ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
ዘርህ ካላማረ፣ቆዳህም ካልነጣ፣
በእግር ይበየናል፤የመሰንበት ዕጣ!
በበዳይህ ስሌት፣በአሳሪህ አቋም፣
መተንፈስ ለመቻል
ሰው መሆን አይበቃም(!)(?)

#ፈረሀን
Luk 33

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
"ለምን ሞተ?" ቢሉ
እንደዚህ ብላችሁ ፣ ንገሩ ለሁሉ
ሳትሸፋፍኑ ፣ ሳትደብቁ ከቶ
"እጁን በሳሙና ፣ ሳይታጠብ ቀርቶ
አትሰብሰብ ሲሉት ፣ ስብሰባ አብዝቶ
የትም ሲንጦሎጦል ፣ ቤት መሆንን ጠልቶ
ከሰው ተጨባብጦ ፣ ከሰው ተጠጋግቶ
ከምክር ተኳርፎ ፣ ከተግሳፅ ተጣልቶ
ዘመድ መገኖቹን ፣ ለክፎ ለሞት አጭቶ
ሞተ በቃ ሞቶ።
።።።
#Faysal Ahmed
Luk 35

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
ወንጀላችን በዝቶ መቶበት ሢሳነን
የአምላክ ቁጣ መጥቶ ይሀው ተሠቃየን
‼️
በአይን እማናያት በትንሽ ፍጥረት
የት እንኩዋን እንደምትኖር ያላወቅንላት
🔥
በአየር ላይማትቆይ ለብዙ ሰአት
ምድርም ካረፈች ነብሷ ሚለያት
🦠🦠🦠
#COVID19 ብለው ሰየሟት
አሏህ ይጠብቀን በሱዋ ከመሞት!!

#ጌታዬ
Luk 36

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
ሀሊማ ክፍል ① በሂክማ ጀማል ፡ ፡ "ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠችው ነው የምንኖረው" . ዛሬም እንደ ወትሮዋ ከእኩዮቿ ጋር ለመጫወት ከ ቤት ወጥታ ወደ ጓደኞቿ ጋር ሄደች፡፡ ሀሊማ በጣም ተጫዋች ደስተኛ እና ሁሉም ሰው የሚወዳት አይነት ልጅ ናት የተወሰነ ሰአት ከተጫወተች ወዲህ እረሀብ ቢጤ ተሰማት ያው የልጅ ነገር እረሀቡን…
"ሀሊማ"
ክፍል 2
ሂክማ ጀማል




......አባቴ መናገር ጀመረ ግን እኔ እንደጠበቁት ሳያሆን የበለጠ እንደገደላት የሚያረጋግጥ ነገር ነበር የተናገረው
"ሰሙ ልክ ነሽ "አለ ግን..... ሲል እንዳትጨርሰው
"ምንም ግን የሚባል ነገር የለም ባይሆን ሬሳዋን ምን እንደምናደርገው እናስብ" አለችው፡፡
...."እሺ ልጆቼስ "አላት "ለእነሱ እኔ አለሁ ደግሞ ተነጋገርንበት አይደል" አለችው ፡፡
..........አባቴ በጣም በጨነቀው ድምፅ" እሺ ለ ሀሊማስ እናቴስ ካለችኝ ምን ልላት ነው?"
........"የሆነ ምክንያት እንነግራታለን ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ክፍለ ሀገር እንደ ሄደች ወይም ሌላ ምክንያት እንነግራታለን"አለችው
ሌላ አማራጭ ስለሌለው እሺ አላት ይህንን ሀሊማ ስትሰማ ምድር የተደፋባት የህል ነበር የተሰማት በሩን ከፍታ ወደ ወስጥ ገብታ የእናቷን ሬሳ ለመንካት፣ ድጋሚ የማላገኛት ከሆነ ልሳማት ብላ አስባ በሩን ጠጋ ለማድረግ ስትሞክር ሰሚራ እጅ ላይ ያለውን ብረት ተመለከተችው፡፡እናቷን ብረቱ መትታት እንደገደለቻት ስትናገር ሰምታለች የእናቷ እጣ ለ እሷም እንዳይደርሳት ፈራች፡፡ ልትከፍተው የነበረውን በር መልሳ ተወችው የእናቷን ሬሳ ለመደበቅ ሲዋከቡ አየቻቸው፡፡ ሞት ማለት ምን እንደሆነ በማታውቅበተ እድሜ ላይ ሆና በንጹህ አእምሮዋ የ እናቷን አሰቃቂ ሞት፣የ አባቷ ጭካኔ አየች፡፡ አባቷ ይህ ሁሉ ሲሆን ሀሊማ እንደማታውቅ ነው ያሰበው፡፡ ከመኝታ ቤቱ ለመውጣት ሲሞክሩ ሀሊማ በሞተ አቅሟ እተንቀጠቀጠች ቤቱ ለቃ ወጣች፡፡ በጣም ስለደነገጠች ሰውነቷ ደርቆዋል ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም፡፡ እንዲሁ እግሯ ወደ መራት አቅጣጫ መሄድ ጀመረች ረጅም መንገድ ከሄደች በሃላ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግራ ገብቷት አንድ ጥግ ላይ ተቀምጣለች፡፡

.....እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሀሊማ በተቀመጠችበት መንገድ የሀሊማ
የእናቷ የቅርብ ዘመድ የሆነችው ፋጡማ በዚያ መንገድ ስታልፍ ሀሊማን በ አትኩሮት ተመለከተቻት ሀሊማ ግን ቀድማ ፉጡማን አይታታለች ግን ማን እንደሆነች ማገናዘብ አልቻለችም፡፡ ፉጡማም ግራ በተጋባ ሁኔታ አየቻት ፊቷ አዲስ አልሆነባትም በደንብ ለማየት ሞከረች ግን የሀሊማ ሂጃብ ስለተዝረከረከ ከፊል ፊቷን ሸፍኗታል፡፡ማን ትሆን እያለች ማሰብ ጀመረች እንደዚ ትንሽ ልጅ የት ነው የማውቀው ብላ ትንሽ እንደማሰብ ካለች በኃላ የ አክስቷ ልጅ የሆነችው ዘይነባ የሷ ልጅ ሀሊማ ትሁን ብላ አሰበች ሀሊማ ብትሆን አይታኝ ዝም አትለኝም፡፡እንኳን እንዲ አይታኝ በ ስልክ እራሱ እንዴት እንደምትሆን እያለች ብቻዋን እያወራች ደግሞ እዚህ ድረስ ምን ልትሰራ መጣች በዛ ላይ ብቻዋን አይ እሷ አይደለችም ብላ አልፋት ሄደች፡፡
:
:
ክፍል 3
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
የፈቲ ባል …….ክፍል 11 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 11◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
"ሀሊማ"
ክፍል 3
ሂክማ
:
:

