kuraztech
3K subscribers
350 photos
25 videos
12 files
310 links
Website - www.kuraztech.com

📌📌📌 Support & Discussion Group:
@kuraztechnologies
Download Telegram
ሀገራችን ነገ የመጀመሪያውን ሳተላይት ታመጥቃለች
ዛሬ ለብዙዎች የራስ ምታት መፍትሄ የሆነ ዌብሳይት እናስተዋውቅዎ
We Transfer ይሰኛል።
ይህ ዌብ ሳይት ትልልቅ ፋይሎችን በጣም በቀላል መንገድ ለመላክ በ 2009 የተቋቋመ ነው።
@kuraztech
ከእርስዎ የሚጠበቀው
1. Follow this link
2. ፋይሎቹን የሚልኩለትን ሰው ኢሜይል ያስገቡ
3. የእርስዎን ኢሜይል አድራሻ ያስገቡ
4. ፋይሎቹን (ወይም ፋይሎችን የያዘዉን ፎልደር) ይምረጡ
5. በመቀጠል Transfer የሚለውን በተን ይጫ'ኑ።
@kuraztech
@kuraztech
አበቃ። ባንድ ጊዜ እስከ 2GB ፋይል ዥውውውውው✈️✈️ ነው።
@kuraztech
Enjoy
Happy morning,

Excellent way to start the day.

5 Steps to do in morning :

Close ur eyes,
Take a deep breath,
Open ur arms wide,

Feel ur heart beat & say,Here I AM OH LORD, Embrace ME & be my STRENGTH TODAY!!!

Wishing you most & more.
@kuraztech
@kuraztech
💻Entrepreneurship 🔌 -🖐🏿🖐🏿Hello Dear Kuarztech @kuraztech @kuraztech families today we will suggest you youtube channel that will help you to enhance your Entrepreneurial skills and to Establish your own startups like www.kuraztech.com . Please click here ... 👉🏿👉🏿👉🏿👉🏿👉🏿 https://www.youtube.com/channel/UCydShVfAub9TSmL1N4BTlGQ
ከሚቀጥለው የፈረንጆቹ ጃንዋሪ 14/2020 በኋላ ማይክሮሶፍት ለዊንዶው-7 ምርቶች የሚያደርገውን የደህንነት ድጋፎች በይፋ እንደሚያቋርጥ መግለጹ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ተጠቃሚዎች የዊንዶው 7 ምርትን በቀጣይነት እጠቀማለሁ ብለው ካሰቡ የተራዘመ የደህንነት ማዘመኛዎችን /Extended Security Updates/ መግዛት ይገባቸዋል
፨፨#Nividia እና ከ #AMD Graphics የትኛው ይሻላል?፨፨

