ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ዘጠኝ(9)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

ጋሽ አይሀም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ቆሞ ሰላምታ ከሰጠ ቡሗላ መክፈቻ ቢጤ ንግግር አደረጎ ዛሬ አዲሱን የድርጅታችንን.....
.......ዛሬ አዲሱን የድርጅታችንን ስራ አስኪያጅ ላስተዋውቃችሁ አቶ ቩራል ነምሩድ ይባላል ከአሁን ቡሗላ ስለ ድርጀቱ ማንኛውንም ነገር እሱ ነው የሚመለከተው ከሱ በላይ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ናቸው ወደ እኔ የምትመጡት ብሎ ንግግሩን ቋጨ፤.. ከዛም ሁሉንም መተዋወቅ ጀመርኩ አንዱ ነኢም ሌላው አሲም ምን ልበላችሁ ሰምቸቻቸው የማላቃቸው ስሞች በአይነት ተዘረዘሩልኝ ከተላላኪና ፅዳት እስከ አዛዥ አንድ በአንድ ስም ተለዋወጥን በሉት ከዛም እንደጨረስኩ ጋሽ አይሀም....ፀሀፊዋስ የት ነች አለ ከመሀል አንድኛው ተነስቶ የምታዘጋጀው ሪፖርት ስላላት በጧት ነዉ የገባችው አለ፤
....እሽ! ቩራል ወደ ቢሮህ እንሂድ አለኝ እሽታዬን ነግሬ ወደ ቢሮው አመራን እንደደርስንም፤
ከኮምፒውተር ላይ አንገቷን የደፋች ልጅ ተቀምጣለች ይቺ መሆን አለባት ፀሀፊዋ እያልኩኝ ወደ ዉስጥ ገባን

ከተደፋችበት ቀጥ አለችና የበሩን መከፈት በድምፅ ሰምታ በሚያምር ፈገግታ....እንኳን ደህና መጣቹህ አቶ አይሀም አለች ዉስጤ ደነገጠ ልጂቱ አዲስ አልሆነችብኝም ከዚህ በፊት የማዉቃት አይነት ስሜት ተሰማኝ ከዛም ጋሽ አይሀም ሰላም አላትና እኔ አዲሱ አለቃዋ እንደሆንኩ ነገራትና ቀድሞኝ ወደ ቢሮው ገባ ..ከዛም ጠጋ ብዬ እጄን ዘረጋሁና ስሜን ስነግራት በአንድ ጊዜ ያፈገግታዋ ጠፋ ሁኔታው ሁላ በአንዴ ተቀያየረ ምን ነካት እያልኩ በተንቀጠቀጠ ድምፅ መ...መ...#መይሙና እባላለሁ አለችኝ ዉስጤ ይበልጥ ፍርሀት ተሰማው መልስ ሳልመልስላት አንገቴን ነቅነቅ አድርጌ ወደ ቢሮዉ ገባሁ እሚገርም ነው ሁሉም ነገር የተሟላለት ቢሮ ነው ጋሽ አይሀምም ወደድከዉ አለኝ አዎ በጣም ያምራል ምን ነው የነበርኩበትን ረሳሀው እንዴ አልኩት ለውጥ ግድ ነው ደግሞ መይሙና ጎበዝ ልጅ ናት ምንጊዜም በስራ መጠመድን ትመርጣለች ስለዚህ እምትፈልገውን ነገር ሁሉ ጠይቃት ታስረዳሀለች አለኝ

እኔም እጄን አገጬ ላይ አድርጌ ራሴን እየነቀነኩ ወዲያ ወዲህ እተንጎራደድኩ ሳለ የጋሽ አይሀም ስልክ ጠራ አነሳና ላዉድ ስፒከር ላይ አደረገውና #ሀሎ አይሀም ጓደኛዬ እንዴት ነህ ከማለቱ ካርመላ መሆኑን አወኩ ከዛም ወደ ስልኩ ጠጋ አልኩ በደምብ ለመስማት እሱም ጉራውን ጀመር #አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾምክ አሉ ምን ነው አይሆንልህ አለ እንዴ አለ ኮራ ባለ ድምፅ
ጋሽ አይሀም ዝምታን መረጠ ካርመላ ግን ወሬውን ቀጠለ እስኪ እናየዋለን አንተ ጋ መቀጠል እንደሚችል ለማንኛውም የሞተው ጓደኛችን እጣ ፈንታ እንዳይደርስህ አለዉ እና ዘጋው፤....ሁለታችንንም በፈገግታ ተሞላን ምክንያቱም አሁን ወደ እቅዳችን ለመግባት ዳር ዳር እያለ ነዉ ቩራል ደግሞ ድርጅቱ ውስጥ የሱ ሰዎች ስላሉት ጠነቀቅ በል አለኝ ጋሽ አይሀም""
..ከዛ ቡሗላ የተለያዩ መረጃዎችን እያየሁ የመጀመሪያ የስራ ቀኔን አሳለፍኩ ምሳም ከህንፃው ፊትለፊት ካለው ካፌ ነበር የበላሁት ከስራ ቡሗላ ወደ ቤት ስመለስ ለሲትና ጣፋጭ ነገሮች ገዝቼላት ስለነበረ በጣም ደስ አላት የሷ ደስታ ደግሞ ለኔ እርካታ ተሰማኝ እናም ከዛን ቀን ጀምሮ እየገዛሁ ለመምጣት ለራሴ ቃል ገባሁ ከዛም ራት በልተን ወደምኝታችን ሄድን

#የመይሙናን ሆኔታ ግን እያሰብኩ ግን መተኛት አልቻልኩም ለምን ደነገጠች ፈገግታዋስ ለም ባንዴ ተለወጠ ምን አልባት ግን የኔ መይሙና ብትሆንስ ብዬ አሰብኩ እሷ እስካሁን የስንት ልጆች እናት ትሆን ይሆናል #የኔ መይሙና ያልኳችሁ ከአመታት በፊት ተማሪ እያለሁ በፍቅሯ ክንፍ የምልላት ልጅ ነበረች ስለሷ ከጀመርኩ ማቆሚያ የለኝም ለነገሩ እሷ አትሆንም ብትሆንም እስከ አሁን አትጠብቀኝም ግን ብትሆንስ ምክንያቱም ወይዘሪት ናት ብታገባ ኖሮ ደግሞ እያልኩ ሳሰላስል እንቅልፌን አጥቼ አደርኩ፤ ያው እንደተለመደው መታጠብ መብላት ከዛ ወደ ስራ መሄድ ቢሮ ደግሞ መይሙና ጋር ከስራ ጉዳይ ውጭ ለማውራት መፈራራት ከስራ መልስ ደግሞ መኪና መለማማድ ወደ ቤት ስገባ የሲቱን ደስታ እያያየሁ መደሰት የዕለት ተግባሬ ሆነ ፤

....ዛሬ ስራ ከጀመርኩ ሁለት ሳምንታት አስቆጠርኩ መንጃ ፈቃዴ ከመምጣቱ ውጭ ሌላ የተፈጠረ ምንም አዲስ ነገር የለም ስለ መይሙና ግን በግልፅ ላዋራት ወስኛለሁ እዉነቱን አውቄ ቁጭ ማለትን መረጫለሁ እናም የቢሮውን ስልክ አንስቼ ደወልኩና ሰላም ወይዘሪት መይሙና አንድ ጊዜ ቢሮ ነይ የማናግርሽ ጉዳይ አለኝ አልኳት እሽ ብላ መጣችና፤ ምን ልታዘዝ አቶ ቩራል አለችኝ ሚስኪን ታዛዦቼ ግን በዙብኝ እስኪ አረፍ በይ አንድ እንቅልፍ ያጣሁበት ነገር አለ እሱን ላማክርሽ እና በግልፅ እንድትነግሪኝ ፈልጌ ነበር ፤የምታዋሪኝ ግን እንደ አለቃሽ ሳይሆን እንደ ጓደኛሽ አልኳት በፈገግ እሽታዋን ነገረችኝ ከዛም ቀጥታ ወደ ገደለው ለመግባት አፌ እየተያያዘ አ.. አ.. አንች እኔን ስታዪ ለምንድን ነው ሁኔታሽ የሚቀያየረው አልኳት በተንቀጠቀጠ ድምፅ ፤....ወዲያው አንገቷን ደፋችና አይኖቿ እምባ አዘሉ ከዛም ለመናገር ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ስልኬ ጠራ ቶሎ ብዬ ዘጋሁና ይቅርታ ቀጥይ አልኳት፤...ድጋሜ ልትናገር ስትል አሁንም ጠራ ሳየው ያልታወቀ ቁጥር ነዉ አነሳሁና ሄሎ አልኩት ጤና ይስጥልኝ አቶ ቩራል አለ ለጆሮዬ አዲስ ያልሆ ድምፅ......

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
እንድምን ከረማቹልኝ ውድ ተካታዮቼ በጌታችን እዝነት ከዛሬ ጀምሮ ተመልሰናል።
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስር(10)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
ወዲያው አንገቷን ደፋችና አይኖቿ እምባ አዘሉ ከዛም ለመናገር ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ስልኬ ጠራ ቶሎ ብዬ ዘጋሁና ይቅርታ ቀጥይ አልኳት፤...ድጋሜ ልትናገር ስትል አሁንም ጠራ ሳየው ያልታወቀ ቁጥር ነዉ አነሳሁና ሄሎ አልኩት ጤና ይስጥልኝ አቶ ቩራል አለ ለጆሮዬ አዲስ ያልሆ ድምፅ......
አብሮ ይስጥልኝ ማን ልበል አልኩት፥.....ካርመላ እባላለሁ ከአጋር ድርጅታሁ አለኝ በድንጋጤ ቁጭ ብድግ አስባለኝ እሽ አቶ ካርመላ ምን ልታዘዝ አልኩት ድንጋጤዬን ለመደበቅ እየሞከርኩ
.... ስለ ድርጅቶቻችን ተገናኝተን እንድንወያይ ፈልጌ ነበር አለ
.... ደ..ደ ..ደስ ይለኛል
...እሽ እንደዛ ከሆነ ዛሬ ብናደርገውስ መረን ይመስልካል ማለት የተወሰነ ሰዓት ካለህ አለኝ
...ችግር የለውም ለእርሶ የሚሆን ጊዜ እንዴት እናጣለን ብለህ ነው ከማለቴ እንግዲያውስ ሰዓቱን እና ቦታውን በመልዕት እልክልሀላው ቻው ተባብለን ስልኩ ተዘጋ ምን ሆኜ ነው ግን አንቱ ብዬ አንተ ያልኩት ምን አስደነበረኝስ እያልኩ ማብሰልሰል ልጀመር ቀጥ ስል መይሙና አለች

...እንደዛ ስሜታዊ ሆኜ ሳወራ እሷ መኖሯን በጭራሽ ረስቼው ነበር ይቅርታ መይሙ እ...እ.. ማናገር ስለነበረብኝ ነዉ አልኳት
ኧር ችግር የለውም ባይሆን ጠንቀቅ በል ራስህን ጠብቅ ጥሩ ሰው አይመስለኝም
....ታውቂዋለሽ እንዴ ስላት?
..አይ ከዛው ስትሄድ ታገኘዋለህ አለችኝ
.....እሽ በቃ ሌላ ጊዜ እናወራለን ለአሁኑ መካሻ ምሳ እጋብዛለሁ ቀጠሮ ያዥልኝ አልኳት
...ፈገግ ብላ እስኪ እናያለን ብላኝ ሄደች
.......ከዛም በፍጥነት ወደ ጋሽ አይሀም ደወልኩ እና የተፈጠረውን ነገርኩት ተረጋግተህ አናግረው ምንም ቢናገርህ እንዳትፈራ አንተም ለምትናገራቸው ቃላቶች ጠንቀቅ በል ቶሎ ስሜታዊ እንዳትሆን አለኝ፤ እኔም ምክሩን ተቀብዬ ተሰነባብተን፥
..ከዛም የቀጠሮው ሰአት ደርሶ ወደ ተባለው ቦታ ሄድኩኝ ምን አልባት ያወቀኝ እንደሁ ብዬ በጣም ስለፈራሁ ጠቆር ያለ መነፀር ለበስኩና ከመኪናዬ ወርድኩ ከዛም ወደ ውስጥ ለመግባት በሩ ላይ ደረስኩ፤ ሆቴሉ የVIP ሰዎች ብቻ መዝናኛ መሆኑን ከጥበቃዎቹ መረዳት ይቻላል፤ ለመግባት እግሬን ስዘረጋ፤ ይቅርታ! ጌታዬ ቦታ አስይዘዋል አለኝ! እኔ ነኝ ጌታ ይችን ይወዳል ቩራል እንኳን ጌታ ልሆን እኔ ለራሴ ባሪያ ነኝ አድር ባዬ የሆንክ አሽቃባጭ ብዬ ብሰድበው ደስታዬ ነበር፥ ግን አልችልም እሱም ስራው ነው እኔም በለበስኩትና በኪሴ ለጊዜው ጌታ ነኝ.. አይ ቀጠሮ ነበረኝ አልኩ.. ወደ ካሸሯ ወሰደኝና የሰውየውን ስም እንድነግራት ጠየቀችኝ ከዛም እሽ ጌታዬ አንዴ ልየው አለና ኮምፒውተሩን ነካካና ጌታዬ ይከተሉኝ አለ! እሽ ብዬ አብሬው

