ቅንጭብጭብ
7.66K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ቢላል ለምን ሞተ?
* * *

ስምንት ቀን ስንት አመት ነው? ሃዘን ያጠላበት አንድ ቀን በስንት አመት ይመነዘራል? ፍስሃ ከተቀላቀለው ግማሽ ዘላለም እና ሃዘን ከደቆሰው አንድ ሳምንት ረዥሙ የቱ ነው?
ሰቆቃ ቀንን ዘልዛላ ያደርጋል፤ ህይወት ምሬት ሲጫናት የሰኣት አጋማሽ ከአእላፍ ቀናት ይልቅ ይረዝማል።

አይሻ ከሳምንት በፊት ወጣት ነበረች። ሃዘን ሲደቁሳት በቀናት እድሜ አሮጊት መሰለች። ቀይ መልኳ ጠቆረ፥ ፊቷ በማዲያት ተወረረ፥ ሃዘን አጎሳቆላት፥ መጎሳቆሏ አጎበጣት፥ ከናፍሮቿ ተሰነጣጠቁ፥ በረዶ መሳይ ጥርሶቿ ዝገት ያገኛቸው መሰሉ።
ከስምንት ቀናት በፊት ከነ አይሻ ቤት አቅጣጫ በተሰማ ከባድ ጩኸት ሰፈሩ ተናወጠ። ተሯሩጠን ቤታቸው ስንደርስ አይሻ በድንጋጤ በድን ሆና ቆማለች። ልጇ ዲና ቀሚሷን ጨምድዳ ይዛ በሃይል ታለቅሳለች።

"ምንድነው የተፈጠረው?" ግራ ገባኝ
"ቢላል... ቢላል... ቢ ላ ል" ያቤፅ ተንተባተበ
"ቢላል ምን ሆነ?"
"ቢ... ላል...." ትንፋሽ አጠረው
"ቢላል ምን ሆነ?" ትዕግሥት አጣኹ
"ቢላል...... ራሱን አጠፋ"
"ኢናሊላሂ..."

ዲና በሃይል ጮኸች።

ዲና፥ መልከመልካሟ፥ ትንሿ አበባ፥ ፍልቅልቋ ኮከብ ከፍ ባለ ድምፅ አለቀሰች።
ይህ ከሆነ ሳምንት አለፈው።

ወዳጃችን ቢላል፥ ታታሪው ሰራተኛ፥ የአባትነት ተምሳሌቱ፥ እውነተኛው አፍቃሪ፥ ከልግስና የማይጎድለው፥ ለዲኑ የሚታመነው..... ወንድማችን ቢላል ላይመለስ አንቀላፋ፥ከራሱ ተጣላ፥ በገዛ እጁ ራሱን አጠፋ።

ከአንድ አሏህ በቀር ማንም ቢሆን በሰው ነብስ ላይ የመወሰን ስልጣን እንደሌለው ቢያውቅም ከመርህ አፈነገጠ። ከሚታመንለት እውነት ጋር ተላለፈ።

"ስራ ጠፍቷል። ቤተሰብ ለማስተዳደር እየተቸገረ ነበር" ያቤፅ ከቀብሩ ማግስት ሃዘን በሰበረው መንፈስ ሆኖ አናገረኝ።
"መተጋገዝ እንችል ነበር፥ ራሱ ላይ መፍረድ አልነበረበትም"
"የሰውን እጅ ማየት ያታክታል። እንደቢላል አይነት ኩሩ እና ታታሪ ሰው ራሱን ለጥገኝነት አሳልፎ መስጠት አይሆንለትም። እርሱ መለገስን እንጂ የሰውን እጅ ማየትን አያውቅበትም፥ ከጎዶሎው ላይ ቀንሶ ለሌሎች ቸርነትን ያደርጋል እንጂ ለጎደለው ነገር የሰው እጅ አያይም"
"ቢሆንም ..." ሃሳቤን በእንጥልጥል ተውኩት
ሳምንት አለፈ። ወጣቷ አይሻ አረጀች፥ ፅጌሬዳዋ ጠወለገች፥ ሃዘን አጎሳቆላት፥ ውበቷ ከሸፈ፥ በሳምንት እድሜ ከወጣትነት ወደ እርጅና ተሸጋገረች።

