ለጤናዎ 𝔣𝔬𝔯 𝔶𝔬𝔲𝔯 𝔥𝔢𝔞𝔩𝔱𝔥
504 subscribers
6 photos
7 links
Download Telegram
የአሳ ዘይት ጥቅሞች ለሕጻናት


የአሳ ዘይት በቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ዲ እና ኦሜጋ-3 በተባሉ ማዕድናት የበለጸገ  ነው።

የአሳ ዘይት ለሕጻናት ጤንንት በሳይንስ የተረጋገጡ በርካታ ጥቅሞች ይሰጣል።

1👉🏾 በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል
የአሳ ዘይት፣ ልጆች ከጉንፋን አንሥቶ ልዩ ልዩ ተላላፊ በሽታዎችን የመቋቋም አቅማቸውን  ይጨምራል። የአሳ ዘይትን ለሕጻናት ማጠጣት፣ ሐኪም ቤት መመላለስን እንደሚቀንስ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

2👉🏾 ጤናማ ዕይታ እንዲኖር ይረዳል
የአሳ ዘይት በቫይታሚን ኤ እና ዲ የበለጸገ ነው። እነዚህ ሁለቱም ማዕድናት በጊዜ ሂደት ዓይናችን አጥርቶ ማየቱን እንዲቀጥል ወሳኝ ናቸው። በተለይ ቫይታሚን ኤ ለጤናማ እይታ እጅግ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም የአሳ ዘይት በውስጡ ኦሜጋ-3 የተሰኘ ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን፣ ወደ ዓይን የሚደርስ የደም መጠን የተስተካከል እንዲሆን  በማድረግ የልጆች ዕይታ ለረጅም ዘመን ጤናማ እንዲሆን ያግዛል።

3👉🏾 ለአንጎል እድገት ይጠቅማል፤ መደበትን ይቀንሳል
በአሳ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ኦሜጋ-3 የተሰኘ ንጥረ ነገር በድባቴ (ዲፕሬሽን/depression) የሚጠቁ ሰዎች እንዲሻላቸው የሚረዳ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። እነዚህ ጥናቶች አዋቂዎችን የተመለከቱ ቢሆንም፣ ኦሜጋ-3 በአጠቃላይ የተስተካከለ የስሜት ይዞታ ይዞ ለማደግ፣ እንዲሁም ለአንጎል እድገት እንደሚጠቅም ያሳያሉ።

4👉🏾 የእግር ቀጥ አለማለትን (ሪኬትስ) ይከላከላል
“ሪኬትስ” የሚባለው እግር እንደ ቅንፍ () ሆኖ የሚያድግበት ሁኔታ (እንዲሁም የእጅ አንጓ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ እና የደረት አጥንት ከተገቢው በላይ ወደፊት መውጣት) ከቫይታሚን ዲ እጥረት የሚመጣ ነው። የቫይታሚን ዲ ሁነኛ ምንጭ የጧት ፀሐይ ማሞቅ ነው። ሆኖም በተለይ በቂ ፀሐይ ማሞቅ በማይቻልበት የአየር ሁኔታ፣ የአሳ ዘይት በዚህ ረገድ ቁልፍ ድርሻ አለው።  

5👉🏾 የስኳር ሕመም (ዓይነት I) የመከሰት ዕድልን ይቀንሳል
ከስኳር ሕመሞች ዓይነት I የሚባለው በአብዛኛው ልጆችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ በርግጠኝነት መነሻው ይህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። ይሁን እንጂ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ አንድ ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ የአሳ ዘይት ያገኙ ልጆች በዚህ ሕምም የመያዝ ዕድላቸው ቀንሶ ተገኝቷል።


➢መልካም ጤንነት
🔥3🙏1
9 የከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ምልክቶች

✍️አብዛኛዎቹ የደም ግፊት ህመም ያለባቸዉ ሰዎች ህመሙ እንዳለባቸዉ ሳያውቁ አብረዉት ይኖራሉ። ለዚህም ደግሞ እንደምክንያትነት የሚጠቀሰዉ በርካታ ሰዎች የደም ግፊት አደገኛነት ቢረዱም ምልክቱን እደማያውቁ በዘርፉ የተካሄዱ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ነገር ግን ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ስለሆነ መፍትሄ ፍለጋ የሚጀምሩት ህክምናዉንም ከባድ ያደርገዋል።

✍️የደም ግፊት ህመም መከላከል የምንችለዉ እና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ በማድረግ በሰዉነት ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት መከላከል የምንችለዉ ሲሆን ምልክቶቹን በመረዳት ወይም በየወቅቱ የጤና ምርመራ በማድረግ እና በመለየት ህመሙ የሚያደርሰዉን ጉዳት መቀነስ እና ጤናማ ህይወት መምራት ይቻላል

✍️ነገር ግን ይህን ባለማድረግ ወይም ህመሙ ለረጅም ጊዜ ሳይታወቅ የህመሙ ደረጃ ከፍ በሚልበት ጊዜ በሰዉነታችን ላይ ከሚያሳድረዉ ተጽእኖ የተነሳ የተለያዩ ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ። ከሰር የተጠቀሱ ምልክቶች ከከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች መካከል ስለሚገኙ ምልክቶቹን ካስተዋሉ ከፍተኛ የደም ግፊት ሊሆን ስለሚችል ውለው ሳያድሩ ሃኪም ያማክሩ!

✍️በማንኛውም ዕድሜ ወሰን ሊከሰት የሚችለውን የደም ግፊት በሽታ ምልክቶች በአግባቡ መረዳት ጠቃሚ መሆኑ 9 ዋና ዋና የከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች ከነመንስኤያቸዉ በሚከተለው መልኩ ቀርበዋል፡፡

1.የደም ዝውውር መዛባትን ተከትሎ የሚከሰት የመገጣጠሚያዎች ህመም እንዲሁም የእግር ወይም የእጅ መደንዘዝ፡- ከፍተኛ ከሆነ የደም ግፊት ጋር ለረጅም ጊዜ ከመቆየት የተነሳ ደም የሚያደርሱ የደም ስሮች መጠንከር ስለሚከሰት ወደ እጃችን ወይም እግራችን ላይ የሚደርሰዉ የደም መጠን በቂ ባለመሆኑ ይሄ ምልክት ሊከሰት ይችላል።

2.ተደጋጋሚ ከባድ የራስ ምታት፡- ከአናታችን በኋላ በኩል የሚሰማ ተደጋጋሚ የራስ ምታት የከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች መሃላ አንዱ ነዉ።