ሄድኩኝ ከተያዘው ቦታ ስሄድ ካርመላ ቀድሞኝ ደርሷል፤ ይበልጥ የልብ ምቴ ጨመረ ለምን እንደሆነ አላቅም ፍርሀት ወይስ ድንጋጤ ምን ነካኝ እያልኩ እንደ ምንም ብዬ ራሴን ለመቆጣጠር ሞከርኩ!
ከዛም ጤና ይስጥልኝ ካልተሳሳትኩ አቶ ካርመላ አልኩት
...ኧረ በጭራሽ እራሱ ነኝ እንኳን ደህና መጣህ ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሰላም ተባብለን ከዛም እባክህን ተቀመጥ አለኝ!! ከተቀመጥን ቡሗላ ትወናውን ጀመረ፤
....ያው ምርጫህን ስለማላውቅ የራሴን ብቻ ነው ያዘዝኩት ምን ይምጣልህ አለኝ
ሜኑ ላይ ካለው ስጋ ነክ የሆነው አዘዝኩኝ ያው ስጋ ለአመታት ስለተመገብኩ ልረሳው አልቻልኩም
..እሽ ጌታዬ ብሎ አስተናጋጁ ሄደ፤
..እሽ አቶ ቩራል የሚገርም ነው ገና ወጣት ነህ ደስ ይላል ነገሮችን ቶሎ ትረዳለህ እና እንዴት ነው ስራ እየለመድክ ነው አለኝ
...አዎ ምን እማይለመድ ነገር አለ ብለህ አልኩት፥
...ጡሩ ደመዎዝ ይከፍልሀል፤
...አዎ ብዙ ባይባልም አልኩት፥ እ...ብሎ መናገር ሊጀምር ሲል በምንግዜው ፍጥነት ምሳው ደረሰና መጣ፥ ሁለታችንም ምሳውን በዝምታ መመገብ ጀመርን፤

..እኔ ግን የእናንትና የአባቴን ደም የመብላት ያክል ነው ስለተሰማኝ ነካ ነካ አድርጌ ተውኩት፥
...አትበላም እንዴ አለኝ በላሁ በቂ ነው አልኩት፤
....አቤት የአሁን ልጆች እንደው ምን ይሻላችሗል እኛ ወጣት ሳለን ይሄ የምትሰራበት ድርጅት ባለቤት አይሀምና በጣም የምንወደው የምናከብረው ነፍሱን ይማርና ሌላኛው ጓደኛችን ነምሩድ ጋር በአንድ ሆነን ለዉድድር የቀረብን ነበር የምንመስለው ስንበላ ታዲያ ምን ያደርጋል ሁሉም ነገር በነበር ቀረ አለ ባንቋረረ ድምፅ፤
..ይሄኔ ይበልጥ ንዴቴ እየጨመረ መጣ አንተ አስመሳይ ብዬ አልሰድበው የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ሊሆንብኝ ሆነ በዚህ መሀል እምባዬ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ በመነፀሬ ስር ወረደ
..ምን ነው ምን ሆንክ አለኝ ኧረ ምንም እኔም በጣም የምወደው ጓደኛዬን በሞት ስላጣሁት ነው አልኩት ኦ... ይቅርታ ያንተንም ትዝታ ቀሰቀስኩብህ አለ ችግር የለውም አውቀህ አደለም አልኩት ከዛም ጥያቄ መደርደር ጀመረ ከየት እንደመጣሁ በምን ዘርፍ እንደተማርኩ ጭምር ጠየቀኝ ከዛም የመጣልኝን መመለስ ጀመርኩ ተወልጄ ያደኩት ከደማስቆ የጎረቤት አገራት አንዷን ነገርኩት ደግነቱ ልዩ ቦታውን ማን ነው ብሎ አልጠየቀኝም፤

..ትምህርቴ ደግሞ በማኔጅመንት ማስተርስ እንዳለኝ ነገርኩት በጣም ተገረመና እሚገርም ነው በዚህ እድሜህ ማስተርስ ካለህ ጡሩ ጭንቅላት እንዳለህ ያስታውቃል እና ለምን ወደዚህ መጣህ ማለቴ ከዛ በጣም ጡሩ በሆነ ደመወዝ መቀጠር ትችል ነበር አለኝ፤ አዎ! እውነት ብለሀል ለብር ቢሆን ትክክል ነህ አልመጣም ነበር አላማዬ ሌላ ነው ለበቀል! ነው ወደዚህ አገር የመጣሁት ስለው አልኩት፤
...በተረበሽ ድምል አልገባኝም በደምብ ንገረኝ አለ በልጅነቴ ያልጠገብኳቸውን አባትና እናቴን የነጠቀኝን ነፍሰገዳይ ለመበቀል ነው የመጣሁት አልኩት...

መከታተል ጀምረናል ይቀጥል👍👍
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
መኖርን ባልታሰበ ስለዘገየን ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ ጀምሮ በየ ቀኑ የሚለቀቅ ይሆናል🙏🙏
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ አንድ(11)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
...በተረበሽ ድምፅ አልገባኝም በደምብ ንገረኝ አለ በልጅነቴ ያልጠገብኳቸውን አባትና እናቴን የነጠቀኝን ነፍሰገዳይ ለመበቀል ነው የመጣሁት አልኩት...
በጣም ነዉ ደነገጠ ይገርማል ምን ጊዜም ስራ ያለበት ሰው ስራው ሲነሳበት መሸማቀቅ ነዉ ስራዉ እያለልኩኝ "በሆዴ!!
........ማን! ማን! ነው የገደለብህ አለ በተቆራረጠ ድምፅ!
...ብነግርህ ምን ያህል ሚስጥር ጠባቂ ነህ ምክንያቱም የቤተሰቦቼን ንብረት ሞጣጦ አሁን ትልቅ ባለሀብት ሁኗል ስለው
....አይዞህ በኔ እርግጠኛ ሁን አለ! በፍርሀት ስሜት!
...ፊቴን ኮስተር አድርጌ አይሀም ነው አለቃዬ አይሀም! አልኩት!!
...በደስታ ድንጋጤ ዉስጥ ሆኖ ኣ..ያነ መናጢ ነው ምንም እንኳ ጓደኛዬ ቢሆንም አያደርግም አይባልም ያውም አንድ ጊዜ ከሚስቱ ውጭ ሲባልግ ቀርፀውት በስንት መከራ እና ልፋት መሰለህ ቪድዮውን እንዳይለቁት ተደራድሬ ካሴቱን የተቀበልኳቸው እሚገርምህ ይሄን ሁሉ ውለታ አድርጌለት ግን እሱ በምላሹ ድርጂቴን ለማክሰር ያልፈነቀለው ዲንጋይ የለም ንግግሩን ይሄ ካሀዲ የበላበትን ወጨት ሰባሪ!!! እያለ ራሱን መነቅነቅ ጀመረ

....እኔም ማስመሰሌን ቀጠልኩኝ ፊቴን አጨማደድኩና በቃ ያ!! አረመኔ የማይገባበት የለም!! ከእናቱ ሆድ ቢገባ አለቀውም አጠፍዋለሁ የቤተሰቦቼን ቀን ነው የምሰጠው አልኩኝ፤
...ስማኝ ቩራል ዛሬ የፈለኩህ ዋና አላማዬ ይሄ ነበር በአንድ ሆነን ህልዉናውን ማለትም ድርጅቱን እሱ በማያዉቀዉ መንገድ እንዲሸጥ እናደርገዋለን በዚህ ደግሞ አንተም የቤተሰቦችህን ንብረት ታስመልሳለህ እሱ ደግሞ ዳግም የሰው አይንን ቀጥ ብሎ እንዳያይ ራሱን በራሱ እንዲያጠፍ እናደርገዋለን አለኝ!!!
.......በጣም ደስ ይለኛል እንዳንተ አይነት ምኞቴን በቀላሉ ሊያሳካልኝ የሚችል ሰው በማግኘቴም እድለኛ ነኝ እንዴት አድርገን እንደምናጠፍው እቅድ አወጣለው ባይሆን ካንተ ትልቅ እምነት እፈልጋለሁ አልኩት
......ምንም ስጋት አይግባህ እንደውም አለና ከኪሱ ቼክ አውጥቶ ብዙ ዜሮዎች የበዙበት ቁጥር ፅፎ ይችን ያዛት አለኝ፤
......ምንድ ነው አቶ ካርመላ አልኩት፥
.........አቶውን ተወው እና ካርመላ በለኝ ይሄ ለአንዳንድ ነገር ይሆንሀል አለኝ፤
...አስፈላጊ አይመስለኝም እያልኩ መግደርደር ጀመርኩ፤
.......ለዕምነትና ለስራ ማስኬጃ ያክል ነው አለ
...ትንሽ አንገራገርኩና ተቀበልኩት አንድ ሚሊዮን ብር ይላል
......ይሄ ነገር አልበዛም አልኩት
.....አታስብ ስራው ሲያልቅ ደግሞ #ሁለት ቢሊዮን ብር ታገኝበታለህ አለኝ፤
...እሽ ካርመላ በቃ ከአሁን ቡሗላ ሆቴል ላይ መገናኘት አንችልም ምክንያቱም ያ! መናጢ እንዲከታተሉኝ ሰው ቀጥሯል አልኩት፤
........ችግር የለዉም እኔ ቤት መገናኘት እንችላለን ብሎ የቤቱን አድራሻ ሰጥቶኝ በዛው ተሰነባብተን ተለያየን፤
....ለጋሽ አይሀምም የተፈጠረውን ነገርኩት የሁልጊዜ የአባትነት ምክሩ የሆነችውን ""ራስህን ጠብቅ ለሁሉም ነገር አንተ ስትኖር ነው የሚሳካው"" አለኝ ገንዘቡንም ወደ አካውንቴ እንዳላስገባና የሀሰት መረጃዎችንም እንደሚዘጋጁ አሳወቀኝ!!!
......ከቀናት ቡሗላ ቃል በገባሁት መሰረት መይሙናን ምሳ ለመጋበዝ ይዣት ሄድኩኝ መንገድ ላይ የሆነች መኪና ለብዙ ሰአት ስትከተለን ነበር ምን ፈልገው ነው እያልኩ ራሴን እየጠየኩ ሆቴሉ ጋር ደረስን ከመኪና እንደወረድን አይኔን በቅርብ ርቀት ሲከተለን የነበረውን መኪና ላይ አደረኩ መኪናው ጥር መስታውት ስለነበረው ሰዎቹ ሊታዩኝ አልቻሉም....

ከዛም ሆቴሉ ውስጥ ገባን እና ቁጭ ከማለታችን የሆኑ ሰዎች ተከትለውን ገቡና ራቅ ብለው ተቀመጡ ቀስ አድርጌ ሳላስነቃ ስመለከታቸው ሙሉ አትኩሮታቸው እኛ ጋር ነበር!! ይህን ከካርመላ ውጭ ማንም እንደማይሰራው የታወቀ ስለሆነ፤ መይሙ! አንዴ መታጠቢያ ደርሼ ልምጣ ብያት ተነሳሁና ሄድኩኝ ከዛም ለካርመላ ደወልኩ!!!
....ሄሎ ካርመላ
.....ሰላም ወጣት ቩራል እንዴት ነህ አለኝ!!
....ትሸማኛለህ ገንዘብህን በፈለከው ሰአት ተገናኝተን ልመልስልህ እችላለሁ ግን እነዚህን የማይረቡ ሰላዮችህን ዳግም እንዳይከተሉኝ ንገራቸው ከአሁን ቡሗላ በስራዬ ላይ እጅህን እንዳታስገባ አልኩት፤
.....ቩራል እኔ እኮ ላንተ ደህንነት ብዬ ነው አለ፤
...ያም ቢሆን እኔን ፍላጎት መጠየቅ ነበረብህ ግን አንተ ምን አደረክ በራስህ ወሰንክ!!
...እሽ ቩራል በቃ ከአሁን ቡሗላ አይከተሉህም ልጅቷ ጋር ምን እያደረክ ነው
...የአይሀም ታማኝ ሰራተኛው ናት ሙሉ መረጃው እሷ ጋር ስለሆነ እንድትሰጠኝ ለማግባባት ነው አልኩት
...ልጅቷ እኮ ደረቅ ነገር ናት አለ..
""መይሙ ወዳ አደለም አትቅረበው ያለችው እሷን የሆነ ነገር ጠይቋት ነበር ማለት""
...ያን ለኔ ተወው ብር የማይገዛው ነገር የለም አልኩት!!
.....ይቅርታ ጠይቆኝ ተሰነባበትን
....ከዛም ወደ መይሙና ሄድኩ ዘወር ዘወር ብዬ ሳይ የሉም ሄደዋል!!