* * *
"ይኼ ቆሻሻ መንግስት ቢላልን ነጠቀን" ያቤፅ ደነፋ
"ምን አልክ?" የሰማሁትን ማመን አልሆነልኝም። ጆሮዬን በአጭበርባሪነት ጠረጠርኩት
"ቢላልን የቀማን መንግስት ነው"
አሁንም ጆሮዬን ማመን ስላልቻልኩ 'ሰልሰው እስቲ' ማለት ቃጥቶኝ ነበር። 'ያቤፅ አብዶ ይሆን' የቅፅበት ጥያቄ አቃጨለብኝ።
"ቢላል ለምን የሞተ ይመስልሃል?" ጠየቀኝ
"ኑሮ ስለከበደው" መለስኩ
"ኑሮ ለምን ከበደው?" ተኮሳተረ
"ሲሚንቶ ስለተወደደ፥ የግንባታ እቃዎች ዋጋ ስለናረ፥ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ክፉኛ ስለተጎዳ፥ የግንባታ እንቅቃሴ መቋረጥ ስለጀመረ ፥ ግንበኛው ጓደኛችን ላይ ስራ አጥነትን አመጣበት። ስራ ማጣቱ ኑሮውን አከበደው። ይኸው ነው" ሁለታችንም የምናውቀውን ነገርኩት
"ይኽ ለምን ሆነ?"

....

ነገን ፍለጋ
ተስፋአብ ተሾመ
ኤጭ! ...ይኼ እሁድ መጣ ደ'ሞ!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

"አንተ!"

"የፈጣሪ ያለኽ! ...ምን ያስጮኽሻል? ...አስደነገጥሽኝ እኮ!"

"ይኼ ምንድን ነው?"

"ምኑ እናቴ?"

"ይኼ!"

"እስኪ መነጽሬን አቀብዪኝ፤ ምንድን ነው?"

"አታሹፍ!"

"ኣ? ...ምን? ...ምኑ? ...የቱ? ...የማን ነው?"

"ከምትንተባተብ ራስኽ ንገረኝ እንጂ!"

"በ ለ ው! ...እነዚኽ ከይሲ ልጆች ከየት አግኝተው አምጥተውት ነው!? ...ትናንት ከቤት ወጥተው ነበር እንዴ?"

"ዝጋ! ...ልጆቼን ያለ ኀጢአታቸው አትስደባቸው! ...የተገኘው ትናንት ለብሰኸው የዋልኸው ጃኬት ውስጥ ነው!"

"ተረጋጊ እናቴ! ...ተረጋጊ! ...መቸም በዚኽ ትዳር የማይቀናብኝ የለም። አንዷ ምቀኛ! ...ኦ! ይቅርታ! አንዱ ምቀኛ መስክሬን ዐይቶ ኪሴ ውስጥ ከትቶብኝ ይኾናል እንጂ፣ እኔም ይኸው ካንቺ እኩል ማየቴ ነው!"

"ዝ..ም በል እኮ ነው የምልኽ!"

"እንዴ! ...እንዴ! ጥፊው ታዲያ ምንድን ነው? ...አበድሽ እንዴ?"

"ማበድ ይነሰኝ!? በዚኽ ልክስክስ አመልኽ ጨርቄን መጣል ይነሰኝ!?"

"ግዴለም እናቴ! ተረጋጊ! ...ትዳር መቼም እንደዚኽ ነው። አንዳችን እሳት ስንኾን አንዳችን ውኃ መኾን አለብን! ...ተረጋጊ! ...የሚጠጣ ውኃ ላምጣልሽ?"

"ቆይ እሺ ምን ልኹን!? ...ትዳሬን ባልኹ! ልጆቼን ባልኹ! ኑሬዬን ባልኹ! እድሜ ልክ ያንተ መጫወቻ ኾኜ ልቅር!?"

"ቀስ! ኧረ ቀስ! ...ልቅሶውን ምን አመጣው ታዲያ!? ...ልጆቹም ይተኙበት!"

"የራሳቸው ጉዳይ!"

"ቀስስስስ... ! ይኸውልሽ እናቴ! ...ነገሩን በማስተዋል ብታዪው እኮ ይኼን ያኽል የሚያበሳጭ አይደለም!"

"ተው እንጂ! ...እ!"

"ጤናዬን ለመጠበቅ! ...ያንቺን የሚስቴን፣ የልጆቼን እናት ጤና ለመጠበቅ እንደምጠቀም፣ ኦ! ይቅርታ! ማለቴ እንደገዛኹት ብታስቢው ጥሩ ነው!"

