ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
ብዙ ነገር አድርገሽ ሊሆን ይችላል ግን ሁሉንም ያደረግሽው ለክፋ ነገር ነው ደግሞ ሰሚራን ብትገድያት ምንም የምታገኝው ነገር የለም እንደውም በተቃራኒው የህሊናሽ ወቀሳ ነው የምታተርፊው መቼም ሰላም አታገኝም አላህ አንድን ነገር ሲያደርግ ያለ ምክንያት አያደርግም ምን አልባት እናትሽ በሂወት ብትኖር ኖሮ ዛሬ እዚህ መግባት አትቺይም ነበር ለምን ልትይኚ
ይሆናል አንቺ አሁን እንደዚ ትምህርትሽ ላይ ጠንክረሽ የምትማሪው አንደኛው ምክንያት ሰሚራን ለመጉዳት ነው ግን አንቺ ለክፋት አስበሽ ቢሆንም የተማርሽው ግን አንቺን ነው የሚጠቅመው እናትሽ ብትኖር ግን እንደ አሁኑ ወጤታማ ላትሆኝ ይችል ነበር እያለ ብዙ ከመከራት በኃላ ውሳኔው የ አንቺ ነው እሺ አስብበታለሁ ስለምክርህ እና አብረኃኝ ስለሆነክ አመሰግናለሁ ብላው ሄደች ቀኑ ሀሙስ ነበር አርብ ቀን ነው ሀሊማ ወደ ቤቷ የምትሄደው ቀኑን እንዲሁ ሁሉም ሲጨነቁ ሲያስቡ አለፈ አርብ ጠዋት ሀሊማ ከድር ጋር ደውላ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
... ባባ ዛሬ ብቻዬን አይደለም የምመጣው ላሳውቅህ ብዪ ነው ከድርም እሺ ብሎ ስልኩን ዘግቶ ሰሚራ ጋር ደውሎ ነገራት ሀሊማ ለሳሊም ደውላለት አብሯት እንዲሄድ ለምናው እሺ አላት ከጁምአ በኃላ እንገናኝ ብላ ስልኩን ዘጋችው ሀሊማ በጣም ፈርታለች ጁምአ ሰግዳ ከሳሊም ጋር ተደዋውለው ወደ ሀሊማ ቤት ሄዱ ሲደርሱ አንኳኩ ሰሚራ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ጋበዘቻቸው ሁለቱም ወደ ሳሎን ቤት ገቡ ሀሊማ እቤት ስትደርስ ለ ከድር ደውላ እቤት እንዲመጣ እና ሰው ልታስተዋውቀው እንደሆነ ነግራው ስልኩ ተዘጋ ብዙም ሳይቆይ ከድር እቤት ደረሰ ምግብ ቀርቦ ሁሉም አብረው ተመገብ ሰሚራ እና ሀሊማ እቃዎቹን አነሳስተው መጨዋወት ጀመሩ ትንሽ አንደተጨዋወቱ ሀሊማ አንዴ በቅድሚያ እንግዳዬን ለስተዋውቃቹ ሳሊም ይባላል ልክ እንደ ሴት ጓደኛዬ ነው እና ለምን ይዤው እንደመጣሁ በኃላ አነግራችኃለሁ ዛሬ የማውቀውን ልነግራቹ እና አፋ እንድንባባል ነው አለች ሰሚራ እና ከድር ግራ ገብቷቸው ሀሊማ የምትለውን ነገረ ማዳመጥ ጀመሩ ሀሊማ ያየችውን የሰማችውን ነገር አንድ በአንድ ነገረቻቸው ሰሚራ የምትገባበት አጣች ከድርም በጣም ደንግጦ ባለበት ደርቆ ቀረ እስከዛሬ አታውቀውም ብለው የሚያስቡትን ነገር እያወቀች ዝም ማለቷ ከድርን አሸመቀቀው ሳሊም በተራው መናገር ጀመረ ያለፈውን ረስታቹ ይቅር ተባብለቹ በሰላም ኑሩ ብሎ ዝም አለ ሁሉም ዝም አሉ ሰሚራ ለሀሊማ አፉ በይኝ ይሄን ሁሉ ነገር እያወቅሽ አብረሽኝ እንዴት ኖርሽ ከበደልም በላይ በድዬሻለሁ አፉ በይኝ ከድርም አፉ በይኝ ብሎ በፀፀት ጠየቃት ሀሊማ ሁለታችሁንም አፋ ብያቸዋለሁ ሁሉም ተቃቅፈው አለቀሱ ሳሊምን ይዤው የመጣሁት እንድታመሰግኑልኝ ነው እንደዚህ የመሆኑ ምክንያት እሱ ነው ብላ ተናገረች ....... ቀኑ በደስታ አሳለፋት ሊመሽ አካባቢ ሳሊም ወደ ቤቱ ሄደ በነጋታው በዘይነባ ስም ሰደቃ አድርገው ለሚስኪኖች አከፋፈሉ........
ከ 15 ቀናት በኃላ ከድር እና ሰሚራ አነስ ባለ ዝግጅት ኒካ አሰሩ ሳሊም እና ሀሊማም ከድር እና ሰሚራ ኒካ ባሰሩ በሳምንቱ አነሱ ኒካ አሰሩ ሁለቱም ከተመረቁ በኃላ ተጋብተው አብረው መኖር ጀመሩ ፡፡ እነሱ ሲጀምሩ እኔ እዚህ ላያ ጨረስኩ፡፡


