#አድዋ_ድል
የጥቁር ሕዝብ ኩራት
21 ቀናት ብቻ ቀሩት #ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ አድዋን በፌስቡክ እናክብር እና ከ ጉዞ አድዋ ጋር በመተባበር ታሪኮችን ያጋራችኋል ሼር ማድረግዎን አይርሱ።
ወዳጅዎን ወደዚህ ገጽ ይጋብዙ
@kinchebchabi @kinchebchabi

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#አድዋ 💚💛❤️
ታላቁ የጥቁር ህዝብ ድል ዓድዋ ድል የጀመረው ከጦርነቱ በፊት ህዝቡ የንጉሡን ጥሪ ሰምቶ ከጫፍ ጫፍ የተመመ ዕለት ነው። መነሻው ላይም ድል አድራጊነት መንፈስ ነበር። መነሻው ይህ ነበር ....
“እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፣ አገሬን ጠብቆ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለኔ ሞት ኣላዝንም። ደግሞም እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም። እንግዲህም ያሳፍረኛል ብየ አልጠራጠርም።
.
.
አሁንም አገር የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቸ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።
.
.
አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ! ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም። በድየህም ከሆነ ለሀገርህ ስትል ይቅር በለኝ። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ስለዚህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለሚስትህ፥ ለሃይማኖትህ፥ ለሀገርህና ለታሪክህ ስትል በጸሎትህ እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጠላኝ አለህ ፣ አልተውህም ! ማርያምን ! ለዚህ አማላጅ የለኝም!
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

"የዳግማዊ ምኒልክ የክተት አዋጅ ከወራሪዎቹ እንቅስቃሴ አንፃር ከተጠበቀበት ወቅት ዘግይቷል፡፡ ይህም በአፍሪካና አውሮፓ ሀገሮች አይን ምንሊክን እንደ ፈሪ እንዲታዩ አድርጎ ነበር ይላል" ራይሞን ጆንስ የአድዋ ጦርነት በሚለው መፅሀፉ፡፡ ፀሀፊው ሲቀጥል "የመሪ ብልህነት የሚለካው ቸኩሎ በመወሰኑ ሳይሆንበወቅቱ ያሉትን አመቺ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሲያሳልፍ ነው ይላል፡፡
የክተት አዋጁ በራሱ በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የፈተና ጊዜ ማለፍንና የመረጋጋት ዘመን መምጣቱን ገላጭ ከመሆኑም በላይ፤ ህዝቡ ከሃይማኖት፣ ከዘርና ግዛት ማስፋፋት ፍጭት በመውጣት ስለ አንድ ሀገሩ ደህንነት በጋራ የሚቆም እንደነበረ ያረጋግጣል።
" እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፣ አገር አስፍቶ አኖረኝ" ሲሉ ከአድዋ በፊት ጠንካራ የውጭ ጠላት አልነበረምና ጦርነት በሌለበት ሀገር እርጋታ ላይ ሆና አስተዳደሯን እያደረጀች እንደነበረ ይነግረናል።
" አሁንም አገር የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።"
ይህ ንግርት በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የመከራ ዘመን "ክፉ ቀን" ደግመን እንድንመረምር ያደርገናል። በከ1881 ዓ.ም ጀምሮ የነበረው በኢጣሊያኖች አማካኝነት ወደ ሀገር የገባው የከብት በሽታ ለአራት አመታት ህዝቡን ከብቱን ጎድቶ ነበር። ረሀብ በመፅናቱ እናት ልጀቿን የበላችበት ክፉ ዘመን ነበር። እናም የዓድዋ ጦርነት ለምን ዘገየ ሲባል ራሱ አዋጁ ይነግረናል " የሰውን መድከም የከብቱን ማለቅ አይቼ እስካሁን ዝም ብለው" ይህ ሀሳብ ከላይ ራይሞን ጆንስ ከጠቀሰው ጋር የሚስማማ ነው፡፡
እምዬ በጥሪያቸው " ማርያምን አልምርህም! ለዚህ አማላጅ የለኝም " ብለዋል። ግን ሀገሬው በሙሉ ሃይማኖቱን አስቀድሞ በእምነቴ አልተጠራሁም ብሎ ሀገሩን ከመታደግ አልቀረም። ንጉሱን ተከትሎ ከንጉሱ ጋር ተዋደቀ እንጂ።
ለዛ ነው እምዬ ከምንም በላይ ሀገር እንደሚቀድም አሳይተው በአንድነት የመምራት ብቃት ነበራቸው የሚያሰኘው።
ክብር ይሁን!

…ሀገሬ…
:
ትሄጃለሽ አሉ፤ ትሄጃለሽ መንገድ
ጠላት የማያጣሽ፤ ሀገሬ ስር ሰደድ
እጅሽን አትሰጪ፤ ወይ በጅሽ አትበልጪ
በመሸነፍ አለም፤ ከሁሉ ምትበልጪ
እማማ ኢትዮጵያ፤ የዘላለም ቅኔ
ፍቆ ማይለውጥሽ፤ የጊዜ እርዝማኔ
እነደ ነበርሽ ኑረሽ፤ እንደ ነበርሽ ያለሽ
ሀገሬ ቅኔ ነሽ፤
በመጓዝ ላይ መቆም፤ ትችይበታለሽ።
ጠላቶችሽ በዝተው፤ ጦርን ቢሰብቁ
ግራ ገብቷቸዋል፤ ጋሻሽ የት እንዳለ ባለመታወቁ
ሰይፍሽ የተያዘው፤ በማን ይሆን እንጃ
ሳይወድሽ ወዶሻል፤ አለም በግድጃ
ሰንጥቀው ሊቆርሱሽ፤ ይሽቀዳደማሉ
ሳይቀዳደሙ፤ ባንቺ ይወድቃሉ።
:
ሀገሬ ጡንቻቸው፤ ብረት የነበረ
ባንቺ ስንጥር መዳፍ፤ ቀልጦ ተሰበረ
ለታምር የሰራሽ፤ ታምር የምትሰሪ
በአምላክሽ ጠብቆት፤ ሳትፈሪ ምትኮሪ
ምን ቢሉሽ ኋላ ቀር፤ ከፊት የምትመሪ።
ሀገሬ ምስጢር ነሽ፤ ምስጥር ምትፈቺ
ወኔሽ የጎመራ፤ ጠላትሽን ምትረቺ
በድሎት ተፈጥሮሽ፤ የምትንገላቺ
ህዝብሽ ወኔ ገዳይ
ነብር ነው ጠላት ሲያይ
ጉራማይሌ መልኩ፤ ዘምቶ በጦር ሜዳ
ሳይገፍ አይመለስ፤ የጠላትሽን ቆዳ
ህዝብሽ አስፈሪ ነው፤ ባንድነት ከቆመ
ከኋላ እየቀረ፤ ከፊት የቀደመ።
:
ስላ'ቺ ፊትነት፤ ሚስጥር ነው የሚያውቀው
ከመለኮት በቀር፤ ማን ሊያውቅሽ ተቻለው!
