ቅንጭብጭብ
7.63K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
http://t.me/kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ግዕዝ_ክብር_ይእቲ
#ዘዘዮሐንስ (አለቃ)

መፈወስ ነፍስ ወይነ ለምንት ኢተኃሥሢ?
ዘታፈቅሪ ነፍስየጨቤተ መያሲ ትጊሢ
ወእንዘ ታነብቢ ዘልፈ ምዕዳነ ዳዊት ነጋሢ
እም እኩይ ግብር ለምንት ኢትትጋኀሢ?
.
.
.
ጠዋት በማለዳ
ወደ ጠጅ አደይ ቤት
የምትገሰግሺ አንቺ የኔ ነፍስ ሆይ!
ከጠጅ የተሻለ
ሕይወት የተሞላ ጥበብ የተሞላ
የሚፈዉስ ወይንን ለምን አትፈልጊም እሱ አይሻልም ወይ?
አዉቃለሁ ታዉቂያለሽ
የንጉስ ዳዊትን
ቅኔዉን ምክሩን ዞትር ታነቢያለሽ
ዞትር ትደግሚያለሽ።
ነገር ግን በተግባር
ወይንን ተጸይፈሽ እዛው ጠጅ ቤት ነሽ
ከማለዳ አንስቶ ጀንበር እስክትሸሽ።
ታዲያ!
ከቶ ምን ዋጋ አለው ቢያዉቁ ቢራቀቁ
ከመፅሐፍ ዉቂያኖስ ጫፍ ድረስ ቢጠልቁ
በሕይወት ካልታየ
የዕዉቀት ወሰኑ የዳዊት ድጋሙ
ጸሎትና ዕዉቀትሽ
ያለ'ካል የሚታይ ረጅም ጥላን ነው ሚሆነው ትርጉሙ
እባክሽ ነፍሴ ሆይ?

✍️ዉርስ ትርጉም
#በኤፍሬም_ሥዩም_ተሰማ

📚ምንጭ #ተዋነይ_ብሉይ_የግዕዝ_ቅኔያት_ፍልስፍና_ከቀደምት_የኢትዮጵያ_ነገሥታት_እና_ሊቃዉንት

join join join join
👇👇👇👇👇
@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset
👆👆👆👆👆
📚📚📚📚📚📚📚📚
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
"..አመታት ከሚመስሉ ወር ከማይሞሉ ቀናት በኋላ አየኋት፣ ቀረብኳት፣ የምትተነፍሰዉን አየር እኩል ተነፈስኩኝ፣ ደግሞ እጆቿን ያዝኩ በስስት ተሳለምኩ አክየም አቀፍኳት ትንፋሽ እስከሚያጥራት ከንፈሯን ጎረስኩኝ አንገቷ ስር ገባሁ ጠረኗ አወደኝ! ሰከርኩ! ሰከርኩ! ሰከረኩ! ይባስ ናፈቀችኝ!..ከጎኔ እንዳትርቅ ካይኔ ሰር እንድትኖር ቃልኪዳን አሰብኩኝ..አስቤ አልቀርም..!!

✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join join join join
👇👇👇👇👇
@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset
👆👆👆👆👆
📚📚📚📚📚📚📚📚
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
.
ካሜራ ማን ነኝ..!
ሁሌ ባጋጣሚ በመንገድ ላይ ሳያት
እድልም ብሎልኝ በድንገት ሳገኛት
ስትስቅ ነው ማስተዉላት
ስትስቅ ነው እምቀርፃት
በካሜራየ አይን በአልበም እማሰፍራት
ሰርክ አዲስ ፈገግታዋን በፎቶ ምይዛት
በአካል ግን በቅርበት
አልነካት አላቅፋት..
ዛሬም ከርቀት በጎዳናው ሽር ስትል
ካሜራየን አነጣጥሬ ልክ ልስላት ስል
አይኔን አላመንኩም ፈገግታዋ የለም
መልኳ ደማምኗል ዝም ብላለች ዝም..?!?
.
.
✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join join join join
👇👇👇👇👇
@YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset
🤫🤫🤫🤫🤫🤫🤫🤫🤫
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ


#ሰው_ከመሆን_ሰውሩኝ! ፬
.
.
"..ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት ሲባል ሰምቻለሁ፤ ሰው ሆኘ ለሰው ካላዘንኩ ሰው ሆኘ ሰው ሲሞት ከእነገሌ ስለሆን የማይገደኝ ከሆነ ሰው ከመሆን ሰውሩኝ፤ ከሰው ተራ አውጡኝ።"

✍️Unknown
(ከነፃ ሃሳብ ጋዜጣ ላይ የተወሰደ)

join join join join
💔💔💔💔💔💔
@YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset
ይህን ለምታዩ ኹሉ ሰላም ይሁን #ሰላም!
#ኢትዮጵያ @Bcrazykid
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
"በልቤም ሆነ በአዕምሮዬ አላፈቅርሽም። እንዲያው ምንአልባት ልብም መምታቱን ስለሚያቆም አዕምሮም ስለሚረሳ። በነብሴ አፈቅርሻለሁ። ነብስ በፍፁም አትቆምም ወይም አትረሳምና።"

✍️Rumi

join and share
@YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#አበባ_አየሁ

©ሲራክ ወንድሙ

እሩቅ ለሩቅ ሆነን
ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር
ፀደይ እየዳኸ
ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር

አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ
እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ

ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ
የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ
በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ።

የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ?
እግሬን ላወላዳ ፥
ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት
ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ
ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ

የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ
የሀምሌ ጨለማ
ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ
እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ
ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ
በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ
....
©ሲራክ @siraaq
https://t.me/kinchebchabi
ይመስላል ፍለጋ

@siraaq
.

ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላት፣
ያቺ ፡ የአደራ ፡ ፍሜ ፥ በመንገድ ፡ አግኝታ ፡ ቦታ ፡ ብትጠይቃት ፣
አላውቃትም ፡ ብላ ፥ ዘማ ፡ አሳለፈቻት።
ፍም ፡ አላት ፡ ይሉኛል ፥ አይሞቃትም ፡ ዳሴን፣
ነብስ ፡ አለህ ፡ ይሉኛል ፥ አልሞላም ፡ በድኔን።
ፈልጌ ፡ አስሼ ፡ አገኛት ፡ እንደሆን ፥ ውብ ፡ ቀኔን ፡ ብሰዋ፣
አልተገናኘችም ፡ ከጥንት ፡ እስከዛሬ ፥ ነብሴ ፡ ከስጋዋ።
....****......*****.....
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
''''''''''''''''' ' " ''''''''''''''''''''''''''
©ሲራክ ወንድሙ
https://t.me/kinchebchabi
ንጥል ፥ ተጓዥ አዳም
.
©ሲራክ ወንድሙ
.
ነብሴ የግጥም ድርድር
ልቤ የ' ዋ ባህር
ስሜ አፈር ገፊ - ኮስታራ ፏፏቴ
አደዬን አክስሜም - አልደርስም ከቤቴ
°°°°°°°°°
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
-------------
https://t.me/kinchebchabi
የታላቁ ሩጫ ቲሸርቶች አሉን

1 ፍሬ 1500
2 እና ከዛ በላይ1300

0945965456 ይደውሉ
Forwarded from Ibex Events & Hiking
ወደ ቡልጋ - የለኝ ገደል የምናደርገው ጉዞ 4 ቀናት ብቻ ቀሩት

እሁድ - ሕዳር 18

ክፍያው ምንን ያጠቃልላል?
የቁርስ፣ ምሳ፣ የታሸገ ውኃ፣ የመግቢያ ክፍያዎች፣ የአስጎብኚ፣ የፎቶግራፍ የሻይ ቡና መጠጥ... ክፍያዎችን በሙሉ

በዚህ ጉዞ ለመሳተፍ እርግጠኛ ሲሆኑ በ telegram @ibexet , @yoti27 "አለሁ" ይበሉ ወይም 0945965456 / 0928412796 ይደውሉልን።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን በውስጥ መስመር የምንልክ ይሆናል

በ Telegram t.me/ibexevents
በ facebook m./facebook.com/ibexevent ይቀላቀሉን።

መልካም ቀን!

ሰላም ለኢትዮጽያ! 💚💛
#Ethiopia #LandOfOrigins #hikinglovers #VisitAmhara #Bulga #Travel
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ከማስታዎሻየ_ማህደር!!
.
.
#ሌላ_ዓለም!!
(ክፍል አንድ)
.
.
.. ትናንት ህዳር 8/2015 ዓ.ም "አርባተንሳ" ክብረ በዓልን ልታደም ወደ ገጠራማው መንደር ካ'ንድ ወዳጄ በቀረበልኝ ጥሪ መሰረት ወርጀ ነበር። ወዳጀ ካለኝ ቦታ ደርሸ ካገኘሁት በኋላ ያው እንደተለመደው 'ቅርብ ነው ደርሰናል!' እያለ ሰፈር ለሰፈር ትንሽ ተጉዘን ከቤታቸው ደረስን የቤቱ ግቢ በላም በጥጃዎችና በእርሻ የተከበበ ነው። ግቢው በር ላይ የተቀመጡ ሰዎችን ሰላምታ ሰተን ወደ ቤቱ ዘለቅን.. የቤቱ አባወራ ከሳሎኑ ጥግ ይዘው ተቀምጠዋል..ቅድሚያ እርሳቸዉን ሰላምታ ሰተን በቤቱ ያሉ እንግዶችንም ጨበጥናቸው እና የበግ ቆዳ ከተጎዘጎዘበት መደብ ቁጭ አልን። ወዳጄ ቀልጠፍ አለና ወደ ኩሽናው ዘልቆ እህቱን ምግብ እንድታመጣ አዘዛትና "ክቡር ዘበኛ" እሚባለዉን ብርጭቆና በጆክ ጠላ ይዞ መቶ ከፊቴ ቆመ.. እኔም ከቤቴ እንደበላሁና ያው ጠላም እንደማልጠጣ በመናገር አስቤ የመጣሁት "ወተት ለመጠጣት!" እንደሆነ አስታወስኩት!😋 ቢሆንም 'ካልበላህ ወተት የለም!'😑 እሚል እይታ አሳይቶኝ ለራሱ ጠላዉን ቀድቶ ቁጭ አለ። በልቤም አንድ ቁርጥ አንስቼ እበላና ወተቴን እጠጣለሁ ብየ መጠበቅ ያዝኩ ታዲያ የወዳጄ እህት በሰሃን(ባቲ) የሰማይ ስባሪ እሚያክል እንጀራ በድንች በስጋ ወጥ ይዛ መታ አስረከበችኝ!! 'ኧረ በዝቷል ይተርፋል!' ብልም ሰሚ ስላላገኘሁ ወደ ወዳጄ አባት ፊቴን መልሸ 'አባት ይባርኩልኝ?' አላኳቸው(አክባሪ ለመባል) ምን ዋጋ አለው! 'ለወንድ አይባረክም! ዝም ብለህ ብላ!' ብለው ጨነገፉኝ።😬 ኩርኩሜን ተቀብየ ከወዳጀ ጋር የቀረበልኝን ምግብ መብላት ጀመርኩ.. ወዳጄ ምግቡን አቋርጦ ወደ ኩሽናው ተወነጨፈና በግራም ሰሃን እርጎ ይዞ መጣና እንጀራዉን መሸከም ያቃታት ሰሃን(ባቲ) ላይ እርጎዉን አጥለቀለቀው..😇 በላየላይ የወረደዉን መና እያጣጣምኩ በላሁ..😋 ታዲያ በየ መሃሉ አባወራው በመገረም ለምን ጠላ እንደማልጠጣ እየደጋገሙ ይጠይቁኛል! እኔም የተለያዩ መልሶችን እነግራቸዋለሁ.. ወዳጄና እህቱም እንጀራና ወጥ እያመጡ ጨምር እያሉ ከድንች በስጋው ወጥም ከእርጎና ከንጀራዉም ይከምሩብኛል..🙄'ኧረ በቃኝ!' ብልም የቤቱ አባዎራ ጨምሮ እንግዳቹ ሁሉ 'ትንሽ ብላ እንጅ!' እያሉ አጨናነቁኝ እኔ ግን ተሎ መሃላ ዉስጥ ገብቼ ድርቅ በማለት እጄን ታጠብኩና ቁጭ አልኩ..መቼም የገጠር ሰዎች እማይበላ እማይጠጣ አይወዱም።
.
.
ይቀጥላል..


✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
እወዳታለሁ ገራሚ ናት ደስስስ ትለኛለች።
ብዙ ግሩም ጊዜ አሳልፈናል አብረን ስንሆን ሰአቱ ይበርብኛል አብረን ውለን ከመቼው መሸ ትለኛለች ቶሎ ቶሎ ትናፍቀኛለች።

ቀልድ ይገባታል ኮስተር ብዬ ስኮምክ ታሽካካልኛለች፣ ነፍሳችን ይናበባል ፣ ሳናወራ እንግባባለን ።

ከስምንት ወር በፊት <<አግባኝ>> አለችኝ አልተዘጋጀሁም አልኳት፣ ጊዜ ስጪኝ ፣ ትንሽ ታገሺኝ አልኳት
<<አልችልም >>አለችኝ።

የመንደሩ ሰዎች ሽሙጥ ፤ የቤተሰቦቿ ጭቅጭቅ እና እድሜዋ አስጨነቃት ።

እኔ ደግሞ ባልተዘጋጀሁም አቋም ፀናው።

ከህይወቴ መስመር መሰስ እያለች ሄደች። እየደበረኝ ቅር እያለኝ በአቆሜ ፀናው።

አልፎ አልፎ ከአንገት በላይ ሃይ እንባባላለን።

ባለፈው ሳምንት እንገናኝ አለችኝ። ተገናኘን ፤ አይኗ ውስጥ ጉጉት፣ ተስፋ እና ደስታ ምንም አላየሁም። <<በነገራችን ላይ ቅዳሜ ሰርጌ ነው ከቻልክ ልጠራህ ነው የመጣሁት>> አለችኝ።

ትኩር ብዬ አየኋት ቅናቴን ለመደበቅ የደረቀ ፈገግታ ፈገግኩ (ደስስስ የማይል ስሜት ወረረኝ) ያሳዝናል አመለጥሺኝ አልኳት።

<<ብሽቅ ስለሆንክ ተፈላሰፍክ መጠበቅ ፈልጌ አልቻልኩም>>አለችኝ እኔን የምትወደኝን ያህል የምታገባውን ልጅ እንደማትወደው ገብቶኛል።

ያዘዘችውን ቢራ ተጎነጨች እና መጨዋወታችንን ቀጠልን።

<<በእድሜህ ማሳካት የምትፈልገው ነገርን ዛሬ ካልጀመርከው መሽቶ በነጋ ቁጥር ጭንቀትህ ይበረታል ።

ትልቅ ለመምሰል እንዳልጣርን ፤ አንድ ፍሬ ለመባል እንባክናለን።

መንደርተኞች ሳይታወቃቸው ጫና ውስጥ ይከቱሃል ። ባገኙህ ቁጥር ጨዋታ ለመፍጠር ይሆን አሳስቧቸው ይሆን ብቻ ምንጩ ባልታወቀ ምክንያት እንደቀልድ ምንድን ነው መፍዘዝ አግቢ እና ሰርግ አብይን እንጂ ይሉኛል ።

ቤተሰቦቼ ተጠርተው ስለበሉት ሰርግ ከሰርግ ሲመለሱ ይተነትናሉ ይገባኛል መልእክት እያስተላለፉ ነው

ተረድቼሃለሁ ችስታ ነህ ብታገባ ድህነት ፓራላይዝ የሚያደርግህ ይመስልሃል በልጅነት እየራበህ እንዳደክ የነገርከኝን አልረሳሁም ።

አሁን ካገባሁ የትላንት ህይወቴን እደግመዋለሁ ብለህ ትሰጋለህ።

ሁኔታህ እና የኔ ፍላጎት አራምባ እና ቆቦ ሆነ ። እንደሁኔታ በቅርቡ በቀላሉ ትዳር የሚባል ስብጥር ውስጥ እንደማትገባ እርግጠኛ ነኝ

ጌታ ይሁንህ ፤ እህቴ እንዴት ቆማ እንደቀረች አውቃለሁ .. . .. . ዘግይቶ ማግባት ለወንድም ምቾት እንደማይሰጥ ከልጅህ ጋ እየተንከባለልክ መጫወት ሲሳንህ ይገባሃል።

ብልጥ ነኝ ባዮች ቆመው የሚቀሩት እየተመራመሩ ነው ፤ ህይወት በስሌት እና በምርምር ብቻ የሚሳካ እየመሰላቹ ነው>>

ዝም አልኳት ንግግሬ ከዝምታዬ ካነሰ ለምን እናገራለሁ ። ያወራችው የቱ ነው ስህተት ?!

ከነፍ ዝምታ በኃላ አይኖን ትክ ብዬ እያየሁ ትዳርሽ የተባረከ ይሁን አልኳት ።

ፈጥኖ ከመሳሳት ዘግይቷ ትክክል መሆን በእጅጉ ይሻላል ደሞ ያልተሳካ ትዳር ቆሜ ቀረው የሚል ጥድፍያ ውጤት ነው ብዬ ተፅናናው።

© Adhanom Mitiku
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ከማስታዎሻየ_ማህደር!!
.
.
.
#ህይወት_የመኖር_እዳ!!
.
.
.. ከተወለድኩ ጀምሮ እድሜዬ በጨመረ ቁጥር ወደ ህይወት እየመጣሁ ይሆን ወይስ ወደ ሞት እየሄድኩ እንደሆን አላዉቅም! ስለ ህይወት እያወኩ ለመኖር እየጀመርኩ ግን ወደ ሞት እየሄድኩ ይመስለኛል! መኖር ታዲያ እንዴት ስጦታ ሊሆን ይችላል?? ሐይማኖተኛ ሰዎች አንደበት ላይ እማይጠፋ ቃል "በህይወት ስላለህ ብቻ አመስግን!!" እሚለው ነው!! ግን ለኔ አይታየኝም! መፈጠሬን እንደስጦታ አይቼ ለማመስገን ህይወት በቃኝ እስክል መኖር አለብኝ! ካልሆናማ እንዲሁ ወደ ህይወት እየመጣሁ ወደ ሞት ከሄድኩ ስጦታነቱ ቀርቶ ኑሮ እዳ ይሆንብኛል!! ሳልሞት በፊት ተሽቀዳድሜ መኖር ያለብኝ እዳ ሁኖ ይሰማኛል። ሰው ሳይኖርም ይሞታል!
   ህይወት ከፈጣሪ እምትሰጠን ብድር ትመስለኛለች ብድራችን ለመክፈል ስንፈጋ ስንታገል የተሰጠን የክፍያ የቀን ገደብ አልቆ እኛም በነፃነት ሳንኖር እምንነጠቃት ናት። የሰው ልጅ ሁሉ "የህይወት ግብ ደስተኛ መሆን ነው!" በምትለው ህግ ይተዳደራል! ይሄን ህግ ሐይማኖተኞች ቢያጥላሉትም በነሱ ልብ እንደማያምኑበት ቢናገሩም እነሱም በሆነ የህይወት ዘመናቸው ይከተሉታል። ሁሉም ሰው በራሱ ዛቢያ ኑሮን ለማሸነፍ ይሽከረከራል፤ ኑሮን ማሸነፍ ያው ሀፍታም መሆን ነው! ብሎ አዕምሮው ላይ በሰቀለው ሃሳብ ይነዳል። መፈጠሩን እንደ እዳ ለማየት ወይንም እንደ ስጦታ ለመቀበል በቀላሉ በአኗኗር ዘይቤው ይወስናል፤ ብዙዉን ጊዜ ሀፍትን ካካበተ ስጦተነቱን በተቃራኒው በድህነት ከተሰቃየ ደግሞ እዳነቱን ይቀበላል፤ እዚህ ላይ አንዳንድ ነገረኛ አንባቢ "ታዲያ አንተ በድህነት ተሰቃይተህ ነው! ህይወት የመኖር እዳ ናት የምትል" ይል ይሆናል! ግን ህይወት እንዳለህ ሀብት ወይም እዉቀት የምትወሰን ናት በሚለው አልስማማም!! ምክኒያቱም ህይወት አወቅንም አላወቅን ሀፍታም ሆን ወይ ፀደቅን እስክንሞት ድረስ እዳ ናት!! አዋቂው ህይወትን ተረዳኋት ባላት መጠን ሲያብራራና ሲያወጣ ሲያወርዳት ትንሽ በተጠጋት ቁጥር እማያዉቀው እልፍ መሆኑን እየተረዳ አለማወቁን አዉቆ እንኳ እረፍት ሳያገኝ የእዉቀት ጥሙን ሳያረካ ያርፋል!! አላዋቂዉም መኖር ባለማወቅ የሰጠችዉን ሰላም ተቀብሎ መኖሩ ሳይታወቅ በሚራመድበት መሬት የሆነ መስመር የእግሩ አሻራ ሳይታይ ይሞታል!! ሀፍታሙ ሃፍቱን የደከመበትን ያህል ሳያጣጥመው ወይ ደግሞ በሀፍቱ ልክ ደስተኛነቱ የወረደ ሲሆንበት! ወይ ሀፍቱ እረፍት እንደነሳው ሌላ አስደሳች ግብ ወይ ምላሽ ሲፈልግ ያልፋል!! ፃዲቁ ደግሞ የፈጣሪው ፍርድ እያስፈራው በአካባቢው ያሉ ሰዎች ኑሯቸዉን በሐጢያታቸው እየለካ የመኖር ጣእሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ ሞቱ እንዲቀርብለት እየፀለየ ይኖራል!? መፈጠሩ ስጦታ ነው ብሎ ግን መኖሩን ከመሞት በላይ አይወደዉም! ስጦታ ብሎ የተቀበለዉን ህይወት በሞት መነጠቅን ይናፍቃል እንደናፈቀዉም አይቀርምና ያገኘዉና ይቀበላል!!
   በነዚህ ሁሉ መሃል እኛ "ሁሉን ቀመስ!" እምንባል አይነት ሰዎች አለን!! የማህል ዳኛ ማለት ነን፤ ሌሎች በተለያየ አቅጣጫ የመኖራችን ግብ ብለው ያመኑበትን ሲያስቆጥሩ እምናጨበጭብ አንዳንዶች ደግሞ ሲደናቀፉም (ፋዎል) ሲሰሩ እምንታዘብ!! አለን። ለኛ ህይወት ጥያቄ እንጅ መልስ ሁና እማታዉቅ!! ህይወት የመኖር እዳ እንጂ ስጦታ ሁና እማትታየን!! ብዙ የገባን ይመስለናል ግን አንዳች ነገር አንፈታም! እምናምን ግን ደግሞ እማናምን! ወደ ህይወት እንመጣል ግን ደግሞ እማንደርስ! ወደ ሞት እምንሄድ!! እዉቁ ፈላስፋ.. "ያልተመረመረ ህይወት ለመኖር ያልተገባ ነው!" እንዳለው የኛ እዳ ጥያቄ የሆነ ነን። የናንተስ የመኖር እዳ ምንድን ነው?? እዳ ካልሆነ ስጦታነቱን በምን አመናቹህ? ስጦታነቱ ምኑ ላይ ነው? ተሰቶ እሚነጠቅ ስጦታ መሆኑንስ እንዴት ታዩታላቹህ? ወደ ህይወት እየመጣቹህ ነው ወይስ ወደ ሞት እየሄዳቹህ??
.
.
.
ህዳር 28/2015 ዓ.ም

✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join 👇👇👇
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23


@kinchebchabi @kinchebchabi
Live stream started
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ተመልሷል። 🙏
ከ 1962 ጀምሮ እንቅልፍ ያልተኛው ሰው...
@kinchebchabi
ቅንጭብጭብ
ከ 1962 ጀምሮ እንቅልፍ ያልተኛው ሰው... @kinchebchabi
ከፈረንጆቹ 1962 ጀምሮ እንቅልፍ ያልተኛው ሰውዬ በቬትናም ትንሽዬ ከተማ ውስጥ:
በሰላም
በጤና
ከሰዎችም ሳይጣላ
ኡ ኡ ኡ ኡ እያለ ሳይጮህ
ሳያብድ
ሳይደባደብ
ስቅስቅ ብሎ ሳያለቅስ
ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ሳያስቸግር
ሳያቅለሸልሸው
ሳያጥወለውለው
ነገር አለሙ ሳይጠፋበት
ኧረ ወየው እያለ ሳይጮህ

ጭራሽ ትዳር ኖሮት ልጆች ወልዶ ፤ ከአንድም ሦስት ቤት በእጁ ገንብቶ ፤ በቀን ሁለት ስራ እየሰራ አለ ይኖራል።

እንዴት እንደሆነ እንጃ የሆነ ቀን ለታ ነቃ ነቃ ነቃ! በቃ እንቅልፉ ብን ብሎ ጠፋ!

ጥቂት እየተመገበ፤ ሲጃራውን እየጠጣ፤ ቤቱ የሚጠምቀውን የሩዝ አረቄ እየጠጣ ... አለ በሰላም በጤና

መቼ እንደተኛህ ትዝ ይልሃል ሲሉት: ድሮ ነው ሩቅ ጊዜ እያለ
ሚስቱን: ሲተኛ አይተሽው ታውቂያለሽ ስትባል Never እያለች
ልጁን: አንተስ ትተኛለህ ሲሉት "በሚገባ" እያለ

በዙሪያው ያሉ መንደርተኞች በሙሉ መሸ ደና ደሩ ሲሉ እሱግን ይኸው ለ 62 አመታት ቁልጭ እንዳለ አለ🧐

እናንተስ እንቅልፍ ሳትተኙ ኑሩ ብትባሉ የሚሆን ይመሥላችኋልን?

እንቅልፍ ህይወት ነው

🎶 ኦሆኦኦ መለስ አርገው ጋሜ
አይዞህ ወንድሜ🎶 ማለት ይሄኔ ነው 🧐

ሰውየው ግን የሚፈልገው ነገር ... መተኛት ነው አለ።
እውነቱን ነው .... በዚች አለም ላይ ከእንቅልፍ በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ?

ብቻ: በእውነት! ታሪኩ ውስብስብ ነው።

join us
@kinchebchabi
ይግረማችሁ - የምትተኙበት ፍራሽ ምን ይመስላል?

ይመቻል? ይቆረቁራል? ወገቤን አንገቴን አስብሏችኋል? በሉ ስለዚህ ፍራሽ አንብቡ...
ቅንጭብጭብ
ይግረማችሁ - የምትተኙበት ፍራሽ ምን ይመስላል? ይመቻል? ይቆረቁራል? ወገቤን አንገቴን አስብሏችኋል? በሉ ስለዚህ ፍራሽ አንብቡ...
የምናወራው ስለ ፍራሽ ነው ለማለት ያስቸግራል ።

DeRUCCI Smart ' T 11 - Pro  ይባላል  ።  ይህ በ 8,250. ዶላር ለገበያ የቀረበው ስማርት ፍራሽ ከተገጠሙለት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ   ቴክኖሎጂዎች መሀል . ...

በዚህ ፍራሽ ላይ የተኛ ሰው እንቅልፍ እንደተኛና እንዳልተኛ ፡ ፍራሹ በደንብ ያውቃል ። እና እንቅልፍ ካልወሰደው ፡ የመኝታ ቤቱን ብርሀን ቀስ እያለ ይቀንስና ለተኛው ሰው ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ቅርፁን ለዋውጦ ይበልጥ ምቹ ሆኖ እንቅልፍን ለመጋበዝ ይሞክራል ።

ሰውየው በእንቅልፍ ሰአት ሙዚቃዎችን የመስማት ልምድ እንዳለው ፡ ተደርጎ ፕሮግራም ከተደረገ ፡ ከስለስ ያለ በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ በትንሹ ይከፍትለታል ።
እና ቀስ እያለ ፡ ማሳጅ እንደማድረግ አይነት በመጠኑ እየተንቀሳቀሰ ሰውየውን ለማስተኛት ይሞክራል ።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ሰውየው እንቅልፍ ከተኛ ፡ የተከፈተውን ለስላሳ ክላሲካል ሙዚቃ ይዘጋና  የመኝታ ቤቱን መብራት ያጠፋል ።
.......
የዚህ ፍራሽ ስራ  ይህ ብቻ አይደለም ፡ ሰውየው እንቅልፍ ከተኛ በኋላም ፡ የልብ ምቱን ፡ የደም ዝውውሩን ፡ የሰውነቱን ሙቀት እና አጠቃላይ የጤናውን  ሁኔታ እየተከታተለ ይመዘግባል ።
.......
በዚህ አልጋ ላይ የተኛው ሰው ፡ ሰውነቱ ላይ ያልተለመደ አይነት ትኩሳት እንዳለው ፍራሹ  ካስተዋለ ፡ በተገጠመለት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት ፡ የትኩሳቱን ሁኔታ መዝግቦ .........
ማታ ስትተኛ ሙቀትህ ልክ አልነበረም ፡ ትኩሳት አለህ ፡  ሀኪም ቼክ ማድረግ ይኖርብሃል የሚል ቴክስት ጠዋት ወደሰውየው ስልክ ይልካል ።

......

ይህ የሚሆነው የሰውየው የጤና ሁኔታ  ለክፉ የማይሰጥ ከሆነ ነው ። ነገር ግን ሰውየው በተኛበት ወቅት የአተነፋፈስና የሰውነቱ ሙቀት ወይም የልብ ምቱ  ኖርማል ካልሆነና ሰውየው በድንገት ከታመመ ፡ ይህ ስማርት ፍራሽ ፡ ከሰውየው ስልክ ጋር ባለው የኢንተርኔት ግንኙነት አማካኝነት ፡ ወዲያውኑ ለድንገተኛ ህመም ተብሎ ወደተመዘገበው የህክምና ተቋም ወይም ሀኪም ጋር ስልክ ደውሎ ፡ Mr.. እንትና. .  በድንገተኛ ህመም ላይ ስለሆነ ቶሎ ድረሱለት ሲል ይደውላል ። ቴክስት ያደርጋል ።
....
ሰላም ከሆነና ሆኖም ሰውየው እያንኮራፋ ከሆነ ፡ በሚያንኮራፋው ሰው በኩል ብቻ ያለውን  የፍራሽ ክፍል ቅርፁን በመቀየር፡ ሰውየው  አስተኛኘቱን እንዲቀይርና ትራሱን በማስተካከል  አተነፋፈሱ ኖርማል እንዲሆን  ያደርጋል ።
.....
ለሊት ላይ የአየር ንብረቱ ተለውጦ ብርድ ከመጣ ፡ ይህ ፍራሽ ወደ AC ው መልእክት በመላክ ክፍሉ እንዲሞቅ ያደርጋል ። በተቃራኒው ሙቀት ከሆነም ክፍሉ እንዲቀዘቅዝ ያደርጋል ።

... ለሊቱ በዚህ መልኩ አልፎ ሲነጋ ፡ ሰውየው ከእንቅልፍ መንቃት ያለበት ሰአት ላይ ፡ እንደተለመዱት አላርሞች ድምፅ በመልቀቅ አይረብሽም ። ይህ ፍራሽ ጨዋ ነው ።
ከዛ ይልቅ ሰውየውን የሚቀሰቅሰው ፡ የክፍሉን ብርሀን በመጨመር እና በተወሰነ መልኩ ቀስ እያለ በመንቀሳቀስ እያባበለ ነው  ።
ይህን ከማድረጉ በፊት ግን ፡ ወደቡና ማፍያው ማሽን መልእክት በመላክ ፡ ቡና እንዲፈላ ያዛል ።
......
ማታ ሰውየው ጥሩ እንቅልፍ እንዳልተኛ ካስተዋለ ፡ ሲነጋ በሰውየው ስልክ ላይ ፡ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮችን ይልካል ።
.............
ሆኖም  የሰላማዊ እንቅልፍ ጉዳይ  በምቹ ፍራሽ ላይ ከመተኛት ጋራ የተያያዘ  ባለመሆኑ እዚህ ላይ ተኝተውም  ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሊቸግር ይችላልና , ይህን መሰል መኝታ ሳያስፈልገን ስለምንተኛው  ስለ ጥሩው እንቅልፋችን እናመስግን ። ቴክኖሎጂው ግን እዚህ ደርሷል ።
© ዋስይሁን

በአብሮነት እንቆይ
t.me/kinchebchabi