ተፈፀመ

ሌላ ምርጥ ታሪክ ከ300👍 ቡሀላ እንጀምራለን።
ለማንኛውም አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
🙋‍♂እንዴት ናቹሁልኝ ውድ ተከታዮቼ!🙋
በአስደናቂ ፁሁፎቿ የምናውቃት ነኢማ ኸድር😘 አስደማሚ አስተማሪ እና አስለቃሽ ታሪክ ሂጃቤ💓በሚል ርዕስ ልታቀርብልን እንደሆነናዝግጅቷን እየጨረሰች እንደሆነ አሳውቃለች እንደተመለስኩም መልዕክት አድርሰልኝ ብላለች ነው

እስከዛ ግን በኔ 🕺የተደረሰው እና የተፃፈውና መኖርን ባልታሰበ🚶የሚለውን ታሪክ ነገ ጀምሮ ላስነብባቹሁ ወድጃለው!💁‍♂
እናንተም እየተከታተላቹሁን እንደሆነና ቻናሉን እንደምትወዱት እስኪ በ👍 አሳዩንመልካም ንባብ ይሁንላቹ
አንድ ጊዜ ይባላል... የሆነች አይጥ የድመት ጓደኛ ነበራት። ድመቷና አይጧ በጣም ይዋደዳሉ። ሁለቱም ቤተሰብ ያላቸው ሲሆን ተጠልለው የሚኖሩት በአንድ ቤት ውስጥ ነበር። እናትና አባቶቻቸው ሁለቱ ባላንጣዎች ጓደኛ መሆናቸውን አያውቁም። ትንሿ ድመት በበኩሏ #አይጥ ለድመቶች ጣፋጭና ልዩ ምግብ መሆኗን የማታውቅ ሲሆን አይጧም #ድመት አስፈሪ እና ዋና የአይጥ ጠላት መሆኗን አታውቅም

በእንዲህ ጓደኝነታቸው ብዙ ግዜን ይቆያሉ። ከእለት ወደ እለትም ፍቅራቸው እየጨመረ ሄደ።

ከእለታት አንድ ቀን የድመት #እናት ትንሿ ድመት ከውሎ ስትመለስ "የት ውለሽ ነው የመጣሽው?" ስትል ጠየቀቻት። ትንሿ ድመትም "እኔማ ከውዷ ጓደኛዬ አይጥ ጋር ተጫውቼ እየመጣሁ ነው" ብላ ለእናቷ መለሰች። እናትም በቁጭትና በእልህ መንፈስ ...."አይጥ ማለት እኮ የእኛ ጣፋጭ ምግብ ናት። እሷ ጓደኛ ሳትሆን የምትበላ ምግብ ናት። ከዚህ በኋላ ካገኘሻት ቀስ ብለሽ ተመገቢያት" በማለት ልጇ ን አስጠነቀቀች።

አይጧም ከውሎዋ ወደ #እናቷ ጋር ስትመለስ ትንሿ ድመት የተነገራትን ንግግር የመሰለ ለአይጧ ነገረቻት። እንዲህ አለቻት.."ድመት ማለት የእኛ ጠላት፣አስፈሪ አውሬ ናት። እሷ እኛን ለመመገብ የተፈጠረች ፍጡር በመሆኗ ከዚህ በኋላ እንዳትቀርቢያት። በስህተት ብትቀርቢያት እንኳ በፍጥነት ከአጠገቧ አምልጪ"... በማለት ለትንሿ አይጥ መከረቻት።

እንደተለመደው ትንሿ ድመት ወደሚጫወቱበት ቦታ ሃዳ አይጧን ብትጠብቃት ልትመጣ አልቻለችም። ድመት ብዙ ጠበቀች አይጧ ግን አልመጣችም። በስተመጨረሻ ትንሿ ድመት "እናቴ የነገረችኝ እውነት ነው። ይቺን ሚጢጢ አይጥ ሳልበላ መመለስ የለብኝም በማለት ወደ አይጧ ቤት ትጓዛለች። የአይጧ ባት አቅራቢያ በመቆምም ጮክ ብላ አይጧን ጠራቻት።

አይጧም" አባት ድመት ለምን ፈልገሽኝ ነው?" በማለት በትዝብት መልክ ጠየቀቻት። ድመቷም "ነይ ጠጋ በይና የድሮ ጫወታችንን እንጫወት" ትላታለች። አይጧም ... "እኔም አራዳ አንቺም አራዳ፣ እናትሽ ላንቺ የነገረችሽን የኔም እናት ለእኔ ነግራኛለች" በማለት መለሰቻት። ከዚህ በኃሏም ሁለቱ እንስሳ ሲገናኙ፣ ድመት ስታሯርጥ አይጥ ደግሞ በመሸሽ ታመልጣለች።

#አስተምህሮ...
ወላጆች ልጆቻችን የት እንደሚውሉ ልናውቅ ይገባል። የአይጧ እናት ደርሳ ለልጇ ባትመክር ኖሮ ፣እናት ልጇን ታጣ ነበር። እኛም ልጆቻችን የትና ከማን ጋር እንደሚውሉ በማወቅ ከአልባሌ እና ብልሹ ስነ ምግባር ልንጠብቃቸው ይገባል።

"ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ። ከምትጠብቁትም ትጠየቃላችሁ። ሰውየው በቤቱ ውስጥ ጠባቂ ነው። ከሚጠብቀውም ነገር ይጠየቃል..." #ረሱል ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም

JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
አህመድ እና መርየም የሚባሉ ባል እና ሚስት ነበሩ። በጣም ደስ የሚል ቤትና ሁለት የሚወደዱ ልጆችም አሏቸው፤ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት።

ከዕለታት አንድ ቀን አህመድ ለስራ ጉዳይ ወደ ሌላ ከተማ እንዲሄድ በአለቆቹ ይነገረዋል። ለበርካታ ቀናት ሊቆይ እንየሚችልም ይገለፅለታል።

ሚስቱ መርየም ይህንን ስትሰማ እሷም ከከተማ ወጣ ብሎ ትንሽ የመቆየት ፍላጎት ስላደረባት አብረው ለመሄድ ጥያቄ ታቀርብለታለች። እርሱም በደስታ እሺታውን ይገልፅላትና ለጉዜ ላይ ዝግጅት ይጀምራሉ። ከሁሉም በፊት ግን #ሁለቱ ልጆቻቸውን በቅርበት የምትጠብቅላቸው አንዲት ታማኝ ሴትን ይቀጥራሉ።

ባልና ሚስቱ ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ተባለው ከተማ ይሄዳሉ.......