መይሙናም """ምን ሆነክ ነው ቆየህ አለችኝ""
.....ይቅርታ ስልክ ላይ ስለነበርኩ ነው ምሳ አዘዝሽ ስላት
....ምርጫህን ባላውቅም ተጋባዥ ስለሆንኩ የመምረጥ መብቱ የኔ ስለሆነ አዝዣለሁ አለች!!
......ፈገግ ብዬ ጥሩ አድርገሻል አልኳት
ቀጥሎም ምሳ እስኪደርስ ወደ ጥያቄዬ ገባሁ ባለፈው የጠየኳትን ጥያቄ ደገምኩላት
.....እንደባለፈው ሁሉ አሁንም አይኗ በእምባ ተሞልቶ መርገብገብ ጀመረ ከዛም መናገር ጀመረች ከአመታት በፊት ተማሪ እያለሁ በጣም........

ወደነዋል ይቀጥል👍👍
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
1
#برنامج_العيد❤️
#مع_إذاعة_ياسمين😍
تابعو.........
عيدكم مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🎊🎊

#ልዩ_አዝናኝ_አስተማሪ 🎊የኢድ አልአድሀ አረፋ🎊በአል ፕሮግራም

#ከያስሚን_ጋር
እንዳያመልጥዎ ይከታተሉ

ኢድ ሙባረክ ተቀበለሏህ ሚና ወ ሚንኩም ሳሊሀል አዕማል!

@M3_Yasmina
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ሁለት(12)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
.....እንደባለፈው ሁሉ አሁንም አይኗ በእምባ ተሞልቶ መርገብገብ ጀመረ ከዛም መናገር ጀመረች ከአመታት በፊት ተማሪ እያለሁ በጣም......ግትር እና አይናፍር ነበርኩ ከሴት ጓደኞቼ በቀር ወንድ ማናገር አልፈልግም ነበር፤አለመፈለግ ብቻ አይመስለኝም እፈራ ጭምር ስለ ነበር ነው በዚህ መሀል ግን አንድ ልጅ በፍቅር ጣለኝ፥ ልጁ በጣም ፈጣንና ፈጣጣ ነበር በዛ ላይ ቆንጆ ነው፤
....እንዴት እንደ ቀረበኝና በፍቅሩ እንድትወድቅ እንዳደረገኝ አሁንም ሳስበው ህልም ህልም ነው የሚመስለኝ ምን ግዜም እንደሚያፈቅረኝ ከኔ ውጭ ሌላ እንደማያገባ እየማለ ሁሉ ይነግረኛል፥
...ቢሆንም ግን እኔ አንድም ቀን ስሜቴን በግልፅ ነግሬው አላቅም እናም መቼም የማረሳት አንድ የተረገመ ቀን እሱን ድጋሜ እንዳላየው አደረገችኝ አለች እምባዋ ከአይኖቿ ኩልል ብለው እየወረዱ እኔም በአትኩሮት ሁሉ ነገሬን ሰጥቼ እያዳመጥኳት ነው ቀጠለች ....

ዕለተ ሀሙስ ትምህርት ቤት ውለን ወደ ቤት ተመለስን ቤት ዩኒፎርሜን ቀያይሬ መክሰስ እየበላሁ ስልኬ ጠራ አንስቼ ሳየው የሱ ስልክ ነው ከዛ በፊት በዛ ሰአት ደውሎልኝ አያውቅም ነበር ፤......ማሚ አጠገቤ ስለነበረች ዘጋሁበት አሁንም ደግሞ ደወለ ደግሜ ዘጋሁበት ለሶስተኛ ጊዜ ሲደውል አነሳሁና ማሚ እንዳትነቃ በሴት ጓደኛዬ አስመስዬ ማዋራት ጀመርኩ ሄሎ! ውዴ ደና ነሽ ዛሬ ጥናት አለን እንዴ እና ምን እግር ጣለሽ አልኩት፥
.....ግራ ገብቶት ነው መሰል ዝም አለኝ እኔ ማውራቴን ቀጠልኩ ማሚዬ ደና ናት እሽ ሰላም እልልሻለሁ ያውም አጠገቤ ናት ያለችው አልኩት፤
...የዛኔ ገባውና በተኮሳተረ ድምፅ ዛሬ ማታ ከተለመደው ቦታ እንገናኝ እፈልግሻለው! የጓደኞቼን ስም እየጠራ እነሱም ይመጣሉ አንችም እንዳትቀሪ አለኝ
..አይመቸኝም አልመጣም አልኩት
...መይሙ ዛሬ እንዳት ቀሪ ከቀረሽ ድጋሜ አታይኝም ከመጣሽ ደግሞ..የምነግርሽ ነገር አለ ከቀረሽ ግን ያው እንደነገርኩሽ ነው አለኝ፥
.........አልመጣም በጭራሽ አይመቸኝም አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት
....ያንን ያልኩት ግን ላለመሄድ ፈልጌ ሳይሆን ሳያስበው ሂጄ ላስደንቀው ስለፈለኩ ነበር እናም ያን አስቤ እሱ ከቀጠረኝ ሰአት አርፍጄ ከተባለው ቦታ ስደርስ አላገኘሁትም ነበር ሄዶዋል ፤ ጓደኛኞቼንም ስጠይቃቸው ፈጣሪ ካለ ምን አልባት አንድ ቀን እንገናኛለን በሏት አሁን ውስጤ ሰላም አይደለም ብቻ ብሎን ሄደ አሉኝ
.....በቃ ከዛን ቀን ጀምሮ አይቼው ስለሱ ሰምቼም አላቅም በጣም ብዙ ጊዜ እና ብዙ ቦታ ፈለግኩት ላገኘው አልቻልኩም ቤተሰቦቹ እንደሞቱ ግን ሰምቻለሁ እሱ ግን በዛው ድራሹ ጠፍ ብላ ሲቃ በተሞላው እና በእምባ በታጀበ ንግግር ወሬዋን ጨረሰች፤

እኔ ውስጤ ቢደማም እንደ ምንም አምባዬን እየተቆጣጠርኩ ሰማሗት ንግግሯን ብትጨርስም ማንባቷን አላቆም አለች፤
...እንዴት እንደተነሳሁ ባላውቅም እሷን አቅፌ ማፅናናት ጀመርኩ
...........ከዛም ድንገት ይቅርታ ስላቋረጥኳቹህ ያዘዛቹሁት ምግብ ደርሷል አለ አስተናጋጁ ከእንቅልፍ የቀሰቀሰን ያከል ነው የተሰማን ከዛም ተነስታ መታጠቢያ ቤት ፊቷን ታጥባ መጣች እኔም ሄጄ ታጠብኩና መመገብ ጀመርን በመሀላችን ፀጥታ ሰፈነ እኔም መብላቴን ትቼ እሷን ማየት ጀመረኩ፤
...ድንገት ሳላስበው ለምን አንተን ሳይ ለምን እንደምደነግጥ ታቃለህ አለችኝ ራሴን እየነቀነቅኩ እንደማላቅ ነገርኳት ስምህ እንደሱ ቩራል ነው አፍንጫህ አካባቢ ደግሞ እሱን ትመስላለህ ቆንጅዬ ነበር ለዛ ነው
....እሱን ለመርሳት ግን አማራጭ ያልኩትን ሁሉ ሞከርኩ ሌላ ጓደኛ ከመያዝ ውጭ መዝናናት ሳይኮሎጂስቶች ጋር መሄድ ግን ምንም ለውጥ የለውም ትንሽ በስራ ስጨናነቅ ይሻለኛል አለች፤

...ያኔ በጣም ውስጤ አዘነ እኔ ነኝ ራሱ ቩራል ነኝ ብላት ደስ ባለኝ ግን አልችልም አሁን በጀመርኩት ነገር ላይ ህይወቴን ላጣ ስለምችል ድጋሜ እንድትጎዳ አልፈልግም ያለኝ ምርጫ ዝምታ ብቻ ነው፥
....አይዞሽ እንዳለው አንድ ቀን ታገኝዋለሽ ቆንጆ ነህ ላልሽኝ ግን አመሰግናለው አልኳት
....ፈገግ እያለች እንዴ አንተን አደለም የኔን ቩራል ነው ያልኩት
በዛው የሚያስቁ ወሬዎችን እያወራሁ በመከራ ፈገግታዋን መለስኩላት ከዛም ስራ ገባን፤
...እንደተለመደው ለጋሽ አይሀም ደወልኩ ስራ ቦታ ስለነበረ ወደ ቢሮው እንድመጣ ነገረኝ ከሄድኩ ቡሗላ የተፈጠረውን አስረዳሁት
...አንተ እንደሆንክ በነርካት አለኝ

..አይ አልነገርኳትም ምክንያቱም እየሰራን ባለነው እቅድ ላይ የሚፈጠረው አይታወቅም ስኬት ብቻ ሳይሆን መውደቅም ሊኖር ይችላል ምን አልባት ሞት ከማለቴ አቋረጠኝና እውነተኛ የአባትነት መገለጫ የሆነ ንግግር ተናገረኝ
......""እኔ ከመሬት በላይ እያለሁ ፈጣሪ ብቻ እንጂ ማንም አይነካህም ባንተ ለመጣብኝ ህይዎቴንም ቢሆን ሰጥች እከላከልልሀለሁ"" ልጄ ነህ እኮ ቩራል የልጆቼ ወንድም ሲል
.....አንገቱ ላይ ሂጄ ጥምጥም አልኩበት እሱም አቀፈኝና ትንሽ ደቂቃዎች ቆየን

ከዛም ቩራል አዝጋጅልኝ ያልከውን መረጃ ተዘጋጅቶልሀል እየውና የቀረ ካለ ንገረኝ አለኝ፤
...እሽ ብዬ ተቀበልኩና ምንም የጎደለ እንደሌለ ነገሬው ወዲያው ለካርመላ ደወልኩለት እንድንገናኝ እፈልጋለሁ ያልከውን መረጃ ከፀሀፊዋ ተቀብያለው እናም አንተ ጋር ያለውን መረጃ አዘጋጅተህ ጠብቀኝ ለጥንቃቄ ሲባል መኪና ሳልይዝ እንደምመጣ ስነግረው
....የኔ ሰዎች እዚህ ቦታ ይጠብቁሀል አለኝ እሽ ብዬ ወደ ተባለው ቦታ ሄድኩ አግኝቻቸው ወደሱ ቤት ወሰዱኝ ግቢ ውስጥ ካስገቡኝ ቡሀላ ተመለሱ እኔ ወደ ቤቱ በር አመራው በሩ ላይ እንደደረስኩ መጥሪያውን ተጫንኩ የሚከፍትልኝ ሰው እስኪመጣ ድረስ የጫማ ማሰሪያዬን ተፈትቶ ሳየው ለማሰር ጎምበስ አልኩኝ እዛው እንደተጎነበስኩ በሩ ተከፈተና
...እልኳል ደህላ መጣቹህ የሚል ኮልተፍ ያለ የትልቅ ሰው ድምፅ ሰማሁ፤
....ቀጥ ብዬ ሳይ እንኳን በውኔ ይቅርና በህልሜም ለማለም አስቤው የማላውቀው ነገር........

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1👏1
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ሶስት(13)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
....ቀጥ ብዬ ሳይ እንኳን በውኔ ይቅርና በህልሜም ለማለም አስቤው የማላውቀው ነገር ስለነበር አይኔ በእምባ ተሞላ እንደምንም ከተጎነበስኩበት ቀና አልኩኝ እግሬ መራመድ ቢፈልግም ጉልበቴ ተብረከረከ ዘልዬ ባቅፋት ደስታዬ ነበር ግን ምን ላድርግ አይን አይኗን እያየሁ በራፉን የጨበጠውን እጇን ዳደሰስኩት የእናትነት ስሜቱ የልብ ትርታዬን ጨመረው እሷም የእናትነት አንጀቷ ልጇ እንደሆንኩ ነገሯት እምባዋ ከጉንጮቿ መሬት ላይ ተንጠበጠቡ እንደምንም ብዬ ራሴን ለመቆጣጠር ሞከርኩና ወደ በራፉ ጠርዞች ስመለከት የጥበቃ ካሜራዎች አሉ
...ፈጠን ብዬ አመሰግናለሁ አልኩ እና ገባሁ ከዛም እምባዬን ጠራረኩና ወደ ሳሎኑ ስሄድ ካርመላ ጋር ተገናኘን እና ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጥን...
...ከዛም ምን ነው ቩራል ፊትህ ላይ ጥሩ ስሜት አይነበብህም አለኝ
....ያ! አይሀም እሚባል መናጢ እያለ ምን ላድርግ ብለህ ነው የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሬ ውጭ ሊያደርገኝ እየሞከረ ስለሆነ ስበሳጭ ንዴቴን በውስጤ ነው የማደርገው ለዛ ነው ፊቴ የሚለዋወጠው እና ካላስቸገርኩህ ፊቴን ብታጠብ አልኩት
......አኒሳ አኒሳ አላት
......አቤል አቶ ካርመላ እያለች መጣች
.....ለአቶ ቩራል መታጠቢያ ቤቱን አሳዪዉ አላት እሽ ብላ ፊት ፊት እየመራች ወሰደችኝ ከመታጠቢያ ቤቱ እንደደረስንም ዘልዬ አንገቷ ላይ ተጠመጠምኩባት የለበሰችው ጨርቅ እስኪረጥብ ድረስ አለቀስኩባት!!
...ልጄ ለምል ወደዚህ ተመልሰህ መጣህ ካርመላ ይገልሀል እባክህ ከዚህ አካባቢ ጥፍ አለችኝ በተቆራረጠ ድምፅ....

