ቅንጭብጭብ
7.18K subscribers
413 photos
9 videos
5 files
502 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ታሪክ ሲደገም
°°°°°°°°°°°°°
‹‹እዘምታለሁ!››
‹‹አትዘምትም!››
‹‹እዘምታለሁ!››
‹‹አይሆንም! አትዘምትም! . . . ዛሬ ከመቅፅበት አስነስቶ ካላዘመትኩ የሚያሰኝህ ምንድን ነው? ቆይ እኔ እናትህ ምን አጎደልኩብህ? እ?›› እናቴ አፈጠጠችብኝ፡፡ ምን ብዬ መልስ ልስጥ? መልሴስ እናቴን ያሳምናት ይሆን?

እናቴ ሁሌ ምትጨቃጨቀኝ በፀጉሬ ምክንያት ነበር፡፡ ‹‹ይኼ ፀጉርህ ተንጨብርሮ ሽፍታ አስመሰለህ፤ ምናለ ብታስቀንሰው!›› ትለኛለች፡፡ ‹‹አልስተካከልም!›› ብዬ እወጣለሁ፡፡ ለምን የሚል ጥያቄ ከማንሳቷ በፊት ሸሽቼ ማምለጥ እፈልጋለሁ፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ ፀጉሬን ማልስተካከለው ማሳደግ ፈልጌ አይደለም፡፡ ከፀጉር አስተካካይ ደንበኛዬ ድብን ያለ ፍቅር ስለያዘኝ፤ ከእሷ ውጭ ራሴን ለማንም አሳልፌ መስጠት አልፈልግም፡፡ (ራሴን ስል ፀጉሬ የተከመረበት የአዕምሮዬን ቅል መሆኑ ልብ ይባልልኝ) እሷ ደግሞ ቤተሰብ ልትጠይቅ ከሄደች ወር አለፋት፡፡ በሄደችበትም በጣም ቆየች፡፡ የኔም ፀጉር ያለቅጥ አደገ፡፡
.
.
ከትናንት በስቲያ የመጣችው ፍቅሬ… ዛሬ ፀጉር ቤቷን መክፈቷን ሳውቅ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ደግሞ ይበልጥ አምሮበታል፡፡ ብር ቢኖረኝ በወር የምታገኘውን እየከፈልኳት የማንንም ፀጉር ሳትነካካ የኔ ብቻ ፀጉር አሽሞንሟኝ አደረጋት ነበር፡፡ እሷ ፀጉሬን ስታሽሞነሙን፤ ፊት ለፊት ባለው መስታውት ሙሉ ገጿን እያየሁ ሀሴትን እጠጣለሁ፡፡ ፀጉር ቤት ውስጥ መስታውት ባይኖር ምን ይውጠኝ ነበር? እንጃ!!

ፀጉሬን ስታበጥር በመስታውት እያጮለቅኩ ሳያት ቆየሁ፡፡ ለእሷ ስል ምንም ነገር አደርጋለሁ፡፡ ምንም ነገር!! እሷን የሚያስደስታትን ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አልልም፡፡ ግን አፍ አውጥቼ ፍቅሬን ልገልፅላት ድፍረት የለኝም፡፡ ታፍቅረኝ አታፍቅረኝ እንኳ አላውቅም፡፡ ግን ተጫወችነቷና ለኔ ያላት አቀራረብ ተስፋን ይፈነጥቅልኛል፡፡

