ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ሁለት(2)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

.........ምን አልባት ትምህርት ሊሆንህ ይችላልና ከልብ አዳምጠኝ ብሎ ትረካውን ጀመረ እኔ ማለት.......
.........""ስሜ አይሀም ይባላል ለቤተሰቦቼ አንድ ልጅ ነበረኩ የወንድም እና የእህትን ፍቅር አላውቀውም በኢኮኖሚ ደካማ የሚባሉ ቤተሰብ ልጅ ስለነበርኩ! ኑሯችንን የማሻሻል እና በእርጅና ዘመናቸው የምንከባከባቸው ብቸኛ ተስፍቸው ነበርኩ እንደምታስበው አልጋ በአልጋ ባይሆንም ተስፍ ባለመቁረጥ የፈጣሪ እገዛ ተጨምሮበት ያሰብኩትን አሳካሁ፤ ወላጆቼንም ከሁለት አመት በፊት ተካታትለው ሞቱ! አሁን ከነበርኩበት ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስዋእትነት ከፍያለሁ!
አሉ ከታባሉ የናጠጡ ባለፀጋዎች አንዱ መሆን ቻልኩ የስራው አለም ያገናኘን እኔን መሰል ጓደኞችንም ማፍራት ቻልኩ ከ20 አመት በፊት ትዳር መስርቼ አሁን የ19 እና 12 አመት ቆንጆ ሴት ልጆች አባት ነኝ አብዛሀኛውን ጊዜ ከቤት ስለማልኖር በጣም ይናፍቃሉ... ብሎ በእምባ የተሞሉ አይኖቹን እየጠራረገ አንገቱን አቀረቀረ""

... እኔም ታሪኩን እያዳመጥኩ ሳይታወቀኝ መቃፈፌን ጨርሼ ስጋውን ለመጥበስ እሳት እያቀጣጠልኩ ነው! ታሪኩን እንዲቀጥልልኝ
ታዲያ ይሄን እዚህ መገኘትህ ጋር ምን ያገናኘዋል አልኩት፥ .....""አንገቱን ቀጥ አደረገና ከንፈሩን እየመጠጠ.. ነገሩ እንዲህ ነው ከጓደኛቼ መካከል አንዱ ልጄን እንደወደዳት እንደ ቀልድ በተገናኘን ቁጥር ይነግረኛል እኔም እንዳልድርልህ አግብተሀል ኧረ እንደውም ከማግባት አልፎ የአንድ ልጅ አባትም መሆኑንም ስለማውቅ! ልጄን ለቀቅ አድርጋት እየተባባልን ተሳስቀን እንለያያለን ነገር ግን እኔ እንዳሰብኩት አልነበርም እንደውም በተቃራኒዉ ነበር ይባስ ብሎ እንደለመድንው አንድ ቀን ምሽት ላይ ተገናኘን እና ፊቱን ኮስተር አድርጎ ስለ ልጄ ደጋግሞ ይጠይቀኛል እኔም በንዴት ምንድን ነው አላበዛሁም በቃህ ብዬ ጮኩበት! እሱ ግን የሚመለስ አልበረም እንደውም ልጄ እንድድርለት እና ካልሆነ ግን! አለ? እንዴ ካልሆነ ምን ልታመጣ ብዬ አፈጠጥኩበት?!ቤተሰብህን በታትኜ ህይወትህን ጋሀነም ነው የማደርገው ብሎ ዝቶብኝ ወጣ! እኔም በንዴት አንዲት ነገር አደርጋለሁ ብትል ራስህን ማረሚያ ቤት ነው የምታገኘው ብዬ አስጠነቀኩት""...

በመሀል ንግግሩን አቋርጬ..ማለት በድብቅ ወንጀል ሰርቶ ነበር ማለት ነው ስል ጠየኩት!""በትካዜ ስሜት... ከአመታት በፊት በጣም አንድ ሚስኪን ለሰው አዛኝ ተጨዋች ጓደኛ ነበረን እናም አንድ ጊዜ ህይወታችንን ሊቀይር የሚችል የማዕድን ጨረታ ነበረ ጨረታውን ከሁላችንም ተሽሎ ያ ጓደኛችን አሸነፈ በሱ ማሸነፍ ሌሎቻችን በጣም ደስተኛ ነበረን እሱ ግን የሱ ማሸነፍ አልተዋጠለትም ከጓደኛው ይልቅ ገንዘብን አስበለጠ ስራውን በጁ ለማስገባት አማራጭ ብሎ ያሰበውንም እሱነ ማስወገድ ነበር እና እንዳሰበውም አደረገ ያ አረመኔ አስገደለው ስራውንም በጁ አስገባ!! ያን ወንጀል መስራቱን ደግሞ እኔ ደረስኩበት! እንዳወኩበትም ሲያውቅ አንድ ቀን ምሽት ከሁሉም ጓደኞቻችን ጋር ራት ለመብላት ተሰባሰብን ነበር እኔ ግን ራቱ ላይ መቆየት የቻልኩት ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ ነው የቀረበልኝን ኮካ ከጠጣሁት ቡሀላ የሚታወቀኝ ሁሉም ነገር ሲጨልምብኝ ብቻ ነበር! ከሰኣታት ቡሀላም ከተኛሁበት ስነቃ ሸሚዜ ወልቋል ቀበቶዬ ተፈቷል፤ ሰአቴን ስመለከት 3:00 ሰአት ይላል የተገናኘነው 2:00 ሰአት ነበር እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሞኝ ስለማያውቅ በድንጋጤ ልብሴን ለብሼ እነሱ ወደሚገኙበት በችኮላ አመራሁ! ከነሱ ስደርስ ራቱን ጨራርሰው ሊወጡ ሲል ነበር ምን እንደሆንኩ ስጠይቃቸው ራሴን ስስት ወደ አልጋ ወስደው እንዳስተኙኝ ብቻ ነገሩኝ ታዲያ ልብሴን ማን አወለቀው እያለኩ ለራሴ አሰብኩኝ! ከመካከላቸውም አንድኛው ወደ ቤት የሚል ቃል እንደወጣው ያ አረመኔ ከአፍ ተቀብሎ እኔ አደርሰዋለሁ አታስቡ ሂዱ ብሎ ላካቸው እንሱም ተሰናብተውን እንደወጡ
ላንተ ጥሩ ሰርፕራይዝ አዘጋጅቸልሀለሁ ብሎ እንድከተለው በምልክት ነገረኝ ግራ እየተጋባሁ ተኝቼበት ወደነበረው ክፍል ወሰደኝ ክፍሉን ከፈተውና ወደ ውስጥ ገባን በአይኔ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም"" ...

ከወደዳችሁት ይቀጥላል👍

አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
#አላህ ሱ.ወ #ከኩራት #ይጠብቀን

📚ኢብን ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ በለዋል
#ልብሱን #በኩራት የጎተተ አላህ በእለተ ቂያማ አያየውም”

#አቡበከረም “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሽርጤ ይጎተትብኛል “ አሏቸው እርስቸውም<<አንተ በኩራት ከሚጎትቱት አይደለህም>> አሉት (ቡኻሪና ሙስሊም)

📚አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የ አላህ መልዕክተኛ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል
#አንድ #ሰው በውብ ልብስና ተኩራርቶና ተኮፍሶ እየተንበጣረረ በመሄድ ላይ እንዳለ አላህ እስከ እለተ ቂያማ መሬቱን ገለበጠበት።”(ቡኻሪና ሙስሊም)
إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا [٤:٣٦]
“…..አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም” ቁርዓን 4:36
══ •⊰✿✿⊱• ══ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
══ •⊰✿✿⊱• ══
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍃🍃ጤ ና ዎ !🍃🍃
┈┈•✦•┈┈
.
☞ ሰባት ትላልቅ አዕምሮን የሚጎዱ ልምዶች:
.
➊. ቁርስን መዝለል ወይም ጨርሶ አለመመገብ።
➋. ማታ ዘግይቶ ወደ አልጋ መሄድ ወይም ዘግይቶ መተኛት።
➌. ከፍተኛ የስኳር መጠን መውሰድ/መጠቀም።
➍. ከመጠን በላይ መተኛት በተለይ ጠዋት (ከረፈደ በኋላ)።
➎. ቴሌቪዢን እየተመለከቱ ወይም ኮምፒውተር እየተጠቀሙ ምግብ
መመገብ።
➏. በሚተኙበት ወቅት ኮፍያ፣ ሻርኘ ወይም ካልሲ መጠቀም/ መልበስ።
➐. ሽንትን ሸንተው ሳይጨርሱ የማቋረጥ ልማድ።
---------
መልካም ጤንነት!!

