ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በቅርቡ 2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፉ ይታወሳል ፡፡
በዚሁ መሰረት ተቋማችን የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የህበረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡በመሆኑም ቢሮው 3ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለማውጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን እየገለፀ የጨረታ ዝርዝር መረጃውን ቅዳሜ 29/2016 ዓ.ም በሚወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ የሚገለጽ መሆኑን እያሳወቅን በዚሁ አጋጣሚ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ያሳውቃል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ተጨማሪ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆቻችን ያግኙ
YouTube
https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment
Websit :-https://www.aalb.gov.et

❤2👍2
Lemikura.pdf
26.7 MB
ወደማእከል የተላኩ የሰነድ አልባ መረጃዎች
የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ
የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 መውጣቱን ተከትሎ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ምዝገባ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ በሁሉም ክፍለከተማ እና ወረዳዎች የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ከሰኔ1- ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል የተመዘገበ ሲሆን አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ የሚገኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያሳውቃል።
በመሆኑም በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ ምክንያት ቀኑ እንዲራዘም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄው በስፋት በመነሳቱ እና ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች እንደሆነ ተቋሙ የተገነዘበ ስለሆነ በጊዜ ገደቡ ሳይመዘገብ የሚቀር ውል እንዳይኖር ለማስቻል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም በማስፈለጉ የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24/2016ዓም መራዘሙን ቢሮው ይገልፃል።
የግል መኖሪያ ቤት አከራይም ሆነ ተከራይ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ሳይዘናጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ ጊዜያቸውን ተጠቅመው እንዲመዘገቡ ቢሮው በድጋሚ ያሳስባል።
የውል ምዝገባው ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በምሽት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ የሚካሄድ ስለሆነ ተመዝጋቢዎች ሳይጨናነቁ በተመቻቸው ሰአት መሄድ እና መመዝገብ ይችላሉም ተብሏል።

👍4❤2
"የምትተክል ሃገር፣ የሚያጸና ትውልድ!"
ዛሬ ማለዳ የ5ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በከተማችን ከሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አትሌቶች፣ የተለያዩ ስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመሆን አስጀምረናል።
አረንጓዴና ውብ አካባቢን ለመፍጠር፣ በተፈጥሮ የበለጸገችና ከአየር ብክለት የፀዳች አዲስ አበባን ለትውልዱ ለማዉረስ ቃላችንን በተግባር መንዝረን ከነዋሪዎቻችን ጋር በመሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባደረግነው ርብርብ የከተማችንን አረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለናል።
በኮሪደር ልማታችንም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ስንተክል ከርመናል።
ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻዎቻችን የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ እድሜ፣ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንዲሁም ሃይማኖት ሳይገድባቸው የከተማዋን ተፈጥሯዊ ሚዛን መጠበቅ የሚችሉ ሀገር በቀል ዛፎችን፣ ለገፅታ ድምቀት የሚሆኑ የውበት እፅዋቶችን እንዲሁም የአትክልትና የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።
ዘንድሮም በከተማችን 20 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ ለመስራት የተዘጋጀን ሲሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ ላይ በመሳተፍ ለትውልድ የሚሆን አሻራችሁን እንድታኖሩ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍2
ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ ፣በአቃቂ ቃሊቲ፤በአዲስ ከተማ ፣ልደታ እና በጉለሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በ(2merkato.com link :- https://addisland.2merkato.com afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ማንኛዉም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል፡፡
3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች ሞልተዉ የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘዉን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወረክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር ቢሮው አይጠየቅም፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣
7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
7.2 የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፒ (ደረሰኝ)
7.5 ኦርጅናል የአቅም ማሳያ ማስረጃ
7.6 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ
7.7 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ ጽ/ቤት/ የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት፡፡
7.8 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
7.9 ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
7.10 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች
ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ
ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7.11 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የቸረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፖስታው ላይ በመጻፍ ሐምሌ 12/2016ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ስዓት ድረስ ብቻ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ በ05/11/16ዓ.ም፣08/11/16 ዓ.ም እና በ10/11/16 ዓ.ም ጠዋት በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል፡፡
9. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት ከ15 የስራ ቀናት በኀላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ መ/ቤት ለባንክ በመላክ ወዳሰሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ በካሽ ያሰሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም፡፡
10. መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-
በስልክ ቁጥር +251111570595 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
https://www.aalb.gov.et/
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

👍15❤8
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ ፤በአቃቂ ቃሊቲ፤በአዲስ ከተማ፣ልደታ እና በጉለሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በ(2merkato.com link:- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ፤ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 7 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ በስልክ ቁጥር +251111570595 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በድህረ ገፅ https//www.aalb.gov.et/መመልከት ይችላሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

👍15❤5