3. መወዛገብ ወይም የራስ መክበድ

4. መተንፈስ መቸገር

5. ጩሀት በሌለበት የጩሀት ድምጽ መሰማት፡- የአንጎላችን የደም ስሮቸች መወጠር

6.የሰውነት አካላት መደንዘዝ

7.ተደጋጋሚ የአፍንጫ መድማት

8.የዕይታ ችግር (የአይን ብዥ ማለት)

✍️ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከግፊቱ የተነሳ በ በሰዉነታችን በተለያዩ አካላት ዉስጥ የሚገኙ የደም ስሮች ስለሚወጠሩ እና የደም ስሮች ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል ጉዳቱ የደረሰበት እና ደም ከሚያነሰዉ አካል ላይ ከሚደርሰዉ ጫና የተነሳ ሊፈጠሩ ይችላል።

9. ደም የተቀላቀለበት ሽንት ፡- ረጅም ጊዜ የቆየ የደም ግፊት የኩላሊታችንን ጥቃቅን የደም ስሮች ከጥቅፅ ዉጭ በማድረግ ለዚህ ሊዳርገን ይችላል።
ከላይ የተቀመጡ ምልክቶች እንዳስተዋሉ የከፍተኛ የደም ግፊት ምልክት ሊሆኑ ስለሚችሉ ሃኪም ባፋጣኝነት ቢያማክሩ እና ተገቢዉ ምርመራ እና ህክምና ቢያደርጉ መልካም ነዉ።


➢መልካም ጤንነት

የ ቻናሉን ቤተሰብ በመሆን ሾለ ጤናዎ የበለጠ  ይወቁ 🙏
❤5👏1🙏1
ከመጠን በላይ ማላብ / Hyperhidrosis /

ላብ ምንድነው?

ላብ ሰውነታችን ራሱን የሚያቀዘቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው፡ ፡ አብዛኛው ይህ ሁኔታ ተፈጥሯዊ እና የጤንነት ምልክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ተደጋጋሚ እና የማያቋርጥ ላብ ይታይባቸዋል እና ይህ ሁኔታ በህክምና ቋንቋ ሃይፐርሃይድሮሲስ/Hyperhidrosis/ ይባላል፡፡
ሃይፐርሃይድሮሲስ/ከባድ ላብ/ በላብ ዕጢዎች የሚመረተው ላብ ሰውነት ራሱን ለማቀዝቀዝ ከሚፈልገው በላይ ነው፡፡ ይህ በሽታ በአብዛኛው መዳፍንና የእግር ስርን እና ብብትን ያጠቃል፡፡ የዕለት ተዕለት ስራን ከማወኩም በተጨማሪ ከባድ ላብ ማህበራዊ ጭንቀት እና የመሸማቀቅ ስሜት ብሎም ራስን ማግለል ሊያስከትል ይችላል፡፡

➥ ጥሩው ነገር ግን ይህንን ችግር ለማከም የተለያዩ ዘዴዎች መኖራቸው ነው፡፡ ከባድ ላብ እጅግ ከባድ ሲሆን እስከ ቀዶ ጥገና የሚያደርስ ህክምና አለው፡፡ ምንም እንኳን መቼ፣ የት እና ምን ያክል ያልበናል የሚለው በስፋት ቢለያይም አብዛኛው ሰው ከበድ ያለ የጉልበት ስራ ሲሰራ፣ ሞቃታማ ቦታ ሲሆን፣ ድንጋጤ ወይም ጭንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ያልበዋል፡፡ ከባድ ላብ ሃይፐርሃይድሮሲስ ያለበት ሰው የላብ ሁኔታ ግን ከላይ ከተጠቀሰው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡

➥ የከባድ ላብ ዋና ዋና ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መምጣቱ የሚታይ ከሚገባው በላይ የሆነ እና ብብትን የሚያበሰብስ ሲሆን ነው፡፡ ከሚገባው በላይ የሆነ የሚያስጨንቅ የላብ መኖር በተለይም በእግር ስር፣ በብብት፣ በራስ እና በፊት ላይ የሚታይ ሲሆን፣ የቆዳ ማጣበቅ ወይም ከእጅ መዳፍና ከእግር መርገጫ ጠብ ጠብ የሚል ላብ ሲታይ ነው፡፡

➥ ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚለው ስያሜ የሚሰጠውን የተቸጋሪውን የዕለት ተዕለት ስራን የሚያደናቅፍ ከፍተኛ የላብ መጠን/ከባድ ላብ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ክስተት ያለ ምንም በቂ ምክንያት ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ይታያል፡፡ ለእነዚህ ሰዎ ች ከባድ ላብ የማህበራዊ ህይወትን ያውክባቸዋል፡፡
እጃቸው ያለማቋረጥ ስለሚረጥብ ስራ መስራትም ሆነ መዝናኛ ቦታ ራሳቸውን ማዝናናት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከሰው ጋር ሲጨባበጡ በእጃቸው ላብ ምክንያት እና ሸሚዛቸው የላብ ቅርፅ ስለሚያሳይ አንዳንዴም ጠረን ስለሚኖረው በዚህ በሚፈጠርባቸው መሸበር ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ፡፡

➥ እንደዚህ ያለ ችግር ያለበት ሰው ከተለመደው በላይ ድንገት ከፍ ያለ ላብ ሲያይ፣ ላብ የዕለት ተዕለት ስራውን ሲያደናቅፍበት፣ እና የሌሊት ላብ ያለ በቂ ምክንያት ሲኖረው ሐኪም ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የብርድ ላብ የታየበት ማንኛውም ሰው ሐኪም ዘንድ መቅረብ አለበት፡፡
በተለይም ደግሞ ሁኔታው ከጭንቅላት ቅል መቅለል እና የደረት ወይም የሆድ ህመም ስሜት ጋር አብሮ ከመጣ የልብ በሽታ፣ የጭንቀት ወይም የሌላ ከፍተኛ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሊሰጠው አይገባም፡፡
➥ የከባድ  ላብ ምንጩ ሰውነታችን ሙቀቱን ከሚቆጣጠርበት የቁጥጥር ስርዓት ይመነጫል በተለይ ደግሞ የላብ ዕጢዎች ቆዳችን ሁለት አይነት የላብ ዕጢዎች አሉት፡፡ አንደኛው ኢክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛው ደግሞ አፓክራይን ዕጢዎች ይባላሉ፡፡

➥ ኢክራይን  ዕጢዎች በአብዛኛው ሰውነታችን ውስጥ ሲገኙ በቀጥታ አፋቸው ወደ ቆዳ ላይኛው ክፍል ይከፈታል፡፡ አፓክራይን ዕጢዎች ግን የሚገኙት በብዛት ፀጉር በሚሸፍናቸው የቆዳ ክፍሎች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ የራስ ቅል፣ ብብት እና ጭገር አካባቢ ነው፡፡