"እስከ ዛሬስ በሽታ ላይ እንዳልጣልኸኝ በምን አውቃለኹ!?"

"በስማም በዪ አንቺ! ...የሰይጣን ጆሮ ይደፈን! ...ሆ!"

"በቃኝ! በቃኝ! በቃኝ!"

"ምኑ?"

"ይኼ ኑሮ! ...ካንተ ጋር የምኖረው የተልከሰከሰ ሕይወት! ...ከዚኽ በላይ በደል የምሸከምበት ጫንቃ የለኝም!"

"ኮንዶም ባሌ ኪስ ተገኘ ብሎ ይኽን ያኽል ምሬት!? ...ኧረ ተዪ! ፈጣሪን በጦር አትውጊ!?"

"ዝ...ም በል አንተ ልክስክስ ሴሰኛ! ...ዝም በል!"

"እሺ! ...እሺ! ...በዪኝ ግዴለም! ...አጋጭኝ! ...እችለዋለኹ! ...እጅሽ ደግሞ ማቃጠሉ!"

"ቆይ ከእኔ ምን አጥተኽ ነው? ...ምን አጎደልኹብኽ!?"

"ያገኘሽው ኮንዶም እኮ ዐዲስ ነው። አገልግሎት ላይ አልዋለም!'

"ኡኡይ! ዝ...ም በል እኮ ነው የምልኽ! ...ሰይጣኔን አታምጣው!"

"የምን አታምጣው ነው? ...መጥቷል እኮ! ...መጥተዋል። አብራችኹ ናችኹ እኮ! ...ጥፊውን ብቻ አስቀሪልኝ! ...ሌላውን እችለዋለኹ።"

"ውሻ ነኽ እሺ!"

"ነኝ! ...ለዛሬ ነኝ! ...ይኹን! ብቻ አንቺ ተረጋጊ!"

እ ፎ ይ! ኼደች።

"ኧረ ቀስ በሩን! ...ያን የጸሎት መጽሐፍ የት ነው ያደረግሽው? ...በ ለ ው! ደኅና የኼደችልኝን እጠራታለኹ እንዴ! ...እውነት የት ነው ያደረግኹት!? ...ወይኔ! በእኩለ ጾም እንዲኽ ልነጀስ!? ...አይ አንተ ሰይጣን ለዛሬ ተሳኽቶልኻል። ...ቆይ ግዴለም! ...አኹን ጸሎቴ ላይ ድፍት ስል የቤቱ ሰላም ይመለሳል። ...ኤጭ! ይኼ መጽሐፍ የት ኼደ ደ'ሞ!?

© በኃይሉ ገብረእግዚአብሔር

በአብሮነት እንቆይ
@kinchebchabi
አፍሪካን በ 352 ቀናት...

አፍሪካን በ352 ቀን ሮጦ የጨረሰው 🌍

ይህ ሰው ከባድ ፈተናዎችን ሲጋፈጥ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት ከቱርኳ ኢስታንቡል እስከ እንግሊዟ ለንደን ድረስ ሮጧል፡፡ ለአንድ ሳምንት በህይወት ተቀብሯል፡፡ መኪና እየጎተተም ማራቶን ለመሮጥ ሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ የአፍሪካን ርዝመት መሮጥ የህይወቱ ከባዱ ፈተና ነበር ተብሏል፡፡

ረስ ኩክ ይባላል፡፡ እንግሊዛዊ ነው፡፡ ከ352 ቀናት በፊት በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የመጨረሻው ደቡባዊ ጫፍ ላይ ነበር የሚገኘው፡፡ ቦታዋ ደሞ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ አጉላስ ናት፡፡ ታዲያ ማድረግ አይደለም ለማሰብ የሚከብደውን ተግባር አንድ ብሎ ጀመረ፡፡ በሩጫ አፍሪካን መጨረስ፡፡ በሩጫ ከደቡብ እስከ ሰሜን ጫፍ ማቋረጥ፡፡ መንገዱ ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡

ከፍተኛ የሆነ የጤና እክል ገጥሞት ያውቃል፣ መሳርያ ተደግኖበት ተዘርፏል፣ ቪዛ ለማግኘት ተቸግሯል፣ በሰሃራ በረሃ ሙቀት ነዷል፣ የተለያዩ አስፈሪና ከባድ ተራራዎችን እንዲሁም ጥቅጥቅ ደኖችን አቋርጧል፡፡