......አህመድና መርየም መመለስ ከሚገባቸው ቀን ዘግይተው ነበር ወደ ቤት የተመለሱት። መኖሪያ ከተማቸው ሲደርሱ ሁለቱም ደስ አላቸው። ነገር ግን ከሚኖሩበት ሰፈር አካባቢ አቅጣጫ ጭስ መሰል ነገር ሲመለከቱ ምን እንደሆነ ለማጣራት በቀጥታ ወደ ቦታው ያመራሉ። አንድ ቤት ተቃጥሎ በእሳት እየነደደ ነበር። #መርየምም "የሚገርም ነው! የእኛ ቤት አይደለም። ወደ ቤታችን ሄደን ልጆቻንን እንይ" ትላለች።

አህመድ ግን መኪናውን እየነዳ ወደ ተቃጠለው ቤት ቀርቦ ተመለከተ። በጣም በማዘንም "የማን ቤት እንደሆነ አወቅሽ? እዚያ ትልቁ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰራው የጀማል ቤት እኮ ነው። እስካሁን ከስራ የተመለሰ አይመስለኝም። አንድ ልናደርገው የምንችለው ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ" በማለት ተናገረ።

ሚስቱ መርየም ግን ተቃወመችው "እኛን የሚያገባን ምንም ነገር የለም። ይህ የለበስከው በጣም የሚያምርና ውድ ልብስህ ከጥቅም ውጭ ነው የሚሆነው" በማለት ወደ ባት እንዲሄዱ ገፋፋችው።

አህመድ ለመርየም ንግግር ምላሽ ሳይሰጥ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ሚቀጣጠለው ቤት ደረጃ አጠገብ አቆማት። ቤቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዟል። አንዲት ሴት ከቤቱ ውስጥ የስቃይ ድምፅ ታሰማለች። "ልጆቹ! ልጆቹ!!" በማለትም ታለቅሳለች። ባልና ሚስቱ ከሚገባው በላይ ደነገጡ።

አህመድ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ የወደቀችውን ሴት ትከሻ ክንድ በመያዝ ካነሳት በኋላ ልጆቹ የት እንደሆኑ ጠየቃት። ሴትየዋም ልጆቹ ምድር ቤት ውስጥ መሆናቸውን እያቃሰተች ተናገረች።

አህመድ እየተጣደፈ አጠገቡ ያገኘውን ባልዲ ሙሉ ውሃ በለበሰው ልብስ ላይ በማፍሰስና በውሃ የተነከረ ፎጣ አናቱ ላይ በማሰር ወደ ምድር ቤቱ ይገባል። ምድር ቤቱ በጭስ ታፍኗል። ሙቀቱ ሰው አያስቀርብም። እንደምንም ብሎ ልጆቹን በትከሻው ተሸክሞ ሲወጣ ሌላ የህፃናት የጭንቀት ድምፅ ይሰማዋል። በትከሻው የተሸከማቸውን በፍርሃት የሚንቀጠቀጡ ልጆች ይዞ ከወጣ በኋላ ቤቱ ውስጥ ሌሎች ህፃናትም እንዳሉ ይነገረዋል። ምን ያህል እንደሆኑ ሲጠይቅ ሁለት መሆናቸው ይገለፅለታል።

በድጋሚ ተመልሶ ሊገባ ሲንቀሳቀስ ሚስቱ እጁን ይዛ ልትከለክለው ትሞክራለች። "መሞት ትፈልጋለህ እንዴ!? ተመልሰህ እንዳትገባ!" በማለት ስትናገር አህመድ የያዘችውን እጇን መንጭቆ እሳቱ ወደሚነድበት ቤት ሮጦ ይገባል። በጭስ ታፍነው ለመሞት የተቃረቡ የሚመስሉ ሁለት ህፃናትን ያገኛል። ወዲያውኑ በጎንና ጎኑ አንገቱን በደንብ እንዲይዙ አድርጓቸው ከቤቱ በመውጣት ላይ እያለ አንዳች የሚያውቀው የሚመስለው ነገር ሰውነቱን ይወረዋል። ጎንና ጎኑን አንገቱን በሁለት እጆቻቸው ጨምድደው የያዙት ልጆች የሚያውቃቸው መሰለው። እየሮጠ ከሚቃጠለው ቤት እንደወጣ የተመለከተው ነገር የማይታመን ሆነበት። ሳያስበው ጉንጩ በእንባ ተሞላ። ሁለቱ ህፃናት የራሱ ልጆች ነበሩ። እንድትጠብቃቸው የተቀጠረችው ሴት ገበያ ስትሄድ በአደራ ጎረቤት አስቀምጣቸው ነበር።

#እስተምህሮት....