....የተወሰነ መንገድ ከሄደች በኃላ ግን ውስጧን የሆነ ነገር ከነከናት፡፡ እና ልጅቷ ምን ሆና ይሁን ብላ አሰበች፡፡ ለምን ሄጄ አልጠይቃትም ብላ ትንሽ ቆም ብላ አሰበችና ወደ መጣችበት መንገድ ተመለሰች፡፡ ነገር ግን ሀሊማ ከነበረችበት ቦታ ለቃ ሄዳለች፡፡ ፋጡማ በጣም ተናደደች ለምን መጀመሪያ ሄጄ አላናገርኳትም ብላ እራሷን ወቀሰች፡፡ እዛው አካባቢ ዞር ዞር እያለች መፈለግ ጀመረች ወደ አንዱ አቅጣጫ ስትመለከት ሀሊማ በተዳከመ አቅሟ እየተጎተተች እየሄች ተመለከተቻት ፡፡ በጣም ቢራራቁም ማየት ችላለች ፡፡
.
በፍጥነት እየተራመደች እርቀታቸውን እያጠበበች ሄደች በጣም ስትቀርባት "ሚጣ.....ሚጡ .... ኧረ ሚ....ጡ.... "እያለች ተጣራች ሀሊማ ግን ጭራሽ አልሰማቻትም አሁንም እየሄደች ነው፡፡ ፈጡማ ከመጀመሪያው በላይ በጣም እየፈጠነች የሞት ሞቷን አጠገቧ ደረሰች፡፡ "እንኪ ሚጡ" ብላ እጇን ይዛ ወደ እራሷ ስታዞራት ጭራሽ ያላሰበችውን ነገር ነበር ያየችው "ሀ..ሊ..ማ" አለቻት ምንም መልስ አልሰጠቻትም እራሷን ለማረጋጋት እየሞከች "እዚህ ብቻሽን ምን ታደርጊለሽ ?"አለቻት የሀሊማ ያለወትሮዋ ዝም ማለቷ እየገረማት አላወቅሽኝም እንዴ ፋጡማ አክስትሽ እኮ ነኝ ምንም አይነት መልስ የለም፡፡ በሁኔታው ግራ እንደተጋባች ፋጡማ ቤቷ እዛው እቅራቢያ ስለነበር ይዛት ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ ሰውነቷ ጠውልጎዋል ከንፈሯም ከሚባለው በላይ ደርቆዋል ፋጡማም ፊቷን ፣እጇን እና እግሯን አጠበቻት፡፡ሀሊማ ከቅድሙ ትንሽ እንደ መንቃት እያለች ነው ወደ ውስጥ ይዛት ገብታ የሚበላ አቅርባላት እያበለቻት ሳለች ስልኳን አንስታ ወደ አባቷ ጋር ለመደወል "ቤት ልደውልላቸው አይደል?" አለቻት አንገቷን በመነቅነቅ እንዳትደውል በምልክት ነገረቻት፡፡ "እሺ ቤት አልደውልም ግን ምን እንደሆንሽ ንገሪኝ" አለቻት ምን ብላ ትንገራት ዝም አለቻት፡፡ "እሺ በቃ ልደውል ነው"ስትላት ሀሊማ በድንገት እንባዋ እንደ ጉድ መውረድ ጀመረ መናገር ትፈልጋለች ግን አፏ ተሳስሮባታል፡፡

ፍጡማ በሁኔታዋ ትንሽ ተረበሸች፡፡ "እሺ በቃ ተይው አትነገሪኝ" ብላ ከተቀመጠችበተ ተነስታ ሀሊማ አጠገብ ሄዳ እቅፋ አባበለቻት በጣም እርቧት ስለነበር የበላችው ምግብ አደካከማት፡፡ ገና አቅፋት ጸጉሯን ማሻሸት እንደጀመረች እንቅልፍ ይዟት ሄደ ፈጡማም ሀሊማ እንደተኛች ስታይ አስተካክላ አስተኝታት የሀሊማ አባት ጋር ለመደወል ስልኳን ይዛ ወጣች::
:
:
:
ክፍል 4
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
የፈቲ ባል …….ክፍል 12 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል-1
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 12◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒
የመጨረሻ ክፍል ነገ ማታ ከ100👍 ቡሀላ ይለቀቃል
➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
"ሀሊማ"
ክፍል 4
ሂክማ ጀማል
:
:

ለመደወል ስልኳን ይዛ በሩን ጠጋ አድርጋላት ወጣች፡፡ "ልደውል ወይስ ይቅር ሀሊማ ልደውል ስላት ለምን አለቀሰች?አባቷ ጋርእንድደውል ለምን አልፈለገችም? ለነገሩ አባቷ ጋር ከመደወል ዘይነባ ጋር መደወል የተሻለ ይመስለኛል፡፡" ብላ አሰበች "ግን ደግሞ ምን ልትሰራ እዚህ ድረስ መጣች ለዛውም ብቻዋን" ብዙ ጥያቄዎች አእምሮዋ ውስጥ ተፈራረቀባት፡፡ ግን ለማንኛውም አባቷ ጋር ከመደወል ዘይነባ ጋር መደወል የተሻለ ነው ብላ አሰበች፡፡

091325...... የዘይነባን ስልክ ቁጥር ተጭና መደወል ጀመረች ይጠራል ከአሁን አሁን ስልኩ ተነሳ እያለች በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆና እየጠበቀች ነው፡፡

የዘይነባ ስልክ ቻርጀር እንደተሰካ ነው ሰሚራና ከድር ሳሎን ቤት ውስጥ ቁጭ ብለዋል፡፡ከድር ማለት የሀሊማ አባት ነው ዘይነባን ለመግደል ሲያስቡ ነገሩ እንዲህ ከባድ ይሆናል ብለው አላሰብም ነበር፡፡ እስኪመሽ ጠብቀው ሬሳውን የሆነ ቦታ ላይ ለመደበቅ ተስማምተው እስኪመሽ እየጠበቁ ነው፡፡ድንገት ግን የ ዘይነባ ስልክ ሲጠራ ሁለቱም በጣም ደነገጡ፡፡ ሰሚራ ከተቀመጠችበት ተነስታ ስልኩ ወደሚጠራበት ቦታ ሄዳ ስልኩን ከቻርጀሩ ላይ ነቀለችው የተመዘገበ ስልክ ነው ፈጡማ ይላል ብላ ልታቀብለው እጇን ስትዘረጋ "እኔ አንስቼ ምን እንድላት ነው የምትሰጭኝ እራስሽ አንሽው" በዚህ መሀል ሁለቱም እየተጨቃጨቁ ስልኩ ተዘጋ ሰሚራ ስልኩን ይዛ መጀመሪያ ወደ ተቀመጠችበት ቦታ ሄደች፡፡ ከ ጥቂት ደቂቃዎች በሀላ ድጋሚ ስልኩ ጠራ ስልኩን ደፍሮ አንስቶ የሚያናግር ጠፋ ሰሚራ አሁንም ስልኩን እንደያዘች ነው፡፡
ፋጡማ ከመጀመሪያው በላይ አሁን ይበልጥ ተጨነቀች፡፡ የሀሊማ ሁኔታ የስልኩ አለመነሳት አንድ ላይ ሲሆኑ ብዙ መጥፎ መጥፎ ሀሳቦች እንድታስብ አደረጋት፡፡ ኧረ ምን ሆነሽ ነው ፋጡማ ደግ ደጉን አስቢ እንጂ አለች ፈጡማ እራሷን ለማረጋጋት እየሞከረች ምን አልባት አላየችው ይሆናል ብላ ድጋሚ ስልኩን መደወል ጀመረች፡፡ ከድርና ሰሚራ እንደዛው እንደተፈጠጡ ናቸው፡፡ ፋጡማ ኔትዎርክ አስቸገሯት ደጋግማ እየሞከረች በመጨረሻ ተሳካላት መጥራት ጀመረ ሁለቱም በድጋሚ በጣም ደነገጡ ሰሚራ ከድርን አፍጥጣ እያየችው ነው በ አይኗ አንሳው እያለች ትእዛዝ የምትሰጥ ነው የሚመስለው፡፡ ሰሚራ በከድር ዝምታ ተናዳለች ፡፡ፋጡማ በበኩሏ ኧረ አንሽው ...አንሽው እያለች ነው ሀሊማ አሁንም እንደተኛች ናት ግን ድንገት ሰሚራ ስልኩን ብድግ አድርጋ የማንሻውን ቁልፍ ተጭና ሄለው አለች