ሀገሬ የብዙ ጥያቄ፤ አንድ ጥያቄ ነሽ
ከሲኦል ማታንሺ፤ አንቺ እኮ ገነት ነሽ!
ሀገሬ የብዙ ምሳሌ፤ ነሽ አንድ ምሳሌ
የፍጥረት አንድምታ፤ የጅምሮች ቅኔ
ሀገሬ አንቺን ያየች ለታ፤
ጥበብ ነኝ የምትል፤ ጥበብም ታፍራለች
አንቺን ያየች ለታ፤ ውበት ነኝ የምትል፤ ውበት ትረግፋለች።
ሀገሬ፤ እንደ አለመሆን ያለሽ
መሆን እራሷን ነሽ
እንዲ አይወስኑሽም
እንዲያም አይሉሽም
የሁሉ ጅማሬ፤ የመፈጠር ምራፍ
የፍጥረት ሁሉ ሀገር፤ የገነቶች በራፍ
የሲኦሎች ደጃፍ
ብቁ የሆንሽ ነገር
ብቁ ያልሆንሽ ሀገር።
"ትሄዳለች አሉ፤ ተጓዥ ናት የኔ ሀገር
ሰላማዊት መሳይ፤ ይቺ የጦር ሰፈር"
ወይ አትሸነፍም፤ ወይ አታሸንፍም
ሀገሬ ብትወድቅም፤ ወድቃ ግን አታውቅም።
ሀገሬ ቅኔ ነች፤ ፅፈው የማይፅፏት
ሀገሬ ሀገር ነች፤ አውቀው የማያውቋት
ብቻ የኔ ሀገር፤ እናቴ አበባዬ
የውልደቴ ታሪክ፤ ናት መጀመሪያዬ
እያሰብኳት ምሞት፤ ናት መጨረሻዬ።
:
እንቺ ሀገሬ ሆይ፤ እኔው ላወድስሽ
እሚያከብርሽ ባይኖር፤ የለም የሚንቅሽ
ሀገሬ!
በነጋ በጠባ፤ ጠሎት ምታረጊ
በጥበብ ቃሎችሽ፤ ጠላት የምትወጊ
መሳሪያ የሌለሽ፤ ቀን ከሌት ተዋጊ
የብዙ ጠላቶች፤ አንድ ድል አድራጊ።
ሀገሬ ብቸኛ!፤
የእልፍ መላዕክታን፤ የሚስጥር ጓደኛ
ጉድፍ የሌለብሽ፤ ምትባይ ጉደኛ
ጥጋብ የበዛብሽ፤ የሆንሽ እራብተኛ።
ሀገሬ……ሀገሬ!
ዘመን ተጠብቀሽ፤ ዘመናት ምትኖሪ
ምስጢረ ኢትዮጵያ፤ በመኩራትሽ ኩሪ!!!።
፩-፮-፳፻፲፩ | @Abb21
© አብርሀም የሙሉ ልጅ
@kinchebchabi @kinchebchabi
…ሀገሬ…
:
ትሄጃለሽ አሉ፤ ትሄጃለሽ መንገድ
ጠላት የማያጣሽ፤ ሀገሬ ስር ሰደድ
እጅሽን አትሰጪ፤ ወይ በጅሽ አትበልጪ
በመሸነፍ አለም፤ ከሁሉ ምትበልጪ
እማማ ኢትዮጵያ፤ የዘላለም ቅኔ
ፍቆ ማይለውጥሽ፤ የጊዜ እርዝማኔ
እነደ ነበርሽ ኑረሽ፤ እንደ ነበርሽ ያለሽ
ሀገሬ ቅኔ ነሽ፤
በመጓዝ ላይ መቆም፤ ትችይበታለሽ።
ጠላቶችሽ በዝተው፤ ጦርን ቢሰብቁ
ግራ ገብቷቸዋል፤ ጋሻሽ የት እንዳለ ባለመታወቁ
ሰይፍሽ የተያዘው፤ በማን ይሆን እንጃ
ሳይወድሽ ወዶሻል፤ አለም በግድጃ
ሰንጥቀው ሊቆርሱሽ፤ ይሽቀዳደማሉ
ሳይቀዳደሙ፤ ባንቺ ይወድቃሉ።
:
ሀገሬ ጡንቻቸው፤ ብረት የነበረ
ባንቺ ስንጥር መዳፍ፤ ቀልጦ ተሰበረ
ለታምር የሰራሽ፤ ታምር የምትሰሪ
በአምላክሽ ጠብቆት፤ ሳትፈሪ ምትኮሪ
ምን ቢሉሽ ኋላ ቀር፤ ከፊት የምትመሪ።
ሀገሬ ምስጢር ነሽ፤ ምስጥር ምትፈቺ
ወኔሽ የጎመራ፤ ጠላትሽን ምትረቺ
በድሎት ተፈጥሮሽ፤ የምትንገላቺ
ህዝብሽ ወኔ ገዳይ
ነብር ነው ጠላት ሲያይ
ጉራማይሌ መልኩ፤ ዘምቶ በጦር ሜዳ
ሳይገፍ አይመለስ፤ የጠላትሽን ቆዳ
ህዝብሽ አስፈሪ ነው፤ ባንድነት ከቆመ
ከኋላ እየቀረ፤ ከፊት የቀደመ።
:
ስላ'ቺ ፊትነት፤ ሚስጥር ነው የሚያውቀው
ከመለኮት በቀር፤ ማን ሊያውቅሽ ተቻለው!
ሀገሬ የብዙ ጥያቄ፤ አንድ ጥያቄ ነሽ
ከሲኦል ማታንሺ፤ አንቺ እኮ ገነት ነሽ!