እማዬ ...አሁን ሁለተኛ አባት አግኝቻለሁ እሱ ስለሚያግዘኝ ምንም አያደርገኝም ደግሞ በቅርቡ እንደማስወጣሽ ቃል እገባልሻለው እያልኳት ሳለ
...ያ መናጢ አኒሳ አኒሳ የት ነሽ እያለ መጣራት ጀመረ እንዳቀፍኳት ብቆይ ደስታዬ ነበር እየከፍኝም ቢሆን ለቀኳት
...ከዛም ተጣጥቤ ወደሱ ሄድኩኝ እና ጡሩ ሰራተኛ አለችህ አቶ ካርመላ አልኩት
....አንተ ወጣት ግን ይሄ አቶ የሚል ነገር ተው አላልኩህም! አለኝ ይቅርታ ካርመላ ያው ለአይሀም ማሽቃበጡ ስለለመደብኝ እኮ ነው ስለው
...ያማስጠያ ፊቱን እያፈገገ ለማንኛውም የአኒሳ ታሪክ ረዥም ታሪክ ነው በአጭሩ ግን ሁልጊዜ እየመጣች ገንዘብ ትለምነኝ ነበር እኔም በመጣች ቁጥር በባዶ አልመልሳትም እናም አንድ ቀን ሚስቴ ለምን ሰራተኛችን አድርገን አንቀጥራትም አለችኝ እኔም ተስማማሁ እና ቀጠርናት አለኝ
.......አስመሳይ አሁንተም ጡሩ ሰው ነኝ፤ እያልክ አፍህን ትከፍታለህ ማፈሪያ ቢስ ብዬ እየተሳደብኩ በሆዴ!! እንዴ ጡሩ ሚስት አለችህ ለነገሩ ካንተ የተማረችው ደግነት ነው አሁን የት ሂዳ ነው ባለቤትህ አልኩት....
መዝናናት ትወዳለች ብዙ ጊዜ ቤት አትቀመጥም አለኝ
...እሽ ብዬ ወደ ጉዳያችን ገባሁ ከዛም እኔ ጋር ያለውን መረጃ በሙሉ አሳየሁት
...በጣም ተገርሞ ተአምረኛ ልጅ ነህ በዚህ ፍጥነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሁሉ ነገር ማድረግህ በጣም ጎበዝ እና ፈጣን ነህ ከጠበኩህ በላይ ነው ያገኘውህ ሙገሳ መሆኑ ሴራ መሆኑን አለማወቁ ጠቀመው ከዛም እሱ ጋ ያለውን መረጃ እንዲያሳየኝ ጠየኩት ላፕቶፑን ከሻንጣው አወጣና የሲዲ ካሴት ካስገባ ቡሀላ መረጃ የያዘውን ፎልደር ከፈተው በጣም ደባሪ ቪድዮ ቢሆንም ጋሽ አይሀም ቀድሞ ስለ ነገረኝ አዲስ አለልሆነብኝም ነበር አይተን ከጨረስን ቡሀላ ስለ ቀጣይ ስራዎቻችን መነጋገር ጀመረን፤

...የመጀሪያው ተግባር የድርጅቱን የሽያጭ ፍቃድ ማውጣት ሲሆን ሁለተኛውና የመጨረሻ ስራችን የሆነውን ጋሽ አይሀምን በቪድዮው አስፈራርቶ ማስፈረም ነው የመጀመሪያውን ተግባር ካጠናቀክ ቃል የገብሁልህን ሁለት ቢሊዮን ብር እሰጥሀለሁ አለኝ እሽ ብዬ ተሰነባብተን ልወጣ ስል እማዬ በሩን ለመዝጋት መጣች በሩ ጋ ልወጣ ስል ከኪሴ ብር አወጣሁ እና መሀሉ ላይ ስልክ ቁጥሬ ያለበትን ወረቀት ጋር ሰጠሗት ተቀብላኝ ቻው ብያት ሄድኩ፥
...ያው እንደተለመደው ጋሽ አይሀም ጋር ሂጄ አለቃቀስኩ መረጃውንም አዘጋጅ አልኩት እሱም የእማዬ በህይዎት መኖር በጣም ደስ አለው ፤
.....ከቀናት ቡሗላም ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብዬ በቤት ስልክ ተደወለልኝ እማዬ እንደምቶን እርግጠኛ ነበርኩ አነሳሁትና ድጋሜ የእናቴን ድምፅ ሰማውት እናም አንድ ጥያቄ ጠየኳት ለምን አንችን አልገደለሽም እማ? እሷም እያለቀሰች አባትህን አፍኖ ገደለና እኔን ምላሴን ሲቆርጠኝ አንተ የጮክ ጊዜ ተደናግጠው እኔን ተውኝና አንተን መፈለግ ጀመሩ ከዛም እንደሞትክ ሲያረጋግጡ ንብረታችንን ጠቅላላ ለመሸጥ የኔ ፊርማ ስለሚያስፈልጋቸው ከፈረምሽልኝ አልገልሽም ብሎ ቃል ገባልኝ ከዛም ፈረምኩለትና እኔን ሳይገለኝ ቀረ ከዛም ሜዳ ለይ ወደኩ የምበላው ነገር አጥቼ ባዶዬን ስቀር ያለኝ አማራጭ መልሶ እሱን መማፀን ነበርና በስንት ልመና ያለ በደመወዝ ሰራተኛ አደረገኝ ብላ ድንፇ እየተቆራረጠ ነገረችኝ እኔም እምባ እየተናነቀኝ እማ ስንት ብር ይሆናል የነበረን ካርመላ የወሰደብን አልኳት ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ነው አለችኝ...እሽ እማ ይሄንም እነወደማስመልሰው ቃሌ ነው አልኳት ከዛም
..... አንድ ስራ ሰጠሗት የቪድዮ ካሴቱን እንደ ምንም ፈልጋ እንድታገኝልኝ ነገርኳት እሽ ብላኝ ንግግራችንን ጨረስን

.......ከዛም ወዲያው ለካርመላ ደወልኩለት
...ሰላም ካርመላ እንዴት ነህ አልኩት
....ደና ነኝ ቩራል አንተስ መቼም መረጃው አገኘሁት እንዳትለኝ አለ
...አይ አሁን በጄ አልገባም እስከ ማታ ድረስ ግን አስገባለሁ ከዛ አይሀምን እስከ መጨረሻው እናጠፋዋለን አልኩት
..እንደዛ ከሆነ ሰሞኑን እንገናኛለን አለ
...አዎ ግድ ግን የዛ ቪድዮ ቅጅ አለህ እንዴ አልኩት
...ኧረ የለኝም ከፈለከው ግን ኮፒ አደርግልሀለሁ አለ
....ኧረ አታድርገው ችግር የለውም በፈለኩት ሰአት እነግርህና መጥቼ ኮፒ አደርጌ እወስዳለሁ አልኩት እሽ ብሎኝ ስልኩን አናግሬ እንደጨረስኩ ከቢሮ ለመውጣት በሩን ስከፍት መይሙና ከቢሮው በር ቁማ እያዳመጠችኝ ነበር....


በጣም እየዘገየ ነው እንዴ👍👍
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ አራት(14)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
.............ስልኩን አናግሬ እንደጨረስኩ ከቢሮ ለመውጣት በሩን ስከፍት መይሙና ከቢሮው በር ቁማ እያዳመጠችኝ ነበር....
..........ምን ልበላት እ...እ ምን መሰለሽ መይሙ ላስረዳሽ አልኳት
.........ምንም የምታስረዳኝ ነገር የለም ጋሽ አይሀም ምን አደረገህ አንተ ካርመላ ጋር ሁነህ ልታጠፋው!!! በጭራሽ አልፈቅድልህም አለችኝ
....መይሙ እባክሽ ተረጋጊ አንቺ የማታውቂው ነገር አለ ልንገርሽ
....መይሙ አትበለኝ ከሀዲ ነህ ሁሉንም ነገር ሰማሁት'ኮ እኔ ነኝ እንጂ ሞኚቷ የውስጤን ነግሬ አንተን ለመውደድ መሞከሬ አለች እምባ በተናነቀው ድምፅ ከዛም ለጋሽ አይሀም ደውላ በፍጥነት እንዲመጣ ነገረችው ላረጋገት ብሞክርም ጭራሽ ልትሰማኝ አልቻለችም
....እሱም ብዙም ሳይቆይ መጣና ምንድን ነው የተፈጠረ ችግር አለ እንዴ ሲል ከአፉ ተቀብላ
አዎ አለ! ያውም ትልቅ ችግር አቶ ቩራል አንተ ትነግራቸው ወይስ እኔ ላስረዳቸው
...በቃ ኑ! ወደኔ ቢሮ እንሂድ እና እናውራ ብሎ ይዞን ገባና ምን ሆናችሁ ነው አለ!!
.....ምን መሰሎት አቶ አይሀም አንድ ጊዜ ካስታወሱ መረጃ በገንዘብ እንድለውጠው የጠየቀኝ የእርሶዎ ጓደኛ ካርመላ የሚባለው ሰውዬ ጋር ተባብሮ ድርጅቱን ሊያጠፉ እንደሆነ በስልክ ሲያወራ ሰምቸዋለሁ ጥሩ ሰው መስሎ አስመሳይ ነው እንዳያምኑት አቶ አይሀም አለችው
.....እሱም ቩራል አንተ መሄድ ትችላለህ አለኝ
.......እሽ ብዬ ወጣሁ ቢሮዬ ውስጥ ቁጭ አልኩ ከትንሽ ቆይታም ቡሗላ እማዬም ደወለች
...ሄሎ እማ ደናነሽ አልኳት
...አዎ ደህና ነኝ ልጄ ምን ሆንክብኝ ድምፅህ ተቀይሯል አለችኝ የእናት ነገር ሁሉንም ልባቸው ይነግራቸዋል እንዳታስብ ብዬ ትንሽ ተኝቼ ነበር ለዛ ነው አልኳት

.....እንዳልክ ልጄ!! ያነ ባለፈው ያልከኝን ነገር አግኝቼዋለሁ አንተ ያልከኝ ለመሆኑ ግን እርግጠኛ አይደለሁም የምሞክርበት ነገር አጣሁ አለችኝ
.....ችግር የለውም እማዬ ብቻ አንቺ ተጠንቀቂ ነገ እንደምንም ብዬ እመጣለሁ አልኳት እሽ!!? ብላኝ ስልኩን ዘጋን
.....መይሙና እና ጋሽ አይሀም እስከ አሁን ከቢሮ አልዎጡም ለብዙ ሰአታት ጠበኳቸው በጣም ሲዘገዩ እኔ ወደ ቤት ሄድኩ የኔ ወደ ቤት መምጣት የምተደሰተው ሲትና እየሮጠች መጣችና በሩን ለመክፈት አቅሙ ባይኖራትም ወንድሜ ቩራል ወንድሜ ቩራል እያለች እስከምገባ በጉጉት ትጠባበቃለች ገዝቼላት የመጣሁትን ከሰጠሗት ቡሗላ ለእናቷ ለማሳየት እየሮጠች ሄደች
.....እኔ ዛሬ በጣም ስለደበረኝ ቀጥታ ወደ ክፍሌ ገብቼ ጋደም አልኩና ስለሁሉም ማሰብ ጀመርኩኝ በተለይ ስለ እማዬና መይሙ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እቅድ ለማውጣት እየሞከርኩ ሳላስበው መሽቷል!!
....ሲትና መጥታ ወንድሜ ቩራል ወንድሜ ቩራል ራት ደርሷል አባቢም መጥቷል አለችኝ
......ሲቱ ዛሬ እራት መብላት አልፈልግም ተኝቷል በያቸው ብያት ሄደች!!
.....ደግማም አልመጣችም እኔም በዛው የረባ እንቅልፍ ሳይዘኝ ነጋ ከመንጋቱ በጧት ተነስቼ ነበር ከቤት የወጣሁት!!!
....ቁርስ አንድ ካፌ ላይ በላሁ እና ወደ ስራ ገባሁ ወደ ቢሮ ስሄድ መይሙ የለችም ያለ ወትሮዋ ዛሬ እንዴት አረፈደች ብዬ ለሰአታት ብጠብቃትም አልመጣ አለች
.....አላስችል ሲለኝ ሰራተኞቹን ጠየኳቸው
.......ትናንት ጋሽ አይሀም ጋር አውርተው ከወጡ ቡሗላ የአመት ረፍት ወስዳ መሄዷን ነገሩኝ ግን ነገሩኝ ከምል አረዱኝ ብል ይቀለኛል በጣም ተናደድኩ ተበሳጨሁ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳ አላውቅም ለዚህ ሁሉ ነገር ያበቃኝን ካረመላን መጨረሻውን ማቅረብ አለብኝ ብዬ ደወልኩለት...