ክፍል 5
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍2
Audio
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 13(የመጨረሻ)◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒
➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
ታሪኩ እንዴት ነበር ከወደዳችሁት👍👍👍👍
─── ── ✦ ── ───
👍1
📜 የህይወት ሰሌዳህ ያንተ ብቻ ናት
ቀለሞቿን አንተ መርጠህ ተደሰትባት
ሰውም ሆነ ሁካታዎች በቀለሞቿ ላይ
ተፅእኖ እንዲፈጥሩ በፍፁም አትፍቀድ

» » @ketibeb
"ሀሊማ"
ክፍል5
ሂክማ ጀማል




የማነጋገሪያ ቁልፉን ተጭና ስልኩን አንስታ ሄለው አለችው፡፡ ፈጡማ ስልኩ በመነሳቱ በጣም ተደስታ
."...ሄለው....ሄለው አሰላሙ አለይኪ ዚ አይሰማም አንዴ" አለች
ሰሚራ ምንም አይነት መልስ ሳትመልስ እያዳመጠቻት ነው፡፡ ፋጡማ
"ይሰማም እንዴ ሄለው....ሄለው....ሄለው" አያለች ነው ፡፡ሰሚራ ድንገት አንድ ሀሳብ መጣላት፡፡ ከድር ሁኔታዋ ግራ ገብቶት በዝምታ እየተመለከታት ነው ሰሚራ ብዙም ሳትቆይ
........."ይቅርታ የኔ እህት ዘይነባ የለችም ማለቴ ስልኳ ቻርጀር ላይ ነው፡፡"
"አልገባኝም" አለች ፈጡማ
.."መብራት ስለሌላቸው ቻርጀር ለማድረግ እኔ ጋር አምጥታው ነው፡፡"
........."እና የሰው ስልክ እንዴት ታነሻለች" ሳታሰጨርሳት "በተደጋጋሚ ስለደወልሽ ነው፡፡ ይቅርታ ደና ዋይ "ብላ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘጋችባት፡፡ ፉጡማ በሰሚራ ሁኔታ ተበሳጨች፡፡ ግን አሁን ትንሽ ተረጋግታላች፡፡ ሰላም ነው ብላ አሰበች ፡፡ ከድርና ሰሚራም ትንሽ ተረጋጉ፡፡
..."ግን እንዴት እንዲ ልትያት ቻልሽ" ከድር ነበር ያላት
......"እሱ ምንም ትርጉም የሌለው ጥያቄ ነው፡፡ተወው ይልቅ ደግማ ከደወለች ምን እንደምንላት እናስብ "አለችው ......
ፉጡማ ሀሊማ አጠገብ ሄዳ ተቀመጠች ላለመረበሽ ትንሽ ራቅ ብላ ተቀመጠች ከ አስር ደቂቃ በኃላ ሀሊማ በተኛችበት የሆነ ድምፅ ማሰማት ጀመረች፡፡ ፍጡማ ወደ ሀሊማ ቀረብ ብላ ሁኔታዋን አየች፡፡ እየቃዠች ነው ፊቷ በላብ ተጠምቋል አሁን ከቅድሙ ይበልጥ የምትናገረው ነገር ይገባል፡፡ "ኡሚ.... ኡሚ.....ኡሚ "እያለቸ በመጣራት እያለቀሰች ነው ፈጡማ ነገሩ ስላስፈራት ቀሰቀሰቻት፡፡ ሀሊማ ከ እንቅልፏም ነቅታም እያለቀሰች ነው፡፡ ምን ነው ሀሊማ በህልምሽ ምን አይተሽ ነው እስቲ ንገሪኝ እያለች ለማግባባት ሞከረች፡፡ ሀሊማም ከረጅም ዝምታ በኃላ ኡሚ... ብላ ዝም አለች ኡሚ ምን ንገሪኝ የኔ ቆንጆ ሀሊማ ያየችውን ለመናገር ስትሞክር እናቷ እንደሞተች አስታውሰች፡፡ በድጋሚ አለቀሰች በቃ ተይው አትንገሪኝ አለቻት፡፡
ሰአቱ እየመሸ ነው 11፡45 ሆኖዋል ፡፡ የ ሀሊማ እህትና ወንድሟ እያለቀሱ ነው ሰሚራ እንደምንም አባብላ ምግብ አብልታ አስተኛቻቸው ፡፡ ያኔ ነበር ከድር ሀሊማን ያስታወሳት፡፡"ሰሙ ሀሊማ እኮ እስከ አሁን አልመጣችም" አላት "እውነትህን እኮ ነው የት ሄዳ ነው?" አለችው "እስቲ ጓደኞቿ ጋር ሄጄ ልጠይቅ" ብሎ ከቤት ወጣ፡፡ አብራቸው የምትውለቸው ጓደኞቿ ጋር ሄዶ ቢፈልጋትም ሊያገኛት ስላልቻለ ወደ እቤት ተመለሰ፡፡ ሁኔታውን ለ ሰሚራ ነገራት ሰአቱ እየሄደ ነው ምን ሆና ይሁን የት ሄዳ ነው እየለ በመጨነቅ እየጠበቃት ነው 4፡00 ሆኖዋል ግን አልመጣችም በጣም ተጨንቋል ድንገት ሰሚራ" ተነስ... ተነስ "አለችው
..."ምነው" .. "ምነው ትላለህ እንዴ ሬሳውን የሆነ ቦታ እንውሰደው እንጂ" እሺ ብሏት ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ መኝታ ቤቱ አብረው ሄዱ ሬሳውን እንደነገሩ በጨርቅ ጠቅልለው ለማንሳት ሲሞክሩ ከድር ጉልበቱ ከዳው፡፡ ከ ዘይነባ ጋር ያሳለፉት ምርጥ ጊዜዎች ውል ብለው ታዩት ድንገት እነባዎቹ ጉንጩ ላይ ዱብ ዱብ ማለት ጀመሩ ሰሚራ በአንድ ጊዜ ፊቷ ተቀያየረ ፡፡ ለምንድ ነው እኔ ጨካኝ አንተ ደግሞ የዋህ እንደሆንክ የምታስመስለው ፡፡ብላ ጮሀችበት እሺ እሺ አላት ለማንሳት እየተዘጋጀ መሸከም አቃታቸው እንደምንም ታግለው ከ ቤተ አወጡት ከቤቱ ጀርባ ክፍትቦታ ላይ የተወሰነ ከቆፈሩ በሃላ ሬሳውን አስቀመጡት ከላዩ ለይ አፈር አለበሱት፡፡ ......በወጉ እንኳ ሳትገነዝ ሳትታጠብ ሳይሰገድባት እንደ እንስሳ በአንድ ብጣሽ ጨርቅ ጠቅልለው ጣሏት፡፡
.
ፋጡማ እስከ አሁን ድረስ ለምን መልሳ አለደወለችም እያለች ተጨነቀች፡፡ ስልኳን አንስታ ልትደውለ አስባ ትንሽ ልጠብቅ ብላ ስልኩን ወደ ነበረበት መለሰችው ሀሊማ የተወሰነ ሰአት ትተኛና ብዙም ሳትቆይ ትነቃለች ፡፡ ቀን ያየቸው የእናቷ ሁኔታ ማታም እንቅልፍ ነሳት ፋጡማ ድጋሚ ልጠይቃት አስባ ግን ድጋሚ እንዳታለቅስ ስለፈራች መጠየቁን ተወችው እቅፏ ውስጥ አድርጋት ተረጋግታ እንድትተኛ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ አላገኘችም፡፡