አበጥራ እንደጨረሰች ማስተካከያ መሳሪያውን አነሳችና በመስታውቱ ስታየኝ አየኋት፡፡ ፈገግ አልኩ! ፈገግ ብላ ‹‹አርበኛ መስለህልኝ የለ እንዴ! ፀጉርህን ከምትቆረጥ ብትዘምት ደስ ይለኛል›› አለችኝ፡፡ ፀጉሬ ልብሴ ላይ እንዳይራገፍ ያነጠፈችልኝን ጨርቅ ከላዬ ገፍፌ፤ ፀጉሬን እንዳጎፈርኩ ፀጉር ቤቱን ለቅቄ ወደ ቤቴ አቀናሁ፡፡ እናም ፍቅሬ ደስ የሚላትን ላደርግ ከእናቴ ጋር የጦፈ ጭቅጭቅ ጀመርኩ፡፡
.
.
ለእናቴ ይኼን እውነታ ነግሬ፤ በቃ ለፍቅር ስል በቁርጠኝነት ለመዝመት መወሰኔን ሳሳውቃት… ራሷን ይዛ ‹‹ለካ ታሪክ ራሱን ይደግማል የሚባለው እውነት ነው›› አለች፡፡
‹‹እንዴት?›› ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ፡፡

‹‹እኔ ባንተ እድሜ ሳለሁ… የሰፈሩን ኮበሌ በምላጭ ፀጉሩን እየሸለትኩ ሸጋ አስመስዬ እሰደው ነበር፡፡ … "የወርቅዬ እጅ ወርቅ ነው! ያውም የነጠረ!" እያለ፤ ከኔ ዘንድ መጥቶ ፀጉሩን ማይዋብ ኮበሌ አልነበረም፡፡ ከአባትህ በቀር!! አባትህ ለካ በዐይን ፍቅር ተለክፎ ወደኔ መጠጋት ይፈራ ነበር፡፡ … "ተው ወርቂቱ ዘንድ ሂደህ ተዋብ!" ቢባል… "ወይ ፍንክች!" ይል ነበር አሉ፡፡ ታዲያ አንዴ እንደምንም መጥቶ ከእግሬ ስር ተቀመጠ፡፡ እኔም ከመሸለቴ በፊት ፀጉሩን በጠር በጠር ሳደርገው፤ አርበኛ መስሎ ቁጭ! … "አንተዬ አርበኛ ስትመስል ሸጋ አይደለህ እንዴ! ከምትሸለትስ አርበኛ ብትሆን ደስ ይለኛል!" ከማለቴ ወፈፍ ብሎ ተነሳ፤ መዋቡን ትቶ ከጎኔ ራቀ፡፡ ከዛ ከሰፈሩ ሳላየው ስቀር ጭንቅ ጥብብ እያለኝ ወዳጆቹን ስጠይቃቸው፤ የአባቱን ነፍጥ አንግቶ አርበኛ ሊሆን ጫካ መውረዱን ሰማሁ እልኃለው፡፡››
.
.
‹‹እናቴ ታሪክ ሙሉ በሙሉ እንጂ ተቆንፅሎ በከፊል ሊደገም አይገባም!›› ብዬ ለመዝመት ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፡፡
.
.
ኤልዳን ለፍቅር (ዳን ኤል)

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ፀበል ፥ በሚፀበሉ ፥ የጋኔን ፥ ማደሪያ ፥ በሆኑ ፥ ሰዎች : መሀል : ተከብቤያለው ፥ እንደርቢ ፣ ቡዳ ፣ አዛዝኤል : መተት ፣ ሰላቢ ፣ ድግምት...ወ..ዘ.ተ..........እዝጎ: ብዛታቸው ፥ ግን : እግዜሩ : ብዙ : ተባዙ ያለው : እነሱን ፥ ሳይሆን ፥ አይቀርም። እንዲህ : አንደ : ምድር : አሸዋ : ያበዛቸው። ምናልባት :ውስጣቸው :ስለማይገኝ : ይሆናላ : ብዬ ፥ የጥያቄም ፥ አባት ፥ የመልሱም ፥ እናት ፥ ሆኜ ፥ ቁጭ አልኩ።

እኩለ : ሌት : ላይ ጋደም : ብዬ : ሳለ እማሆይ በደጃፌ : አለፉ ብሩኬ...... ብሩኬ........ በለሆሳስ : ተጣሩ

እ......... አቤት : እማሆይ .... በመደነባበር : ስሜት

አንት : ሙዠሌያም : በሩን : ክፈት .....

ቀጭን : ትእዛዝ ......