....ሄሎ ካርመላ ሰላም ነው አልኩት
...ደህና ነኝ ቩራል አንተ እንዴት ነህ ምን አዲስ ነገር አለ
.......ያልከኝን መረጃ ሁሉንም አግኝቼዋለሁ ዛሬ መገናኘት አለብን አልኩት
....እሽ ቩራል እኔ አሁን ቢሮ ነኝ እዛው እንገናኝ አለኝ
........እሽ ብዬ ስልኩን ዘጋሁና ላፕቶፔን እና የተዘጋጀውን መረጃ አንዷ ብቻ አስቀርቼ ሁሉንም ሰብስቤ እማዬን ቀድሜ ለማገኘት ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ መኪናዬ ሄድኩኝ ከዛም መኪናውን አስነስቼ በፍጥነት እየነዳሁ ከቤቱ ደረስኩ ከዛም ፥
....ከመኪናዬ ወረድኩ እና የጥበቃ ካሜራዎች ስላሉ ረጋ ብዬ ወደ በሩ ሄድኩ እና አንኳኳሁ እማዬ ብዙም ሳትቆይ ወዳው መጣችና ከፈተችኝ
በአይናችን ሰላም ተባብለን ወደ ውስጥ ቀድሚያት ገባሁ እሷም ብዙም ሳትቆይ መጣችና እንድከተላት በምልክት ጠቀሰችኝ ከዛም ወደ መታጠቢያ ቤት ሄድን በጉያዋ የያዘችውን ካሴት ሰጠችኝ እና ከወደ ውጭ የሚመጣውን ሰው ለመከታተል ጥላኝ ሄደች
.....እኔም የተቀበልኩትን ካሴት ላፕቶፔ ውስጥ አስገባሁት ውስጡ ምን እንደያዘ ለማየትና የምፈልገው ካሴት እንዲሆን እየተመኘሁ አይኔን ጨፍኜ ከፈትኩት.......


ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍41
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ አምስት(15)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
....እኔም የተቀበልኩትን ካሴት ላፕቶፔ ውስጥ አስገባሁት ውስጡ ምን እንደያዘ ለማየትና የምፈልገው ካሴት እንዲሆን እየተመኘሁ አይኔን ጨፍኜ ከፈትኩት.......
ከዛም ቪዲዮው ማጫዎት መጀመሩን በድምፁ ስሰማ አይኔን ገልጬ አፈጠጥኩበት በጣም ተደሰትኩ ውስጤ በሀሴት ተሞላ እንደ መሳቅ እንደ ማልቀስም አልኩኝ
....ወደር ባጣ ደስታ ውስጥ ሆኜ ከዚህኛው ጠርዝ ወዳዛኛው ጠርዝ እየተዟዟርኩ ቪድዮውን እያየሁ ከውጭ የመኪና ድምፅ ሰማሁ ቶሎ በዬ ውስጥ ላይ ያለውን ሁሉንም ዶክመንት እንዳይመለስ አድርጌ ደመሰስኩትና እንዳይጠረጥር አንድ የቀልድ ቪድዮ ጫንኩበት!!
...እማዬም መጣችና ልጄ ካርመላ መጥቷል ከጨረስክ ወደ ቦታው ልመልሰው፤
.....ግን! የምትፈልገውን መረጃ አገኘህ አለችኝ፤
.....አዎ! እማዬ ብዬ ግንባሯን ከመንከስ ባልተናነሰ ሳም አደረኳትና፥እናቴ!! አንቺን ከዚህ ለማስወጣት ቢበዛ አንድ ሳምንት ነው የሚፈጅብኝ አልኳት፤ ልጄ አንተን ከሞት የመለሰ አምላክ ምንም አይሳነውም ባይሆን አንተ ራስህን ጠብቅልኝ አሁን ካርመላ እየጠበቀህ ነው ሂድ ብላ ካሴቱን ተቀብላኝ ወደ ቦታው ልትመልስ ሄደች.....እኔም ፊቴን ተጣጠብኩና ወደ ካርመላ ሄድኩ የሚገርም ነበር በደስታ ፈክቶ እየጠበቀኝ ነበር እኔም በቪድዮው መገኘት ስለተደሰትኩ ሁለታችንም የሞቀ እና በደስታ የታጀበ ሰላምታ ተለዋወጥን፤

....ከዛም ቁጭ ብለን መነጋገር ጀመርን የያዝኩትን መረጃዎች አሳየሁት ሁሉንም አንድ በአንድ አያቸው ፊቱ ደስታውን መግለጫ ያጣ ፈገግታ ይነበብበታል ከዛም አይቶ ጨረሰና
....ቩራል! እኔ ለአመታት ላሳካው ያልቻልኩትን አንተ በወራት ፈፀምከው ግን አንድ ወረቀት ብቻ የለችም አለኝ!...ውይ!! እሷማ ቢሮ መሳቢያዬ ውስጥ እንዳስቀመጥኳት ረስቻት ነው እንጂ በጄ ገብታለች ሰው ልኬ እንዳላስመጣት ትኩረት እስባለሁ ብዬ ነው ነገ አይሀምን ወደዚህ ሳመጣ አብሬ ይዣት እመጣለሁ ደግሞ እነዚህ መረጃዎች አንተጋ ይቀመጡ አልኩት እሱ ላይ ሙሉ እምነት እንዳለኝ ለማሳየት..
....እሱም በጣም ተማምነናል ብሎ ስላሰበ በደስታ አነጋገር ቆይ ቩራል አንዴ አለና ኪሱን ዳበስ ዳበስ አደረገና የባንክ ቡክ አውጥቶ ሰጠኝ ቡኩን ስከፍተው ስሜ እስነ አያቴ ተፅፏል ቀጣዩን ገፅ ስከፍተው ባለ ብዙ ዜሮዎች ባለቤት የሆነውን ሁለት ቢሊዮን ብር ይላል ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም እምባዬ መጣ ወደሱ ጠጋ አልኩና እየቀፈፈኝም ቢሆን አቅፌ አባቴ ማለት ነህ መቼም አረሳውም ያደረክልኝን አልኩት
...አንተም ልጄ ማለት ነህ ለወደፊት ብዙ ስራዎችን እንሰራለን ነገ ደግሞ አይሀምን ወደዚህ እንዳመጣሀውና ፊርማውን አስፈርመን ድርጅቱን እንደተረከብን ትልቅ ድግስ እናዘጋጃለን እንደ ትልቅ በዓል እናከብረዋለን አለኝ
...እኔም እምባዬን እየጠራረኩ እርግጠኛ ነኝ የተሻለ ቀን እናደርገዋለን ቤት ውስጥ ደግሞ ለነገ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አዘጋጅቶ እንዲጠብቀኝ ነገሬው አይሀምን ደግሞ በተባለው ሰዓት ይዤው እንደምመጣ ቃል ገብቼለት ተሰነባብተን ወጣሁ

....በፈነጠዝያ ወደ ጋሽ አይሀም አመራሁ ጋሽ አይሀምን እስካገኘው መንገዱ ረዘመብኝ ስልክ ደወልኩና
....ጋሽ አይሀም ተሳካ! ተሳካ! እያልኩ ጮኩበት
.....እሱም መኪና እየነዳህ ነው እንዴ አለኝ!
.....አዎ አልኩት!!!
...እባክህ ተረጋጋ ከዚህም የበለጠ ደስተኛ ትሆናለህ ግን ያንተ መኖር ግድ ነው ቢሮ ነኝ እጠብቅሀለው አለኝ
.....የዛኔ ረጋ አልኩና እሽ ጋሼ መጣሁ ጠብቀኝ አልኩት ከዛም መኪናው ከመንዳት አልፎ እያበረርኩት ቢሮ ደረስኩኝ
ጋሽ አይሀም ከእስከ ዛሬው በተለየ በሚያምር ፈገግታ ተቀበለኝ እኔ ግን ገና ሳየው እምባዬ መጣ የሱ መደሰት ለኔ ትልቅ ነገር ነበር ምንም ሳልናገረው ተጠመጠምኩበት እና ትንፍሼ እየተቁረጠረጠ እ..እ..ጋሽ አይሀም አ..አ..አሳካንው በድል ተወጣንው አልኩት!!!
..አዎ! ልጄ ትክክል ነህ አንድ ነገር ይቀረናል እናትህን ነፃ ማውጣት አለኝ!!
....ችግር የለውም ጋሼ እናወጣታለን ነገሮችን አስተካክያለሁ አልኩት
......እሱም ዛሬ ከካረመላ ጋር የነበረንን ቆይታ ጠየቀኝ?
...ከመጀመሪያው ጀምሮ ተረኩለት እንዴት አድርጌ ቪድዮውን እንደደመሰስኩት ጭምር ሌላ ቪድዮ እንደጫንኩበት ግን አልነገርኩትም.....ከዛም ነገ አብረን ሂደን እስከ ዛሬ ሲመፃደቅበት የነበረውን ነገር መና እንደ ቀረ አሳይተን አንገቱ ማስደፋትና እማዬን ነፃ ማድረግ እሱም በደስታ እንደምናደርገውና የሚያስፈልገንን ነገር አዘጋጅን ወደ ቤት ሄድን

....መሽቶ አይነጋ የለም እና የተባለው ሰአት ደርሶ ጋሽ አይሀምን ይዤው ወደ ካርመላ ቤት ሄድን!!
..ከዛም ከመኪናው ልንወርድ ስንል ጋሽ አይሀም ሽጉጡን ከመኪናው አወጥቶ ሲይዝ አየሁት
....ቆይ!! ጋሽ አይሀም እሷ ነገር እኔ ጋ ትቀመጥ አልኩት!!
....አይ ችግር የለውም አለ
...ኧረ ለኢላማውም ለምኑም እኔ እሻለሁ ምናምን እያልኩ በመከራ አግባባውት...
......እሱም ፈገግ ብሎ እሽ እንካ አደራ! ግን አደራ! ለውሳኔ ግን እንዳቸኩል ቩራሌ አለኝ!!
....እሽ ብዬው እሱ ከመኪናው ቀድሞ ወረደ ከዛም እኔ! መቼም ካርመላ በጥበቃ ካሜራ እንደሚያየን ስለ ገመትኩ ደወልኩለት እና መጥተናል ከበር ነን አልኩት እንደገመትኩትም
...እያየሗችሁ ነው ግቡ አለኝ!!
....እሽ ብዬ ልወርድ ስል ምን አልባች ችግር ተከስቶ ሽጉጡን ብተኩሰው የጋሽ አይሀም አሻራ እንዳይገኝ ብዬ መልሼ ገባሁና በደምብ ወለወልኩት ጋሼም የቆየሁበት ጊዜ
.....ምን ነው ቆየህ ልጄ አለኝ
.......መጣሁ መጣሁ ጋሼ ብዬ ተያይዘን ወደ በሩ ሄድን እንደተለመደው ግን እማዬ አልነበረችም የከፈተችን ቀድሞ ነበር በሩ ተከፍቶ የጠበቀን!!
....በጣም ደነገጥኩ ምን አልባች ቪዲዮውን ቀድሞ አይቶት ባዶ ሲሆንበት ሁሉንም ነገር አወቀብን እንዴ እማዬንስ ምን አደረገብኝ እያልኩ ፈራ ተባ እያልኩ ወደ ውስጥ ገባን ስንገባ........