ክፍል 6
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍2
ሀሊማ
ክፍል 6
ሂክማ ጀማል



ሰሚራ አሁን ትንሽም ቢሆን እፎይታ ተሰማተ፡፡ መጅሊሱ ላይ ተደለድላ ደገፍ ብላ ተቀመጠች ከከድር ፊት ለፊት ዘይነባ እንደምትቀመጠው ተቀምጣለች፡፡ ከድር የልጁ ጉዳይ በጣም አስጨነቀው ሰሚራ ገና በመጀመሪያ ቀን እንዲ ግዴለሽ መሆኗ ገረመው፡፡ "ዛሬ በጣም ከባድ ቀን ነው ያሳለፍኩት እራት ለቅርብ? ደክሞኛል ልተኛ ነው" አለችው ምንም አይነት ነገር አልመለሰላትም "አታወራም እንዴ "በዝምታ ይመለከታታል እንጂ መልስ አልሰጣትም፡፡ መብላት ስትፈልግ ንገረኝ ብላው ወደ መኝታ ቤቱ ሄደች ሁሉም ነገሯን ከ ዘይነባ ጋር እያመሳሰለ ነው ይሄኔ ዛይነባ ብትሆን ከድር ዝም የሚለው ሲከፋው እንደሆነ ስለምታውቅ አጠገቡ ሄዳ "ወዴ ምነው ማን ነው ያስከፋብኝ ንገረኝ ለሰው ሲነግሩት ይቀላል" እያለች እንደ ህፃን እያባበለችትጠይቀው ነበር፡፡ እሱ ግን እሱን ለመቆጣጠር አድርጎ ነበር የሚያስበው፡፡ ያኔ በመለሰላት መልስ አሁን ፀፀተው፡፡ ሰሚራ የዘይነባን ያአዳር ልብስ እና የእሷን ፎጣ ለብሳ ምንቅር ምንቅር እያለች ወደ ሳሎኑ መጣች፡፡ ከድር ልክ እንዳያት ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ ተነሳ፡፡ሰሚራም ግራ ገብቷት ምን ነው አለችው፡፡ ከድር ገና ዘይነባ ከሞተች 24 ሰአት ሳይሞላ ስራው የፀፀተው ይመስላል፡፡ "ኧረ ምነው " ደገመችው አውልቂ ብሎ ፎጣውንም ቢጃማውንም አውልቆ ቢወስድባት ምኞቱ ነው፡፡ ግን አልቻለም መልሶ ተቀመጠ፡፡"ሰውዬ ምን እየሆንክ ነው" ዘይነባ እንዲ ብላው አታውቅም አይኑ እንባ አቀረረ እሱም በተራው ወደ መኝታ ቤቱ ሄደ ፡፡ግን ሌላ ቀን ወደ መኝታ ቤቱ ሲገባ የሚያውደ ጥሩ መአዛ ያለው የሚስቱ ሽቶ ዛሬ የለም አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ በፈገግታ የምትቀበለው ሚስቱ ዛሬ የለችም፡፡ መኝታ ቤቱ የተለቀቀ ቤት መስሏል፡፡ መጋዘን መስሏል አልጋው ጫፍ ለይ ተቀምጦ ከ ልብ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፡፡ ከዘይነባ ውጪ ማንም ሊረዳው እንደማይችል አሁን ነው የገባው፡፡ ግን ምን ያደርጋል ይቅርታ ጠይቆ እንኳ ወደ ማትመለስበት ሀገር እራሱ ሸኛት! በእጅ ያለ ወርቅ .......አለ ያገሬ ሰው
ከድር ፊቱን ታጥቦ ተመለሰ፡፡ ሰሚራ እዛው እንደተቀመጠች ናት፡፡ ቦታው ላይ ተመልሶ ተቀመጠ ሰሚራ የጎሪጥ እያየችው "ሰአቱ እየሄደ እኮ ነው እንተኛ እንጂ" አለች በሁኔታዋ በጣም ተበሳጨ እንዲ ይሆናል ብሎ አልጠበቀም ነበር ፡፡በጣም ደስተኛ እንደምታደርገው ነበር ስትነግረው የነበረው ግን አሁን እንኳን ደስተኛ ለማድረግ እንደ ባል እራሱ ልታከብረው አልቻለችም ልክ እንደ ታናሽ ወንድሟ ነው የምታናግረው ድጋሚ ልታወራ ስተዘጋጅ "ይበቃኛል! ዝም አልኩሽ እኮ ለምን አይገባሽም መብላት ከፈለግሽም ቢይ መተኛት ከፈለግሽም እንደዛው" ብሏት አንገቱን ደፎቶ ማሰብ ጀመረ፡፡
"እንዴ አንተስ አለችው" ሰሚራ
...." ሚስቴም ልጄም አጠገቤ የሉም እንዴት ነው እንደቀላል ያየሽው"
.... "የሚስትህን እንኳ ተወው ባይሆን ልጅህን ብትል ያምርብሀል"
..."እንዴት ማለት"
"ወደህና ፈቅደህ መስሎኝ እስከመጨረሻው የሸኘሀት" በስራው በጣም አፈረ ያቺ ሚስኪን ሚስቱ አነጋገሯ ትህትናዋ ፈገግታው ሁሉ ነገሯ ናፈቀው ፣ ሰሚራ እሱ እንደተቀመጠ ትታው ለነገሩ ያህል ምግቡን ቀመስ ቀመስ አድርጋ ገብታ ተኛች፡፡ "ሀሊማ የት ነሽ የኔ ልጅ" እያለ ማልቀስ ጀመረ ሰሚራ ለጥ ብላ ተኝታለች .....
ሰአቱ ከለሊቱ 8፡00 ይላል ፋጡማ ሀሊማን እንዳቀፈች እንቅልፍ ይዟት ሄደ ሊነጋጋ ሲል ከድር እንቅለፍ ሸለብ አደረገው፡፡ ብዙም ሳይቆይ ነቃ ድጋሚ እንቅልፍ ሸለብ አደረገው አሁንም ነቃ ዘይነባ በህልሙ እየመጣች እንቅለፍ ነሳቸው፡፡ትንሽ ቁጭ እንዳለ የሱብሂ አዛን ተአዘነ እንደ ማይነጋ የለም ነጋ ፡፡ ፈጡማ ቁርስ ለመስራት ሽር ጉድ ማለት ጀመረች ሀሊማ ከነገጋ ወዲህ ነው ጥሩ እንቅልፍ የወሰዳት ሰሚራም ቁርስ ሰርታ አቀረበች እሷ መመገብ ጀመረች እሱ ግን የሚጠብቀው ነገር እንዳለ ነገር ምግብን አይን አይኑን ያየዋል፡፡"ብላ እንጂ" አለችው ሰሚራ
ሊናገራት ቀና ሲል ሰሚራ ናት ዘይነባ ብትሆን የመጀመሪያ ጉርሻዋ ለሱ ነበረ ከ እሷ ቀጥላ ሀሊማ እኔም ካለጎረስኩ ብላ ታጎርሰው ነበ፡፡ር እሱም እንደዘው ለሁለቱም ካጎረሰ በኃላ ነበር የሚበለው ዛሬ ግን የሚያጎርስም ጎራሽም የለም ውስጡ በሀዘን ኩምሽሽ አለ ምግብን ትቶ ተነሳ አትበላም እንዴ በቃኝ ብሎ ልብሱን ለመቀየር ወደ ወስጥ ገባ አሁንም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ነው የገጠመው ሁሌም የሚለብሰውነ ልብሰ ዘይነባ ነበር መርጣ የምታስቀምጥለት ከ ለበሰ በኃላም እሷ ነበር የምታስተካክልለት ዛሬ ግን ከ የት ይምጣ .......
ሀሊማ ትንሽ ረፈርፈድ ሲል ከ እንቅልፏ ነቃች ፈጡማ ያዘጋጀችላትን ምግብ በላች፡፡ መጣሁ አሺ እሰከዛው ቴሌቨዥን እያየሽ ጠብቂኝ ብላ ወጣች ከድር ወደስራ የሚሄደው እንደወትሮው ለመስራት ሳያሆን ትንሽም ቢሆን ከተረጋጋሁ ብሎ ነው፡፡ የሀሊማ እህትና ወንድም አሁንም እያለቀሱ ነው ሌሊት ለይም በጣም ሲያለቅሱ ነበረ አባብሎ ለማስተኛት እየሞከረ ነበር፡፡ ለነገሩ ማን እንደ እናት ይሆናል ሊነጋጋ ሲል ነበር የተኙለት እነርሱን ለማስተኛት ሲሞክር ነበር ሰውነቱ የዛለው ለዚህም ነው የተወሰነም ቢሆን የተኛው ፡፡
ፋጡማ ከ ቤቱ የተወሰነ እራቅ ብላ ዘይነባ ጋር በድጋሚ ደወለች በሰአቱ ከድር ወደ ስራ ለመሄድ ዝግጅቱን ጨርሶ በሳሎን ቤት በኩል ለመውጣት በሩ ላይ እንደቆመ ነበር የዘይነባ ስልክ መጥራት ጀመረው፡፡ መውጣቱን ትቶ ወደ ውስጥ ተመልሶ ገብቶ ስልኩ ወደ ሚጠራበት አቅጣጫ ተመለከተ ስልኩን ሰሚራ ይዛዋለች
...ማን ነው?አላት
..... የትላንቷ ሴትዮ ናት
ከድር" ስጪኝ ሰጪኝ"
"ምን ልትላት"
"የምላትን እኔ አውቃለሁ"ሁኔታው ስላላማራት
አልሰጥህም ምን እንደምትላት ካልነገርከኝ አልሰጥህም አለችው፡፡
.... "ኧረ ሊዘጋ ነው ስጭኝ"
..... "አይቻልም አለች" ከድር ተናዶ በጩሀት ያደረኩትን ሀሉንም ነግሪያት ቢያንስ በስነ ስርአት ትቀበር ብሎ ተናግሮ ሲጫርስ ስልኩ ተዘጋ፡፡ ፋጡማ ድጋሚ ደወለች እሺ ነገርኩሽ አይደል አሁን ስጪኝ? ...
:
:
:
ክፍል 7
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
ታሪኩ ተመችቷችሀል😍 ወይስ ሌላ ይጀመር👍
1👍1
"ሀሊማ"
ክፍል 7
ሂክማ ጀማል