➥ የሰውነታችን ሙቀት ሲጨምር አውቶኖሚክ ነርቨስ ሲስተም የተባለው የአዕምሮ ክፍል እነዚህን ዕጢዎች ላብ ወደ ቆዳ የላይኛው ክፍል እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ ላቡም ሰውነታችንን ከቀዘቀዘ በኋላ ይተንና ቆዳችን ይደርቃል፡፡ ይህ ላብ በውስጡ በአብዛኛው ውሃ እና ጨው ይይዛል አልፎ አልፎ ደግሞ ሌሎች ኬሚካሎችም በተጨማሪ ይይዛል፡፡

➥ ከባድ ላብ በአንድ ቦታ የተወሰነ ወይም ጠቅላላ ወይም በርካታ ሰውነታችንን የሚያካትት /generalized hyperhidrosis/ በመባል ይከፋፈላል፡፡ የመዳፍና የእግር ከባድ ላብ በአብዛኛው ቀን ቀን የሚ ከሰት ነው፡፡ አንዳንዴም በብብት አካባቢም ይታያል፡፡ ይህ ላብ ሌሊት በአመዛኝ አይታይም፡፡
በሁለቱም የሰውነታችን ክፍል በእኩል መልኩ ይታያል፡፡ ይህ አይነት ከባድ ላብ ወደ ሃያው የዕድሜ ክልል አካባቢ በአብዛኛው ይጀምራል፡፡ ከሌላ በሽታ ጋር ግንኙነት የሌለውና ራሱን የቻለ ችግር ነው፡፡ ትክክለኛው ምክንያት ወይም መነሻ ገና አይታወቅም፡፡ ነገር ግን በዘር የመምጣት አዝማሚያም ይኖረዋል፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን የሚያጠቃው የከባድ ላብ ችግር አይነት በድንገት የሚጀምር ነው፡፡

➥ በርካታ የሰውነት ክፍልን ያጠቃል፡፡ በአብዛኛው ሌላ ምክንያት አለው፡፡ ለምሳሌ የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት፣ የበሽታ ምልክት፣ የማረጥ ምልክት፣ የስኳር መጠን በደም ውስጥ ዝቅ ማለት፣ የታይሮይድ በሽታ፣ የደም ካንሰር በሽታ፣ የልብ ድካም በሽታ ወይም የአንድ ወይም የሌላ ኢንፌክሽን በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አስፈላጊውን መድሃኒት በመውሰድ ወይም መንስኤውን በሽታ በማከም ላቡን ያጠፋዋል፡፡

➥ በከባድ ላብ መንስኤነት የሚመጡ በርካታ የአካልና የስነ ልቦና ች ግሮች መካከል የፈንገስ ኢንፌክሽን፣ በባክቴሪያ ምክንያት የቆዳ እና የቆዳ ፀጉር አካባቢ ኢንፌክሽን በእግር ጣቶች አካባቢ የሚመጡ ኢ ንፌክሽኖች፣ የቆዳ ኪንታሮት /wart/ በሽታ ወይም ኪንታሮት ሲታከም ቶሎ ያለመዳን ችግር፣ በቆዳ ላይ በሙቀት የሚመጡ ሽፍታዎች መብዛት፣ እና ማህበራዊ መገለል ዋናዎቹ ናቸው።
ለአንዳንድ ከባድ ላብ ላላባቸው ሰዎች መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ከፋርማሲ በሚገዛ ላብ መከላከያ ሊቆም ይችላል፡፡ እነዚህ የላብ ማቆሚያ መድሃኒቶች የላብ መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት ይህንንም በአልሙኒየም ጨው አማካኝነት ወደ ቆዳ የሚደርሰውን የላብ መጠ ን ይቀይሳል፡፡ ማስታወስ ያለብን ላብ መከላከያ ላብ ሲከላከል ዲኦድራንት ደግሞ የላብን መጥፎ ጠረን ብቻ ነው የሚከላከለው፡፡


➢መልካም ጤንነት
⚡2🔥1🙏1
የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን + የካካ መንጣት ‼️

የጨቅላ ህፃናት አይን እና ገላ ቢጫ መሆን በተለያየ ከቀላል እስከ ከባድ የጤና እክል ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል።

ነገር ግን በዋነኝነት አሳሳቢ የሚሆነው
👉 በተወለዱ 24ሰአት ውስጥ ከተከሰተ
👉 ቢጫነቱ ከ 2 ሳምንት በላይ ከቆየ
👉 ቢጫነቱ ከጭንቅላት ጀምሮ ወደታች ከእንብርት አልፎ ከሄደ
👉 የካካ ነጭ መሆን ወይም የሽንት መጥቆር ካለ
👉 ተያይዞ ማስመለስ ፣ የክብደት አለመጨመር ፣ የእንቅልፍ መዛባት እና የመሳሰሉት የህመም ምልክቶች ካሉ ነው።

ስለዚህ እነዚህን ምልክቶች ካስተዋሉ በጊዜ የልጅዎን ሀኪም ማማከር እና የደም ምርመራ  እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ የሆድ አልትራሳውንድ ምርመራ በማስመርመር መንስኤው ምን እንደሆነ መለየት እና ተገቢውን ህክምና ህፃኑ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል።

ይህን ርዕስ ያነሳውበት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ከአፈጣጠር ጋር በተያያዘ ከጉበት ወደ ትንሹ አንጀት ክፍል የሀሞት ፈሳሽን የሚያስተልፈው ቱቦ መዘጋት ወይም አለመኖር ሊከሰት ይችላል። በዋነኝነት የሚታየው ምልክት የአይን እና ገላ ቢጫ መሆን እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በምስሉ ዳይፐሩ ላይ እንደሚታየው የካካ ቀለሙ ነጣ ማለት ነው።

ይህ የጤና እክል ደግሞ በመጀመሪያ 3 ወር እድሜያቸው በጊዜ ታውቆ በቀዶ ህክምና ተፈጥሮአዊ ችግሩ ካልታከመ ጉበትን በጊዜ ሂደት በመጉዳት  ከጥቅም ውጪ ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ከተከሰተ ደግሞ በጉበት ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና ካልታከመ የህፃኑን ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ይቀጥፋል።

ስለዚህ ወላጆት በተለምዶ አባባል የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን  በፀሀይ መሞቅ ብቻ በጊዜ ሂደት በራሱ ይጠፋል ብላችሁ እንዳትዘናጉ እና ጥንቃቄ እንዳታደርጉ እንዲሁም ተያይዞ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች ካስተዋላቹ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ልጃችሁን ማስመርመር ያስፈልጋቹሀል።

ሰላምና ጤና በያላችሁበት ይሁን!
🙏3❤1
ጤናማ የማህፀን ፈሳሽ ምን አይነት ነው ?
----------------------


   አንዲት ሴት በተፈጥሮ የማህፀን ፈሳሽ እንደሚኖራት ሁሉም ሰው የሚያውቀው ጉዳይ ነው። በተለይ ይህ ፈሳሽ ከጉርምስና ጊዜ በኋላ በተለይ ደግሞ በእርግዝና ጊዜ የበለጠ ይጨምራል።

   ✍️ የማህፀን ፈሳሽ ከየት ይመነጫል?