ሀገሬ የብዙ ምሳሌ፤ ነሽ አንድ ምሳሌ
የፍጥረት አንድምታ፤ የጅምሮች ቅኔ
ሀገሬ አንቺን ያየች ለታ፤
ጥበብ ነኝ የምትል፤ ጥበብም ታፍራለች
አንቺን ያየች ለታ፤ ውበት ነኝ የምትል፤ ውበት ትረግፋለች።
ሀገሬ፤ እንደ አለመሆን ያለሽ
መሆን እራሷን ነሽ
እንዲ አይወስኑሽም
እንዲያም አይሉሽም
የሁሉ ጅማሬ፤ የመፈጠር ምራፍ
የፍጥረት ሁሉ ሀገር፤ የገነቶች በራፍ
የሲኦሎች ደጃፍ
ብቁ የሆንሽ ነገር
ብቁ ያልሆንሽ ሀገር።
"ትሄዳለች አሉ፤ ተጓዥ ናት የኔ ሀገር
ሰላማዊት መሳይ፤ ይቺ የጦር ሰፈር"
ወይ አትሸነፍም፤ ወይ አታሸንፍም
ሀገሬ ብትወድቅም፤ ወድቃ ግን አታውቅም።
ሀገሬ ቅኔ ነች፤ ፅፈው የማይፅፏት
ሀገሬ ሀገር ነች፤ አውቀው የማያውቋት
ብቻ የኔ ሀገር፤ እናቴ አበባዬ
የውልደቴ ታሪክ፤ ናት መጀመሪያዬ
እያሰብኳት ምሞት፤ ናት መጨረሻዬ።
:
እንቺ ሀገሬ ሆይ፤ እኔው ላወድስሽ
እሚያከብርሽ ባይኖር፤ የለም የሚንቅሽ
ሀገሬ!
በነጋ በጠባ፤ ጠሎት ምታረጊ
በጥበብ ቃሎችሽ፤ ጠላት የምትወጊ
መሳሪያ የሌለሽ፤ ቀን ከሌት ተዋጊ
የብዙ ጠላቶች፤ አንድ ድል አድራጊ።
ሀገሬ ብቸኛ!፤
የእልፍ መላዕክታን፤ የሚስጥር ጓደኛ
ጉድፍ የሌለብሽ፤ ምትባይ ጉደኛ
ጥጋብ የበዛብሽ፤ የሆንሽ እራብተኛ።
ሀገሬ……ሀገሬ!
ዘመን ተጠብቀሽ፤ ዘመናት ምትኖሪ
ምስጢረ ኢትዮጵያ፤ በመኩራትሽ ኩሪ!!!።
፩-፮-፳፻፲፩ | @Abb21
© አብርሀም የሙሉ ልጅ
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#አድዋ
፨ የዓድዋ ጦርነት መነሻ
(ሥነ-ልቦናዊና ማኅበረሰባዊ ዳራ)
ድርጊት ከሐሳብ እንደሚጀምር የሐሳብ መሠረቱ ደግሞ ሥነ ልቦና ነውና ዓድዋን ስናስብ መነሻው ላይ የነበረው የሁለቱም ወገኖች ሥነ ልቦና ምን ይመስል እንደነበር መመርመር ጠቃሚ ነው። የወራሪው ፀብ አጫሪነት፣ ንቀትና እብሪት፤ የጥቃት መላሽ ደሞ የአልደፈርምና እምቢ ባይነት።...
፩) ጣልያን ከዓድዋ ጦርነት በፊት
ጣልያኖች እንደ ወራሪ ኃይል ወደ አፍሪካ ለመስፋፋት ሲወጥኑና ከኢትዮጵያም ጦር ሲማዘዙ በሀገራቸው የነበረው ማኅበራዊ ሥነ-ልቦናዊ ሁኔታ የተዛነቀ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡
የበታችነትን ስሜት መቀልበስ ወይስ አቅምን አውቆ ለመኖር በማሰብ።
የበታችንት ስሜት ሲባል፡-
ከጥንታዊው የሮማ ስልጣኔና ጥንካሬ በተቃራኒ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት ጣሊያኖች እንደ ሀገር እንኳን ለመቆም ቸግሯቸው ነበር፡፡ ጥንት ከነበሩበት የዓለም ልዕለ ኃያልነት ወርደው ወደ የበዪ ተመልካችነት ደረጃ አቆልቁለው ራሳቸውን አገኙት፡፡ ይህን ነባራዊ ሁኔታ ላለመቀበልና ግፋም ሲል ለመቀየር የነራቸውው የዘመኑ ዘዴ ከሀገር ውጪ ግዛት ማስፋፋትና መያዝ ነበርና ቅኝ ለመግዛት ሩጫ ገቡ፡፡ ኢትዮጵያን መውረራቸው ውስጥ ውስጡን ሲታይ ጣሊያኖች ከጎረቤቶቻችን አናንስም ከሚል ሀገራዊ (ማኅበረሰባዊ) የበታችነትን ሥነ-ልቦና ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡
ንቀትና እብሪት
ጣሊያኖች ለራሳቸው የነበራቸው ከእውነታው የራቀ ግምት የተለየ ሚና እንዳላቸው አድርገው እንዲቆጥሩ ሳያድረጋቸው አልቀረም፡፡ "ኋላ ቀርን ሕዝብ እናሰልጥናለን" ብለው ለወረራና መስፋፋታቸው ትክክለኝነት ምክንያት ሲያቀርቡ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወቅቱ እነሱ ይጠቅሱ እንደነበረው እጅግም "ኋላ የቀረች" ሀገር አልነበረችም፡፡ በሌላ ወገን በዓለም አቀፍ ውል በማሰር ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር የሞከሩት የብልጣብልጥነት መንገድ አልሰራ ሲል፤ እልፍም ሲል ንጉሡ ውሉን ውድቅ ሲያደርጉት፤ ምኒልክ እንደመሪ ኢትዮጵያዊ እንደ ሕዝብ ንቆኛል ብለው እንዲያስቡ አደረጋቸው፡፡ ለዚህም ጦር መማዘዝን እንደ መፍትሔ ቆጥረው ወረራውን ጀመሩ፡፡
ታሪክን የተረዱበት መንገድ
ከዓድዋው ጦርነት ቀደሞ አጤ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በእንግሊዞች፤ አጤ ዮሐንስ በደርቡሾች መተማ ላይ መረታታቸው ለኢጣሊያ ቀጣይ ወረራ የተመቸና የኢትዮጵያ ህዝብ "ገብር" -ቢሉት የሚቀበል አቅሙ ያልደረጀ "ኋላ ቀር" አድርገው ቆጠሩት፡፡ በአንጻሩ ጣሊያን ከጎኗ ያሉ ትንንሽ ግዛቶችን በማሸነፍ ሀገራዊ አንድነቷን ያወጀችበት ወቅት ስለነበር ኢትዮጵያን ለመዉረር ተጨማሪ የማን ያሸንፈኛል ሥነ-ልቦና ሰጥቷቸው ነበር፡፡
ከዓድዋ ጦርነት በፊት የኢትዮጵያ ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ዳና እንዴት ይገለፃል?
.
ይቀጥላል...