ለዚህም እንደ አብነት ጉዞውን ከጀመረ በኋላ በ200ኛ ቀኑ ላይ በጤና ችግር ምክንያት ናይጄሪያ ውስጥ በሚገኝ ጤና ተቋም ገብቷል፡፡ ከምርመራው በኋላም በቀን የሚጓዘውን ርቀት መጠን ቀንሶ በማስታገሻዎች ጉዞውን ቀጠለ፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ኩክ መነሻውን ከደቡብ አፍሪካ ደቡባዊ ጫፍ / ኬፕ አጉላስ / እስከ ከሰሜን አፍሪካ ሰሜናዊ ጫፍ ቱኒዚያ /ራስ አንጀላ/ ድረስ ሮጠ፡፡ የማይታሰበውን አሳካ፤ ሊደረግ አይችልም ተብሎ የታመነውንም አደረገ፡፡ በዚህም 16 ሀገራትን አቋርጧል፤ 16 ሺሕ ኪሎ ሜትሮችን አካሏል፡፡ ጠቅላላ የሮጠው በማራቶን ቢቀየር ደሞ 376 ማራቶን የመሮጥ ያህል ነው ይለናል የዘጋርዲያን ዘገባ፡፡ የሆነው ሆኖ ኩክ የመጀመሪያው የአፍሪካን አህጉር ርዝመት የሮጠ ሰው ሆኗል፡፡

ኩክ በሩጫው ጊዜያት ከ756 ሺሕ ዶላር በላይ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ይህንን ገንዘብም በሚያስገርም ሁኔታ ለሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንደሚያውለው ገልጿል፡፡

ኩክ ጉዞውን በማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ ለጋዜጣው እንደገለጸው ከቤተሰብ ተለይቶ ይህንን ከባድ ጉዞ መጀመር ከባድ እንደነበር ገልጾ በዛ ላይም ህመም ይሰማው እንደነበርና ሌሎች ችግሮችም እንዳጋጠሙት ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ህልሙን ሳያሳካ መቆም እንዳልፈለገ ጠቁሟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች ሰዎች ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ማሳያ ለመሆን ጉዞውን እንደጀመረ ጠቅሶ በመጨረሻም እንዳለው ተሳክቶለት የጽናት ምሳሌ ለመሆን ችሏል፡፡

በአብሮነት እንቆይ
@kinchebchabi
ከ112 ዓመታት በፊት በዛሬው ዕለት የሰጠመችው ግዙፏ የታይታኒክ መርከብ

ታይታን (ታይታኒክ) - Unsinkable Ship ...
ቅንጭብጭብ
ከ112 ዓመታት በፊት በዛሬው ዕለት የሰጠመችው ግዙፏ የታይታኒክ መርከብ ታይታን (ታይታኒክ) - Unsinkable Ship ...
#Ethiopia | ታይታኒክ የተገነባችው ሰሜን አይርላንድ ውስጥ “White Star Line” በተባለ ካምፓኒ ነው፡፡

ታይታኒክ 269 ሜትር ርዝመት፣ 28 ሜትር ስፋት፣ 32 ሜትር ቁመት እንዲሁም ከ47 ሚሊዮን ኪ.ግራም በላይ ክብደት ነበራት፡፡

ታይታኒክ የተሰራችው በ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ እ.አ.አ በ1997 ለእይታ የበቃው የጀምስ ካሜሮን ፊልም ታይታኒክ 200 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶበታል፡፡

ታይታኒክ በቀን 600 ሺህ ኪ.ግራም ከሰል ትጠቀም ነበር፡፡

ታይታኒክ ከእንግሊዝ ሳውዝ ሀምፕተን ከተማ ወደ ኒውዮርክ ጉዞ የጀመረችው እ.አ.አ ሚያዚያ 10 ቀን 1912 ነው፡፡

መርከቧ ለ4 ቀናት የተሳካ ጉዞ ካደረገች በኃላ 30 ሜትር ቁመት ካለው የበረዶ ግግር ጋር የተላተመችው ሚያዚያ 14 ቀን 1912 ከሌሊቱ 5 ሰዓት ከ40 አካባቢ ነው፡፡ መርከቧ ሙሉ በሙሉ ለመስጠም 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ፈጅቶባታል፡፡