ከ500👍 ቡሀላ ይቀጥላል
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ስድስት(16)
#ድርሰት:- በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ
:
:
....በጣም ደነገጥኩ ምን አልባች ቪዲዮውን ቀድሞ አይቶት ባዶ ሲሆንበት ሁሉንም ነገር አወቀብን እንዴ እማዬንስ ምን አደረገብኝ እያልኩ ፈራ ተባ እያልኩ ወደ ውስጥ ገባን ስንገባ........
..... ስንገባ ወደ ጋሽ አይሀምን ጠጋ አልኩና ጋሼ ከሁሉም ነገር በፊት እማዬ መኖሯን ማረጋገጥ አለብን አልኩት፤
..ምንም ችግር የለውም እሱን በኔ ጣለው ባይሆን በደምብ አድርገህ ተውን አለኝ
...እሽታዬን ነገርኩትና ተያይዘን ወደ ሳሎን ገባን
...ከዛም ድራማው ተጀመረ የቤት ውስጥ ድባቡ በጣም ያስፈራል ፀጥ ብሏል ባለ ትልቅ ስክሪን ቴለቭዥን ግድግዳው ላይ ተሰቅሏል ጠረንጴዛው ላይ ብዙ ዶክሜንቶች ተደርድረዋል ካርመላ ከወደ አንድኛው የሶፋ ጫፍ አንድ እግሩን ታፋው ላይ ሰቅሎ አንገቱን ጠነን አድርጎ ተቀምጧል፥
...እንኳን ደህና መጣቹህ አለን
...ጋሽ አይሀም ቀበል አለና ቩራል ያልከኝ ስብሰባ ይሄ ነው ከዚህ አረመኔ ቤት ነው ያመጣኸኝ ወይኔ አንተን ማመኔ ብሎ ሊወጣ ሲል
....እየከበደኝም ቢሆን በስሙ ጠራሁት #አይሀም ወዴት ልትሄድ ነው ትንሽ የምንጫወታት ጨዋታ አለች ደግሞ ከአንተ በላይ አረመኔ መች አለ እና ነው ሰውን የምትሳደበው አልኩኝ
....ካርመላ ከተቀመጠበት ተነስቶ መጣና ትካሻዬን አቀፍ አደረጎ
...እንዴ አይሀም ገና ሳይጀመር እንዲህ ከሆንክ ወደ ቡሗላ ጨርቅህን ልትጥል ነው ማለት ነው አለና እንኔን እንዳቀፈኝ ወደ ጠረንጴዛው ይዞኝ ሄደ ጋሽ አይሀምም ተመለሰ
...ካርመላም በጆሮዬ ጠጋ ብሎ ያችን ትናንት አምጣት ያልኩህን ወረቀት እንድሰጠው ጠየቀኝ
.........እኔም ከኪሴ አወጣሁና ሰጠሁት እሱም ተቀብሎ አየና ጎዝብ ልጅ ቩራል ብሎኝ ዘወር አለና አቶ አይሀም እስኪ እዚች ጋር የተከበረ ፊርማዎትን ያሳርፉበት አለው
....ጋሽ አይሀም ተቀብሎ ምንም እንደማያውቅ ማንበብ ጀመረ ከትንሽ ቆይታ ቡሗላ አላደርገውም! ባ ጭራሽ አልፈርምም! ብሎ ጮኸ
...ካርመላም ተረጋጋ ተረጋጋ ገና ምን አይተህ! ቀዝቀዝ የሚያደርግህ ነገር ምን ይመረጣልህ አለው
..ጋሽ አይሀም ዝም አለው ምንም አልመለሰለትም
..ወደኔ ዘወር አለና አንተስ ምን ይምጣልህ ቩራሌ አለኝ በቁልምጫ
...በፍጥነት ውሃ ውሃ ይምጣልኝ አልኩት እሽ አይሀም አንተስ አትፈልግም አለው በድጋሜ
....ያንተን ደም መጠጣት ነው የምፈልገው አንተ አውሬ ነብሰ ገዳይ አለው
..እሱን እናያለን ሀሀሀሀሀ እያለ በፌዝ አኒሳ! አኒሳ! እያለ እየጮኸ መጣራት ጀመረ
የዛኔ በደስታ ፊቴ ፈገገ ጋሽ አይሀም አየኝና ፈገግታዬን እንዳቆም ሳያስነቃ በምልክት ነገረኝ እኔም ወዳው ፊቴን ኮስተር አደረኩኝ ከዛም እማዬ መጣች
...ጠሩኝ አቶ ካርመላ አለችው
... የት ሄደሽ ነው ይሄን ያክል የምታስጮኺኝ አላት በቁጣ
....ይቅርታ አቶ ካርመላ እ..ብላ ልትናገር ስትል፤ ወዳ ይቅርታውን ተይውና ቀዝቃዛ ነገር ይዘሽልን ነይ አላት
...እሽ ብላ ተለመልሳ ሄደች፤ ቀጥሎም ..
...ካርመላ ወደኛ ዘወር አለና #አይሀም እስከ አሁን ፊርማውን አልፈረምክም ማለት ነው እስኪ አንዲት ድራማ አለች ሳስበው ረስተሀታል መሰል ላስታውስህ አለና ከላፕቶፑ ሻንጣ ውስጥ የቪድዮ ካሴት አውጥቶ ማጫወቻው ዉስጥ ከተተው ውስጤ በጣም ፈራ ምክንያቱም ምን አልባት ኮፒ አስቀምጦ ከሆነ ብዬ ሰውነቴ ተርበተበተ ቀጥሎም ቪድዮው ያለበትን ፎልደር ከፈተው አንድ ቪድዮ አለ የዛኔ ጋሽ አይሀም በአይኑና አፉን እያንቀሳቀሰ ቪድዮውን እንዳላጠፍሁት ጠየቀኝ ዝም ብሎ ተረጋግቶ እንዲጠብቅ ነገረኩት
ከዛም ካርመላ ቪድዮውን ከፈተው ቪድዮው ግን መጫወት ሲጀምር ያየውን ማመን ያቃተው ይመስላል፤ ዘጋውና ደግሞ ከፈተው ምን አልባት ተሳስቼ ከሆነ ብሎ በድጋሜ ያው ምስል ነው
...ጋሽ አይሀም በአግራሞት ፊቱ ከጨረቃ በላይ ፈገገ፣ ካርመላ ግን ፊቱ ወዳው አመድ መሰለና ለሶስተኛ ጊዜ እንዲከፍት አዘዘው አሁንም በድጋሜ ያው ሆነበት በዚህ መሀል እማዬ የሚጠጡ ነገሮች ይዛ መጣችና
....እየው የታዘዝኩትን አለች ዘወር አለና ካርመላ አኑሪና ወደዛ ጥፊ አላት
...እኔም ጮክ አልኩና ብትፈልግ አንተ ጥፍ ገደል መግባት ትችላለህ እሽ እማዬ ወዴትም እንዳትሄጂ አልኳት
.....ከተቀመጠበት ብድግ አለና ምን አልክ እማዬ! እማዬ! የምን እማዬ ነው! ደግሞ የት አውቀሀት ነው ኣ ኣ ኣ እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፤ ከዛም እኔ የልብ የልቤን መናገር ጀመርኩ......ምን ነው ምን አስደነገጠህ የሰራሀው ስራ ታወሰህ እንዴ ያቺ! ቀን በመስኮት በኩል ሆኜ ስከታተል አባቴን አፍነህ ስትገድል እናቴን ደግሞ ምላሷን ስትቆርጥ ያኔ በዛ እድሜዬ ማየት የማይገባኝን ነገር አሳየኸኝ አባቴን ገለህ ወላጅ አልባ አደረከኝ እናቴን ደግሞ ገረድህ አደረካት እኔ መኖር የማይገባኝ ኑሮ እንድኖር አደረከኝ ያ አልበቃ ብሎጅ ሚስኪኑን ጋሽ አይሀምን ልታጠፍ እሱን አልፈቅድልህም ደግሞ እስከ ዛሬ ስነግርህ የነበረው ታሪክ እውነት የአይሀም ይመስልህ ነበር በጣም ሞኝ ነህ አዋቂ መሳይ ስለው
...በንዴት አንት ውሻ የውሻ ልጅ እሱን ወግነህ ልትጎዳኝ ነው ማለት ነው ገንዘቤን ትመልሳታለህ አንተንም አጠፍሀለው አለኝ
....እኔም የምን ብር ያ'ኮ የአባቴ ብር ነው የኛን ንብረት በሁለት ቢሊዮን እንደሸጥከው እማዬ ነግራኛለች አየህ ካርመላ ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳኒቱ የሚለውን አባባል አንተ እንድትማርበት ፈልገን ነበር እንዳሰብንው ተሳካልን እንደውም ካሰብነው በታች ነህ ስለው
....ድንገት ሳናስበው በመሀላችን ተንደርድሮ አለፈና በጀርባው በኩል ይዞት የነበረውን ሽጉጥ አወጣና እማዬ ላይ ደቀነባት እኔም የያዝኩትን ሽጉጥ አወጣሁ እና፤ ካርመላ እናቴን ልቀቃት ብዙ አመት ያንገላታሀት ይበቀሀል እሷን ልቀቃት እና እኔ ጋር ተነጋገር አልኩት በጣም እየጮኩ
....ጋሽ አይሀምም ስማኝ ካርመላ እኛ እንዳንተ አይደለንም አንድ ነገር መስማማት እንችላለን አንተም አኒሳን ልቀቃት እኛ ደግሞ ምንም አይነት ነገር ለፖሊስ አንናገርም አንተም እኛም ሂይዎታችንን ዳግም እንምራ ቩራልም ይቅርታ ያደርግልሀል እያለ ወደኔ ተጠግቶ ቆመ፤

....በጭራሽ አላደርገው ቩራል! የያስከውን ሽጉጥ መሬት ላይ ጣለው አለኝ
......ምን ብዬ ነው የምጥለው መጀመሪያ እናቴን ልቀቅ ካልሆነ ግን እደፍሀለው ስለው
....ጣል ብዬሀለሁ ጣል አለና ጭንቅላቷ ላይ አቀባበለው፤ምን አልባች ከተኮሰው ብዬ ፈራሁ ያኔ ለውድ ጓደኛው ለአባቴ ያልተመለሰ እናቴን ይጨርሳታል ብዬ አሰብኩ እናቴን ከገደለ ቡሀላ ብገለው ምን እጠቀማለው፤...እሽ በቃ እጥላለሁ ብዬ መሬት ላይ ሽጉጡን አስቀመጥኩ
...በእግርህ ወደኔ ግፋው አለኝ
......እሽ ብዬ ከሱ እንዲደርስ አድርጌ ገፋሁለት በጨረቅ አነሳና የራሱን ሽጉጥ ጀርባው ውስጥ ከተተና አሁን ከሁለት አንዳችን ካልሞትን በሰላም መኖር አንችልም አለና እማዬን ገፍትሮ የሽጉጡን አፈ- ሙዝ ወደኔ አዞረ
.....ጋሽ አይሀምም ተረጋጋ ካርመላ ራስህን ተቆጣጠር ልጅህን እና ሚስትህን አስብ አንተ አሁን አንዳችንን ከገደልክ መታሰርህ አይቀሬ ነው ያኔ ቤተሰቦችህ ምን ይውጣቸዋል አለው
....እኔ አይደለሁም የምታሰረው አንተ ራስህ ነህ እንጦረጦስ የምትገባው ብሎ ወደኔ አነጣጥሮ ተኮሰብኝ...

ቀጣይ ክፍል ከ500👍 እንደሞላ ይለቀቃል
👍4
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ሰባት(17)
#ድርሰት:- በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ
:
:
....ጋሽ አይሀምም ተረጋጋ ካርመላ ራስህን ተቆጣጠር ልጅህን እና ሚስትህን አስብ አንተ አሁን አንዳችንን ከገደልክ መታሰርህ አይቀሬ ነው ያኔ ቤተሰቦችህ ምን ይውጣቸዋል አለው
....እኔ አይደለሁም የምታሰረው አንተ ራስህ ነህ እንጦረጦስ የምትገባው ብሎ ወደኔ አነጣጥሮ ተኮሰብኝ...
....ሲተኩስ እማዬ ልጄ እያለች በጣም እየጮኸች እንደሆነ ይሰማኛል የትኛውን አካሌን በስቶ ሊገባ ነው የሚል ሀሳብ ውስጥ እያለው ጋሽ አይሀም ዘሎ ከፊቴ ቆመና የተተኮሰው ቀልሀ እሱ ላይ እንዲያርፍ አደረገውና እና መሬት ላይ ወደቀ በድንጋጤ እሪታዬን አቀለጥኩት፤ ካርመላ ሽጉጡን ጥሎ በሩጫ ከግቢው ወጣ ጋሽ አይሀም ልቡ አካባቢ ነበር የተመታው አንገቱን ቀና አድርጌ በጩኸት እያለቀስኩ.....ጋሼ አይሆንም! ጋሽ አይሀም እባክህን! ጥለኸኝ እንዳትሄድ እባክህ! ደግሜ አባት አልባ እንድሆን አታድርገኝ እያልኩ እምባዬን ማፍሰስ ጀመርኩ
.............እሱም በተቆራረጠ ድምፅ በስስት እያየኝ ባ...ባለፈው ያልኩህን ታ.. ታ.. ታስታውሳለህ! አንተ እንደ ልጄ ነህ ባንተ የመጣን ህ...ህ...ህይወቴንም ህ..ህ ቢሆን ሰጥቼ አድንሀለሁ ያልኩህ ከልቤ ነበር..

