ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ስድስት(6)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

.....ኧረ በጭራሽ #ካርመላ የሚባል አረመኔ ከምድረ ገፅ ያጥፍኝ ብለህ ነው ከማለቴ ድንጋጤና እብደት በተሞላበት ስሜት ምን! ማን ነው ያልከው ካርመላ! ካረመላ! እያለ መጮህ ጀመረ...
......በሁኔታው በጣም ተደናገጥኩ የማደርገው ቅጡ ጠፋኝ እንደምንም ብዬ አግባብቼ ቀስ አድርጌ እንዲቀመጥ አደረኩት.....ከዛም ምን ሆነህ ነው አልኩት፥ ከእግሬ ስር ተምበርክኮ ይቅር በለኝ! እባክህን ይቅር በለኝ! ልጄ እያለ ይማፀነኝ ጀመር ፤ምንም ነገሩ ስላልገባኝ ኧረ! ጋሽ አይሀም ራስህን ተቆጣጠርና ምን እያደረክ ነው አንተ ምን አድርገከኛል ብለው ሊሰማኝ አልቻለም እሽ በስርዐት አስረዳኝ አልኩት ""እ..እ..እ...ነምሩድ ልጅ እንዳለው አላውቅም ነበር ለፖሊስ ባለማጋለጤም ጥፋተኛ ነኝ፤ ግን እመነኝ ሳልፈልግ ቀርቼ ሳይሆን ማስረጃ ስላልነበረኝ ነው"" አለ እምባውን እያንጠበጠበ፥
......... እኔ ግን ነገሮች ይበልጥ ተወሳሰቡብኝ፤ ምን ለማለት ፈልገህ ነው አልኩት ኮስተር ብዬ
.....""ባለፈው ታስታውሳለህ ስለ ራሴ ስነግርህ እኔን ከዚ ሁሉ ጣጣ የከተተኝ ሰውዬ! የሰራውን ወንጀል እንደማጋልጠው የዛትኩበት ካ..ካ..ካርመላ ነው"" አለ፥ በተቆራረጠ ድምፅ.

ስሜቴ የተደበላለቀ ሆነ እምባዬ እየተናነቀኝ እግሬን ከሱ አላቅቄ ጥዬው ሄድኩኝ ከዛም ብቻዬን ለብዙ ሰኣት ራሴ ጋ አወራው ጥሩው ነገር ቀድሞ ስለራሱ ስለነገረኝ በሱ ላይ መፍረድ አልቻልኩም...ወደሱ እየመሸ ስለነበር ወደ ማደሪያችን ተመልስኩ ጋሽ አይሀም በፀፀት እና በቁጭት ስሜት ውስጥ ሆኖ አንገቱን ደፍቶ አገኘውት ደሱ ቀረብ አልኩና ጋሽ አይሀም ስለው
.....እረዳሀለው ልጄ ልክ ነህ ግን አማራጭ አልነበረኝም አለ...አዎ ልክ ነህ ሁሉንም ነገር አስቤበታለው ቢያንስ እሱን እነጦሮጦስ ለመክተት አናንስም አሁን ሁለት ሆነናል፥ ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ አይደል የሚባለው"" አልኩና አቀፍ አርጌ አነሳሁት...ግን ይቅር በለኝ ልጄ ማለቱን አላቆመም ጋሽ አይሀም ከልቤ ይቅር ብዬሀለው እንዳያስስብህ ብዬ እየተሳሳቅን ገባን

...... ከዛም ቀን ጀምሮ እቅድ ማውጣት ጀመርን ሁሉም ነገር አንድ በአንድ እንዴት አድርገን መበቀል እንዳለብን ሙሉ ፕላኑን አዘጋጀን፥ እንደዚ አይነት እቅድ ፊልም ላይ ነበር ያየሁት አሁን በገሀዱ አለም ልጋፈጥ ነው..ቀናቶች እየተቀያየሩ ወራቶች አለፉ! እንሆ ዛሬ ጋሽ አይሀም ጋር ከተገናኘን ሶስት ወር አለፈን፤..ዛሬ ለኔ ታላቅ ቀን ነው ከስድስት አመት በላይ ከመሸኩበት ጫካ ወጥቼ በድጋሜ #ኑሮዬን ባልታሰበዉ መንገድ ልመራ ለመውጣት እየተዘጋጀን ነው..... ይህ ነገር ለኔ በጣም ትልቅ እድልም ነው በህልሜ እንኳን አልሜው የማላቀው ነገር፤ ከጫካ ው መዉጣታችን ደግሞ የበቀል ጅማሬውን ማብሰሪያ ነው! ዋሻችንን ተሰነባብተን ከጫካው ወጣን ከእስር የተለቀኩ ያክል ነው የተሰማኝ፤ ቅጠሎችና ሀረጎች አልፍ ከኔ የምትደርሰው ፀሀይ ዛሬ በፎቆች መካከል በነፃነት ከአመታት ቡሗላ ተያየን!....ከኪሱ ዉስጥ ለወራት እየተቆራመተች በቆየችው ሀምሳ ብር ታክሲ ይዘንባት መሄድ ወደቤቱ አመራን፤

አቤት! የሰው ነገር ታክሲ ለይ ተሳፍረን እየሄድን ሳለ የኛን የልብስ መቆሸሽ አይተው ለመጠጋት እንኳ ሲፀየፉ! ለጡሩ ለባሾች ሲያጎበድዱ የነበሩ ሰዎችን እያየን ለኛም ለነገ ትምህርት ነውና በትዝብት ከምንፈልገው አካባቢ እንደደረስን ወረድን...አካባቢው ፀጥ ያለ ነው ከወረድንባት ቦታ እስከ ቤት የአምስት ደቂቃ የሚሆን መንገድ አላት ወደ ሰፈሩ ውስጥም እየገባን ሳለ ሰወች እየዞሩ በዚህ ባለሀብት ሰፈር ውስጥ እነዚህ ቡቲቶ ለቤሽ ሰወች ምን ይሰራሉ የሚል አስተያየት ያዩናል፤....ግን እኮ አብዘሀኛው የሰው ልጅ ስንባል የሰውን ማንነት በልብስ ነው የምንለካው እያልኩ ለራሴ እየነገርኩ ከቤቱ ደረስን መሰለኝ! ጋሽ አይሀም እዚ ጋ ነው ብሎ ወደ በራፉ እንድጠጋ አመለከተኝ ከዛም የጥሪ ደወሉን ተጫነዉ!.....ማን ነዉ! መጣን! መጣን! የሚል ጎርነን ባለ ድምፅ ከወደ ውስጥ ሲናገር ይሰማል...ከዛም በሩ ተከፈተ እንደጠበኩትም የገጠር ሰው አክት ያለው ጎልማሳ ሰውዬ! ነው! ....ምንድን ነዉ! ምን ፈልጋችሁ ነዉ አለ!

ትብዝቴ በዛብኝም እንደው በአክብሮት እንኳ ቢያናገረንስ ለነገሩ የጋሽ አይሀም ፂሙና ፀጉሩ ስላደገ መለየት ያቃተዉ ይመስላል፥.. ከዛም ጋሽ አይሀም ምንም ሳይናገር ፈገግ አለ የዛኔ አንዴ ጋሼ ነሁ እንዴ! አለና ዘሎ ወጣበትና የመንከስ ያክል አዟዙሮ አዟዙሮ ሳመውና ወደውስጥ ገባ ብሎ እልልታውን አቀለጠው ልጆቹ ምን ሆነ ብለው እየተሯሯጡ ሲመጡ አባታቸዉ ነው አባቢ! አባቢ! እያሉ መጥተዉ ወጡበት አየሳሙ አቅፈው ምን ሆነህ ነው እያሉ እያካለቡ ይዘዉት ሊገቡ ሲሉ ና! እንጂ ግባ አትፍራ አለኝ! አንድኛዋ ልጅ ቀጠል አድርጋ ማን ነዉ አባቢ አለችው..
.....ቩራል ይባላል ከአሁን ቡሗላ እኛ ጋ ነው የሚኖረው በደምብ ይረፍና ትተዋወቃላቹ አሁን ግቢና ክፍሉን አሳዪው ሻወርም ይውሰድ አላት እሽ ወንድም ቩራል #ኒሀል እባላለሁ ግባ አለችኝ ውበቷ አይቶ አለማድነቅ ይከብዳል እንደመሽኮርመም እያደረገኝ እሽ ብዬ ወደውስጥ ስንገባ ትንሿ ልጅ ማሚ ማሚ! አባቢ መጣ እያለች ቤቱን በጩከት ቀወጠችው ሚስቱም ከሩጫ ባልተናነሰ መጥታ ተጠመጠመችበት እዚ ለይ ግን አንድ ነገር ተረዳሁ በምንም አይነት ሁኔታ በፈገግታ ሰላም አለችን

........ከዛም እኔን ኒሀል ክፍሌን ልታሳየኝ ደረጃውን መውጣት ስንጀምር ፤እንኳን ደህና መጣህ ዉድ ጓደኛዬ የሚል ማፌዝ የተሞላበት የወንድ ድምፅ ሰማሁ ቶሎ መለስ! አልኩና የሰዉየውን ማንነት ሳይ፤......ያቺ ቤተሰቦቼን ያጣሁበትን ምሽት አስታወስኩ ሽጉጥ ደቅኖ ሲዝት የነበረው ሰዉዬ #ካ ር መ ላ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ ዘልዬ ላንቀውም ፈለኩ........

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
1
አሞራው በሰማይ ላይ

ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት
«ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት
«አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።

በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ
«አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን።

አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።
ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር
《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት።

ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያዳርሱ።

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ሰባት(7)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

የሰዉየውን ማንነት ሳይ፤......ያቺ ቤተሰቦቼን ያጣሁበትን ምሽት አስታወስኩ ሽጉጥ ደቅኖ ሲዝት የነበረው ሰዉዬ #ካ ር መ ላ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ ዘልዬ ላንቀውም ፈለኩ........
ጋሽ አይሀም አይቶኝ ስለነበር ስሜቴን እንድቆጣጠር ጠቀሰኝ እየሸስኩመ ቢሆን ራሴን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ጋሽ አይሀምን አቀፈውና በጀሮዉ የሆነ ነገር ተናገረው እና
......በቃ አባታችሁ ጋር ጡሩ ጊዜ አሳልፉ ብሎ ወጥቶ ሄደ ጋሽ አይሀምም እሱ እንደወጣ ብዙ ጊዜ ይመጣል እንዴ አላቸው!
.....አዎ አባቢ! አጎቴ ካርመላ በጣም ጡሩ ሰው ነው እናንተ እኮ የጓደኛዬ አደራዎች ናቹህ'ኮ እያለ በየ ጊዜው ያዝናናል፤ ይዞን ይወጣል አለችው ትንሿ ልጅ! ጎበዝ የኔ ጣፋጭ እናንተን ሲንከባከብልኝ ነበር ኣ! እየተባባሉ....እኔ ከዛው ቁሜ እያዳመጥኩ የቆየሁባት ጊዜ ኒሀል፤ ቩራል ቩራል! ብላ ስትጣራ ሰማሗት ወዳው ድምፇን ተከትዬ ወዳለችበት ሄድኩ....... ምን ነው ቆየህ አለችኝ? ያለሽበት ጠፍቶኝ ነው ብዬ ፈገግ አስባልኳት፤ ውስጥ አስገብታ ዉስጡን በደምብ አሳየችኝ ከዛም እሷ ወጥታ እንደሄደች፤

ለዘመናት በጠጠር አና በአፈር የቆሰለውን ወገቤን ላሳርፍ አልጋው ላይ ተንከባለልኩበት በህልሜ እንዳይሆን ፈርቼ ወደ ሻወር ቤቱ ገባሁና ስማቸውን በረሳሗቸው ሳሙና እና ሻምፖ በሞቆ ውሀ የሰዉነቴን እድፍ(ቆሻሻ) አላቀኩ ከዛም የተዘጋጀልኝን ፎጣ አሸርጬና ከላዬ ላይ ደርቤ ስለምቀይረው ልብስ እያሰብኩ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩኝ፥..በሀሳብ ተመስጬ ሌላ አለም ዉስጥ ሳለሁ የአዲሷ ክፍሌ በር ተቆረቆረች ሽርጤ ወልቆ እንዳያሳፍረኝ አጠባብቄ በሩን ከፈትኩ ጤና ይስጥልኝ አቶ ቩራል መግባት ይቻላል አለኝ ......የያዘውን የልብስ ብዛት ተመልክቼ አይኔ ፈዘዘ በሁኔታዬ ተገረሞ አቶ ቩራል.... ብሎ ሳይጨርስ ግባ ግባ ይቻላል አዎ! አልኩት!! ማን ብሎ ነበር ደግሞ የጠራኝ አቶ ቩራል ሆ ሆ....... ከአልጋዉ በፊለፊት አቅጣጫ ከተገተረው ቁም ሳጥን ቻል አትቻል እያለ ሁሉንም ከተታቸውና በፖርሳ የያዛቸውን ሽቶና ቅባቶች እዚህ ጋር ይደረጉ አለኝ፤...አዎ አድርጋቸዉ አልኩት እሱም ስራውን ጨረሰና እናመሰግናለን!! ብሎ ጥሎ ወጣ

እኔም በችኮላ በሩን ቆልፌ ቁም ሳጥኑን ከፈትኩት የትኛውን መርጬ እንደምለብስ ጨነቀኝ እናም ከደቂቃዎች በፊት የነበረውን አስታወስኩ አቤት!! የሰው ነገር ይገርማል ስናጣም ሀሳብ ስናገኝም ለመምረጥ ሀሳብ ከዚህ ሁሉ ብዬ ..የሞኝ! አመራረጥ መረጥኩ አይኔን ጨፈንኩና ከእጄ የገባውን ለበስኩ ሳላበዛ ሽቶ ነሰነስኩና ከመስታውቱ ፊት ለፊት ቁሜ በፈገግታ እያየሁ፤ ..ወንድሜ ቩራል ደስ በሚል የልጅነት ድምፅ ስትጣራ ሰማው ሮጥ ብዬ በሩን ከፈትኩት!! ወንድሜ ቩራል ምሳ ደርሷል ና! እየተባልክ ነው አለችኝ እሽ መጣሁ ...ግን ስምሽን አልነገርሽኝም እኮ አልኳት #ሲትና ነው ስሜ እያለች ተፍለቀለቀች እሽ እህቴ ሲትና አሁን መሄድ እንችላለን አልኳት፤....ኧረ ወንድሜ ቩራል ለትንሽ ልጅ እኮ እህቴ አይባልም ለትልቅ ሰው ነው እያለች እየተሳሳቅን ወደ ምሳው ሄድን እናቷም አየችንና ምን ተገኘ ሲቱ አለቻት

ኧረ ማሚ ያለውን በሰማሽ እያለች ወደሷ ሄደች....እኔም ወደ ቀረበዉ የምግብ ጠረንቤዛ አመራሁ፤ ጋሽ አይሀም ቁጭ ብሎ አገኘሁት ፈገግ ብሎ ዋዉ! ዋዉ! በጣም አምሮብሀል ከአይን ያውጣህ አለኝ ከትንሽ ቆይታም ቡሗላም ምግብ በአይነት ቀረበ መምረጥ እስኪያቅተኝ ድረስ ነበረ ከዛም ሁሉም ቤተሰብ ተሰባስበን መብላቱን ተያያዝንው፤.. በመሀል ጋሽ አይሀም ቩራል የኔ ልጅ ረስቼው ሳልሰጥህ ብሎ በትንሽ ካርቶን የተጠቀለለ ዕቃ ሰጠኝ እኔም ተቀብዬ ቁጭ ሳደርገዉ መክፈት ይቻላል አለኝ፤ እሽ ብዬ ከፈትኩት ስከፍተው...........

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
...አንድ ግዜ የሆነ ልጅ ነው። የሚበላ ዳቦ ፈልጎ በዙሪያው ካሉት ህፃናቶች ውስጥ ገለል ብሎ የገረጣውን ይጠራውና ዳቦውን ገዝቶለት እንዲመጣ ይልከዋል። ህፃኑም የተባለበት ቦታ በደስታ እንዲሁም በፍጥነት ደርሶ የታዘዘውን ዳቦ ገዝቶ ይመጣል።

...ቅድም ከጨዋታ የተገለለው እቤት ቁርስ ስላልበላና ስለራበው ነበር። ትድያ ይህ የላከኝ ግለሰብ አንድ ፍሬ ይሰጠኛል ብሎ በተስፋ አይን አይኑን እያየ ሲጠባበቅ የላከው ልጅ "አንተ...ሂድ እንጂ!! ከጓደኞችህ ጋር ተጫወት በሜለት በግልምጫ ያባረዋል። ህፃኑም እየራበውም ቢሆን ስለፈራ ደንግጦ ከአጠገቡ ዞር አለ።

.....ትንሽ ቆይቶ አንድ የዝህ የህፃኑ ላኪ ግለሰብ #ጓደኛ ይመጣል። ሰላም ከተባባሉም በኋላ የያዘውን ዳቦ አብረው እንዲበሉ ይጋብዘዋል። ጓደኛው አሁን በቅርብ ቁርስ እንደበላና ሆዱ በጣም እንደጠገበ ይነግረዋል። ሰውየው ግን በግድ ጓደኛውን ካልበላህ ብሎ በመለመን ከያዘው ዳቦ ግማሽ የሚሆነውን አካፍሎት አብረው ተመገቡ። የቅድሙ #ህፃን ድርጊቱን ተመልክቶ በጣም አዘነ። እሱ እየተራበ ሳይሰጠው ለጠገበና አልፈልግም ላለ በመሰጠቱ በጣም አስከፋው። ውሎውንም በትካዜ ተሞልቶ አሳለፈ።


... ከዚህ ታሪክ የምንማረው ሁላችንም ያሉንን ነገራቶች ለሚገባቸው አካላት በመለገስ ምንዳውን ከአላህ እንተሳሰብ። ብዙ ግዜ ሰርግ ይዘጋጃል፤ሰደቃም እንደዛው ነገር ግን እነዚህ ዝግጅቶች ላይ የሚጠሩት በረሃብ የተመቱ ደካሞች ሳይሆን ቤት የተረፋቸው ቦርጫምና የጠገቡ ሃብታሞች ናቸው። ይህ መሆን የለበትም። ህፃናትንም ቢሆን ልከን ለላክናቸው እንዲደሰቱ ሌላም ቀን በደስታ እሺ እንዲሉን ስሜታቸውን በመረዳት እናስደስታቸው።

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
👍2
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ስምንት(8)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

የኔ ልጅ ረስቼው ሳልሰጥህ ብሎ በትንሽ ካርቶን የተጠቀለለ ዕቃ ሰጠኝ እኔም ተቀብዬ ቁጭ ሳደርገዉ መክፈት ይቻላል አለኝ፤ እሽ ብዬ ከፈትኩት ስከፍተው...........
..........ስከፍተው በጣም የሚያምር የእጅ ሰአትና ስማርት ስልክ ከዛ በላይ ግን ከሰኣቱ ጎን መኪና ቁልፍ ተቀምጧል፤ ያኔ ደስታዬ ወደር አጣ የትልቅነት ስሜትም ይሰማኝ ጀመር..... ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ጋሽ አይሀምን አቅፌ ሳም ባደርገው ደስ ባለኝ ነበር ያን ማድረግ ባልችልም ግን ባለሁበት ቁጭ ብዬ ሀሴት በተሞላው ድምፅ ኧረ ጋሽ አይሀም ይሄ ሁሉ ከአቅሜ በላይ ነዉ ደግሞ መኪናው ብዬ ሳልጨርስ...... ጋሽ አይሀም ለመንጃ ፈቃዱ ከሆነ ስጋት አይግባህ ብዙ የማውቃቸው ሰዎች አሉ አናግራቸዋለሁ ልምምዱን እኔ አሰለጥንሀለሁ አታስብ አለ እኔም ለመናገረ ጉሮሮዬን ስጠራርግ
.........በመሀል ሲትና ወንድሜ ቩራል መኪና ስትይዝ መጀመሪያ እኔን ነዉ ኣ ከትምህርት ቤት የምታመጣው አይደል ብ ሁሁላችንንም አሳቀችን
..... እኔም ልናገር የነበረዉን በዛው ተውኩት ምሳችንን በልተን ከጨረስን ቡሗላ ቀኑ ቅዳሜ ስለነበር እኔ እዛው ጊቢ ውስጥ ሲትና ጋር ስጫዎት ዋልኩ ጋሽ አይሀም ደርሼ የምመጣበት አለኝ ብሎ ወቷል ኒሀል ከቤት ዉስጥ እናቷ ጋር ነው ስራ እያገዘቻት ነውየዋለችው፤

ሁሉም በየፊናዉ ወዲያ ወዲህ ሲል ፀሀይ ወደ ቤቷ ገብታ ጨለማ የሚባል ሁሉን ሰታሪ ሲመጣ ጋሽ አይሀምም ከዋለበት ውሎ ተመልሶ መጣና በጊዜ እራት በላን ከዛም ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን ጋሽ አይሀም ነገ ሁላችንም ምርጥ ቦታ ሽርሽር እንወጣለን እንድትዘጋጁ ብሎን ወደ ክፍሉ ሄደ፤ ሲትና ከጉልበቴ ላይ ቁጭ እንዳለች እንቅልፍ ይዟት ስለ ነበረ አልሰማችም ከዛም ብዙ አልቆየንም እኛም ወደ ምኝታችን ሄድን ከተኛሁ ቡሗላ ግን ካርመላ ጋሽ አይሀምን ምን እንዳለው አልጠየኩትም ለነገሩ ብቻችንን አልተገናኘንም ነገ እጠይቀዋለሁ ብዬ ተኛሁ ወደዛ ወደዚህ እያልኩ ስገላበጥ የረባ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነጋ፤ በሰመመን ውስጥ ሆኜ ክፍሌ ተንኳኳ አይኔን እየጠራረኩ ስከፍተው ሲትና ነበረች፤ ውይ ሲቱዬ ነይልኝ ብዬ አስገባሗትና ልብስ ቀያይሬ አብረን ተጣጠብንና ወደ ቁርስ ሄድን ከዛም.. ሲቱ! አልኳት አቤት ወንድሜ አለች ዛሬ እኮ ሰርፕራይዝ ተዘጋጅቶልናል አልኳት በደስታ እየተፍነከነከች ቁርስ በላንና ወደ ተዘጋጀው ቦታ ሄድን የሚገርም መዝናኛ ነበር የወሰደን...እኔ ግን ያን ያህል አላስደሰተኝም ምክንያቱም እነሱ ሲጫወቱ ቤተቦቼ ታወሱኝና ቁጭ ብዬ መቆዘም ጀመርኩ! ኒሀል!! ድንገት ስትዞር አየችኝና መጣች ከዛም ምን ሆንክ ቩራል ና! እንጂ እኛ ዘና በል አለችኝ
....አይ ይለፈኝ እዚህ ይሻለኛል አልኳት እንደዛ ከሆነ እኔም ላቀማምጥህ ብላ ቁጭ አለች በዛው ወሬ ጀመርን ስለራሷ ሁሉንም ባይባልም አወራችኝ የሁለተኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች እና የቀጣይ አመት ተመራቂ መሆኗን ጭምር ነገረችኝ ስለ እኔ ግን ምን ልንገራት ምንም የሚነገር ታሪክ ስለለኝ ዝም ብዬ አንገቴን ደፋሁ! ድንገት ጋሽ አይሀም መጥቶ ልጆች እዚህ ናቹህ እንዴ አለ!

....አዎ አባቢ ደብሮት ሳገኘው እያዋራሁተ ነዉ አለችው እንዴ ቩራል የምን ድብርተ ነው ና ተነስ እንደውም መኪና መንዳቱን ላለማምድህ አለኝ ኒሁ ደግሞ ወደነ ሲትራ ሂጂ አላት እሽ ብላ ሄደች እኔም ጋሽ አይሀም ጋር ወደ መኪናው ሄድን በነገራችን ላይ ኒሀል በጣም ቆንጆ ልጅ ናት ብትፈቀርም አያንሳትም ደስ የሚል ስብዕና አላት!! ሌላ አስቤ ግን አደለም።....መኪናው ውስጥ ገብተን ልምምድ ጀመርኩ ድሮ አባቴ ያስነዳኝ ስለ ነበር አዲስ አልሆነብኝም በመሀል አንድ ነገር ትዝ አለኝና ካርመላ በጆሮው ምን እንዳለው ጠየኩት...."" ያው የጠበኩት ነገር ነው 'ባትመጣ ይሻልህ ነበር' ነዉ ያለው እና ደግሞ ቩራል ያው በእቅዳችን መሰረት ነገ ወደ ድርጅቱ እንሄዳለን በዛውም ሰራተኛቹን ትተዋወቃለህ አለኝ"" ጋሽ አይሀም እኔም እሽታዬን ነግሬ ሲያለማምደኝ፤እነ ሲትናም ሲጫወቱ ውለን ወደ ቤት ተመለስን ሁላችንም ስለደከመን ወደ አልጋችን ሮጥን ሰውነቴ ዝሎ ስለነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ነበር የያዘኝ ፤

....አይነጋ የለምና ነጋ! የወፎቹ ዝማሬ ግን ቅር ቅር አለኝ፤ አሁን ይጮሀሉ! እያልኩ ብጠብቅም የለም!!.... ምን ይደርጋል ብዬ ለመጀመሪያ የስራ ቀኔ ዝግጅቴን ጀመርኩ የለለ ሽክ አልኩኝ ከዛም ቁርስ በላንና ተሰነባብተን ጋሽ አይሀም ጋር ወደ ድርጅቱ ሄድን ከዛም እንደደረስን ጥበቃዎቹ መጥተው የሚኪናውን በር ከፍተው እንኳን ደህና መጣቹህ አቶ አይሀም ብለው ቁልፉን ተቀብለው ወደ ፖርኪንጉ ወሰዱት፤ በጣም ትልቅ ድርጅት እነደሆነ ከህንፃዉ መረዳት ይቻላል!! ከዛም ተያይዘን ወደ ውስጥ እንደገባንም ሰራተኛው በሙሉ ተሰብስቦ እየጠበቀን ነበር ከዛም ጋሽ አይሀም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ቆሞ ሰላምታ ከሰጠ ቡሗላ መክፈቻ ቢጤ ንግግር አደረጎ ዛሬ አዲሱን የድርጅታችንን.....

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
አስደናቂው #ለማኝ እና የባለታሪኩ ገጠመኝ

በመንገድ ላይ በመጓዝ ላይ ሳለ፣ አንድ ምስኪን ለማኝ የሚሰራው ድርጊት ላይ አይኑ አረፈ። ትኩረቱን ሰጥቶ መከታተሉን ቀጠለ። ለማኙ እንዲህ ነበር የሚያደርገው.... መጥቶ ሰደቃ የሚሰጠው ሰው ጋር ረዘም ያለ ንግግር ያደርጋል። ሁሉም ሰው ሰደቃ ሊሰጠው በመጣ ቁጥር፣ እንደ ሌሎቹ ሳይሆን ረዘም ያለ ጊዜን ያናግራል። እሩቅ ላይ ስለነበሩ የሚሉትን ነገር ለመስማት አልቻለም። በመሆኑም ጠጋ ብሎ ሰደቃ በመስጠት የሚናገረውን ነገር ለማዳመጥ ወሰነ።

ኪሱ ውስጥ የነበረው 50ብር ብቻ ነበር። ታድያ 10ብር ሰጥቼ በዛውም 40ብቅ እስኪመልስልኝ ሰፊ ግዜን ወስጄ አዳምጣለሁ በማለት፤ ሄዶ ያሰበውን አደረገ። 50ብር ሰጠውና 40ብር መልስልኝ አለው። ለማኙም እንዲህ አለው........ "ያንተ ብር የሚሆነው ይህ ወደ ኪስህ የመለስከው 40ብር ሳይሆን ለእኔ የሰጠኀኝ 10ብር ነው። ምክንያቱም ይህንን 40ብር የምታውለው ምናልባት ለዱንያዊ ጥቅም ይሆናል። ጥቅሙም እዚሁ ዱንያ ላይ ይቀራል። ነገር ግን ለእኔ የሰጠኀኝ ብር ወደ አኼራ ካዝናህ ተዘዋውሯል "....

ንግግሩ ውስጤን ስለነካው በቃ እሺ መልስ አልፈልግም አልኩት። "አይይይ እኔ አንተ ብር እንድትሰጠኝ ብዬ አይደለም ይህንን የነገርኩህ። ቀሪውን 40ብር ለኔ ሳይሆን ሌላ እኔን ለመሰለ አልያም ከእኔ ለባሰ ምስኪን ለግሰው" ሲል በድጋሚ ልቤን የሚነካ ንግግር ተናገረ። ያለኝን ለመፈፀም ልጓዝ ዞር ስል እንደገና ወደ ኋላ ጠራኝ። እኔም አቤት ብዬ በደስታ ተመለስኩ። እንዲህ አለኝ "ሌላ ንግግር ጀምረን ዋናውን ጉዳይ ረሳሁት። የብርህ ምንጭ ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ። እኔም ሃላል እንደሆነ በደንብ አስረዳሁት። እሱም"እንደዛ ከሆነ ማሻ አላህ!! ብርህ ምንጩ ሃራም ቢሆን ኖሮ አልቀበልህም ነበር። ወላሂ የሚመለከተኝ አላህ ምስክሬ ነው። ከማንም ሰው የብሩን ሃላል መሆን ሳላረጋግጥ ተቀብዬ አላውቅም። ሃራም ከሆነ የሰጠኝ የብር መጠን የፈለገ ቢበዛ መልስልምታለሁ" እንዲህ እያወራን የዝሁር አዛን ወጣ። እሱም አንስቼው ዊልቸሩ ላይ እንዳስቀምጠው ነገረኝ። የዙሁር ሰዓት ብዙ ሰው ከስራ ስለሚወጣ ለልመና አመቺ ሰዓት ነው። ነገር ግን እሱ ሰላቱን በማስቀደም ለአላህ እጁን ሰጠ። ወደ መስጅድ እየገፋሁኝ ወሰድኩት። እናንተ እግር፣ እጅ፣አይን እያላችሁ ሰላተል ጀመዓ የሚያመልጣችሁ ወንዶች ከዚህ ሰውዬ የት አላችሁ!!? አንቺም ሙሰልሰል እየተመለከትሽ ሰላት የሚያልፍሽ፣ቻት ላይ ተጥደሽ ወቅቱን የምታሳልፊ እህቴ ወንድሜ ከዚህ ለማኝ አንፃር አላህ ምን ይለን ይሆን!!?

ከዓመታት በኋላ ይህንን ሰው ከቦታው ላይ አጣሁት። በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን ስለ እሱ እንዲነግሩኝ ጠየኳቸሁ። እነሱም እርሱ ልመናውን ትቶ። ከውጭ ሀገር በመጡ #በጎ_ፍቃደኞች እግሩን ታክሞ ድኖ፣ልመና ከመተዉም አልፎ ውጭ ሀገር ሄዶ ባካበተው ሃብት አማካኝነት ትልቅ ደካሞችንና ህፃናትን የሚረዳ ተቋም ማቋቋሙን ነገሩኝ። እኔም በአላህ ስራ ተደንቄ ከዚያን ቀን ጀምሮ በቀን ሰደቃ ሳልሰጥ ውዬ አላውቅም።


ሁላችንም ዛሬ፣አልያም ይህን ሳምንተ በየቀኑ ከ5ብር በማንሳት እስከ 1ብር ሰደቃ በመስጠት ለሰባት ተከታታይ ቀናት ታላቅ አጅርን እናግኝ!!

"#ውሃ እሳትን እንደምታበርደው ሁሉ #ሰደቃ የአላህን ቁጣ ታበርዳለች" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አላህ በብዙ ነገር ሊቆጣብን ይችላል። ይህን ሃያል የጌቴችን ቁጣ ሰደቃ በመስጠት እናብርደው።

ይህንን ፅሁፍ #ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
ምርጥ አስተማሪ ታሪክ እነሆ!!

በአንድ ወቅት አንድ ቀልጣፋ እንጨት ቆራጭ በአንድ የስራ መስክ በጥሩ ደሞዝ ተቀጠረ።ስለዚህም እንጨት ቆራጩ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ እና ጥሩ ስራ ለመስራት ይወስናል።

በመጀመሪያው ቀን ሃላፊው መፍለጫ ሰጠውና የሚሰራበትን ቦታ አሳየው። መቁረጥ የሚችላቸው ዛፎች እነዚህ እንደሆኑ አስረድቶት ሄደ።በርግጥም እንጨት ቆራጩ በመጀመሪያው ቀን 15 ዛፎችን ቆርጦ ማስተካከል ቻለ።

በሁለተኛው ቀን የበለጠ ለመስራት ወስኖ ቢሞክርም ከ10ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም ነበር።

በሶስተኛው ቀን ከሁለቱ ቀናት የበለጠ ቢተጋም ከ7 ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም።

ቀናቶች ባለፋ ቁርጥ የሚቆርጣቸው ዛፎች መጠን እያነስ እያነስ መሄድ ጀመረ። በስተመጨረሻም አንዲትን ዛፍ መቁረጥ ከበደው። ሞከረ ሞከረ ሊሳካለት አልቻለም።

ይሄኔ ሃይሉን እንዳጣ ተሰማው። ጉልበቴም ከዳኝ ብሎ በማሰብ ላይ ሳለ የሆነ ሌላ ሰው ሲያልፍ ይህንን ሰው አንዲትን ዛፍ ያለጥቅም ሲደበድብ ይመለከተዋል።

"ሰውየው ወደ እንጨት ቆራጩ ጠጋ አለና አንድ ምክር ልምከርህ ትፈቅድልኛለህ?" አለው።

እንጨት ቆራጩም "አሁን ስራ ላይ ስለሆንኩ ምንም መስማት አልፈልግም" ይለዋል።

ሰውየውም እንዲህ አለው" እየፈለጥክበት ያለከው ፋስ(መፍለጫ) ስለት የለውም ዶምድሟል። ከጥቅም ውጭም ሆኗል። ይህን አውቀህ እረፍት በማድረግ የምትሰራበትን #ፋስ ልታስለው ይገባል" አለው።

ይሄኔ ይህ እንጨት ቆራጭ ቆም ብሎ አሰበ። እንዲህም አለ"እውነትም ፋሴን አሞረድኩትም። ዛፎችን በመቁረጥ ቢዚ ስለነበርኩ" ብሎ ፋሱን በእርጋታ ሞረደና ከድሮ በተሻለ መልኩ ስራውን በአግባቡ ማከናወን ቀጠለ።

በህይወትህ ውስጥ መለወጥ ያለብህን ነገቅ ለመለወጥ ግዜ አትስጥ። ሁሉንም ነገር በጊዜ ለማከናወን ሞክር።

••••#Share ••••
━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ዘጠኝ(9)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

ጋሽ አይሀም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ቆሞ ሰላምታ ከሰጠ ቡሗላ መክፈቻ ቢጤ ንግግር አደረጎ ዛሬ አዲሱን የድርጅታችንን.....
.......ዛሬ አዲሱን የድርጅታችንን ስራ አስኪያጅ ላስተዋውቃችሁ አቶ ቩራል ነምሩድ ይባላል ከአሁን ቡሗላ ስለ ድርጀቱ ማንኛውንም ነገር እሱ ነው የሚመለከተው ከሱ በላይ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ናቸው ወደ እኔ የምትመጡት ብሎ ንግግሩን ቋጨ፤.. ከዛም ሁሉንም መተዋወቅ ጀመርኩ አንዱ ነኢም ሌላው አሲም ምን ልበላችሁ ሰምቸቻቸው የማላቃቸው ስሞች በአይነት ተዘረዘሩልኝ ከተላላኪና ፅዳት እስከ አዛዥ አንድ በአንድ ስም ተለዋወጥን በሉት ከዛም እንደጨረስኩ ጋሽ አይሀም....ፀሀፊዋስ የት ነች አለ ከመሀል አንድኛው ተነስቶ የምታዘጋጀው ሪፖርት ስላላት በጧት ነዉ የገባችው አለ፤
....እሽ! ቩራል ወደ ቢሮህ እንሂድ አለኝ እሽታዬን ነግሬ ወደ ቢሮው አመራን እንደደርስንም፤
ከኮምፒውተር ላይ አንገቷን የደፋች ልጅ ተቀምጣለች ይቺ መሆን አለባት ፀሀፊዋ እያልኩኝ ወደ ዉስጥ ገባን

ከተደፋችበት ቀጥ አለችና የበሩን መከፈት በድምፅ ሰምታ በሚያምር ፈገግታ....እንኳን ደህና መጣቹህ አቶ አይሀም አለች ዉስጤ ደነገጠ ልጂቱ አዲስ አልሆነችብኝም ከዚህ በፊት የማዉቃት አይነት ስሜት ተሰማኝ ከዛም ጋሽ አይሀም ሰላም አላትና እኔ አዲሱ አለቃዋ እንደሆንኩ ነገራትና ቀድሞኝ ወደ ቢሮው ገባ ..ከዛም ጠጋ ብዬ እጄን ዘረጋሁና ስሜን ስነግራት በአንድ ጊዜ ያፈገግታዋ ጠፋ ሁኔታው ሁላ በአንዴ ተቀያየረ ምን ነካት እያልኩ በተንቀጠቀጠ ድምፅ መ...መ...#መይሙና እባላለሁ አለችኝ ዉስጤ ይበልጥ ፍርሀት ተሰማው መልስ ሳልመልስላት አንገቴን ነቅነቅ አድርጌ ወደ ቢሮዉ ገባሁ እሚገርም ነው ሁሉም ነገር የተሟላለት ቢሮ ነው ጋሽ አይሀምም ወደድከዉ አለኝ አዎ በጣም ያምራል ምን ነው የነበርኩበትን ረሳሀው እንዴ አልኩት ለውጥ ግድ ነው ደግሞ መይሙና ጎበዝ ልጅ ናት ምንጊዜም በስራ መጠመድን ትመርጣለች ስለዚህ እምትፈልገውን ነገር ሁሉ ጠይቃት ታስረዳሀለች አለኝ

እኔም እጄን አገጬ ላይ አድርጌ ራሴን እየነቀነኩ ወዲያ ወዲህ እተንጎራደድኩ ሳለ የጋሽ አይሀም ስልክ ጠራ አነሳና ላዉድ ስፒከር ላይ አደረገውና #ሀሎ አይሀም ጓደኛዬ እንዴት ነህ ከማለቱ ካርመላ መሆኑን አወኩ ከዛም ወደ ስልኩ ጠጋ አልኩ በደምብ ለመስማት እሱም ጉራውን ጀመር #አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾምክ አሉ ምን ነው አይሆንልህ አለ እንዴ አለ ኮራ ባለ ድምፅ
ጋሽ አይሀም ዝምታን መረጠ ካርመላ ግን ወሬውን ቀጠለ እስኪ እናየዋለን አንተ ጋ መቀጠል እንደሚችል ለማንኛውም የሞተው ጓደኛችን እጣ ፈንታ እንዳይደርስህ አለዉ እና ዘጋው፤....ሁለታችንንም በፈገግታ ተሞላን ምክንያቱም አሁን ወደ እቅዳችን ለመግባት ዳር ዳር እያለ ነዉ ቩራል ደግሞ ድርጅቱ ውስጥ የሱ ሰዎች ስላሉት ጠነቀቅ በል አለኝ ጋሽ አይሀም""
..ከዛ ቡሗላ የተለያዩ መረጃዎችን እያየሁ የመጀመሪያ የስራ ቀኔን አሳለፍኩ ምሳም ከህንፃው ፊትለፊት ካለው ካፌ ነበር የበላሁት ከስራ ቡሗላ ወደ ቤት ስመለስ ለሲትና ጣፋጭ ነገሮች ገዝቼላት ስለነበረ በጣም ደስ አላት የሷ ደስታ ደግሞ ለኔ እርካታ ተሰማኝ እናም ከዛን ቀን ጀምሮ እየገዛሁ ለመምጣት ለራሴ ቃል ገባሁ ከዛም ራት በልተን ወደምኝታችን ሄድን

#የመይሙናን ሆኔታ ግን እያሰብኩ ግን መተኛት አልቻልኩም ለምን ደነገጠች ፈገግታዋስ ለም ባንዴ ተለወጠ ምን አልባት ግን የኔ መይሙና ብትሆንስ ብዬ አሰብኩ እሷ እስካሁን የስንት ልጆች እናት ትሆን ይሆናል #የኔ መይሙና ያልኳችሁ ከአመታት በፊት ተማሪ እያለሁ በፍቅሯ ክንፍ የምልላት ልጅ ነበረች ስለሷ ከጀመርኩ ማቆሚያ የለኝም ለነገሩ እሷ አትሆንም ብትሆንም እስከ አሁን አትጠብቀኝም ግን ብትሆንስ ምክንያቱም ወይዘሪት ናት ብታገባ ኖሮ ደግሞ እያልኩ ሳሰላስል እንቅልፌን አጥቼ አደርኩ፤ ያው እንደተለመደው መታጠብ መብላት ከዛ ወደ ስራ መሄድ ቢሮ ደግሞ መይሙና ጋር ከስራ ጉዳይ ውጭ ለማውራት መፈራራት ከስራ መልስ ደግሞ መኪና መለማማድ ወደ ቤት ስገባ የሲቱን ደስታ እያያየሁ መደሰት የዕለት ተግባሬ ሆነ ፤

....ዛሬ ስራ ከጀመርኩ ሁለት ሳምንታት አስቆጠርኩ መንጃ ፈቃዴ ከመምጣቱ ውጭ ሌላ የተፈጠረ ምንም አዲስ ነገር የለም ስለ መይሙና ግን በግልፅ ላዋራት ወስኛለሁ እዉነቱን አውቄ ቁጭ ማለትን መረጫለሁ እናም የቢሮውን ስልክ አንስቼ ደወልኩና ሰላም ወይዘሪት መይሙና አንድ ጊዜ ቢሮ ነይ የማናግርሽ ጉዳይ አለኝ አልኳት እሽ ብላ መጣችና፤ ምን ልታዘዝ አቶ ቩራል አለችኝ ሚስኪን ታዛዦቼ ግን በዙብኝ እስኪ አረፍ በይ አንድ እንቅልፍ ያጣሁበት ነገር አለ እሱን ላማክርሽ እና በግልፅ እንድትነግሪኝ ፈልጌ ነበር ፤የምታዋሪኝ ግን እንደ አለቃሽ ሳይሆን እንደ ጓደኛሽ አልኳት በፈገግ እሽታዋን ነገረችኝ ከዛም ቀጥታ ወደ ገደለው ለመግባት አፌ እየተያያዘ አ.. አ.. አንች እኔን ስታዪ ለምንድን ነው ሁኔታሽ የሚቀያየረው አልኳት በተንቀጠቀጠ ድምፅ ፤....ወዲያው አንገቷን ደፋችና አይኖቿ እምባ አዘሉ ከዛም ለመናገር ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ስልኬ ጠራ ቶሎ ብዬ ዘጋሁና ይቅርታ ቀጥይ አልኳት፤...ድጋሜ ልትናገር ስትል አሁንም ጠራ ሳየው ያልታወቀ ቁጥር ነዉ አነሳሁና ሄሎ አልኩት ጤና ይስጥልኝ አቶ ቩራል አለ ለጆሮዬ አዲስ ያልሆ ድምፅ......

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
እንድምን ከረማቹልኝ ውድ ተካታዮቼ በጌታችን እዝነት ከዛሬ ጀምሮ ተመልሰናል።
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስር(10)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
ወዲያው አንገቷን ደፋችና አይኖቿ እምባ አዘሉ ከዛም ለመናገር ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ስልኬ ጠራ ቶሎ ብዬ ዘጋሁና ይቅርታ ቀጥይ አልኳት፤...ድጋሜ ልትናገር ስትል አሁንም ጠራ ሳየው ያልታወቀ ቁጥር ነዉ አነሳሁና ሄሎ አልኩት ጤና ይስጥልኝ አቶ ቩራል አለ ለጆሮዬ አዲስ ያልሆ ድምፅ......
አብሮ ይስጥልኝ ማን ልበል አልኩት፥.....ካርመላ እባላለሁ ከአጋር ድርጅታሁ አለኝ በድንጋጤ ቁጭ ብድግ አስባለኝ እሽ አቶ ካርመላ ምን ልታዘዝ አልኩት ድንጋጤዬን ለመደበቅ እየሞከርኩ
.... ስለ ድርጅቶቻችን ተገናኝተን እንድንወያይ ፈልጌ ነበር አለ
.... ደ..ደ ..ደስ ይለኛል
...እሽ እንደዛ ከሆነ ዛሬ ብናደርገውስ መረን ይመስልካል ማለት የተወሰነ ሰዓት ካለህ አለኝ
...ችግር የለውም ለእርሶ የሚሆን ጊዜ እንዴት እናጣለን ብለህ ነው ከማለቴ እንግዲያውስ ሰዓቱን እና ቦታውን በመልዕት እልክልሀላው ቻው ተባብለን ስልኩ ተዘጋ ምን ሆኜ ነው ግን አንቱ ብዬ አንተ ያልኩት ምን አስደነበረኝስ እያልኩ ማብሰልሰል ልጀመር ቀጥ ስል መይሙና አለች

...እንደዛ ስሜታዊ ሆኜ ሳወራ እሷ መኖሯን በጭራሽ ረስቼው ነበር ይቅርታ መይሙ እ...እ.. ማናገር ስለነበረብኝ ነዉ አልኳት
ኧር ችግር የለውም ባይሆን ጠንቀቅ በል ራስህን ጠብቅ ጥሩ ሰው አይመስለኝም
....ታውቂዋለሽ እንዴ ስላት?
..አይ ከዛው ስትሄድ ታገኘዋለህ አለችኝ
.....እሽ በቃ ሌላ ጊዜ እናወራለን ለአሁኑ መካሻ ምሳ እጋብዛለሁ ቀጠሮ ያዥልኝ አልኳት
...ፈገግ ብላ እስኪ እናያለን ብላኝ ሄደች
.......ከዛም በፍጥነት ወደ ጋሽ አይሀም ደወልኩ እና የተፈጠረውን ነገርኩት ተረጋግተህ አናግረው ምንም ቢናገርህ እንዳትፈራ አንተም ለምትናገራቸው ቃላቶች ጠንቀቅ በል ቶሎ ስሜታዊ እንዳትሆን አለኝ፤ እኔም ምክሩን ተቀብዬ ተሰነባብተን፥
..ከዛም የቀጠሮው ሰአት ደርሶ ወደ ተባለው ቦታ ሄድኩኝ ምን አልባት ያወቀኝ እንደሁ ብዬ በጣም ስለፈራሁ ጠቆር ያለ መነፀር ለበስኩና ከመኪናዬ ወርድኩ ከዛም ወደ ውስጥ ለመግባት በሩ ላይ ደረስኩ፤ ሆቴሉ የVIP ሰዎች ብቻ መዝናኛ መሆኑን ከጥበቃዎቹ መረዳት ይቻላል፤ ለመግባት እግሬን ስዘረጋ፤ ይቅርታ! ጌታዬ ቦታ አስይዘዋል አለኝ! እኔ ነኝ ጌታ ይችን ይወዳል ቩራል እንኳን ጌታ ልሆን እኔ ለራሴ ባሪያ ነኝ አድር ባዬ የሆንክ አሽቃባጭ ብዬ ብሰድበው ደስታዬ ነበር፥ ግን አልችልም እሱም ስራው ነው እኔም በለበስኩትና በኪሴ ለጊዜው ጌታ ነኝ.. አይ ቀጠሮ ነበረኝ አልኩ.. ወደ ካሸሯ ወሰደኝና የሰውየውን ስም እንድነግራት ጠየቀችኝ ከዛም እሽ ጌታዬ አንዴ ልየው አለና ኮምፒውተሩን ነካካና ጌታዬ ይከተሉኝ አለ! እሽ ብዬ አብሬው

ሄድኩኝ ከተያዘው ቦታ ስሄድ ካርመላ ቀድሞኝ ደርሷል፤ ይበልጥ የልብ ምቴ ጨመረ ለምን እንደሆነ አላቅም ፍርሀት ወይስ ድንጋጤ ምን ነካኝ እያልኩ እንደ ምንም ብዬ ራሴን ለመቆጣጠር ሞከርኩ!
ከዛም ጤና ይስጥልኝ ካልተሳሳትኩ አቶ ካርመላ አልኩት
...ኧረ በጭራሽ እራሱ ነኝ እንኳን ደህና መጣህ ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሰላም ተባብለን ከዛም እባክህን ተቀመጥ አለኝ!! ከተቀመጥን ቡሗላ ትወናውን ጀመረ፤
....ያው ምርጫህን ስለማላውቅ የራሴን ብቻ ነው ያዘዝኩት ምን ይምጣልህ አለኝ
ሜኑ ላይ ካለው ስጋ ነክ የሆነው አዘዝኩኝ ያው ስጋ ለአመታት ስለተመገብኩ ልረሳው አልቻልኩም
..እሽ ጌታዬ ብሎ አስተናጋጁ ሄደ፤
..እሽ አቶ ቩራል የሚገርም ነው ገና ወጣት ነህ ደስ ይላል ነገሮችን ቶሎ ትረዳለህ እና እንዴት ነው ስራ እየለመድክ ነው አለኝ
...አዎ ምን እማይለመድ ነገር አለ ብለህ አልኩት፥
...ጡሩ ደመዎዝ ይከፍልሀል፤
...አዎ ብዙ ባይባልም አልኩት፥ እ...ብሎ መናገር ሊጀምር ሲል በምንግዜው ፍጥነት ምሳው ደረሰና መጣ፥ ሁለታችንም ምሳውን በዝምታ መመገብ ጀመርን፤

..እኔ ግን የእናንትና የአባቴን ደም የመብላት ያክል ነው ስለተሰማኝ ነካ ነካ አድርጌ ተውኩት፥
...አትበላም እንዴ አለኝ በላሁ በቂ ነው አልኩት፤
....አቤት የአሁን ልጆች እንደው ምን ይሻላችሗል እኛ ወጣት ሳለን ይሄ የምትሰራበት ድርጅት ባለቤት አይሀምና በጣም የምንወደው የምናከብረው ነፍሱን ይማርና ሌላኛው ጓደኛችን ነምሩድ ጋር በአንድ ሆነን ለዉድድር የቀረብን ነበር የምንመስለው ስንበላ ታዲያ ምን ያደርጋል ሁሉም ነገር በነበር ቀረ አለ ባንቋረረ ድምፅ፤
..ይሄኔ ይበልጥ ንዴቴ እየጨመረ መጣ አንተ አስመሳይ ብዬ አልሰድበው የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ሊሆንብኝ ሆነ በዚህ መሀል እምባዬ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ በመነፀሬ ስር ወረደ
..ምን ነው ምን ሆንክ አለኝ ኧረ ምንም እኔም በጣም የምወደው ጓደኛዬን በሞት ስላጣሁት ነው አልኩት ኦ... ይቅርታ ያንተንም ትዝታ ቀሰቀስኩብህ አለ ችግር የለውም አውቀህ አደለም አልኩት ከዛም ጥያቄ መደርደር ጀመረ ከየት እንደመጣሁ በምን ዘርፍ እንደተማርኩ ጭምር ጠየቀኝ ከዛም የመጣልኝን መመለስ ጀመርኩ ተወልጄ ያደኩት ከደማስቆ የጎረቤት አገራት አንዷን ነገርኩት ደግነቱ ልዩ ቦታውን ማን ነው ብሎ አልጠየቀኝም፤

..ትምህርቴ ደግሞ በማኔጅመንት ማስተርስ እንዳለኝ ነገርኩት በጣም ተገረመና እሚገርም ነው በዚህ እድሜህ ማስተርስ ካለህ ጡሩ ጭንቅላት እንዳለህ ያስታውቃል እና ለምን ወደዚህ መጣህ ማለቴ ከዛ በጣም ጡሩ በሆነ ደመወዝ መቀጠር ትችል ነበር አለኝ፤ አዎ! እውነት ብለሀል ለብር ቢሆን ትክክል ነህ አልመጣም ነበር አላማዬ ሌላ ነው ለበቀል! ነው ወደዚህ አገር የመጣሁት ስለው አልኩት፤
...በተረበሽ ድምል አልገባኝም በደምብ ንገረኝ አለ በልጅነቴ ያልጠገብኳቸውን አባትና እናቴን የነጠቀኝን ነፍሰገዳይ ለመበቀል ነው የመጣሁት አልኩት...

መከታተል ጀምረናል ይቀጥል👍👍
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
መኖርን ባልታሰበ ስለዘገየን ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ ጀምሮ በየ ቀኑ የሚለቀቅ ይሆናል🙏🙏
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ አንድ(11)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
...በተረበሽ ድምፅ አልገባኝም በደምብ ንገረኝ አለ በልጅነቴ ያልጠገብኳቸውን አባትና እናቴን የነጠቀኝን ነፍሰገዳይ ለመበቀል ነው የመጣሁት አልኩት...
በጣም ነዉ ደነገጠ ይገርማል ምን ጊዜም ስራ ያለበት ሰው ስራው ሲነሳበት መሸማቀቅ ነዉ ስራዉ እያለልኩኝ "በሆዴ!!
........ማን! ማን! ነው የገደለብህ አለ በተቆራረጠ ድምፅ!
...ብነግርህ ምን ያህል ሚስጥር ጠባቂ ነህ ምክንያቱም የቤተሰቦቼን ንብረት ሞጣጦ አሁን ትልቅ ባለሀብት ሁኗል ስለው
....አይዞህ በኔ እርግጠኛ ሁን አለ! በፍርሀት ስሜት!
...ፊቴን ኮስተር አድርጌ አይሀም ነው አለቃዬ አይሀም! አልኩት!!
...በደስታ ድንጋጤ ዉስጥ ሆኖ ኣ..ያነ መናጢ ነው ምንም እንኳ ጓደኛዬ ቢሆንም አያደርግም አይባልም ያውም አንድ ጊዜ ከሚስቱ ውጭ ሲባልግ ቀርፀውት በስንት መከራ እና ልፋት መሰለህ ቪድዮውን እንዳይለቁት ተደራድሬ ካሴቱን የተቀበልኳቸው እሚገርምህ ይሄን ሁሉ ውለታ አድርጌለት ግን እሱ በምላሹ ድርጂቴን ለማክሰር ያልፈነቀለው ዲንጋይ የለም ንግግሩን ይሄ ካሀዲ የበላበትን ወጨት ሰባሪ!!! እያለ ራሱን መነቅነቅ ጀመረ

....እኔም ማስመሰሌን ቀጠልኩኝ ፊቴን አጨማደድኩና በቃ ያ!! አረመኔ የማይገባበት የለም!! ከእናቱ ሆድ ቢገባ አለቀውም አጠፍዋለሁ የቤተሰቦቼን ቀን ነው የምሰጠው አልኩኝ፤
...ስማኝ ቩራል ዛሬ የፈለኩህ ዋና አላማዬ ይሄ ነበር በአንድ ሆነን ህልዉናውን ማለትም ድርጅቱን እሱ በማያዉቀዉ መንገድ እንዲሸጥ እናደርገዋለን በዚህ ደግሞ አንተም የቤተሰቦችህን ንብረት ታስመልሳለህ እሱ ደግሞ ዳግም የሰው አይንን ቀጥ ብሎ እንዳያይ ራሱን በራሱ እንዲያጠፍ እናደርገዋለን አለኝ!!!
.......በጣም ደስ ይለኛል እንዳንተ አይነት ምኞቴን በቀላሉ ሊያሳካልኝ የሚችል ሰው በማግኘቴም እድለኛ ነኝ እንዴት አድርገን እንደምናጠፍው እቅድ አወጣለው ባይሆን ካንተ ትልቅ እምነት እፈልጋለሁ አልኩት
......ምንም ስጋት አይግባህ እንደውም አለና ከኪሱ ቼክ አውጥቶ ብዙ ዜሮዎች የበዙበት ቁጥር ፅፎ ይችን ያዛት አለኝ፤
......ምንድ ነው አቶ ካርመላ አልኩት፥
.........አቶውን ተወው እና ካርመላ በለኝ ይሄ ለአንዳንድ ነገር ይሆንሀል አለኝ፤
...አስፈላጊ አይመስለኝም እያልኩ መግደርደር ጀመርኩ፤
.......ለዕምነትና ለስራ ማስኬጃ ያክል ነው አለ
...ትንሽ አንገራገርኩና ተቀበልኩት አንድ ሚሊዮን ብር ይላል
......ይሄ ነገር አልበዛም አልኩት
.....አታስብ ስራው ሲያልቅ ደግሞ #ሁለት ቢሊዮን ብር ታገኝበታለህ አለኝ፤
...እሽ ካርመላ በቃ ከአሁን ቡሗላ ሆቴል ላይ መገናኘት አንችልም ምክንያቱም ያ! መናጢ እንዲከታተሉኝ ሰው ቀጥሯል አልኩት፤
........ችግር የለዉም እኔ ቤት መገናኘት እንችላለን ብሎ የቤቱን አድራሻ ሰጥቶኝ በዛው ተሰነባብተን ተለያየን፤
....ለጋሽ አይሀምም የተፈጠረውን ነገርኩት የሁልጊዜ የአባትነት ምክሩ የሆነችውን ""ራስህን ጠብቅ ለሁሉም ነገር አንተ ስትኖር ነው የሚሳካው"" አለኝ ገንዘቡንም ወደ አካውንቴ እንዳላስገባና የሀሰት መረጃዎችንም እንደሚዘጋጁ አሳወቀኝ!!!
......ከቀናት ቡሗላ ቃል በገባሁት መሰረት መይሙናን ምሳ ለመጋበዝ ይዣት ሄድኩኝ መንገድ ላይ የሆነች መኪና ለብዙ ሰአት ስትከተለን ነበር ምን ፈልገው ነው እያልኩ ራሴን እየጠየኩ ሆቴሉ ጋር ደረስን ከመኪና እንደወረድን አይኔን በቅርብ ርቀት ሲከተለን የነበረውን መኪና ላይ አደረኩ መኪናው ጥር መስታውት ስለነበረው ሰዎቹ ሊታዩኝ አልቻሉም....

ከዛም ሆቴሉ ውስጥ ገባን እና ቁጭ ከማለታችን የሆኑ ሰዎች ተከትለውን ገቡና ራቅ ብለው ተቀመጡ ቀስ አድርጌ ሳላስነቃ ስመለከታቸው ሙሉ አትኩሮታቸው እኛ ጋር ነበር!! ይህን ከካርመላ ውጭ ማንም እንደማይሰራው የታወቀ ስለሆነ፤ መይሙ! አንዴ መታጠቢያ ደርሼ ልምጣ ብያት ተነሳሁና ሄድኩኝ ከዛም ለካርመላ ደወልኩ!!!
....ሄሎ ካርመላ
.....ሰላም ወጣት ቩራል እንዴት ነህ አለኝ!!
....ትሸማኛለህ ገንዘብህን በፈለከው ሰአት ተገናኝተን ልመልስልህ እችላለሁ ግን እነዚህን የማይረቡ ሰላዮችህን ዳግም እንዳይከተሉኝ ንገራቸው ከአሁን ቡሗላ በስራዬ ላይ እጅህን እንዳታስገባ አልኩት፤
.....ቩራል እኔ እኮ ላንተ ደህንነት ብዬ ነው አለ፤
...ያም ቢሆን እኔን ፍላጎት መጠየቅ ነበረብህ ግን አንተ ምን አደረክ በራስህ ወሰንክ!!
...እሽ ቩራል በቃ ከአሁን ቡሗላ አይከተሉህም ልጅቷ ጋር ምን እያደረክ ነው
...የአይሀም ታማኝ ሰራተኛው ናት ሙሉ መረጃው እሷ ጋር ስለሆነ እንድትሰጠኝ ለማግባባት ነው አልኩት
...ልጅቷ እኮ ደረቅ ነገር ናት አለ..
""መይሙ ወዳ አደለም አትቅረበው ያለችው እሷን የሆነ ነገር ጠይቋት ነበር ማለት""
...ያን ለኔ ተወው ብር የማይገዛው ነገር የለም አልኩት!!
.....ይቅርታ ጠይቆኝ ተሰነባበትን
....ከዛም ወደ መይሙና ሄድኩ ዘወር ዘወር ብዬ ሳይ የሉም ሄደዋል!!

መይሙናም """ምን ሆነክ ነው ቆየህ አለችኝ""
.....ይቅርታ ስልክ ላይ ስለነበርኩ ነው ምሳ አዘዝሽ ስላት
....ምርጫህን ባላውቅም ተጋባዥ ስለሆንኩ የመምረጥ መብቱ የኔ ስለሆነ አዝዣለሁ አለች!!
......ፈገግ ብዬ ጥሩ አድርገሻል አልኳት
ቀጥሎም ምሳ እስኪደርስ ወደ ጥያቄዬ ገባሁ ባለፈው የጠየኳትን ጥያቄ ደገምኩላት
.....እንደባለፈው ሁሉ አሁንም አይኗ በእምባ ተሞልቶ መርገብገብ ጀመረ ከዛም መናገር ጀመረች ከአመታት በፊት ተማሪ እያለሁ በጣም........

ወደነዋል ይቀጥል👍👍
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
1
#برنامج_العيد❤️
#مع_إذاعة_ياسمين😍
تابعو.........
عيدكم مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🎊🎊

#ልዩ_አዝናኝ_አስተማሪ 🎊የኢድ አልአድሀ አረፋ🎊በአል ፕሮግራም

#ከያስሚን_ጋር
እንዳያመልጥዎ ይከታተሉ

ኢድ ሙባረክ ተቀበለሏህ ሚና ወ ሚንኩም ሳሊሀል አዕማል!

@M3_Yasmina
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ሁለት(12)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
.....እንደባለፈው ሁሉ አሁንም አይኗ በእምባ ተሞልቶ መርገብገብ ጀመረ ከዛም መናገር ጀመረች ከአመታት በፊት ተማሪ እያለሁ በጣም......ግትር እና አይናፍር ነበርኩ ከሴት ጓደኞቼ በቀር ወንድ ማናገር አልፈልግም ነበር፤አለመፈለግ ብቻ አይመስለኝም እፈራ ጭምር ስለ ነበር ነው በዚህ መሀል ግን አንድ ልጅ በፍቅር ጣለኝ፥ ልጁ በጣም ፈጣንና ፈጣጣ ነበር በዛ ላይ ቆንጆ ነው፤
....እንዴት እንደ ቀረበኝና በፍቅሩ እንድትወድቅ እንዳደረገኝ አሁንም ሳስበው ህልም ህልም ነው የሚመስለኝ ምን ግዜም እንደሚያፈቅረኝ ከኔ ውጭ ሌላ እንደማያገባ እየማለ ሁሉ ይነግረኛል፥
...ቢሆንም ግን እኔ አንድም ቀን ስሜቴን በግልፅ ነግሬው አላቅም እናም መቼም የማረሳት አንድ የተረገመ ቀን እሱን ድጋሜ እንዳላየው አደረገችኝ አለች እምባዋ ከአይኖቿ ኩልል ብለው እየወረዱ እኔም በአትኩሮት ሁሉ ነገሬን ሰጥቼ እያዳመጥኳት ነው ቀጠለች ....

ዕለተ ሀሙስ ትምህርት ቤት ውለን ወደ ቤት ተመለስን ቤት ዩኒፎርሜን ቀያይሬ መክሰስ እየበላሁ ስልኬ ጠራ አንስቼ ሳየው የሱ ስልክ ነው ከዛ በፊት በዛ ሰአት ደውሎልኝ አያውቅም ነበር ፤......ማሚ አጠገቤ ስለነበረች ዘጋሁበት አሁንም ደግሞ ደወለ ደግሜ ዘጋሁበት ለሶስተኛ ጊዜ ሲደውል አነሳሁና ማሚ እንዳትነቃ በሴት ጓደኛዬ አስመስዬ ማዋራት ጀመርኩ ሄሎ! ውዴ ደና ነሽ ዛሬ ጥናት አለን እንዴ እና ምን እግር ጣለሽ አልኩት፥
.....ግራ ገብቶት ነው መሰል ዝም አለኝ እኔ ማውራቴን ቀጠልኩ ማሚዬ ደና ናት እሽ ሰላም እልልሻለሁ ያውም አጠገቤ ናት ያለችው አልኩት፤
...የዛኔ ገባውና በተኮሳተረ ድምፅ ዛሬ ማታ ከተለመደው ቦታ እንገናኝ እፈልግሻለው! የጓደኞቼን ስም እየጠራ እነሱም ይመጣሉ አንችም እንዳትቀሪ አለኝ
..አይመቸኝም አልመጣም አልኩት
...መይሙ ዛሬ እንዳት ቀሪ ከቀረሽ ድጋሜ አታይኝም ከመጣሽ ደግሞ..የምነግርሽ ነገር አለ ከቀረሽ ግን ያው እንደነገርኩሽ ነው አለኝ፥
.........አልመጣም በጭራሽ አይመቸኝም አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት
....ያንን ያልኩት ግን ላለመሄድ ፈልጌ ሳይሆን ሳያስበው ሂጄ ላስደንቀው ስለፈለኩ ነበር እናም ያን አስቤ እሱ ከቀጠረኝ ሰአት አርፍጄ ከተባለው ቦታ ስደርስ አላገኘሁትም ነበር ሄዶዋል ፤ ጓደኛኞቼንም ስጠይቃቸው ፈጣሪ ካለ ምን አልባት አንድ ቀን እንገናኛለን በሏት አሁን ውስጤ ሰላም አይደለም ብቻ ብሎን ሄደ አሉኝ
.....በቃ ከዛን ቀን ጀምሮ አይቼው ስለሱ ሰምቼም አላቅም በጣም ብዙ ጊዜ እና ብዙ ቦታ ፈለግኩት ላገኘው አልቻልኩም ቤተሰቦቹ እንደሞቱ ግን ሰምቻለሁ እሱ ግን በዛው ድራሹ ጠፍ ብላ ሲቃ በተሞላው እና በእምባ በታጀበ ንግግር ወሬዋን ጨረሰች፤

እኔ ውስጤ ቢደማም እንደ ምንም አምባዬን እየተቆጣጠርኩ ሰማሗት ንግግሯን ብትጨርስም ማንባቷን አላቆም አለች፤
...እንዴት እንደተነሳሁ ባላውቅም እሷን አቅፌ ማፅናናት ጀመርኩ
...........ከዛም ድንገት ይቅርታ ስላቋረጥኳቹህ ያዘዛቹሁት ምግብ ደርሷል አለ አስተናጋጁ ከእንቅልፍ የቀሰቀሰን ያከል ነው የተሰማን ከዛም ተነስታ መታጠቢያ ቤት ፊቷን ታጥባ መጣች እኔም ሄጄ ታጠብኩና መመገብ ጀመርን በመሀላችን ፀጥታ ሰፈነ እኔም መብላቴን ትቼ እሷን ማየት ጀመረኩ፤
...ድንገት ሳላስበው ለምን አንተን ሳይ ለምን እንደምደነግጥ ታቃለህ አለችኝ ራሴን እየነቀነቅኩ እንደማላቅ ነገርኳት ስምህ እንደሱ ቩራል ነው አፍንጫህ አካባቢ ደግሞ እሱን ትመስላለህ ቆንጅዬ ነበር ለዛ ነው
....እሱን ለመርሳት ግን አማራጭ ያልኩትን ሁሉ ሞከርኩ ሌላ ጓደኛ ከመያዝ ውጭ መዝናናት ሳይኮሎጂስቶች ጋር መሄድ ግን ምንም ለውጥ የለውም ትንሽ በስራ ስጨናነቅ ይሻለኛል አለች፤

...ያኔ በጣም ውስጤ አዘነ እኔ ነኝ ራሱ ቩራል ነኝ ብላት ደስ ባለኝ ግን አልችልም አሁን በጀመርኩት ነገር ላይ ህይወቴን ላጣ ስለምችል ድጋሜ እንድትጎዳ አልፈልግም ያለኝ ምርጫ ዝምታ ብቻ ነው፥
....አይዞሽ እንዳለው አንድ ቀን ታገኝዋለሽ ቆንጆ ነህ ላልሽኝ ግን አመሰግናለው አልኳት
....ፈገግ እያለች እንዴ አንተን አደለም የኔን ቩራል ነው ያልኩት
በዛው የሚያስቁ ወሬዎችን እያወራሁ በመከራ ፈገግታዋን መለስኩላት ከዛም ስራ ገባን፤
...እንደተለመደው ለጋሽ አይሀም ደወልኩ ስራ ቦታ ስለነበረ ወደ ቢሮው እንድመጣ ነገረኝ ከሄድኩ ቡሗላ የተፈጠረውን አስረዳሁት
...አንተ እንደሆንክ በነርካት አለኝ

..አይ አልነገርኳትም ምክንያቱም እየሰራን ባለነው እቅድ ላይ የሚፈጠረው አይታወቅም ስኬት ብቻ ሳይሆን መውደቅም ሊኖር ይችላል ምን አልባት ሞት ከማለቴ አቋረጠኝና እውነተኛ የአባትነት መገለጫ የሆነ ንግግር ተናገረኝ
......""እኔ ከመሬት በላይ እያለሁ ፈጣሪ ብቻ እንጂ ማንም አይነካህም ባንተ ለመጣብኝ ህይዎቴንም ቢሆን ሰጥች እከላከልልሀለሁ"" ልጄ ነህ እኮ ቩራል የልጆቼ ወንድም ሲል
.....አንገቱ ላይ ሂጄ ጥምጥም አልኩበት እሱም አቀፈኝና ትንሽ ደቂቃዎች ቆየን

ከዛም ቩራል አዝጋጅልኝ ያልከውን መረጃ ተዘጋጅቶልሀል እየውና የቀረ ካለ ንገረኝ አለኝ፤
...እሽ ብዬ ተቀበልኩና ምንም የጎደለ እንደሌለ ነገሬው ወዲያው ለካርመላ ደወልኩለት እንድንገናኝ እፈልጋለሁ ያልከውን መረጃ ከፀሀፊዋ ተቀብያለው እናም አንተ ጋር ያለውን መረጃ አዘጋጅተህ ጠብቀኝ ለጥንቃቄ ሲባል መኪና ሳልይዝ እንደምመጣ ስነግረው
....የኔ ሰዎች እዚህ ቦታ ይጠብቁሀል አለኝ እሽ ብዬ ወደ ተባለው ቦታ ሄድኩ አግኝቻቸው ወደሱ ቤት ወሰዱኝ ግቢ ውስጥ ካስገቡኝ ቡሀላ ተመለሱ እኔ ወደ ቤቱ በር አመራው በሩ ላይ እንደደረስኩ መጥሪያውን ተጫንኩ የሚከፍትልኝ ሰው እስኪመጣ ድረስ የጫማ ማሰሪያዬን ተፈትቶ ሳየው ለማሰር ጎምበስ አልኩኝ እዛው እንደተጎነበስኩ በሩ ተከፈተና
...እልኳል ደህላ መጣቹህ የሚል ኮልተፍ ያለ የትልቅ ሰው ድምፅ ሰማሁ፤
....ቀጥ ብዬ ሳይ እንኳን በውኔ ይቅርና በህልሜም ለማለም አስቤው የማላውቀው ነገር........

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1👏1
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ ሶስት(13)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
....ቀጥ ብዬ ሳይ እንኳን በውኔ ይቅርና በህልሜም ለማለም አስቤው የማላውቀው ነገር ስለነበር አይኔ በእምባ ተሞላ እንደምንም ከተጎነበስኩበት ቀና አልኩኝ እግሬ መራመድ ቢፈልግም ጉልበቴ ተብረከረከ ዘልዬ ባቅፋት ደስታዬ ነበር ግን ምን ላድርግ አይን አይኗን እያየሁ በራፉን የጨበጠውን እጇን ዳደሰስኩት የእናትነት ስሜቱ የልብ ትርታዬን ጨመረው እሷም የእናትነት አንጀቷ ልጇ እንደሆንኩ ነገሯት እምባዋ ከጉንጮቿ መሬት ላይ ተንጠበጠቡ እንደምንም ብዬ ራሴን ለመቆጣጠር ሞከርኩና ወደ በራፉ ጠርዞች ስመለከት የጥበቃ ካሜራዎች አሉ
...ፈጠን ብዬ አመሰግናለሁ አልኩ እና ገባሁ ከዛም እምባዬን ጠራረኩና ወደ ሳሎኑ ስሄድ ካርመላ ጋር ተገናኘን እና ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጥን...
...ከዛም ምን ነው ቩራል ፊትህ ላይ ጥሩ ስሜት አይነበብህም አለኝ
....ያ! አይሀም እሚባል መናጢ እያለ ምን ላድርግ ብለህ ነው የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሬ ውጭ ሊያደርገኝ እየሞከረ ስለሆነ ስበሳጭ ንዴቴን በውስጤ ነው የማደርገው ለዛ ነው ፊቴ የሚለዋወጠው እና ካላስቸገርኩህ ፊቴን ብታጠብ አልኩት
......አኒሳ አኒሳ አላት
......አቤል አቶ ካርመላ እያለች መጣች
.....ለአቶ ቩራል መታጠቢያ ቤቱን አሳዪዉ አላት እሽ ብላ ፊት ፊት እየመራች ወሰደችኝ ከመታጠቢያ ቤቱ እንደደረስንም ዘልዬ አንገቷ ላይ ተጠመጠምኩባት የለበሰችው ጨርቅ እስኪረጥብ ድረስ አለቀስኩባት!!
...ልጄ ለምል ወደዚህ ተመልሰህ መጣህ ካርመላ ይገልሀል እባክህ ከዚህ አካባቢ ጥፍ አለችኝ በተቆራረጠ ድምፅ....

