"ሐሊማ"
ክፍል 11
✍ ሂክማ ጀማል
፡
፡
፡
ሀሊማ ቀጥታ ወደ ትምህርት ቤት ነበር የሄደችው፡፡ ትምህርት ቤት እንደደረሰች መምህራኖቹ አልመጡም ነበር ሁሉም ተማሪ ተሰብስቦ እየጠበቃቸው ነው ፡፡ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ መምህራን መምጣት ጀመሩ ሁሉም ተማሪ በየ ክፍሉ እንዲገባ ተደረገ፡፡ ሀሊማ እንደ ወትሮዋ ብቻዋን ናት እሷም ወደ ክፍልገባች ትምህርት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ታመጣለች ተብላ የምትጠበቀው ሀናን የምትባል ልጅ ብቻ ነች፡፡ ከ አባቷ ጋር የመጣችው ሀናን የነ ሀሊማ ክፍል ተማሪ ነች፡፡ ውጤት መሰጠት ተጀምሮዋል እንደተጠበቀውም ሀናን 91.9 ነጥብ አመጣች ሁሉም አጨበጨቡ እነ ሀሊማ ክፍል ለሁሉም ተሰጥቶ አለቀ ከ ሀሊማ ውጪ አስተማሪው ሀሊማን በደንብ አያውቃትም ሁሉም ካለቀ በኃላ "የ እኔስ ወጤት" ብላ አስተማሪውን ጠየቀችው "አልደረሰኝም ለወደቁ ተማሪዎች አዳራሽ ነው የሚሠጠው" አላት ሀሊማ በጣም ደነገጠች፡፡ የ አክስቷን ምክር አስታወሰች፡ እየደበራት ወደ አዳራሽ ሄደች ሁሉም ክፍል ተሰጥቶ ካለቀ በኃላ ሀሉም ተማሪ ወደ አዳራሽ እንዲገባ ተደረገ፡፡ ከትንሽ ደቂቃዎች ቆይታ በኃላ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ንግግር ማድረግ ጀመረ "በዛሬው ቀን የልፋታቹን ውጤት ያገኛችሁበት ቀን ነው አብዛኞቻቹ እንዳለፋቹ ይታወቃል፡፡ ለሚቀጥለው ከዚህ የተሻለ እንደምታመጡ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የወደቃቹ ተማሪዎች በዚህ ውጤት ተምራቹ ለሚቀጥለው አመት በቁረጠኝነት ሰርታቹ አሪፍ ወጤት ለማምጣት ሞክሩ፡፡ ዛሬ እዚህ አንድትሰበሰቡ ያደረግናቹ በጣም የገረመን የሚገርም ነገር ስላጋጠመን ነው አስተማሪዎች አናውቃትም ስላሉ በግሏ ክፍል ውስጥ እንዲሰጣት ስላልፈለግን እና እኛም ቢሆን ተማሪዋን ማወቅ ስለፈለግን እዚህ መድረክ ላይ መጥታ ውጤቷን እንድትቀበል ብለን ነው ፡፡"
....ብለው የተማሪዋን ስም ለመናገር ጎሮሮአቸውን ሲጠራርጉ መብራት ሄደ የተወሰነ ሰአት ጠብቀው ጄኔኔተር ተገጥሞ በድጋሚ ለመናገር ጎሮሮውን ጠራርጎ መናገር ጀመረ "እሺ እባካችሁን አንዴ ጆሮአቹን ስጡኝ" አዳራሹ በዝምታ ተዋጠ ሀሊማ ማን ትሁን እያለች በጉጉት እየጠበቀች ነው፡፡ እሷ ብቻ ሳትሆን ተማሪው በሙሉ እየጠበቀ ነው እሺ ብሎ መናገሩን ቀጠለ "ተማሪ ሀሊማ ከድር ብሎ" ተናገረ፡፡ ተማሪው ማንሾካሸክ ጀመረ ማን ናት እያለ "እባክሽ ሀሊማ ወደ መድረኩ " ተማሪው ማጨብጨብ ጀመረ ሀሊማ ግን ደንግጣ ከተቀመጠችበት አልተነሳችም፡፡ "እባክሽን ሀሊማ" በድጋሚ ሲናገር ሀሊማ ከተቀመጠችበት ወንበር ተነስታ ወደ መድረኩ ሄጀች፡፡ ሁሉም ያልጠበቁት ነገር ነው፡፡ ትምህርት ቤታችን እስከ ዛሬዋ እለት እንደዚህ አይነት ወጤት አስመዝግቦ አያውቅም፡፡ ሀሊማ የመጀመሪያዋ ናት ያመጣችው ነጥብ 99.9 ሁሉም ተማሪ ተነስቶ አጨበጨበላት ከ ሀናን ውጪ ሁሉም ተደስቷል ትምህርት ቤቱ ያዘጋጀላትን ሽልማት ተቀብላ ከመድረክ ላይ ወረደች፡፡
አስተማሪዎቿ እየመጡ ይስሟታል ሀሊማ ከትምህርት ቤቱ ወጥታ ፋጡማ ጋር እስክትሄድ በጣም ቸኩላለች፡፡ ሁሉም ተማሪ ወደ እቤቱ ሲሄድ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሀሊማን ወደ ቢሮ እንድትመጣ አድርጎ አድንቆቱን ገለፀላት፡፡ ከቢሮ ወጥታ ቀጥታ ወደ ፋጡማ ቤት ሄደች፡፡ እንደደረሰችም በሩን ለረጅም ሰአት አንኳኳች ግን አልተከፈተም፡፡ ልትሄድ ስትል ፍጡማ ያላትን ጉልበት ተጠቅማ በሩን ከፈተችላት ሀሊማ ፍልቅልቅ እያለች ሳመቻትና ወደ ውስጥ ገባች ምነው አክስቴ በጣም አመመሽ እንዴ? አንገቷን እየነቀነቀች መታመሟን ነገረቻት ፡፡ "ዛ..ሬ...ም...ን..ድ..ነ...ው..እ..ን..ዲ.ያ...ስ..ደ..ተ..ሽ ልጄ ብላ ጠየቀቻት" የሆነውን ነገረቻት ፍጡማ ወደ እራሷ ሳብ አድርጋ አቅፋ ሳመቻት፡፡ ፋጡማ ከድርን ጥሪው አለቻት አይሆንም ብላ ተከራከረቻት ስትለምናት እሺ ብላ ደወለችለት፡ ባባ አክስቴ ትፈልግሀለች እሺ መጣሁ ብሎ ስልኩ ተዘጋ ከድር ብዙም ሳይቆይ መጣ ሰላም ብሏቸው ተቀመጠ ሀሊማን ሱቅ ላከቻት ከከድር ጋር ለማውራት እና ሁሉንም ነገር ልትነግረው አስባ ነበር ግን አንዳሰበችው አልሆነም ሀሊማ ከተላከችበት ቦታ በፍጥነት ተመለሰች፡፡ የፈጡማ እግር ጋር ተቀመጠች፡፡ ፋጡማ በድጋሚ ተነሺ ማለት ከበዳት ትንፋሿ እየተቆራረጠ ነው ሀሊማም ሆነ ከድርም አልተረዷትም ነበር ልትሞት እንደሆነ ታውቋታል፡፡ ለከድር ለመንገር የፈለገችው ለዚህም ነው ግን መናገር አልቻለችም ፋጡማ እጃን ዘርግታ ሀሊማ ወደ እራሷ እንድትመጣ አድርጋ ሳመቻት የሀሊማን እጅ ለ ከድር አስጨበጠችው ብቻዋን እንዳትተዋት አደራ አለችው፡፡ "አክስቴ ለምንድ ነው እንደዚህ የምትይው የተነጋገርነውስ ነገርስ አክስቴ" ከድር የሀሊማን እጅ ይዞ "እንዲህ አይባልም ልጄ" እያለ እያወራት ሳለ ፋጡማ ወደ ማይቀርበት አለም ወደ አሄራ ሄደች ሀሊማና ከድር ፋጡማ እንደሞተች አላወቁም ከድር ከሀሊማ ጋር እያወራ ነው፡፡
፡
፡
፡
ክፍል 12
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•

👍4
ሐሊማ
ክፍል 12
✍ሂክማ ጀማል
፡
፡
፡
ሀሊማ ድንገት ወደ ፈጡማ ስትዞር የፋጡማ አይን
ፈጦዋል፡፡ ሀሊማ ደንግጣ ባባ አክስቴን ተመልከታት ብላ ጮኃችበት፡፡ ከድር በጣም ደንግጦ " ፋጡማ .....እህት ፋጡማ "እያለ ጮኃ ፋጡማ ግን እስከመጨረሻ አሸልባለች፡፡ ከድር አይኗን ገርበብ አደረገላት ሀሊማ
"ባባ ምን እያደረክ ነው?"
"ልጄ አይዞሽ እኔ ከጎንሽ አለሁ"
"ምን እያልከኝ ነው"
" አክስትሽን ድጋሚ አናገኛትም ሞታለች" አላት ፡፡ ሀሊማ የሰማችውን መቋቋም አቅቷት እራሷን ስታ ወደቀች፡፡ ከድር የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው ባንድ በኩል የፋጡማ ሬሳ አለ በሌላ በኩል ልጁ እራሷን ስታ ወድቃለች ፡፡ ሰሚራ ጋር ደውሎ እንድትረዳው ጠየቃት፡፡ ግን እንደ እድል ሆኖ ሰሚራ የፋጡማን ቤት አታውቀውም፡፡ በምልክት እንድትመጣ ነገራት ሰሚራም ታክሲ ተኮናትራ ከከድር ጋር እየተደዋወለች በምልክት ደረሰች፡፡ ከድር ከ እቤት ወጥቶ ተቀበሏት አንድ ላይ ወደ ቤቱ ገቡ፡፡ ሀሊማ ልትነቃ ስላልቻለች ከድር አቅፎ ወደ ሀኪም ቤት ይዟት ሄደ፡፡
ሰሚራ ከፋጡማ ጋር ብቻዋን ነች በጣም ፈርታታለች ፡፡ ልትቀርባት አልቻለችም ፋጡማ የቀረ ዘመድ የላትም ሰሚራ ለጥቂት ግዜ ተረጋግታ አስባ አንድ ሀሳብ መጣላት የፋጡማ ጎረቤቶች ጋር ሄዶ መናገር ፡፡ ወዲያው ከ ቤቱ ወጥታ ለተወሰነ ሰው ተናገረች የሰፈሩ ሰው ተባብሮ ድንኳን ተደኮነ ሬሳውንም እንዲከፈን ተደርገ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ እየያዘ ነው፡፡ በዚህ መሀል ግን ሰሚራ እንደዛ በብጣሽ ጨርቅ ጠቅልላ የጣለችው ሬሳ ትዝ አላት፡፡ ስራዋ ለእራሷ ቀፈፋት አሁን ቢቀፋትም ባይቀፋትም ከ አለፈ ወዲያ ምን ያደረጋል፡፡
ሀሊማ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ነቃች፡፡ ከድር ትንሽ ሰላም ተሰማው ወዲያውኑ ዶክተሩን ጠራው፡፡ ዶክተሩም የተወሰነ ነገር ቼክ ካደረገ በኃላ ከድርን 1 ውጪ ላናግርህ ብሎ አብረው ከክፍሉ ወጡ በሩን ጠጋ አድርጎላት መነጋገር ጀመሩ፡፡
" ያን ያህል አደጋ ላይ ሊጥላት የሚችል ነገር የለም አንዳንድ ሰው ከመጠን ያለፈ ደስታ እና ሀዘን ሲያጋጥመው መቋቋም ያቅተውና እንደዚህ አይነት ችግር ሊፈጠር ይችላል" ብሎ ዶክተሩ ለ ከድር ይነግረዋል ፡፡ የተወሰነ ሰአት እረፍት ታድርግና ትወጣለች ብሎ ዶክተሩ ከድርን ተሰናብቶ ይሄዳል ከድር የሀሊማን ጉዳይ ከሰማ በኃላ ወደ ሰሚራ ጋር ይደውላል ሰሚራ ከሰፈር ሰዎች ጋር አንዳንድ ነገሮችነን እየሰራች ነው፡፡ 6፡00 ይላል ሰአቱ የዝሁር ሰላት ሰአት እየደረሰ ነው ከድር ከሀኪም ቤቱ አሁን ካሎጣ ሰአቱ ይሄዳል ሀሊማንም ጥሎ መሄድ አይችልም ከድር ወዲያውኑ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ሄዶ ለዶክተሩ ሁኔታውን አሰረዳው ዶክተሩም ሀሊማን ይዟት እንዲሄድ ፈቀደለት ከድር ዶክተሩን አመስግኖ ያለበትን ሂሳብ ከፍሎ ሀሊማን ይዞ ወደ ፋጡማ ቤት መሄድ ጀመሩ፡፡ የሰሚራን ጩኃት እያሰበ ነው እስከ አሁን ብቻዋን እንደሆነች ነው የሚያውቀው ወደ ፋጡማ ቤት የሚወስደው ቅያስ ጋር ሲደርስ ሀሊማ በድጋሚ እራሷን እንዳትስት ፈራ ሰአቱ 6፡25 ይላል ወደ እቤት ላድርሷት ቢል እንኳ ሰአቱ አይበቃውም፡፡ አማራጭ ስለሌለው ሀሊማን ወደ ፋጡማ ቤትይዟት መሄዱን ቀጠለ ቤት ሲደርሱ ድንኳን ተደኩኖ ያያል ማን እንዲህ እንዳደረገ ለማወቅ በፍጥነት ወደ ውስጥ ገባ ጭራሽ ያልጠበቀው ነገር ነበር ሀሊማ አካሏ ነው እንጂ የለችም ማለት ይቻላል፡፡ ወደ ወስጥ ሲገባ የሚያለቅስ ሰው ምግብ የሚሰራ ሰው ብቻ ግቢው በሰው ተሞልቶ ከድር በጣም በተገረመ ሁኔታ ያያል የሰውን ሁኔታ ሲያይ እሱም ሚስቱ ትዝ አለችው፡፡ አንገቱን ደፍቶ ወደ ውስጥ ገባ ሰሚራን በአይኑ መፈለግ ጀመረ ሰሚራ አይታው ስለነበር ወደ ከድር መጣች ከድር ሰሚራን እንዳገኛት በቅድሚያ የጠየቃት ስለ ፋጡማ ሬሳ ነበር ሁሉንም ነገር ነገረችው እና ሬሳውም መስጅድ ወስጥ እንዳለ ነገረችው ሀሊማን ወደ መስጅድ ይዟት ሄዶ እንድትሰናበታት አደረገ ከዝሁር ሰላት በኃላ ተሰግዶባት ተቀበረች፡፡
ሰው ትንሽ ቀዝቀዝ ብሏል ከድር ሁለቱን ለጆቹን ይዞ መጣ ሁሉም አንድ ላይ ናቸው ሀሊማን ከፋጡማ ሞት ይልቅ የእናቷ አሟሟት ነው ይበልጥ የጎዳት በስርአቱ እንኳን አልተለቀሰላትም.....
በዛ ላይ አንድ አለችኝ የምትላት ፋጡማን ማጣቷ ጓደኛዋ እናቷ አክስቷ በቃ ሀሉ ነገሯ ነበረች ሀሊማ አሁን ከምንም ጊዜውም በላይ ብቸኝነት ተሰማት፡፡
፡
ዛሬ ፋጡማ ከሞተች ሶስተኛ ቀኗ ነው እንደመጀመሪያው ቀን የሰፈሩ ሰው በጋራ ሆነው ድንኳኑን አፈረሱት፡፡ ሀሊማ ሀዘኑን ለመርሳት እየሞከረችነው፡፡ ጠንካራ ለመሆን እየጣረች ነው፡፡ የ አክስቷን አላማ ለማሳካት ወስናለች ከ ሳምንት በኃላ እነ ከድር ወደ እቤታቸው ተመለሱ፡፡ ሀሊማ ሀዘኑ አለቀቃትም ለ እህትና ለወንድሟ ብላ ጠንካራ መሆን አለባት እሱን እያሰበች ጠንካራ ለመሆን እየሞከረች ነው፡፡ ክረምት አልፎ በጋ እየመጣ ነው ሀሊማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታለች እህትና ወንድሞቿም ትምህርት ጀምረዋል ሀሊማ በመጀመሪያ ሴሜስተር የትምህርት ቤቱ የመጀመሪያው ነጥብ የእሷ ነበር አባቷ በሀሊማ ውጤት በጣም ተደሰተ የሀሊማ ወንድም እና እህትም ሀያትና መሀመድ 1ኛ እና 2ኛ ወጡ ይህ ውጤት የሀሊማ የልፍት ውጤት ነው ሁለቱም ሀሊማን እንደ እናትም እንደ እህትም ነው የሚያዮዋት እሷም ቢሆን የእናትነቱም የእህትነቱን ሀላፊነት በሚገባ ትወጣዋለች፡፡ ሀሊማ ለሰሚራ ከምንም ግዜ በላይ ጥሩ እየሆነችላት ነው እናቷ የምታደርጋቸው ነገሮችን ሀሊማም እያደረገች ነው፡፡ ሰሚራ በስራዋ እንድትፀፀት እያደረገቻት , በይበልጥ ደግሞ ህሊነዋ እንዲወቅሳት እያደረገቻት ነው፡፡ ለከድርም ቢሆን አንድ አይነት ነገር እያደረችው ነው፡፡ ሰሚራ በከድር ልጆች የቀናች ይመስላል ከድር ከስራ እስኪመለስ ጠብቃ እራት በልተው ጨርሰው ሁሉም ተኙ ከድር እና ሰሚራ ብቻ ሲቀሩ "ከድር.....ከድር" አለችው ለዘብ ባለ ድምፅ "አቤት"
"አንድ ጥያቄ ለጠይቅህ ነበር"
"ምንድ ነው ጠይቂኛ"
"እኔ ለ አንተ ምንህ ነኝ?"
ዝም አላት ብትጠብቅ መልስ የለም እሺ አትመልስለኝ ግን ልጅ መውለድ እፈልጋለሁ ቢያንስ ይሄን መልስልኝ
፡
፡
፡
ክፍል 13
ይቀጥላል

👍2❤1
"ሐሊማ"
ክፍል 13
✍ ሂክማ ጀማል
፡
፡
፡
ሰሚራ የከድርን አፍ አፍ እያየች የሚለውን እየጠበቀች ነው ከድር ግን አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይል ወደ መኝታ ቤት ሄደ ሰሚራ በጣም ከፋት ዝም ከማለት ውጪ አማራጭ የላትም ጭለማው አልፎ በብርሀን ተተካ ሀሊማ እህትና ወንድሟን ለትምህርት ቤት አዘጋጅታ እሷም ተዘጋጅታ ሁሉም በአንድ ላይ ቁርስ በልተው ሀሊማ እህትና ወንድሟን ይዛ ወጣች ሰሚራ በድጋሚ ልጠይቀው ፈልጋ ነበር ግን ሊመልስልኝ ይችላል ብላ ዝም አለች ከአሁን አሁን ምን ተናገረ እያለች ስትጠብቅ እሱም ልብሱን ቀያይሮ ደና ዋይ ብሏት ወጣ ምንም ሳትመልስለት በዝምታ በአይኗ ሸኘችው ............