እጄ ፥ ወደበሩ ፥ መክፈቻው ፥ አኮበኮበ..... ሲጢጢጢጢጥ... በሩ ፥ ተከፈተ።

እማሆይ ፥ እርቃናቸውን ፥ ናቸው ደነገጥኩ ራሴን እማሆይ : ፃድቅ : ናቸው : የፀጋ : ልብስ : (ፀጉር) ፈጣሪ : አከናንቧቸዋል : ብዬ ራሴን : መሸወድ ፈለኩ።

በርግጥ ፥ እሳቸው ፥ አፍላ ፥ እድሜ ላይ ናቸው። ቁንጅናቸውም ፧ እንኳን ለንደኔ ፥ አይነቱ አለማዊ መናኝንም ፥ ከአቋሙ ፥ ያዋዥቃል።

የጌታ ፥ ፍቃድ : ሆነና : እማሆይም : በውበታቸው ማርከው : መደቡ : ላይ : አጋድመው ፧ ደጋግመው : ነጠሩብኝ....

መቼም ልጄ ነገር በሶስት ይፀናል አሉኝ...... ልክ አንደኛውን ፧ ዙር እንደጨረሱ....

በተወደደ ፥ መቅኔ ፥ መተኪያ በማይገኝበት ፥ ቦታ ላይ ምን ፥ ኩነኔ ፧ ገባሁ? ፥ ጃል! አዎንታዬን ፥ ራሴን በመነቅነቅ ፧ ሶስት ግዜ ፧ እንጢነጥሩብኝ ፈቀድኩላቸው።


ስብሀት ለአብ_____ ቸፍ
ስብሀት ለወልድ_____ ቸፍ
ስብሀት ለመንፈስ ቅዱስ____ ቸፍ

ጠበል ፥ የሚረጩኝ ፥ ግርማ ፧ የ ሞገስ ፥ ተላበሱ አባት በመስቀላቸው ፧ ጀርባዬን እየደለቁ። አንተ ማነህ ?
ፈርጠም ፧ ብለው ፧ በነጎድጓድ ፧ ድምፃቸው....

ሴት ነኝ ያውም መነኩሴ.....

ሴት......ምንድነሽ?

ሴት አይነጥላ ፣ ሴት ሳር

የምንኩስና ስምሽ ማነው?

#እማሆይ_ረታ_ነጠረች

ወደሲኦል ትገቢዘንድ በእግዚአብሄር ስም አዝሻለው ጮኸሽ ውጪ..

ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ጮሄ ወደኩኝ .

ከወደኩበት ስነሳ ብዙ ምዕመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ታድሞ የሚሆነውን በጥሞና ይመለከታል

ስምህ ማነው አሉኝ ግርማቸው የሚያስፈራ አባት

#ካሳ_ውቤ_ልዋጥህ

ህምምም ¡ አለ ነገር......

ፀሀፊ
ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ
@surabirabiro🦋

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ግንኮ እወዳታለው.......
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅንጭብጭብ
ግንኮ እወዳታለው.......
መውደድም ብቻ አደለም አፈቅራታለው!
ቅንጭብጭብ
💋 Sticker
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅንጭብጭብ
መውደድም ብቻ አደለም አፈቅራታለው!
ይሄንንም እሷ አታውቅምኮ.....
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅንጭብጭብ
ይሄንንም እሷ አታውቅምኮ.....
አደራ ንገሩልኝ....
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድንቡሽ ፣ ድንቡሽቡሽ
እንትፍ ፣ ጣል የጠላን ጉሽ።

ሱራ ቢራቢሮ🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
////////////////////

#ልቤ_ልብ_እሚለው?!

ዘመን መቀየሩን በጋና ክረምቱን
ተፈራርቆ መቆም ጨረቃ ፀሐዩን
ሙቀትና ብርድን አካሌ እሚለየው
ብርሃንና ጨለማን ላይኔ የሚታየው
ከጎኔ ስትሆኝ ወይ ስትርቂ ነው
ልቤ ልብ እሚለው..
ከጎኔ ስትሆኝ በጋ፣ፀሐይ፣ሙቀትና ብርሃን
ከጎኔ ስትርቂ ጨረቃ፣ብርድና ጨለማን!!


✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

@kinchebchabi
@kinchebchabi
እስስት : ስትጎተትና : ስትቀያየር እንደምትጠላ : አታውቅም : አካሄዷም : ቢሆን ፥ አይኗ : ልቧን : ይመራዋል : እንጅ ልቧ : አይኗን : እንደሚከተለው : አታውቅም.....
ግንኮ : አይን : ያየውን : ለልብ : ካልነገረው : ልብም : አድምጦ : ካላመነበት : አይንን : ይከተለዋልን?

መቼም አንዴ ለጉዞ ፈጥሮኛልና መንገድም : እወድ የለ .....
በጉም : ላይ : እየተረማመድኩ : ሳለ ብቻዬን : አግዜሩን : አግኝቸው : ነበር : በምናባዊ : ፀዳል እንደምናስበው : አደለም : ኮስማና ነው።

እናተ : ሰዎች: ለምን : ትጠሉኛላችሁ : ስለምንስ ከክብሬ : ቁልቁል : አፈረጣችሁኝ : ማቅለላችሁ : ሳይቀር : ለሌሎች : መሳለቂያ : አረጋችሁኝ ፥ ከዙፋኔ እያለሁ : እንደሌለሁ : አበሸቀጣችሁኝ ለምን? ስለምንስ? ተጠራጣሪ : ሆናችሁ : በኔ ለምን? እንባ እንቅ እንባ እንቅ ,,,,,
እያረገው : ሶስት : የእንባ : ዘለላ :ከገፁ ፥ ሲረግፍ እየሁ።

እንባው ፥ ወደስቅለቱ : ትዝታ : እያላጋ : ወሰደን በስቅለቴ : ግዜ አንድ : ደንባራ : ወታደር : በጦር ጎኔን ሲወጋኝ : ህመሙን : አታውቅም : ይሁዳ : በከንፈሮቹ ሀሞት : ተጎንጭቶ : ጉንጨ : ላይ : ሲተፋብኝ : የተሰማኝን : አታውቅም : ጴጥሮስ : ሶስት : ግዜ : አንድ ለአብ አንድ ለወልድ አንድ ለመንፈስቅዱስ ለያንዳንዳችን : በአንድነት : የክህደትን : ኮሶ : ሲያግተን : ምሬቱን : አታውቅም።

40 ቀን 40 ለሊት ስፆም ሰይጣን በእባብ ተመስሎ ሲፈትነኝ የፈጠርኩትን መልሶ የኔ ሊያረጋቸው ሲደራደረኝ ቤተ መቅደሴን ሲሻቀጡበት እናቴን ከቁሻሻ መሀል ትቢያ እንደተደፋ ልቅላቂ ሲጠየፏት አታውቅም።

አዎ አታውቅም ........ እናት ሰዎች ህመሙን አታውቁም .........

የእግዜር እንባ ግን ምን አይነት ነው?

እኔም: ሆድ : ብሶኝ : የልቤን : ዘረገፍኩለት :ጌትዬ : በሁለት : አለም : ሰካር : ውስጥ: አየዳገርኩ: ለምን ዝም አልከኝ? አንተኮ: ብትታመምም : አምላክ ነህ የአምላክነትህ : ባህርይ ረቂቅ : ነው ያስችልሀል::

ግን ለምን ፈጠርከኝ? ማጥ: ረመጥ : ውስጥ : ከተትከኝ? እውነት አውጣኝ : ብዬ : ስለምንህ: ሳትሰማኝ : ቀርተህ ነው?
የህይወትስ ጣዕሙ በምን ይለካል ? በድን : አካልን አሸክመኸኝ : ለአመመታት : መክረሜን ዘንግተኸው ነውን?

እኔ : የነካሁት : ሁሉ : ርኩሰትን : እንዲላበስ : ሁሌ እንድሸሸግ : የምታረገኝ : ራሴን : በራሴው እንደ እፉኝን : ስውጥ አላሳዝንህምን?