#የጥቁር_ሕዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
* ከላይ ያለው ምስል፦ የጣሊያን ንጉሥ ክሪስፒ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን ቆንፅል የነበረው አንቶኔሊ።
ለወዳጅዎ ያጋሩ @riviben

ሥነ ልቦናዊና ማኅበረሰባዊ ዳራ
•ክፍል ሁለት
" ባትዋጋ እንኳን በል እርገፍ እርገፍ
ያባትህ ጋሻ ትኋኑ ይርገፍ"
፪) ከኢትዮጵያ ወገን
ከዓድዋ ጦርነት በፊት በኢትዮጵያ ወገን የነበረው ማኅበረሰባዊ እሳቤና ሥነ ልቦናዊ ቅኝት ከወራሪያቸዉ የኢጣሊያ ጦር የተለየ ነበር፡፡ ። የአሸናፊነትና የልበ ሙሉነት የሆነ ።
ኢትዮጵያውያን መሪዎችም ሆኑ ተመሪዎቹ ሀገርና ግዛት የፈጣሪ ስጦታ ነው የሚል የፀና እምነት አላቸው፡፡ ኢትዮጵያዊ በርስቱና በሚስት ሲመጡበት አንገትን ለካራ ለመስጠት ያለማመንታቱ ልማድ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። ይህን ሳይረዳ መሬትህን እንዲሁ ነጥቄ ልውሰድ ብሎ የመጣን ባላንጣ መመከት ለኢትዮያውያን የመብትና የክብር ጉዳይ ነበር፡፡ ለዚያም ይመስላል ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሲባል ሳያቅማማ ከያለበት ወደ ዓድዋ የዘመተው፡፡
የህልውና ጉዳይ...
ምኒልክ እንደ ንጉሥ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የመዝለቅ ጥያቄ
በኢትዮጵያ ከዘመነ-መሳፍንት ያልተማከለ አስተዳደር ተወጥቶ እንደሀገር ለመጽናት የተሞከርው ጣሊያን ሀገር ልሁን ብላ በምትታትረበት ዋዜማ እ.ኤ.አ 1855 ዓ.ም ላይ ነበር፡፡ በአጤ ቴድሮስም ይሁን በአጤ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የሀገሪቱ ወሰን በደቡብ ከሸዋ ለማለፍ አልቻለም ነበር፡፡
የየክፍለ ሀገሩ ገዢዎች (የሸዋው ምኒልክን ጨምሮ) ለማዕከላዊ መንግሥት ማደርን አይሹም ነበር፡፡ ይህም የወጭ ጠላት ሲመጣ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር አብሮ ከመቆም ይልቅ የአካባቢውን ገዢነት ማስጠበቅ ላይ ያተኩሩ ነበር፡፡ ለዚህም እንግሊዞች በአጤ ቴዎድሮስ ደርቡሽ በአጤ ዮሐንስ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ የበረታ መከላከል ያልገጠማቸው፡፡፡ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ግን ይህ ተቀይሮ ነበር፡፡ የወስጥ የስልጣን ሽኩቻው ከሞላ ጎደል በመጠቃለሉና ራሶቹም በምንሊክ ስር በመግባታተቸው ኢትዮጵያ ወስጣዊ ሽኩቻዋን አስታርቃ በመገኘቷ በጣሊያን ላይ የሥነ-ልቦና የበላይነት እንዲኖራት አድርጓል፡፡ የቀረ እነኳን ቢኖር ንጉሡ “አመልህን በጉያ ስንቅህን በአህያ” ያሉት ትዕዛዝ የሚገዛው ነበር።
የንጉሡ የስልጣን ቅቡልነት
በአጤ ምኒልክ ጥላ ስር ያደሩት ሀገረ ገዥዎችና ራሶች ለንጉሠ ነገሥቱ ባለ ሙሉ ሥልጣን እውቅና የሰጡ ሲሆን፤ በተማከለው የዘመናዊት ኢትዮጵያ አስተዳደር ውስጥ የየራሳቸውን ግዛት ማስተዳደሩን ብዙሃኑ ተቀብለውት ነበር፡፡ ይህንን አዲስ አሰራር ሊያፋልስ የመጣን ጠላት መመከት አንድም ለንጉሠ ነገሥቱ ያላቸውን ታማኝነት ማሳያ ሁለትም ያሉበትን የየግለ ግዛታቸውን ማጽኛ መንገድ አድርገው ወስደውታል፡፡ ስለዚህም ለሀገርና ለንጉሥ መሞትን ከክብርም በላይ አድርገው በማሰብ አልጋውን ለማቅናት ብዙዎቹ ህይወታቸውን ሰውተዋል፡፡
የንጉሡ ልበ ሙሉነት
አጤ ምኒልክ ጣሊያንን እንደሚያሸንፉት በሙሉ ልባቸው ያምኑ ነበር፡፡ ከክተት አዋጁ ቢጀመር " ……..ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ አልተውህም ማሪያምን………" ሲሉ አቅም እያለው አልዋጋም ያለውን ለማስፈራራትና ስለመቅጣት ብቻ አልነበረም፤ ለመቅጣትም ቢሆን እኮ ወደ ርስተ ዙፋናቸው መመለስ አለባቸው፡፡ ታዲያ ጦርነቱን አሸፈው እንደሚመለሱ በማመናቸው ነበር ወስላታውን በኋላ አማላጅ የለኝም ሲሉ ማሳሰባቸው፡፡ ከዚህም ሌላ እነ ካዎ ጦና፣ አባ ጅፋርን ሀገር ጠብቁ ብለው ከጦርነቱ አለመጨመራቸው ለጣሊያን እኛ መች አንሰነው የሚል መልክት ነበረው፡፡
በመጨረሻም የጦርነቱ መነሻ ኢትዮጵያውያን ለራሳቸው ከሚሰጡት ክብር፣ ጭቆናና ሽንፈትን መጠየፍ፣ ሳያደገድጉ በነፃነት ለኖሮ የማለፍ እሳቤ ጋርም ተዛማጅነት አለው፡፡
በልበ-ሙሉነት የተገራው ኢትዮጵያዊው ተክለ-ስብዕና ተናነሶ መኖርን የሚጠየፍ ነበር ስለዚህም ድንበር ጥሶ አጥር አፍርሶ የመጣን ወራሪ ለመመከት አለማመንታት ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
ሼር ያድርጉ @roviben

#ፍቅር
ፍቅር የደስታ ሁሉ ንጉስ ነው፤
ፍቅር የህይወት መስረት ነው፤
ፍቅር የአዕምሮ ዕረፍት ነው፤
ፍቅር የደስታዎች ሁሉ ምንጭ ነው፤
ፍቅር የመንፈስ እርካታ ነው፡፡
💝💖❤️❤️💜❤️❤️💖💝
Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ፍቅር
ፍቅር የደስታ ሁሉ ንጉስ ነው፤
ፍቅር የህይወት መስረት ነው፤
ፍቅር የአዕምሮ ዕረፍት ነው፤
ፍቅር የደስታዎች ሁሉ ምንጭ ነው፤
ፍቅር የመንፈስ እርካታ ነው፡፡
💝💖❤️❤️💜❤️❤️💖💝
Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#አድዋ
### የዓድዋ ድልና ዳግማዊ ምኒልክ ###
የዓድዋ ድል ያለ መሪዉ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ፈፅሞ ማሰብ አይቻልም ። በእሳቸው የአመራር ብቃት፣ስልትና አርቆ አስተዋይነት የመጣ ነዉና።
....