      የማህፀን ፈሳሽ በዋናነት የሚመነጨው ከውስጠኛው የብልት ግድግዳ ( vaginal wall ) ላይ ከሚገኙ ጥቃቅን እጢዎች ሲሆን ኢስትሮጂን በተባለው ሆርሞን አማካኝነት እንዲፋፉና ፈሳሹን እንዲያመርቱ ይደረጋል።

     ✍️የማህፀን ፈሳሽ ምን ምን ጥቅሞች አሉት?

ጤናማ የማህፀን ፈሳሽ ልዩ ልዩ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ

  1) የብልት ግድግዳ ድርቀትን ይከላከላል
   2) የሞቱ እና የማያስፈልጉ ሴሎችን በማጠብ እና ወደውጭ በማውጣት ጽዳት እንዲጠበቅ ያደርጋል  
   3) አደገኛ ባክቴሪያዎችን ወደውጭ በመጥረግ እንዲሁም የአሲድነት ባህርይው ከፋ ያለ ስለሆነ ከበሽታ ይከላከላል።

     ✍️ጤነኛ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ ምን አይነት ነው?

ከላይ ከተጠቀሱት ጥቅሞቹ በዘለለ የማህፀን ፈሳሽ የበሽታ ምልክትም ሊሆን ይችላል።
   1) ሽታ ያለው ፈሳሽ ከሆነ
   2) ቀለሙ ቢጫ ፣ ግራጫ ወይም አረንጓዴያማ ከሆነ
   3) ጠጠር ያለ ወይም ነጭ ፈርፈር የሚል አይነት ከሆነ
  4) መግላማ ፈሳሽ ከተቀላቀለ

      በእነዚህ ሁኔታዎች ግዜ የባክቴርያ ፣ የፈንገስ ወይም የፕሮቶዝዋ ኢንፌክሽን ምልክት አለፍ ሲልም በተለይ እድሚያቸው በገፋ ሴቶች ላይ የማህፀን በር ወይም የማህፀን ካንሰር ምልክት የመሆን እድልም ስላለው ሴቶች እነዚህን ምልክቶች ሲያዩ ወደ ህክምና ቦታ ሄደው ምርመራ ቢያደርጉ እና በግዜ ህክምናን እንዲያገኙ ይመከራል።
   
       
⚡1❤1🔥1👏1🙏1
ለወር አበባ መዛባት ዋነ ዋና ምክንያቶች

✍️ 1) የሆርሞን መዛባት፦ የተለያዩ የሰውነት ተግባራትን የሚቆጣጠሩ እንደ ኢስትሮጅን፣ ፕሮጄስትሮን እና ቴስቶስትሮን ያሉ የሆርሞኖች ደረጃ ላይ ያለውን መዛባትን ያመለክታል። የወር አበባ መዛባት በመደበኛ የወር አበባ ዑደት ላይ ብዙ አይነት መስተጓጎሎችን ያጠቃልላል፣ የዑደት ርዝመት፣ የወር አበባ መቅረት ወይም ያልተለመደ የደም መፍሰስን ጨምሮ።

የሆርሞን መዛባት በተለያዩ መንገዶች ሊገለጽ ይችላል እና በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላል። ወደ እንደዚህ አይነት አለመመጣጠን የሚያመሩ የተለመዱ ምክንያቶች ውጥረት(stress) ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ ከልክ ያለፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ አንዳንድ መድሃኒቶች እና እንደ ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ወይም የታይሮይድ እክሎች ያሉ የጤና እክሎች ናቸው።

ኤስትሮጅን እና ፕሮጄስትሮን ማህፀንን ለእርግዝና በማዘጋጀት እና በወር አበባ ወቅት የማህፀን ሽፋን በጊዜው እንዲጠረግና በአዲስ እንዲተካ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ. በእነዚህ ሆርሞኖች ውስጥ ያለው አለመመጣጠን መደበኛ ያልሆነ ወይም የወር አበባ አለመኖርን ያስከትላል።

✍️ 2) ውጥረት (Stress)

ውጥረት፦ አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ሲሆን በሰውነት ውስጥ የሆርሞን ሚዛን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል, ይህም የወር አበባ ዑደት ውስጥ መስተጓጎል ያስከትላል። እንደ ኮርቲሶል(cortisol)  ያሉ የጭንቀት ሆርሞኖች ከፍ ያሉ ደረጃዎች የሃይፖታላመስ ፣ ፒቱታሪ እጢ  እና ኦቫሪ መደበኛ ሥራን ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ ።

የወር አበባ መዛባት ላይ የጭንቀት ተጽእኖ በተለያዩ መንገዶች ሊገለጽ ይችላል። አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ መቋረጥ ሊያጋጥማቸው ይችላል፣ ሌሎች ደግሞ ባልተለመደ ሁኔታ ከባድ ወይም ረዥም ደም መፍሰስ ይኖራቸዋል። በተጨማሪም ጭንቀት ቀደም ሲል የነበሩትን የወር አበባ ሁኔታዎች እንደ ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOS) ወይም endometriosis ሊያባብስ ይችላል።

✍️ 3) የክብደት መለዋወጥ (Weight fluctuation)
አንድ ሰው ጉልህ የሆነ የክብደት መለዋወጥ ሲያጋጥመው ሰውነቱ የሆርሞን ለውጦችን ሊያደርግ ይችላል። እነዚህ ለውጦች እንደ ኢስትሮጅን እና ፕሮጄስትሮን ያሉ የወር አበባ ዑደትን በመቆጣጠር ላይ ያሉትን ጨምሮ በሰውነት ውስጥ ባሉ የተለያዩ ሆርሞኖች መካከል ያለውን ሚዛን ሊጎዱ ይችላሉ። በእነዚህ ሆርሞኖች ውስጥ ያለው መለዋወጥ የወር አበባ መዛባት ሊያስከትል እና የወር አበባ ዑደት መደበኛውን ሂደትሊያስተጓጉል ይችላል.

የክብደት መቀነስ, በተለይም ፈጣን ወይም ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ, ሃይፖታላሚክ amenorrhea  ሊያስከትል ይችላል። ይህ ሁኔታ በቂ ያልሆነ ጉልበት እና ከልክ ያለፈ አካላዊ እንቅስቃሴ ምክንያት በሆርሞን መዛባት ምክንያት የሚከሰት ነው። በሌላ በኩል ድንገተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር ወይም ከመጠን በላይ መወፈር ኤስትሮጅን በብዛት እንዲመረት ስለሚያደርግ መደበኛውን የወር አበባ ዑደት ሊያስተጓጉል ይችላል።

✍️ 4) ከመጠን በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ከመጠን በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የወር አበባ ዑደትን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ የሆነውን hypothalamus-pituitary-ovarian axis ላይ ተጽእኖ በማድረግ የሆርሞን መዛባት ሊያስከትል ይችላል። ጠንካራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደ ኮርቲሶል ያሉ  ሆርሞኖችን በመጨመር  እንደ ኢስትሮጅን እና ፕሮጄስትሮን ያሉ የመራቢያ ሆርሞኖችን መጠን በመቀነስ የእንቁላልን መለቀቂያ ጊዜ ኡደትሊያውኩ ይችላሉ፤ ይህም መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ያስከትላል።

በተጨማሪም ከመጠን በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የካሎሪክ እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የኃይል ሚዛን ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

ምንም እንኳን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአጠቃላይ ጤና ጠቃሚ ቢሆንም ሚዛናዊ አካሄድን መጠበቅ እና ሰውነትዎን ማዳመጥ በጣም አስፈላጊ ነው።

✍️ 5) መድሃኒቶች
ብዙ መድሃኒቶች በሴቶች የወር አበባ ዑደት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። አንዳንድ እንደ ሆርሞን የወሊድ መከላከያ (የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖች፣ patches ወይም implants) የመሳሰሉ በተለምዶ የሚታዘዙ መድሃኒቶች ተፈጥሯዊ የሆርሞን ሚዛንን ሊቀይሩ ይችላሉ።

በተጨማሪም አንዳንድ የጤና ችግሮችን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውሉ አንዳንድ መድሃኒቶች የወር አበባን መደበኛነት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ. ለምሳሌ, ለ polycystic ovary syndrome (PCOS) ወይም ታይሮይድ እክሎች የታዘዙ መድሃኒቶች በሆርሞን አመራረትና እና ቁጥጥር ላይ ባላቸው ተጽእኖ ምክንያት የወር አበባ ዑደት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

በተጨማሪም እንደ ፀረ-coagulants ወይም corticosteroids ያሉ ለተለያዩ ሁኔታዎች የታዘዙ መድሃኒቶች የወር አበባ መፍሰስ ክብደት እና የቆይታ ጊዜ ላይ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በመድሃኒት  አንዳንድ ሴቶች በወር አበባ ዑደታቸው ላይ ሊታዩ የሚችሉ ለውጦች ሊያጋጥሟቸው ቢችሉም ፣ ሌሎች ግን ምንም አይነት ተጽእኖ ላይኖራቸው ይችላል. በተጨማሪም, የተወሰነው መድሃኒት, መጠን እና የአጠቃቀም ጊዜ በጥንቃቄ ሊታወቅ ይገባል።
👍2🔥1
ደም ማነስ በእርግዝና ወቅት

❶ በእርግዝና ወቅት የደም ማነስ አለ ለማለት የደም ምርመራ ውጤቱ ስንት ሲሆን ነው?

✍️ በመጀመሪያው 3 ወራት ማለትም (እስከ 14 ሳምንት) እና በመጨረሻው 3 ወራት (ከ28-42 ሳምንት) የሂሞግሎቢን መጠን ከ11 gm/dl በታች ሲሆን ደረጃውም
👉 10.0 - 10.9 gm/dl ከሆነ መጠነኛ
👉 7.0 - 9.9 gm/dl መካከለኛ
👉 <7 gm/dl ከፍተኛ (የከፋ) ደም ማነስ አለ እንላለን።

✍️ በመካከል ላለው 3 ወር (14-28 ሳምንት) ደግሞ ከ10.5 gm/dl በታች ሲሆን የደም ማነስ አለ እንላለን። ክብደቱን ስናይ
👉 9.5 - 10.4 gm/dl ከሆነ መጠነኛ
👉 7.0 - 9.4 gm/dl መካከለኛ
👉 <7 gm/dl ከፍተኛ (የከፋ) ደም ማነስ አለ እንላለን።

ይህም ልዪነት የሚታየው ከ3-6 ወር ባለው ጊዜ የፕላዝማ መጠን መጨመር እና የሂሞግሎቢን ክምችት ማነስ እንደሆነ ይታመናል።

❷ ምርመራው መቼ ይደረግ?

⌚️ ልክ ክትትል በምትጀምሪበት ወቅት እና ሌሎች ችግሮች ካልታዩ ደግሞ 28 ሳምንት ወይም 7 ወር ሊሞላ ሲል ተመራጭ ጊዜ ነው።

ደም መፍሰስ, የደም ግፊት መጨመር  አይን ቢጫ መሆን እነዲሁም ኢንፌክሽን ከታየ CBC (FBC) ሀኪምሽ እንደ አስፈላጊነቱ ሊላክ ይችላል።

❸ በእርግዝና ወቅት አይረን ለምን ይወሰዳል?

በእርግዝና ወቅት የIron ተፈላጊነት በአስር እጥፍ ይጨምራል (አጠቃላይ በእርግዝና የሚያስፈልገው መጠን ደግሞ 1200 mg) ይህም ከሆነበት ምክንያት ዋናዎቹ
👉 የእናት የቀይ ደም ሴል መጨመር
👉 የፅንስ እና የእንግዴ ልጅ መጨመር እና
👉 የወለዲ ጊዜ ደም መፍሰስ ናቸው

እለታዊ የ አይረን አቅርቦት በአማካኝ 4.4 ግራም መሆን አለበት።

የሚያስፈልግሽን የአይረን መጠን በ3 ወራት ከፋፍለን ብናየው ደግሞ በመጀመሪያው 3 ወር 0.8 ግራም በቀን በቀጣይ 3 ወር ደግሞ 4-5 ግራም በቀን ሲሆን በመጨረሻው 3 ወር ደግሞ ከ7.5-10 ግራም በቀን ይደርሳል። 

በመደበኛ አመጋገብ የሚገኘው የIron መጠን ደግሞ 15 ግራም በቀን ሲሆን ወደ ሰውነሽ ተመጦ የሚገባው 10% (1.5 ግራም) ብቻ ነው።

❹ በእርግዝና ጊዜ የሚወሰደው የIron መጠን ስንት ነው?

ሁሉም እርጉዝ ሴቶች በቀን ከ30-60 ግራም Iron መውሰድ እንዳለባቸው ጥናቶች ያመለክታሉ።

✍️ ከ60 ግራም በላይ እንዲወሰድ ከሚመከሩባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ
👉 ደም ማነስ ካለ
👉 መንታ እና ከዛ በላይ ፅንስ ካለ
👉 ከአንድ አመት በፊት እርግዝና ከነበረ
👉 Vegetarian ከሆንሽ

Iron ሲወሰድ ጠዋት በባዶ ሆድ (ከምግብ 1 ሰአት በፊት ወይም ከምግብ 2 ሰአት በኋላ) ቢሆን ተመራጭ ነው።

ሻይ ፣ ቡና ፣ ወተት ፣ እንቁላል ፣ አኩሪ አተር ፣ ለጨጓራ ህመም የሚሰጡ መዳኒቶች ደግሞ በአንጀት የሚመጠጠውን የIron መጠን ስለሚቀንሱ ከላይ የተጠቀሱትን ከተጠቀምሽ ከ2 ሰአተ በኋላ ውሰጂ።

❺ በIron የበለፀጉ ምግቦች የትኛቹ ናቸዉ ?

👉አንዱ ከእንስሳት ተዋፅኦ (ቀይ ስጋ ፣ ጉበት ፣ ኩላሊት ፣ አሳ ፣ ዶሮ) የሚገኘው Haem Iron የሚባለው ሲሆን በቀላሉ ወደ ሰውነትሽ ይዋሀዳል።

👉ሁለተኛው የIron አይነት ከእፅዋት የሚገኘው Non-haem Iron የሚባለው ከእፅዋት የሚገኘው እና በአንፃራዊነት በአንጀት ለመመጠጥ የሚያስቸግረው አይነት ነው። ድንች፣ ለውዝ ፣ባቄላ ፣ ቶፍ ፣ ቴምር ፣ ዱባ ፣ ምስር ወዘተ... ተጠቃሽ ናቸው።

❻ በIron እጥረት ምክንያት የደም ማነስ አጋጥሞ Iron በመርፌ የሚሰጥባቸው ሁኔታዎች እና መቼ የሌላ ሰው ደም ሊለገስሽ ይችላል

✍️Iron በአፍ ከሚወሰድ ይልቅ በመርፌ ከሚሰጥባቸው ሁኔታዎች ዋና ዋናዎቹ

👉 በአፍ እየወሰድሽ በቂ ወይም ደካማ ምላሽ ከታየ (የhemoglobin መጠን ከነበረበት ውጤት በሁለት ሳምንት ውስጥ ካልጨመረ ወይም ከ1gm/dl በታች ከጨመረ ወይም ከ አንድ ወር በኋላ ከ2gm/dl በታች ከጨመረ)

👉 በጨጓራ ህመም ምክንያት ለመውሰድ ከተቸገርሽ ወይም በተደጋጋሚ መዘንጋት ካለ

👉 ለመውለድ 4-6 ሳምንት ሲቀር መካከለኛ ወይም የከፋ ደም ማነስ ከተስተዋለ

👉 የጨጓራ ቀዶ ጥገና (Gastric surgery) እና Inflammatory bowel disease ካለ ሲሆን

✍️ የሌላ ሰው ደሞ የሚሰጥባቸው አጋጣሚዎች ደግም

👉 የመውለጃ ጊዜ ላይ የከፋ ደም ማነስ ከተገኘ
👉 ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ (Acute severe bleeding or risk of further bleeding)እና
👉ልብ ላይ ጫና ያሳደረ ደም ማነስ ካለ

❼ Multivitamin ከወሰድሽ እነዚህን 15 micronutrients check አርጊ

1 folic acid (400 Îźg)
2 iron (30 mg)
3 copper (2 mg)
4 iodine (150 Îźg)
5 selenium (65 Îźg),
6 vitamin A (800 Îźg)
7, vitamin B1 (thiamin, 1.4 mg),
8, vitamin B2 (riboflavin, 1.4 mg)
9, vitamin B3 (niacin, 18 mg), 10, vitamin B6 (pyridoxine, 1.9 mg)
11, vitamin B12 (cobalamin, 2.6 Îźg)
12, vitamin C (ascorbic acid, 70 mg)
13, vitamin D (200 IU)
14, vitamin E (10 mg) and
15, zinc (15 mg).

❽ ወባ ያለበት ቦታ ከሆንሽ

የወባ ስርጭት የሚታይበት ቦታ ላይ ከሆንሽ

1, ሁልጊዜ አጎበር መጠቀም 
2, የመጀመሪያው 3 ወር እንዳለቀ ደግም ሀኪምሽ የሚሰጥሽን መድሀኒት እሰከምትወልጂ መቀጠል ይመከራል።
❤3🙏2🏆1
አዲስ የወለድሺውን ልጅ ገላውን አትጠቢዉ::

ጥያቄ: አዲስ የወለድኩትን ልጅ መቼ ማጠብ ልጀምር?

✅️መልስ: ከተወለደ 24 ሰዓት ሲሞላው
  ምክንያት:- የሰውነቱን ሙቀት ለመጠበቅ ይረዳዋል::

🟢vernix caseosa (አዲስ የተወለደ ህፃን ቆዳ ላይ የሚገኝ ነጭ ለስላሳ ሽፋን) ሳይለቅ አንዲቆይ ይረዳል::

🟢አንቺም ቢሆን 24ሰዓት ሳይሞላዉ ለማስለቀቅ አትሞክሪ::

ጥያቄ : መቼ መቼ ልጄን ልጠብ?

✅️መልስ: አንድ ቀን እያለፍሽ እጠቢ
ምክንያት: ቶሎ ቶሎ ማጠብ የሚያመጣውን የቆዳ መድረቅ እና የቆዳን በሸታ የመከላከል አቅም ከመቀነስ ይከላከላል::

ጥያቄ : ልጄን እንዴት አድርጌ ልጠብ?

✅️መልስ: ልጅሽ እትብቱ አስኪወድቅ ድረስ sponge bath (በገላ ማጠቢያ ስፖንጅ/ምቹ ጨርቅ) ከወደቀ በኈላ ደሞ Tub bath(በገንዳ ዉስጥ) አድርገሽ እጠቢው::
🟢አንገቱን እና ጭንቅላቱን መደገፍ አትርሺ

ጥያቄ : ልጄን በምን ልጠበው?

✅️መልስ: በዉሃ ብቻ ማጠብ ብዙ ጊዜ በቂ ነው
🟢የልጅሽ ቆዳ ደረቅ ሚባለው አይነት ከሆነ ግን: ሸታ የሌለው እና ለልጅሽ ሚስማማውን ሳሙና (እንደቆዳው አይነት ስለሚለያይ) መርጠሽ ተጠቀሚ::
👏2🔥1
በፖሊዮ ዘመቻ ወቅት – በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች
Polio Campaign Frequently Asked Questions (FAQ)

1. የፖሊዮ በሽታ ምንድን ነው፣ ፈውስ አለው፣ ማን ከፍተኛ ተጋላጭ ነው፣ እና እንዴት ይተላለፋል?

ፖሊዮ (ፖሊዮማይላይትስ) ሽባነትን ሊያመጣ የሚችል የቫይረስ በሽታ ነው።

ለፖሊዮ መድኃኒት የለውም; ክትባት በመከተብ መከላከል ይቻላል.

ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው.

በቫይረሱ በተበከለ ውሃ፣ ምግብ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ ካለ በሽታው ይተላለፋል።

2. ዛሬ በጤና ተቋም የፖሊዮ ክትባት የወሰደ ህጻን በዛሬው ቀን በዘመቻው እንደገና ሊያገኝ ይችላል?

አዎ። ልጆች በተመሳሳይ ቀን ቀደም ብለው የፖሊዮ ክትባት ቢወስዱም የዘመቻውን የፖሊዮ ክትባት መከተብ አለባቸው። በተጨማሪ የፖሊዮ ክትባት መጠኖች አስተማማኝ እና የሚመከሩ ናቸው።

3. መደበኛ ክትባት የጨረሱ ህጻናት በዘመቻዎች ወቅትም ለምንድ ነው የሚከተቡት?

በዘመቻ ወቅት የሚሰጡ ክትባቶች በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራሉ እናም የቫይረስ ስርጭትን ለማስቆም ይረዳሉ። የመደበኛ ክትባት ብቻውን ወረርሽኙን ማስቆም አይችልም።

4. የዘመቻ የፖሊዮ ክትባት ለመውሰድ የክትባት ካርድ ያስፈልገኛል?

አያስፈልግም ማንኛውም ብቁ ልጅ የካርድ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን የፖሊዮ ክትባት መውሰድ ይችላል።

5. ህፃኑ የፖሊዮ ክትባት ጠብታዎችን ቢተፋ ወይም ቢያስታውከው ምን ማድረግ አለብን?

ወዲያውኑ ከተተፉ ወይም ካስታወኩ, ደግመው ይወስዳሉ. ከ5 ደቂቃዎች በኋላ ከሆነ, ግን አትድገሙ.

6. የታመሙ ልጆች የፖሊዮ ክትባት መከተብ ይችላሉ?

አዎ። ቀላል ሕመም ያላቸው መከተብ ይችላሉ. ነገር ግን ሆስፒታል መተኛት የሚያስፈልገው ከባድ ህመም ካለበት ብቻ ክትባቱን ዘግይተው ወይም ሊዘላቸው ይችላል.

7. አዲስ የተወለዱ (ዛሬ የተወለዱ) ሕፃናት መከተብ ይቻላሉ?

አዎ። ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሁሉም ልጆች የፖሊዮ ክትባት መከተብ ይችላሉ።

8.  የተመጣጠነ ምግብ እጥረት (malnourished) ያለባቸው ልጆች የፖሊዮ ክትባት መከተብ ይችላሉ?

አዎ። ይህ ቡድን ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆኑ የግድ መከተብ አለባቸው። ነገር ግን ከፍተኛ የምግብ እጥረት (Severe malnourished) ያለባቸው ግን መከተብ አይችሉም፡፡

9.  የፖሊዮ ክትባት ከሌሎች ክትባቶች ጋር በተመሳሳይ ቀን ሊሰጥ ይችላል?

አዎ። የፖሊዮ ክትባት ከማንኛውም መደበኛ ክትባት ጋር ሊሰጥ ይችላል።

10. የልጁ ቤተሰቦች “ልጄ አስቀድሞ የመደበኛ የፖሊዮ ክትባት ስለተቀበለ/ች ክትባቱ አይስፈልግም “ ቢሉ ምን ማድረግ አለብን?

የዘመቻ ክትባት ተጨማሪ የመከላከል አቅም እንደሚጨምር በደንብ ማስረዳት አለቦት፡፡ ካሎነ ለሱባይዘር ሪፖርት ያድርጉ፡፡

11. የፖሊዮ ክትባት ከተወሰደ በኋላ የሚታዩ የጎንዮሽ ምልክት አሉ?

ትንሽ ሙቀት ወይም ቀላል ተቅማጥ ሊታይ ይችላል፣ እነዚህ ጎጂ አይደሉም እና በራሳቸው ጊዜ ይጠፋሉ፡፡ ነገር ግን ከዚ የተለየ ክፍ ያለ ምልክት ካሳዩ ወደ ጤና ተቋም መሄድ አለቦት፡፡

12.  ልጁ ተቅማጥ ካለበት ወይም አንቲባዮቲክ እየወሰደ ከሆነስ የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል?

አዎ ። በተቅማጥ ወይም በአንቲባዮቲክስ ጊዜ የፖሊዮ ክትባት መውሰድ ምንም ተቃርኖ የለም.

13. የፖሊዮ በሽታ የሌለባቸው ቦታዎች ለምን እንከትባለን?

ስርጭትን ለመከላከል. ፖሊዮ በጣም የሚተላለፍ በሽታ ስለወነ ; ስርጭቱን ለመስበር እና እያንዳንዱን ልጅ ለመጠበቅ ዘመቻዎች ሁሉንም ክልሎች ያጠቃልላል።

14.  ለፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የወላጅ ፈቃድ እንፈልጋለን?

ቤት ለቤት በሚሄዱበት ወቅት የጽሁፍ ስምምነት የለምውም። የቃል ግንኙነት እና ማረጋገጫ በቂ ነው። ነገር ግን በትምርት ቤት እና በዴኬር(በልጆች ማቆያ) ክትባቱ የሚሰጥ ከወነ የጽሁፍ ስምምነት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

ዘመቻዎች ብሄራዊ የህዝብ ጤና አስቸኳይ እርምጃዎች ናቸው።

15.  የጤና ባለሙያዎች ለተሳሳቱ መረጃሆች ምን ምላሽ መስጠት አለባቸው?

ቀለል ያሉ መልዕክቶችን በመጠቀም ለተሳሳቱ መረጃሆች ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል ፡- “ይህ ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። በአለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናትን ከለላ አድርጓል። ፖሊዮ አደገኛ ነው፣ ነገር ግን የፖሊዮ ክትባት ይከላከለዋል ብለን ማስረዳት”።
🔥5🙏1
🍭 ስኳርን መቀነስ ጤናችን ላይ ያለው ተፅዕኖ
በዕለት ተዕለት ኑሯዋችን ላይ ትንሽም ቢሆን የምንወስደውን የስኳር መጠን መቀነስ ከፍተኛ የጤና ጥቅሞች አሉት

✅ ክብደትን ያስተካከላል - አነስተኛ ስኳር ማለት ባዶ ካሎሪዎችን እና የስብ ክምችትን መቀነስ ማለት ነው።

✅ የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል - ከመጠን በላይ ስኳር የደም ግሉኮስን ከፍ ያደርገዋል።

✅ ጤናማ ልብ እንዲኖረን - ከፍተኛ የስኳር መጠን መውሰድ መጥፎ ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን ይጨምራል።

✅ ጠንካራ ጥርሶች - ስኳር የጥርስ መቦርቦርን እና የድድ በሽታን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎችን ይመገባል።

✅ ጥርት ያለ ቆዳ - ስኳርች መቀነስ ብጉር እና የቆዳ መቆጣትን ለመቀነስ ይረዳል።

✅ ጠንካራ የበሽታ መከላከያ - ከመጠን በላይ ስኳር የሰውነትዎን የመከላከያ ስርዓት ያዳክማል።

📞 ለበለጠ መረጃ
0992927171/0913577685
❤‍🔥2👏2🙏2
የፊንጢጣ ኪንታሮት በሽታ (hemorrhoid) ምንድን ነው?

የፊንጢጣ ኪንታሮት ማለት በሰገራ መውጫ (ፊንጢጣ) አከባቢ የሚኖር የሰውነት ክፍል እብጠት መሰል አካል ነው፡፡
በተፈጥሮ የሰው ልጅ ፊንጢጣ ዙርያ ላይ በሶሰት ቦታዎች የደም ስሮችን ያካተቱ እብጠቶች ይኖሩታል፡፡
ለመቆጣጠሪያትም ያገለግላሉ፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሰው እነዚህ እብጠቶች ይኖሩታል፡፡ ስለዚህ ኪንታሮት በሽታ ሆኖ ህክምና የሚያስፈልገው የህመም ስሜቶች ወይም ምልክቶች ሲኖሩት ብቻ ነው፡፡
ኪንታሮት ውጫዊና ውስጣዊ በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ ውጫዊ ኪንታሮት የሚባለው ከፊንጢጣ ጫፍ ወደ ውስጥ 2ሳ.ሜ አከባቢ ከፍ ብሎ ከሚገኘው (dentate line) በታች የሚገኝ ሲሆን ከዚህ መስመር ወደ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት ውስጣዊ ይባላል፡፡ ውስጣዊ እና ውጫዊ ኪንታሮት በተመሳሳይ ሰዓት እብጠት ሊኖራቸው ይችላል፡፡

የኪንታሮት ምልክቶች፡
- በሰገራ መውጫ (ፊንጢጣ) አከባቢ ህመም
- በፊንጢጣ ዙሪያ የሚወጣ እብጠት
- የደም ማነስ
- ሰገራ ከወጡ በኋላ/ሲወጡ መድመት ዋነኞቹ ምልክቶች ናቸው።

መንስዔዎች፡
ለኪንታሮት በሽታ መንስዔ ተብለው የሚጠቀሱ ሚከተሉት ናቸው፡፡
- የሆድ ዕቃን ግፊት የሚጨምሩ ነገሮች፡ ለምሳሌ፡ ማማጥ ፣ በሆድ ውስጥ የሚያድጉ ዕጢዎች
- የደረቀ ሰገራ
- ለረጅም ሰዓት ሽንት ቤት መቀመጥና ማማጥ
- የንፅህና ጉድለት …… ናቸው፡፡

የኪንታሮት በሽታ ደረጃዎች፡
የኪንታሮት በሽታ አራት ደረጃዎች አሉት
1ኛ ደረጃ ኪንታሮት፡ የመድማት ምልክት ያለው ፤ ወደ ውጭ የሚወጣ እብጠት የሌለው፡፡
2ኛ ደረጃ ኪንታሮት፡ ወደ ውጭ የሚወጣ እብጠት ያለው ነገር ግን በራሱ የሚመለስ
3ኛ ደረጃ ኪንታሮት፡ ወደ ውጭ የሚወጣ እብጠት ያለውና በእጅ ግፊ የሚመለስ
4ኛ ደረጃ ኪንታሮት፡ ወደ ውጭ የወጣ እና የማይመለስ እብጠት…… ናቸው፡፡

የኪንታሮት በሽታ ህክምናዎች፡
የኪንታሮት በሽታ እንደየደረጃው የተለያዩ ህክምናዎች አሉት፡፡

1ኛ ደረጃ ኪንታሮት
- የሆድ ድርቀትን መከላከል
o ፋይበር የበዛባቸውን ምግቦች (ጎመን ፣ ቆስጣ ፣ ሰላጣ) አብዝቶ መመገብ
- ፈሳሽ አብዝቶ መውሰድ
- ሰገራ በመጣበት ሰዓት መውጣት
- ንፅህናን መጠበቅ
- ሰገራ ሲወጡ አብዝቶ አለማማጥ
- ከላይ በተጠቀሱት ዘዴዎች ካልተስተካከለ በመድኃኒቶች ይታከማል፡፡

2ኛ ደረጃ ኪንታሮት
- ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ አነስተኛ የሆኑ የቀዶ ህክምና አማራጮች (እብጠቱን ማሰር ፣ በመርፌ
በሚሰጡ መድኃኒቶች ……) ይታከማል፡፡

3ኛ ደረጃ ኪንታሮት
- በአብዛኛው በቀዶ ህክምና ይታከማል፡፡

4ኛ ደረጃ ኪንታሮት
- ድንገተኛ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው የበሽታ ደረጃ ሊሆን ይችላል፡፡


ስለነዚህና የመሳሰሉ ችግሮች ህክምናና የምክር አገልግሎት በሰንላይት ክሊኒክ ያገኛሉ፡፡
አድራሻ፡ እንጅባራ ቅዱስ ሚካኤል ህንፃ
0937044711
በማበራዊ ሚድያ አማራጮች
Facebook
Telegram_channel
Tiktok
ያግኙን፡፡
❤3👍1