የእናትህስ : ህመም : አንተን : ብቻ : የሚቆረቁርህ ይመስልሀል?
እሷኮ : አምጣ : አልወለደችህም : ደም : አልፈሰሳትም
ምነው_ቸሩ _መድሀኔ_አለም : የኔዋ : እናት: ወዝ ወዘናዋን : አጠንፍፋ : ባማጠች : የህመሟን ሲቃ ባስረቀረቀች : አኔን : ወልዳ : እንኳ_ማርያም : ማረችሽ ቢሏት : አንተው : የማርካት መሰለህ? በድኩም : አካሏ : ተንፏቃ : አፈር : ልሳ : ብትለምንህ : መች ምሬሻለው : አልካትና? የማርያም ልጅ...!!

አንተ : ብትፆም :ባህሪህ : ቅዱስ : ነህና : ይፈቅድልሀል እኛስ :አንጀታችን :ሲታለብ :ቆርቆሮ :ቤታችን :ውስጥ : በችጋር : ስንለበለብ :ዞር ብለህ : አይተኸናል : እንዴ?
ቅፅበታዊ : ደስታን : አሳይተህ : ዛላቂያዊ : ህመምን ከልባችን : የቸነከርከው : እውነት : ከሳዶርና ፣ አላዶር የሚተናነሱ : ይመስልሃልን?

ተው : እንጅ : ቤዛ ከሉ መድሀኔ አለም..... ተው እንጅ የማርያም ልጅ!!

ተስፋዬን : በምኞት : ደግፌ : ብጓዝ :ባንተ : አይደል የጨነገፈው : ማያዬ :መመልከቻ : አድማሴን : ባገኛት
ባንተም : አይደል : ያጣኃት? እንደኩታ : አይሽሞንሙነህ : ያለበስከኝ : ይህን :ማንነት አንተም አደል : የፈጠርከው ? ይኸው : እሷም /ወደመሸሹ አጋደለች....
እስቲ : ልወቀው : ጥፋቴን :ለምን : ግራ አርገህ ፈጠርከኝ?
ምን ትለኝ ይሆን? ምንስ ምላሽ ይኖርህ?

ግን ለምን አትወስደኝም? ኖሬ : የህይወት : ጣዕሙንስ በምን :ምላሴ : ላጣጥመው? ምላሴን : ቆርጠህብኝ ......ሳላጣጥመው : ኮመጠጠኝ።

ተፈጥሮ : ፊቱን : አጨፍግጎብኝ : ሳለ : ከነፍሴ የተጣባች : እንስትን : ወዳንተ : ልካኝ : ነበር። አንተ የምድርና ፣ የሰማይ : ጌታ : ሆይ : ቸኮሌት : ላክልኝ ብልሀለች።

ከጥሪው : መዝብ : ሳሟ :ሳይሰፍር : ወደኔ መታ የነበረችው : ማያዬን አወካት?

ለነገሩ : አንተ : ብታቅም : አላቅም :ከማለት : ወደኃላ አትልም...... ብቻ እሷ ታቅሀለች።

በቃና : ዘገሊላ :ግዜ : ውሀውን : ወይን : ጠጅ : አድገህ : ነበር : በሰው : ሰርግ : እንደዚ : የሆክ : በራህ : ሰርግ : እንዴት: ትሆን?
በስቅለትህ : ወቅት : ጎንህን : ሲወጉህ : ውሀ፣ ደም፣ ወተት : ፈሶህ ነበር ።

በመጀመሪያ :ቀን : ማያዬን : ሳገኛት : ውሀ ጠጥታ ነበር ።
በሁለተኛው : ቀን : ስንገናኝ : በተፈጥሮ : ደም እየፈሰሳት :ነበረ ።
በሶስተኛ : ቀን : ፈጣሪ : ቸኮሌት : በኔ : በኩል እንዲልክላት : ጠይቃኝ ነበር።

በቸኮሌት: ውስጥ : ወተቱን : ለማግኘት :ፈልጋለው ይሆናላ....


ቸኮሌቷን : አንድቀን : ይዤላት: እንምመጣ :ታውቅ ይሆን?

አታውመቅም.........

የእግዚአብሄርን : ልጅ : ሰርግ : አይቼ : ከድግሱ : በልቼ ጠጥቼ : መሞቴን : እንኳን : አታውቅም..........


አዎ አታውቅመም.....

አደራ
******ንገሩልኝ******


ፀሀፊ
🦋 ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ🦋
(🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
አታውቅም

(🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ምሽቴን በ( Ali_faraka)

ዘፈን ነውዝ


🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
አልቦ : መጋት : ምን ይሉታል? ምንስ : ይሉት ፥ የአንጀት እከክ : ቢጣባው : ነው?
ደርሶ :ግንፍል ፣ ክብልል የሚያደርገው።

መቼም : ዲያቢሎስ : ሹክ : ብሎት ነው እንጂ.... እንዲህ : ልቡ : የደነደነው።
ልጓሙን : በጥሶ : ያጠጠው .እወነት : ለመገራት : ልቡ : ባይከጅል ነው እንጂ : እውነታው : ሳይገዝፍበት ቀርቶ አደለም።

ሲናውዝ : የዋለው : በከቻ : ስጋውን : ሊያሳርፍ : ከመደቡ : ላይ ዝለታም አካሉን : ጣለው።

ሁፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ,,,, ተመስገን አለ።

ቤቱ : ግድግዳ : ላይ ኢየሱስ : በመስቀል የተቸነከረበትን : ምስል አንጋጦ : እያየ።

ልቡናው : የተሰለበው : ከእሷ ዘንድ ነበርና : የዛለውስ : ያመሰገነውስ : እሷን በማግኘቱም : አደል።

ጌታን : ያለ : መስቀል : እሷን : ያለ : ሀፍረቷ : ሊስላቸው : መቼ ፈቅዶ!!

ወትሮስ የባተሌ ነገር........

🦋ቅዱስ አርዮስ🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋

እንደ ይሁዳ ሳመችኝ.....

እንደ ጌታ ተሸጥኩላት !


🦋ቅዱስ አርዮስ🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
አምሳለ ሰው አምሳለ በግ

እምበበበበበበ.......
ለተራበ
ለሞላለት ፥ ለተካበ

እሰይ! ለተከፋ ፣ የተደፋ
መጥፎ ሽታ የከረፋ!

ምናምንቲያም ፥ ምናምኒት
የዶሮ ጦስ ሽክርክሪት፣

ሽክርክር.... ሽክርክር....
ደቂቃ ሰአታት
አብረን ስንቆጥር፣
አስትንፋስ በደም ውስጥ
ዘልቆ ሲዘዋወር፣
በአራራይ ዜማ ጮህ ብዬ ስናገር
ፋታም አላቆየኝ ከህመሜ እስክሽር።

ሽክርክር...... ሽክርክር.....
አስብቶ ሸክ አንገት ክርክር
ሽክርክር...... ሽክርክር.....

ከቀኝ ወደግራ ከግራ ወደቀኝ
እንዲያው ቢራራልኝ፣

ቃኘት አየት መለስ
ገረፍ ቀለስ መለስ፣

በአይነ ድምፅ በአራራይ
ላይሰማ በለሆሳስ የምሰቃይ፣

በአርምሞ
ካራ ከአንገት ተቀጣጥሞ፣

ሸክ!
ክርክር!
ብጥስ!
አንገት ቅንጥስ፣

ቀይ ደም ፍስስ
ከአፈር ልውስ፣

የገዳይ አንጀት ሲርስ
ሟች ቅልስልስ።

እምበበበበበበበበበ.....

እምበ ለተራበ


ጠኔ ሆዱን ገዝግዞት በሙክቱ ከጠረቃ በኃላ ማሰብ ጀመረ ሲያብሰለስል ከአስርቱ ትእዛዛት ውስጥ አትግደል የሚለው ትውስ አለው
አትግደል ብሎ መግደል ምን ይሉታል? አይ እግዜር ሞኝ ነህ ልበል....



እርሱም ሚስጥር መቋጠር አይችልም። ብናበላውና ብናጠጣው ካባቱ ዘንድ ያየውን ሁሉ ነገረን (የዘር ያዕቆብ ንግርት ትውስ አለው)

ከልቡ ፈገግ...... አለ

አዬ ...ሆድ አምላኩ¡


ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ሞት ሞት ከረፋኝ

ወላዲቴን......

🌓 የግማሽ አለም ጣኦት🌗
ከምኔው !!?

ጠዋት አይደል እማማ ሩቂያ ከእንቅልፌ ቀስቅሰው ሱቅ የላኩኝ?? ከምኔው ባስ ውስጥ "አባባ እዚህ ይቀመጡ " ተባልኩኝ?

- አሁን አጠገቤ አልነበርሽ ? ከምኔው ሄደሽ ተሰወርሽኝ?

- ቡና እያቀራረብሽ አይደል የሳምኩሽ? እያፈርሽ "ሰው ቢመጣስ!" ያልሽኝ ?

- ቅድም አይደል ቤቱን የጠረግሽው ?"ቤቱን ወልዬዋለሁ እስኪደርቅ በረንዳው ላይ ሁን " ያልሽኝ ?/ከምኔው ቤቱን አቧራ ዋጠው ሸረሪት አደራበት !!

- ቅድም ከምሳ በኋላ አይደል ቡና ያፈላሽልኝ ?? ታዲያ ከምኔው ያፋሽከኛል?

- ማታ ከራታችን መልስ አይደል እንዳረገዝሽ የነገርሽኝና አብረን ያለቀስነው ?? ከምኔው ልጄ "እማዬስ" አለችኝ?

- እብዱ ታገል እንኳን ትላንት እራቱን ካበላነው በኋላ አይደል "ውይ የናንተ ፍቅር" ብሎ ሲያደንቅ አሁን በጆሮዬ የሠማሁት?? ከምኔው ፎቶሽ ያለበት የ10ኛ አመት ሙት አመት መታሰቢያን ካርድ ይዞ አየሁት "ወ/ሮ ርብቃ እኚህ ነበሩ" የሚል ያለበት
ትላንት ሌሊት አይደል እንዴ ኑኑዬ ሸንታ አቃጥሏት አልቅሳ ከእንቅልፋችን ባነን ተነስተን ስንሯሯጥ የነበረው???

- ከምኔው ኑኑዬ አድጋልኝ "እማዬስ??" አለችኝ

ከምኔው????....

ከምኔው...

ከምኔው ትዝታ ሆንሽኝ??? አልገባኝም


"(ዘምሽ ያልግዬ)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ሲርሲርታ ፥ የሚንቦለቦል ፥ እቶን ፥ ትንፋሽ። አየር ፥ቀዶ ና ሰንጥቆ ፥ ከብርሃን ፥ ተላግቶ ፥ ወደ ፥ ጨለምተኝነት ሲያዘም ፥ ዘሞም ፥ ጭልጥ ፥ ብሎ ፥ ሲነጉድ እንደገደል ፥ ማሚቱ ፥ ሲያስተጋባ።

ምላሽ ሰጪ ማን ይሆን?

የሲቃ ፥ ናዳ ፥ ሲግተለተል። ራስ ፥ ከራስ ፥ ሲጣረስ ማንስ ወደ ማን ሊጮህ? የጮኸስ ምን አግኝቶ?

ካለ ንገሩ እንጂ? በእግዜር.....

እንጃ እኔስ ሞት ሞት ከረፋኝ
አይኖቼ ደም ሰቀዙብኝ፣

እንጃ የሞት ጠረኑንን
ውል እያለ ማፍገምገሙን፣

አልወደድኩት......አልተመቸኝ

እንጃ.....



ቅዱስ አርዮስ(🦋 )
🌗የግማሽ አለም ጣኦት 🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