.....ጋሼ እባክህ ምንም አትናገር እማዬ አምቡላንስ ጠርታለች ቶሎ ወደ ሆስፒታል እንሄዳለን ምንም አትሆንብኝም፤
..ቩራሌ ሁሉም..ያሰብነው ነገር ተሳክቶልናል እኔም ከነ ክብሬ እሞታለሁ
......አዎ ተሳክቶልናል ግን አንተ እኮ ምንም መሆን የለብህም እቅዳችን እንደዚ አልነበረም፤ እ..እ የኔ ልጅ አንድ ሰው መስዋት መሆን ግድ ነው ደግሞኮ መይሙ በጣም በጣም ነው የምተወድህ የተፈጠረውን ሁሉንም ነገር ስነግራት ከደስታዋ እና ሀዘኗ ብዛት መቋቋም ስላልቻለች ነው ፍቃድ ብላ ስራ ያቆመችው ትመጣለች ጠብቃት ም..ም..ምክንያቱም እሷ ብዙ አመታት ጠብቃሀለች መቼም እንዳታስቀይማት አለኝ
...በመሀል እማዬ የአምቡላንስ ሰራተኞቹ ጋር ደረሰች ከዛም አንስተው ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ
...እጄን ያዘኝ አለኝ እኔም እጁን ይዤ ወደ ክሊኒክ ለመሄድ አምቡላንሱ ውስጥ ገባን ከዛም መንገድ ላይ እያለን ተሰክቶለት የነበረውን መተንፈሻ አወለቀና እጄን ይዞ
...ቩ..ቩራሌ አንድ ነገር ቃ..ቃል ግባልኝ አለኝ፤
..ኧረ ጋሼ በፈጠረህ ለኔ ስትል ተስፍ አትቁረጥ ብዬ እጁን ሳምኩት፤
ቢሆንም ግን #ኒሀልን እና #ሲቱ እንደ እህቶችህ እናታቸውን ደግሞ እ..እንደ እናትህ ልትንከባከባቸው ቃል ግባልኝ አለኝ በተቆራረጠ ድምፅ፤
....ኧረ ጋሼ እንደሱ እያልክ ሆዴን አታባባው ብዬ ከአንገቱ ቀና አድርጌ አቀፍኩት፤
..እባክህ ቩራል ልጄ እባክህ አለኝ
.....እሽ እሽ ቃል እገባለሁ ጋሼ አልኩት አይኔ በእምባ ተሞልቶ
...እተማመንብሀለሁ እ.. እ ህ.. ህ ብሎ በጄ እንዳቀፍኩት አይኑን ጨፈነ በዛው ቅፅበት ሰውነቱ ዛለብኝ፤ እየተጣራው ልቀሰቅሰው ብሞክር መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም፤ ህይዎቱ አልፍለች
.....መቋቋም አልቻልኩም እንዳቀፍኩተት ማልቀስ ጀመርኩ አይሆንም! አይሆንምን! እባክህ እባክህን! ጥለኸኝ አትሂድ! እያልኩ ብጮህም እሱ ግን ላይመለስ ሄድዋል፤
...አብረውኝ የነበሩት ነርሶች እንድረጋጋ እየነገሩኝ ሆስፒታሉ ጋር ደረስን ከወረድን ቡሗላ ወደ ሬሳ ምርመራ ክፍል ይዘውት ሄዱ እማዬ በታክሲ ተከትላን ስለነበር ብቻዬን እያለቀስኩ ስታገኘኝ
......ምን ተፈጠረ ልጄ ምንድን ነው እያለች ተጠጋችኝ
...እየተንሰቀሰኩ ወደ እቅፏ ጠጋ ብዬ ጥሎኝ ሄደ እማዬ ላይመለስ ሄደ አልኳት እሷም
....እያነባች ካርመላ የጁን ያገኛል ሞትን እስኪመኝ ድረስ በህይወቱ ይቀጣታል ሁሉንም ነገር ለፖሊስ አሳውቂያለሁ ከእናቱ ሆድ ቢገባ አያመልጥም አለችኝ፤

....እኔ ግን ሀሳብ የሆነኝ እንዴት ብዬ ነው ለነ ሲቱ አባታቹህ ሞተ ብዬ የምነግራቸው ያውም በኔ ምክንያት ምን ነው እዛው ጫካ ውስጥ በቀረው የቲም ከማደርጋቸው እያልኩ ነበር፤
ከቆይታ ቡሗላ አንዱ ዶክተር መጥቶ፤
.....ምርመራ ስለጨረስን ለቀብር እንድንዘጋጅ እና መፀናናትን ተመኝቶልን ሄደ እኔም ከቢሮ ለአንዳንድ ሀላፊዎች ደውዬ ጋሽ አይሀም ማረፉን እና ቀብሩን የሚያስፈፅም ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲያቋቁሙ ነገርኳቸው የሆስፒታሉንም አድራሻ ሰጠሗቸው
......ከዛም እኔ እማዬን ከዛው እንድትጠብቃቸው ነግሪያት ወደ ቤት ሄድኩ
....ሲቱ እንደለመደችው ወንድሜ ቩራል እያለች መጣች እንዴት ብዬ አኗን ልየው ዝም ብዬ እቅፍ አድርጌ ወደ ቤት ይዣት ገባሁ ደጋግማ ስሜን እየጠራች ምን እንደሆንኩ ትጠይቀኛለች እኔ ግን እምባ እየናነቀኝ ዝም ብያት ገባሁ ሳሎን ስደርስም ኒሀል ከእናቷ ጋር ቁጭ ብላለች ሲቱ አወርጄ ሶፍው ላይ ቁጭ አልኩኝ ፊቴ ስለተለወጠ እነሱም በድንጋጤ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ጀመር እኔ ግን ምን ልበላቸው አባትቹህ ካርመላ ተኩሰሶት ሞተ አይ እሱን እንኳ አልልም ኒሀል ከጣገቤ መጥታ ቁጭ ብላ ደጋግማ መጠየቅ ጀመረች ጋሽ ጋሽ አይሀም ከማለቴ፤ አባቴ ምን ሆነ ንገረኝ አለችኝ፤ አርፏል ብዬ ሳልጨርስ ቤቱ በጩኸት ተናጋ እኔም እንደ አዲስ አብሬ አለቀስኩኝ ከዛም እንደ ምንም እራሴን እየተቆጣጠርኩ እነሱን ማረጋጋት ጀመርኩ እነሱም፤
...አንድ ጊዜ ለመጨረሻ ፊቱን ማየት እንደሚፈልጉ ነገሩኝ እኔም ወደ ክሊኒኩ ይዣቸው ሄድኩኝ ከዛም አስክሬኑን ገብተን አየን በጣም ከባድ ነበር መቼም ልረሳው የማልችለው ነበር ኒሀል ተሰናበቱ የተቋቋመው ኮሚቴም ለቀብሩ የሚያስፈልጉ ነገሮች ተዘጋጅቶ ስለጨረስን ወደ ቀብር እንሂድ ብለው አስክሬኑን ይዘን ወደ መቃብሩ ሄድን ከዛም ሊቀበር ወደተዘጋጀበት ወደማይቀርበት አለም የሚሄደውን ጋሽ አይሀምን ልቤ እየደማ አይኔ በእምባ እያተጠበ ተሰናበትኩት በአንድ ቀን #ለሁለተኛ ጊዜም ደፈረኩት #የመጀሪያው አይሀም ብዬ ጠራሁት አሁን ደግሞ አፈር ለማልበስ ደፈርኩት ይገርማል እያልኩኝ በውስጤ ወደ ሗላ ስዞር የሰው ብዛት እንደ ማዕበል ሁኗል የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን የቴሌቪዥን ስርጭቶች በዳር በዳር ደግሞ በርከት ያሉ ፖሊሶች አሉ!፤ አይ ፖሊስ ከአሁን ቡሗላ ጣልቃ እንዳትገቡብኝ ያኔ አባቴ ሲገደል ምንም ሳይሉ በዝምታ አለፉ አሁን ደግሞ ያልጠገብኩትን ሁለተኛ አባቴ ተገደለ የሁለቱንም ገዳይ መግደል እንጂ ሌላ እንደማልፈልግ ለራሴ ቃል ገባሁ፤ ከዛም ቀብሩን ጨርሰን ወደ ቤት መሄድ ስንጀምር እንዳልኩትም እነዛ ፖሊሶች ወደኔ መጡና
...አቶ ቩራል አሉኝ
....አዎ ነኝ ለጥያቄ ምናምን ከሆነ ነገ አናግሩኝ አልኳቸው
....ይቅርታ አቶ ቩራል ለጥያቄ አደለም በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው ብለው ወረቀት ሰጡኝ አነበብኩ እና በምን ምክንያት አልኳቸው እሱን እዛው እንነጋገራለን ብለው እጄን በካቴና ሲያስሩኝ ሁሉም ቀረፃ ላይ የነበሩ ሰዎች የካሜራ አይኖቻቸውን ወደኔ አዞሩ......

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍2
መኖርን ባልታሰበ የመጨረሻ ክፍል ነገ የሚለቀቅ መሆኑን ከይቅርታ ጋር ለመግለፅ እወዳለው👍😘😘 ለትዕግስታቹ እናመሰግናለን👏
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ስምንት(18)(የመጨረሻ!)
#ድርሰት:- በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ
:
:
....ይቅርታ አቶ ቩራል ለጥያቄ አደለም በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው ብለው ወረቀት ሰጡኝ አነበብኩ እና በምን ምክንያት አልኳቸው እሱን እዛው እንነጋገራለን ብለው እጄን በካቴና ሲያስሩኝ ሁሉም ቀረፃ ላይ የነበሩ ሰዎች የካሜራ አይኖቻቸውን ወደኔ አዞሩ......

...እኔን ጥያቄ ለመጠየቅ አንዱ ከአንዱ ላይ ይረባረባል አቶ ቩራል ለምንድን ነው የታሰርከው! አቶ ቩራል የገደልከው አንተ ነህ እንዴ! የሚሉትን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ጫጫታ በሚመስል መልኩ ሲያጨናንቁኝ ፖሊሶች በጎን እና በጎኔ አጅበውኝ በእጃቸው መንገዱን እየከፈቱ ወደ መኪና ውስጥ አስገብተው ወደ ጣቢያ ይዘውኝ ሄዱ እዛ እንደደረስኩም ወድያው ወደ ምርመራ ክፍል ሊያስገቡኝ ሲሉ እነ ኒሀል እና እማዬ መጡ እማዬ እየሮጠች መጥታ...ልጄን ልቀቁት ልጄን ልቀቁት እሱ ምንም አላደረገ እያለች መጮኽ ጀመረች

.....አንዱ ፖሊስም የኔ እናት ይሄ ስራችን ነው ሁሉንም ነገር ደግሞ በመረጃ ላይ ተመስርተን ነው የምንሰራው ምስክርነት ለመስጠት ከፈለጉ ቃላችሁን መስጠት ትችላላቹህ ችሎት ላይም መገኘት ይችላሉ አላት እና እኔን ይዘዉኝ ወደ ውስጥ ሊገቡ ሲሉ አንዴ እንድናገር ጠየኳቸው እነሱም ፈቀዱልኝ ና ዘወር ብዬ
....ኒሁ እንዳላደረኩት ታውቂያለሽ ኣ አልኳት አምንሀለው ወንድሜ ቩራል አለችኝ!
እሽ ኒሁ አደራ ደግሞ እማዬን እስክፈታ ድረስ ጠብቂልኝ አልኳት እሷም አንገቷን እነቀነቀች እሽታዋን ነገረችኝ
........ከዛም ይዘውኝ ገቡ እና በጥያቄ መጨቃጨቅ ጀመሩ ለምን ገደልከው እንዴት አድርገህ ገደልኩው አንተ ልትገለው ካልፈለክ ለምን ወደዛ ቤት ወሰድከው የሚሉ ጥያቄዎች ወድጄ እስክጠላ እስኪያንቀጠቅጠኝ ድረስ ጠየቁኝ ምንም እንዳላደረኩ ስመልስላቸው
.....የኔ አሻራ ብቻ ያለበትን ጋሽ አይሀም የተገደለበትን ሽጉጥ አመጥተው አሳዪኝ ምን ልበል በምንስ ቋንቋ አስረድቼ ላሳምናቸው ምንም ማለት እነወደማልችል ሳውቅ ክርክሩም ስለደከመኝ እንደገደልኩት አመንኩላቸው እነሱም ከአንድ ሳምንት ቡሗላ ችሎት እስክቀርብ ማረፊያ ቤት ወሰዱኝ ከዛም ለአንድ ሳምንት መቆየት ግድ አለኝ
....ብዙ የዕስር ቤት ልጆች ጋር መተዋወቅ መላመድ ቻልኩኝ ሁሉም የታሰረበትን ምክንያት እናወራ ነበር አንዱ ያለ ጥፋቱ ሌላው ሰርቆ ሰው ደብድቦ በቻ ብዙ ብዙ በየ ቀኑ ደግሞ እነ እማዬ ይመጡ ነበር
......ኒሀል በመጣች ቁጥር አላደረከውም ያለ ጥፍትህ አትቀጣ እያለች ሀሳቤን እንድቀይር በጣም ትገፍፍኛለች፤
ግን ምን ላድርግ ከአቅሜ በላይ ነው.........
እያንዳንዷ የእስር ቀን ግን ስለ መይሙ አስባለው አንድም ቀን ልትጠይቀኝ አልመጣችም ምን አልባት የእውነት ገዳዩ እኔ መስያት ይሆን እያለኩ አዝናለው ድጋሜ እንድትጎዳ አደረኳት
ብዙ ነገሬን ያሳጣኝ ካርመላ ግን በነፃነት ይኖራል ምን አልባት ሊሸነፍ የማችል ሰው ነው ብዬ አስባለው፤
የማይነጋ ሌሊት እና የማይመሽ ቀን የለምና ያቺ የችሎት ቀን ደረሰች እኔም ከማረፊያ ቤት ወደ ችሎት ቦታው ይዘውኝ ለመሄድ አጃቢ ፖሊሶች መጥተው ጠሩኝ እኔም የአንድ ሳምንት ጓደኞቼ ጋር መልካም እድልን ተመኛኝተን ፖሊሶቹ ጋር ወደ ቦታው ሄድን ወደ ውስጥ ስገባ ከወደ አንድኛው አቅጣጫ በኩል እማዬ ኒሀል እና እናቷ ተቀምጠዋል እኔን ሲያዩኝም በ አይናችን ሰላም ተባባልን ወደዛኛው በኩል ሳይ ደግሞ ካርመላ ከአንድ ጠበቃ ጋር ቁጭ ብሏል ዘልዬ ባንቀው ደስታዬ ነበር ግን ምን ያደርጋል በድጋሜ አሸነፈኝ በኔ ላይ ሊመሰክር እንደመጣ ደግሞ የታወቀ ነው እያልኩ በተከሳሽ ቦታ ሂጄ ቁጭ ልል ስል አንድ
...የጠበቃ ልብስ የለበሰ ሰው ሰላም አቶ ቩራል ኢምራን እባላለው ተጠበቃህ ነኝ አለኝ እኔም ተዋወኩትና ዳኛው ገባና ችሎቱ ተጀመረ በቅድሚያ ምስክሮች እንዲወጡ ታዘዙ እንደጠበኩትም ካርመላ ወጣ እማዬም ለኔ ስለምትመሰክር እሷም ወጣች ከሳሽ የነበረው
.......አቃቢ ህግ ስለ ነበር በጠበቃቸው በኩል ብዙ አንቀፆችን እያወሳ እኔን ወንጀለኛ ስለሆነ ብዙ አመት እስር እንዲፈረድብኝ እና ለዚህም ሽጉጡን እና የካርመላ ቃል እንዳላቸው ተናገረ
.....የኔ ጠበቃም አንድ ሳያስቀር ሁሉንም ነገር ብትንትን አድርጎ ተናገር በጣም ገረመኝ እማዬም አንድም ነገር ሳታስቀር ነግራዋለች ዳኛውም ምስክሮች እንዲገቡ አዘዘ
......መጀመሪያ ካርመላ ገባና ውሸቱን መደርደር ጀመረ መጀመሪያ ላይ አይሀምን ቤቴ ውስጥ ይዞት መጣና ስለ ስራ ብዙ ነገር አውርተን ተወያይተን ጨረስን እና ከሁለታችንም ድርጅት አክሲዮን ስጡኝ አለ እኛም ተስማምተን ሰጠነው እሱ የሰጣችሁኝ ያንደኛል በሚል ተልካሻ ምክንያት አሻፈረኝ ብሎ ሽጉጥ ሲያወጣ እኔ አመለጥኩ ያ ውዱ ጓደኛዬን ደግሞ በሽጉጥ ደፋው ብሎ የአዞ እምባውን አፈሰሰ
.....የኔ ጠበቃም ተነስቶ ስለ እማዬ ጠየቀው እሱም እንደማያውቃት እና ሊረዳት ብሎ እንደቀጠራት ተናግሮ ጨረሰ እና ቁጭ አለ
.........እማዬም ገባች እና ስለ ተፈጠረው ሁሉንም ነገር አስረድታ ቁጭ አለች ዳኛው ግን የእማዬን ምስክር ከምንም እንዳልቆጠረው ከፊቱ መረዳት ያስችላል እናም ዉሳኔ ብሎ ፍርዱን መናገር ጀመረ።።።።።።።።