ፋጡማ ድጋሚ እየደወለች ነው፡፡ ከድርም ስልኩን እንድትሰጠው እየጠየቃት ነው፡፡ በንግግሩ በጣም የተበሳጨችው ሰሚራ ስልኩ እየጠራ ሳለ በሀይል ወርውራ ከግድግዳው ጋር አጋጨቸው፡፡ ወዲየው ስልኩ ብትንትኑ ወጠ! ከድር እራሱን መቆጣጠር አቃተው ዘሎ ሰሚራን አነቃት፡፡
"ሰው ለመግደል አዲስ አይደለህ ግደለኝ" ስትለው ወዲያው ለቀቃት ከትንሽ ዝምታ በኃላ "ግን ምን ብለህ ነበር ልትነግራት የነበረው እ...እ .."
"ሁሉንም ነዋ"
"ከዛ አንተ ምንም እንዳልነካሀትና ለመግደል እንዳሰብክ ብቻ ልትነግራ ነበር"
ባክሽን ተይኝ!
....ከድር ጋር የፋጡማ ስልክ ቁጥር ስላልነበረው መልሶ መደወል አልቻለም፡፡ ዘይነባ ከፋጡማ ወጪ ሌላ ምንም ዘመድም ቤተሰብም የላትም ፋጡማ ነገሩ ሁሉ ግራ እየገባት ነው ለምን ስልኩ ተዘጋ ለማንኛውም ትንሽ ልጠብቅ ብላ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ከድር ልጁን ፍለጋ ወጣ የት ብሎ እንደሚፈልጋት ግራ ገባው፡፡ የእርሱ ቤተሰቦች ዘመዶችጋር ደወለ ማንም ጋር እንደሌለች አረጋገጠ፡፡ እሷንም እንደ አጣ አሰበ በጣም አዘነ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው ለማን ምን ብሎ እንደሚናገር ግራ ገባው መሄጃ ስላጣ ወደ መስሪያ ቤት ሄደ፡፡ መስሪያ ቤት ሲገባ ሌላ ቀን የሚያሳየው ፈገግታ ዛሬ የለም ፊቱ ጠውልጓል የመስሪያ ቤት ባልደረቦቹ በሁኔታው ግራ ተጋብተዋል ግን ማንም ደፍሮ ምን እንደሆነ መጠየቅ አልቻለም፡፡ ቢሮ ገብቶ ከመቀመጡ የከድር ፀሀፊ የሆነችው ሰአዳ አንኳክታ ገባች ጨረታውን አሸንፈናል መፈረም ያለብህ ወረቀቶች አሉ ፡፡ስትለው ዛሬ ምንም መስራት አልፈልግም ቀጠሮም እንዳተትየዢ "ግን እኮ" ብላ ሳተጨርስ ....ነገ ይደርሳል ሲላት በሩን ዘግታለት ወጣች፡፡ ከድር በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄዷል ዘይነባ ሳትሞት በፊት ከ ሰሚራ ጋር ያበዱበት ፍቅር ሰው እስከመግደል ያደረሳቸው ፍቅር ዛሬ እንዴት እንዲ እንደሆነ ምንም አልገባውም፡፡ ሰሚራን ለ አይኑ እራሱ ጠልቷቷል፡፡ ከሀሳቡ ያባነነው የስልኩ ጥሪ ነበር ስልኩን አውጥቶ ተመለከተው ያልተመዘገበ ስልክ ነበር የስራ ስልክ ነው ብሎ ስላሰበ አላናሳውም፡፡ በድጋሚ ተደወለ በንዴት የማነጋገሪያ ቁልፋን ተጭኖ አነሳው፡፡ "ሄለው" "ሰላሙአለይኩም" .. "ወአለይኪሰላም"
"ማን ልበል"
..."ፈጡማ ነኝ ከድር ዘይነባ ጋር ስደውል ስልኳ አይነሳም ተጨንቄ እኮ ነው ምነው በሰላም ነው?"
....ከድር ለመንገር የነበረው ድፍረት ሙሽሽ ሲልበ ታወቀው
..."ምን ነው ችግር አለ እንዴ"
... "አይ የለም የለም ሀሊማ ትላንት ከወጣች አልተመለሰችም እሱ በጣም አስጨንቆን ነው"
..."ከዚህ ውጪ ችግር የለም?"
"አዎ .......እሱ ከሆነ ሀሊማ እኔ ጋር ናት"
የሰማውን ማመን አቃተው በድጋሚ እንድትነግረው በማሰብ ምን አልሽኝ አላት ፋጡማም ንግግራን ደገመችለት በድጋሚ ሰማ አሁኑኑ መጣሁ ብሎ ቢሮውን ለቆ ወጣ፡፡ ፋጡማ ለሀሊማ ልንገራት አልንገራት እያለች ተጨንቃለች ሀሊማ የልጆች ፕሮግራም እያየች ነው ፈጡማ አጠገቧ ሄዳ ልትነግራት እየሞከረች ሳለች ድንገት በር ተንኳኳ ማን ይሁን ብላ ለመክፈት ወጣች ከድር ነበረ፡፡ በዚህ ፍጥነት መድረሱ ገረማት "ከመቼው መጣህ?" ምንም አልመለሰላትም
"ደና ነሽ እንዴት ነሽ ፋጡማ"
ሰውነቱ እንጂ መንፈሱ ሀሊማ ጋር ቤት ገብቷል ሀሊማን ለማየት በጣም ጓጉቷል ፋጡማም ተረድታዋለች ብዙ ሀተታ ሳታበዛ ወደ ውስጥ እንዲገባ ጋበዘችው፡፡ ከመሮጥ ባልተናነሰ ፍጥነት ወደ እቤቱ ውስጥ ገባ ሀሊማን ሲያያት አይኑን ማመን አልቻለም፡፡ ድንገት እንባዎቹ ጉንጩ ላይ ዱብ ዱብ አሉ ፋጡማ "ኧረ ምን ሆነክ ነው አልሞተችም እኮ አላህን አታማር" ልክ ነሽ ብሎ እንባውን ጠራርጎ ወደ ሀለማ መራመድ ጀመረ፡፡ ሀሊማ አባቷ እንደመጣ አላወቀችውም አላየችውም ........



ክፍል 8
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍2
😔 ሁላችንም ብንሆን
በሆነ መልኩ የተፈተንን ነን‥
ጌታዬ ሆይ! በእያንዳንዱ ህመምተኛ
በህመሙ ላይ እርዳው 😓

» » @ketibeb
"ሐሊማ"
ክፍል - 8
ሂክማ ጀማል




ሀሊማ ፕሮግራሙን በተመስጦ እያየች ስለነበር አባቷን አላየችውም፡፡ ከድር ወደ ሀሊማ ይበልጥ ቀረብ ብሎ አጠገቧ ተቀመጠ "የኔ ልጅ ሀሊማዬ" ብሎ ሲጠራት "ባባዬ" ብላ አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡ እሱም አቅፎ እያገላበጠ ሳማት ፋጡማ በሀሊማ ሁኔታ ግራ ተጋብታ አጠገባቸው ቆማ በመገረም አየቻት፡፡ ከድርም የናፍቆቱን ያህል ከሳማት በኃላ ለመውጣት ከተቀመጠበት ተነስቶ የሀሊማን እጅ ይዞ ወደ በራፉ ተራመደ፡፡ ፋጡማ ሁኔታውን ልትነግረው ብላ አሁን ደስተኛ ስለሆነች ባልነግረው ይሻላል ብላ ለመሸኘት ከኃላ ወጣች፡፡ የግቢው መውጫ ድረስ ሸኝታቸው "ከድር" ብላ ስተጠራው አልሰማትም ነበር በድጋሚ "ከድር" ስትለው "አቤት" ፋጡማ "ሀሊማን ብቻዋን እንዳተዋት አደራ" አለችው ግራ በተጋባ ሁኔታ ውስጥ እሺ አላህ ይስጥልኝ ብሎ ተሰናብቷት ሀሊማን ይዟት ወጣ፡፡
... "ወዴት እንሂድ?"
"ወደ እቤት ኡሚ ጋር ወሰደኝ" አለችው ሀሊማ ትላንት የሆነውን ነገር ሙሉ በሙሉ ረስታዋለች፡፡ ከድር ደነገጠ ምን ሊላት እንደነበር ጭራሽ ረስቶት እሺ ብሎ ወደ ቤት መሄድ ጀመሩ፡፡ ሀሊማ ለግዜውም ቢሆን ደስተኛ ሆናለች፡፡ "ባባ" ብላ ጠራችው ከድር በሀሳብ ሄዶዋ ሀሊማ በድጋሚ ባባ ስትለው "አቤት የኔ ቆንጆ"
... "አንድ ነገር ልጠይቅህ እንቢ አትለኝም? "
...."የፈለግሽውን ጠይቂኝ"
"እሺ እንደምትለኝ ቃል ትገባለህ?"
" አዎ ንገሪኝ"
"እሺ ተዘጋጅ"
"ተዘጋጅቻለሁ"
"ኡሚ ጋር ደውለህ ሀሊማን አጣኃት በላት ከዛ እቤት ስንገባ እናስደንግጣት"
ከድር በጣም ደንግጦ ዝም አለ "እ...እ ደውላ " ሀሊማዬ አንድ ነገር ልንገርሽ! "አይቻልም ቃል ቃል ነው ደውል" ብላ አስጨነቀችው፡፡
" እሺ እደውላለሁ ግን በቅድሚያ አንድ ነገር ልንገርሽ"
"አይሆንም ቅድሚያ ደውል "
"አሁን መደወል አልችልም" ሀሊማ እንደ ማኩረፍ እያለች
" ኡሚ ምን እንደምትለኝ ታውቃለህ "እሺ ምን ትልሽ ነበር አንቺ "ለ አንድ ሰው ቃል ስትገቢ እርግጠኛ ሁኚ አንዴ ቃል ከገባሽ በኃላ ግን ቃልሽን ማጠፍ የለብሽም ምንም ነገረ ቢሆን ማድረግ አለብሽ አላህ ቃሉን የሚያጥፍን ሰው አይወድም ብላኛለች ስለዚህ ትደውላለህ ቃል ገብተሀል ቃልህን ካጠፍክ አላህ አይወድህም" ከድር እንዴት ብሎ እንደሚያሳምናት ግራ ገባው የ ዘይነባ ስልክ አንደተሰበረ ረስቶታል ከደወለ ሰሚራ ነው የምታነሳው ደውል ብላ መጨቀጨቋን ቀጠለች አማረጭ ስላጣ መደወል ጀመረ ከ ትንሽ ፍላጋ በኃላ " የደወሉላቸው ደንበኛ ቴሌፎን ለግዜው ጥሪ አይቀበልም እባኮ ትንሽ ቆይተው ይሞክሩ" ከድር በደስታ ነበር ስልኩን የዘጋው፡፡ "ደወልክ"
"አው አይሰራም" "ድጋሚ ሞክር እሺ ብሎ ድጋሚ መደወል ጀመረ "ለእኔ ስጠኝ ብላ" ተቀበለችው "ከጠራ እሰጥሀለው" አለችው እሺ ብሎ ሰጣት እሷም ተመሳሳይ ነገር ነበር የሰማችው፡፡ ስልኩን መልሳ ሰጠችው፡፡ "አሁን ቃልህን ስላከበርክ አላህም እኔም እኖድሀለን ብላ ጉነጩን ሳመችው የ ሀሊማ ሁኔታ ገርሞት ፈገግ አስባለው ፡፡ወደ ቤት እየደረሱ ነው ከድር በጣም መፍራት ጀመረ ምን እንደሚላት እያሰበ በራፍ ለይ ደረሱ ቁልፋን አውጥቶ የግቢውን በር ከፍቶ ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ የሀሊማ የመጀመሪያ ስራዋ ወደ መአድ ቤት ሄዶ እናቷን መፈለግ እንደተለመደው ድምፅ ሳታሰማ ገባች፡፡ እናቷ የለችም ከድር ሀሊማ ብሎ ሲጠራት ዝም በል ኡሚን ለስደነግጣት ነው፡፡ ከድር ሳያስበው አለቀሰ እዛው ባለችበት ትቷት ወደ ሳሎን ገባ፡፡ ሀሊማ በድጋሚ ወደ ሳሎኑ ድምፅ ሳታሰማ ገባች ቤቱ በጣም ይቀፋል ሀሊማ "ባባ ኡሚ የለችም እንዴ ደግሞ ለምን ዛሬ ቁርአን አልተከፈተም? "
ለምን ይከፈታል አላት
" ቤታችንን ከሰይጣን ለመጠበቅና ቤታችን ኑር እንዲሆን"
"ማን ነው እነደዚህ ያለሽ" ብሎ ጠየቃት
"ኡሚ ናታ "
ከድር ከተቀመጠበት ተነስቶ ቁርአን መክፈት ጀመረ ሀሊማ እሱን እዛው ትታው ወደ መኝታ ቤቱ መራመድ ጀመረች እንደ በፊቱ በዝግታ እየተራመደች ወደ መኝታ ቤቱ ለመግባት በሩን ጠጋ ስታደርገው ድንገት እዛ መኝታ ቤት ውስጥ ያየችው ነገር አስታወሰች፡፡ በጣም ጮኀች ከድር ከተቀመጠበት ዘሎ ተነሳ ወደ መኝታ ቤቱ ሄደ ሀሊማን ቀረብ ብሎ "ምነው ምንሆንሽ ብሎ" ሊያቅፋት እጁን ሲዘረጋ ከሱ መራቅ ጀመረች፡፡ ምን ሆነሽ ነው እያለ ሲጠጋት ትሸሸዋለች እሺ ወደ ሳሎን እንሂድ መልስ አልሰጠችውም በዚህ መሀከል ነበር ሰሚራ አስቤዛ ገዛዝታ ወደ ቤት የተመለሰችው፡፡ እቃውን ኩሽና አስቀምጣ ወደ ሳሎን ስትሄድ የከድርን ድምፅ ሰማች ሳሎን መግባቷን ትታ ወደ መኝታ ቤቱ ሄደች እንዴ ሀሊማዬ መጣሽ እንዴ ብላ ልትስማት ስትጠጋ ሸሸቻት "ምን ሆና ነው" ሰሚራ ነበር ያለችው፡፡ እኔ እንጃ ሰሚራ ለማግባባት እየሞከረች የት "ሄደሽብን ነው እንዴት እንደናፈቅሽኝ ነይ እስቲ እቀፊኝ ደግሞ የምቶጅውን ብስኩት አምጥጬለሻለሁ ነይ ወደ እኔ" ብለ ወደ እሷ ስተቀርብ ይበልጥ ሸሸቻት



ክፍል 9
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍4
📚የሰው ልጆች በዱንያ ላይ
ከተሽቀዳደሙህ ተውላቸው
๏ ነገር ግን በአኺራ ላይ ከተሽቀዳደሙህ
ቀዳሚያቸው አንተ ሁን ።
⇘ አላህ ዱንያን ለሚወደውም ሆነ
ለማይወደውም ይሰጣል ግን አኺራን
ለሚወደው ብቻ ነው የሚሰጠው ።
                     Te » @ketibeb
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሐሊማ
ክፍል 9
ሂክማ ጀማል



ሰሚራ ሀሊማ ስለሸሸቻት ተናደደች፡፡ ግን እንዳያስታውቅባት ደጋግማ እንድታናግራት መጠየቁን አላቆመችም፡፡ ሀሊማ የበለጠ ራቀቻቸው፡፡ ከድር እንደምንም ብሎ ወደ ክፍሏ አስገባት ሀሊማ ሳቋ ሁሉ ጠፍ፡፡ ከተወሰነ ቀን በኃላ ከድርን ከሰሚራ በተሻለ ሁኔታ ቀረበችው፡፡ እሱንም ቢሆን አንዳን ነገሮችን ሲጠይቃት ከመመለስ ውጪ ምንም አታወራውም፡፡ ጊዜው ክረምት አልፎ በጋ የሚገባበት የመስከረም ወር ነው፡፡ ሀሊማ 1 ኛ ክፍል የምትገባበት አመት ነው ትምህርት ሊጀመር 2 ቀናቶች ብቻ ነው የቀሩት፡፡ ከድር ለሀሊማ የሚያስፈልጓትን ነገር በሙሉ ገዝቶላታል ቢሆንም ሀሊማ ብዙም ደስተኛ አልነበረችም፡፡

ሰሚራና ከድር ጭቅጭቃቸው ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት መጥቶዋል፡፡ ከድር ከሰሚራ ጋር አንድ አልጋ ላይ ላለመተኛት ለራሱ ቃል ገብቷል፡፡ ሰሚራ እና ከድር እራሳቸውን ባል እና ሚስት ብሎ ሰይመዋል ግን ምንም አይነት ኒካ የላቸውም ዝም ብለው ነው አብረው የሚኖሩት ሁለቱም ብዙም ኢስላማዊ እውቀት የላቸውም በዘፈቀደ ነው የሚኖሩት፡፡ ሰሚራም ከከድር ጋር መኖር የሰለቻት ትመስላለች፡፡ ሀሊማ ብቸኛ የምትቀርባት እና የቀረቻት ዘመድ ፋጡማ ነች፡፡
ፋጡማ ልጠይቃቸው እነ ሀሊማ ጋር በሄደች ቁጥር ዘይነባን አታገኛትም የት ናት ብላ ስጠይቅ የሆነ ምክንያት ፈጥረው ይነግሯታል ባይወጥላትም እሺ ከማለት ወጪ ምርጫ የላትም ፋጡማ ወደ እቤት በምትመጣበት ጊዜ ሰሚራ ከእቤት ትወጣለች ፡፡ እንዲህ እንዲህ እየተባለ 3 አመታት አለፋ ሀሊማ አሁንም ቢሆን ከሰሚራ ጋር ምንም አይነት ንግግር የላቸውም፡፡ እንደውም የበለጠ አቂማለች ሰሚራን ለመበቀል ወስናለች፡፡
ሀሊማ ውጤቷ ብዙም አሪፍ አይደለም ጓደኛም ሆነ ትንሽም ቢሆን የምትቀርበው ሰው የለም ሁሌም ቢሆን ብቻዋን ናት መንታ እህትና ወንድሟ 4 አመት አልፏቸዋል ትምህርት ጀምረዋል፡፡ ሀሊማ የእናቷን ያህልም ባይሆን ትንከባከቸዋለች ታስጠናቸዋለች ሀሊማ 5 ክፍል ከገባች በኃላ ግን ውጤቷ በጣም አሪፍ መሆን ጀምሮዋል፡፡ ከበፊቱ በጣም ተሻሽላለች እህትና ወንድሞቿ Kg3 ጨርሰው አንደኛ ክፍል ሊገቡ ነው ሀሊማ ደግሞ የ8 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወጤት እየጠበቀች ነው.......
ሀሊማ እድሜዋ በጨመረ ቁጥር ሙሉ ለሙሉ የእናቷን መልክ እየያዘች ነው፡፡ ከድር አንዳንዴ ሀሊማን ሲመለከታት ዘይነባን ትመስለው እና ይደነግጣል፡፡ ለተወሰነ ሰአት በትኩረት ከተመለከተችው የሰራውን ነገር የምታውቅበት ይመስለዋል፡፡ እና ከፊቷ ዞር ይላል ከድር አሁንም ቢሆን ሀሊማ ምንም እንደማታውቅ ነው የሚያስበው፡፡ አንድ ቀን ከድር ሌላ ቀን ከስራ ከሚመለስበት ሰአት ቆየ፡፡ ሀሊማ እየጠበቀችው ነው ሰአቱ እየመሸ ነው እህትና ወንድሟ ተኝተዋል፡፡ ለምን እስኪመጣ አልፅፍም ብላ አሰበች ሀሊማ የህይወት ታሪኳን ትፅፋለች፡፡ ከልጅነቷ ጀምሮ ያሳለፈችውን ነገር ትፅፍ ነበር የቀን ውሎዋን ለመፃፍ ወደ ክፍሏ ገብታ መፃፍ ጀመረች የተወሰነ ከፃፈች በኃላ እዛው ዲያሪዋ ላይ ሆና እንቅለፍ ይዟት ሄደ ከድር ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ መጣ ሀሊማን ሳሎን ሲያጣት ወደ ሀሊማ ክፍል ሄደ፡፡ ሀሊማ ዲያሪዋ ላይ እንደተኛች ናት........
ፋጡማ ከቅርብ ቀን ጀምሮ ታማለች ከቀን ወደ ቀን በሽታዋ እየባሰበት ነው ጠያቂ ዘመድ አይዞሾ እያለ ከጎኗ የሚሆን ሰው የላትም፡፡


ክፍል 10
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍3
ሐሊማ
ክፍል 10
ሂክማ



ሀሊማ አሁንም እንደተኛች ናት ከድር ወደ ሀሊማ ክፍል ሄዶ ሲያንንኳኳ መልስ የለም፡፡ በሩን ለመክፈት የበሩን መክፈቻ ተጭኖ በሩን ለመክፈት ሲሞክር.....