እነ ሀሊማ ከትምህርት ቤት መምጫቸው ደርሷል ሰሚራ አንድ ነገር አስባለች ........ እነ ሀሊማ አስኪመለሱ ያላትን ሞያ ተጠቅማ ቆንጆ ምግብ ሰርታ ጠበቀቻቸው እነ ሀሊማ ሲመለሱ በሞቀ ፈገግታ ተቀበለቻቸው ሀሊማ ግን ፈገግታውን አሎደደችውም ያለመደባትን ብላ ግራ ገባት በውስጧ ምን ተገኘ እያለች አሰበች በሰአቱ ሀሊማ የ 10 ክፍል ማትሪክ ፈተና ልቶስድ 2 ወር ብቻ ነበር የቀራት ሰሚራ የሚበሉትን አቀረበችላቸው ፡፡ ሀሊማ
.....እኔ አቀርበው ነበር እኮ ለምን ተቸገርሽ
......ስለደከመሽ ብዬ ነው ምን ነው ችግር አለው?
...... ኧረ የለውም ብላ መመገብ ጀመረች:: በጣም ይጣፍጣል አለቻት ሀሊማ ሰሚራ በአድናቆቱ ተደሰተች መሀመድ እና ሀያት በልተው ወደ ቁርአን ቤት ለመሄድ ወጡ ሀሊማም እነሱን ተከትላ ለመውጣት ስትነሳ አንዴ ሀሊማ የአንድ የማናግርሽ ነገር አለ እነሱ ይሂዱ አለቻት ሀሊማም እሺ ብላ እንዲሄዱ ነግራቸው እሷ ተቀመጠች
......ምንድን ነው ንገሪኝ እየሰማሁሽ ነው
....እሺ እነግርሻለሁ ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ካቀረቀረችበት ቀና ብላ እኔ እና አባትሽ አንድ ላይ መኖር ከጀመርን ረጅም ጊዜ ሆኖናል እና.... ብላ ዝም አለች
......እና ምን እናእማ ለእኔ ልጅ ለእናንተ ደግሞ ታናሽ ወንድም ያስፈልጋችኃል
.......ታዲያ እኔ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጊው
.... ከእኔ ይልቅ አባትሽ አንቺን ስለሚሰማሽ እንድትጠይቂው ነው
...ምን ብዬ
....ልጅ ወለዱ በይው
...ምን እንዴት ነው እንደዚህ የምለው ብላ አፈጠጠችባት ሀሊማ እናቷ እንደሞተች እንደማታውቅ ለማስመሰል እየሞከረች
... እናቴስ እሷ እያለች እንዴት ነው ከአንቺ እንዲወልድ የምጠይቀው ደግሞ ምን ያህል ሀራም እንደሆነ አታውቂም እንዴ ብላ በንዴት ተናገረቻት ስሚኝ ድጋሚ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳትጠይቂኝ ብላት ወጣች ፡፡
ሰሚራ ያሰበችው ባለመሳካቱ ተበሳጨች እንጂ የሀሊማ ንግግር ምንም አልመሰላትም ተስፋ ሳትቆርጥ የመጨረሻ እድሏን ለመመኮር ወሰነችከድር ሌላ ቀን ከሚመጣበት ሰአት አርፎዶዋል ሀሊማ እና ሰሚራ ሲቀሩ ሌሎቹ ተኝተዋል ሀሊማም መጠበቅ እያቃታት ነው ወደ ክፍሏ ገባች ለሰሚራ ከአሰበችው በላይ እቅዷ እየተሳካ ነው ሀሊማ መተኛቷን ካረጋገጠች በኃላ መጀመሪያውኑም ሳሎን ቤቱንም መኝታ ቤቱንም ከሌላ ግዜ በተለየ አሳምራዋለች በተለይ መኝታ ቤቱን አልጋውን ቆንጆ አድርጋ አስተካክላዋለች ፍዝዝ ያለ አንፖል ብቻ ለመኝታ ቤቱ ውበት ይሰጠዋል ያለችውን ነገር ሁሉ አድርጋለች ሀሊማ እንደተኛች ሰሚራ አሪፍ የምትለውን ቀሚስ ለብሳ መልኳን ይበልጥ ጎላ ብሎ እንዲታይ የተወሰነ ሜካፕ ተቀብታለች በጣም አምሮባታል ጨራርሳ ከድርን መጠበቅ ጀመረች..... ብዙም ሳይቆይ ከድር በሩን ከፍቶ ገባ........
ከምንመ ግዜውም በላይ በፈገግታ ተቀበለችው ከድርም ሲያያት በጣም ደሰ አለው የሰራችውን አሪፍ እራት አቀረበችለት ደስ እያለው በላ ሰሚራ ያሰበችወ ለማሳካት ግማሽ መንገድ ሄዳለች ሌላው ቢቀር ዛሬ ፊት አነሳትም የተቀባችው ሽቶ ከ እሩቁ ይስባል ከድር በልቶ ሲጨርስ እቃውን አነሳስታ አጠገቡ ተቀመጠች ሁለቱም ዝም ተባባሉ ሰሚራ ወሬ ለመፍጠር ያህል
...ስራ እንዴት ነበር ብላ ጠየቀችው
.....አሪፍ ነበር
.....በሰላም ነው የቆየኃው
....አው ያልጨረስኩት ስራ ነበር አላት
ሌላ የምታወራውን ነገር ማሠብ ጀመረች
......ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንዲህ ያማረብሽ ከድር ነበር ያለው ሰሚራም ትንሽ ሰአት ዝም ካለች በኃላ አው ሁሉም ነገር እንደ ድሮ እንዲሆን ፈልጌ ነው ብላ የተወሰነ ወደ ከድር ጠጋ አለች እሱም ወደ እሷ ጠጋ ብሎ ጥሩ ሀሳብ ነው አላት ሰሚራ በመልሱ በጣም ተደሰተች ከድር እኔም ተስማምቻለሁ ብሎ አቀፋት ሰሚራ ከከድር እቅፍ ውስጥ ሳቶጣ እሱም እንዳቀፋት ለ እረጅም ሰአት ቆዮ ዛሬ አተኛም እንዴ ኧረ እተኛለሁ ቡሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ መኝታ ቤት ለመሄድ አንድ እግሩን ሲያነሳ ሰሚራ እጁን ጎትታ አስቀመጠችወ ደንግጦ ተቀምጦ ወደ ሰሚራ ሲዞር ሳያስበው ሰሚራ ግጥም አድርጋ ሳመችው ከድር የተደበላለቀ ስሜት ተሰማው ደንግጦ ስለ ነበር የሚላት ነገር ጠፋው እንደመጣለት ተናገራት
...... ምን ማድረግሽ ነው እንደ ድሮ እንሁን ማለት በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከሆነ እንደመጀመሪያችን ብንሆን ነው የሚሻለን ብሏት እንደተቀመጠች ትቷት ወደ መኝታ ቤት ገባ እንደዛ ለፍታ ያስተካከለችውን መኝታ ቤት በአትኩሮት እንኳ ሳይመለከተው ልብሱን ቀያይሮ ሳሎን ቤት ተኛ ሰሚራ የመጨረሻ እድሏን ሞክራለች ቅስሟ ተሰባበረ መኝታ ቤት ገብታ ከልቧ አለቀሰች ሰሚራ እንደዛ ቀን ከፍቷት አያውቅም ........
ሰሚራ ተስፋ ቆርጣ መኖር ጀምራለች ሀሊማ ለሰሚራም ለከድርም ከመጀመሪያው በላይ ጥሩ እየሆነች ነው ከድር እና ሰሚራም እንደ በፊቱ ናቸው ሀሊማ 10 እና11 ክፍልን በጥሩ ወጤት አልፍለች ሀያትና መሀመድም እንደዛው ሀሊማ በአሁኑ ሰአት የ 12 ክፍልማትሪክ ፈተና ተፈትና ወጤት እየጠበቀች ነው.......
፡
፡
፡
ክፍል 14

👍2
"ሐሊማ"
ክፍል አስራ አራት (14)
✍ ሂክማ ጀማል
፡
፡
፡
የሀሊማ እህትና ወንድም አሪፍ ወጤት አምጥተው ወደ አምስተኛ ክፍል አልፈዋል፡፡ ሀሊማ 12ኛ ክፍልን በጣም በጥሩ ውጤት ነው አልፋ አዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ ተመድባ ጥቅምት ላይ ትምህርት ትጀምራለች፡፡ እህትና ወንድሞቿ ትምህርት ጀምረዋል ሀሊማ እንደ በፊቱ እነሱን መንከባከብ አትችልም፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በ ሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው የምታገኛቸው ፡፡
.
...ሀሊማ ትምህርት ጀምራለች እንደተለመደው የመጀመሪያውን ሴሜስተር በአሪፍ ውጤት አጠናቃለች እህትና ወንድሟም ቢሆን አሪፍ ወጤት አምጥተዋል፡፡ በጊዜው ሁሉምእረፍት ላይ ስለሆኑ አንድ ላይ እቤት ውስጥ ነው የሚውሉት፡፡ ሀሊማም በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ስለምታገኛቸው ቶሎ ቶሎ ይናፍቋታል፡፡ ከ 15 ቀን እረፍት በኃላ ሁሉም ትምህርት ጀመሩ ሀሊማም ጀምራለች ፡፡ሀሊማ አብዛኛውን ግዜዋን የምታሳልፈው ላይብረሪ ውስጥ ነው ከ ዶርሟ ተማሪዎችም ጋር ብዙ ቅርርብ የላትም አሁንም ብቸኛ ናት፡፡ሀሊማ እንደ ወትሮዋ ወደ ላይብረሪ ለመሄድ ከዶርሟ ወጥታ ወደ ላይብረሪው የሚወስደውን መንገድ ይዛ በዝግታ እየተራመደች ነው፡፡ ሀሊማ እድሜዋ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ቁጭ እናቷን እየመሰለች ነው፡፡ ሀለማ ቀጥ ያለ አፍንጫ ያለት አይኖቿ ጎላ ጎላ ያሉ በጣም የሚስብ የፊት ከለር ያለት የፊቷ አቀማመጥ በዛ ላይ የደም ግባቷ ተጨምሮ ቁመቷ ከመልኳ ጋር ምጥን ተደርጎ የተሰጣት ነው የሚመስለው፡፡ የምትለብሳቸው ልብሶች ለእሷ ብቻ ተብሎ የተሰሩ ነው የሚመስሉት፡፡ ባጠቃላይ እንደ ዘይነብ ሀሊማም እጅግ በጣም ውብ ነች ፡፡
.
....ሀሊማ ወደ ላይብረሪ ልትደርስ ትንሽ መንገድ ሲቀራት ድንገት ከላይብረሪው በጥድፊያ የሚወጣ አንድ ተማሪ ሀሊማ ወደ ምትመጣበት አቅጣጫ በፍጥነት እየተራመደ ሀሊማ አጠገብ ሲደርስ ገፍትሯት በእጇ የያዘቸውን መፅሀፍ፣ ደብተር አንዳለ መሬት ላይ ተበታትኖ ወደቀ ይቅርታ ብቻ ብሏት አለፈ፡፡ ሀሊማ በልጁ ሁኔታው ተናደደችበት፡፡
.
... ልጁ ግን ድጋሚ እንኳ ሳይዞሮ ትቷት ሄደ ሀሊማ በጣም ተናዳለች የወዳደቁትን መፅሀፍ እና ደብተር ሰብስባ ወደ ለይብሪው ገባችግን በጣም ተናዳ ስለነበረ ተረጋግታ ማጥናት አልቻለችም መፅሀፉን ከፍታዋለች እያነበበች ነው ግን ምንም እየገባት አይደለም፡፡ እራሷን አረጋግታ ማጥናት ስላልቻለች ላይብሪውን ለቃ ወጣች ቀጥታ ወደ ዶርሟ ሄዳ ብቻዋን ተቀመጠቸ ግን ልጁን መርሳት አልቻለችም፡፡ ......
.
በሚገርም ሁኔታ ሰሚራ ከማንም በላይ ሀሊማ ናፍቃታለች በእርግጥ ሁሉም ሀሊማን ናፍቀዋታል ቤቱ ያለ ሀሊማ በጣም ያስጠላል እንደ ቤተሰብ ባይሆኑም ከወዲህ ወዲያ የምትለው ነገር ቤቱን ጭር አድርጎታል፡፡ እህትና ወንድሞቿን እያሳቀች ቤቱን ታደምቀው ነበር ፡፡ከድር እና ሰሚራ ማን ያውራቸው በትንሹም ቢሆን ሀሊማ ታወራቸው ነበር፡፡ ከድር አንዳንድ የሚፈልጋቸውን ነገሮችን ሀሊማን ነበር የሚጠይቀው አሁን እሷ ስለሌለች የግድ ሰሚራን ነው የሚጠይቃት ይሄ በትንሹ ማውራት ለሁለቱም የጠቀመ ይመስላል ፡፡ ሰሚራና ከድርን እንደ አዲስ እያግባባቸው እየተቀራቡ ነው፡፡
.
ሀያት እህቷን ለመተካት ይመስል እንደሷ ለመሆን እየሞከረች በትንሹም ቢሆን ሰሚራን ትረዳታለች፡፡ በዚህ ደግሞ ሰሚራ ተደስታለች ሰሚራ የራሷ ልጅ ባይኖራትም የከድር ልጆችን እንደ ልጇ ተቀብላ ማሳደግ ጀምራለች በዚህ ደግሞ ደስተኛ እየሆነች ነው ........
..... ሀሊማ ንዴቷ ረገብ ሲልላት ለምንድን ነው ይሄን ያህል የተናደድኩት ብላ እራሷን ጠየቀች፡፡ ነገረ ስራዋ ለራሷ ገረማት፡፡ ከ 1 ወር በኃላ ያኔ ከገፈተራት ልጅ ጋር የገፈተራት ቦታ ላይ በድጋሚ ተገናኙ ሀሊማ ብዙም ትኩረት ሳትሰጠው ልታልፍው ስትል "የኔ እህት ባለፈው እንደዛ ገፍትሬሽ ስለሄድኩ በጣም ይቅርታ" አላት ችግር የለውም ብላው አልፋው ሄደች ፡፡
.
ትኩረት አለመስጠቷ ትንሽ ገረመው ሳሊም እንኳን እንዲ አውርቶ አይደለም ያየችው ሴት ሁሉ የምታደንቀው አይነት ሰው ነው መልኩ ስነስርአቱ እርጋታው ወንዳወንድነቱ ሁሉም ነገሩ የትኛዋም አይነት ሴት የምታደንቀው አይነት ወንድ ነው ለነገሩ ሱና ማንን አያሳምርም!! ሀሊማ ግን በሙሉ አይኗ እንኳ ሳታየው ነው ያለፈችው፡፡ከዛ ቀን በኃላ ግን ሀሊማ እና ሳሊም ለይብረሪ ውስጥ ይገናኛሉ አልፎ አልፎ ሰላምታ ይለዋወጣሉ ፡፡
አልፎ አልፎ የነበረው ሰላምታ ቀስ በቀስ ቀን በቀን ሆነ ሀሊማ ለመጀመሪያ ግዜ ከ ቤተሰቧ ወጪ ሌላ ሰው ተግባባች አንዳንድ ነገሮችን ማውራት ጀምረዋል፡፡ ግን ሀሊማ ሌላ ሰው ቀርባ ስለማታውቅ ብዙም ነፃ ሆና አታወራውም፡፡
.
....እንዲህ እየተባለ ሀሊማ የ4ኛ አመት ተማሪ ሆናለች በአሁኑ ሰአት ሳሊም እና ሀሊማ በጣም ተግባብተዋል በይበለጥ ግን ሳሊም ሁሉን ነገሩን ያጋራታል አብዛኛውን ነገር አብሯት ነው የሚያደርገው ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን አንድም ቀን ተጨባብጠውም ሆነ ተነካክተው አያውቁም ነበር፡፡
... በከድር እና ሰሚራ መካከል የነበረው ክፍተት በጣም እየጠበበ መጥቶዋል ከድር ከ 3 አመት በፊት በሀሊማ ጎትጓችነት ኢስላማዊ ትምህር ከሚሰጡ ሰዎች ጋር አብሮ መዋል መማር ጀምሮዋል፡፡ እና የ እሱና የ ሰሚራ ግንኙነት ሀራም እንደሆነ ተገንዝቦዋል ግን ምን ማድረግ እንዳለበት አለወቀም ኒካህ እንሰር ቢል እንኳ ሀሊማ ትከፋለች መመለስ የማይችላቸው ብዙ ጥያቄዎችን እንደምትጠይቀው አሰበ ታዲያ ለሰሚራ ሀራም ስለሆነ አብረን መኖር አንችለም ብሎ ሰሚራን ማባረር በጣም ከብደው፡፡ ሚስቱ እንኳ ባትሆን ይሄን ያህል አመት ልጆቹን እሱን ስትንከባከብ ቆይታለች ምንም እንኳ ሚስቱን የማጣቱ ምክንያት ብትሆንም ከድር በጣም ተጨንቆ እያሰበ ነወ፡፡
ሀሊማ ለሳሊም ስለ ቤተሰቧ ልትነግረው አስባለች በጣም ስለተቀራረቡ ይረዳኛል የሚል እምነት አላት የግድ የሚረዳት ሰው እንደሚያስፈልጋት ስለገባተ ለሳሊም ለመንገር ወስና ቀን የሚገናኙበት ቦታ ላይ ቀጠረችው፡፡
፡
፡
፡
የመጨረሻው ክፍል15
ከ200👍 ቡሀላ ይለቀቃል

ክፍል 15(የመጨረሻ)
✍ ሂክማ ጀማል
፡
፡
፡
ሳሊም አስቀድሞ ከተቀጣጠሩበ ቦታ ደርሶ እየጣበቃት ነው ሀሊማ ብዙም ሳትቆይ መጣች ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ተቀመጠች ስለ ተለያዪ ነገሮች ካወሩ በኃላ ለምን እንደፈለገችው ጠየቃት ሀሊማ እንዴት እንደምትነግረው ግራ ገባት ዝም አለችው እንድትነግረው ማግባባት ጀመረ....
.
ከድር እንደተጨነቀ ነው ግን ለምን ያሰብኩትን አልነግራትም ብሎ አሰበ ከስራ ሲመለስ ለመንገር ወሰነ ሰሚራ ከከድር ብዙ ነገሮችን ተምራለች በይበልጥ ከሀሊማ ጥሩነት ለሷ በምታደረጋቸው ነገሮች የሰራችው ስራ በጣም እየፀፀታት ነው ተውበት አድርጋ ወደ አላህ ተመልሳለች ግን ሀሊማን ይቅርታ መጠየቅ አለባት ግን ምን ብላ ልትነግራት ነው ምን ያህል ጨካኝ እንደሆነች አሰበች ብነግራት ይቅርታ ታደርግልኝ ይሁን ወይስ ይበልጥ ትጠላኛለች እያለች ከራሷ ጋር እያወራች ነው ........
.
...ሀሊማ ለሳሊም እንደምንም ከራሷ ጋር ታግላ ሁሉንም ነገር ነገረችው ሳሊም የምትነግረውን ነገር በተመስጦ እያዳመጣት ድንገት እንበው ጉንጭላይ ዱብ ዱብ ማለት ጀመሩ ሀሊማ የበለጠ ተረበሸች እሷም አብራው ማልቀስ ጀመረች ለቅሶዋን ማቆም አልቻለችም ሳሊም ከራሱ አልፎ ሀሊማን የማባበል አቅም አጣ ከአጠገቧ ትንሽ ራቅ አለ እሱም ለቅሶውን ለማቆም እየሞከረ ነው ግን አልቻለም በዛ እድሜዋ እንደዚ አይነት ነገር ተቋቁማ መኖር መቻሏ በጣም አሳዘነችው ለምን ብቻዋን እንደምትሆን አሁን ነወ የገባው እንደምንም እራሱን አረጋግቶ ሀሊማ አጠገብ ሄደ "አሁን ላለፈ ነገር ማልቀስ የለብሽም አንቺ በጣም ጠንካራ ልጅ ነሽ እስከዛሬ ኖረሻል ከ አሁን በኃላ ከዚህ በላይ ወጤታማ ሆነሽ ትኖሪየለሽ ሲላት ድንገት አቋርጣው
... ሰሚራን ሳልበቀል ሰላም አላገኝም አለችው
.....ሳሊም በሀሊማ ንግግር በጣም ደነገጠ ምን አድረገሽ ነው የምትበቀያት....
... እናቴን እንዳደረገቻት አደርጋታለሁ
ማለት ልትገድያት
አዎ
ሳሊም ደንንግጦ ይሄን ካአንቺ አልጠብቅም እሷን ከገደልሻት እናትሽን መመለስ ተችያለሽ ?
... አትመለስም ግን እናቴ ያየችውን ስቃይ ማየት አለባት ሀሊማ አንዲህ አድርገሽ ይበልጥ ስቃይሽን አታብዢው ለአንቺም ሰላም እንድታገኚ ሁሉንም ነገር እንደምታውቂ ንገሪያቸውና ይቅርታ አድርጊለቸው ሁሉንም እያወቅሽ አብረሻቸው መኖርሽን ሲያውቁ ውስጣቸው የሚሰማቸው ስሜት በራሱ ትልቅ በቀል ነው ፡፡
አላህ ይቅር ባይ ነው ይቅር ባዮችን ይወዳል
.....ምንም ብትለኝ አልሰማህም ብላ ጥላው ሄደች
አስቢበት አላት ዝም ብላው ሄደች ሀሊማ ቀጥታ ወደ ዶርሟ ነበር የሄደችው ነገሮች እንደጠበቀችው ስላልሆነ ተናዳለች ሳሊም ከተቀመጠበት ሳይነሳ ስለ ሁኔታው ማሰብ ጀመረ ሀሊማ በጣም አሳዝናዋለች ግን ደግሞ ሀሳቧን በጭራሽ አይደግፈውም ሀሊማ በበኩሏ ሳሊም ያለትን ነገር መቀበል በጣም ከብዷታል አንድ በአንድ እያብጠረጠረች ማሰብ ጀምራለች .....
.
.... ከድር ለሰሚራ እንዴት መንገር እንዳለበት እያሰበ ነው እንዳላስከፋት ብሎ ፈርቶዋል ..... ሰሚራም ምን ማድረግ እንዳለባት ግር ብሏታል ሀሊማን ነው ወይስ ከድርን ነው በቅድሚያ ማናገር ያለብኝ ለነገሩ ለምኑም ለምኑም ለከድር መንገር የተሻለ ነው ግን ባይቀበለኝስ እንቢ ቢለኝስ ሀሊማን እስከመጨረሻው ይቅርታ መጠየቅ አልችልም ማለት ነው ይሄ ደግሞ እንዲሆን አልፈልግም እያለች በቻዋን ታወራለች አእምሮዋ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ተፈጠሩ አንዱ ላይ ወስና መቆም አልቻለችም .....ሁሉም ተጨንቀዋል አንዱ ለአንዱ ምን ማለት እንዳለበት ግራ ገብቶታል ሁሉም እንደተጨነቁ ናቸው እንደማይመሽ የለምና መሸ ከድር ወደ ቤቱ መሄድ በጣም ከብዶታል መንገዱ ሙሉ ምን እንደሚላት እያሰበ ነው ቤቱ የደረሰው የግቢውን የበር ቁልፉ ከኪሱ አወጥቶ በሩን ከፍቶ ገባ ሰሚራም በጣም ተጨንቃለች ልንገረው ወይስ ይቅር እያለች ከ ራሷ ጋር ሙግት ጀምራለች የሳሎኑን በር አንካኩቱ ወደ ውስጥ ገባ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ከድር መጅሊሱ ላይ አረፍ አለ ሰሚራ እራት ለማቀራረብ ወደ ውስጥ ገባች እራት አቅርባ ሁሉም አብረው በሉ የተወሰነ ሰአት ከተጨዋወቱ በኃላ ሀያትና መሀመድ ወደ ክፍላቸው ገብተው ተኙ ከድር እና ሰሚራ ብቻቸውን ቀሩ ሁለቱም ያሰቡትን መናገር አቅቷቸው አይን ለአይን ተፈጠዋል እንደ ድንገት ሁለቱም
. ..እንትን ብለው ሁለቱም ዝም አሉ ከድር ምንድን ነው ሰሚራም ምንድን ነው አለች..
እነግርሻለሁ ባይሆን ምን ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነው ቀድመሽ ንገሪኝ አለ ከድር ግድ የለም ቀድመህ ያንተን ንገረኝ የኔ ከ አንተ በኃላ ይደርሳል .....አንተ አንቺ እየተባባሉ በመጨረሻ ሰሚራ ቀድማ ለመናገር ተስማማች እና መናገር ጀመረች፡፡
ከድር እኔ ጥሩ ሰው እንዳልነበርኩ አውቃለሀ ግን ከ አሁን ወዲህ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳ ባልሆን መጥፎ ሰው መሆን አልፈልግም ሁሉንም ነገር በ አዲስ መልኩ መጀመር እፈልጋለሁ....... እና ለሀሊማ ሁሉንም ልነግራት አስቢያለሁ
....ከዛስ... አለ ከድር በንግግሯ ደንግጦ ለሀሊማ ሁሉን ነገር ከነገረቻት እሱም ሰራው ውስጥ እንዳለበት ካወቀች እንደምትጠለው ያውቃል.. ይሄን ደግሞ ከድር መቋቋም አይችልም.... ከዛማ ይቅርታ ከደረገችልኝ አደረገችልኝ ካልሆነ እንደፈለገች ታድርገኝ ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ከድር ዝም አለ እሱም ቢሆን ነግራት ሰላም ቢያገኝ በጣም ደስተኛ ነው ግን የሚመጣው ውጤት አስፈርቶታል ከድር ለሰሚራ ሊነግራት የነበረውን ነገር ትቶ ስለ ሀሊማ መልስ መጨነቅ ጀመረ ከተቀመጠበት በዝግታ ተነስቶ ወደ መኝታው ሄደ ሰሚራ እዛው ሳሎን ቤት ወስጥ ባለችበት ጋደም አለች .......
.
.... ሀሊማ በአንድ በኩል ሳሊም የተናገራትን ነገር እያሰበች በሌላ በኩል የእናቷን ደም እንደፈሰሰ ሊቀር እንደሆነ እያሰበች በጣም ተጨንቃለች ለሀሊማ በቀሏ እስከ አሁን ድረስ የለፋችለት ነገር ነው አላማዋ ነው እስከ አሁን በትእግስት የኖረችበት ምክንያትም ነው ይሄን መተው ለሀሊማ ከመሞት አይተናነስም ይሄን መተው በጣም ከብዷታል እየተጨነቀች እንቅለፍ የሚባል ነገር በአይኗ ሳይዞር ነጋ ፡፡ ሀሊማ ከ አልጋዋ ላይ ሳትነሳ ስልኳን ከትራሷ ወስጥ አውጥታ ሳሊም ጋር ደወለች ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ልታገኘው እንደምትፈልግ ነገረችው ይቅርታ ሀሊማ ሀሳብሽን ካለቀየርሽ ላገኝሽ አልፈልግም ሀሳብሽን ከቀየርሽ እንገናኝ .....
ሀሳቤን አልቀየርኩም ማለት ምንም መወሰን አልቻልኩም እባክህን ላግኝህና እርዳኝ ትንሽ ካንገራገረ በኃላ እሺ የተለመደው ቦታ አጠብቅሻለሁ ብሏት ስልኩ ተዘጋ ......ሀሊማ ከተኛችበት ተነስታ ታጥባ ቀያይራ ወደ ተቀጣጠሩበት ቦታ ሄደች ቀድማ ነበር የደረሰችው ብዙም ሳትቆይ ሳሊም መጣ የቀዘቀዘ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ቀጥታ ወደ ጉዳያቸው ገቡ ሀሊማ ይህንን አላማዋን ለማሳካት ያደረገችውን ነገር ነገረችው እንዴት ብዪ ነው የምተወው እያለች ያደረገችውን ነገር ሁሉ ነገረችው ....

❤1👍1
ብዙ ነገር አድርገሽ ሊሆን ይችላል ግን ሁሉንም ያደረግሽው ለክፋ ነገር ነው ደግሞ ሰሚራን ብትገድያት ምንም የምታገኝው ነገር የለም እንደውም በተቃራኒው የህሊናሽ ወቀሳ ነው የምታተርፊው መቼም ሰላም አታገኝም አላህ አንድን ነገር ሲያደርግ ያለ ምክንያት አያደርግም ምን አልባት እናትሽ በሂወት ብትኖር ኖሮ ዛሬ እዚህ መግባት አትቺይም ነበር ለምን ልትይኚ
ይሆናል አንቺ አሁን እንደዚ ትምህርትሽ ላይ ጠንክረሽ የምትማሪው አንደኛው ምክንያት ሰሚራን ለመጉዳት ነው ግን አንቺ ለክፋት አስበሽ ቢሆንም የተማርሽው ግን አንቺን ነው የሚጠቅመው እናትሽ ብትኖር ግን እንደ አሁኑ ወጤታማ ላትሆኝ ይችል ነበር እያለ ብዙ ከመከራት በኃላ ውሳኔው የ አንቺ ነው እሺ አስብበታለሁ ስለምክርህ እና አብረኃኝ ስለሆነክ አመሰግናለሁ ብላው ሄደች ቀኑ ሀሙስ ነበር አርብ ቀን ነው ሀሊማ ወደ ቤቷ የምትሄደው ቀኑን እንዲሁ ሁሉም ሲጨነቁ ሲያስቡ አለፈ አርብ ጠዋት ሀሊማ ከድር ጋር ደውላ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
... ባባ ዛሬ ብቻዬን አይደለም የምመጣው ላሳውቅህ ብዪ ነው ከድርም እሺ ብሎ ስልኩን ዘግቶ ሰሚራ ጋር ደውሎ ነገራት ሀሊማ ለሳሊም ደውላለት አብሯት እንዲሄድ ለምናው እሺ አላት ከጁምአ በኃላ እንገናኝ ብላ ስልኩን ዘጋችው ሀሊማ በጣም ፈርታለች ጁምአ ሰግዳ ከሳሊም ጋር ተደዋውለው ወደ ሀሊማ ቤት ሄዱ ሲደርሱ አንኳኩ ሰሚራ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ጋበዘቻቸው ሁለቱም ወደ ሳሎን ቤት ገቡ ሀሊማ እቤት ስትደርስ ለ ከድር ደውላ እቤት እንዲመጣ እና ሰው ልታስተዋውቀው እንደሆነ ነግራው ስልኩ ተዘጋ ብዙም ሳይቆይ ከድር እቤት ደረሰ ምግብ ቀርቦ ሁሉም አብረው ተመገብ ሰሚራ እና ሀሊማ እቃዎቹን አነሳስተው መጨዋወት ጀመሩ ትንሽ አንደተጨዋወቱ ሀሊማ አንዴ በቅድሚያ እንግዳዬን ለስተዋውቃቹ ሳሊም ይባላል ልክ እንደ ሴት ጓደኛዬ ነው እና ለምን ይዤው እንደመጣሁ በኃላ አነግራችኃለሁ ዛሬ የማውቀውን ልነግራቹ እና አፋ እንድንባባል ነው አለች ሰሚራ እና ከድር ግራ ገብቷቸው ሀሊማ የምትለውን ነገረ ማዳመጥ ጀመሩ ሀሊማ ያየችውን የሰማችውን ነገር አንድ በአንድ ነገረቻቸው ሰሚራ የምትገባበት አጣች ከድርም በጣም ደንግጦ ባለበት ደርቆ ቀረ እስከዛሬ አታውቀውም ብለው የሚያስቡትን ነገር እያወቀች ዝም ማለቷ ከድርን አሸመቀቀው ሳሊም በተራው መናገር ጀመረ ያለፈውን ረስታቹ ይቅር ተባብለቹ በሰላም ኑሩ ብሎ ዝም አለ ሁሉም ዝም አሉ ሰሚራ ለሀሊማ አፉ በይኝ ይሄን ሁሉ ነገር እያወቅሽ አብረሽኝ እንዴት ኖርሽ ከበደልም በላይ በድዬሻለሁ አፉ በይኝ ከድርም አፉ በይኝ ብሎ በፀፀት ጠየቃት ሀሊማ ሁለታችሁንም አፋ ብያቸዋለሁ ሁሉም ተቃቅፈው አለቀሱ ሳሊምን ይዤው የመጣሁት እንድታመሰግኑልኝ ነው እንደዚህ የመሆኑ ምክንያት እሱ ነው ብላ ተናገረች ....... ቀኑ በደስታ አሳለፋት ሊመሽ አካባቢ ሳሊም ወደ ቤቱ ሄደ በነጋታው በዘይነባ ስም ሰደቃ አድርገው ለሚስኪኖች አከፋፈሉ........
ከ 15 ቀናት በኃላ ከድር እና ሰሚራ አነስ ባለ ዝግጅት ኒካ አሰሩ ሳሊም እና ሀሊማም ከድር እና ሰሚራ ኒካ ባሰሩ በሳምንቱ አነሱ ኒካ አሰሩ ሁለቱም ከተመረቁ በኃላ ተጋብተው አብረው መኖር ጀመሩ ፡፡ እነሱ ሲጀምሩ እኔ እዚህ ላያ ጨረስኩ፡፡
ተፈፀመ
ሌላ ምርጥ ታሪክ ከ300👍 ቡሀላ እንጀምራለን።
ለማንኛውም አስተያየት>>>> @ketibebot

❤1
🙋♂እንዴት ናቹሁልኝ ውድ ተከታዮቼ!🙋
በአስደናቂ ፁሁፎቿ የምናውቃት ነኢማ ኸድር😘 አስደማሚ አስተማሪ እና አስለቃሽ ታሪክ ሂጃቤ💓በሚል ርዕስ ልታቀርብልን እንደሆነናዝግጅቷን እየጨረሰች እንደሆነ አሳውቃለች እንደተመለስኩም መልዕክት አድርሰልኝ ብላለች ነው‼
እስከዛ ግን በኔ 🕺የተደረሰው እና የተፃፈውና መኖርን ባልታሰበ🚶የሚለውን ታሪክ ነገ ጀምሮ ላስነብባቹሁ ወድጃለው!💁♂
እናንተም እየተከታተላቹሁን እንደሆነና ቻናሉን እንደምትወዱት እስኪ በ👍 አሳዩን‼መልካም ንባብ ይሁንላቹ‼

አንድ ጊዜ ይባላል... የሆነች አይጥ የድመት ጓደኛ ነበራት። ድመቷና አይጧ በጣም ይዋደዳሉ። ሁለቱም ቤተሰብ ያላቸው ሲሆን ተጠልለው የሚኖሩት በአንድ ቤት ውስጥ ነበር። እናትና አባቶቻቸው ሁለቱ ባላንጣዎች ጓደኛ መሆናቸውን አያውቁም። ትንሿ ድመት በበኩሏ #አይጥ ለድመቶች ጣፋጭና ልዩ ምግብ መሆኗን የማታውቅ ሲሆን አይጧም #ድመት አስፈሪ እና ዋና የአይጥ ጠላት መሆኗን አታውቅም
በእንዲህ ጓደኝነታቸው ብዙ ግዜን ይቆያሉ። ከእለት ወደ እለትም ፍቅራቸው እየጨመረ ሄደ።
ከእለታት አንድ ቀን የድመት #እናት ትንሿ ድመት ከውሎ ስትመለስ "የት ውለሽ ነው የመጣሽው?" ስትል ጠየቀቻት። ትንሿ ድመትም "እኔማ ከውዷ ጓደኛዬ አይጥ ጋር ተጫውቼ እየመጣሁ ነው" ብላ ለእናቷ መለሰች። እናትም በቁጭትና በእልህ መንፈስ ...."አይጥ ማለት እኮ የእኛ ጣፋጭ ምግብ ናት። እሷ ጓደኛ ሳትሆን የምትበላ ምግብ ናት። ከዚህ በኋላ ካገኘሻት ቀስ ብለሽ ተመገቢያት" በማለት ልጇ ን አስጠነቀቀች።
አይጧም ከውሎዋ ወደ #እናቷ ጋር ስትመለስ ትንሿ ድመት የተነገራትን ንግግር የመሰለ ለአይጧ ነገረቻት። እንዲህ አለቻት.."ድመት ማለት የእኛ ጠላት፣አስፈሪ አውሬ ናት። እሷ እኛን ለመመገብ የተፈጠረች ፍጡር በመሆኗ ከዚህ በኋላ እንዳትቀርቢያት። በስህተት ብትቀርቢያት እንኳ በፍጥነት ከአጠገቧ አምልጪ"... በማለት ለትንሿ አይጥ መከረቻት።
እንደተለመደው ትንሿ ድመት ወደሚጫወቱበት ቦታ ሃዳ አይጧን ብትጠብቃት ልትመጣ አልቻለችም። ድመት ብዙ ጠበቀች አይጧ ግን አልመጣችም። በስተመጨረሻ ትንሿ ድመት "እናቴ የነገረችኝ እውነት ነው። ይቺን ሚጢጢ አይጥ ሳልበላ መመለስ የለብኝም በማለት ወደ አይጧ ቤት ትጓዛለች። የአይጧ ባት አቅራቢያ በመቆምም ጮክ ብላ አይጧን ጠራቻት።
አይጧም" አባት ድመት ለምን ፈልገሽኝ ነው?" በማለት በትዝብት መልክ ጠየቀቻት። ድመቷም "ነይ ጠጋ በይና የድሮ ጫወታችንን እንጫወት" ትላታለች። አይጧም ... "እኔም አራዳ አንቺም አራዳ፣ እናትሽ ላንቺ የነገረችሽን የኔም እናት ለእኔ ነግራኛለች" በማለት መለሰቻት። ከዚህ በኃሏም ሁለቱ እንስሳ ሲገናኙ፣ ድመት ስታሯርጥ አይጥ ደግሞ በመሸሽ ታመልጣለች።
#አስተምህሮ...
ወላጆች ልጆቻችን የት እንደሚውሉ ልናውቅ ይገባል። የአይጧ እናት ደርሳ ለልጇ ባትመክር ኖሮ ፣እናት ልጇን ታጣ ነበር። እኛም ልጆቻችን የትና ከማን ጋር እንደሚውሉ በማወቅ ከአልባሌ እና ብልሹ ስነ ምግባር ልንጠብቃቸው ይገባል።
"ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ። ከምትጠብቁትም ትጠየቃላችሁ። ሰውየው በቤቱ ውስጥ ጠባቂ ነው። ከሚጠብቀውም ነገር ይጠየቃል..." #ረሱል ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም

አህመድ እና መርየም የሚባሉ ባል እና ሚስት ነበሩ። በጣም ደስ የሚል ቤትና ሁለት የሚወደዱ ልጆችም አሏቸው፤ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት።
ከዕለታት አንድ ቀን አህመድ ለስራ ጉዳይ ወደ ሌላ ከተማ እንዲሄድ በአለቆቹ ይነገረዋል። ለበርካታ ቀናት ሊቆይ እንየሚችልም ይገለፅለታል።
ሚስቱ መርየም ይህንን ስትሰማ እሷም ከከተማ ወጣ ብሎ ትንሽ የመቆየት ፍላጎት ስላደረባት አብረው ለመሄድ ጥያቄ ታቀርብለታለች። እርሱም በደስታ እሺታውን ይገልፅላትና ለጉዜ ላይ ዝግጅት ይጀምራሉ። ከሁሉም በፊት ግን #ሁለቱ ልጆቻቸውን በቅርበት የምትጠብቅላቸው አንዲት ታማኝ ሴትን ይቀጥራሉ።
ባልና ሚስቱ ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ተባለው ከተማ ይሄዳሉ.......
......አህመድና መርየም መመለስ ከሚገባቸው ቀን ዘግይተው ነበር ወደ ቤት የተመለሱት። መኖሪያ ከተማቸው ሲደርሱ ሁለቱም ደስ አላቸው። ነገር ግን ከሚኖሩበት ሰፈር አካባቢ አቅጣጫ ጭስ መሰል ነገር ሲመለከቱ ምን እንደሆነ ለማጣራት በቀጥታ ወደ ቦታው ያመራሉ። አንድ ቤት ተቃጥሎ በእሳት እየነደደ ነበር። #መርየምም "የሚገርም ነው! የእኛ ቤት አይደለም። ወደ ቤታችን ሄደን ልጆቻንን እንይ" ትላለች።
አህመድ ግን መኪናውን እየነዳ ወደ ተቃጠለው ቤት ቀርቦ ተመለከተ። በጣም በማዘንም "የማን ቤት እንደሆነ አወቅሽ? እዚያ ትልቁ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰራው የጀማል ቤት እኮ ነው። እስካሁን ከስራ የተመለሰ አይመስለኝም። አንድ ልናደርገው የምንችለው ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ" በማለት ተናገረ።
ሚስቱ መርየም ግን ተቃወመችው "እኛን የሚያገባን ምንም ነገር የለም። ይህ የለበስከው በጣም የሚያምርና ውድ ልብስህ ከጥቅም ውጭ ነው የሚሆነው" በማለት ወደ ባት እንዲሄዱ ገፋፋችው።
አህመድ ለመርየም ንግግር ምላሽ ሳይሰጥ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ሚቀጣጠለው ቤት ደረጃ አጠገብ አቆማት። ቤቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዟል። አንዲት ሴት ከቤቱ ውስጥ የስቃይ ድምፅ ታሰማለች። "ልጆቹ! ልጆቹ!!" በማለትም ታለቅሳለች። ባልና ሚስቱ ከሚገባው በላይ ደነገጡ።
አህመድ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ የወደቀችውን ሴት ትከሻ ክንድ በመያዝ ካነሳት በኋላ ልጆቹ የት እንደሆኑ ጠየቃት። ሴትየዋም ልጆቹ ምድር ቤት ውስጥ መሆናቸውን እያቃሰተች ተናገረች።
አህመድ እየተጣደፈ አጠገቡ ያገኘውን ባልዲ ሙሉ ውሃ በለበሰው ልብስ ላይ በማፍሰስና በውሃ የተነከረ ፎጣ አናቱ ላይ በማሰር ወደ ምድር ቤቱ ይገባል። ምድር ቤቱ በጭስ ታፍኗል። ሙቀቱ ሰው አያስቀርብም። እንደምንም ብሎ ልጆቹን በትከሻው ተሸክሞ ሲወጣ ሌላ የህፃናት የጭንቀት ድምፅ ይሰማዋል። በትከሻው የተሸከማቸውን በፍርሃት የሚንቀጠቀጡ ልጆች ይዞ ከወጣ በኋላ ቤቱ ውስጥ ሌሎች ህፃናትም እንዳሉ ይነገረዋል። ምን ያህል እንደሆኑ ሲጠይቅ ሁለት መሆናቸው ይገለፅለታል።
በድጋሚ ተመልሶ ሊገባ ሲንቀሳቀስ ሚስቱ እጁን ይዛ ልትከለክለው ትሞክራለች። "መሞት ትፈልጋለህ እንዴ!? ተመልሰህ እንዳትገባ!" በማለት ስትናገር አህመድ የያዘችውን እጇን መንጭቆ እሳቱ ወደሚነድበት ቤት ሮጦ ይገባል። በጭስ ታፍነው ለመሞት የተቃረቡ የሚመስሉ ሁለት ህፃናትን ያገኛል። ወዲያውኑ በጎንና ጎኑ አንገቱን በደንብ እንዲይዙ አድርጓቸው ከቤቱ በመውጣት ላይ እያለ አንዳች የሚያውቀው የሚመስለው ነገር ሰውነቱን ይወረዋል። ጎንና ጎኑን አንገቱን በሁለት እጆቻቸው ጨምድደው የያዙት ልጆች የሚያውቃቸው መሰለው። እየሮጠ ከሚቃጠለው ቤት እንደወጣ የተመለከተው ነገር የማይታመን ሆነበት። ሳያስበው ጉንጩ በእንባ ተሞላ። ሁለቱ ህፃናት የራሱ ልጆች ነበሩ። እንድትጠብቃቸው የተቀጠረችው ሴት ገበያ ስትሄድ በአደራ ጎረቤት አስቀምጣቸው ነበር።
#እስተምህሮት....
ሁሌም ጥሩ እንሁን፤ አላህ ለእኛ በጎን ነገር ይወፍቀናል። አዛኝ እንሁን፤ አላህ ያዝንልናል። ለራሳችን የምንወደውን ለወንድማችን እንውደድ፤ ለራሳችን የምንጠላውንም ለወንድማችን እንጥላ።
JOIN ⇒
https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ

☺️ አእምሮአችን የመረጠውን
በፍላጎታችን ልንቀይረው እንችላለን‥
ነገር ግን ልብ የመረጠውን ውሳኔያችን
የቱንም ያህል ቢሆንም ልንቀይረው አንችልም
Te» @ketibeb
በፍላጎታችን ልንቀይረው እንችላለን‥
ነገር ግን ልብ የመረጠውን ውሳኔያችን
የቱንም ያህል ቢሆንም ልንቀይረው አንችልም
Te» @ketibeb
እውነተኛ አፈ ታሪክ ነው
በድሮ ጊዜ አንድ አግኝቶ ያጣ ባለፀጋ ሰውዬ በአገሪቱ አሉ የተባሉ ባለሀብት ሰው ጋር ይሄድና
"ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡
ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከዶሮ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡
ነዳያኑም "ቆዳዋ" አለ፡፡
ባለጠጋውም "እውነትም አግኝተክ ያጣክ ነህ፤ በሉ ከእህሉ ስፈሩለት፤ ከከብቶቹም የሚበቃውን ያህል ስጡት ብሎ አሰናበተው፡፡
ይህ ሰው ወደ ቀየው ሲመለስ አንድ ወዳጁ ይሄን ሁላ ሀብት ከየት እንዳገኘ ይጠይቀዋል፡፡ ተመፅዋቹም ሁሉን ነገር ነገረው፡፡ ከዛ ባልንጀራው እንደሱ ሀብት ለመቀበል ወደ ባለጠጋው ሰው ሄደ፡፡
እዛም እንደደረሰ "ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡
ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከበሬ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡
ነዳያኑም "ቆዳው" አለ፡፡
ባለጠጋውም አንተ አጭበርባሪ ነክ ብሎ በባዶ ሰደደው፡፡
የፈለገ ብንቸገር መዋሸት ግን አይሆኑ ውድቀት ላይ ይጥለናል፡፡

የኮሮና ቫይረስን እጅን በመሳም አጠፋለዉ ያለዉ ህንዳዊዉ የሀይማኖት መሪ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ
በፓርዲያሽ ግዛት ራትላም በተባለች አዉራጃ ነዋሪ የሆነዉ የመንፈሳዊ መሪ አስላም ባባ ለተከታዮቹ በተለይም ለሴቶች እጆቻቸዉን በመሳም ብቻ የኮሮና ቫይረስን እንደሚፈዉስ
ይናገራል፡፡
ይህንን የሰሙ 40 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ላለመያዝ በሚል እጃቸዉ እንዲሳምላቸዉ ወደ ስፍረዉ ያቀናሉ፡፡
እጃቸዉ በባባ አስላም ከተሳመላቸዉ 40 ሰዎች መካከል 20 ያህሉ በቫይረሱ መያዛቸዉሲረጋገጥ ሰባቱ የመንፈሳዊዉ መሪ አስላም ባባ ቤተሰቦች መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡
የቫይረሱ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በቅርበት ሲያገኝ የነበረው ባባ አስላም እርሱ በቫይረሱ ይያዛል፡፡ህክምና ቢያገኝም ማገገም ሳይችል ህይወቱ ማለፉን የህንድ ሚንስቴር ይፋ አድርጓል፡፡
ልክ እንደ አስላም ሁሉ ከወራቶች በፊት የጤናናይጄሪያዊዉ ፓስተር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ቻይና ሄጆ አጠፋዋለሁ በማለት ወደ ቻይና በመጓዝ ቫይረሱን አጠፋዋለሁ ቢልም በቫይረሱ ህይወቱ አልፎ ስርዓቱ ቀብሩ በቻይና ተፈጽሟል፡፡
⊰━━━━━━⊱🌸⊰━━━━━━⊰
Share | @ketibeb
⊰━━━━━━⊱🌸⊰━━━━━━⊱

👍3
የ ኑራ ልጅ ኒዐም
ውድ አንባቢያን የዚህchannel አላማ በምንፅፍቸው ግጥሞች እና ልቦለዶች በገሀድ የምናየውን ሁኔታ በጥበበባዊ መንገድ ለህብረተሠብ ማድረስ ነው
https://telegram.me/yanuralij

✍ #ይህ #ቻይናዊ ገበሬ ከአመታት በፊት ባጋጠመው የኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ሁለት እጁን አጥቷል ።
↘️ነገርግን ህይወትን ለማሸነፍ ነገሮችን ሁሉ በእግሩ በመከወን እራሱን ከመቻሉም በላይ በቁጥር በዛ ያሉ ከብቶችንም ማፍራት ችሏል።
↘️እና የዚህ ታታሪ ሰው እናት ሁለመናቸውን ማንቀሳቀስ በማይችሉበት ደረጃ ይታመማሉ በዚህ ጊዜ ይህ ሰው እናቱን ለማስታመም እንደ እጅ በሚያገለግለው በእግሮቹ የሰራውን ምግብ ማንኪያ በአፉ ይዞ ለእናቱ ያጎርሳል።
💐💐እናትየው በቃኝ ብለው ጭንቅላታቸውን እስከሚነቀንቁ ድረስ በየእለቱ ማንኪያ ጎርሶ እናቱን ያጎርሳል ፣ #ሰው #ያለውን ነውና የሚሰጠው ለዚህ ተግባሩ long live to both of dem.