እማዬ ...አሁን ሁለተኛ አባት አግኝቻለሁ እሱ ስለሚያግዘኝ ምንም አያደርገኝም ደግሞ በቅርቡ እንደማስወጣሽ ቃል እገባልሻለው እያልኳት ሳለ
...ያ መናጢ አኒሳ አኒሳ የት ነሽ እያለ መጣራት ጀመረ እንዳቀፍኳት ብቆይ ደስታዬ ነበር እየከፍኝም ቢሆን ለቀኳት
...ከዛም ተጣጥቤ ወደሱ ሄድኩኝ እና ጡሩ ሰራተኛ አለችህ አቶ ካርመላ አልኩት
....አንተ ወጣት ግን ይሄ አቶ የሚል ነገር ተው አላልኩህም! አለኝ ይቅርታ ካርመላ ያው ለአይሀም ማሽቃበጡ ስለለመደብኝ እኮ ነው ስለው
...ያማስጠያ ፊቱን እያፈገገ ለማንኛውም የአኒሳ ታሪክ ረዥም ታሪክ ነው በአጭሩ ግን ሁልጊዜ እየመጣች ገንዘብ ትለምነኝ ነበር እኔም በመጣች ቁጥር በባዶ አልመልሳትም እናም አንድ ቀን ሚስቴ ለምን ሰራተኛችን አድርገን አንቀጥራትም አለችኝ እኔም ተስማማሁ እና ቀጠርናት አለኝ
.......አስመሳይ አሁንተም ጡሩ ሰው ነኝ፤ እያልክ አፍህን ትከፍታለህ ማፈሪያ ቢስ ብዬ እየተሳደብኩ በሆዴ!! እንዴ ጡሩ ሚስት አለችህ ለነገሩ ካንተ የተማረችው ደግነት ነው አሁን የት ሂዳ ነው ባለቤትህ አልኩት....
መዝናናት ትወዳለች ብዙ ጊዜ ቤት አትቀመጥም አለኝ
...እሽ ብዬ ወደ ጉዳያችን ገባሁ ከዛም እኔ ጋር ያለውን መረጃ በሙሉ አሳየሁት
...በጣም ተገርሞ ተአምረኛ ልጅ ነህ በዚህ ፍጥነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሁሉ ነገር ማድረግህ በጣም ጎበዝ እና ፈጣን ነህ ከጠበኩህ በላይ ነው ያገኘውህ ሙገሳ መሆኑ ሴራ መሆኑን አለማወቁ ጠቀመው ከዛም እሱ ጋ ያለውን መረጃ እንዲያሳየኝ ጠየኩት ላፕቶፑን ከሻንጣው አወጣና የሲዲ ካሴት ካስገባ ቡሀላ መረጃ የያዘውን ፎልደር ከፈተው በጣም ደባሪ ቪድዮ ቢሆንም ጋሽ አይሀም ቀድሞ ስለ ነገረኝ አዲስ አለልሆነብኝም ነበር አይተን ከጨረስን ቡሀላ ስለ ቀጣይ ስራዎቻችን መነጋገር ጀመረን፤

...የመጀሪያው ተግባር የድርጅቱን የሽያጭ ፍቃድ ማውጣት ሲሆን ሁለተኛውና የመጨረሻ ስራችን የሆነውን ጋሽ አይሀምን በቪድዮው አስፈራርቶ ማስፈረም ነው የመጀመሪያውን ተግባር ካጠናቀክ ቃል የገብሁልህን ሁለት ቢሊዮን ብር እሰጥሀለሁ አለኝ እሽ ብዬ ተሰነባብተን ልወጣ ስል እማዬ በሩን ለመዝጋት መጣች በሩ ጋ ልወጣ ስል ከኪሴ ብር አወጣሁ እና መሀሉ ላይ ስልክ ቁጥሬ ያለበትን ወረቀት ጋር ሰጠሗት ተቀብላኝ ቻው ብያት ሄድኩ፥
...ያው እንደተለመደው ጋሽ አይሀም ጋር ሂጄ አለቃቀስኩ መረጃውንም አዘጋጅ አልኩት እሱም የእማዬ በህይዎት መኖር በጣም ደስ አለው ፤
.....ከቀናት ቡሗላም ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብዬ በቤት ስልክ ተደወለልኝ እማዬ እንደምቶን እርግጠኛ ነበርኩ አነሳሁትና ድጋሜ የእናቴን ድምፅ ሰማውት እናም አንድ ጥያቄ ጠየኳት ለምን አንችን አልገደለሽም እማ? እሷም እያለቀሰች አባትህን አፍኖ ገደለና እኔን ምላሴን ሲቆርጠኝ አንተ የጮክ ጊዜ ተደናግጠው እኔን ተውኝና አንተን መፈለግ ጀመሩ ከዛም እንደሞትክ ሲያረጋግጡ ንብረታችንን ጠቅላላ ለመሸጥ የኔ ፊርማ ስለሚያስፈልጋቸው ከፈረምሽልኝ አልገልሽም ብሎ ቃል ገባልኝ ከዛም ፈረምኩለትና እኔን ሳይገለኝ ቀረ ከዛም ሜዳ ለይ ወደኩ የምበላው ነገር አጥቼ ባዶዬን ስቀር ያለኝ አማራጭ መልሶ እሱን መማፀን ነበርና በስንት ልመና ያለ በደመወዝ ሰራተኛ አደረገኝ ብላ ድንፇ እየተቆራረጠ ነገረችኝ እኔም እምባ እየተናነቀኝ እማ ስንት ብር ይሆናል የነበረን ካርመላ የወሰደብን አልኳት ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ነው አለችኝ...እሽ እማ ይሄንም እነወደማስመልሰው ቃሌ ነው አልኳት ከዛም
..... አንድ ስራ ሰጠሗት የቪድዮ ካሴቱን እንደ ምንም ፈልጋ እንድታገኝልኝ ነገርኳት እሽ ብላኝ ንግግራችንን ጨረስን

.......ከዛም ወዲያው ለካርመላ ደወልኩለት
...ሰላም ካርመላ እንዴት ነህ አልኩት
....ደና ነኝ ቩራል አንተስ መቼም መረጃው አገኘሁት እንዳትለኝ አለ
...አይ አሁን በጄ አልገባም እስከ ማታ ድረስ ግን አስገባለሁ ከዛ አይሀምን እስከ መጨረሻው እናጠፋዋለን አልኩት
..እንደዛ ከሆነ ሰሞኑን እንገናኛለን አለ
...አዎ ግድ ግን የዛ ቪድዮ ቅጅ አለህ እንዴ አልኩት
...ኧረ የለኝም ከፈለከው ግን ኮፒ አደርግልሀለሁ አለ
....ኧረ አታድርገው ችግር የለውም በፈለኩት ሰአት እነግርህና መጥቼ ኮፒ አደርጌ እወስዳለሁ አልኩት እሽ ብሎኝ ስልኩን አናግሬ እንደጨረስኩ ከቢሮ ለመውጣት በሩን ስከፍት መይሙና ከቢሮው በር ቁማ እያዳመጠችኝ ነበር....


በጣም እየዘገየ ነው እንዴ👍👍
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ አራት(14)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
.............ስልኩን አናግሬ እንደጨረስኩ ከቢሮ ለመውጣት በሩን ስከፍት መይሙና ከቢሮው በር ቁማ እያዳመጠችኝ ነበር....
..........ምን ልበላት እ...እ ምን መሰለሽ መይሙ ላስረዳሽ አልኳት
.........ምንም የምታስረዳኝ ነገር የለም ጋሽ አይሀም ምን አደረገህ አንተ ካርመላ ጋር ሁነህ ልታጠፋው!!! በጭራሽ አልፈቅድልህም አለችኝ
....መይሙ እባክሽ ተረጋጊ አንቺ የማታውቂው ነገር አለ ልንገርሽ
....መይሙ አትበለኝ ከሀዲ ነህ ሁሉንም ነገር ሰማሁት'ኮ እኔ ነኝ እንጂ ሞኚቷ የውስጤን ነግሬ አንተን ለመውደድ መሞከሬ አለች እምባ በተናነቀው ድምፅ ከዛም ለጋሽ አይሀም ደውላ በፍጥነት እንዲመጣ ነገረችው ላረጋገት ብሞክርም ጭራሽ ልትሰማኝ አልቻለችም
....እሱም ብዙም ሳይቆይ መጣና ምንድን ነው የተፈጠረ ችግር አለ እንዴ ሲል ከአፉ ተቀብላ
አዎ አለ! ያውም ትልቅ ችግር አቶ ቩራል አንተ ትነግራቸው ወይስ እኔ ላስረዳቸው
...በቃ ኑ! ወደኔ ቢሮ እንሂድ እና እናውራ ብሎ ይዞን ገባና ምን ሆናችሁ ነው አለ!!
.....ምን መሰሎት አቶ አይሀም አንድ ጊዜ ካስታወሱ መረጃ በገንዘብ እንድለውጠው የጠየቀኝ የእርሶዎ ጓደኛ ካርመላ የሚባለው ሰውዬ ጋር ተባብሮ ድርጅቱን ሊያጠፉ እንደሆነ በስልክ ሲያወራ ሰምቸዋለሁ ጥሩ ሰው መስሎ አስመሳይ ነው እንዳያምኑት አቶ አይሀም አለችው
.....እሱም ቩራል አንተ መሄድ ትችላለህ አለኝ
.......እሽ ብዬ ወጣሁ ቢሮዬ ውስጥ ቁጭ አልኩ ከትንሽ ቆይታም ቡሗላ እማዬም ደወለች
...ሄሎ እማ ደናነሽ አልኳት
...አዎ ደህና ነኝ ልጄ ምን ሆንክብኝ ድምፅህ ተቀይሯል አለችኝ የእናት ነገር ሁሉንም ልባቸው ይነግራቸዋል እንዳታስብ ብዬ ትንሽ ተኝቼ ነበር ለዛ ነው አልኳት

.....እንዳልክ ልጄ!! ያነ ባለፈው ያልከኝን ነገር አግኝቼዋለሁ አንተ ያልከኝ ለመሆኑ ግን እርግጠኛ አይደለሁም የምሞክርበት ነገር አጣሁ አለችኝ
.....ችግር የለውም እማዬ ብቻ አንቺ ተጠንቀቂ ነገ እንደምንም ብዬ እመጣለሁ አልኳት እሽ!!? ብላኝ ስልኩን ዘጋን
.....መይሙና እና ጋሽ አይሀም እስከ አሁን ከቢሮ አልዎጡም ለብዙ ሰአታት ጠበኳቸው በጣም ሲዘገዩ እኔ ወደ ቤት ሄድኩ የኔ ወደ ቤት መምጣት የምተደሰተው ሲትና እየሮጠች መጣችና በሩን ለመክፈት አቅሙ ባይኖራትም ወንድሜ ቩራል ወንድሜ ቩራል እያለች እስከምገባ በጉጉት ትጠባበቃለች ገዝቼላት የመጣሁትን ከሰጠሗት ቡሗላ ለእናቷ ለማሳየት እየሮጠች ሄደች
.....እኔ ዛሬ በጣም ስለደበረኝ ቀጥታ ወደ ክፍሌ ገብቼ ጋደም አልኩና ስለሁሉም ማሰብ ጀመርኩኝ በተለይ ስለ እማዬና መይሙ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እቅድ ለማውጣት እየሞከርኩ ሳላስበው መሽቷል!!
....ሲትና መጥታ ወንድሜ ቩራል ወንድሜ ቩራል ራት ደርሷል አባቢም መጥቷል አለችኝ
......ሲቱ ዛሬ እራት መብላት አልፈልግም ተኝቷል በያቸው ብያት ሄደች!!
.....ደግማም አልመጣችም እኔም በዛው የረባ እንቅልፍ ሳይዘኝ ነጋ ከመንጋቱ በጧት ተነስቼ ነበር ከቤት የወጣሁት!!!
....ቁርስ አንድ ካፌ ላይ በላሁ እና ወደ ስራ ገባሁ ወደ ቢሮ ስሄድ መይሙ የለችም ያለ ወትሮዋ ዛሬ እንዴት አረፈደች ብዬ ለሰአታት ብጠብቃትም አልመጣ አለች
.....አላስችል ሲለኝ ሰራተኞቹን ጠየኳቸው
.......ትናንት ጋሽ አይሀም ጋር አውርተው ከወጡ ቡሗላ የአመት ረፍት ወስዳ መሄዷን ነገሩኝ ግን ነገሩኝ ከምል አረዱኝ ብል ይቀለኛል በጣም ተናደድኩ ተበሳጨሁ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳ አላውቅም ለዚህ ሁሉ ነገር ያበቃኝን ካረመላን መጨረሻውን ማቅረብ አለብኝ ብዬ ደወልኩለት...

....ሄሎ ካርመላ ሰላም ነው አልኩት
...ደህና ነኝ ቩራል አንተ እንዴት ነህ ምን አዲስ ነገር አለ
.......ያልከኝን መረጃ ሁሉንም አግኝቼዋለሁ ዛሬ መገናኘት አለብን አልኩት
....እሽ ቩራል እኔ አሁን ቢሮ ነኝ እዛው እንገናኝ አለኝ
........እሽ ብዬ ስልኩን ዘጋሁና ላፕቶፔን እና የተዘጋጀውን መረጃ አንዷ ብቻ አስቀርቼ ሁሉንም ሰብስቤ እማዬን ቀድሜ ለማገኘት ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ መኪናዬ ሄድኩኝ ከዛም መኪናውን አስነስቼ በፍጥነት እየነዳሁ ከቤቱ ደረስኩ ከዛም ፥
....ከመኪናዬ ወረድኩ እና የጥበቃ ካሜራዎች ስላሉ ረጋ ብዬ ወደ በሩ ሄድኩ እና አንኳኳሁ እማዬ ብዙም ሳትቆይ ወዳው መጣችና ከፈተችኝ
በአይናችን ሰላም ተባብለን ወደ ውስጥ ቀድሚያት ገባሁ እሷም ብዙም ሳትቆይ መጣችና እንድከተላት በምልክት ጠቀሰችኝ ከዛም ወደ መታጠቢያ ቤት ሄድን በጉያዋ የያዘችውን ካሴት ሰጠችኝ እና ከወደ ውጭ የሚመጣውን ሰው ለመከታተል ጥላኝ ሄደች
.....እኔም የተቀበልኩትን ካሴት ላፕቶፔ ውስጥ አስገባሁት ውስጡ ምን እንደያዘ ለማየትና የምፈልገው ካሴት እንዲሆን እየተመኘሁ አይኔን ጨፍኜ ከፈትኩት.......


ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍41
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አስራ አምስት(15)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

:
:
....እኔም የተቀበልኩትን ካሴት ላፕቶፔ ውስጥ አስገባሁት ውስጡ ምን እንደያዘ ለማየትና የምፈልገው ካሴት እንዲሆን እየተመኘሁ አይኔን ጨፍኜ ከፈትኩት.......
ከዛም ቪዲዮው ማጫዎት መጀመሩን በድምፁ ስሰማ አይኔን ገልጬ አፈጠጥኩበት በጣም ተደሰትኩ ውስጤ በሀሴት ተሞላ እንደ መሳቅ እንደ ማልቀስም አልኩኝ
....ወደር ባጣ ደስታ ውስጥ ሆኜ ከዚህኛው ጠርዝ ወዳዛኛው ጠርዝ እየተዟዟርኩ ቪድዮውን እያየሁ ከውጭ የመኪና ድምፅ ሰማሁ ቶሎ በዬ ውስጥ ላይ ያለውን ሁሉንም ዶክመንት እንዳይመለስ አድርጌ ደመሰስኩትና እንዳይጠረጥር አንድ የቀልድ ቪድዮ ጫንኩበት!!
...እማዬም መጣችና ልጄ ካርመላ መጥቷል ከጨረስክ ወደ ቦታው ልመልሰው፤
.....ግን! የምትፈልገውን መረጃ አገኘህ አለችኝ፤
.....አዎ! እማዬ ብዬ ግንባሯን ከመንከስ ባልተናነሰ ሳም አደረኳትና፥እናቴ!! አንቺን ከዚህ ለማስወጣት ቢበዛ አንድ ሳምንት ነው የሚፈጅብኝ አልኳት፤ ልጄ አንተን ከሞት የመለሰ አምላክ ምንም አይሳነውም ባይሆን አንተ ራስህን ጠብቅልኝ አሁን ካርመላ እየጠበቀህ ነው ሂድ ብላ ካሴቱን ተቀብላኝ ወደ ቦታው ልትመልስ ሄደች.....እኔም ፊቴን ተጣጠብኩና ወደ ካርመላ ሄድኩ የሚገርም ነበር በደስታ ፈክቶ እየጠበቀኝ ነበር እኔም በቪድዮው መገኘት ስለተደሰትኩ ሁለታችንም የሞቀ እና በደስታ የታጀበ ሰላምታ ተለዋወጥን፤

....ከዛም ቁጭ ብለን መነጋገር ጀመርን የያዝኩትን መረጃዎች አሳየሁት ሁሉንም አንድ በአንድ አያቸው ፊቱ ደስታውን መግለጫ ያጣ ፈገግታ ይነበብበታል ከዛም አይቶ ጨረሰና
....ቩራል! እኔ ለአመታት ላሳካው ያልቻልኩትን አንተ በወራት ፈፀምከው ግን አንድ ወረቀት ብቻ የለችም አለኝ!...ውይ!! እሷማ ቢሮ መሳቢያዬ ውስጥ እንዳስቀመጥኳት ረስቻት ነው እንጂ በጄ ገብታለች ሰው ልኬ እንዳላስመጣት ትኩረት እስባለሁ ብዬ ነው ነገ አይሀምን ወደዚህ ሳመጣ አብሬ ይዣት እመጣለሁ ደግሞ እነዚህ መረጃዎች አንተጋ ይቀመጡ አልኩት እሱ ላይ ሙሉ እምነት እንዳለኝ ለማሳየት..
....እሱም በጣም ተማምነናል ብሎ ስላሰበ በደስታ አነጋገር ቆይ ቩራል አንዴ አለና ኪሱን ዳበስ ዳበስ አደረገና የባንክ ቡክ አውጥቶ ሰጠኝ ቡኩን ስከፍተው ስሜ እስነ አያቴ ተፅፏል ቀጣዩን ገፅ ስከፍተው ባለ ብዙ ዜሮዎች ባለቤት የሆነውን ሁለት ቢሊዮን ብር ይላል ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም እምባዬ መጣ ወደሱ ጠጋ አልኩና እየቀፈፈኝም ቢሆን አቅፌ አባቴ ማለት ነህ መቼም አረሳውም ያደረክልኝን አልኩት
...አንተም ልጄ ማለት ነህ ለወደፊት ብዙ ስራዎችን እንሰራለን ነገ ደግሞ አይሀምን ወደዚህ እንዳመጣሀውና ፊርማውን አስፈርመን ድርጅቱን እንደተረከብን ትልቅ ድግስ እናዘጋጃለን እንደ ትልቅ በዓል እናከብረዋለን አለኝ
...እኔም እምባዬን እየጠራረኩ እርግጠኛ ነኝ የተሻለ ቀን እናደርገዋለን ቤት ውስጥ ደግሞ ለነገ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አዘጋጅቶ እንዲጠብቀኝ ነገሬው አይሀምን ደግሞ በተባለው ሰዓት ይዤው እንደምመጣ ቃል ገብቼለት ተሰነባብተን ወጣሁ

....በፈነጠዝያ ወደ ጋሽ አይሀም አመራሁ ጋሽ አይሀምን እስካገኘው መንገዱ ረዘመብኝ ስልክ ደወልኩና
....ጋሽ አይሀም ተሳካ! ተሳካ! እያልኩ ጮኩበት
.....እሱም መኪና እየነዳህ ነው እንዴ አለኝ!
.....አዎ አልኩት!!!
...እባክህ ተረጋጋ ከዚህም የበለጠ ደስተኛ ትሆናለህ ግን ያንተ መኖር ግድ ነው ቢሮ ነኝ እጠብቅሀለው አለኝ
.....የዛኔ ረጋ አልኩና እሽ ጋሼ መጣሁ ጠብቀኝ አልኩት ከዛም መኪናው ከመንዳት አልፎ እያበረርኩት ቢሮ ደረስኩኝ
ጋሽ አይሀም ከእስከ ዛሬው በተለየ በሚያምር ፈገግታ ተቀበለኝ እኔ ግን ገና ሳየው እምባዬ መጣ የሱ መደሰት ለኔ ትልቅ ነገር ነበር ምንም ሳልናገረው ተጠመጠምኩበት እና ትንፍሼ እየተቁረጠረጠ እ..እ..ጋሽ አይሀም አ..አ..አሳካንው በድል ተወጣንው አልኩት!!!
..አዎ! ልጄ ትክክል ነህ አንድ ነገር ይቀረናል እናትህን ነፃ ማውጣት አለኝ!!
....ችግር የለውም ጋሼ እናወጣታለን ነገሮችን አስተካክያለሁ አልኩት
......እሱም ዛሬ ከካረመላ ጋር የነበረንን ቆይታ ጠየቀኝ?
...ከመጀመሪያው ጀምሮ ተረኩለት እንዴት አድርጌ ቪድዮውን እንደደመሰስኩት ጭምር ሌላ ቪድዮ እንደጫንኩበት ግን አልነገርኩትም.....ከዛም ነገ አብረን ሂደን እስከ ዛሬ ሲመፃደቅበት የነበረውን ነገር መና እንደ ቀረ አሳይተን አንገቱ ማስደፋትና እማዬን ነፃ ማድረግ እሱም በደስታ እንደምናደርገውና የሚያስፈልገንን ነገር አዘጋጅን ወደ ቤት ሄድን

....መሽቶ አይነጋ የለም እና የተባለው ሰአት ደርሶ ጋሽ አይሀምን ይዤው ወደ ካርመላ ቤት ሄድን!!
..ከዛም ከመኪናው ልንወርድ ስንል ጋሽ አይሀም ሽጉጡን ከመኪናው አወጥቶ ሲይዝ አየሁት
....ቆይ!! ጋሽ አይሀም እሷ ነገር እኔ ጋ ትቀመጥ አልኩት!!
....አይ ችግር የለውም አለ
...ኧረ ለኢላማውም ለምኑም እኔ እሻለሁ ምናምን እያልኩ በመከራ አግባባውት...
......እሱም ፈገግ ብሎ እሽ እንካ አደራ! ግን አደራ! ለውሳኔ ግን እንዳቸኩል ቩራሌ አለኝ!!
....እሽ ብዬው እሱ ከመኪናው ቀድሞ ወረደ ከዛም እኔ! መቼም ካርመላ በጥበቃ ካሜራ እንደሚያየን ስለ ገመትኩ ደወልኩለት እና መጥተናል ከበር ነን አልኩት እንደገመትኩትም
...እያየሗችሁ ነው ግቡ አለኝ!!
....እሽ ብዬ ልወርድ ስል ምን አልባች ችግር ተከስቶ ሽጉጡን ብተኩሰው የጋሽ አይሀም አሻራ እንዳይገኝ ብዬ መልሼ ገባሁና በደምብ ወለወልኩት ጋሼም የቆየሁበት ጊዜ
.....ምን ነው ቆየህ ልጄ አለኝ
.......መጣሁ መጣሁ ጋሼ ብዬ ተያይዘን ወደ በሩ ሄድን እንደተለመደው ግን እማዬ አልነበረችም የከፈተችን ቀድሞ ነበር በሩ ተከፍቶ የጠበቀን!!
....በጣም ደነገጥኩ ምን አልባች ቪዲዮውን ቀድሞ አይቶት ባዶ ሲሆንበት ሁሉንም ነገር አወቀብን እንዴ እማዬንስ ምን አደረገብኝ እያልኩ ፈራ ተባ እያልኩ ወደ ውስጥ ገባን ስንገባ........

ከ500👍 ቡሀላ ይቀጥላል
ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1