ሁሌም ጥሩ እንሁን፤ አላህ ለእኛ በጎን ነገር ይወፍቀናል። አዛኝ እንሁን፤ አላህ ያዝንልናል። ለራሳችን የምንወደውን ለወንድማችን እንውደድ፤ ለራሳችን የምንጠላውንም ለወንድማችን እንጥላ።

JOIN ⇒
https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1👍1
☺️ አእምሮአችን የመረጠውን
በፍላጎታችን ልንቀይረው እንችላለን‥
ነገር ግን ልብ የመረጠውን ውሳኔያችን
የቱንም ያህል ቢሆንም ልንቀይረው አንችልም

Te» @ketibeb
እውነተኛ አፈ ታሪክ ነው

በድሮ ጊዜ አንድ አግኝቶ ያጣ ባለፀጋ ሰውዬ በአገሪቱ አሉ የተባሉ ባለሀብት ሰው ጋር ይሄድና

"ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡

ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከዶሮ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳዋ" አለ፡፡

ባለጠጋውም "እውነትም አግኝተክ ያጣክ ነህ፤ በሉ ከእህሉ ስፈሩለት፤ ከከብቶቹም የሚበቃውን ያህል ስጡት ብሎ አሰናበተው፡፡

ይህ ሰው ወደ ቀየው ሲመለስ አንድ ወዳጁ ይሄን ሁላ ሀብት ከየት እንዳገኘ ይጠይቀዋል፡፡ ተመፅዋቹም ሁሉን ነገር ነገረው፡፡ ከዛ ባልንጀራው እንደሱ ሀብት ለመቀበል ወደ ባለጠጋው ሰው ሄደ፡፡

እዛም እንደደረሰ "ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡


ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከበሬ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳው" አለ፡፡

ባለጠጋውም አንተ አጭበርባሪ ነክ ብሎ በባዶ ሰደደው፡፡

የፈለገ ብንቸገር መዋሸት ግን አይሆኑ ውድቀት ላይ ይጥለናል፡፡

JOIN ⇒
https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍21
የኮሮና ቫይረስን እጅን በመሳም አጠፋለዉ ያለዉ ህንዳዊዉ የሀይማኖት መሪ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ

በፓርዲያሽ ግዛት ራትላም በተባለች አዉራጃ ነዋሪ የሆነዉ የመንፈሳዊ መሪ አስላም ባባ ለተከታዮቹ በተለይም ለሴቶች እጆቻቸዉን በመሳም ብቻ የኮሮና ቫይረስን እንደሚፈዉስ
ይናገራል፡፡

ይህንን የሰሙ 40 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ላለመያዝ በሚል እጃቸዉ እንዲሳምላቸዉ ወደ ስፍረዉ ያቀናሉ፡፡

እጃቸዉ በባባ አስላም ከተሳመላቸዉ 40 ሰዎች መካከል 20 ያህሉ በቫይረሱ መያዛቸዉሲረጋገጥ ሰባቱ የመንፈሳዊዉ መሪ አስላም ባባ ቤተሰቦች መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡

የቫይረሱ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በቅርበት ሲያገኝ የነበረው ባባ አስላም እርሱ በቫይረሱ ይያዛል፡፡ህክምና ቢያገኝም ማገገም ሳይችል ህይወቱ ማለፉን የህንድ ሚንስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

ልክ እንደ አስላም ሁሉ ከወራቶች በፊት የጤናናይጄሪያዊዉ ፓስተር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ቻይና ሄጆ አጠፋዋለሁ በማለት ወደ ቻይና በመጓዝ ቫይረሱን አጠፋዋለሁ ቢልም በቫይረሱ ህይወቱ አልፎ ስርዓቱ ቀብሩ በቻይና ተፈጽሟል፡፡



⊰━━━━━━⊱🌸⊰━━━━━━⊰
Share | @ketibeb
⊰━━━━━━⊱🌸⊰━━━━━━⊱
👍3
የ ኑራ ልጅ ኒዐም
ውድ አንባቢያን የዚህchannel አላማ በምንፅፍቸው ግጥሞች እና ልቦለዶች በገሀድ የምናየውን ሁኔታ በጥበበባዊ መንገድ ለህብረተሠብ ማድረስ ነው
https://telegram.me/yanuralij
#ይህ #ቻይናዊ ገበሬ ከአመታት በፊት ባጋጠመው የኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ሁለት እጁን አጥቷል ።
↘️ነገርግን ህይወትን ለማሸነፍ ነገሮችን ሁሉ በእግሩ በመከወን እራሱን ከመቻሉም በላይ በቁጥር በዛ ያሉ ከብቶችንም ማፍራት ችሏል።
↘️እና የዚህ ታታሪ ሰው እናት ሁለመናቸውን ማንቀሳቀስ በማይችሉበት ደረጃ ይታመማሉ በዚህ ጊዜ ይህ ሰው እናቱን ለማስታመም እንደ እጅ በሚያገለግለው በእግሮቹ የሰራውን ምግብ ማንኪያ በአፉ ይዞ ለእናቱ ያጎርሳል።
💐💐እናትየው በቃኝ ብለው ጭንቅላታቸውን እስከሚነቀንቁ ድረስ በየእለቱ ማንኪያ ጎርሶ እናቱን ያጎርሳል ፣ #ሰው #ያለውን ነውና የሚሰጠው ለዚህ ተግባሩ long live to both of dem.

Join

@ketibeb
👍1
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጌታችን #ሆይ!!!

🍃ኖረን ኖረን መሞት አይቀርምና ዋጋቢስ ሆኖ ከመኖር ዋጋቢስ ሆኖ እንደተራ ሰው
ከመሞትም ጠብቀን!!

🍃ነበረ ሞተ ሳይሆን፣ ዛሬም ነገም ዘላቂ ስራ የሚኖረን ከሞትን በዃላ አጅራችን
የማይቋረጥ አድርግልን!!!
አሚን!!
JOIN @Ketibeb
══ •⊰✿💚✿⊱• ══
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል አንድ
በከድር አወል
በ( @KETIBEB) የተዘጋጀ

.... ከወትሮ ለየት ያለ የወፎች ዝማሬ አይሉት ጫጫታ እንቅልፌ መተኛ አሳጡኝ ይባስ ብለው ድምፃቸው እኔ ወደተኛሁበት እየቀረበ መጣ ይሄ ደግሞ የሆነ ባዕድ ነገረ እየመጣ መሆኑን ያስረዳል ወዲያውኑ ደመነፍሴን በፍጥነት የተንተራስኩትን ታጣፊ ክላሼን አቀባብዬ ፊቴን በእጄ እየጠራረኩ በቅጠል ከታጀበ ዋርካ ዛፍ ወደ ጫፍ ተንጠላጥዬ ቁጭ አልኩ እና፥ አካባቢውን በአይኔ ማሰስ ጀመርኩ፤ በአንደኛው የጫካው አቅጣጫ ከሩቅ በፀሀይ መውጣት የደነገጠ በሚመስለው ጉም መሀል፥
በከዘራው መንገዱን የሚያሰናክሉትን የጫካውን ሀረገ እየከፈተ እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ የሚመጣ ሰው ይታየኛል፧ እንደ መደናገጥ እያልኩ ምን አልባት እኔን ለማጥቃት የተላከ ሰው ይሆናል ብዬ ካለሁበት እስኪደርስ በተጠንቀቅ መጠበቅ ጀመርኩ ፡

በተንጠላጠልኩበት ዋርካ ሲደርስም ከስሩ ከሚፈሰው ምንጭ ውሃ ጎምበስ ብሎ በእጁ እየጠለፈ የሚበቃውን ያህል ከጠጣ ቡሀላ፤ በረዥሙ ተነፈሰ ከዛም በአይኑ አካባቢውን ከቃኘ ቡሀላ ጠፍጣፍ ዲንጋይ ላይ አረፍ አለ ጉዞውን መቀጠል የሚፈልግ አይመስልም፤ እኔ ቀስ ብዬ ኮሽታ ሳላሰማ ከዛፉ ወረድኩ እና በቅንጭላቱ ትክክል አነጣጥሬ ኮስተር ባለ ድምፅ ጮክ ብዬ እንዳትንቀሳቀስ አልኩት፤ ቢንቀሳቀስ ግን ምን ላደርገው ነው ልተኩስበት ኧረ..ምንነቱን ሳላጣራ እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ፤ሰውዬው ግን ምንም የመደናገጥ አይነት ስሜት አይታይበትም ይባስ ብሎ እንደ ሬሳ ደርቆ ዝም አለ፤ እኔም ደግሜ ማን ነው የላከህ ! ብልም እንኳን ሊናገር ዞሮም አላየኝ ፥ ግራ በታገባ ስሜት ምን አልባት ጆሮው አይሰማ ከሆነ ብዬ ከወደ ፊት ለፊቱ ሄድኩና ግምባሩ ላይ ደቀንኩበት፤ የዛኔ አንገቱን ቀና አደረገና ""ምን ፈለክ ልትገለኝ ነው፥ አትፍራ ተኩስብኝ እንደውም ከዚህ ከማይረባ አለም ገላግለኝ አለ፧ ቁጭት በተሞላበት ድምፅ፤ ይሄኔ ተስፍ መቁረጥን አቃታለሁና በትንሹም ቢሆን አሳዘነኝ :ምን ሆኖ ይሆን በዚህ እድሜው ምን አይነት ችግር ቢገጥመው ነው እዚህ ድረስ የመጣው፥ ጥሩ ኑሮ ኗሪ እንደሆነ ከልብሱና ከፊቱ መለየት ይቻላል!

ከ50-60ዎቹ ባሉት ኤድሜ ውስጥ እንዳለም መገመት አያዳግትም ፥ ግን! ያም ሆነ ይህ የሰውየውን ምንነት ስለማላውቅ፤ ብዙ ላወራው አልፈለኩም ምን አልባት እኔን የሚፈልጉኝ ሰዎች በኔ ላይ እንዲተውንብኝ ልከውት ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ከአካባቢው ለመሰወር ወሰንኩ ትቸው መሄድ ስጀምር በድጋሜ መናገር ጀመረ ""ምን ነው ወጣቱ? ድፍረት አጣህ ለነገሩ ገና ልጅ ነህ ሽፍታ እንዳልሆንክም እኔን እንኳ በቅጡ ማስፈራራት አልቻልክም ጥሩ ልብ ያለህ ትመስላለህ አለኝ"" ቆም ብዬ ካዳመጥኩ ቡሀላ ከሱ ጋ ብቆይ ጉዳት ሊያደርስብኝ መቼም አቅም አይኖረውም ብዬ አሰብኩና፥ መንገዴን ትቼ ወደ ሰውየው ተመለስኩ፤ ከሱ በቅርብ ርቀትም ቁጭ አልኩ፥ በመካከላችን ረዘም ያለ ፀጥታ ሰፈነ በድንገት ከኛ በተወሰነ ርቀት አንድ ድኩላ ብቅ አለ በፍጥነት አነጣጥሬ ተኮስኩበት እየሮጥኩ ስሄድም እየተፈራገጠም አገኘውት ጩቤዬን አወጣሁና አረድኩት ከዛም ተሸክሜ ወሰድኩና መቃፈፍ ጀመርኩ!

ቅድም ግን ድንገት ስተኩስ አደነጋገጡ ትዝ አለኝ እና ፈገግ እያልኩ ወደሱ ስዞር፤ ወደ ኪሱ ገባ አለና ብስኩት ነገር አውጥቶ እንድቀበለው እጁን ዘረጋ ቀጥ ብዬ አይቼ ፍላጎቴን ሳልገልፅ አትኩሮቴን ወደ ስራዬ አደረኩ ሀሳቤን የተረዳ መሰለኝ ከመሀል አንድ አውጥቶ ለራሱ በላና አሁንስ አለኝ! ትንሽ ስለራበኝ ሳላንገራግር ተቀበልኩ ያን እየበላሁ ስራዬን እየሰራው ሳለ በመሀል አየህ ወጣቱ ሰው ማለት እንደ ታዳኝ እንሰሳ ነው አለኝ፥ እያናገረኝ ዝም ማለቱ ጥሩ አይለም በዛ ላይ የትልቅ ሰው ምክር የሚባል ነገር አለ ዘወር ብዬ....እንዴት? አልኩት.. ምክንያቱም ምን ጊዜም በወጥመድ ውስጥ ነው ለማደግ ስትፍጨረጨር ለምን ብሎ ይመቀኝሀል የቻለውን ያክል ሊጥልህ ይሞክራል እንደምንም ተቋቁመህ ካለፍክ ይበልጥ ይበሳጫል እናም አንድ ቀን ልታመልጥበት የማትችል ወጥመድ አዘጋጅቶ አነጣጥሮ ይተኩስብሀል ከዛም ደካማ ጎንህን ተጠቅሞ ይጥልሀል በቃ ሰው እንደዚህ ነው አለ፧፧ ከዚህ ቅኔ ጀርባ የሆነ ታሪክ እንዳለ ተረድቻለሁ ስራዬን ገታ አደረኩና ግን አንተ ማን ነህ? ማለቴ ምን አይነት ችግር ቢገጥምህ ነው ወደዚህ የመጣሀው ከአለባበስህ ደህና ኑሮ እንዳለህ ያስታውቃል አልኩት.....
ራሱን እየነቀነቀ! ምን ያደርጋል ሁሉ ነገር በነበር አለቀ አለ ሲቃ በተሞላበት ድምፅ ስሜት!
ምን አልባት ትምህርት ሊሆን ይችላልና ከልብ አዳምጠኝ ብሎ ትረካውን ጀመረ እኔ ማለት.......

ከወደዳችሁት ይቀጥላል😘

ሰሞኑን ስለጠፍን ይቅርታ እንጠይቃለን🙏
አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
ሰው ሆይ👌👌

👉ዛሬ ላይ ምንም ቆንጆ ብትሆን ነገ ልክ ቀብር ስገባ አስቀያሚ ነህ፤
👉ዛሬ ላይ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ ትባላለህ፤
👉ዛሬ ላይ ምንም ሃብታም ብትሆን ነገ ግን 1ሜትር ከፈን ብቻ ነው የሚኖርህ፤
👉ዛሬ ላይ ምንም እንኩዋን በቤተሰብ ብትከበብ ነገ ቀብር ውስጥ ብቻህን ትቀራለክ፤
👉ዛሬ ላይ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህ ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነህ፤
👉ዛሬ ምንም በዘርና በጎሳ ብትመካ ነገ አንተ ብቸኛ ነህ፤
👉ዛሬ ላይ ምንም ሁን ምን ነገ አንተ ሬሳ ነህ ሬሳ።
👉ዛሬ ብትናፈቅ ነገ እንዳትሸታቸው ሰዋች ቶሎ ይጥሉካል ፤
ስለዚህ ዛሬ ላይ ለዘለአለም ህይወት የሚጠቅመንን ስራ ብንሰራ መልካም ነው።
ወደ አሏህ እንመለስ መንገዱንም እሱ ያቅናል
🌺🌺🌺🌺
አሚን ያ ረብ....
•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ሁለት(2)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

.........ምን አልባት ትምህርት ሊሆንህ ይችላልና ከልብ አዳምጠኝ ብሎ ትረካውን ጀመረ እኔ ማለት.......
.........""ስሜ አይሀም ይባላል ለቤተሰቦቼ አንድ ልጅ ነበረኩ የወንድም እና የእህትን ፍቅር አላውቀውም በኢኮኖሚ ደካማ የሚባሉ ቤተሰብ ልጅ ስለነበርኩ! ኑሯችንን የማሻሻል እና በእርጅና ዘመናቸው የምንከባከባቸው ብቸኛ ተስፍቸው ነበርኩ እንደምታስበው አልጋ በአልጋ ባይሆንም ተስፍ ባለመቁረጥ የፈጣሪ እገዛ ተጨምሮበት ያሰብኩትን አሳካሁ፤ ወላጆቼንም ከሁለት አመት በፊት ተካታትለው ሞቱ! አሁን ከነበርኩበት ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስዋእትነት ከፍያለሁ!
አሉ ከታባሉ የናጠጡ ባለፀጋዎች አንዱ መሆን ቻልኩ የስራው አለም ያገናኘን እኔን መሰል ጓደኞችንም ማፍራት ቻልኩ ከ20 አመት በፊት ትዳር መስርቼ አሁን የ19 እና 12 አመት ቆንጆ ሴት ልጆች አባት ነኝ አብዛሀኛውን ጊዜ ከቤት ስለማልኖር በጣም ይናፍቃሉ... ብሎ በእምባ የተሞሉ አይኖቹን እየጠራረገ አንገቱን አቀረቀረ""

... እኔም ታሪኩን እያዳመጥኩ ሳይታወቀኝ መቃፈፌን ጨርሼ ስጋውን ለመጥበስ እሳት እያቀጣጠልኩ ነው! ታሪኩን እንዲቀጥልልኝ
ታዲያ ይሄን እዚህ መገኘትህ ጋር ምን ያገናኘዋል አልኩት፥ .....""አንገቱን ቀጥ አደረገና ከንፈሩን እየመጠጠ.. ነገሩ እንዲህ ነው ከጓደኛቼ መካከል አንዱ ልጄን እንደወደዳት እንደ ቀልድ በተገናኘን ቁጥር ይነግረኛል እኔም እንዳልድርልህ አግብተሀል ኧረ እንደውም ከማግባት አልፎ የአንድ ልጅ አባትም መሆኑንም ስለማውቅ! ልጄን ለቀቅ አድርጋት እየተባባልን ተሳስቀን እንለያያለን ነገር ግን እኔ እንዳሰብኩት አልነበርም እንደውም በተቃራኒዉ ነበር ይባስ ብሎ እንደለመድንው አንድ ቀን ምሽት ላይ ተገናኘን እና ፊቱን ኮስተር አድርጎ ስለ ልጄ ደጋግሞ ይጠይቀኛል እኔም በንዴት ምንድን ነው አላበዛሁም በቃህ ብዬ ጮኩበት! እሱ ግን የሚመለስ አልበረም እንደውም ልጄ እንድድርለት እና ካልሆነ ግን! አለ? እንዴ ካልሆነ ምን ልታመጣ ብዬ አፈጠጥኩበት?!ቤተሰብህን በታትኜ ህይወትህን ጋሀነም ነው የማደርገው ብሎ ዝቶብኝ ወጣ! እኔም በንዴት አንዲት ነገር አደርጋለሁ ብትል ራስህን ማረሚያ ቤት ነው የምታገኘው ብዬ አስጠነቀኩት""...

በመሀል ንግግሩን አቋርጬ..ማለት በድብቅ ወንጀል ሰርቶ ነበር ማለት ነው ስል ጠየኩት!""በትካዜ ስሜት... ከአመታት በፊት በጣም አንድ ሚስኪን ለሰው አዛኝ ተጨዋች ጓደኛ ነበረን እናም አንድ ጊዜ ህይወታችንን ሊቀይር የሚችል የማዕድን ጨረታ ነበረ ጨረታውን ከሁላችንም ተሽሎ ያ ጓደኛችን አሸነፈ በሱ ማሸነፍ ሌሎቻችን በጣም ደስተኛ ነበረን እሱ ግን የሱ ማሸነፍ አልተዋጠለትም ከጓደኛው ይልቅ ገንዘብን አስበለጠ ስራውን በጁ ለማስገባት አማራጭ ብሎ ያሰበውንም እሱነ ማስወገድ ነበር እና እንዳሰበውም አደረገ ያ አረመኔ አስገደለው ስራውንም በጁ አስገባ!! ያን ወንጀል መስራቱን ደግሞ እኔ ደረስኩበት! እንዳወኩበትም ሲያውቅ አንድ ቀን ምሽት ከሁሉም ጓደኞቻችን ጋር ራት ለመብላት ተሰባሰብን ነበር እኔ ግን ራቱ ላይ መቆየት የቻልኩት ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ ነው የቀረበልኝን ኮካ ከጠጣሁት ቡሀላ የሚታወቀኝ ሁሉም ነገር ሲጨልምብኝ ብቻ ነበር! ከሰኣታት ቡሀላም ከተኛሁበት ስነቃ ሸሚዜ ወልቋል ቀበቶዬ ተፈቷል፤ ሰአቴን ስመለከት 3:00 ሰአት ይላል የተገናኘነው 2:00 ሰአት ነበር እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሞኝ ስለማያውቅ በድንጋጤ ልብሴን ለብሼ እነሱ ወደሚገኙበት በችኮላ አመራሁ! ከነሱ ስደርስ ራቱን ጨራርሰው ሊወጡ ሲል ነበር ምን እንደሆንኩ ስጠይቃቸው ራሴን ስስት ወደ አልጋ ወስደው እንዳስተኙኝ ብቻ ነገሩኝ ታዲያ ልብሴን ማን አወለቀው እያለኩ ለራሴ አሰብኩኝ! ከመካከላቸውም አንድኛው ወደ ቤት የሚል ቃል እንደወጣው ያ አረመኔ ከአፍ ተቀብሎ እኔ አደርሰዋለሁ አታስቡ ሂዱ ብሎ ላካቸው እንሱም ተሰናብተውን እንደወጡ
ላንተ ጥሩ ሰርፕራይዝ አዘጋጅቸልሀለሁ ብሎ እንድከተለው በምልክት ነገረኝ ግራ እየተጋባሁ ተኝቼበት ወደነበረው ክፍል ወሰደኝ ክፍሉን ከፈተውና ወደ ውስጥ ገባን በአይኔ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም"" ...

ከወደዳችሁት ይቀጥላል👍

አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
#አላህ ሱ.ወ #ከኩራት #ይጠብቀን

📚ኢብን ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ በለዋል
#ልብሱን #በኩራት የጎተተ አላህ በእለተ ቂያማ አያየውም”

#አቡበከረም “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሽርጤ ይጎተትብኛል “ አሏቸው እርስቸውም<<አንተ በኩራት ከሚጎትቱት አይደለህም>> አሉት (ቡኻሪና ሙስሊም)

📚አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የ አላህ መልዕክተኛ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል
#አንድ #ሰው በውብ ልብስና ተኩራርቶና ተኮፍሶ እየተንበጣረረ በመሄድ ላይ እንዳለ አላህ እስከ እለተ ቂያማ መሬቱን ገለበጠበት።”(ቡኻሪና ሙስሊም)
إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا [٤:٣٦]
“…..አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም” ቁርዓን 4:36
══ •⊰✿✿⊱• ══ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
══ •⊰✿✿⊱• ══
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍃🍃ጤ ና ዎ !🍃🍃
┈┈•✦•┈┈
.
☞ ሰባት ትላልቅ አዕምሮን የሚጎዱ ልምዶች:
.
➊. ቁርስን መዝለል ወይም ጨርሶ አለመመገብ።
➋. ማታ ዘግይቶ ወደ አልጋ መሄድ ወይም ዘግይቶ መተኛት።
➌. ከፍተኛ የስኳር መጠን መውሰድ/መጠቀም።
➍. ከመጠን በላይ መተኛት በተለይ ጠዋት (ከረፈደ በኋላ)።
➎. ቴሌቪዢን እየተመለከቱ ወይም ኮምፒውተር እየተጠቀሙ ምግብ
መመገብ።
➏. በሚተኙበት ወቅት ኮፍያ፣ ሻርኘ ወይም ካልሲ መጠቀም/ መልበስ።
➐. ሽንትን ሸንተው ሳይጨርሱ የማቋረጥ ልማድ።
---------
መልካም ጤንነት!!