ዛሬ ፍጡማ ከሌላው ቀን በተለየ በጣም ታማለች፡፡ ሰአቱ መሽቶዋል ከድር ጋር ለመደወል ስትሞክር ስልኳ ለመደወል የሚያስችል ያህል ሂሳብ አልነበረውም፡፡ "ይቅርታ የሎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው እባኮን ሂሳቦን ይሙሉ" ፈጡማ ህመሙ እየበሰባት ነው፡፡ እቤቱ ውስጥ ማንም የለም፡፡...

ከድር ሊከፍተው የነበረውነ በር መልሶ ተወው፡፡ ተኝታ ከሆነ ባልረብሻት ይሻላል ብሎ አስቦ ወደ ሳሎን ቤት ተመለሰ ሰሚራ እራት አቅርባ መመገብ ጀመሩ፡፡ ከድር እንዲሁ ቀመስ ቀመስ አድርጎ በቃኝ ብሎ ተነሳ፡፡
"ሰሚራ ሀሊማ እራቷን በልታለች" ብሎ ጠየቀ፡፡ "አይ አልበለችም " ካልበለች በቃ ልቀስቅሳት ብሎ ድጋሚ ወደ ሀሊማ ክፍል ሄደ አሁንም በሩን አንኳኳ መልስ የለም፡፡ በሩን ከፍቶ ወደ ወስጥ ገባ፡፡
የበሩን መከፈት የሰማችው ሀሊማ ወዲያው ከእንቅልፏ ነቃች፡፡ በፍጥነት ዲያሪዋን ዘጋችው፡፡
...ከድርም "ምን እየሰራሽ ነው እንቅልፍ ይዞሽ የሄደው"
... "እያነበብኩ ነበር፡፡"
..."ምንድ ነበር የምታነቢው እስቲ አሳይኝ" ሲላት
... "አይ ዝም ብሎ ነገር ነው" ከድርም ከዚህ በላይ ላለማስጨነቅ "እሺ እራትሽን ብይ" አላት
... እሺ መጣሁ አንተ ሂድ
እሺ ብሎ ወጣ፡፡ ሀሊማ ዲያሪዋን ማንም የማያገኘው ቦታ አስቀምጣ ወደ ሳሎን ሄደች ፡፡ እራቷን በልታ እህትና ወንድሞቿን አይታ ወደ ክፍሏ ሄደች አልጋዋ ላይ ጋደም አለች፡፡ ነገር ግን እንቅልፍ ማግኘት አልቻለችም ነበር፡፡ ድንገት ፋጡማ ትዝ አለቻት፡፡ ለምን አልደውልላትም ብላ አሰበች ግን ተኝታ ሊሆን ይችላል ከተኛች አታነሳውም፡፡ ሀሊማ ነገ የ 8ተኛ ክፍል ውጤት የምትቀበልበት ቀን ነው፡፡ ውጤት ተቀብዬ ስመለስ ወደ እሷ እሄዳለሁ ብላ አሰበች ፡፡ ሀሊማ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ስለ እናቷ የሆነውን ሁሉ ለፋጡማ ነግራታለች፡፡ ፋጡማ በይበልጥ እንዲያማት ያደረጋት ይህ ዜና ነበር 1 ዘመዷን እንዲ እንደ ታኘከ ማስቲካ አውጥተው መጣላቸው እንደ እግር እሳት አቃጠላት፡፡ ለመክሰስ ፈልጋ ነበር ግን እንደምንም ሀሊማ አሳምና አስቆመቻት ፋጡማና ሀሊማ ሰሚራንም ከድርንም ለመበቀል ወሰኑ፡፡ ነገር ግን ለመበቀል ከፈለግሽ ትምህርትሽ ላይ አሪፍ ውጤት ማምጣት አለብሽ ምክንያቱም ጠላትሽን በቅድሚያ የምተበቀይው የ አንችን ስኬት በማሳየት ነው ብላት ነበር፡፡ ሀሊማ በራስ ተነሳሽነት ውጤቷ ቢስተካከልም በይበልጥ ሞራል የሆናት ግን ፋጡማ ምክር ነበር ፡፡
ስለዚህ ልደውልና ካነሳችልኝ ነገ እንደምመጣ ልንገራት ብላ አሰበች፡፡ ሀሊማ ወደ ፋጡማ ጋር ደወለች ይጠራል ግን አይነሳም በድጋሚ ደወለች በሁለተኛው ተነሳ ፈጡማ በጣም በተዳከመ ድምፅ "ሄ...ለ....ው" አለቻት "ሄለው አክስቴ"
"አሰለሙአለይኪ ቀሰቀሰኩሽ እንዴ"
"አ...ይ ል...ጄ አ...ል...ተ...ኛ...ሁ...ም"
.. ሀሊማ "እሺ አክስቴ ነገ እመጣለሁ ልንገርሽ ብዬ ነው" እ....ሺ አለች እሺ ቻው አክስቴ ብላ ስልኩን ዘጋቸው ብዙም ሳትቆይ ሀሊማ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡
እንደ ማይነጋ የለምና ነጋ ሰሚራ ቁርስ ልትሰራ ሽር ጉድ ማለት ስትጀምር ሀሊማ ያለወትሮዋ ላግዝሽ ብላ አብራት መስራት፡፡ ጀመረች ሰሚራ ምንም ነገሩ አላማራትም ፡፡ ይቅርብሽ ብትላትም አሻፈረኝ አለች፡፡ ለሀሊማ እንዲህ እንድታደርግ የነገረቻት ፋጡማ ነች ጥሩ ሁኚላት እና ህሊናዋ እንዲወቅሳት አድርጊያት ብላት ነበር፡፡ እሷም የተባለችውን እያደረገች ነው፡፡ ቁርሱ ሲደርስ ሀሊማ አቀራረበች ሁሉም አብረው በሉ ፡፡ ከድር ወደ ስራው ሊሄድ ሲነሳ ሀሊማ እናቷ እንደምታደርገው የሚለብሰውን ልብስ አዘጋጀችለት፡፡ ሰሚራ በሁኔታው ብትቀናም ምንም አላየችም ነበር ፡፡ከድር ሀሊማን ሲያያት የመልኳ መመሳሰል ሁኔታዋ ሁሉ ነገሯ ዘይነባን አስታወሰው፡፡ ሆዱ ተላወሰ በድንገት አለቀሰ፡፡ ሀሊማ ይህን ስታይ ደስ አላት አላማዋ ይሄ ስለሆነ እንዳላየ ሆና ወጣች ክፍሏ ገብታ ልብሷን ቀያይራ ወጣች፡፡



ክፍል 11
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍21
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM