ አታውቅም ወደፊትም አታይም.....
ኒቃቤ💜
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
✨وَمَا تَسْقُطُ مِن وَرَقَةٍ إِلَّا يَعْلَمُهَا
ከ ቅጠልም አንዲትም አትረግፍም
አሏህ የሚያውቃት ቢሆን እንጂ
ከ ቅጠልም አንዲትም አትረግፍም
አሏህ የሚያውቃት ቢሆን እንጂ
Forwarded from እንተዋወስ(entewawes) (. .,)
Forwarded from ☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭 (:))
ያስለቀሰኝ ታሪክ
.
.
.. ከሼይኮች አንዱ ባለቤቱ ሞተችበት አላህም ለሚስቱ ምህረትን ያብዛላትና ሸይኹ በጣም አዘነ.. ሀዘኑም በእሷ ላይ የበረታ ሆነ, እናም አንድ የባለቤቱ ጓደኛ ትዕግስት (ሰብር) እንዲሰጠው ብላ መልእክት ላከችለት እና ደብዳቤዋ እንዲህ ይላል... "ሰላም ለእናንተ ይሁን ሼክ እኔ ከሚስትህ ጓደኞች አንዷ ነኝ ስለ ውድ ሚስትህ ኡሙ ሙዓዝ ሞት ተነገረኝ። ያለፍክበት ሀዘንህን ሰምቻለሁ.. እና ታሪኬን አንብብ ... ስለ ማጣት እና ህመም የተከሰተ የመጀመሪያው ታሪክ አይደለም. እንደ እኔ በህመም እና በእጦት የሚሰቃዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሉ። አንዱ ወላጆቹን አጥቶ፣ ወይም ወንድሞቹንና እህቶቹን፣ ወይም ሁለቱንም አጥቶ የሚኖር አለ። ታሪኬ የጀመረው በረመዷን 27ኛው በቀኑ የመጨረሻ ሰአት ላይ ነው። በእለቱ ሁላችንም በአንድ መኪና ተሳፍረን ዑምራ ለማድረግ ወደ ተከበረው የአላህ ቤት ልንሄድ ተስማማን። ወንድሞቼ በየራሳቸው መኪና መምጣትን ትተው ከኛ ጋር በ አንድ መኪና ለመሄድ መፈለጋቸው የ አላህ ውሳኔ ነው ... ስምንት ሰዎች ነበርን... እኔ፣ ወላጆቼ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ..
መኪናውን ሚነዳው አባቴ ነበር እና እናቴ ከጎኑ ነበረች። በዚያን ጊዜ እያንዳንዳችን ቁርኣንን ይዘን ሀረም እስክንደርስ ድረስ ሙሉ ቁርዓኑን ቀርተን (አንብበን) ለመጨረስና ዱኣ ለማድረግ ተስማማን ። እናም በዝምታ እና በተመስጦ ማንበብ ቀጠልን ዳግመኛ ማንበብ እንደማንችል ነገር ይመስላል አቀራራችን። እህቴ እያነበበች ታለቅሳለች ሌላኛዋም ወደ እኔ እያየች እያለቀሰች ዱኣ ታደርጋለች... እንባው ለምን እንደሆነ ጠየኳቸው..? ከመካከላቸው አንዷ፡- እያነበብኩ ሳለ የአላህ ድምፅ ወደ እኔ ቅርብ ነው አለችኝ ። በዛን ጊዜ .. ይመስለኛል አባቴ አላህ ይዘንለትና እንቅልፍ አሸነፈው .. መኪናው ከ ኮረብታው ጫፍ ላይ ተንሸራተተ.. ይህ ኮረብታ በተራራው አናት ላይ ነበር የነበረው.
መኪናው ከረጅም ርቀት ወደ ሸለቆው ውስጥ ያስገባን ጀመረ.. እና ገለበጠን መኪናው በተንከባለለ ቁጥር አንድ ሰው ከመኪናው ውስጥ ተወርውሮ ይወድቃል .. እኔ ዛፍ ላይ ወደቅኩኝ የቀሩት በሸለቆው ውስጥ ወደቁ.. አደጋው በደረሰበት ሰአት የመግሪብ ሰላት አዛን እየተጣራ ነበር እና ፆመኞች ነበርን..ከዛ... ራሴን ሳትኩኝ ብዙ ደማሁኝ.. አስታውሳለሁ ከእንቅልፌ እንደነቃሁ እየጮህኩኝ ፈልጌያቸው ነበር። ስብራት እና ጉዳት ቢደርስብኝም አንድ ጊዜ እየተራመድኩ አንዴ ደግሞ ተኝቼ እየተሳብኩ እነሱን መፈለግ ጀመርኩኝ ። መኪናው ሲወድቅ ማንም አላየንም ነበር። እነሱ ጋር እስክደርስ ድረስ መጎተት ጀመርኩ
ከዛም እህቶቼን አገኘውና ልሸፍናቸው ሞከርኩ.. ሞተውም አገኘኋቸው እያንዳንዳቸውም የፊት ጣታቸው ከፋ አድርገው ነበር ነእና ምስጋና ለ አላህ ይሁን ሸሃዳ ይዘው ነው የሞቱት ። በአንድ ቦታ ሰበሰብኳቸው። ከዛ ጨለመ... የእንስሳት ድምፆችን እና ጨለማን መፍራት ጀመርኩኝ . ወንድሞቼን በጭራሽ ላገኛቸው አልቻልኩም ። እየተሳበኩ ስሄድ እናቴን ሞታ አገኘኋት። እሷም ሸሃዳ ይዛ ነበር ..አባያዋም እንደ ከፈን ተጠቅልሎባት፣ጣቷ ብቻ ከሷ ላይ ይታይ ነበር ፣እናም ሸሃዳ ይዛለች...የተሸፋፈነቺው እንኳን አልወደቀም።በእቅፏ ላይ ሆኜ እሷ እንድትሰማኝ ለማድረግ ሞከርኩ.. ግን ምንም ውጤት የለም .. አባቴ ጋር ደረስኩ፣ እሱ አሁንም በህይወት አለ እና እየደማ ነበር። እኔ ህይወትሽን አደራ እልሻለሁ .. እዚህ ለረጅም ጊዜ እንዳትቆዪ.. ወደ ተራራው ውጪ እና የሚረዳሽን ሰው ጥሪ.. ወንድሞችሽን እና እናትሽን እርጂያቸው አለኝ. ያን ጊዜ የውሻዎችን ድምፅ ፈራሁ፤ በዚህ በድቅድቅ ጨለማ አላህ በዙሪያዬ አቆየክ ብዬ
በአባቴ እቅፍ ላይ ቆየሁ.. ደም እየደማሁ ነው እናም መንቀሳቀስ እንደማልችል ነገርኩት እና ከአንተ ጋር እቆያለሁ አልኩት.. በዚያን ጊዜ ደረቱ ላይ ወሰደኝ.. በገባው ቃል መሰረት እንድሆን መከረኝ .. ዱኣ ያደርግልኝም ነበር.. እሱም እየመከረኝ እያለ በዛው ህይወቱ አለፈች.. እራሴን ስቼ እስከምወድቅ ድረስ ብቻዬን እያለቀስኩ ዱኣ እያደረኩኝ ቆየሁ..ራሴን አልተሰማኝም, በጣም ደም ስለፈሰሰኝ እራሴን ሳትኩኝ.. በ ዓይነ ህሊናህ አስበው እስኪ በሁለተኛው ቀን እስከ አስር ድረስ ማንም አላየንም ነበር አንድ ሙሉ ቀን ማንም አላየንም።ከዛ ቡሃላ አንድ እረኛ አገኘን.. ለአከባቢ ጠባቂዎች አሳወቀ..ከዛ የመከላከያ ቡድኑ ከአውሮፕላን እና ከመኪና ጋር መጡ.. በቡድን ተጎተትን.. ከዚያ በኋላ እስከ አምስት ወር ድረስ ከኮማ አልነቃሁም ነበር። እና የሆነውን ነገር ገባኝ.. እንደ ቅዠትና ህልም ይመስል ነበር.. ሁለት አመት በካናዳ በህክምና ውስጥ አሳለፍኩ። በጭንቅላት፣ አንገት፣ ጀርባ፣ ዳሌ፣ ብዙ ቦታዎች ላይ ከባድ ስብራት ነበረብኝ።
በደም መፍሰስ ምክንያት እናት የመሆንን ፀጋ አጣሁ። በዶክተሮቹ በኩል ብዙ ሙከራዎች ቢደረጉም አልተሳካም. ስለዚህ ምርጫው ወይ ሕይወቴ ማጣት ነበር...ወይ ደግሞ የልጆችን የማግኘት በረከት ሊያሳጣኝ የሚችለው ቀዶ ጥገና... ምርጫው ከባድ ነበር ... እና ብዙ አሰቃየኝ ... አሁን ደህና ነኝ እና ጤነኛ ነኝ (አልሃምዱሊላህ) አላህ ይመስገን። ያ ሸይኽ እኔም ሆን ብዬ ታሪኬን የነገርኳቹህ በጣም የምትወዱትንና የምትሳሱለትን ሰው ያጣቹት እናንተ ብቻ እንዳልሆናችሁ እንድታውቁ ነው። እና አለም ከነሱ አንዳቸውን በማጣት እንደማያበቃ...ነገር ግን የ ኢማን መሟለት ምንክያት በሆነው በአላህ ቅድመ ውሳኔ (በቀደር) መታገስ አለብን። እና አላህ ይመስገን እነሆ ወደ ስራዬ ተመልሻለው ..ወደ ሪያድ ተዘዋውሬ ከአዲሱ ህይወቴ ጋር መኖር እና መኗኗር ጀምሪያለው.... ስለ ሁሉም ነገር አላህ ይመስገን.. ሳልነግራችሁ ረሳሁት...የእህቶቼ ሰርግ ሁለት ሳምንት ቀርቶት ነበር...ከሰርጋቸው በፊት ዑምራ ለማድረግ ፈልገን ነበር። እስከ አሁን ድረስ የሰርግ ልብሳቸው ከእኔ ጋር ነው እኔም እስክሞት ድረስ እጠብቃቸዋለሁ ።
💡
💡
መልእክት ፡
በዙሪያቸው ካለው ነገር ሁሉ ምኞታቸው ለዘገየባቸው ሁሉ ጥቂት አመታት መታገስ ምንም ችግር የለውም በዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላት ወሰላም) ላይ የሆነው ነገር ሁሉ ታጋሽ በሆኑት ላይ ሁሉ ይፈጠራል ። አላህ የወሰደው ለጥበብ ነው፣ ያስቀረው ለምህረት ነው ... በእርግጥም የሚሰጠን ነገር መጠኑ ሊጨምር ሲል ምኞቶቻችን ይቆያሉ ። ስለዚህ በ አላህ ላይ ያላቹን እምነት አስተካክሉ።
ሶስት ዱኣዎችን ሱጁድ ላይ ስትሆን ማድረግን አትርሳ፡- ጌታዬ ሆይ የ ኻቲማን ማማር እለምንሃለሁ ጌታዬ ሆይ ከሞት በፊት ቅን ንስሐን ስጠኝ አንተ ልቦችን የምትገለባብጥ የሆን አምላኬ ሆይ ልቤን ዲንህ ላይ አፅናት። ይህን መልእክት እንኳን ሼር ለማድረግ ካሰብክ፤ ንያህን በመልካም ነገር አሳምረው ፤ ምናልባት አላህ ከቅርቢቱና ከኋለኛይቱ ዓለም ጭንቀት ሊገላግልህ ይችላል።
.
አንብበው ከጨረሱ ቡሃላ አልሀምዱሊላህ ብለው ይፃፉ!!
#join us👇 & share
╭┈─────── ೄ🌻ྀ࿐ ˊˎ-
╰┈➤ᢀ @fafiru_illahi
@fafiru_illahi

🌹የነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአመጋገብ ሱና🌹
#1ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) መብላት ከመጀመራቸው በፊት እጃቸውን ይታጠብ ነበር ።የሚበሉት በቀኝ እጃቸው ሲሆን ከፊታቸው ካለው ምግብ ነበር የሚበሉት
#2የነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተደግፈው በልተው አያውቁም፣ምግብ ሲበሉ የተለያየ ዓይነት አቀማመጥ ነበራቸው ።
ሀ,ልክ ተሽሁድ ላይ እንደሚቀመጡት አይነት ይቀመጡ ነበር ።
ለ,ልክ እንደዚሁ ይቀመጡና የአንድ እግራቸው ጉልበት ደረታቸው ጋር ይደርስ ነበር።
ሐ,የውስጥ እግራቸው መሬት ላይ ተለጥፎ ቁጢጥ ይሉ ነበር።
#3ነቢያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጠረጼዛ ተደግፈውም ሆነ ወንበር ላይ ተቀምጠው በልተውም አያውቁም ።ደስታርኸዋን (ቆዳ ወይም ጨርቅ) መሬት ላይ አንጥፈውአንጥፈው ይመገቡ ነበር።
#4አብዛኛውን ጊዜ ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (በአውራ ጣት፣ጠቋሚ ጣት እና መሀል ጣታቸው )በመጠቀም ነው።ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ግን የቀለበት ጣታቸውንም ጨምረው ይመገቡ ነበር
#5ተመግበው ሲጨርሱ ጣቶቻቸውን አፋቸው ውስጥ ከትተው ያፀዱዋቸው ነበር ።ከመሀል ጣታቸው ጀምርው አውራ ጣታቸው ላይ ያቆማሉ ።
#6በገበታው ላይ ያለው ምግብ ከመሀል ጀምሮ የተደረደረ ከሆነ ከፊታቸውና ከሥር ካለው ይጀምሩ ነበር። የምግብ በረካ ወደ መሀል እየቀነሰ ይሄዳል ብለዋል።
#7ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በብዙ ሰሀኖች የሚቀርብ የተለያየ አይነት ምግብ አይወዱም ነበር ።
#8ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሀለዋ (ጣፋጭ) ማር ፣ኮምጣጤ፣ተምር ፣ሀብሀብ ፣ኪያር እና ዝኩኒ ይወዱ ነበር ።
#9ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሽንጥ ፣የአንገት የትከሻ ስጋ ይወዱ ነበር።
#10ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንዳንድ ግዜ ሁለት ምግቦችን ይመገቡ ነበር ፤ሀብሀብ ና ተምር ፣ኪያር ና ተምር....
#11ይቀጥላል

🌹የነብዩ ((ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) )የአመጋገብ ሱና🌹
#11ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገብ ይተዉ ነበር ።
#12ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያልበሰለ ሽንኩርት ፣ነጭም ይሁን ቀይ በልተው አያውቁም ።
#13ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተነፋ ዱቄት አይበሉም ነበር ።(ነገር ግን አልከለከሉም)
#14ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቀጭን ቂጣ (መለዋ) በልተው አያውቁም፣ነገር ግን በስጋ ወይም በአትክልት ሶስ(ቁሌት )ከተነከረ ይመገቡ ነበር።
#15ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እርሾ የሌለው ዳቦ በልተው አያውቁም ።
#16ተምር ወይም ዳቦ ንፁህ ቦታ ላይ ከወደቀ ጠርገው ይበሉ ነበር ።
#17በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም ነበር፤መጀመሪያ ያቀዘቅዙት ነበር። አላሁ ተዓላ እሳት አይመግበንም። ይሉ ነበር።በጣም በሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል።
#18ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምግባቸውን አሽትተው አያውቁም። ጥሩ ያልሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል።
#19ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲበሉም ሆነ ሲጠጡተቀምጠው ነው ።ነገር ግን ፍራፍሬዎች ቆመውም ሆነ እየተራመዱ በልተው ነበር።
#20ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምግብ እንደቀረበ ወድያው በእጃቸው ከምግቡ አይቆነጥሩም ነበር ።እጃቸውን ምግቡ ላይ ያስቀምጡ ነበር።
#21 አንዳንዴ የበሰለን ሥጋ በቢላዋ ቆርጠው ይበሉ ነበር።
#22ይቀጥላል......

🌹የነብዩ ሰ.ዐ.ወ የአመጋገብ ሱና🌹
#22ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ምግብ የያዘን የምግብ ዕቃም ሆነ መጠጥ የያዘ መጠጫን ይከድኑ ነበር።የሚከድኑበት ነገር ካጡ ካላዩ ላይ ስንጥር ያስቀምጡ ነበር።
#23ተሰባስበው ለተቀመጡ ሰዎች የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር ሊያከፋፍሉ ሲፈልጉ ከቀኛቸው ይጀምሩ ነበር ።ከግሬቸው ለመጀመር ከፈለጉ ከቀኛቸው ያለውን ሰው ፍቃድ ይጠይቁ ነበር ።
#24ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ማታ የተሰራን ምግብ እስከጠዋት ፣ጠዋት የተሰራን ምግብ እሰከ ማታ አያቆዩም ነበር።(ለሚቀጥለው ምግባቸው በአላህ ላይ ይተማመኑ ነበር።
#25ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ሥጋ ወደቤት ሲያመጡ ለጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያደርጉ ነበር ።
#26ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ምግብም ላይ ሆነ መጠጥ ላይ ተንፍሰው (እፍ ብለው)አያውቁም። ምግብ ላይ መተንፈስን መጥፎ ልማድ አድርገው ይቆጥሩት ነበር ።
#27ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ሁለት ፍራፍሬዎችን በሁለት እጆችቻቸው ላይ አስቀምጠው ተራ በተራ ይመገቡ ነበር ።
#28ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ተምር ከተመገቡ በኋላ ፍሬውን በግራ እጃቸው ይጥሉት ነበር።ፍሬውን በሸሀዳ ጣታቸውና በመሀል ጣታቸው ጀርባ ላይ ላይ አድርገው ይወረውሩት ነበር።
#29የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር።
#30የማያውቁት ሰው ምግብ ሲያመጣላቸው አስቀድመው እርሱ ከምግቡ እንዲበላ ያደርጉ ነበር።ይህንን ማድረግ የጀመሩት ጠላቶቻቸው መርዝ በምግብ ካበሉዋቸው ቦኋላ ነው።
#31ረሱል ሰ.ዐ.ወ የጎድን አጥንት በጣም ይወዱ ነበር።
#32ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ከተጠሩበት ቤት ሲሄዱ መንገድ ላይ ሰው ካጋጠማቸው ይዘውት ይሄዱና ጠሪዎችን ፍቃድ ይጠይቁዎቸው ነበር ።ከተፈቀደላቸው ይዘውት ይገባሉ።
#33ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንግዳቸውን በቃኝ እስኪላቸው ጠግቦ እንዲበላ ይገፋፉ ነበር።
#34ይቀጥላል https://t.me/leihte/299

🌹የነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአመጋገብ ሱና🌹
#34ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሰዎች ጋር እየበሉ ከሆነ ከገበታው የሚነሱት በመጨረሻ ነበር ። ይህንን የሚያደርጉት አንዳንድ ሰዎች ቀስ ብለው ስለሚመገብ ሌሎቹ ሲነሱ አፍረው መመገባቸውን እንዳያቆሙ ነበር ።ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እነዚህ ሰዎች እስኪጨርሱ ቀስ እያሉ እየተመገብ ይጠብቁዋቸው ነበር።
#35ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመጀመሪያዎች ሦስት ጉርሻዎች ቢስሚላህ ይሉ ነበር።
#36አንድ ሰው ቢስሚላህ ሳይል ከበላ እጁን ይይዙትና ቢሰሚላህ እንዲል ያደርጉት ነበር።
#37ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሰው በግራ እጁ ሲበላ ካዩት እጁን ይይዙትና ምግቡን ያስጥሉታል፣ከዚያም በቀኝ እጁ እንዲበላ ይነግሩታል።
#38አንድ አይነት ምግብ ከቀረበላቸው ከፊታቸው ብቻ ይበሉ ነበር ።ነገረ ግን ከአንድ በላይ ምግብ ከቀረበላቸው ከሰዎች ፊት ሄደው ከመብላት አይቆጠቡም ነበር።
#39ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የቀይ ተምሮችን ውስጣቸውን ካፀዱ በኋላ ይበሉ ነበር ።
#40በልተው ጨርሰው ከታጠቡ በኋላ በጺማቸውና በራስ ፀጉራቸው ላይ ያደርቁ ነበር።
#41ዶሮ መብላት ከፈለጉ ቤታቸው ውስጥ ለብዙ ቀን ካቆዩት በኋላ አርደዋት አብስለው ይበሉ ነበር።
#42ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሾርባ ውሰጥ ቂጣ ከተው መብላት ይወዱ ነበር።
#43ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቅቤ ከተምር ጋር መመገብ ይወዱ ነበር ።ተምርም ከወተት ጋር ይመገቡ ነበር፤ሁለቱም ምርጥ ምግቦች ናቸው ብለዋል።
https://t.me/leihte

Telegram
እንተዋወስ(entewawes)
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
እህቴ 🌸⑧
የበፊት ሰዎችን ታሪክ ለማንበብ እንደምትጓጊና ታሪካቸዉን ማወቅ እንደሚያስደስትሽ አዉቃለሁ። የዛሬዉ ቀጠሯችን በእስልምና ታሪክ ዉስጥ ካለፉት እጅግ ምርጥ ከሆኑት ሴቶች መሀል የአንዷ ነዉ። ዛሬ የጀግንነት፣ የቆራጥነት ተራራ ስለሆነችዋ ሴት እናወራለን። ዛሬም በፊርዖን ቤተ መንግስት እንቆያለን።
እቺ ሴት በዱንያ ላይ እንደሱ ያለ ክፉ ሰዉ አልፎ የማያዉቅ ሰዉ ሚስት ናት። የዚያ በሞኝነትና በቅጥፈት ‘እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ!’ ሲል ህዝቡ ዉስጥ ዉሸት የሚለፍፈዉ ሰዉ ሚስት ነች። ይህ ሞኝ ሰዉ እንዲያመልኩት ብሎ ሰዎችን ያስገድዳል። እምቢ ያሉትን ይገላል፣ ይቀጣል። ቤተመንግስቱ በበደል የተሞላ ነበር።
እንደዚያ ከመሆኑም ጋር ግን በዚህ ቤተመንግስት ዉስጥ የሱን አምላክነትን ማይቀበሉ፣ አላህን በብቸኝነት የሚገዙ ምርጥ ባሮች ነበሩ። ከነሱ መሀል የራሱ የፊርዖን ሚስት አሲያ ቢንት መዛሂም ትገኛለች።
አሲያ ኢማን በልቧ የገባዉ ገና በጠዋቱ ነበር። ግን ምን ያረጋል ባሏን ከማንም በላይ ዉሸታም፣ ከሀዲና በዳይ እንደሆነ ስለምታዉቅ ኢማኗን ደብቃ ቆየች። ነገር ግን ከጊዜ ብኋላ የተለያዩ ተዓምራትን በሙሳ እጅ ስታይ፣ ሙሳ በምን አይነት መረጃ ፊርዖንን እንደሚከራከርና የሀሩንን አንደበተ‘ርቱዕነትን ስትመለከት ኢማኗ ጨመረ። እሷ በንፁህ አዕምሮዋ ይህ የሚታመም፣ የሚደክም፣ የሚበላና የሚጠጣዉ ተራ ባሏ በፍፁም ፈጣሪ ሊሆን እንደማይችል ታዉቃለች። በሀቅ ሊገዙት የሚገባዉ ብቸኛ ፈጣሪ መኖሩን ታምናለች። ያ ፈጣሪም የሙሳና የሀሩን ጌታ ነዉ።
ኢማኗን ለተወሰነ ጊዜ ከደበቀች ብኋላ ኢማኗ ከፍ ብሎ ልቧን በሙሉ መቆጣጠር ሲጀምር ፊርዖንን ፊት ለፊት አናገረችዉ። ያ የግብፅ ህዝብ ሙሉ የሚፈራዉን ጨካኝ ባሏ ፊት ቆማ ‘ፊርዖን ሆይ! (አልፈራህም!) ባንተ ክጃለዉ!’ አለችዉ። በሙሉ ራስ መተማመን ‘የሙሳና የሀሩንን አምላክ ተከትዬ ባንተ ክጃለሁ።’ አለችዉ። በዳይነቱን ፊት ለፊቱ ነገረችዉ። ፊርዖን የተዉሂድን ቃል በሚስቱ መስማቱ ለሱ ከባድ ነበር። ተቆጣ፣ ገነፈለ።
እጅግ ከባድ ቅጣትን እሷን መቅጣት ጀመረ። የተለያዩ ቅጣትን ቀጣት። እሱም አልበቃ ብሎት ወታደሮቹን ወደ በረሃ ይዘዋት ወተዉ ወጥረዉ አራት ቦታ ላይ እስረዋት እንዲቀጧት አደረገ። ምግብና መጠጥንም ከለከሏት። ቀኑን ሙሉ ፀሀይ ዉስጥ አቆያት።
በሁለተኛዉ ቀንም ከእምነቷ ትመለስ እንደሆነ ጠየቃት። በጭራሽ እንደማታረገዉ ስትነግረዉ አሁንም ያለምግብና መጠጥ እዚያ ፀሀይ ላይ ሲያሰቃያት ዋለ።
በሶስተኛዉ ቀንም ወደ ቤቷና ወደ እምነቷ ብትመለስ እንደሚሻላት ነገራት። ቅጣቱን ልትቋቋመዉ እንደማትችል አሳወቃት። እሷ ግን ቅጣቱ ከኢማንና ከሰብር ዉጪ ሌላ ነገርን እንዳልጨመረላት ነገረችዉ።
ፊርዖንም ከሷ ላይ ተስፋ በቆረጠ ጊዜ ወታደሮቹ ትልቅ ቆጥኝን ከፍ አርገዉ አንስተዉ ጭንቅላቷን እንዲፈጠፍጡት አዘዛቸዉ። በዚህ ጊዜ አላህ እሱን የጠየቀችዉን የጀነት ቤቷን አሳያትና ፈገግ እንዳለች ቆጥኙ ተወረወረ።
አላህም ዝንተ ዓለም በየ ሚህራቦች በሚቀራዉ ቁርዓን ዉስጥ የምርጥ ሴቶች ምርጥ ምሳሌ እንደሆነች አወሳት። ለነዚያ ላመኑት ምርጥ ሞዴል እንደሆነች ተናገረላት። ያቺ ከጀነት በፊት የአላህን ጉርብትና የፈለገችዋን እንስት አላህም መሬትና በዉስጧ ያሉትን ነገር በሙሉ እስኪወርሳት ድረስ የምትወሳ እንቁ ሴት አድርጎ አቆያት።
እህቴ! እስልምናሽ ደምሽ፣ አጥንትሽ እንደሆነ እንዳትዘነጊ። ለዚህ እስልምናሽ የምትከፊዪዉ የትኛዉ ዋጋ ቀላል ነዉ። አሲያ ኮ የግብፅ ሴቶች አለቃ ነበረች። አንድን ነገር ስትፈልግ በጣቷ መጠቆም ብቻ ይበቃት ነበር። የዱንያ ጀነት በእጆቿ ላይ ናቸዉ። ነገር ግን እሷ ዱንያን ስትመለከታት ጠፊ እንደሆነችና አላህ ጋር ያለዉ በረከት ዘላለማዊ እንደሆነ አወቀች። ዘላለማዊዉን መርጣ ጠፊዉን ተወች።
እህቴ ሆይ! ዲንሽን ለዱንያ ብለሽ አትሽጪ!
🌻ከአላህ የሚያርቅሽን ሀራም ምግብን አትመገቢ!
🌷ከአላህ የሚያርቅሽን የትኛዉንም ፍቅረኛ አትቅረቢ!
🌹ኸይርሽን ሟጧ የሚበላን የትኛዉንም ስብስብ አትቀላቀዪ!
🥀እነሱ ፊት አላህን መታዘዝን የምታፍሪበትን የትኛዉንም ጀመዓ ራቂ!
🍁የአላህን ዉዴታ የሚያሳጣሽን የትኛዉንም ድርጊት አትፈፅሚ!
🍂ሁሉም ሴቶች በፋሽን ተታለዉ ሂጃባቸዉን ቢተዉ እንኳን አንቺ ግን እንዳተዩዉ!
🍃ሁሉም ሴቶች ላይፍ ነዉ እያሉ ወንድ ቢጨብጡም፣ ሙዚቃ ቢያዳምጡም፣ ከወንድ ጋር ተቃቅፈዉ ቢወጡም አንቺ ግን የአላህ ዉዴታ በመሻት ፅኚ!
አዉቃለሁ! ይህን ሁላ ስታረጊ ያለጓደኛ ብቻሽን ትቀሪያለሽ። ግን ኮ አንቺ የዱንያን ጀነት ለአኼራ ጀነት ብላ የተወች የአሲያ ልጅ ነሽ። አንቺስ ልክ እንደሷ ከሰዉ ፍቅርና ቀረቤታ በፊት የአላህ ፍቅርና ቀረቤታን አትፈልጊም እንዴ?
እህቴ ይህን አትርሺ!
ሰዉ ብቻዉን ይሞታል፣ ብቻዉን ይቀበራል፣ ብቻዉን ይነሳል፣ ብቻዉን ይገመገማል። ዘላለማዊ የሆነዉን የአላህ ቀረቤታ ጠፊ በሆነዉ በሰዎች ቀረቤታ አትቀይሪዉ! ልክ እንደእናትሽ አሲያ በአምነትሽ ጉዳይ ላይ የማንንም ወቀሳ አትፍሪ!
ከሁሉም በፊት የአላህ ዉዴታ ይቀድማል!!
منقول