ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️::::::::::::የሰዉ ልጅ::::::::::::⚡️

የሰው ልጅ ትንሽ ስህተት ከሰራህ
ያሳለፍካቸውን ውብ ነገሮችን እንዳለ
እንዳልሰራህ አድርገው ያፈርሱታል‥

ከአላህ (ሱ.ወ) እዝነት ስፋት ደግሞ
አንዴ ባደረግካት እውነተኛ ተውባ ሰበብ
ያሳለፍካቸውን መጥፎ ወንጀሎችህን ሁሉ
እንዳልነበሩ ያብሳቸዋል/ወደ መልካምም
ይቀይራቸዋል።

📐:::::::::::: ቴሌግራማችን::::::::::::📐

https://t.me/ketibeb
👍43🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❥::::::::::::::::ሀያዕ::::::::::::::❥

☞☞ሀያዕ ከኢማን ነው!! ሀያዕ ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም ሀያዕ ነው!!

#እህቴ__ሆይ!👇👇

☞ሰላት የጋብቻ ዋነኛ መስፈርትሽ ይሁን!!
ለፈጠረው አምላክ ያልተናነሰ፣ ለነብሱ ያላዘነና ትእዛዝን ያላከበረ ሰው ላንቺ የሚያስብና የሚራራ አይሆንም!!

አላህን ከወደድሽ ወዳጆቹን ትወጃለሽ ለትእዛዛቱ እጅ የማይሰጡ ፋሲቆችን ትጠያለሽ፣ ትርቂያለሽም!! ሰው እንደውሎው ነው!!

📩::::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::📩

https://t.me/ketibeb
👍71
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❥:::::::::::: ልብ በል:::::::::::❥

☞ችግርህን አላህ ካልፈታው ገንዘብ ችግርህን አይፈታውም አላህ ካልሞላው ሰው ጎንህን አይሞላውም አላህ ካልገለጸልህ እውቀት ጥበብ አይሆንም

ይቺ ዓለም ለሁሉም እኩል ናት፡፡ ዛሬ ብታገኝ ነገ ታጣለህ ዛሬ ብታሸንፍ ነገ ትሸነፋለህ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚባል መዶሻ አለ፡፡ መልካምነት ዋጋ ያስከፍልሃልና ሁሌም ፍጹም መልካም ሰው ሁን

ህይወትህ ትርጉም እንዲኖራት ዓላማ ይኑርህ፡፡

የአንተነትህ ትልቁ ምዕራፍ ከእውቀትህ በላይ ስራህ መሆኑን አትርሳ፡፡

ንጹህ ልብ ልክ እንደ አበባ ናት! ፍሬ ባናገኝባትም ውበቷ ግን እጅግ ማራኪ ነው፡፡
:
የውድቀት መጀመሪያ ራስህን አዋቂና ብቸኛ አድርጎ ማሰብ ነው

ፍጻሜህ እንዲያምር ራስህን አታመጻድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመታረም ፈቃደኛ ሁን ጥፈፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሰልህ፡፡

ጠቢብ ሰው እንኳን ከራሱ ከሰው ስህተት ተምሮ ራሱን ይጠብቃል ይመለሳልና፡፡

በህይወት ውስጥ አንዱ ሲታወር አንዱ መሪ መሆን አለበት

እውነትነ የሚናገር ሰው አፉ ክፉ ይመስላል ልቡ ግን ንጹህ ነው

ህይወት በመደጋገፍ የተሞላች ናትና ወንድምህን ለመርዳት ወደሗላ አትበል!

📩:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::📩

https://t.me/ketibeb
2👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍1
()اللـهـمَّ ﷺصَـلِّﷺوَسَـــلِّـمْ ﷺ وَبَارِك ﷺْ عـلـى ﷺ نَبِيِّنَـــا ﷺ مُحــمَّد
┊┊┊┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
┊┊┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
┊┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
መልካም ጅምዓ 🌹

https://t.me/ketibeb
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የወንጀል መዘዙ ከባድ ነው በተለይ እያወቁ ሲያጠፉ!

(وَلَوْ يُؤَاخِذُ اللَّهُ النَّاسَ بِمَا كَسَبُوا مَا تَرَكَ عَلَىٰ ظَهْرِهَا مِنْ دَابَّةٍ وَلَٰكِنْ يُؤَخِّرُهُمْ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِعِبَادِهِ بَصِيرًا)

"አሏህ ሰዎችን በሰሩት በደልና ወንጀል ሁሉ እዚሁ ዱኒያ ላይ የሚቀጣቸው ቢሆን ኖሮ ምድር ላይ ማንንም ሳያስቀር
-ወንጀል የሰሩትንም ያልሰሩትንም እንስሳትንም ጭምር- ባጠፋቸው ነበር
ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ያቆያቸዋል አጀላቸውም ሲደርስ እርሱ የባሮቹን ምንነት ጠንቅቆ በሚያውቀው መሰረት የስራቸውን ይሰጣቸዋል" አል ፋጢር 45

https://t.me/ketibeb
👍42
አዲስ ልብወለድ በቅርቡ ወደናንተው አደርሳለሁ።

ማነው ዝግጁ? 💝
4
የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም በድምፅ.apk
83 MB
የጁሙዓ + የረመዳን ስጦታ እነሆ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ቁርአን የአማርኛ ትርጉም
ድምጽ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ተዘጋጅቶ ተለቀቀ!

በተጨማሪም በቅርቡ በplay store እና በApp store ላይ ማግኘት ይችላሉ!

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
👍43
ወዳጆቼ የአላህ ሰላም እና እዝነት በናንተ ላይ ይሁን
ኢድ ሙባረክ
በቅርቡ እንገናኛልን ኢንሻ አላህ!
2👍1
ጣፋጭ የአላህ ጥሪ .....


۞ وَسَارِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَغْفِرَةٍۢ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ

۞ ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡

۞ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ ۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

۞ ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ( ተደግሳለች ) ፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል ፡፡

۞ وَٱلَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا۟ فَٰحِشَةً أَوْ ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا۟ ٱللَّهَ فَٱسْتَغْفَرُوا۟ لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلُوا۟ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

۞ ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች) ፡፡

۞ أُو۟لَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُم مَّغْفِرَةٌۭ مِّن رَّبِّهِمْ وَجَنَّٰتٌۭ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا ۚ وَنِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ

۞ እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች! ፡፡

سورة آل عمران ( 133 - 136 )
👍51
ጠፊዋ ዱንያ



ቀን ቀን የደከምንለት ሌት ሌቱን የቃዠንለት ሃብትና ንብረት አመድ መሆኑ አይቀሬ ነው! ! እንኳን ተሰብሳቢው ሰብሳቢውም አይቀርለት!!
كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍۢ
በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡

ያለ የሌለንን ሁሉ ጥለን ወደ ዘላለማዊው የአኺራ ኑሮ የምንጓዝበት አንድ ቀን ከተፍ ማለቱ አይቀሬ ነው! የዛኔ አሳደን ያጠራቀምንው ሸቀጥና ገንዘብ ከአስከፊው የቀብርና የጀሃነም ቅጣት አያድነንም ። ከአላህ እዘነት ጋር መልካም ከለላ የሚሆነን ተውሒዳችንና በትእግስት ያካበትንው መልካም ስራ ነውና ያለፈውን ሁሉ ሊምር ቻይ ወደሆነው الله እንመለስ እና መልካም ስራዎችን እናካብት!!
አላህ በተከበረው ቁርአኑ በዱንያ ላይ የለገሰልንን ሁሉ ጥለን ቤሳቢስቲን ሳይኖረን እሱን የምንገናኝበት ቀን እንደሚመጣ እንዲህ በማለት ያስታውሰናል ፣
وَلَقَدْ جِئْتُمُونَا فُرَٰدَىٰ كَمَا خَلَقْنَٰكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَتَرَكْتُم مَّا خَوَّلْنَٰكُمْ وَرَآءَ ظُهُورِكُمْ ۖ ...
መጀመሪያም ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ኾናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ ለየብቻችሁ ኾናችሁ በእርግጥ መጣችሁን ....
ያለፈው ሁሉ አልፏል በዱንያ ሸቀጦች መታለላችን ይብቃና ወደ አላህ እንመለስ — ፈጣሪያችን አዛኝና መሃሪ ነው!!
አላህ ይምራን!!
👍8🥰2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረከቱህ ?? ዉድ የጥበበ ሉቅማን ቻናል ተከታታዮች እንደምን ከረማችሁ?? ጠፍን አይደል በጣምይቅርታ? ከዚህበኋላ አዳዲስ አስተማሪ መጣጥፎን ታሪኮችን የምናቀርብ ይሆናል ወኢንሿአላህ
👍9🥰2👏21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍4
#ሁለቱ_ልጃገረዶች

#ክፍል_አንድ


ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ወደዚህች ምድር ከመምጣታቸው በፊት ሁለት ወዳጅ የሆኑ ልጃገረዶች መካ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህ እጅግ ቅርብ የሆነ ወዳጅነት የነበራቸው ልጃገረዶች አሚና እና ኸዲጃ ይባላሉ። መካ የተቆረቆረችው ግብፅን፣ ፍልስጤምን፣ ፋርስን፣ ሜሶፖቶሚያን፣ ህንድንና አፍሪካን በሚያገናኙና የአካባቢው አገራት ቁልፍ የንግድ መዳረ በነበሩ መንገዶች ላይ ነበር፡፡ በወቅቱ ከመላው ዓለም የሚመጡ የተለያዩ ሸቀጦች የሚቀርቡበት ዓመታዊ የገበያ ልውውጥም በዚሁ አካባቢ ይካሄድ
ነበር። እዚያው መካ ውስጥ ደግሞ ሰዎች አንድ ፈጣሪን ብቻ ያመልኩበት ዘንድ በኢብራሂምና እስማኢል የተገነባው ጥንታዊው የአላህ(ሱ.ወ) ቤት ካዕባ ይገኝ ነበር፡፡

ካዕባ በዓለም ውስጥ ከሚገኙት እጅግ ጥንታዊ የሆኑ ህንፃዎች ሁሉ ቀዳሚው በመሆኑ የመላው ዐረብ ህዝብ የኩራት ምንጭ ተደርጎም ይወሰድ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን ዐረቦች የኢብራሂምን ንፁህ የሆነ እምነት በመዘንጋት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ጣኦታት አንፀው በዚህ ታሪካዊ የካዕባ ህንፃ ውስጥ በማኖር ያመልኩ ነበር፡፡ እናም ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ ሸቀጡን ገበያው ላይ በማቅረብ ለመሸጥና ለራሱ የሚፈልገው ካለ ደግሞ ከሌላው ለመሸመት እንደዚሁም በአላህ ቤት ካዕባ በመገኘት የሐጅ ስረዓተ-ጸሎትን ለመከወን በየዓመቱ ወደመካ ይጎርፍ ነበር፡፡ በዚሁ ወቅት የተለያዩ ገጣሚያን የግጥም ድርሰቶቻቸውን በማንበብ እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩበት ትርኢትም የተለመደ ነበር፡፡ መንገደኛ የታሪክ ተራኪዎችም ከየመጡባቸው አካባቢዎች ያጠናቀሯቸውን አዳዲስ ዜናዎች እንዲሁም ከያኒያን ልዩ ልዩ የጥበብ ክህሎቶቻቸውን ከተለያየ የዓለም ክፍል መካ ላይ ለተሰባሰበው ህዝብ ያቀርቡ ነበር፡፡ በወቅቱ እነዚህን ክዋኔዎች በምታስተናግደው መካ ህይወት ደስ የሚል ነበር፡፡

በዘመኑ የአረብ ማህበረሰብ ዝናንና እውቅናን ለመጎናፀፍ ዘወትር
የሚጠመድበትን የውድድር ህይወት ከግብ ለማድረስ እገዛ ያደርጉልኛል በሚል እምነት ለወንድ ልጆች ይሰጠው የነበረው ቦታ የላቀ፤ ለሴት ልጆች ነበረው ክብርም ሆነ ፍላጎት ደግሞ እጅግ የወረደ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ሚስቶቻቸው ሴት ልጅ በሚወልዱ በአብዛኛዎቹ የዐረብ አባቶች ዘንድበከፍተኛ ሐፍረት መሸማቀቅ አሊያም በብስጭት ቤተሰቡን ማወክ በወቅቱ የተለመደ ሁኔታ ነበር። በዚህም ሳያበቁ አባቶች የሚወለዱ ሴት ልጆቻቸውን ከነህይወታቸው በመቅበር ያስወግዷቸው ነበር፡፡ ያም ሆኖ የዚሁ ማህበረሰብ አባል የሆኑት ሁለቱ ባልንጀራ ልጃገረዶች ግን የገጠማቸው የህይወት እድል የተለየ ሆነ፡፡

ባለፀጋ ከሆኑ የተከበሩ ቤተሰቦች የተገኙት አሚና እና ኸዲጃ በወላጆቻቸው ዘንድ በእጅጉ የሚወደዱ ነበሩ፡፡ እናም በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈፀሙትን መልካምም ሆነ ክፉ ተግባራት በዓይናቸው እየተመለከቱ ነበር ያደጉት፡፡

በወቅቱ ጣኦታትን የሚገዛው ሁሉም የመካ ህዝብ አልነበረም፡፡
ጥንታዊ የእምነት መጽሐፍትን የሚያነቡ ፧ ህግጋቱንም አጥብቀው
የሚተገብሩና ከፍልስጤም፣ከየመንና ከየስሪብ የመጡ ሰዎችም መካ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ከዚህም ሌላ ነብዩላህ ዒሣን የሚከተሉ
ክርስቲያኖችም ከመካ ነዋሪዎች መካከል ነበሩ፡፡ የክርስትና እምነት
መጽሐፍትን ጠንቅቆ ያጠናው አላህን፣ ነብያቱን፣ መላኢካዎቹንና
የመጨረሻውን የፍርድ ቀንን በተመለከተ አያሌ እውቀቶችን ያካበተው የኸዲጃ የአጎት ልጅ ወራቃ ቢን ነውፈል በወቅቱ መካ ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር ከመካ ህዝብ መካከል የይሁዳ ወይም የክርስትና እምነት ተከታዮች ሳይሆኑ እንደ ኢብራሂም አንድ አምላክን በመፈለግ ዘወትር ለእርሱ ብቻ የሚፀልዩ ሰዎችም ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች "ሐነፊዎች" በሚል
ስያሜ ነበር የሚጠሩት፡፡
👍3611👏9🥰1😱1
☝️☝️ሁለቱ ልጅ አጎረዶች ይቀጥላል ኢንሻአላህ
━─━────༺༻────━─━
👍18
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3