☟ SHARE ☟
══ •⊰✿✿⊱• ══ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
══ •⊰✿✿⊱• ══
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📜መኖርን ባልታሰበ
ክፍል ሶስት(3)
በከድር አወል
በ( @KETIBEB ) የተዘጋጀ

ወደ ውስጥ ገባን በአይኔ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም"" ...
........ በስክሪን የኔ ምስል ያለበት ቪዲዮ ፥የሆነች ወጣት ልጅ ሸሚዜን አውልቃ ቀበቶዬን እፈታች የባለጌ ፊልም እንደሰራው አድርጎ የተቀረፀ ምስል በቃ ምን ልበልህ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ ልጆቼ ሚስቴ ትዝ አሉኝ ይሄን ሲያዩ ምን ሊሆን እንደሚችል በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ እያለ ራሱን መነቅነቅ ጀመረ""
.....በመሀል ወሬውን ማቋረጥ ባልፈልግም ስጋውን ጠብሼ ስለጨረስኩ ቁምሳ ደርሷል ከብዙ ጊዚያት ቡሀላ ሰው ጋ ልበላ ነው ብዬ አቋረጥኩትና እሱም ከነበረበት ስሜት ለመውጣት ፈገግ እያለ ወደኔ ቀረበ ከዛም መመገብ ጀመረን በመሀል ደስ የሚል ህይወት ውስጥ እንዳለሁ እና ብቸኝነቴን እንደወደደልኝ ነገረኝ "አልሰሜን ግባ በለው ይላል የሀገሬ ሰው ወዶ አደለም" ምን ደስ ይላል የኔ ህይወት አልኩኝ በሆዴ " ከዛም በልተን እንደጨረስን ትንሽ አረፍ ካልን ቡሀላ ትረካውን እንዲቀጥልልኝ ዳር ዳር ማለት ጀመረኩ እሱም ሀሳቤ ስለገባው ያቆመበትን ጠየቀኝ እኔም ነገረኩትና ትርክቱ ቀጠለ ....

ከዛም .. ሁሉም ነገር ጨለመብኝ የምይዘውንም ሆነ የምጨብጠውን ነገር፥ አላቅም በጣም ጮኩኝ፧ እሱ ግን እኔ በምሆነው ነገር በደስታ ይስቃል፥ ይባስ ብሎ ሀሀሀሀ...ለመሆኑ ምን ላይ እንድለቅልህ ትፈለጋለህ fb, YouTube ወይስ ጋዜጠኞችን ጠርቼ ለነሱ ልስጣቸው የትኛው ይመችሀል እያለ አፌዘብኝ እኔም ምንም ሳልናገር ሀፍረቴን ተኮናንቤ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ፥
እንግዲህ ከዛ ቀን ጀምሮ ነው በዛ ሲዲ እያስፈራራኝ ልጄን ይቀርባት ጀመር፤ይህን በአይኔ እያየሁ መቋቋም አልቻልኩም ከማንኛው ልሁን ልጄን ልኩኝ ሙሉ ትዳሬ ሊፈርስ ነው በተዘዋዋሪ ላዋርዳቸው ነው እያየሁ ዝም ካልኩ ደግሞ ልጄን አይኔ እያየ ገደል ልትገባብኝ ነው ስ መስራትም መኖርም አልቻልኩም አማራጭ ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ ሞከርክ ግን አልቻልኩም መጨረሻ ላይም ወደዚ ጫካ ራሴን ላመሸሽ መጣሁ አለ ሲቃ በተሞላበት ድምፅ፥

.........ሰውዬው ግን ማን ነው? ብዬ ልጠይቀው አሰብኩና ማንስ ቢሆን ምን ይለወጣል፤ ሰውዬው አንዴ ወደዚህ መጥቷል ባቀውስ ሂጄ ልገለው ነው፥ እያልኩ በሆዴ አጉረመረምኩ። የጊዜ ነገር ይገረማል! ሳናስበው ፀሀይ ወደ ቤቷ ለመጥለቅ አዘንብላለች፥ ሰውየውንም ይህን ሁሉ ታሪክ ከነገረኝ ቡሗላ፤እንዳልሰማ መሆን ስላልፈለኩ ከቋጥኝ ስር ወዳለችው መኖሪያ ዋሻዬ ወሰድኩት ብርሀንም ጊዜውን ጨርሶ ለጨለማ አስረክቧል እስክንተኛ ድረስ የምንሞቀው እሳት አቀጣጥዬ፥ ከጧት የተረፈንን ስጋ እየጠባበስን ስንበላ አመሸን፥ በመሀል ስለኔ ማንነት ለምን ወደዚህ እንደመጣሁ ሲጠይቀኝ ነበር። ለመናገር አልደፈርኩም ነገ እናወራለን ብዬ የሚተኛበት ቦታ አሳየሁት፤ ደክሞት ስለነበር ቶሎ ነው እንቅልፍ የያዘው ተኝቶ ግን ልጄ ልጄ እያለ ሲቃዥ! ነበር ያደረው፤ አይነጋ የለምና የሌሊቱ ተራ አብቅቶ ለብርሀን ለማስረከብ ወገግ ሲል የምንበላው ለማደን እሱ በተኛበት ወጥቼ ሄድኩ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የሚታደን እንሰሳ ሳላገኝ በባዶው ነበር የተመስኩት ከዋሻው እንደደርስኩግን ለማመመን የሚከብድ ነገረ ነበር ያየሁት..........

ይቀጥላል

አስተያየት>>>> @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1👍1