☟ SHARE ☟
══ •⊰✿✿⊱• ══ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
══ •⊰✿✿⊱• ══
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ሶስት(3)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

ወደ ውስጥ ገባን በአይኔ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም"" ...
........ በስክሪን የኔ ምስል ያለበት ቪዲዮ ፥የሆነች ወጣት ልጅ ሸሚዜን አውልቃ ቀበቶዬን እፈታች የባለጌ ፊልም እንደሰራው አድርጎ የተቀረፀ ምስል በቃ ምን ልበልህ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ ልጆቼ ሚስቴ ትዝ አሉኝ ይሄን ሲያዩ ምን ሊሆን እንደሚችል በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ እያለ ራሱን መነቅነቅ ጀመረ""
.....በመሀል ወሬውን ማቋረጥ ባልፈልግም ስጋውን ጠብሼ ስለጨረስኩ ቁምሳ ደርሷል ከብዙ ጊዚያት ቡሀላ ሰው ጋ ልበላ ነው ብዬ አቋረጥኩትና እሱም ከነበረበት ስሜት ለመውጣት ፈገግ እያለ ወደኔ ቀረበ ከዛም መመገብ ጀመረን በመሀል ደስ የሚል ህይወት ውስጥ እንዳለሁ እና ብቸኝነቴን እንደወደደልኝ ነገረኝ "አልሰሜን ግባ በለው ይላል የሀገሬ ሰው ወዶ አደለም" ምን ደስ ይላል የኔ ህይወት አልኩኝ በሆዴ " ከዛም በልተን እንደጨረስን ትንሽ አረፍ ካልን ቡሀላ ትረካውን እንዲቀጥልልኝ ዳር ዳር ማለት ጀመረኩ እሱም ሀሳቤ ስለገባው ያቆመበትን ጠየቀኝ እኔም ነገረኩትና ትርክቱ ቀጠለ ....

ከዛም .. ሁሉም ነገር ጨለመብኝ የምይዘውንም ሆነ የምጨብጠውን ነገር፥ አላቅም በጣም ጮኩኝ፧ እሱ ግን እኔ በምሆነው ነገር በደስታ ይስቃል፥ ይባስ ብሎ ሀሀሀሀ...ለመሆኑ ምን ላይ እንድለቅልህ ትፈለጋለህ fb, YouTube ወይስ ጋዜጠኞችን ጠርቼ ለነሱ ልስጣቸው የትኛው ይመችሀል እያለ አፌዘብኝ እኔም ምንም ሳልናገር ሀፍረቴን ተኮናንቤ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ፥
እንግዲህ ከዛ ቀን ጀምሮ ነው በዛ ሲዲ እያስፈራራኝ ልጄን ይቀርባት ጀመር፤ይህን በአይኔ እያየሁ መቋቋም አልቻልኩም ከማንኛው ልሁን ልጄን ልኩኝ ሙሉ ትዳሬ ሊፈርስ ነው በተዘዋዋሪ ላዋርዳቸው ነው እያየሁ ዝም ካልኩ ደግሞ ልጄን አይኔ እያየ ገደል ልትገባብኝ ነው ስ መስራትም መኖርም አልቻልኩም አማራጭ ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ ሞከርክ ግን አልቻልኩም መጨረሻ ላይም ወደዚ ጫካ ራሴን ላመሸሽ መጣሁ አለ ሲቃ በተሞላበት ድምፅ፥

.........ሰውዬው ግን ማን ነው? ብዬ ልጠይቀው አሰብኩና ማንስ ቢሆን ምን ይለወጣል፤ ሰውዬው አንዴ ወደዚህ መጥቷል ባቀውስ ሂጄ ልገለው ነው፥ እያልኩ በሆዴ አጉረመረምኩ። የጊዜ ነገር ይገረማል! ሳናስበው ፀሀይ ወደ ቤቷ ለመጥለቅ አዘንብላለች፥ ሰውየውንም ይህን ሁሉ ታሪክ ከነገረኝ ቡሗላ፤እንዳልሰማ መሆን ስላልፈለኩ ከቋጥኝ ስር ወዳለችው መኖሪያ ዋሻዬ ወሰድኩት ብርሀንም ጊዜውን ጨርሶ ለጨለማ አስረክቧል እስክንተኛ ድረስ የምንሞቀው እሳት አቀጣጥዬ፥ ከጧት የተረፈንን ስጋ እየጠባበስን ስንበላ አመሸን፥ በመሀል ስለኔ ማንነት ለምን ወደዚህ እንደመጣሁ ሲጠይቀኝ ነበር። ለመናገር አልደፈርኩም ነገ እናወራለን ብዬ የሚተኛበት ቦታ አሳየሁት፤ ደክሞት ስለነበር ቶሎ ነው እንቅልፍ የያዘው ተኝቶ ግን ልጄ ልጄ እያለ ሲቃዥ! ነበር ያደረው፤ አይነጋ የለምና የሌሊቱ ተራ አብቅቶ ለብርሀን ለማስረከብ ወገግ ሲል የምንበላው ለማደን እሱ በተኛበት ወጥቼ ሄድኩ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የሚታደን እንሰሳ ሳላገኝ በባዶው ነበር የተመስኩት ከዋሻው እንደደርስኩግን ለማመመን የሚከብድ ነገረ ነበር ያየሁት..........

ይቀጥላል

አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1👍1
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አራት(4)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

ከዋሻው እንደደርስኩግን ለማመመን የሚከብድ ነገረ ነበር ያየሁት..........
............ ያ! ሚሊየነሩ ሰውዬ ስጋ እየጠበሰ ነበር በሁኔታው በጣም ተገርሜ እንደት ሊያደርገው ቻለ እያልኩ ከሱ በቅርብ ርቀት ቆምኩኝ ድንገት ዘወር ሲል አየኝና ""እንዴ ነህ ወጣቱ ደና መጣህ እንዴ ደና አደርክ ና! ቁርስ ደርሷል"" እንብላ አለኝ
.....ፊቴን ፈገግ አያደረኩ ከመብላቱ ይቀድም ግን እንዴት ማለት በምን አድነህ ነው ስል ጠየኩት?
የሽፍታ አጓጉል "ጩቤህን አይተኸዋል" አለኝ ጎምበስ ብዬ ሳይ የለም እንዴት ልትወስድብኝ ቻልክ....☺️
........"እንካ ረስተከው ነው" ብሎ ሰጠኝ እኔም ተቀበልኩና ወደ ቦታው መልሼ የተዘጋጀውን ምግብ እየበላን በዛው ወሬ ጀመርን ገጠመኞቹን ስለህይወቱ ሁሉንም ነገረኝ የልጆቹን ፎቶ ከያዘው ዋሌት አውጥቶ አሳየኝ እውነትም በጣም ቆንጆዎች ናቸው፤

.........እንዲህ እንዲህ እያልን ባለ ብርሀኗ ፀሀይ፤እንደነሀስ ከምትጠራው ጨረቃ ጋር እየተቀያየሩ ቀናቶች ነጉዱ፥ይበልጥ መቀራረብ ጀምርናል እየበላን መጎራረስ መጫወት መዝናናት ከዛ የበለጠ ግን ወጣቱ ማለቱን ትቶ <የኔ ልጅ> እያለ ነው የሚጠራኝ ያም ሆኖ ግን ግልፅ ልሆንለት አልቻልኩም ፥ሁሌም ስለ እኔ ሲጠይቀኝ ቶሎ ብዬ ወሬ እቀይራለሁ፤ እሱም ብዙ አያጨናንቀኝም ዛሬ ግን ልነግረው ወስኛለሁ።
.............ጋሽ አይሀም አልኩት ""አቤት የኔ ልጅ አለኝ"" እንደዚህ ሲለኝ ዕውነት የሱ ልጅ የሆንኩ ያክል ነው የሚሰማኝ
.........'' የምነግርህ ነገር አለ አልኩት "" እሽ ደስ ይለኛል ጥሩ ነገር እንደሆነ ታ ፍ አደርጋለው እያለ ጥላ ወዳለው ዛፍ ስር ቁጭ አልን፤ መናገር ጀመርኩኝ እ..እ..እኔ ዛሬ ሁሉንም ነገር ልነግርህ ፈልጌ ነው አልኩት
..........""እያዳመጥኩህ ነው እሽ" የኔ ልጅ ቀጥል አለኝ