በአደጋው ወቅት ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች መርከቧ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በህይወት የተረፉት 706 ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

ታይታኒክ ውስጥ 20 ህይወት አድን ጀልባዎች ነበሩ፡፡ ጀልባዎቹ እያንዳንዳቸው እስከ 64 ሰው የመያዝ አቅም ቢኖራቸውም መርከቧ ውስጥ በተፈጠረው ትርምስ ጥቂት ሰዎችን ብቻ ነበር እየያዙ የወረዱት፡፡

በታይታኒክ አደጋ የሞቱት አብዛኞቹ ወንዶች ናቸው፡፡ ይህም የሆነው ወደ ማምለጫ ጀልባዎች እንዲገቡ ቅድሚያ ለሴቶች እና ለህጻናት በመሰጠቱ ነው፡፡

ከሟቾች ውስጥ 26ቱ ጫጉላ ላይ የነበሩ ጥንዶች ናቸው፡፡

የታይታኒክ የሙዚቃ ባንድ አባላት መርከቧ እስክትሰጥም ድረስ ሙዚቃ መጫወት አላቆሙም ነበር፡፡

መርከቧ ውስጥ የነበሩ አንድ ቄስ ሁለት ጊዜ ወደ ህይወት አድን ጀልባዎች እንዲገቡ ተጠይቀው እሺ ሳይሉ ቀርተዋል፡፡ ቄሱ እስኪሰጥሙ ድረስ ከሞት ጋር የተፋጠጡ ክርስቲያኖችን ኑዛዜ (ንስሐ) ሲሰሙ እና ስርየት ሲለምኑ ነበር፡፡
የታይታኒክ ዋና ካፒቴን ኤድዋርድ ስሚዝ ለመርከቧ ሰራተኞች ያስተላለፉት የመጨረሻ መልዕክት እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ወድ ሰራተኞች የሚጠበቅባችሁን ሁሉ አድርጋችሁል፡፡ ከዚህ በላይ እንድታደርጉ የምጠይቃችሁ ምንም ነገር የለም፡፡ የባህር ላይ ህግን ታውቃላችሁ፡፡ አሁን ሁሉም ሰው ለራሱ ነው፡፡ ፈጣሪ ይባርካችሁ”፡፡

ታይታኒክ ከባህር በታች በ3 ሺህ 840 ሜትር ጥልቀት ነው የሰጠመችው፡፡

ታይታኒክ ከመስጠሟ ከ14 ዓመታት በፊት በ1898 ሞርጋን ሮበርትሰን የተባለ እውቅ ደራሲ ‘ሊሰጥም የማይችለው መርከብ (unsinkable ship) ከበረዶ ግግር ጋር ተላትሞ ሰጠመ’ የሚል ጭብጥ ያለው መጽሐፍ ለንባብ አብቅቶ ነበር፡፡ ደራሲው በምናብ ለፈጠራት መርከብ የሰጣት መጠሪያም “ታይታን” የሚል ነበር፡፡

የታይታኒክ መርከብ ፍርስራሽ የተገኘው አደጋው ከደረሰ ከ73 ዓመታት በኋላ ዶ/ር ሮበርት ባላርድ በተባለ አሜሪካዊ የስነ ውቅያኖስ ተመራማሪ ነበር፡፡ ጊዜውም እ.አ.አ 1985 ዓ.ም ነበር፡፡

የታይታኒክ ፊልም መሪ ተዋናይት ኬት ዊንስሌት “ማይ ኸርት ዊል ጎ ኦን” የተሰኘውን የፊልሙን ማጀቢያ ሙዚቃ እንደምትጠላው ተናግራ ነበር፡፡ ኬት “ሙዚቃውን ስሰማው ሊያስመልሰኝ ይደርሳል“ ነበር ያለችው፡፡

ታይታኒክ ፊልም በ11 ዘርፎች ኦስካር (አካዳሚ አዋርድ) አሸንፏል፡፡ ከሽልማቶቹ ውስጥ ግን አንዱም በተውኔት ዘርፍ የተገኘ አይደለም፡፡ የፊልሙ መሪ ተዋናዮች ኬት ዊንስሌት እና ሊዮናርዶ ዲ ካፔሪዮ በምርጥ ትወና አልተሸለሙም፡፡

© ኢዮብ መንግስቱ - በአብሮነት እንቆይ
@kinchebchabi
የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ።

ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ።

አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ።

ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ።

ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ።
አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ።

ጠፋሁኝ ...ጠፋች

ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ

"ምን ሆነች?" አልኩ

"ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ።

ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ።

የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ።

"ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ።
..
ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ...
እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! !