Join
@ketibeb

👍1
📜መኖርን ባልታሰበ✍
ክፍል አንድ
በከድር አወል
በ( @KETIBEB) የተዘጋጀ
.... ከወትሮ ለየት ያለ የወፎች ዝማሬ አይሉት ጫጫታ እንቅልፌ መተኛ አሳጡኝ ይባስ ብለው ድምፃቸው እኔ ወደተኛሁበት እየቀረበ መጣ ይሄ ደግሞ የሆነ ባዕድ ነገረ እየመጣ መሆኑን ያስረዳል ወዲያውኑ ደመነፍሴን በፍጥነት የተንተራስኩትን ታጣፊ ክላሼን አቀባብዬ ፊቴን በእጄ እየጠራረኩ በቅጠል ከታጀበ ዋርካ ዛፍ ወደ ጫፍ ተንጠላጥዬ ቁጭ አልኩ እና፥ አካባቢውን በአይኔ ማሰስ ጀመርኩ፤ በአንደኛው የጫካው አቅጣጫ ከሩቅ በፀሀይ መውጣት የደነገጠ በሚመስለው ጉም መሀል፥
በከዘራው መንገዱን የሚያሰናክሉትን የጫካውን ሀረገ እየከፈተ እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ የሚመጣ ሰው ይታየኛል፧ እንደ መደናገጥ እያልኩ ምን አልባት እኔን ለማጥቃት የተላከ ሰው ይሆናል ብዬ ካለሁበት እስኪደርስ በተጠንቀቅ መጠበቅ ጀመርኩ ፡
በተንጠላጠልኩበት ዋርካ ሲደርስም ከስሩ ከሚፈሰው ምንጭ ውሃ ጎምበስ ብሎ በእጁ እየጠለፈ የሚበቃውን ያህል ከጠጣ ቡሀላ፤ በረዥሙ ተነፈሰ ከዛም በአይኑ አካባቢውን ከቃኘ ቡሀላ ጠፍጣፍ ዲንጋይ ላይ አረፍ አለ ጉዞውን መቀጠል የሚፈልግ አይመስልም፤ እኔ ቀስ ብዬ ኮሽታ ሳላሰማ ከዛፉ ወረድኩ እና በቅንጭላቱ ትክክል አነጣጥሬ ኮስተር ባለ ድምፅ ጮክ ብዬ እንዳትንቀሳቀስ አልኩት፤ ቢንቀሳቀስ ግን ምን ላደርገው ነው ልተኩስበት ኧረ..ምንነቱን ሳላጣራ እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ፤ሰውዬው ግን ምንም የመደናገጥ አይነት ስሜት አይታይበትም ይባስ ብሎ እንደ ሬሳ ደርቆ ዝም አለ፤ እኔም ደግሜ ማን ነው የላከህ ! ብልም እንኳን ሊናገር ዞሮም አላየኝ ፥ ግራ በታገባ ስሜት ምን አልባት ጆሮው አይሰማ ከሆነ ብዬ ከወደ ፊት ለፊቱ ሄድኩና ግምባሩ ላይ ደቀንኩበት፤ የዛኔ አንገቱን ቀና አደረገና ""ምን ፈለክ ልትገለኝ ነው፥ አትፍራ ተኩስብኝ እንደውም ከዚህ ከማይረባ አለም ገላግለኝ አለ፧ ቁጭት በተሞላበት ድምፅ፤ ይሄኔ ተስፍ መቁረጥን አቃታለሁና በትንሹም ቢሆን አሳዘነኝ :ምን ሆኖ ይሆን በዚህ እድሜው ምን አይነት ችግር ቢገጥመው ነው እዚህ ድረስ የመጣው፥ ጥሩ ኑሮ ኗሪ እንደሆነ ከልብሱና ከፊቱ መለየት ይቻላል!
ከ50-60ዎቹ ባሉት ኤድሜ ውስጥ እንዳለም መገመት አያዳግትም ፥ ግን! ያም ሆነ ይህ የሰውየውን ምንነት ስለማላውቅ፤ ብዙ ላወራው አልፈለኩም ምን አልባት እኔን የሚፈልጉኝ ሰዎች በኔ ላይ እንዲተውንብኝ ልከውት ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ከአካባቢው ለመሰወር ወሰንኩ ትቸው መሄድ ስጀምር በድጋሜ መናገር ጀመረ ""ምን ነው ወጣቱ? ድፍረት አጣህ ለነገሩ ገና ልጅ ነህ ሽፍታ እንዳልሆንክም እኔን እንኳ በቅጡ ማስፈራራት አልቻልክም ጥሩ ልብ ያለህ ትመስላለህ አለኝ"" ቆም ብዬ ካዳመጥኩ ቡሀላ ከሱ ጋ ብቆይ ጉዳት ሊያደርስብኝ መቼም አቅም አይኖረውም ብዬ አሰብኩና፥ መንገዴን ትቼ ወደ ሰውየው ተመለስኩ፤ ከሱ በቅርብ ርቀትም ቁጭ አልኩ፥ በመካከላችን ረዘም ያለ ፀጥታ ሰፈነ በድንገት ከኛ በተወሰነ ርቀት አንድ ድኩላ ብቅ አለ በፍጥነት አነጣጥሬ ተኮስኩበት እየሮጥኩ ስሄድም እየተፈራገጠም አገኘውት ጩቤዬን አወጣሁና አረድኩት ከዛም ተሸክሜ ወሰድኩና መቃፈፍ ጀመርኩ!
ቅድም ግን ድንገት ስተኩስ አደነጋገጡ ትዝ አለኝ እና ፈገግ እያልኩ ወደሱ ስዞር፤ ወደ ኪሱ ገባ አለና ብስኩት ነገር አውጥቶ እንድቀበለው እጁን ዘረጋ ቀጥ ብዬ አይቼ ፍላጎቴን ሳልገልፅ አትኩሮቴን ወደ ስራዬ አደረኩ ሀሳቤን የተረዳ መሰለኝ ከመሀል አንድ አውጥቶ ለራሱ በላና አሁንስ አለኝ! ትንሽ ስለራበኝ ሳላንገራግር ተቀበልኩ ያን እየበላሁ ስራዬን እየሰራው ሳለ በመሀል አየህ ወጣቱ ሰው ማለት እንደ ታዳኝ እንሰሳ ነው አለኝ፥ እያናገረኝ ዝም ማለቱ ጥሩ አይለም በዛ ላይ የትልቅ ሰው ምክር የሚባል ነገር አለ ዘወር ብዬ....እንዴት? አልኩት.. ምክንያቱም ምን ጊዜም በወጥመድ ውስጥ ነው ለማደግ ስትፍጨረጨር ለምን ብሎ ይመቀኝሀል የቻለውን ያክል ሊጥልህ ይሞክራል እንደምንም ተቋቁመህ ካለፍክ ይበልጥ ይበሳጫል እናም አንድ ቀን ልታመልጥበት የማትችል ወጥመድ አዘጋጅቶ አነጣጥሮ ይተኩስብሀል ከዛም ደካማ ጎንህን ተጠቅሞ ይጥልሀል በቃ ሰው እንደዚህ ነው አለ፧፧ ከዚህ ቅኔ ጀርባ የሆነ ታሪክ እንዳለ ተረድቻለሁ ስራዬን ገታ አደረኩና ግን አንተ ማን ነህ? ማለቴ ምን አይነት ችግር ቢገጥምህ ነው ወደዚህ የመጣሀው ከአለባበስህ ደህና ኑሮ እንዳለህ ያስታውቃል አልኩት.....
ራሱን እየነቀነቀ! ምን ያደርጋል ሁሉ ነገር በነበር አለቀ አለ ሲቃ በተሞላበት ድምፅ ስሜት!
ምን አልባት ትምህርት ሊሆን ይችላልና ከልብ አዳምጠኝ ብሎ ትረካውን ጀመረ እኔ ማለት.......
‼ከወደዳችሁት ይቀጥላል😘‼
ሰሞኑን ስለጠፍን ይቅርታ እንጠይቃለን🙏
አስተያየት>>>> @ketibebot