ከየትኛው እንደምጀምርለት ባላውቅም ከውልደቴ መጀመርን ሻሁ፤
.......እኔ ከዚህ በአምስት ኪሎሜትር ከምትርቀው ደማስቆ ውስጥ ነው ውልደቴ እና እድገቴ ስሜ ደግሞ #ቩራል ነምሩድ ይባላል ብዬ ከመጀመሬ ጋሽ አይሀም ፊቱ የመደንገጥ እና መረበሽ ስሜት ይታይበታል"
......ምን ነካው ስሜ ያስደነግጣል እንዴ ብዬ ለራሴ ባላየ ንግግሬን ቀጠልኩ፤
......... በጣም ደስተኛ እና ምርጥ ቤተሰብ ውስጥ ነው የተወለድኩት ፤ እንዳንተ ታላቅም ሆነ ታናሽ ወንድም ወይም እህት የለኝም፥ አባቴ የተካበደ ባይሆንም ሀይለኛ ነጋዴ ነበር መካከለኛ ሀብታም ከሚባሉትም ነበር ለዛም ነበር አቀማጥለው ያሳደጉኝ፥ምን ያደርጋል ያ..ያ..ያ ደስተኛ ቤተሰብ በአንድ ቀን ብትንትኑ ወጣ፤
አልኩኝ እምባዬ እየተቀዳደመኝ፤ እምባዬን ዋጥ አደረኩና ከስድስት አመት በፊት የ 10ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ከትምህርት ቤት ውዬ ስመለስ፥ ግቢያችን ከወትሮ በተለየ በአበባ አሸብርቋል፤ በአግራሞት እያየሁ ወደ ዉስጥ ገባሁ፥ እናቴ እንደዛ ቀን ፊቷ በፈገግታ ተሞልቶ አያቅም፥ ሰላም ካልኳት ቡሗላም ምን አዲስ ነገር እንዳ ጠየኳት፤
......እሷም""የእኔ እና የአባትህ የጋብቻ ቀን ነው"" አለችኝ ኦው እንኳን ደስ ያላችሁ አስታውሳለው የሰርጋቹህ ቀን እኔን ከቤት ትታቹኝ ነበር የሄዳችሁት አልኳት አንተ ወሬኛ ወሬ አይቅርብኝ ነው ኣ እያለች እየተሳሳቅን ወደ ክፍል ገብቼ ልብስ ቀየርኩና ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ አስቤ ወደ እናቴን አስፈቅጄ ጓደኞቼ ጋ ሄድኩ፥
.....ከጓደኞቼም ጋር እየተጨዋወትን ሳለ ድንገት ውስጤ ተረበሸ ሆዴ ዝም ብሎ መንቀጥቀጥ ጀመረ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አልነበርም ጓደኞቼም በሁኔታዬ ሲደናገጡ ሳይ በቃ ተጫወቱ እኔ ቤት መሄድ አለብኝ ብዬ ታክሲ ይዤ ወደ ቤት ተመለስኩ፥

..........ሰፈር እንደደርስኩም ሆኖ የማያውቀውን የግቢያችን የውጭ በር ተከፍቷል ምን ነካቸው መቼም ረስተው አይሆንም እያልኩ በፍርሀት ስሜት ወደ ውስጥ ገባሁ፤ ከቤታችን በር ላይ አንድ ፀጉረ ልውጥ ሰውዬ ቆሞ ግቢውን በአይኑ ይቃኛል፥ ይበልጥ ፍርሀቴ ጨመረው ቶሎ ብዬ ሳያየኝ ቀስ ብዬ ወደ ጀርባ በር ሄድኩኝና አይኔን ወደ ሳሎን ላኩኝ፤ ሁለት ግባብዳ ሰወች የፊጥኝ እናትና አባቴን ይዘዋቸዋል....

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
👍1
#በሕይወትህ #ዘመን #ይህን #አስብ!"

⭐️ #ደስታና #መከራ ባገኘህ ጊዜ ሁለቱም በመጠንና በእርጋታ ተቀበላቸው እንጂ በደስታ ጊዜ ፈንጠዝያ በመከራ ጊዜ ደግሞ መጨነቅ አታብዛ።

⭐️ #ደስተኛ #ሆነህ መኖር ከፈለግክ ልብህን ከጥላቻ እንዲሁም አእምሮህን ከጭንቀት ነፃ አድርግ።

⭐️ #ኑሮ #እንድታለቅስ #መቶ ምክንያቶችን ከሰጠችህ፤ አንተ ደግሞ ፈገግ ለማለት ሺህ ምክንያቶችን ደርድርላት።

⭐️ #በዚህ #ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በእርጋታ ኑር፤ ከፀጥታ ሰላምና እረፍት የሚገኝ መሆኑን አትዘንጋ።

⭐️ #አሁን #እያለፍክበት #ያለው #ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድልህን እንድታማርር እያደረገህ ይሆናል፤
☞ነገ የሚመጣውን ግን አታውቅም፤
☞የአንተ ችሎታና ጥበብ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበል እና ነገን ለአላህ መተዉ ነው።



☟ SHARE ☟
━─━────༺༻────━─━
https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አምስት(5)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

ቀስ ብዬ ወደ ጀርባ በር ሄድኩኝና አይኔን ወደ ሳሎን ላኩኝ፤ ሁለት ግባብዳ ሰወች የፊጥኝ እናትና አባቴን ይዘዋቸዋል....
ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ፀጉሬ ነዘረኝ ከአባቴ ጓደኞች አንዱ ደግሞ ከፊታቸው ሆኖ እየተወራጨ በሽጉጥ እያስፈራራ ሲዝትባቸው ይታየኛል በዛ ሁኔታም ለ30ደቂቃ ያክል አካባቢ በዚሁ ሁኔታ ቀጠለ እነሱንም አንዴ በጥፊ አንዴ በእርገጫ አያለቸው.........ከዛም አባቴን በፌስታል አፈኑትና መፈራገጥ ጀመረ እናቴን ደግሞ ምላሷን አይኔ እያየ ሲቆርጧት ተመለከትኩ የዛኔ መቋቋም ስላልቻልኩ ጮኩኝ ፤ እነሱም ድምፄን እንደሰሙም እየሮጡ ድምፄን ወደሰሙበት አቅጣጫ መጡ.........እኔም በደመ ነበስ ሩጫዬን ተያያዝኩት ለብዙ ሰአታት ተሯሯጥን ከዛም የነበረኝ አማራጭ ወደዚህ ጫካ በመግባት ራሴን ማዳን ስለነበረብኝ ገባሁና በቅጠል ውስጥ ተደበኩ፤

.......በትንሽ ልዩነት ቆይተው ጫካው ውስጥ እየተሯሯጡ ደረሱ ከዛም ማሰስ ጀመሩ በፍረሀት ውስጥ ሁኜ ሳላስበው....አንድ ሰውዬ ከጀርባዬ አፌን አፈነኝ ከዛም ራሴን ሳትኩ እየሞትኩ ነው ብዬ ነበረ ያሰብኩት፤ ከቆይታዎች ቡሀላ ስነቃ ራሴን አሁን ከምንኖርባት ዋሻ ውስጥ በቦዲና ቁምጣ ብቻ ነበረኩ፥ዘወር ዘወር ብዬ ሳይ ዋሻ ውስጥ እንደሆንኩ ተረዳው ከተኛሁበት ተነሳሁና ወደ ውጭ ወጣሁ ውጭ የሆነ ሸምገል ያለ ሰዉዬ ቅጠላቅጠል ይቆራርጣል፤ ከዛም የሆነውን ለማስታወስ ሞከርኩ ከሗላዬ አፌን ያፈነኝ ሰውዬ እሱ ነው ማለት ነው እንዴ ቤተሰቦቼ ትዝ አሉኝና በጩኸት አቀለትኩት!..... ከዛም ያ ሽማግሌው መጥቶ አረጋጋኝና የተከተሉኝ ሰዎች ምን አድርጊያቸው እንደሆነ ጠየቀኝ ከነገርኩት ቡሀላ ግን ወዳው ከጫካው መዉጣት ስለፈለኩት ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ፥ ሽማግሌው ግን በጭራሽ አለኝ ምን አገባህ ብዬ ላመልጥ ስል እንደ ገና ራሴን አስቶ አሰረኝና ተኝቼበት ከነበረበት ቦታ ወሰደኝ! ለአንድ ቀን ያህልም አስቀመጠኝ በመሀል ግን ምግብ ይዞ እየመጣ ብላ ሲለኝ አልፈልግም እያልኩ በጩኸት አስቸግረው ነበረ፤.

ጩኸቴ ሲሰለቸው መጣና የታሰርኩበትን ፈትቶ ""ሂድ ወደፈለከው እንደ ዶሮ ይቦጫጭኩሀል አለኝ"" ይሄኔ ልሮጥ የነበረ ቆም አልኩኝና በርጋታ እንዴት ወደዚህ እንዳመጣኝ ጠየኩት
በሽማግሌ ድምፁ" መጀመሪያ እየተሯሯጣችሁ ስትመጡ አየሗችሁ ከዛም አንተ ስትደበቅ ሳይህ ላንድ ህፃን ልጅ ሶስት ጠብደል ሰዎች ምን አድርጓቸው ነው ብዬ ራስህ እንድትስት አደረኩና ይዤህ መጣሁ...... ከዛም ልብስህን አውልቄ በደም ነከርኩና ትንሽ ስጋ ውስጡ ላይ አድርጌ በሚፈልጉህ ቦታ አካባቢ ጣልኩላቸው እነሱም በቃ ሙቷል ተገላገልን እያሉ ሄዱ ዛሬ ጧት አንተ ተኝተህ ተመልሰው አንድ ባለ መነፀር ሰውዬ ጋር መጥተው ነበር መሞትህ ለማረጋገጥ"" ይመስለኛል አለ የዛኔ ይበልጥ ተስፋዬ ጨለመ፥
.....የአባት እና እናቴን ቤተሰቦች አላቃቸውም ምክንያቱም ቤተሰቦቻቸው የነሱን አብሮ መሆን ስላልፈለጉት እንዲለያዩ ሲያስቸግሯቸው የተወለዱበትን ሀገር ትተው ነው የመጡት ለዛም ነው የማላቃቸው ፤...እናም ከዛም ቀን ጀምሮ እሱ ጋር መኖር ጀመርኩ ብዙ ነገረ አስተምሮኛል አንዳንድ መድሀኒቶችንም መቀመም አስተምሮኛል
....በመሀል ጋሽ አይሀም ""እና አሁን ሰውየው የታለ"" ሲል ጠቀኝ

.......ከወራት በፊት ልጄ ናፈቀኝ አንድ ጊዜ እንኳ አይቸው ልሙት ብሎኝ ሄደ በዛው ሳይመለስ ቀረ ይመጣል ብዬ ብዙ ጊዜ ጠበኩ ጠበኩ!
.......በመጨረሻም አላስችለኝ ሲለኝ የሀገሩን ስም ነግሮኝ ስለነበር እንደምንም ብዬ ሄድኩኝና ከአካባቢው ሰወች ከወሬ ወሬ ሳጣራ ከኔ ጋር ከተለያየን ቡሀላ ብዙ ጊዜ እንዳልቆየና እንደሞተ ነገሩኝ!....... በቃ ከዛን ጊዜ ወዲህ ከሱ በወረስኩት ጫካ እና ዋሻ ዉስጥ እየኖርኩ ነው ይሄው ፈጣሪም ብቻህን አትሁን ሲለኝ አንተን ላከልኝ አልኩት፥..... ""ጋሽ አይሀምም መጥቶ እቅፍ አደረገኝና ለመሆኑ ከዛን ወዲህ ወደ ከተማ ወጥተህ አታቅም አለኝ"
.....ኧረ በጭራሽ #ካርመላ የሚባል አረመኔ ከምድረ ገፅ ያጥፍኝ ብለህ ነው ከማለቴ ድንጋጤና እብደት በተሞላበት ስሜት ምን! ማን ነው ያልከው ካርመላ! ካረመላ! እያለ መጮህ ጀመረ...

ከ200👍 ቡሃላ ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
👍31
#ውርስ

የቤተሰባቸውን የእርሻ መሬት ወርሰው በጋራ የሚሰሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ። አንደኛው ትዳር መስርቶ ትልቅ ቤተሰብ ሲኖረው ሁለተኛው ግን ብቻውን ነበር የሚኖረው።

ከዕለታት አንድ ቀን ወንድማማቾቹ ከቤተሰባቸው የወረሱትን ሃብትና ያፈሩትን ንብረት በመከፋፈል በየግላቸው ለመስራት ይስማማሉ። ያለውንም ሃብት እኩል ተካፋፍለው የየግላቸውን ኑሮ ይጀምራሉ።

ወዲያውኑ ግን ብቻውን የሚኖረው ወንድም ከራሱ ጋር መነጋገር ይጀምራል "ያለውን ሃብትና ንብረት እኩል መከፋፈላችን አግባብ አልነበረም። እኔ ብቻዬን ነው የምኖረው። የሚያስፈልገኝ ነገር በጣም ትንሽ ነው። እርሱ ግን ብዙ የቤተሰብ ኃላፊነት አለበት" በማለት ያስባል። እናም በጎተራው ካለው እህል አንድ ጆኒያ የሚሆነውን ሁል ጊዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል።

በተመሳሳይ ጊዜ ሚስትና ልጆች ያሉት ወንድምም በተመሳሳይ ሁኔታ ያስባል "ይህንን ሃብት እኩል መካፈል አልነበረብኝም። እኔ እኮ ትዳር አለኝ።። ሚስቴ እና ልጆቼ ሁል ጊዜ ከጎኔ በመሆናቸው ወደፊት በደንብ ይንከባከቡኛል። ወንድሜ ግን ብቸኛ ነው። ወደፊት አጠገቡ ሆኖ የሚንከባከበው እንኳ የለውም" ሲል ያስባል። እርሱም እንደዚያኛው ወንድሙ በጎተራው ካለው እህል አንድ አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ጊዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል።

ወንድማማቾቹ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ጊዜ ኖሩ። ከብዙ ጊዜ በኋላ ግን ሁለቱም አንድ ነገር ያስገርማቸው ጀመረ። በጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠን እየቀነሰ አለመሄዱ ግራ ያጋባቸዋል።

ሁለቱም የገጠማቸውን ያልተለመደ ነገር ለመመርመር በየግላቸው እየጣሩ ሳለ ከዕለታት አንድ ቀን ለሊት ላይ የተለመደውን ተግባራቸውን ለመፈፀም እህል የተሞላበት ከረጢት እንደተሸከሙ በድንገት ተገናኙ። ምንም ዓይነት ቃላት ሳይለዋወጡ ሸክማቸውን መሬት ላይ በመጣል በፍቅር ተቃቅፈው አለቀሱ።

አላህ እንዲህ ዓይነት ውዴታ ይወፍቀን...😍

#አስተምህሮት...... ወንድምህ ምንም ቢሆን ምን ወንድምህ፣ ደምህ ፣ ስጋህ ፣ ነው። ከማንም በላይ ክፋ ቢመስልህ እንኳ ይወድሃል። እሱን በማንም እንዳትቀይረው።

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
👍1
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ስድስት(6)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

.....ኧረ በጭራሽ #ካርመላ የሚባል አረመኔ ከምድረ ገፅ ያጥፍኝ ብለህ ነው ከማለቴ ድንጋጤና እብደት በተሞላበት ስሜት ምን! ማን ነው ያልከው ካርመላ! ካረመላ! እያለ መጮህ ጀመረ...
......በሁኔታው በጣም ተደናገጥኩ የማደርገው ቅጡ ጠፋኝ እንደምንም ብዬ አግባብቼ ቀስ አድርጌ እንዲቀመጥ አደረኩት.....ከዛም ምን ሆነህ ነው አልኩት፥ ከእግሬ ስር ተምበርክኮ ይቅር በለኝ! እባክህን ይቅር በለኝ! ልጄ እያለ ይማፀነኝ ጀመር ፤ምንም ነገሩ ስላልገባኝ ኧረ! ጋሽ አይሀም ራስህን ተቆጣጠርና ምን እያደረክ ነው አንተ ምን አድርገከኛል ብለው ሊሰማኝ አልቻለም እሽ በስርዐት አስረዳኝ አልኩት ""እ..እ..እ...ነምሩድ ልጅ እንዳለው አላውቅም ነበር ለፖሊስ ባለማጋለጤም ጥፋተኛ ነኝ፤ ግን እመነኝ ሳልፈልግ ቀርቼ ሳይሆን ማስረጃ ስላልነበረኝ ነው"" አለ እምባውን እያንጠበጠበ፥
......... እኔ ግን ነገሮች ይበልጥ ተወሳሰቡብኝ፤ ምን ለማለት ፈልገህ ነው አልኩት ኮስተር ብዬ
.....""ባለፈው ታስታውሳለህ ስለ ራሴ ስነግርህ እኔን ከዚ ሁሉ ጣጣ የከተተኝ ሰውዬ! የሰራውን ወንጀል እንደማጋልጠው የዛትኩበት ካ..ካ..ካርመላ ነው"" አለ፥ በተቆራረጠ ድምፅ.