© አድኃኖም
ይህ ልብወለድ አይደለም፤ እውነተኛ ታሪክ ነው። ወዳጄ Nebiyu Bazezew "አንተ ብትተርከው ይሻላል" ብሎ የነገረኝን ታሪክ እጅጉን ስለደነቀኝ እኔ ፃፍኩላችሁ።


በሬው ጠፋ።
የሚተዋወቁ የሰፈሩ አባወራዎች ናቸው፤ ለቅርጫ ገንዘብ አዋጡ፦ ለፋሲካ። ተወካዮቹ የቅዳሜ ስዑር ዕለት ገበያ ወጡ። ዞር ዞር ብለው ገበያውን አዩ። ዋጋ ጠየቁ። ተከራከሩ። እንደአቅማቸው በሬ ገዙ፦ በ58 ሺህ ብር። ወደ ሰፈራቸው ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሬውን ይዘው መጥተው አንድ ግቢ ውስጥ አሰሩ። አራጅ ቀጠሩ። ለሊት ሰባት ሰዓት ሊያርዱት ከአራጁ ጋር ተቀጣጥረው ተሰነባበቱ።


ለሊት ሰባት ሆነ።
ሰዎች ተሰባሰቡ፤ በሬውን ሊያርዱት ገመዱን ሲፈቱት አመለጠ። ተከተሉት። በዚያ ድቅድቅ ጨለማ የዕውር ድንብራቸውን ሮጡ። ሊደርሱበት አልቻሉም። ፈረጠጠ። ዳገት ወጡ፣ ወረዱ። ልባቸው ሊፈነዳ ደረሰ። ሩጫቸውን ገታ አድርገው ጨለማው ላይ አፈጠጡ። ከፊታቸው ጥቁር ጨለማ ብቻ ተዘርግቷል። ተስፋ ቆረጡ። በሐዘን ተውጠው ወደ ሰፈራቸው ተመለሱ።


አይነጋ የለም፤ ነጋ።
"እንግዲህ ለቅርጫ ማሕበርተኛው ምን ይባላል?" ተባባሉ። ቅርጫ የገቡት ሰዎች በሬው መገዛቱን አይተዋል፤ አንድ ግቢ ውስጥ መታሰሩንም አይተዋል፤ ለሊት በሬው ጠፋ ቢባል ማን ያምናል? ዓመት በዓሉስ እንዴት ዓመት በዓል ይሆናል?!
"ዕድል ቢቀናን ወደ ጫካ ወጥተን እንፈልግ" ተባባሉ። እናም ወፍ ሲንጫጫ ለሊት በሬው ወደፈረጠጠበት አቅጣጫ ጉዞ ጀመሩ።


በጉዞአቸው መሃል ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ታየቻቸው፤ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ኪዳነምህረት። ተሳለሙ።
"እመቤቴ አንቺ እርጂን" አሉ። ስዕለት ተሳሉ። እናም ፍለጋቸውን ቀጠሉ፦ ወደ አንቆርጫ። አንዱን ኮረብታ አልፈው፣ ወደ ሌላ ኮረብታ። "አይ በዚህ ምንም ዳና የለም" እየተባባሉ በሌላ መንገድ ፍለጋ ቀጠሉ፤ ያኛውንም መንገድ እየተው በሌላ አቅጣጫ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ፣ እግራቸው እንዳመራቸው ሲሄዱ ቆይተው ደረሱ፦ አካኮ።


እዚያ ከአንድ የገጠር ጎጆ ፊት ለፊት ጫካ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበዋል። ብዙ ናቸው፤ በሬ አርደው እዚያው የሚበላውን ሥጋ እየበሉ ነው። እየተጨዋወቱ፤ እየተጎራረሱ፣ መደብ እየመደቡ ወዘተ። የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው።

በሬ ፈላጊዎቹ ጠጋ ብለው ሰላምታ ሰጧቸው።
ከሠላምታ በኋላ፦ "ኑ! ምሰሉን፤ እዚህ ቁጭ በሉ" አሏቸው፤ ወደሚበሉት ሥጋ እየጠቆሙ ጋበዟቸው።
"አይ አንቀመጥም" አሏቸው የታረደው በሬ የእነሱ መሆኑን ለመለየት ወደ ቆዳው እያማተሩ።

"ኧረ ነውር ነው፤ በዓመት በዓል ሳትቀምሱ አትሄዱም"
"የለም፤ እንቸኩላለን"
"ብትቸኩሉስ፤ ቁጭ በሉ አፋችሁ ላይ ይቺን ጣል አድርጉ" አሏቸው ሥጋ በእጃቸው እያቀበሏቸው። በእጃቸው የዘረጉትን
ሥጋ ተቀብለው በሩቅ ሲያማትሩ አንዱ ሽማግሌ ሌላ ጥያቄ ሰነዘሩ።

"ምነው፤ ምን እግር ጣላችሁ? ምን ሆናችሁ ነው?"
ነገሯቸው፤ በሬ እንደጠፋባቸውና ፍለጋ ላይ እንደሆኑ።
ገበሬዎቹ መንደርተኞች እርስ በርስ ተያዩ።


አካኮ፤ ገበሬዎቹ በሬ የጣሉበት ጫካ ፊት ለፊት ያለው ጎጆ ውስጥ ያሉ አንድ እናት አልፈስክም ብለው አስቸግረዋል። ምክንያቱ የተሸጠው በሬ ነው።

ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ አካባቢ የጠፋው በሬ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በፊት "ቤቱ" ደርሷል። የበሬውን መድረስ ያዩት እናት አዝነዋል።

"ይኼንን በሬ የገዙት ሰዎች፤ ቤተሰቦቻቸው፣ ልጆቻቸው ሳያከፍሉ፤ እኔ አላከፍልም" ብለው እህል ሳይቀምሱ ፀሐይ ወገግ ብሏል። ገበሬዎቹ ይህንን ስለሚያውቁ ነው እርስ በርስ የተያዩት።


ገበሬዎቹ በዐይናቸው ተሳስቀው፤ እነዚህ ጥቁር እንግዶች ቁጭ እንዲሉ ወተወቷቸው። እና አረቄ በስኒ እየጋበዟቸው ጥያቄአቸውን ቀጠሉ።

"የት ነው የገዛችሁት?"
"የሸጠላችሁ ሰው መልክ ታውቁታላችሁ?"
"በስንት ገዛችሁ?"
ተጠያቂዎቹ ሁሉንም ጥያቄ በትክክል መለሱ። ይኼኔ አንዱ ወጣት "ልክ ናችሁ፤ እኔ ነኝ የሸጥኩላችሁ" አለ ራሱ ላይ የጠመጠመውን ነጠላ ቢጤ አንስቶ።

"ዐይናችንን የሆነ ነገር ጋርዶት እንጂ ሻጩ ፊት ለፊታችን ነበረ" አለኝ ይኼን ታሪክ የነገረኝ ገዢ።

ቀጠለ ወጣቱ ገበሬ፦
"...በሬው የእናታችን ነው፤ ቤቱ ገብቷል፤አዎ 58 ሺህ ብር ነው የገዛችሁኝ። አሁን ግን እጄ ላይ ያለው 55 ሺህ ነው። እንደገዛችሁኝ አንድ ሺህውን ብር ከጓደኞቼ ጋር ተገባብዘንበታል፤ 2 ሺህ ብር ደግሞ ለደላላ ከፍለናል። የቀረው 55 ሺህ ገንዘባችሁ ነው፤ ውሰዱ"

ተገረሙ።

"እኛ ግን በሬውን...."
አቋረጧቸው አንዱ አባት።
"አይ በሬውን አንሰጣችሁም፤ ይኼ በሬ ካለምክንያት ተመልሶ አልመጣም፤ ከአሁን በኋላ አይሸጥም፤ ከቤትም አይወጣም ብላለች ባለቤቴ"

"ወቸው ጉድ"
"ባይሆን"
"ባይሆን ምን?.."
"ብሩን አንወስድም ካላችሁ ሌላ በሬ እንቀይርላችሁ፤ ሁለት ሺህ ጨምራችሁ ሌላውን በሬ ውሰዱ"

በዚሁ ተስማሙ።
በሬ የጠፋባቸው ሰዎች ሌላ በሬ ይዘው እኩለ ቀን ላይ ወደ ሰፈራቸው ተመለሱ።

እውነተኛ ፋስካም ሆነላቸው።
---
Via ወሰንሰገድ ገብረኪዳን