ከየት ተማሩት?
.
ፕ/ር ጌታቸዉ ኃይሌ "የአፄ ምኒልክ የአመራር ስልትና የአድዋ ድል" በሚለዉ ፅሁፋቸዉ እንዲህ ይላሉ :-
"የምኒልክ አርቆ አስተዋይነት ከምን እንደመጣ ገና ብዙ ጥናት ያስፈልገዋል። ትልቁ ምክንያት ግን በመቅደላ የአፄ ቴዎድሮስ እስረኛ በነበሩበት ጊዜ ከሀገር ሊቃውንትና ከውጭ ሀገር እስረኞች ጋር መጎልመስ ሳይሆን አይቀርም። የአፄ ቴዎድሮስ ጭካኔ ሽንፈትን እንዳስከተለ ስላዩ፥ ተቀናቃኞቻቸውንም በፍቅር አሸነፏቸው። የቅኝ ገዢዎችን ተንኮልና ዲፕሎማሲ አይተው በዘዴያቸው መቷቸው።" ይላሉ።
.....
* የአስተዳደር ጥበብ
አፄ ምኒልክ የአስተዳደር ጥበባቸዉና ነገሮችን የሚመለከቱበት መንገድ እጅግ ብልህነት የተሞላበት ነበር። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከእርሳቸዉ ቀድማ እንደ አፄ ቴዎድሮስና እንደ አፄ ዮሐንስ ያሉ ታላላቅ ነገሥታት አግኝታ የነበረ ቢሆንም እንደ ምኒልክ ግን ጀግንነትን፥ ሃይማኖታዊነትን፥ ብልሃተኝነትን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ አልነበረም። ታዲያ ይህ የአስተዳደር ብልሃታቸዉ ከሹመት አሰጣጥ ጀምሮ እንደነበር አለቃ አፅሜ እንዲህ ፅፈዋል:-
"አፄ ምኒልክ ዘውድ የደፉ ዕለት ከንጉሥ ሥልጣን ሰገድ ሱስንዮስ ጀምሮ የተሠራውን ሠላሳ አምስት ሹመት ለጦር አበጋዞቻቸው ሰጡ። አፄ ዮሐንስም እንደባህሉ አድርገዋል። ሹመቱን የሰጡት ግን ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ነበር። አፄ ምኒልክ ግን ከሌላ አካባቢ ለመጡት ጭምር እንጂ ለሸዌዎች ብቻ አልነበረም።"
አስተዋይነትና ስልት
አፄ ምኒልክ በጣም አስተዋይና ስልት አዋቂም ናቸዉ። በዚህ ስልት አዋቂነታቸዉ ነዉ ጣሊያንን ከራሱ በገዙት ጠመንጃና መድፍ ዓድዋ ላይ ጉድ የሰሩት። ይህንን ስልት አዋቂነታቸዉን ቀድሞ የአፄ ቴዎድሮስ እስረኛ ሆነው ሳለ ከመቅደላ ካመለጡበት ጊዜ ጀምሮ ከአፄ ዮሐንስ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ውጊያ በወቅቱ ያላቸውን አቅም አይተው ከንጉሡ ጋር በአማላጅ የታረቁበት መንገድ ላይ መመልከት እንችላለን ። በተጨማሪም ሸዋ ሲገቡ ግዛቱ ይገባኛል በሚል ሹም ተይዛ ደረሱ። እሱን በጥቂት ሠራዊት ማሸነፍ ትልቅ ዕውቀት ያስፈልግ ነበርና ማድረጋቸውም እንዲሁ የምኒልክን አስተዋይነት አጉልቶ የሚያሳይ ነዉ ።
ሌላኛዉ የአፄ ምኒልክ ጊዜዉን የዋጀ ስልት አዋቂነት ማሳያ አፄ ዮሐንስ በንዴት በሱዳን ደርቡሾች ላይ ሲዘምቱ፥ አፄ ምኒልክ ከደርቡሾች ጋር በእንግሊዞች ላይ የጋራ ግምባር መፍጠራቸው ነዉ። በወቅቱ እንግሊዞች ሪር አድሚራል ሂወትን ልከው አፄ ዮሐንስን እንደቀለዱባቸው፥ ሬነል ሮድን ልከው አፄ ምኒልክን ሊቀልዱባቸው ቢሞክሩ አልተሳካላቸውም። በአንፃሩ አምባሳደር ሬነል ሮድ አፄ ምኒልክ እንደቀለዱበት ያወቀው ወደመጣበት ከተመለሰ በኋላ ነው። ግን እዚያው ባለበት ጊዜ የውል ውይይት ሳይጀምሩ ከማን ጋር እንደሚዋዋል በምልክት ሲያስጠነቅቁት፥ "ጣሊያን ምጽዋን እንድትይዝ ለምን ጋበዛችኋት?" አሉት። ሲሰማ ክው አለ። ምንም ከማያውቅ የዋህ ሰው ጋር የሚነጋገር መስሎት ነበር። የመጣው ኢትዮጵያ ከሱዳን ደርቡሾች ጋር እንዳትስማማ ቃል እንዲገቡለት ነበር። የማይከበር ቃል ያለው እንግሊዝ አገር ብቻ መስሎታል። "ግዴለህም፥ ደርቡሾች የሃይማኖታችን ጠላቶች ናቸው። እኛ እንደናንተ ክርስቲያኖች ነን" ሲሉትና በሰማው ሲደሰት፥ የደርቡሽ መልእክተኞች ከጓዳ ሆነው ይስቁ ነበር። እንግሊዝና ፈረንሳይ በኮሎኒ ሽሚያ ጊዜ በማህላቸው ግጭት እንዳይነሣ ሁለቱ ሀገሮች መስማማታቸውን ንጉሡ ስለሚያውቁ፥ የሱዳኖቹ መልእክተኞች ከመመለሳቸው በፊት የሰጧቸው ምክር፥ "በምሥራቅ (ከግብጽ) እንግሊዞች ሲመጡባችሁ፥ የፈረንሳይ ባንዲራ ሰቅላችሁ ጠብቋቸው። በምዕራብ (በፋሹዳ) ፈረንሳዮቹ ሲመጡባችሁ የእንግሊዝ ባንዲራ እያውለበለባችሁ ተቀበሏቸው" የሚል ነበር።
ታዲያ የተንኮታኮተችውን ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ሌሎቹ ሲሳናቸው አፄ ምኒልክን የቀናቸውም በዚሁ በዘዴኛነታቸው ነው።
.
ይቀጥላል....
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
join

### የዓድዋ ድል እና ዳግማዊ ምኒልክ###
ክፍል ሁለት....
ስልት አዋቂነት እና የዓድዋ ድል
አፄ ምኒልክ በአስተዳደራቸው ስልት አዋቂና አስተዋይ መሆናቸዉ አይተናል። ታዲያ ይህ ችሎታቸዉ በታላቁ የዓድዋ ድል ላይም ይንፀባረቃል። ለዚህም የዓድዋ ድል የተገኘዉ ከዉጊያዉም በተጨማሪ በንጉሡ የጦር አቅድ አውጪነት ነው የምንለዉ ።
እዉቁ የታሪክ ምሁር ዶክተር ሹመት ሲሻኝ ይህን አስመልክተዉ ሲፅፉ "አፄ ምኒልክ የዓድዋ ጦርነት እንደሚነሣ ቀደም ብለው ስላወቁት፥ ሠራዊታቸው ከአዲስ አበባ እስከ ዓድዋ ድረስ ሲጓዝ እንዳይቸገር በሚሰፍሩበት ቦታ ሁሉ አስፈላጊውን ስንቅ ቀደም ብለው አከማችተው ነበር።" ብለዋል
ሌላኛዉ ስልት አዋቂነታቸዉ የታየዉ ዓድዋ ደርሰዉ ለጦርነት ሲዘጋጁ ነበር። የጣሊያን ሠራዊት አፄ ምኒልክ ከምሽጉ ሳይወጣ እንዲገጥሙት ፈልጎ ነበር። አፄ ምኒልክ ግን የመሸገን ሠራዊት በቀላሉ ማሸነፍ እንደማይቻል ከመቀሌዉ ጦርነትና አፄ ዮሐንስ በሰሐጢ ጦርነት ከደረሰባቸዉ ሽንፈት ስለተማሩ ይህንን ከማድረግ ተቆጠቡ።
ከዚያ በተለየ በብልሃት ወደ ጣሊያን ሠፈር ጀግናው አዉአሎም ሀረጎትን ሰላይ ልከዉ "የምኒልክ ሠራዊት ተዳክሟል" ብለዉ አስወሩና ጠላትን በዘዴ ከምሽጉ አስወጡት። ጠላትም የምኒልክ ወሬ እዉነት መስሎት ወደ ሜዳ ሲወጣላቸዉ ጠብቀዉ ወቁት፤ አበራዩት።
አንድ እንጨምር ....
አፄ ምኒልክ የእርሳቸው በሕይወት መኖር ለድሉ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለዉ ከመተማዉ ጦርነት በደንብ ተምረዋል። የታላቁ አፄ ዮሐንስ መዉደቅ ድል አድርጎ ደርቡሽን ሲያሳድድ የነበረዉን የኢትዮጵያን ጦር እንዴት እንደፈታዉና ለሽንፈት እንዳበቃዉ በደንብ ገብቷቸዋል። ስለዚህ ጦርነቱን ከአደጋ ቀጠና ራቅ ብለዉ ነበር የመሩት። በወቅቱ እሳቸዉ ቢሞቱ ኖሮ ዓድዋም ሌላ መተማ መሆኗ የማይቀር ነበር። ነገር ግን ጦርነት ቼዝ መሆኑ የገባቸዉ አፄ ምኒልክ በጥበባቸዉና በጦር ስልት አዋቂነታቸዉ የቼዝ ጨዋታውን በደንብ ተጫዉተዉ ታላቁን የዓድዋ ድል አስመዘገቡ።
....
አፄ ምኒልክ በዚህ ስልት አዋቂነታቸዉና ብልሃታቸዉ ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት ዓድዋ ላይ ድባቅ በመምታት ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በነጻነት የግዛት አንድነቷ ተጠብቆ ዳር ደንበሯ ተከብሮ ለዚህ ትውልድ እንድትደርስና ለኢትዮጵያውያን የትብብር፣ የአንድነት፣ የኩራትና የክብር ምንጭ እንዲሆን አድርገዋል።
ከዚህም ባሻገር የድሉ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ለጥቁሮች ነፃነትና የክብር ፋና ለመሆን በቅታለች፡፡ የዓድዋ ድል ምሳሌነት አፍሪካውያን በቅኝ ገዥዎቻቸው ላይ አንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፣ ለፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ መፋፋምም ጉልህ አስተዋጽኦ አበርከቷል፡፡ ከዚህ አልፎ የዓድዋ ድል ከነጮች ተፅዕኖ ነፃ የሆነ የጥቁሮች የሃይማኖት እንቅስቃሴ እንዲጀመር ምክንያት እስከ መሆን ደርሷል፡፡
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
@roviben @kinchebchabi

የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ.ም.
( የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ያረፈችበት 101ኛ ዓመት)
እቴጌ ጣይቱ በወርሃ ጥር 1908 ዓ.ም ከቤተ መንግሥት ወጥተው እንጦጦ እንዲቀመጡ ከተደረገ በኋላ በእንጦጦ ግቢያቸው ሆነው ከደንገጡራቸው ፈትለ ጋር ከእንጦጦ ቁልቁል የቆረቆሯትን አዲስ አበባ እያዩ ይጫወታሉ....
ጣይቱ... ያ... ከግቢ በወዲህ መሐል ከኪዳነ ምህረት በስተግራ ያለው ዛፍ ይታይሻል?
ፈትለ... አዎ እመቤቴ
ጣይቱ... ከሱ እልፍ ብሎ የሚታየው ጉልላት የየትኛው ነው?
ፈትለ... እ! እሱማ የእቴጌ እልፍኝ... የእመቤቴ ግምጃ ቤት ነበር... ከጌቶች ጋር የብቻ ምክክር የሚያደርጉት ከዚያ ነበር...
ጣይቱ... ነበር!አየሽው ነበር እንዲህ ቅርብ ነው!
አይደረስበት የሚመስለው በሃሳብ ገመድ ሲለካ
እንዲህ ለብቻ ሲመትሩት "ነበር" ቅርብ ኖሯል ለካ!!
ከኢትዮጵያ ሀገሬ በቀር
ስም የሚያስጠራ ልጅም የለኝ!
የትላንትና ኃያል ብርቱ
ዛሬ ግን ደካማ ሴት ነኝ።
ሠላሳ ዘመን ሙሉ ደክሜ
"ነበር " ብቻ ነው የተረፈኝ!
ህም.... ጣይቱ ልጅ የለኝም አለች! የሷ ብርታት ለስንቶቻችን ምሣሌ እንደሆነ... ስሟን መስማት ብቻ ልባችንን እንደሚያሞቀው እና እንደሚያጀግነን አላወቀች! ምንአልባት ነፍሷ ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተክቶ አሁን ላይ የስንቶቻችን ብርታት እና ንግሥት እንደሆነች አይታ ፈገግ ትል ይሆናል! ማንያውቃል! የኛ ጣይቱ! በበገና ተካዥቱ!
የዛሬው ቀን ይህች ዕንቁ ንግሥት ያረፈችበት ቀን ነው። ነፍስሽን በአፀደ ገነት ያኑርልን ንግሥት ሆይ!
ለፅሑፉ መነሻችን የጌትነት እንየው እቴጌ ጣይቱ ታሪካዊ ተውኔት ነው።
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
join @kinchebchabi

የዓድዋ ድልና እቴጌ ጣይቱ
1. ቅድመ ጦርነት
የዓድዋ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ሃገር እስክትረጋና የጦር መሳሪያ እስኪሠበሠብ ድረስ አፄ ምኒልክ ከኢጣልያ ጋር የነበረውን ግንኙነት ፍፁም ብልጠት በተሞላበት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሲያስኬዱት ነበር።
እቴጌ ጣይቱ ከእርሳቸው በፊት ከነበሩትም ሆነ ከሳቸው በኋላ ከመጡት እቴጌዎች የሚለዩት በመንግስቱ ሥራዎች ውስጥ እየገቡ ያማክሩ፣ ታላላቅ ሃገራዊ ጉዳዮችንም ከንገሡና ከመኳንንቱ ጋር በመምከር ውሳኔ እንዲተላለፍም ያደርጉ ስለነበር ነው።
ለዓድዋ ጦርነት መነሳት ትልቁን ሚና የተጫወተው የውጫሌን ውል ጉዳይ ሊያስፈፅም የመጣው የአጣልያ ቆንስላ ኮንት አንቶሎኒ በአንቀጽ 17 ተቃውሞውን አሠምቶ ኢጣልያ ጦርነት እንደምታስነሳ በምኒልክ ቤተመንግስት ውስጥ ሲፎክር እቴጌይቱ የመለሱለት እንዲህ በማለት ነበር
“ … የዛሬ ሳምንት አድርገው፡፡ እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ እግሩን ለጠጠር፤ ደረቱን ለጦር አስጥቶ፤ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ፤ ለአፈሩ ክብር ለብሶ፤ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጵያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን፡፡ ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ጊዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ፡፡”
ይሄ የእቴጌይቱ ንግግር በወቅቱ ያሳደረው ጫና ቀላል የሚባል አልነበረም ለአብዛኛው ዘማች አርበኛ " ሴቷ እንኳን ......" የሚል እሳቤን በውስጡ እንዲኖር ሲያደርግ በተጨማሪም ለኢጣልያ ጦር የሠጠው ግምት አናሳ እንዲሆንና ድል ማድረግ እንደሚችልም ውስጡን እንዲያሳምን አድርጎታል። እዚህ ንግግር ላይ ለሃገር ያላቸውን ከፍ ያለ ፍቅር ያሳያል አይደለም የሃገር ዳር ድንበሯ ተነክቶ ይቅርና ዘለፋን እንኳን መቋቋም የማይችል አመለካከት እንደነበራቸውም ያሳያል ......ሃገሬ እንደዚህ ያለክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ ....
2. ጦርነቱ ላይ
በዓድዋ ጦርነት እቴጌይቱ በራሳቸው በኩል 5,000 ጦር ይዘው የዘመቱ ሲሆን በተጫማሪም ስንቅ በማዘጋጀት፤ የደከመውን በማበርታት፤ የቆሠለውን በማከም፤ የሚሸሸውን በመገሰፅ ታላቅ ተጋድሎን ሲፈፅሙ ውለዋል።
የዕለቱን የእቴጌይቱን ውሎ ጸሃፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ እንዲህ ይተርኩታል
....... በዚህ ቀን በዓድዋ በዐይናችንን ያየነውንና በዦሮአችን የሠማነውን ለመጻፍ ችግር ነው። በዚህ ጊዜ እቴጌ ጣይቱ በማጅራታቸው ድንጋይ ተሸክመው በጉልበታቸው ተንበርክክከው በጋለ ፀሎት ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር። እቴጌ ጣይቱ ጥቁር ጥላ አስይዘው አይነርግባቸውን ገልፀው ወደፊት ጉዟቸውን ቀጠሉ። ወዲያውም የኋላው ወታደር ሲያመነታ አይተው "በርታ ምን ሆነሃል ድሉ የኛ ነው በለው" በማለት ሲያበረቱ ሁሉም ወደፊት ገፋ። እቴጌይቱ በዚህን ቀን የሴትነት ባህሪያቸውን ትተው እንደወንድ ወታደሮቻቸውን በግራና በቀኝ አሠልፈው ወደ ጦርነቱ ገቡ። ቁስለኛና ምርኮ የያዘውም ወደኋላ ሲመለስ ባዩት ጊዜ "ንጉሡ ሳይመለሱ ወዴት ነው የምትመለሱት? ምርኮኞቻችሁንና ቁስለኞቻችሁን ለኔ ስጡኝና ተመለሱ ....... በማለት ጦሩን ያበረቱ ነበር።
ከውጫሌ ውል ጀምሮ ያልተለዩትና በኢጣልያኖች ሃሳብ ሲናደዱ የቆዩት እቴጌይቱ የቁርጡ ቀን ሲመጣ
በፈጣሪ በጣም ይታመኑ ስለነበር በፀሎት መጀመራቸውን ጦርነቱ ሲፋፋምም ይዘው የዘመቱትን 5000 ጦር ይዘው መሃል ገብተው ያዋጉ እንደነበር በመጨረሻም ቁስለኛን ሲያክሙ የደከመውንም ሲያበረቱ በመዋል ታላቅ ስራን ፈፅመዋል። ከዚህም በተጨማሪ እቴጌይቱ ለኢትዮጵያው ዘማች ብቻ ሳይሆን ለኢጣልያኖቹም ምን ያህል ሩህሩህ እንደነበሩ ማሳያው ምርኮኞቹን ጥለውላቸው ከሄዱ በኋላ እንደ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ጣልያኖቹንም በማከምና ውሃ በመስጠት ሲንከባከቡ እንደነበር ተፅፎ ይገኛል ይሄም ምን ያህል ይቅር ባይ ልብ እንደነበራቸው ያሳያል። ከጦርነቱ ፍፃሜ በኋላ የኢትዮጵያ አርበኛ ሲጨፍር "አዳም አዳምን ገደለና ይሄ ሁሉ ደስታ ለምን ነው?" የሚለው ንግግራቸው ምንም ጠላት ቢሆኑ እንኳን በሠው ልጆች ሞት መደሰት እንደማይገባ የሚያሳይ ነው።
ሃገር በምን አይነት መስዕዋትነት እንደቆመች አንዘነጋም።
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#victoryofAdwa

እቴጌ ጣይቱ ዐጤ ምኒልክ በሞቱ ጊዜ ያሰሙት የኀዘን ግጥም
ነጋሪት ማስመታት ነበረ ሥራችን
እምቢልታ ማስነፉት ነበረ ሥራችን
መለከት ማስነፉት ነበረ ሥራችን
ሰው መሆን አይቀርም ደረሰ ተራችን!
እቴጌም ተራቸው ደርሶ የካቲት-4 1910 ዓ.ም አረፉ፡፡ ነፍስ ይማር፡፡
ምንጭ- ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴ፣ ጣይቱ ብጡል-ገጽ-100

ቅንጭብጭብ
Photo
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
#አድዋ
#### ዓድዋ ድል እና ሴቶች ####
" ዳኘው በዲሞትፈር በለው በለው ሲል
የቃኘው መኮንን ደጀኑን አፍርሶ ጦሩን ሲያደላድል
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጎጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል ለቆሰለው ጀግና ውሃ ስታቀብል
እንዲህ ተሠርቶ ነው የዓድዋው ድል።"
የዓድዋ ድል የሀገሬው ህዝብ ጀግንነት እና ቆራጥነት ውጤት ብቻ አይደለም። መልከኣ ምድሩ ለዘማቹ ደጀን ሆኗል፣ እንሰሳት ጓዝ ተሸክመው፣ ጋልበው ጦረኛውን አዋግተዋል።
ስንቁም በማሰናዳት፣ ለተጠማ ውሃ በማቀበል፣ የደከመው አይዞህ በማለት ያበረቱ ነበር ሴቶች። ይህንን እውነታ በልጅነታቸው ከራስ መኮንን ጋር አብረው የዘመቱት ፊታውራሪ ተክለ ሐዋሪያት በመፅሐፋቸው እንዲህ ይተርኩልናል....
... አጎቴ አለቃ አብዩ ( የዚያን ግዜ ሳያደብርን ለቀዋል) መስተንግዶ ለራስ አመጡ። ለታላቅ ወንድሜ ላብዩም ስንቅ አመጡለት ደግሞም ለጭነት አንድ አጋሰስ አንድ ሴት አገልጋይ ሰጡት። ሴት አገልጋይ የተባለችው( የቤት ውልድ ነች ወለተ አማኔል የእንኮዬ ወለተ ማርያም ልጅ ከኛው ጋር ያደገች ነች። ) ከዘመቻው ላይ በጣም አገለገለች ከቶ እሷ ባትኖር እንዴት እሆን ኖሯል እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያስደንቀኛል... ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች ከሰፈርን በኋላ ውሃ ቀድታ እንጨት ለቅማ ቂጣ ጋግራ ወጥ ሠርታ ታበላናለች። ወዲያው እንደዚሁ ለማታ ታሰናዳለች።
እንደዚህ የወለተ አማኔልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደዚህ እንደሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎቹ አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው የአድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልግሎትና በበቅሎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል።.....

ከደጃዝማች ግርማቸው ተክለ ሐዋሪያት " አድዋ ታሪካዊ ድራማ " ከተሰኘው መፅሐፍ ላይ ለዛሬ እነዚህን ቀንጭበን ስንኞችን እንዲህ አመጣናቸው…
ራስ መኮንን
ኢትዮጲያ እንድትኖር ሳይነካ ክብሯ
እንኳንስ ወንዶቹ ትዋጋለች ሴትዋ።
ሀገር የሚያጠቃ ጠላት ከተነሳ
ሀበሻ ይቆጣል ይሆናል አንበሳ።
የኢትዮጲያ ጀግኖች ላገር ይሰዋሉ
ተዋርዶ ከመኖር ሞትን ይመርጣሉ።
ራስ ሚካኤል
ሀበሻ ጀግና ነው ሞትን የማይፈራ
በአባ ቶቹ ሙያ በራሱ የሚኮራ።ላገሩ ለቤቱ ለክብሩ ለመብቱ
ማነው የማይፋለም እስክታልፍ ሕይወቱ።
ሊቀ መኳስ አባተ
የዳኘው አሽከር የይትረፍ ጌታ
ጠላቱን ሳይ ጥል የማይመለስ
አባሮ ገዳይ በግር በፈረስ።መድፍ ተኩሶ ከወንዙ ማዶ
ጠላት የሚገድል ከሩቅ አሳዶ።
ላገሩ ጠላት ምህረት የሌለው
ፊት ለፊት ሄዶ ልግጠም የሚለው!
ላገሩ ታማኝ አባተ ቧለው!
በጅሮንድ ባልቻ
የዳኘው ባሪያ ባልቻ አባ ነፍሶ
አባሮ የሚጥል ከሩቅ ተኩሶ።
በየጎራው ላይ
እኔ ልግጠም ባይ
ያገሩን ጠላት አሳዶ ገዳይ!
ፊታውራሪ ገበየሁ
የዳኘው ባሪያ የማይጠረጠር
ደሙን ያፈሳል ይሞታል ላገር።
የጠላቱን ጦር ያበላል አፈር።
የዳኘውአሽከር ሞትን አይፈሬ
እኔ ገበየሁ የጎራው በሬ።
ራስ አሉላ አባነጋ
ዘራፍ አሉላ በር ጠባቂው
አሉላ ቱርክ አስጨናቂው!
አላሳልፍ ባይ
በየኬላው ላይ።
የበዝብዝ አሽከር የማይበገር።
አፄ ምኒልክ
እኔ ንጉሳችሁ ሀገሬን አልሰጥም
በህ ይወቴ ሳለሁ ጠላት አይዛትም።
ቴዎድሮስ በመቅደላ በመተማ ዮሐንስ እንደተሰዋላት
እኔም ቆርጫለሁ ደሜን ላፍስላት።
ለማንም አልገብር አይገዛኝም ጠላት
ተነስ ታጠቅ ጎበዝ ላገርህ ሙትላት!