፨፨፨ ከደቂቃዎች ቡሀላ ይቀጥላል ፨፨፨፨
👍51🥰1
..............የቀጠለ

.........እማዬም ገባች እና ስለ ተፈጠረው ሁሉንም ነገር አስረድታ ቁጭ አለች ዳኛው ግን የእማዬን ምስክር ከምንም እንዳልቆጠረው ከፊቱ መረዳት ያስችላል እናም ዉሳኔ ብሎ ፍርዱን መናገር ጀመረ
ዉሳኔ ብሎ ፍርዱን መናገር ጀመረ በከሳሽ አቃቢ ህግና በተከሳሽ አቶ ቩራል ነምሩድ ዛሬ በዋለው ችሎት ግራ ቀኙ የተስማማበትን ውሳኔ እንደሚከተለው ነው ብሎ ሊቀጥል ሲል
.....ከወደ ውጭ የሁለት ሴቶች የጩኸት ድምፅ ችሎቱን ረበሸው ምን እንደሆነ እንዲያጣራ እና ፀጥታ እንዲያስከብር ዳኛው ፖሊሱን ላከው ፖሊሱም ወጥቶ አየና ሁለት ሴቶች መግባት እንደሚፈልጉና መናገር የሚፈልጉት ነገር እንዳላቸው ነገረው እሱም እንዲገቡ ፈቀደላቸውና ወደ ውስጥ እስኪገቡ አይኔን በሩ ላይ ጣልኩ መጀመርያ አንድ የማላውቃት ልጅ የያዘች ሴት እና ከሗላዋ መይሙ ተከትላት ገባች ካርመላ ከተቀመጠበት ብድግ አለ ዳኛው ተቀመጥ አለው እሱም መልሶ ተቀመጠ ከዛም ምን እንደፈለጉ ማን እንደሆኑ ጠየቃቸው
....ባለ ልጇ የካርመላ ሚስት መሆኗን ተናገረች እና ፍርድ ቤቱ ሊያተው የሚገባ ነገር አለ ብላ ሁለት የቪድዮ ካሴት ሰጠችው ምን እንደሆነ ጠየቃት ቩራል እውነተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ካሴት ነው አለችው እሱም እንዲከፈት አዘዘ ቪድዮው ከቤት ውስጥ በድብቅ ካሜራ የተቀረፀ ቪድዮ ነበር ሁሉንም ነገር የያዘ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ቤት ውስጥ ለጥንቃቄ ብሎ የገጠመው ካሜራ ነበር
....ካርመላ ደነገጠ
....ዳኛው ደግሞ ካርመላን ወደ ፊት እንዲመጣ አዘዘው
....የካርመላ ሚስትም አንድ ነገር መናገር እንደምትፈልግ ነገረችው እሱም ፈቀደላትና
ስለ ካርመላ መዘርዘር ጀመረች ከአመታት በፊት አንድ ባል እንደነበራትና አቶ ካርመላ ለገንዘብ ብሎ እንዳስገደለው እሱን ለመበቀል ብላ በወቅቱ የሁለት ወር እርጉዝ ስለነበረች ካርመላ በመቅረብና እንዳረገዘችለት በማስመሰልና ይች የወለድኳት ልጅ የሱ እንደሆነችም እንዳሳመነችው እና እሱን የምትቀበልበት መንገድ በዚህ መልኩ በመሆኑ እንዳስደሰታት ይሄን እድል ለሰጣቻት መይሙናን አመስግና ቁጭ አለች.....
......ካርመላ ያ ፊቱ አመድ መሰለ የሱ ልጅ አለ መሆኗን ደግሞ ጭራሽ አምኖ መቀበል አልቻለም

....በወቅቱ ሴትዮዋ የ ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ውጤት የያዘ ወረቀት ለማስረጃነት ለፍርድ ቤቱ ሰጠች
.......እኔ እና እነ እማዬ በደስታ ፈነጠዝን ክሱም ወደ ካርመላ ዞረ በአንድ ጀምበር ደስታዬን አጥቼ ነበር አሁን ደግሞ በአንድ ቀን ውሎ ደስታዬን ላገኝባት ዳኛው ለኔ ሊፈርድ የነበረው ለሱ ፍርድ ብሎ ማንበብ ጀመረ
....አቶ ካርመላ ለሰሩት አሰቃቂ ወንጀል አስተማሪ ነው ያለውን የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል አለ እኔን ደግሞ በነፃ ለቀቁኝ ማመን አልቻልኩም በተለይ መይሙን በጭራሽ ህልም ነው የሆነብኝ በደስታ ወደ ቤት ሄድን ደስ የሚልም ምሽት አሳለፍን ......

💫💫ከስድስት ወር ቡሗላ 💫💫
... ዛሬ የሚገርም እና ለኔ ታላቅ ቀን ነው ምክንያቱም የኔ እና የመይሙ የሰርግ ዝግጅት ቀን ነው ስለ ሰርጋችን በሀሳብ ተመስጬ እያለው እነ ኒሀል በጩኸት ይጣራሉ
.....ምን ተፈጠረ ብዬ እየሮጥኩ ሄድኩኝ ተመልከት ተመልከት አሉኝ ወደ ቲቪው ሰበር ዜና ከማረሚያ ቤት አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት የሶስት ሰውን ህይዎት ያጠፋው እና እድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አቶ ካርመላ ሽንት ቤት ውስጥ በራሳቸው ሸሚዝ ራሳቸውን ሰቅለው መገኘቱን ታውቋል የሚል ነበር በጣም ደስ አለኝ ምክንያቱም ሁለት አባቶቼን የተሰቃዩትን ስቃይ መቅመሱ አረካኝ፤ ከ ሶስት ቀን ቡሗላ እኔ እና መይሙ የምንዳርበት ቀን ነው መልካሙን ተመኙልን እኔ እዚጋ ጨረስኩ ህይዎት ግን ይቀጥላል።
አልተፈፀመ

ፀሀፊውን ለማግኘት👉 ከድር አወል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍42
የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "ከረመዳን ወር በመቀጠል ፆም በላጭ የሚሆንበት ወር የሙሀረም ወር ነው።"
ሶሒሁ ሙስሊም(1163)

ይህ አሁን ያለንበት ወር የሙሀረም ወር በመሆኑ ታላላቅ የፆም ቀናቶች ይገኙበታል።

☆ ጁምዓ (ከአሹራ በፊት ያለው ዘጠነኛው ቀን ነውና ይሄን ቀን መፆም ይወደዳል)፣

☆ ቅዳሜ (አሹራ ነውና እንፁም የአንድ አመት ወንጀል ያስምርላችኃል)፣

☆ እሁድ (አሹራን አስከትለን እሱንም መፆም ይወደዳልና እንፁም)፣

☆ ሰኞ (ይህ ቀን ስራችን ከአላህ ዘንድ የሚቀረብበት ቀን ስለሆነ እንፁም)፣

የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "ሌሎች ሰዎችን ወደ መልካም ስራ ያመላከተ ልክ እርሱም ያን ስራ እንደሰራው ተደርጎ ይያዝለታል።"
ስለዚህ ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን ኢንሻአሏህ!

@ketibeb
2
❥:::::::::::መልካም ጎደኛ::::::::::❥

❥ኢማሙ አል ሻፊዒ እንዳሉት ❥
🌴 የጀነት ሰዎች ጀነት በገቡ ጊዜ በዱንያ ላይ በመልካም ነገር ላይ የነበሩ ጎደኞቻቸውን ጀነት ውስጥ ሲያጧቸው አሏህን እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ

" ጌታችን ሆይ ከኛ ጋር ሲሰግዱ እና ሲፆሙ የነበሩ ጎደኞች ነበሩ ጀነት ላይ አጣናቸው " ብለው ይጠይቃሉ ፡ አሏህም እንዲህ ይላቸዋል ፡ ወደ እሳት ሂዱና ከቀልቡ የዘር ፍሬ የምታክል ኢማን ያለውን ሰው አውጡ ይላቸዋል ,

ሀሰን አል በስሪ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ ፦

ሙእሚን የሆኑ ጎደኞችን አብዙ 、 የቂያም ቀን አሏህ በፈቃዱ መሸምገልን ይሰጣቸዋል እና,
ኢብኑ አል ጀውዚ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ ፡

❥☞በጀነት ውስጥ በመካከላችሁ ካጣችሁኝ , ስለኔ ጠይቁ ፡ ጌታችን ሆይ ያ ባሪያ በዱንያ ላይ ስላንተ ያስታውሰን ነበር የት አለ በሉ ከዛም አለቀሱ።

❥☞ ወዳጆቼ በጀነት ውስጥ ካጣችሁኝ ስለኔ ጠይቁ ምናልባትም በአሏህ መንገድ ላይ አንድ ጊዜም ቢሆን ስለሱ ታላቅነት ፣ ፈጣሪነት አስታውሻችሃለሁና።

❥አሏህ ሆይ ! ያንተን ትእዛዝ በመፈፀም ላይ የሚያበረታቱኝን መልካም ጎደኞች አብዛልኝ ወዳጆቼም ጋር በጀነት አል ፊርደውስ አንድ ላይ ሰብስበኝ ...አሚንንንንን🤲🤲#ሼር

t.me/ketibeb
t.me/ketibeb
👍21
ልጄ ሆይ! ይህች ዓለም ጥልቀት ያላት ባህር ናት ። በርካታ ሰዎች በውስጧ ሰጥመዋል ። በርሷ ላይ ስትጓዝ የአላህን ፍራቻ ሰፊናህ አድርግ። ነዳጇ ኢማንልህ ይሁን ። በአላህ መመካትን (ተወኩልን) መንገድህ አድርግ ። ከመስመጥ ትድናለህና » ሉቅማኑል ሀኪም
2👍1
عبدالعزيز الزهراني - فما ظنكم برب العالمين 1435هـ
[ تلاوات خاشعة ▫️ tvquran@ ]
💚ማራኪ ቲላዋ💚
▫️• فَمَا ظَنُّكُمْ بِرَبِّ الْعَالَمِينَ •▫️

• القارئ ؛ #عبدالعزيز_الزهراني
• ቃሪእ አብደል አዚዝ

JOIN ⇒ https://t.me/Ketibeb
JOIN ⇒ https://t.me/Ketibeb