#AMD( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል።
በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ #Radeon Brand የሚወጣ ነው። #Nividia ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም #ግራፊክስካርዶችን ማምረት ነው። በ #Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ #AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።
25 እጅግ አደገኛ እና ተገማች የይለፍ-ቃሎች/ passwords/ ዝርዝር ይፋ ሆነ
www.welivesecurity.com ድረ-ገጽ ይፋ የተደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በግዴለሽነት የተለያዩ ተግባራትን ሲከውኑ ይስተዋላል ብሏል፡፡ ሰዎች በቸልተኝነት ከሚከወኗቸው ተግባራት መካከል አንደኛው የአካውንታቸውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚጠቀሙት የይለፍ-ቃል አንዱ ነው፡፡
በፈረንጆቹ 2019 በተለያዩ ወቅት በተመዘበሩ 500 ሚሊዮን የይለፍ-ቃሎች ላይ በተደረገ አጠቃላይ ትንተና ‘12345’ እጅግ ተደጋግሞ እንደ ይለፍ-ቃል ከዋሉ የይለፍ-ቃሎች ቀዳሚው ሲሆን ‘123456’ እና ‘123456789’ ተከታዩን ስፍራ መያዛቸውን ኖርድ ፓስ/Nord Pass/ ጠቁሟል፡፡ 6.3 ሚሊዮን አካውንቶች ከላይ የተቀመጡትን የቁጥር ቅደም ተከተሎች እንደ ይለፍ-ቃል እንደሚጠቀሙ መረጃው አመልክቷል፡፡እጅግ ብዛት ባላቸው አካውንቶች እንደ ይለፍ-ቃል የሚውሉ 25 ቀዳሚ የይለፍ-ቃሎች፡-
1 12345
2 123456
3 123456789
4 test1
5 password
6 12345678
7 zinch
8 g_czechout
9 asdf
10 qwerty
11 1234567890
12 1234567
13 Aa123456.
14 iloveyou
15 1234
16 abc123
17 111111
18 123123
19 dubsmash
20 test
21 princess
22 qwertyuiop
23 sunshine
24 BvtTest123
25 11111
ከላይ ከተቀመጡት የአካውንት መግቢያ የይለፍ-ቃሎች መካከል የእርሶም የይለፍ-ቃል ካለ አሁኑኑ መቀየር እና ጠንካራ እና በቀላሉ ተገማች ያልሆነ ይለፍ-ቃል በመጠቀም ሊደርስቦት የሚችለውን የመረጃ ምዝበራ መከላከል ይችላሉ፡፡
ምንጭ፡-welivesecurity
በኦንላይን ከሚደረጉ ግብይቶች መካከል11 በመቶው የተጭበረበሩ ናቸው፡ጥናት
፨፨@kuraztech፨፨
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች መካከል ፌስቡክ እና ኢንስታግራም የመሳሰሉ አማራጮች የሃሰት መረጃዎች መከማቻ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ከፈረንጆቹ ሚያዚያ 1 እስከ ሰኔ 30 2019 በተደረገ 1.2 ቢሊዮን የቀጥታ የኢንተርኔት ግይት ውስጥ 11 በመቶ የሚሆኑት የሳይር ጥቃቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
የሃሰት መረጃዎች ባማረ መልኩ እየቀረቡ የዲጂታል አለም ተጠቃሚዎች ላይ ጫናው እያደገ መሆኑን ጥናት ጠቁሟል፡፡
፨፨@kuraztech፨፨
ፍራውድ ሜዲየተር አርኮስ ላብ ይፋ ያደረገው መረጃበመቶ እንደጠቆመው ከሆነ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ይዘቶች ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በመልቀቅ መጥፎ ስሜት እንዲሰማን እየተደረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከዚህ ባሻገር ከማጭበርበር ጋር የተያያዙ ሪፖርቶች ውስጥ 53 የሚሆነው የማህበራዊ ሚዲያ ሎግኢኖች (logins) የተጭበረበሩ መሆናቸውን ተቋሙ ይፋ አድርጓል፡፡
ከእነዚህ የሳይበር ጥቃቶች መካከልም ህገወጥ የአካውንት ምዝገባዎችን እና ሎግኢን እና ክፍያዎች (logins and payments) እንደሚገኙበት ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡
፨፨@kuraztech፨፨
የሳይበር ጥቃቶች መነሻው ካደጉት እና በማደግ ላይ ካሉ የአለም ክፍሎች እንደሚነሱ ተጠቁሟል፡፡
ሆኖም አብዛኛው በማጭበርበር የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች መነሻቸውን ከአሜሪካ፣ሩሲያ፣ፊሊፒንስ፣እንግሊዝ እና ኢንዶኖዥ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በዚህ ሪፖርት በአስደንጋጭ ሁኔታ የተስተዋለው ደግሞ ለጉዞ ክፍያ የሚደረጉ ግብይቶች መካከል 46 በመቶው የተጭበረበረ መሆኑን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡
፨፨@kuraztech፨፨
ከአጠቃላዩ በተሳሳተ መልኩ አካውንትን ከፍቶ የመግባት ሙከራዎች ውስጥ 10 በመቶ የሚሆነው በጉዞ ሳይቶች ላይ የሚፈጸም መሆኑ ተነግሯል፡፡
በስማርት ስልክ 'አፕሊኬሽኖች' አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉ የመረጃ ጥቃት ተጋላጭነቶች
@kuraztech
@kuraztech
ስልክዎ ላይ የተጫኑ መተግበሪያዎች በየወቅቱ ካላዘመኑ (update) እና የደህንነት ክፍተቶችን መሙላት ካልቻሉ ከታች ለተዘረዘሩት የመረጃ ጥቃት በቀላሉ ይጋለጣሉ፡፡
@kuraztech
@kuraztech
• የስልክ፣ የኢ-ሜይልና የመሳሰሉት አድራሻዎች
• አጭር የፅሑፍ መልእክቶች/SMS
• የጥሪ መዝገብ ማስታወሻዎች/call logs
• የአሳሽ (browser) ታሪኮች ፣ ቡክማርኮች ፣ የቀን መቁጠሪያየሚያሳይ ክስተቶች መረጃ
• ስልካችን የሚገኝበት አካባቢ መረጃ
• መተግበሪያውን እንዴት እንደምንጠቀምበት መረጃ
• የስልካችን ልዩ መለያ ቁጥሮች
• ለተለያየ አላማ የምንጠቀምባቸው የይለፍ-ቃላት (ፓስወርድ) ለምሳሌ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የይለፍ-ቃሎች
👍1
Graphics/Display/Video Card
ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/

@kuraztech
@kuraztech
አሁን አሁን የምንሸምታቸውን ላፕቶፖች Graphics card አለው ወይስ የለውም ብሎ ማጣራት የተለመደ ሆኗል። በነገራችን ላይ መጠኑ እና ጠቀሜታው ይለያይ እንጂ ኮምፒውተር የተባለ ነገር ሁሉ በኛ አጠራር ግራፊክስ ካርድ አለው።RepTech
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የ ማትስ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።
@kuraztech
@kuraztech
♦️ በተለይም አዳዲስ ጌሞች እና ለ Rendering የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች ለመጠቀም( Photo Shop , Revit...) በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተለይ ለ Architecture ተማሪዎች ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። በአሁን ጊዜ በስፋት የሚታወቁት Nividia እና AMD ናቸው።

♦️ ሁለት አይነት ካርዶች ሲኖሩ የመጀመርያዎቹ ከ mother board ጋር ተጣብቆ / integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ intel በስፋት ይታወቅበታል። ሁለተኛው ደግሞ ለብቻ የሚሸጡ dedicated ናቸው።
እኛ ሀገር በስፋት ከ ላፕቶፖች ጋር integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ መጨመርም ሆነ መቀየር የማንችላቸው ናቸው።

፨፨ከ Nividia እና ከ AMD የትኛው ይሻላል?፨፨

AMD( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል። በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ Radeon Brand የሚወጣ ነው። Nividia ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም ግራፊክስ ካርዶችን ማምረት ነው። በ Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።

@kuraztech
@kuraztech

፨፨ ኮምፒዩተራችን Graphics card
እንዳለው እና እንደሌለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?፨፨
♦️ የ window 10 ተጠቃሚ ከሆናቹ Task Manager ላይ ገብታቹ performance ላይ side bar ላይ ያለውን GPU በመጫን ማየት የምትችሉ ሲሆን
♦️ የ window 7 ተጠቃሚዎች ደግሞ Run ( window key + R ) ላይ dxdiag ብላቹ ከጻፋቹ በኻላ በሚመጣላቹ window ላይ display በመጫን ማግኘት ትችላላቹ!
♦️ ብዙ ጊዜ ካልተላጠ ደግሞ keyboard አከባቢ ተለጥፎ ይገኛል።
!!ማሳሰብያ!!
♦️ Driver ያልተጫነበት ኮምፒዩተር በጣም ቀርፋፋ እና graphics ካርዱን ማግኘት አይችልም!
♦️ አንዳንድ ላፕቶፖች ደግሞ ለመሰረታዊ አግልግሎት የሚሆኑ intel graphics እና ከዛ ለበለጡ አገልግሎቶች የሚሆኑ AMD አልያም Nividia geforce graphics ካርዶችን አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል።
@kuraztech
"ሳይበር" ምንድን ነው

ሳይበር የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡
@kuraztech
@kuraztech
የሳይበር ምህዳር የምንለው የተለያዩ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶች ማለትም ኮምፒውተሮች ፣ራውተሮች፣የኮምፒውተር ኔትዎርኮች፣ወ.ዘ.ተ. ተሳስረው የፈጠሩት ምናባዊ ዓለም ሲሆን በዚህ ምህዳር ውስጥ ኢንፎርሜሽን ይቀመጣል፣ይሰራጫል፣እንዲሁም ይተነተናል፡፡
@kuraztech
@kuraztech
የሳይበር ምህዳሩን አንዳንዶች በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሰው ልጅ የተቆጣጠረው አምስተኛው ግዛት በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህም ከየብስ ፣ ውሃ ፣ የአየር እንዲሁም የውጫዊው የህዋ ግዛት መካከከል በመመደብ፡፡
@kuraztech
@kuraztech
የሳይበር ምህዳር፡ የብዙዎቻችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አካል ከሆነም ውሎ አድሯል፡፡ ይህ ሲባል ለስራ ፣ለትምህርት ፣ ለመዝናኛ ከመጥቀምም አልፎ ለተለያዩ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ማሳለጫ አድርገን የምንጠቀምበት ዋነኛ መሳሪያ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አልፎ የምህዳሩ እውን መሆን የኢንፎርሜሽን ዋጋ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጨምር ምክንያት እየሆነ ይገኛል።
ይቀጥላል...
የሳይበር ምህዳር አካላት
@kuraztech
የሳይበር ምህዳር የምንለው ኮምፒውተሮች ብቻ የሚፈጥሩት ሳይሆን የተለያዩ አካላት ተሳስረው እውን ያደረጉት ምህዳር ነው፡፡ እነዚህ የሳይበር ምህዳር አካላት ከላይኛው የምህዳሩ ክፍል እስከ ታችኛው ድረስ በ4 ዋና ዋና ክፍለች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
@kuraztech
@kuraztech
የውስጠኛው የምህዳሩ ክፍል፡ የሳይበር ምህዳር እውን እንዲሆን መሰረት የጣለው አካላዊ ወይም ፊዚካል ደረጃ የምንለው ነው፡፡ ይህም የተለያዩ ማሽኖች፣ኮምፒውተሮች፣ኬብሎችና የመሳሰሉ አካላት ጥምረት ነው፡፡
ሁለተኛው የሳይበር ምህዳር ውስጥ የሚቀመጠው፣ የሚተነተነው እና የሚሰራጨው ኢንፎርሜሽን ነው፡፡
ሶስተኛው የሳይበር ምህዳር ክፍል ለኢንፎርሜሽን መፈጠር፣ መተንተንና መሰራጨት መሰረት የሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት ፕላትፎርሞች ናቸው፡፡
@kuraztech
እንዲሁም የመጨረሻው እና ውጫዊ ክፍሉ፡ የሳይበር ምህዳሩን የሚጠቀመው፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂውን የሚያንቀሳቅሰው የሰው ልጅ የሳይበር ምህዳር ውጨኛው ክፍል ነው፡፡
አስገራሚ የሀኪንግ እውነታዎች
@kuraztech
-በየ 39 ሰከንዶቹ የሀከር ጥቃት አለ።
-የሩሲያ ሀከሮች በጣም ፈጣን ናቸው።
-በየቀኑ 300,000 አዳዲስ ቫይረሶች ይፈጠራሉ።
-የሳይበር ወንጀል ከዓለም አቀፍ ሕገ-ወጥ የአደንዛዥ ዕፅ ንግድ የበለጠ ትርፋማ ነው።
-ሀከሮች በየሴኮንዱ 75 ሪከርዶችን ይሰርቃሉ፡፡
-በአሜሪካ ውስጥ የሳይበር ደለል በጀት በ 2019 14.98 ቢሊዮን ዶላር ነው ፡፡
-ኩባንያዎች ካሏቸው ፋይሎች ውስጥ 3% ብቻውን ነው መከላከል የሚችሉት።
@kuraztech
@kuraztech
ዛሬ ስለ አንድ ጠቃሚ ዌብሳይት እንንገራችሁ
ቶታል ቫይረስ ይባላል

ይህ ዌብሳይት ከ 70 በላይ የፀረ-ቫይረስ መቃኛዎችን እና የURL/Domain ስካነሮችና መመርመሪያዎች አሉት።

ማናቸውም ተጠቃሚ አሳሹን በመጠቀም ከኮምፒዩተሮቻቸው ፋይል መምረጥ እና ወደ VirusTotal መላክ ይችላል።

ፋይሎቹን ስክን አፕሎአድ ካደረግን በኋላ ምንያህል ጎጅ ይዘቶች (ቫይረሶች፣ ወርሞች፣ ማልዌሮች) እንዳሉት ያሳየናል፣ ስለዚህ በነጻነት ፋይሎችን መጠቀም እንችላለን ማለት ነው።

ይህን ዌብሳይት በተለይ ቶረንት ፋይሎችን ከማውረዳችን በፊት የፋይሎቹን URL ወይንም ሊንክ ሰጥተነው ስካን ያደርግልናል።

Website Link - https://www.virustotal.com/gui
ዛሬ ደግሞ 1 ገራሚ ስለሆነ የ Mobile App እናስተዋውቅዎ።
(በተለይ 80..፣ 60 ምናምን እያሉ አዝግ አዝግ መልእክቶች ላስተገሯችሁ ሰዎች)
SMS Organizer ይባላል።

@kuraztech
@kuraztech

ይህ መተግበሪያ በማይክሮሶፍት ጋራጅ ፕሮጀክት የተሰራ ሲሆን ከሁሉም የኤስኤምኤስ መተግበሪያዎች እጅግ የላቀ(the smartest) ነው።
የገቢ መልእክት ሳጥንዎን(Inbox Messages) በራስ-ሰር(Automatically) ያደራጃል ፣ ማስታወሻዎችን ያዘጋጃል እንዲሁም ወጪዎችዎን ይከታተላል። የትኛውንም የግል መረጃዎ ያለ ምንም የኢንተርኔት ግንኙነት ያደራጀዋል።

አፑን ዳውንሎድ አርገው ይጠቀሙበት።
@kuraztech
@kuraztech
@kuraztech
ስልኮ እየተጠቀሙበት በመሃል መስራት ያቆማል?

ለምን? መፍትሄውስ

👉 Fix: Unfortunately, settings has stopped error

ስልኮ ከተለመደዉ በላይ ይዘገያል ወይስ እንዲያ ከናካቴዉ አልሰራም ብሎ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡
እንግዲህ ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል።
ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሾዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡

👉💫 ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡
ስልኮ ላይ ብዙ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች ለምሳሌ ጌሞች ፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ (ኤዲትኢንግ) ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም
ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ(ፕሌየሮች) ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን
ሶፍሮች ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡

👉 የስልኮ ዳታ መያዣ(ስቶሬጅ) በፋይሎች መጨናነቅ በስልኮ ሜሞሪ ላይ አዳዲስ መረጃዎችን ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች፣ቪዲዮች፣ያልጫኑት ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ
ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት(ሜሞሪ) ያስቀምጡት፡፡

👉🔥 የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ
ስልኮ ያሉትን ሶፍተዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል።

🗣ይህም የስልኮን ፐሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ(background play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያደሱት፡፡

👉🌟ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት
ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ
የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading
data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ከች ማፀዳት ተቃሚ ያደርገናል፡፡

👉 💫Widgets መጠቀምን ማብዛት
አንድሮይድ ስልኮች ከሚሰጡን የተለየ ጥቅም አንዱ ዊጄትስ ቢሆንም ያን ያህልም የሚሰሩትን ካልገደብን ስልካችንን በማጨናነቅና እንዲቆም
(ስታክ) እንዲያደርግ በማድረግ ረገድም ከፍ ያለዐድርሻ ያላቸዉ በመሆናቸዉ ዊጄትስን በመቀነስ
ካልሆነም በማጥፋት ስልኮ በየጊዜዉ መቆሙን አላያም መንቀራፈፉን ማስቆም አማራጭ ነዉ፡፡

👉 ⭐️ፋብሪካዉ ሲያመርተዉ ወደነበረበት ማሰተካከያ መመለስ(reset factory setting)
የስልኮ ማርጀት አልያም ለብዙ ጊዜያት መጠቀም ስልኮን እንዲቀራፈፍ አልያም በየማሃሉ እንዲቆም ለመሆኑ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡
አንዳንድ የማስተካከያ(ሴቲንግ) ለዉጦች ወይም አቅጣጫ መጠቆምያ ጂፒስ ኦን ማድረግ (ማብራት) ለስልኮ መንቀራፈፍ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ የስልኮ በመሃል በመሃል መቆም (ስታክ) ሲያጋጥሙ ስልኩ ሲዘጋጅ ወደነበረበት መመለስ (reset factory setting) ችግሩን ሊቀርፍ ይችላል፡፡

👉 ⚡️ዎልፔፐር (Wallpaper) መጠቀም ስልኮ ለዓይን እንዲስብ አልያም በአንድ አንድ አቋራጭ ቴክኒኮች ምክንያት ስልኮ ላይ ላይቭ
ዎልፔፐር (Live Wallpaper) መጠቀም አንዱ የአንድሮይድ ስልኮች ገፀ-በረከት ቢሆንም ለስልኮ መዘግየትም ይሁን መቆም(ስታክ
ማድረግ) ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ማጥፋቱ መንቀራፈፉን አልያም ሰታክ ማድረጉን ሊያስቆም ይችላልና አይሞክሩት፡፡

👉 ስልኮ አቧራ ከሞላዉ
የሚሰሩበት ቦታ አልያም የሚዉልበት አከባቢ አቧራማ ከሆነ ስልኮን ማፅዳትና ከተፀዳም በኋላ
መልሶ በአቧራ እንዳይሞላ መከላከያ መጠቀም፡፡ ከተጠቀሱት አማራጮች ዉስጥ አንዱን ብቻ መርጦ በመተግበር ሳይሆን ሁሉንም አልያም አብዛዛኛዉን መፍቴዎች በአንድ ላይ በመተግበር
ዉጤት ስለሚያስገኝ ከመፍቴዎች ዉስጥ በመምረጥ ሳይሆን ከቻሉ ሁሉንም መፍትሄዎች ስልኮ ላይ መተግበር ካልሆነም የተቻሉትን
መከወን እንደመፍተሄ ይሆናል፡፡
Forwarded from Biruk Mamo
የዊንዶው-7 አልያም ዊንዶው ሰርቨር ( Windows 7 or Windows Server 2008/R2 ) ተጠቃሚ ከሆኑ አሁኑኑ የዊንዶው ምርትዎን ወደ ዊንዶው-10 ማሸጋገር የሚገባዎት ወሳኝ ጊዜ ላይ ይገኛሉ፡፡
ማይክሮሶፍት ለእነዚህ ምርቶች እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 14 ቀን 2020 ጀምሮ ከድጋፍ ማእከሉ ነፃ የደህንነት ማዘመኛዎችን ፣ ክፍተት መሙያዎችን ወይም ቴክኒካዊ ድጋፍዎችን እንደማያቀርብ መግለጹ ይታወቃል፡፡
ከጃንዋሪ 14 በኋላ በዊንዶውስ-7 ማንኛውንም ተግባር መከወን ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን ከመፍጠር ባሻገር በኮምፒውተር ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ አደጋ ያስከትላል፡፡
@kuraztech
#share #share