ስሜቴ የተደበላለቀ ሆነ እምባዬ እየተናነቀኝ እግሬን ከሱ አላቅቄ ጥዬው ሄድኩኝ ከዛም ብቻዬን ለብዙ ሰኣት ራሴ ጋ አወራው ጥሩው ነገር ቀድሞ ስለራሱ ስለነገረኝ በሱ ላይ መፍረድ አልቻልኩም...ወደሱ እየመሸ ስለነበር ወደ ማደሪያችን ተመልስኩ ጋሽ አይሀም በፀፀት እና በቁጭት ስሜት ውስጥ ሆኖ አንገቱን ደፍቶ አገኘውት ደሱ ቀረብ አልኩና ጋሽ አይሀም ስለው
.....እረዳሀለው ልጄ ልክ ነህ ግን አማራጭ አልነበረኝም አለ...አዎ ልክ ነህ ሁሉንም ነገር አስቤበታለው ቢያንስ እሱን እነጦሮጦስ ለመክተት አናንስም አሁን ሁለት ሆነናል፥ ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ አይደል የሚባለው"" አልኩና አቀፍ አርጌ አነሳሁት...ግን ይቅር በለኝ ልጄ ማለቱን አላቆመም ጋሽ አይሀም ከልቤ ይቅር ብዬሀለው እንዳያስስብህ ብዬ እየተሳሳቅን ገባን

...... ከዛም ቀን ጀምሮ እቅድ ማውጣት ጀመርን ሁሉም ነገር አንድ በአንድ እንዴት አድርገን መበቀል እንዳለብን ሙሉ ፕላኑን አዘጋጀን፥ እንደዚ አይነት እቅድ ፊልም ላይ ነበር ያየሁት አሁን በገሀዱ አለም ልጋፈጥ ነው..ቀናቶች እየተቀያየሩ ወራቶች አለፉ! እንሆ ዛሬ ጋሽ አይሀም ጋር ከተገናኘን ሶስት ወር አለፈን፤..ዛሬ ለኔ ታላቅ ቀን ነው ከስድስት አመት በላይ ከመሸኩበት ጫካ ወጥቼ በድጋሜ #ኑሮዬን ባልታሰበዉ መንገድ ልመራ ለመውጣት እየተዘጋጀን ነው..... ይህ ነገር ለኔ በጣም ትልቅ እድልም ነው በህልሜ እንኳን አልሜው የማላቀው ነገር፤ ከጫካ ው መዉጣታችን ደግሞ የበቀል ጅማሬውን ማብሰሪያ ነው! ዋሻችንን ተሰነባብተን ከጫካው ወጣን ከእስር የተለቀኩ ያክል ነው የተሰማኝ፤ ቅጠሎችና ሀረጎች አልፍ ከኔ የምትደርሰው ፀሀይ ዛሬ በፎቆች መካከል በነፃነት ከአመታት ቡሗላ ተያየን!....ከኪሱ ዉስጥ ለወራት እየተቆራመተች በቆየችው ሀምሳ ብር ታክሲ ይዘንባት መሄድ ወደቤቱ አመራን፤

አቤት! የሰው ነገር ታክሲ ለይ ተሳፍረን እየሄድን ሳለ የኛን የልብስ መቆሸሽ አይተው ለመጠጋት እንኳ ሲፀየፉ! ለጡሩ ለባሾች ሲያጎበድዱ የነበሩ ሰዎችን እያየን ለኛም ለነገ ትምህርት ነውና በትዝብት ከምንፈልገው አካባቢ እንደደረስን ወረድን...አካባቢው ፀጥ ያለ ነው ከወረድንባት ቦታ እስከ ቤት የአምስት ደቂቃ የሚሆን መንገድ አላት ወደ ሰፈሩ ውስጥም እየገባን ሳለ ሰወች እየዞሩ በዚህ ባለሀብት ሰፈር ውስጥ እነዚህ ቡቲቶ ለቤሽ ሰወች ምን ይሰራሉ የሚል አስተያየት ያዩናል፤....ግን እኮ አብዘሀኛው የሰው ልጅ ስንባል የሰውን ማንነት በልብስ ነው የምንለካው እያልኩ ለራሴ እየነገርኩ ከቤቱ ደረስን መሰለኝ! ጋሽ አይሀም እዚ ጋ ነው ብሎ ወደ በራፉ እንድጠጋ አመለከተኝ ከዛም የጥሪ ደወሉን ተጫነዉ!.....ማን ነዉ! መጣን! መጣን! የሚል ጎርነን ባለ ድምፅ ከወደ ውስጥ ሲናገር ይሰማል...ከዛም በሩ ተከፈተ እንደጠበኩትም የገጠር ሰው አክት ያለው ጎልማሳ ሰውዬ! ነው! ....ምንድን ነዉ! ምን ፈልጋችሁ ነዉ አለ!

ትብዝቴ በዛብኝም እንደው በአክብሮት እንኳ ቢያናገረንስ ለነገሩ የጋሽ አይሀም ፂሙና ፀጉሩ ስላደገ መለየት ያቃተዉ ይመስላል፥.. ከዛም ጋሽ አይሀም ምንም ሳይናገር ፈገግ አለ የዛኔ አንዴ ጋሼ ነሁ እንዴ! አለና ዘሎ ወጣበትና የመንከስ ያክል አዟዙሮ አዟዙሮ ሳመውና ወደውስጥ ገባ ብሎ እልልታውን አቀለጠው ልጆቹ ምን ሆነ ብለው እየተሯሯጡ ሲመጡ አባታቸዉ ነው አባቢ! አባቢ! እያሉ መጥተዉ ወጡበት አየሳሙ አቅፈው ምን ሆነህ ነው እያሉ እያካለቡ ይዘዉት ሊገቡ ሲሉ ና! እንጂ ግባ አትፍራ አለኝ! አንድኛዋ ልጅ ቀጠል አድርጋ ማን ነዉ አባቢ አለችው..
.....ቩራል ይባላል ከአሁን ቡሗላ እኛ ጋ ነው የሚኖረው በደምብ ይረፍና ትተዋወቃላቹ አሁን ግቢና ክፍሉን አሳዪው ሻወርም ይውሰድ አላት እሽ ወንድም ቩራል #ኒሀል እባላለሁ ግባ አለችኝ ውበቷ አይቶ አለማድነቅ ይከብዳል እንደመሽኮርመም እያደረገኝ እሽ ብዬ ወደውስጥ ስንገባ ትንሿ ልጅ ማሚ ማሚ! አባቢ መጣ እያለች ቤቱን በጩከት ቀወጠችው ሚስቱም ከሩጫ ባልተናነሰ መጥታ ተጠመጠመችበት እዚ ለይ ግን አንድ ነገር ተረዳሁ በምንም አይነት ሁኔታ በፈገግታ ሰላም አለችን

........ከዛም እኔን ኒሀል ክፍሌን ልታሳየኝ ደረጃውን መውጣት ስንጀምር ፤እንኳን ደህና መጣህ ዉድ ጓደኛዬ የሚል ማፌዝ የተሞላበት የወንድ ድምፅ ሰማሁ ቶሎ መለስ! አልኩና የሰዉየውን ማንነት ሳይ፤......ያቺ ቤተሰቦቼን ያጣሁበትን ምሽት አስታወስኩ ሽጉጥ ደቅኖ ሲዝት የነበረው ሰዉዬ #ካ ር መ ላ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ ዘልዬ ላንቀውም ፈለኩ........

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
1
አሞራው በሰማይ ላይ

ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት
«ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት
«አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።

በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ
«አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን።

አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።
ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር
《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት።

ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያዳርሱ።

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ሰባት(7)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

የሰዉየውን ማንነት ሳይ፤......ያቺ ቤተሰቦቼን ያጣሁበትን ምሽት አስታወስኩ ሽጉጥ ደቅኖ ሲዝት የነበረው ሰዉዬ #ካ ር መ ላ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ ዘልዬ ላንቀውም ፈለኩ........
ጋሽ አይሀም አይቶኝ ስለነበር ስሜቴን እንድቆጣጠር ጠቀሰኝ እየሸስኩመ ቢሆን ራሴን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ጋሽ አይሀምን አቀፈውና በጀሮዉ የሆነ ነገር ተናገረው እና
......በቃ አባታችሁ ጋር ጡሩ ጊዜ አሳልፉ ብሎ ወጥቶ ሄደ ጋሽ አይሀምም እሱ እንደወጣ ብዙ ጊዜ ይመጣል እንዴ አላቸው!
.....አዎ አባቢ! አጎቴ ካርመላ በጣም ጡሩ ሰው ነው እናንተ እኮ የጓደኛዬ አደራዎች ናቹህ'ኮ እያለ በየ ጊዜው ያዝናናል፤ ይዞን ይወጣል አለችው ትንሿ ልጅ! ጎበዝ የኔ ጣፋጭ እናንተን ሲንከባከብልኝ ነበር ኣ! እየተባባሉ....እኔ ከዛው ቁሜ እያዳመጥኩ የቆየሁባት ጊዜ ኒሀል፤ ቩራል ቩራል! ብላ ስትጣራ ሰማሗት ወዳው ድምፇን ተከትዬ ወዳለችበት ሄድኩ....... ምን ነው ቆየህ አለችኝ? ያለሽበት ጠፍቶኝ ነው ብዬ ፈገግ አስባልኳት፤ ውስጥ አስገብታ ዉስጡን በደምብ አሳየችኝ ከዛም እሷ ወጥታ እንደሄደች፤

ለዘመናት በጠጠር አና በአፈር የቆሰለውን ወገቤን ላሳርፍ አልጋው ላይ ተንከባለልኩበት በህልሜ እንዳይሆን ፈርቼ ወደ ሻወር ቤቱ ገባሁና ስማቸውን በረሳሗቸው ሳሙና እና ሻምፖ በሞቆ ውሀ የሰዉነቴን እድፍ(ቆሻሻ) አላቀኩ ከዛም የተዘጋጀልኝን ፎጣ አሸርጬና ከላዬ ላይ ደርቤ ስለምቀይረው ልብስ እያሰብኩ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩኝ፥..በሀሳብ ተመስጬ ሌላ አለም ዉስጥ ሳለሁ የአዲሷ ክፍሌ በር ተቆረቆረች ሽርጤ ወልቆ እንዳያሳፍረኝ አጠባብቄ በሩን ከፈትኩ ጤና ይስጥልኝ አቶ ቩራል መግባት ይቻላል አለኝ ......የያዘውን የልብስ ብዛት ተመልክቼ አይኔ ፈዘዘ በሁኔታዬ ተገረሞ አቶ ቩራል.... ብሎ ሳይጨርስ ግባ ግባ ይቻላል አዎ! አልኩት!! ማን ብሎ ነበር ደግሞ የጠራኝ አቶ ቩራል ሆ ሆ....... ከአልጋዉ በፊለፊት አቅጣጫ ከተገተረው ቁም ሳጥን ቻል አትቻል እያለ ሁሉንም ከተታቸውና በፖርሳ የያዛቸውን ሽቶና ቅባቶች እዚህ ጋር ይደረጉ አለኝ፤...አዎ አድርጋቸዉ አልኩት እሱም ስራውን ጨረሰና እናመሰግናለን!! ብሎ ጥሎ ወጣ

እኔም በችኮላ በሩን ቆልፌ ቁም ሳጥኑን ከፈትኩት የትኛውን መርጬ እንደምለብስ ጨነቀኝ እናም ከደቂቃዎች በፊት የነበረውን አስታወስኩ አቤት!! የሰው ነገር ይገርማል ስናጣም ሀሳብ ስናገኝም ለመምረጥ ሀሳብ ከዚህ ሁሉ ብዬ ..የሞኝ! አመራረጥ መረጥኩ አይኔን ጨፈንኩና ከእጄ የገባውን ለበስኩ ሳላበዛ ሽቶ ነሰነስኩና ከመስታውቱ ፊት ለፊት ቁሜ በፈገግታ እያየሁ፤ ..ወንድሜ ቩራል ደስ በሚል የልጅነት ድምፅ ስትጣራ ሰማው ሮጥ ብዬ በሩን ከፈትኩት!! ወንድሜ ቩራል ምሳ ደርሷል ና! እየተባልክ ነው አለችኝ እሽ መጣሁ ...ግን ስምሽን አልነገርሽኝም እኮ አልኳት #ሲትና ነው ስሜ እያለች ተፍለቀለቀች እሽ እህቴ ሲትና አሁን መሄድ እንችላለን አልኳት፤....ኧረ ወንድሜ ቩራል ለትንሽ ልጅ እኮ እህቴ አይባልም ለትልቅ ሰው ነው እያለች እየተሳሳቅን ወደ ምሳው ሄድን እናቷም አየችንና ምን ተገኘ ሲቱ አለቻት

ኧረ ማሚ ያለውን በሰማሽ እያለች ወደሷ ሄደች....እኔም ወደ ቀረበዉ የምግብ ጠረንቤዛ አመራሁ፤ ጋሽ አይሀም ቁጭ ብሎ አገኘሁት ፈገግ ብሎ ዋዉ! ዋዉ! በጣም አምሮብሀል ከአይን ያውጣህ አለኝ ከትንሽ ቆይታም ቡሗላም ምግብ በአይነት ቀረበ መምረጥ እስኪያቅተኝ ድረስ ነበረ ከዛም ሁሉም ቤተሰብ ተሰባስበን መብላቱን ተያያዝንው፤.. በመሀል ጋሽ አይሀም ቩራል የኔ ልጅ ረስቼው ሳልሰጥህ ብሎ በትንሽ ካርቶን የተጠቀለለ ዕቃ ሰጠኝ እኔም ተቀብዬ ቁጭ ሳደርገዉ መክፈት ይቻላል አለኝ፤ እሽ ብዬ ከፈትኩት ስከፍተው...........

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
...አንድ ግዜ የሆነ ልጅ ነው። የሚበላ ዳቦ ፈልጎ በዙሪያው ካሉት ህፃናቶች ውስጥ ገለል ብሎ የገረጣውን ይጠራውና ዳቦውን ገዝቶለት እንዲመጣ ይልከዋል። ህፃኑም የተባለበት ቦታ በደስታ እንዲሁም በፍጥነት ደርሶ የታዘዘውን ዳቦ ገዝቶ ይመጣል።

...ቅድም ከጨዋታ የተገለለው እቤት ቁርስ ስላልበላና ስለራበው ነበር። ትድያ ይህ የላከኝ ግለሰብ አንድ ፍሬ ይሰጠኛል ብሎ በተስፋ አይን አይኑን እያየ ሲጠባበቅ የላከው ልጅ "አንተ...ሂድ እንጂ!! ከጓደኞችህ ጋር ተጫወት በሜለት በግልምጫ ያባረዋል። ህፃኑም እየራበውም ቢሆን ስለፈራ ደንግጦ ከአጠገቡ ዞር አለ።

.....ትንሽ ቆይቶ አንድ የዝህ የህፃኑ ላኪ ግለሰብ #ጓደኛ ይመጣል። ሰላም ከተባባሉም በኋላ የያዘውን ዳቦ አብረው እንዲበሉ ይጋብዘዋል። ጓደኛው አሁን በቅርብ ቁርስ እንደበላና ሆዱ በጣም እንደጠገበ ይነግረዋል። ሰውየው ግን በግድ ጓደኛውን ካልበላህ ብሎ በመለመን ከያዘው ዳቦ ግማሽ የሚሆነውን አካፍሎት አብረው ተመገቡ። የቅድሙ #ህፃን ድርጊቱን ተመልክቶ በጣም አዘነ። እሱ እየተራበ ሳይሰጠው ለጠገበና አልፈልግም ላለ በመሰጠቱ በጣም አስከፋው። ውሎውንም በትካዜ ተሞልቶ አሳለፈ።


... ከዚህ ታሪክ የምንማረው ሁላችንም ያሉንን ነገራቶች ለሚገባቸው አካላት በመለገስ ምንዳውን ከአላህ እንተሳሰብ። ብዙ ግዜ ሰርግ ይዘጋጃል፤ሰደቃም እንደዛው ነገር ግን እነዚህ ዝግጅቶች ላይ የሚጠሩት በረሃብ የተመቱ ደካሞች ሳይሆን ቤት የተረፋቸው ቦርጫምና የጠገቡ ሃብታሞች ናቸው። ይህ መሆን የለበትም። ህፃናትንም ቢሆን ልከን ለላክናቸው እንዲደሰቱ ሌላም ቀን በደስታ እሺ እንዲሉን ስሜታቸውን በመረዳት እናስደስታቸው።

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
👍2
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ስምንት(8)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

የኔ ልጅ ረስቼው ሳልሰጥህ ብሎ በትንሽ ካርቶን የተጠቀለለ ዕቃ ሰጠኝ እኔም ተቀብዬ ቁጭ ሳደርገዉ መክፈት ይቻላል አለኝ፤ እሽ ብዬ ከፈትኩት ስከፍተው...........
..........ስከፍተው በጣም የሚያምር የእጅ ሰአትና ስማርት ስልክ ከዛ በላይ ግን ከሰኣቱ ጎን መኪና ቁልፍ ተቀምጧል፤ ያኔ ደስታዬ ወደር አጣ የትልቅነት ስሜትም ይሰማኝ ጀመር..... ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ጋሽ አይሀምን አቅፌ ሳም ባደርገው ደስ ባለኝ ነበር ያን ማድረግ ባልችልም ግን ባለሁበት ቁጭ ብዬ ሀሴት በተሞላው ድምፅ ኧረ ጋሽ አይሀም ይሄ ሁሉ ከአቅሜ በላይ ነዉ ደግሞ መኪናው ብዬ ሳልጨርስ...... ጋሽ አይሀም ለመንጃ ፈቃዱ ከሆነ ስጋት አይግባህ ብዙ የማውቃቸው ሰዎች አሉ አናግራቸዋለሁ ልምምዱን እኔ አሰለጥንሀለሁ አታስብ አለ እኔም ለመናገረ ጉሮሮዬን ስጠራርግ
.........በመሀል ሲትና ወንድሜ ቩራል መኪና ስትይዝ መጀመሪያ እኔን ነዉ ኣ ከትምህርት ቤት የምታመጣው አይደል ብ ሁሁላችንንም አሳቀችን
..... እኔም ልናገር የነበረዉን በዛው ተውኩት ምሳችንን በልተን ከጨረስን ቡሗላ ቀኑ ቅዳሜ ስለነበር እኔ እዛው ጊቢ ውስጥ ሲትና ጋር ስጫዎት ዋልኩ ጋሽ አይሀም ደርሼ የምመጣበት አለኝ ብሎ ወቷል ኒሀል ከቤት ዉስጥ እናቷ ጋር ነው ስራ እያገዘቻት ነውየዋለችው፤

ሁሉም በየፊናዉ ወዲያ ወዲህ ሲል ፀሀይ ወደ ቤቷ ገብታ ጨለማ የሚባል ሁሉን ሰታሪ ሲመጣ ጋሽ አይሀምም ከዋለበት ውሎ ተመልሶ መጣና በጊዜ እራት በላን ከዛም ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን ጋሽ አይሀም ነገ ሁላችንም ምርጥ ቦታ ሽርሽር እንወጣለን እንድትዘጋጁ ብሎን ወደ ክፍሉ ሄደ፤ ሲትና ከጉልበቴ ላይ ቁጭ እንዳለች እንቅልፍ ይዟት ስለ ነበረ አልሰማችም ከዛም ብዙ አልቆየንም እኛም ወደ ምኝታችን ሄድን ከተኛሁ ቡሗላ ግን ካርመላ ጋሽ አይሀምን ምን እንዳለው አልጠየኩትም ለነገሩ ብቻችንን አልተገናኘንም ነገ እጠይቀዋለሁ ብዬ ተኛሁ ወደዛ ወደዚህ እያልኩ ስገላበጥ የረባ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነጋ፤ በሰመመን ውስጥ ሆኜ ክፍሌ ተንኳኳ አይኔን እየጠራረኩ ስከፍተው ሲትና ነበረች፤ ውይ ሲቱዬ ነይልኝ ብዬ አስገባሗትና ልብስ ቀያይሬ አብረን ተጣጠብንና ወደ ቁርስ ሄድን ከዛም.. ሲቱ! አልኳት አቤት ወንድሜ አለች ዛሬ እኮ ሰርፕራይዝ ተዘጋጅቶልናል አልኳት በደስታ እየተፍነከነከች ቁርስ በላንና ወደ ተዘጋጀው ቦታ ሄድን የሚገርም መዝናኛ ነበር የወሰደን...እኔ ግን ያን ያህል አላስደሰተኝም ምክንያቱም እነሱ ሲጫወቱ ቤተቦቼ ታወሱኝና ቁጭ ብዬ መቆዘም ጀመርኩ! ኒሀል!! ድንገት ስትዞር አየችኝና መጣች ከዛም ምን ሆንክ ቩራል ና! እንጂ እኛ ዘና በል አለችኝ
....አይ ይለፈኝ እዚህ ይሻለኛል አልኳት እንደዛ ከሆነ እኔም ላቀማምጥህ ብላ ቁጭ አለች በዛው ወሬ ጀመርን ስለራሷ ሁሉንም ባይባልም አወራችኝ የሁለተኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች እና የቀጣይ አመት ተመራቂ መሆኗን ጭምር ነገረችኝ ስለ እኔ ግን ምን ልንገራት ምንም የሚነገር ታሪክ ስለለኝ ዝም ብዬ አንገቴን ደፋሁ! ድንገት ጋሽ አይሀም መጥቶ ልጆች እዚህ ናቹህ እንዴ አለ!

....አዎ አባቢ ደብሮት ሳገኘው እያዋራሁተ ነዉ አለችው እንዴ ቩራል የምን ድብርተ ነው ና ተነስ እንደውም መኪና መንዳቱን ላለማምድህ አለኝ ኒሁ ደግሞ ወደነ ሲትራ ሂጂ አላት እሽ ብላ ሄደች እኔም ጋሽ አይሀም ጋር ወደ መኪናው ሄድን በነገራችን ላይ ኒሀል በጣም ቆንጆ ልጅ ናት ብትፈቀርም አያንሳትም ደስ የሚል ስብዕና አላት!! ሌላ አስቤ ግን አደለም።....መኪናው ውስጥ ገብተን ልምምድ ጀመርኩ ድሮ አባቴ ያስነዳኝ ስለ ነበር አዲስ አልሆነብኝም በመሀል አንድ ነገር ትዝ አለኝና ካርመላ በጆሮው ምን እንዳለው ጠየኩት...."" ያው የጠበኩት ነገር ነው 'ባትመጣ ይሻልህ ነበር' ነዉ ያለው እና ደግሞ ቩራል ያው በእቅዳችን መሰረት ነገ ወደ ድርጅቱ እንሄዳለን በዛውም ሰራተኛቹን ትተዋወቃለህ አለኝ"" ጋሽ አይሀም እኔም እሽታዬን ነግሬ ሲያለማምደኝ፤እነ ሲትናም ሲጫወቱ ውለን ወደ ቤት ተመለስን ሁላችንም ስለደከመን ወደ አልጋችን ሮጥን ሰውነቴ ዝሎ ስለነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ነበር የያዘኝ ፤

....አይነጋ የለምና ነጋ! የወፎቹ ዝማሬ ግን ቅር ቅር አለኝ፤ አሁን ይጮሀሉ! እያልኩ ብጠብቅም የለም!!.... ምን ይደርጋል ብዬ ለመጀመሪያ የስራ ቀኔ ዝግጅቴን ጀመርኩ የለለ ሽክ አልኩኝ ከዛም ቁርስ በላንና ተሰነባብተን ጋሽ አይሀም ጋር ወደ ድርጅቱ ሄድን ከዛም እንደደረስን ጥበቃዎቹ መጥተው የሚኪናውን በር ከፍተው እንኳን ደህና መጣቹህ አቶ አይሀም ብለው ቁልፉን ተቀብለው ወደ ፖርኪንጉ ወሰዱት፤ በጣም ትልቅ ድርጅት እነደሆነ ከህንፃዉ መረዳት ይቻላል!! ከዛም ተያይዘን ወደ ውስጥ እንደገባንም ሰራተኛው በሙሉ ተሰብስቦ እየጠበቀን ነበር ከዛም ጋሽ አይሀም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ቆሞ ሰላምታ ከሰጠ ቡሗላ መክፈቻ ቢጤ ንግግር አደረጎ ዛሬ አዲሱን የድርጅታችንን.....

ይቀጥላል
━─━────༺༻────━─━
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─
👍1
አስደናቂው #ለማኝ እና የባለታሪኩ ገጠመኝ

በመንገድ ላይ በመጓዝ ላይ ሳለ፣ አንድ ምስኪን ለማኝ የሚሰራው ድርጊት ላይ አይኑ አረፈ። ትኩረቱን ሰጥቶ መከታተሉን ቀጠለ። ለማኙ እንዲህ ነበር የሚያደርገው.... መጥቶ ሰደቃ የሚሰጠው ሰው ጋር ረዘም ያለ ንግግር ያደርጋል። ሁሉም ሰው ሰደቃ ሊሰጠው በመጣ ቁጥር፣ እንደ ሌሎቹ ሳይሆን ረዘም ያለ ጊዜን ያናግራል። እሩቅ ላይ ስለነበሩ የሚሉትን ነገር ለመስማት አልቻለም። በመሆኑም ጠጋ ብሎ ሰደቃ በመስጠት የሚናገረውን ነገር ለማዳመጥ ወሰነ።

ኪሱ ውስጥ የነበረው 50ብር ብቻ ነበር። ታድያ 10ብር ሰጥቼ በዛውም 40ብቅ እስኪመልስልኝ ሰፊ ግዜን ወስጄ አዳምጣለሁ በማለት፤ ሄዶ ያሰበውን አደረገ። 50ብር ሰጠውና 40ብር መልስልኝ አለው። ለማኙም እንዲህ አለው........ "ያንተ ብር የሚሆነው ይህ ወደ ኪስህ የመለስከው 40ብር ሳይሆን ለእኔ የሰጠኀኝ 10ብር ነው። ምክንያቱም ይህንን 40ብር የምታውለው ምናልባት ለዱንያዊ ጥቅም ይሆናል። ጥቅሙም እዚሁ ዱንያ ላይ ይቀራል። ነገር ግን ለእኔ የሰጠኀኝ ብር ወደ አኼራ ካዝናህ ተዘዋውሯል "....

ንግግሩ ውስጤን ስለነካው በቃ እሺ መልስ አልፈልግም አልኩት። "አይይይ እኔ አንተ ብር እንድትሰጠኝ ብዬ አይደለም ይህንን የነገርኩህ። ቀሪውን 40ብር ለኔ ሳይሆን ሌላ እኔን ለመሰለ አልያም ከእኔ ለባሰ ምስኪን ለግሰው" ሲል በድጋሚ ልቤን የሚነካ ንግግር ተናገረ። ያለኝን ለመፈፀም ልጓዝ ዞር ስል እንደገና ወደ ኋላ ጠራኝ። እኔም አቤት ብዬ በደስታ ተመለስኩ። እንዲህ አለኝ "ሌላ ንግግር ጀምረን ዋናውን ጉዳይ ረሳሁት። የብርህ ምንጭ ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ። እኔም ሃላል እንደሆነ በደንብ አስረዳሁት። እሱም"እንደዛ ከሆነ ማሻ አላህ!! ብርህ ምንጩ ሃራም ቢሆን ኖሮ አልቀበልህም ነበር። ወላሂ የሚመለከተኝ አላህ ምስክሬ ነው። ከማንም ሰው የብሩን ሃላል መሆን ሳላረጋግጥ ተቀብዬ አላውቅም። ሃራም ከሆነ የሰጠኝ የብር መጠን የፈለገ ቢበዛ መልስልምታለሁ" እንዲህ እያወራን የዝሁር አዛን ወጣ። እሱም አንስቼው ዊልቸሩ ላይ እንዳስቀምጠው ነገረኝ። የዙሁር ሰዓት ብዙ ሰው ከስራ ስለሚወጣ ለልመና አመቺ ሰዓት ነው። ነገር ግን እሱ ሰላቱን በማስቀደም ለአላህ እጁን ሰጠ። ወደ መስጅድ እየገፋሁኝ ወሰድኩት። እናንተ እግር፣ እጅ፣አይን እያላችሁ ሰላተል ጀመዓ የሚያመልጣችሁ ወንዶች ከዚህ ሰውዬ የት አላችሁ!!? አንቺም ሙሰልሰል እየተመለከትሽ ሰላት የሚያልፍሽ፣ቻት ላይ ተጥደሽ ወቅቱን የምታሳልፊ እህቴ ወንድሜ ከዚህ ለማኝ አንፃር አላህ ምን ይለን ይሆን!!?

ከዓመታት በኋላ ይህንን ሰው ከቦታው ላይ አጣሁት። በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን ስለ እሱ እንዲነግሩኝ ጠየኳቸሁ። እነሱም እርሱ ልመናውን ትቶ። ከውጭ ሀገር በመጡ #በጎ_ፍቃደኞች እግሩን ታክሞ ድኖ፣ልመና ከመተዉም አልፎ ውጭ ሀገር ሄዶ ባካበተው ሃብት አማካኝነት ትልቅ ደካሞችንና ህፃናትን የሚረዳ ተቋም ማቋቋሙን ነገሩኝ። እኔም በአላህ ስራ ተደንቄ ከዚያን ቀን ጀምሮ በቀን ሰደቃ ሳልሰጥ ውዬ አላውቅም።


ሁላችንም ዛሬ፣አልያም ይህን ሳምንተ በየቀኑ ከ5ብር በማንሳት እስከ 1ብር ሰደቃ በመስጠት ለሰባት ተከታታይ ቀናት ታላቅ አጅርን እናግኝ!!

"#ውሃ እሳትን እንደምታበርደው ሁሉ #ሰደቃ የአላህን ቁጣ ታበርዳለች" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አላህ በብዙ ነገር ሊቆጣብን ይችላል። ይህን ሃያል የጌቴችን ቁጣ ሰደቃ በመስጠት እናብርደው።

ይህንን ፅሁፍ #ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!

━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
ምርጥ አስተማሪ ታሪክ እነሆ!!

በአንድ ወቅት አንድ ቀልጣፋ እንጨት ቆራጭ በአንድ የስራ መስክ በጥሩ ደሞዝ ተቀጠረ።ስለዚህም እንጨት ቆራጩ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ እና ጥሩ ስራ ለመስራት ይወስናል።

በመጀመሪያው ቀን ሃላፊው መፍለጫ ሰጠውና የሚሰራበትን ቦታ አሳየው። መቁረጥ የሚችላቸው ዛፎች እነዚህ እንደሆኑ አስረድቶት ሄደ።በርግጥም እንጨት ቆራጩ በመጀመሪያው ቀን 15 ዛፎችን ቆርጦ ማስተካከል ቻለ።

በሁለተኛው ቀን የበለጠ ለመስራት ወስኖ ቢሞክርም ከ10ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም ነበር።

በሶስተኛው ቀን ከሁለቱ ቀናት የበለጠ ቢተጋም ከ7 ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም።

ቀናቶች ባለፋ ቁርጥ የሚቆርጣቸው ዛፎች መጠን እያነስ እያነስ መሄድ ጀመረ። በስተመጨረሻም አንዲትን ዛፍ መቁረጥ ከበደው። ሞከረ ሞከረ ሊሳካለት አልቻለም።

ይሄኔ ሃይሉን እንዳጣ ተሰማው። ጉልበቴም ከዳኝ ብሎ በማሰብ ላይ ሳለ የሆነ ሌላ ሰው ሲያልፍ ይህንን ሰው አንዲትን ዛፍ ያለጥቅም ሲደበድብ ይመለከተዋል።

"ሰውየው ወደ እንጨት ቆራጩ ጠጋ አለና አንድ ምክር ልምከርህ ትፈቅድልኛለህ?" አለው።

እንጨት ቆራጩም "አሁን ስራ ላይ ስለሆንኩ ምንም መስማት አልፈልግም" ይለዋል።

ሰውየውም እንዲህ አለው" እየፈለጥክበት ያለከው ፋስ(መፍለጫ) ስለት የለውም ዶምድሟል። ከጥቅም ውጭም ሆኗል። ይህን አውቀህ እረፍት በማድረግ የምትሰራበትን #ፋስ ልታስለው ይገባል" አለው።

ይሄኔ ይህ እንጨት ቆራጭ ቆም ብሎ አሰበ። እንዲህም አለ"እውነትም ፋሴን አሞረድኩትም። ዛፎችን በመቁረጥ ቢዚ ስለነበርኩ" ብሎ ፋሱን በእርጋታ ሞረደና ከድሮ በተሻለ መልኩ ስራውን በአግባቡ ማከናወን ቀጠለ።

በህይወትህ ውስጥ መለወጥ ያለብህን ነገቅ ለመለወጥ ግዜ አትስጥ። ሁሉንም ነገር በጊዜ ለማከናወን ሞክር።

••••#Share ••••
━─━────༺༻────━─━
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
━─━────༺༻────━─━
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM