ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
መሀን አራስ
ክፍል አስራ ስምንት
(ሚስጥረ ጀማል)

አንድ የሆነ! ግን በጣም ብዙ የሚመስል ቀን! ሚገርም አጋጣሚ ተከሰተ ...
ከምሽቱ አንድ ሰአት ሆኗል። ሰሚር ወደ ቤት አልገባም። ዛሬ ማርያና ጋር ሥለሚያድር በግዜ ሠግጄ ለመተኛት ውዱዕ ማድረግ ፈልጌ ወደ መታጠብያ ክፍሉ አመራሁ:: ያየሁትን ማመን አቃተኝ!!! መታጠብያ ቤቱ በሠፊው ተከፍቷል ማርያና በተቻኮለ ሥሜት ውሥጥ ሆና የሆነ መድሃኒት ሥትውጥ አገኘኋት:: 'ማርርያና!' አልኳት በእጇ የያዘችው ብርጭቆ ወድቆ እሥከሚሠበር ድረሥ ደነገጠች። የፊቷ ቀለም ተለዋወጠ:: 'አሞሽ ነው እሥቲ የምን መድሃኒት ነው ምትውጭው ?? ' ብዬ የያዘችውን የመድሃኒት ማሸግያ ተቀብያት አየሁት:: ማመን አልቻልኩም!!! በኔ መሃንነት ሲሰቃይ የኖረው ባሌ በዋናነት ልጅ ልትወልድለት አሥቦ ያገባት ማርያና በየ ምሽቱ አንድ አንድ ፍሬ የሚወሠድ የወሊድ መቆጣጠርያ እንክብል ተጠቅማ ዘሩንም ዘሯንን ሥታጠፋ ከርማለች :: ልታሥረዳኝ መንተባተብ ጀመረች ። ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም። በጥፊ ሥመታት ከመታጠብያው ሲንክ ስር ወድቃ ራሷን ሳተች። በዛው ቅፅበት የሠሚር መኪና ወደ ግቢው ሥትገባ አየኋት። ምንም አልደነገጥኩም:: እዛው በቆምኩበት ደረሠብኝ::"አንቺ እብድ ምን አደረግሻት?" ሲል ጮኸ! ወድያውም ሊያነቃት ያደረገው ሙከራ ሰርቶለት ማርያና ራሷን አወቀች:: ' የኔ አለም ለመጀመርያ ግዜ ሠደበኝ ።ለዛውም እብድ አለኝ' ያለ ጥፋቴ! ለሡ ባሠብኩ እሡን እሡን ባልኩ:: ተሠደብኩ::ምንም የመናገር አቅም አጣሁ። እንባዬ እየተናነቀኝ ወደ ልጄ ሄጄ መነፍረቅ ጀመርኩ።
በዚህ መሃል ሠሚርና ማርያ በከፍተኛ ጩኸት ሲጨቃጨቁ ሥለተሠማኝ ለማገላገል ሄድኩ :: "ቆይ ለምን አገባሽኝ,????" እያለ ይጮሃል :: ያለቅሳል ህመሙ አመመኝ ምናልባት እኔ መድሃኒቱን ሥትወሥድ ባላያት እሡ እንዲህ አይሆንም ነበር አልኩ። በራሤ ፈረድኩ!::ወይኔ ባሌ!!!!
"እሺ ሁሉን ነገር እናገራለሁ" ማርያና ከእንባዋ እየታገለች መናገር ጀመረች:: "እኔ በዚህ ሠአት የማግባትም ሆነ የመውለድ እቅድ የለኝም ነበር:: ነገር ግን ቴቴ በየግዜው ሥላንተ በምትነግረኝ ነገር ተታለልኩ። እኔን እንዳገባኸኝ ሂዳያን የምትፈታት መሥሎኝ ነበር:: አንተን በማግባት ብቻ ሃብትህ ዝናህ ሁሉ የኔ ሊሆን የሚችል መሠለኝ ።ጓደኞቼንም አማከርኳቸው ልጅ ከወለድኩልህ በዛው አንተው ቤት እንደምቀር አሥፈራሩኝ። እኔም ከምወደው ሠው ጋር ካልሆነ በቀር ዘላለሜን ካንተ ጋር ለመኖር አሥቤም አላውቅም። በዛ ላይ ሆሆታው ቴቴ ለኔ ያላት ክብር ምናምን አታለለኝ። አገባሁህ ነገር ግን ህይወቴን በሙሉ ልጅ ወልጄ ያንተ መሆንን አልፈለግኩም። በዛ ላይ አዲሷ ሚሥትህ እኔ ብሆንም ከሂዳያ ጋር ሁሌም እንደ አዲሥ ሙሽራ ነው ሥትወዳት የማየው። ሥለዚህ እሥከግዜው እራሤንም እሥከማሣምን ድረሥ ልጅ በሚሉት ገመድ ራሤን ላሥርልህ አይገባም ብዬ አሠብኩ::" ሰሚር ከተቀመጠበት ተነሥቶ እግሬ ስር ወደቀ "ሂዱዬ አንቺ ለአመታት ደሥታዬን ለመሙላት ፍላጎቴን ለማሣካት ጤንነትሽን ያጣሽ ሴት ሆይ፣ ሃላፊነቷን ወሥደሽ ልጇን ልጃችን ለማድረግ በማሠብ የሌላውን እርጉዝ ደፋ ቀና ብለሽ ያሥተናገድሽ ሴት ሆይ፣ ከግዜ ቡሃላ በመሠላቸት ያመጣሁብሽን አዲሥ አመል እንኳን ታግሠሽ በገዛ ቤትሽ ጣውንትሽ ትኖር ዘንድ የፈቀድሽ፣ ባልወለደ አንጀትሽ የሠው ጨቅላ ታቅፈሽ የታረስሽ የኔ መሃን-አራስ ሆይ በደልን ሁሉ በሚምረው ሃያሉ ጌታ ይዤሻለሁ ማሪኝ!" የሠሚር ማዘን ልቤን ሠበረው። ከወደቀበት አንስቼ ልጄን አሥታቀፍኩት እንዲህም አልኩ 'ዓለሜ በዚህ በኔና ባንተ ታሪክ ላይ ነገሮች ሁሉ የእርግማን ያህል ቢከብዱም ልክ እንደዚህ ልጅ ምላሻ ችን ሁሉ አሜን እንጂ ሌላ መሆን የለበትም ::'
ሰሚር ወድያውኑ ቴቴ ጋር ደውሎ ያጠፋችውን ሥህተት እሥከመጨረሻው ዐውፍ እንደማይላት ነገራት::
ይሄኔ ማርያና በዝግታ ተራምዳ ክፍሉን ለቃ ወጣች:: ከደቂቃዎች ቡሃላ በሰሚር እቅፍ ውሥጥ እንዳለሁ ለቅሦውን ለማሥቆም ሥሞክር እቃዋን ሁሉ ይዛ ከደረጃው ሥትወርድ አየኋትና 'ማርያና በዚህ ሰአት..?' ብዬ ለመመለሥ ብድግ አልኩ " አይ ሂዱ ለበደለኛ ሰው ቀኑም ጨለማ ነው:: ሥለዚህ አሁንም ሄድኩ ጠዋት በብርሃንም ሄድኩ በጨለማ እኩል ነው እንቅፋት ሚመታኝ::" የሠሚር ሚሥት ቤቱት ጥላ ሄደች ::
አንዳንድ ቀኖች በእርግጥም የአንዳንድ ቀኖች ተቃራኒ ናቸው :: ምናልባትም ይሄ ቀን ባሌ ሌላ ሚስት ሊያመጣ ሞሽሬ የላኩት ቀን ራሴት ማጥፋት ሣይቀር የተመኘሁበት ቀን ተቃራኒ ነው:: ግራ ገባኝ !! ባሌ እንደ ድሮው የግሌ ሆነ ብዬ ልደሠት?? ወይሥ ሠሚሬ የአብራኩን ክፋይ ለማግኘት እንደጓጓ በመቅረቱ ልዘን???
ለሊቱን እዛው ብርድ ላይ ሥለቆየን ልጄ አሚን ሲያስለው አደረ እኔም ቢሆን ጤንነት አልተሠማኝም ሠሚርም ከባብዶታል :: ሥለዚህ ሱብሂ ሠላት እንደሠገድን ሶስታችንም ተያይዘን ወደ ሆሥፒታል አመራን '' ለልጄ ሽሮፕ ታዘዘልኝ ::ለባሌ ደግሞ ራሱን ፈታ የሚያደርግበት ረዘም ያለ የእረፍት ግዜ እንደሚያሥፈልገው ተነግሮን ወጣን እነሆ የኔ ውጤት ቀረ:: ልጄን እንደታቀፍኩ ከሠሚር አጠገብ ቁጭ ብያለሁ :: ዶክተሩ አይን ላይ ከባድ የሃዘን ድባብ ይነበባል ::ፈራሁ ሠሚር ከዶክተሩ ያሥጥለኝ ይመሥል በትከሻው ምሽግ የዶክተሩን ጮር ሸሸሁ" ምነው ዶክተር ችግር አለ?" ሠሚር የሞት ሞቱን ጠየቀው። ሁለታችንም ፈርተናል :: ዶክተሩ መናገር ጀመረ" am sorry to say this but..." ወይ መከራዬ? ምን ይሆን ቀጣዩ የሃዘኔ ምዕራፍ አልኩ በልቤ ዶክተሩ ቀጠለ.." እንዴት እንደተከሠተ አላውቅም::ግን.....

የመጨረሻ ክፍል 400👍ቡሀላ ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
የፈቲ ባል …….ክፍል 9 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 9◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
👍1
መሀን አራስ
ክፍል አስራ ዘጠኝ(የመጨረሻ)
(ሚስጥረ ጀማል)

ወይ መከራዬ? ምን ይሆን ቀጣዩ የሃዘኔ ምዕራፍ አልኩ በልቤ ዶክተሩ ቀጠለ.." እንዴት እንደተከሠተ አላውቅም::ግን ቢያንሥ መጠንቀቅ መቻል ነበረብሽ!" "ዶክተር በቃ አታጨናንቀን በጣም እየረበሽከን ነውኮ "ሠሚር መቆጣት ጀመረ" እሺ እንግዲህ በዚህ ፍጥነት አርግዘሽ እንዴት survive ልታደርጊ እንደምትችይ አላውቅም ::" ከሃውልት በላይ ደርቄ ቀረሁ!!!
ዶክተሩ ቀጥሏል" እንዴት እንደምትቋቋሙት አላውቅም ቢያንሥ ይሄ ጨቅላ እንኳ ትንሽ እሥኪጠነክር መጠበቅ ነበረባችሁ ካልሆነው መከላከያ መጠቀም ያባት ነበር anyhow ምንም ማድረግ አይቻልም ::
ደግሞኮ በሚገርም ሁኔታ ከ100 እናቶች ቢበዛ 1 እናት ላይ ብቻ የሚከሠት triple pregnancy ወይም 3 ልጆችን ነው በአንዴ ያረገዝሽው::"
ግራ ገባኝ ነፍሴ ለብቻው ሥጋዬ ለብቻው የተናጠለ መሠለኝ:; ውስጤ ለውሥጤ ያወራል::' ማለት??? ጌታዬ የአመታት ፀሎቴን ሰማኝ???? ማህፀኔ ከሞተበት ተቀሰቀሰ??? እኔም ወጉ ደረሰኝ??? አረገዝኩ ?? ሶስት ልጅ??? 'ይሄን ጉድ እንዲያሥረዳኝ ወደ ሠሚር ዞርኩ ሠሚር ካጠገቤ የለም ።እዛው መሬቱ ላይ ሱጁደ ሹክር እያደረገ ነው :: አይ በቃ ቅዠት አይደለም ማለት ነው አሜንን ወንበሩላይ አስቀወጥኩና እኔም ከ ዐለሜ ጎን ሱጁድ ወረድኩ'ሰጀደ ወጅሂየ ሊለዚ ኸለቀሁ ወሸቀ ሰምዐሁ ወበሰረሁ ፈተባረከላሁ አህሰኑል ኻሊቂን'
እኔም ሆነ ሠሚር ቃላትን አዋቅሮ ተነጋግሮ መግባባት አቃተን ። ብቻ አንድ ነገር እናውቃለን እኔ ና እሡ ለመጀመርያ ግዜ ከአመታት ሙከራ እና መከራ ቡሃላ ልጅ ሊኖረን ነው:: ለሠአታት ተቃቅፈን አነባን!! ዶክተሩ ግራ ተጋብቷል። እሡ ያሠበው አሜንን የኔ ልጅ ነው ሥላልኩት በዛ ፍጥነት ማርገዜ ይጎዳኛል ብሎ ነበር :: ይሄንን ሁሉ ውሥብሥብ ታሪክ ለሡ የምናሥረዳበት ግዜ ሥላላገኘን አሜንን ይዘን ወደቤት ሄድን መነጋገር አቃተን እየተያየን መሣቅ ሆነ ውሏችን :: ጉዳዩን እንዳረጋገጥን የእርግዝና ክትትል ለመጀመር ወድያውኑ ከኔ ሱቅ ፊት

ለፊት ወዳለው የእናቶች እና የህፃናት ሆስፒታል አመራን::መኪናዋን በሩ ላይ አቆምንና ወረድን በሩ አካባቢ ያለውን ክፍት ቦታ አየሁት::
ፋኪሀን ለመጀመርያ ግዜ ያገኘኋትእዛ ነበር ቦታ ጭር ብሏል።ሁሉ ነገር በነበር ቀረ::
' አላህ ሆይ ቀብሯን አስፋላት ከመላኢኮች የሆኑ አጫዋቾች መድብላት አሚንንንን' አልኩ:: ከመግባታችን በፊት ሻርፔን በተን አድርጌ ሆዴን ሸፈንኩት:: አሜንን ዐለሜ ያዘልኝ:: በአንድ እጄ ወገቤን ይዤ በትንሹ 15 ዲግሪ ከወገቤ ወደ ኋላ ዘንበል አልኩኝ:: በአንድ እጄ ሠሚርን ያዝኩት::
ሠሚር በድርጊቴ ተገርሞ ፈገግ እያለ ያየኛል ::ከመግባታችን በፊት ወደ ሡቄ መሥኮት ዞር ብዬ አየሁ:: ሱብሀለናህ! ያቺ የዚህን ሆሥፒታል ደንበኛ የሆኑ እርጉዞችን በቅናቻ የምታየው መሃኗ ሂዳያ ዛሬ መስኮቱ ጋር የለችም። ምክንያቱም እሷ ዛሬ አንድ ልጅ አሣቅፋ፣ ከመቶ ሴቶች መሃል ተመርጣ ሦስት ልጅ በሆዷ ያረገዘች እድለኛ ሆናለች:: በዚያው ቀን የእርግዝና ክትትሌን ጀመርኩ::
ቴቴ ድል ያለ ድግሥ ደግሳ በሙሉ ቤተሰባቸው ፊት ቆማ ሰሚርን ዐውፍ በለኝ ብላ ተማፀነችው:: ሰሚርም"ለሁሉም ነገር ሃቅ ሃቁን መሥጠት ግዴታችን ነው ይሄ ያንቺ ይቅርታ ሃቅነቱ ለኔ ሳይሆን ለውዷ ባለቤቴ ለሂዱ ነው :: ያለ ጥፋቷ ለአመታት አሠቃይተሻታልና እንዲሁ እንደቀልድ በደልሽን ልትረሳልሽ ባይቻላትም ቢያንስ ለወጉ ያህል ይቅርታን መጠየቅ አለብሽ" አላት በዛ በተከበረ ቤተሠብ ፊት የኔ አለም እኔን አከበረኝ :: እኔም ይቅርታዋን ተቀብዬ አባሸርኳት ነገር ግን ከዚያን ግዜቡሃላ በእኛም ሆነ በማንኛውም ሠው የትዳር ህይወት ሙሉ ሃላፊነቱን መውሠድ ያለባቸው የጉዳዩ ባለቤቶች ባልና ሚስቱ እንጂ አማች አይደለም :: እንደሷ ባሉ አማቾች ስንት ትዳር እንደፈረሠ አሥጠንቅቄያት ተለያየን::
ሳምንቱን ሙሉ ለመዝናት በማሠብ ከሠሚር ጋር አሜንን ይዘን ከከተማ ራቅ ብለን ለመሄድ መንገድ ጀምረናል:: በዚህ ጉዞ የኔም የእርግዝና የተለያዩ አምሮቶች ይወጡልኝ ዘንድ፣ ለሠሚርም ዶክተሩ እንዳለው ረዥም እረፍትን ያገኝ ዘንድ መድሃኒት እንደሚሆነን እያወራን ነው :: ከመኪናው ኋላ ወንበር የሚያስል ህፃን ልጅ ድምፅ ተሠማን :: ሁለታችንም ደንግጠን ተያየን። የየራሣችንን መድሃኒት ሥናመቻች ለካስ ለአሚን የታዘዘለትን መድሃኒት ረስተናል :: መዘንጋታችን እያሥገረመን ከከተማ ከመውጣታችን ብፊት ከአንድ ፋርማሲ ገዛንለት ::አሚንዬ የኔ ገዳም:: እነሆ ዘንድሮ ሙሉ ቤተሰቤ ከህመሙ ይሽር ዘንድ የለማኝን ዱዐ የማይዘነጋው ፍትሃዊው ጌታ በመሃከላችን መዳንን፣ ደስታን፣ ፀጋን ሁሉ በኛ ላይ "ሁን"ሲል አሠፈነ:: እሥከ ጀነት ያዘልቀን ዘንድ የዘወትር ዱዐዬ ነው ::ለሁሉም ግዜ አለው!!!
ተፈጠመ!!!
ከ 500 👍 ቡሀላ አዲስ ምርጥ ታሪክ እንጀምራለን
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍3
#የደሴቷ_ብቸኛ_ነዋሪ....ደስ የሚል ታሪክ

በርካታ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አንዲት መርከብ በድንገት በተከሰተ ከባድ ማዕበል ምክንያት ባህሩ ውስጥ ትሰጥማለች። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታድያ በአላህ ተአምር አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል። ይህም ሰው በውሃው እየተገፋ አንዲት ደሴት ላይ ራሱን ያገኘዋል።

እርዳታ ለመጠየቅ በደሴቷ እየተዘዋወረ ሰው ለማፈላለግ ቢሞክርም ምንም ዓይነት የሰው ዘር ማግኘት አልቻለም። በአካባቢው ማዕብሉ ከሚያናውጠው ባህርና ከወፎች ድምፅ በስተቀር የሚሰማ ነገርም የለም። በዚህን ግዜ በትንሽየዋ #ደሴት ውስጥ የሚኖረው ብቸኛው ሰው እርሱ ብቻ መሆኑን ሲያረጋግጥ በጣም ተጨነቀ። ፍርሃትም አደረበት። ከዚህ አስፈሪ ችግር ያወጣውም ዘንድ አላህን ለመነ።

አንዳች የአላህ ተዓምር መጥቶ ወደ ቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ እስኪፈጠር ግን በደሴቷ ውስጥ መቆየቱ እንደማይቀር በማሰብም የሚጠለልበት ትንሽ ግዜያዊ ጎጆ ቤት ሰራ። አንገቱ ላይ ባንጠለጠለው ቦርሳ መሰል ይዞት የነበረውንም እቃ ጎጆዋ ቤት ውስጥ አስቀመጠ።

ወደ ጫካው በመግባትም የተለያዩ የሚበሉ ፍራፍሬዎችንና ቅጠላ ቅጠሎችን ማግኘት ቻለ። በዚሁ ሁኔታ በደሴቷ መኖር ጀመረ.....

ከዕለታት አንድ ቀን ምግብ ፍለጋ ወደ #ጫካው ሄዶ ሲመለስ ትንሿ ጎጆ ቤቱ በእሳት እየተቀጣጠለች ደረሰ። በተመለከተው አጋጣሚ በጣም አዘነ። የበለጠ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም አደረበት።

"አላህ ሆይ! ለምንድን ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የምትፈፅምብኝ!?" በማለትም በጣም አለቀሰ።

በተከታዬ ቀን የሆነ ድምፅ ከእንቅልፋ ቀሰቀሰው። ወደ ደሴቷ እየቀረበች የነበረች አንዲት መርከብ ናት ከእንቅልፋ የቀሰቀሰችው። መርከቧ እሱን ለመውሰድ ነበር ወደ ደሴቱ የመጣችው።

ሁኔታውን ማመን ያቃተው ሰውዬው "በዚህ አካባቢ እኔ መኖሬን ማን ነገራችሁ?" በማለት መርከቧ ላይ የነበሩትን ሰዎች ጠየቀ። እነርሱም "ትናንት ከዚህ አካባቢ የሚወጣ #ጭስ አይተን ነው የመጣነው" ሲሉ መለሱለት።


#አስተምህሮት.....
እኛ ሰዎች አጋጣሚዎች ሁሉ መጥፎ ሲሆኑብን በቀላሉ ተስፋ እንቆርጣለን። እንዲህ በቀላሉ መሸነፍ የለብንም። ምክንያቱም አልህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኛን በተመለከተ ሁል ጊዜ ስራ ላይ መሆኑን መዝምንጋት የለብንም። በመከራችንና በህመማችን ወቅትም እንኳ ቢሆን እርሱ አይረሳንም።

JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
#ሀሊማ የተሰኘ ምርጥ ተከታታይ ታሪክ ከነገ ማታ ጀምሮ ልናቀርብ ወደናል ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ👍
ሁለቱ ባል እና ሚስቶች የተጋቡት ዛሬ ነው። በጣም ይዋደዳሉ። የተጋቡት እርስ በእርስ በሸሪዓ ህግ መሰረት ሽማግሌ ልከው ሳይሆን በሶሻል ሚዲያ ትውውቅ ነው። ሆኖም ግን ፍቅራቸው ከዚያ የላቀና የሚያስቀና ነበር። በፍቅር እና በደስታ ሁለት አመታትን በጋራ አሳለፋ። ከሁለት ዓመት በኋላ...

አሁን አሁን ባል በንዴት መበሳጨት ጀምሯል። እሷም ብትሆን ይህ ባህሪው ስላላማራት ነገር ብቻ መፈልፈል ሆኗል ስራዋ። ከእለታት አንድ ቀን ከስራ ተመልሶ መጣ። ያኔ የተጋቡ ሰሞን በፈገግታ እና በደስታ ተቀብላ የምታበላው ሚስቱ፣ ምሳ ሳትሰራ ሞባይሏ ላይ ተጥዳ ይመለከታታል። በንዴት "ለምንድነው ምሳዬን ያልሰራሽው!?" ሲል አንባረቀባት። እሷም በንቀት አይን ሰራተኛህ እየሰራችልህ ነው ስትል መለሰች...

ይሄኔ የንዴት ጣርያ ላይ ደርሶ የነበረው ባል ሞባይሏን ከእጇ መንጭቆ በመወርወር ከቤቱ ግርግዳ ላይ ከሰከሰው። በዚህም አልተብቃቃም የሚስቱን ፊት ባለ በሌለ ሀይሉ በጥፊ አጮላት። እሷም ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች። በዚህ ህመሟ ላይ ሌላ ህመም እንዲህ ሲል ጨመረላት "አንቺን ከማገባ የኛን ቤት ሰራተኛ ባገባ ኖሮ እንዲህ አይልሆንም ነበር። እሷ ካንቺ 100እጅ ትበልጣለች" ሲል የቅናት ቃጠሎ ውስጥ እንድትገባ አደረጋት።

ሰራተኛዋ ለንግግሩ ማፅደቅያ ላይ ይሁን ባይታወቅም ምሳውን ቆንጆ አድርጋ ይዛ መጣች።... ለነገሩ ሰራተኛዋ በፍቅራቸው እጅግ በጣም ትቀና ነበር። ተንኮለኛ መሆኗንም ፊቷን የተመለከተ ማንኛውም ሰው መገመት አያቅተውም። የሆነው ሆኖ አባ ወራው ሚስቱን የበለጠ ጠልቶ ለሰራተኛዋ እንዲያደላ የሚያደርግ ስራ ሰራች።

ይህንን የተመለከትችው ሚስት ስራዋ ሌተ ቀን ባልን ለማስደሰት መጣር ሆነ (ለነገሩ የሚስት ስራ ባልን አስደስቶ ጥሩ ማህበረሰብን መፍጠር አይደል!!)። ነገር ግን ከባሏ የምታገኘው ምላሽ እሷን የሚያስከፋ ብቻ ነው። ጨው በዛ፣ በርበሬው ያቃጥላል፣ ሽንኩርቱ አልበሰለም፣.......ውሃው ቀጠነ የእለት ተዕለት ጭቅጭቁ ሆነ። ሚስት ይህን ሁሉ በሰብር ታሳልፋለች። ጥፋቷ ምንም የማታውቀውን ሰው ከሶሻል ሚዲያ ብቻ ተዋውቃ ማግባቷ እንደሆነ ይሰማታል።

ሆኖም ግን ተስፋ አልቆረጠችም። የሰራተኛዋ ተግባር ደግሞ ልክ እንደሚስቱ ባልን ወደ ራሷ ለመሳብ እና ሚስት ላይ ውሽማ ሆና አረፈችው። ባል ከሰራተኛዋ ጋር ዝሙት ባይፈፅምም ሁል ጊዜ ለርሷ ያደላ ነበር። አንድ ቀን ይህች ሰራተኛ የሚስት ምግብ ውስጥ መርዝ በመክተት ልትገድላት ታስባለች። ባልየውን ማንም እንደማይቀማት በማመን ይህንን ስራ ለመከውን ዝግጅቷን አጠናቃ እነሆ ለሚስት የመጨረሻ እራት የሚመስለው ቀን ደረሰ። ተሳክቶላት መርዙን የሚስት ምግብ ውስጥ ጨመረችው። ሚስት የጎረሰችው 5 ጉርሻ ብቻ ሲሆን ወዲያውኑ ሆዷን ራሷን ሁሉ ነገሯን ያማት ጀመረ። እዚያው የእራት ገበታ ላይ በፊቷ ተደፋች። ይሄኔ ይጠላት የመሰለው ባል ተንደርድሮ አቀፋት። ሚስት አረፋ ከአፏ ውስጥ ይፈሳል። በፍቅር አይን ትመለክተዋለች። ባል በጣም አለቀሰ። ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብሎ በፍጥነት ወደ አቅራቢያው ጤና ተቋም ይዟት በረረ። ከብዙ ርብርብ እና የቀዶ ጥገና ህክምና በኃላ ሚስት.....





በአላህ ፍቃድ ዳነች። ባልየውም በደስታ እቅፍ አድርጎ ሳማት። እጅጉንም እንደሚወዳት ከድሮው በበለጠ ይገልፅላት፣ ያሸታት፣ ይስማት፣ ገባ። በጣም ደስ አላት። እንደ አዲስ የተጋቡ ይመስል አላህን አመሰገነች።

ያቺን መርዝ ሰራተኛ ባል እየጠፈጠፈ ለህግ አሳልፎ ሰጣት። በሰው መክደል ወንጀል ሙከራም 15ዓመት ዘብጥያ ወረደች። ባልና ሚስትም ከዚያ ግዜ በኃላ በሰላምና በፍቅር ይኖሩ ጀመር።

#አስተምህሮት.......
አላህ መጥፎ ነው ብለህ ምታስበውን ነገር ላንተ ኸይር ሊያደርግልህ ይችላል። ስለዚህ ሁሌም #አልሃምዱሊላህ በል!!

JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
2
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀሊማ
ክፍል ①
በሂክማ ጀማል


"ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠችው ነው የምንኖረው"
.
ዛሬም እንደ ወትሮዋ ከእኩዮቿ ጋር ለመጫወት ከ ቤት ወጥታ ወደ ጓደኞቿ ጋር ሄደች፡፡ ሀሊማ በጣም ተጫዋች ደስተኛ እና ሁሉም ሰው የሚወዳት አይነት ልጅ ናት የተወሰነ ሰአት ከተጫወተች ወዲህ እረሀብ ቢጤ ተሰማት ያው የልጅ ነገር እረሀቡን ለማስታገስ ያህል ብቻ ነው እነደነገሩ ምግቡን ቀመስ ቀመስ የሚያደርጉት፡፡ ከዛ ወደ ጨዋታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ሰአቱ ከ ጠዋቱ 5፡30 ይላል ሀሊማ ጓደኞቿን ተሰናብታ ወደ ቤቷ ሄደች ፡፡ ነገር ግን እቤቷ ስትደርስ ያልጠበቀችውን ነገር ያጋጥማታል ያ ክስተት ህይወቷ አንዲከብድ ያ ያሰለፈችው ጨዋታ እንዳይደገም የደረገውን ደስታዋ ሁሉ ጠፍቶ ቀሪ ጊዜዋን በ ሀዘን እንድታሳልፍ ያደረገ ክስተት ነው ሀሊማ በራፍ ላይ ስተደርስ ያልጠበቀችው ነገር ያጋጥማታል ያለ ወትሮ የግቢቸው በር ተከፍቶ ታገኘዋለች ትንሽ ግራ ገባት ምን አልባት ኡሚ እደከፈተችው ረስታው ይሆናል ብላ አሰበች በሩን ድምፅ ሳታሰማ ቀስ አድርጋ ዘጋችው ፡፡

ሌላ ግዜ እንደምታደርገው እናቷን ጋር ሰትደርስ በቀስታ ኮቴ ሳተሰማ ትሄድና ታስደነግጣት ነበር ዛሬም እንደ ወትሮዋ እናቷን ለማስደንገጥ እናቷን ሁሌ ወደ ምታገኝበት ቦታ ኩሽና ሄደች ግን እንደጠበቀችው አልሆነም እናቷን ኩሽናው ውስጥ ልታገኛት አልቻለችም ምን አልባት ሳሎን ትሆናለች ብላ ወደ ሳሎን ቤት በተመሳሳይ መልኩ እየተራመደች ሄደች ግን እዛም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ነው ያጋጠማት ሀሊማ እናቷ ያለወትሮዋ ሁሌ ከምታገኛት ቦታ በማጣቷ ትንሽ ግራ ተጋብታ ቁጭ ብላ መጠበቅ ጀመረች ኡሚ ...ኡሚ... ብላ ልትጠራት አስባ ግን ድንገት አንድ ሀሳብ መጣላተ መኝታ ቤት ለምን አላያትም የሚል አሁንም እዛም ቢሆን ካገኘቻት ከሃላዋ ሆና ለማስደንገጥ እንዲያመቻት ቀስ አያለች ወደ መኝታ ቤቱ አመራች ነገር ግን የሆን ድምጽ ሰማች የ እናቷ ድምጽ አይደለም ማን ይሆናል ያለው እያለች እየፈራች ወደ ክፍሉ ተጠጋች በሩ አልጠበቀም ነበርና ቀስ ብላ ጠጋ አደረገችው የ አባቷ ድመጽ ሰማች በዚህ ሰአት እቤት ምን ይሰራል ብላ አሰበች ጠዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ ስራ እንደሄደ አስታወሰች ታዲያ እንዴት መጣ ብላ እያሰበች በሩን ከመጀመሪያው ትንሽ ጠጋ አድርጋ አንገቷን ወደ ውስጥ አስገባች ግን ምንም ያልጠበቀችው ነገር ነበረ የተመለከተችው ሁለት አንድ አመት ያልሆናቸው ታናናሽ መንታ እህትና ወንድሟ አልጋው ላይ እንደተኙ ናቸው
:
አልጋው ግርጌ ጋር በጀርባዋ ተንጋላ ወድቃለች ከ አንገቷ አካባቢ ደም እየፈሰሰ ነው፡፡ አባቷ ደንግጦ ባለበት ደርቆ ቆሞዋል ከአልጋው ጎን ሰሚራ የሆነ ብረት የሚመስል ነገር ይዛ ቆማለች ሰሚራ ማለት ጓረቤታችን እና የ እናቴ የቅርብ ጓደኛ ነች እኔ ሳልወለድ ጀምረው ጓደኛ ናቸው አሁን እኔ ሰባት አመቴ ነው እነሱ ከዛም በፊት ጀምሮ ጓደኛ ናቸው ነገር ግን ዛሬ ያየሁትን ነገር ማመን አልቻልኩም ብረቱን ለምንድነው የያዘችው ምን ልታደርግበት ነው ብዬ አሰብኩ......
አባቴ ራሱን ከመሳት በማይተናነስ መልኩ ነበር ደንግጦ የቆመው፡፡ አባቴ ትንሽ ወደ እራሱ እንደመመለስ ሲል ወደ እናቴ ተጠግቶ ለማንሳት ሲሞክር በድንገት ሰሚራ ፊቷን አጨማዳ
.
"ምን ለማድረግ እየሞከርክ ነው" ብላ ጮኧችበት
.......ወደ ሀኪም ቤት ልወስዳት ነው አላት እየተርበተበተ በምላሹም ሰሚራ ......."ከዛስ ባክህ ምን ሆና ነው ሲሉህ ምን ልትላቸው ነወ እኔ እና የባለቤቴ ጓደኛ በጣም ስለተዋደድን እሷን ደግሞ መፍታት ስለማልችል እኔ እና ሰሚራ ተመካክረን ልንገድላት አስበን ሰሚራ በብረት ጭንቅላቷን መታት ነው ብለህ ልትነግራቸው ነው " ብላ አፈጠጠችበት ይሄን ስሰማ በዛ በጨቅላ አቅሜ መሸከም ከምችለው በላይ ነበር ሰሚራ ብረቱን ለምን እንደያዘችው ያኔ ነበር የገባኝ መቋቋም አቃተኝ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም አንድ ሰው ከሞተ ድጋሚ ከሰዎች ጋር መገናኘት እንደማይችል ነበር እናቴ የነገረችኝ ታድያ እናቴንም ድጋሚ ላገኛት አልችልም ማለት ነው .......ስለ ሞት እንኳ በቅጡ አላውቅም ነበር አይሆንም አባቴ እንዲህ አያደርግም አባቴ እናቴን በጣም ነወ የሚወዳት እያለኩ ከ እራሴ ጋር አወራለሁ፡፡ አባቴም መናገር ጀመረ ይበልጥ ተጠግቼ ማዳመጥ ጀመርኩ እሱ ይሄን እንደማያደርግ እንዲያረጋግጥልኝ በማሰብ ግን



ክፍል 2
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
Audio
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 10◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒
ስለዘገየን በጣም በጣም ይቅርታ🙏🙏🙏
➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
❤️❤️❤️❤️❤️❤️ጀሊሉ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አንተ ነህ ጀሊሉ የልቤ መድመቂያ፤
ቦታ የሰጠኸኝ እስከ እድሜዬ ማብቂያ፤

ከሁሉም አልቀህ እኔን የፈጠርከኝ፤
በኢስላም መንገድ ላይ እንድኖር ያረግከኝ፤

ይህ ብቻ በቂ ነው ማስተዋል ቢኖረኝ፤
ሌላ ምንም ባይኖር ዲኔን ከሰጠኸኝ፤

ስጦታህን ሁሉ ዘወትር አስታውሰኝ፤
በሰጠኸኝ ፀጋ ማመሰግን አርገኝ!!!
🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲
🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲

#Siham S
LuK 01

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
አልቅሳ አታቅም

አልቅሳ አታቅም ነፍሴ እሳት ፈርታ
ቺኳ ከተቆጣች ያቀልጣል ኡኡታ
ዱንያ ወዶ ልቤ ቀን ማታ ይሰራል
ፊርዶስ ከተባለ ፍራሽ ይፈልጋል
ልቤ ምን ወደደ ለየትኛው ስራ
መልስልኝ ልቤን የአላሁ አደራ
ኸይሩን ምረጥላት ወዳንተ ትመራ
ጠብቀኝ ያረቢ ከመጪው ኪሳራ

#መሀመድ አሚን ይማም
Luk 17

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
👍1
አይረሳኝም ብለሽ!

"ከሠጠሁት ፍቅር፣ካሳየሁት አሳር፣
ከቶ አይረሳኝም፣ካሳለፍነው አንፃር!
"ልርሳት" ቢል እንኳ በሒደት ያረጃል
የመርሳት መንገዱ ዕድሜውን ይፈጃል!"
እያልሽ ታስቢያለሽ...
እያልሽ ታደቢያለሽ...
ከንቱ ነው ሐሳብሽ፣ከንቱ ነው ድካምሽ
እንደውም ...እንደውም. .
ማን ነበረ ሥምሽ?

#ፈይሠል_አሚን
Luk 27

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
👍1
ዘርህ ካላማረ፣ቆዳህም ካልነጣ፣
በእግር ይበየናል፤የመሰንበት ዕጣ!
በበዳይህ ስሌት፣በአሳሪህ አቋም፣
መተንፈስ ለመቻል
ሰው መሆን አይበቃም(!)(?)

#ፈረሀን
Luk 33

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
"ለምን ሞተ?" ቢሉ
እንደዚህ ብላችሁ ፣ ንገሩ ለሁሉ
ሳትሸፋፍኑ ፣ ሳትደብቁ ከቶ
"እጁን በሳሙና ፣ ሳይታጠብ ቀርቶ
አትሰብሰብ ሲሉት ፣ ስብሰባ አብዝቶ
የትም ሲንጦሎጦል ፣ ቤት መሆንን ጠልቶ
ከሰው ተጨባብጦ ፣ ከሰው ተጠጋግቶ
ከምክር ተኳርፎ ፣ ከተግሳፅ ተጣልቶ
ዘመድ መገኖቹን ፣ ለክፎ ለሞት አጭቶ
ሞተ በቃ ሞቶ።
።።።
#Faysal Ahmed
Luk 35

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
ወንጀላችን በዝቶ መቶበት ሢሳነን
የአምላክ ቁጣ መጥቶ ይሀው ተሠቃየን
‼️
በአይን እማናያት በትንሽ ፍጥረት
የት እንኩዋን እንደምትኖር ያላወቅንላት
🔥
በአየር ላይማትቆይ ለብዙ ሰአት
ምድርም ካረፈች ነብሷ ሚለያት
🦠🦠🦠
#COVID19 ብለው ሰየሟት
አሏህ ይጠብቀን በሱዋ ከመሞት!!

#ጌታዬ
Luk 36

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
ሀሊማ ክፍል ① በሂክማ ጀማል ፡ ፡ "ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠችው ነው የምንኖረው" . ዛሬም እንደ ወትሮዋ ከእኩዮቿ ጋር ለመጫወት ከ ቤት ወጥታ ወደ ጓደኞቿ ጋር ሄደች፡፡ ሀሊማ በጣም ተጫዋች ደስተኛ እና ሁሉም ሰው የሚወዳት አይነት ልጅ ናት የተወሰነ ሰአት ከተጫወተች ወዲህ እረሀብ ቢጤ ተሰማት ያው የልጅ ነገር እረሀቡን…
"ሀሊማ"
ክፍል 2
ሂክማ ጀማል




......አባቴ መናገር ጀመረ ግን እኔ እንደጠበቁት ሳያሆን የበለጠ እንደገደላት የሚያረጋግጥ ነገር ነበር የተናገረው
"ሰሙ ልክ ነሽ "አለ ግን..... ሲል እንዳትጨርሰው
"ምንም ግን የሚባል ነገር የለም ባይሆን ሬሳዋን ምን እንደምናደርገው እናስብ" አለችው፡፡
...."እሺ ልጆቼስ "አላት "ለእነሱ እኔ አለሁ ደግሞ ተነጋገርንበት አይደል" አለችው ፡፡
..........አባቴ በጣም በጨነቀው ድምፅ" እሺ ለ ሀሊማስ እናቴስ ካለችኝ ምን ልላት ነው?"
........"የሆነ ምክንያት እንነግራታለን ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ክፍለ ሀገር እንደ ሄደች ወይም ሌላ ምክንያት እንነግራታለን"አለችው
ሌላ አማራጭ ስለሌለው እሺ አላት ይህንን ሀሊማ ስትሰማ ምድር የተደፋባት የህል ነበር የተሰማት በሩን ከፍታ ወደ ወስጥ ገብታ የእናቷን ሬሳ ለመንካት፣ ድጋሚ የማላገኛት ከሆነ ልሳማት ብላ አስባ በሩን ጠጋ ለማድረግ ስትሞክር ሰሚራ እጅ ላይ ያለውን ብረት ተመለከተችው፡፡እናቷን ብረቱ መትታት እንደገደለቻት ስትናገር ሰምታለች የእናቷ እጣ ለ እሷም እንዳይደርሳት ፈራች፡፡ ልትከፍተው የነበረውን በር መልሳ ተወችው የእናቷን ሬሳ ለመደበቅ ሲዋከቡ አየቻቸው፡፡ ሞት ማለት ምን እንደሆነ በማታውቅበተ እድሜ ላይ ሆና በንጹህ አእምሮዋ የ እናቷን አሰቃቂ ሞት፣የ አባቷ ጭካኔ አየች፡፡ አባቷ ይህ ሁሉ ሲሆን ሀሊማ እንደማታውቅ ነው ያሰበው፡፡ ከመኝታ ቤቱ ለመውጣት ሲሞክሩ ሀሊማ በሞተ አቅሟ እተንቀጠቀጠች ቤቱ ለቃ ወጣች፡፡ በጣም ስለደነገጠች ሰውነቷ ደርቆዋል ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም፡፡ እንዲሁ እግሯ ወደ መራት አቅጣጫ መሄድ ጀመረች ረጅም መንገድ ከሄደች በሃላ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግራ ገብቷት አንድ ጥግ ላይ ተቀምጣለች፡፡

.....እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሀሊማ በተቀመጠችበት መንገድ የሀሊማ
የእናቷ የቅርብ ዘመድ የሆነችው ፋጡማ በዚያ መንገድ ስታልፍ ሀሊማን በ አትኩሮት ተመለከተቻት ሀሊማ ግን ቀድማ ፉጡማን አይታታለች ግን ማን እንደሆነች ማገናዘብ አልቻለችም፡፡ ፉጡማም ግራ በተጋባ ሁኔታ አየቻት ፊቷ አዲስ አልሆነባትም በደንብ ለማየት ሞከረች ግን የሀሊማ ሂጃብ ስለተዝረከረከ ከፊል ፊቷን ሸፍኗታል፡፡ማን ትሆን እያለች ማሰብ ጀመረች እንደዚ ትንሽ ልጅ የት ነው የማውቀው ብላ ትንሽ እንደማሰብ ካለች በኃላ የ አክስቷ ልጅ የሆነችው ዘይነባ የሷ ልጅ ሀሊማ ትሁን ብላ አሰበች ሀሊማ ብትሆን አይታኝ ዝም አትለኝም፡፡እንኳን እንዲ አይታኝ በ ስልክ እራሱ እንዴት እንደምትሆን እያለች ብቻዋን እያወራች ደግሞ እዚህ ድረስ ምን ልትሰራ መጣች በዛ ላይ ብቻዋን አይ እሷ አይደለችም ብላ አልፋት ሄደች፡፡
:
:
ክፍል 3
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
የፈቲ ባል …….ክፍል 11 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 11◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
"ሀሊማ"
ክፍል 3
ሂክማ
:
:

....የተወሰነ መንገድ ከሄደች በኃላ ግን ውስጧን የሆነ ነገር ከነከናት፡፡ እና ልጅቷ ምን ሆና ይሁን ብላ አሰበች፡፡ ለምን ሄጄ አልጠይቃትም ብላ ትንሽ ቆም ብላ አሰበችና ወደ መጣችበት መንገድ ተመለሰች፡፡ ነገር ግን ሀሊማ ከነበረችበት ቦታ ለቃ ሄዳለች፡፡ ፋጡማ በጣም ተናደደች ለምን መጀመሪያ ሄጄ አላናገርኳትም ብላ እራሷን ወቀሰች፡፡ እዛው አካባቢ ዞር ዞር እያለች መፈለግ ጀመረች ወደ አንዱ አቅጣጫ ስትመለከት ሀሊማ በተዳከመ አቅሟ እየተጎተተች እየሄች ተመለከተቻት ፡፡ በጣም ቢራራቁም ማየት ችላለች ፡፡
.
በፍጥነት እየተራመደች እርቀታቸውን እያጠበበች ሄደች በጣም ስትቀርባት "ሚጣ.....ሚጡ .... ኧረ ሚ....ጡ.... "እያለች ተጣራች ሀሊማ ግን ጭራሽ አልሰማቻትም አሁንም እየሄደች ነው፡፡ ፈጡማ ከመጀመሪያው በላይ በጣም እየፈጠነች የሞት ሞቷን አጠገቧ ደረሰች፡፡ "እንኪ ሚጡ" ብላ እጇን ይዛ ወደ እራሷ ስታዞራት ጭራሽ ያላሰበችውን ነገር ነበር ያየችው "ሀ..ሊ..ማ" አለቻት ምንም መልስ አልሰጠቻትም እራሷን ለማረጋጋት እየሞከች "እዚህ ብቻሽን ምን ታደርጊለሽ ?"አለቻት የሀሊማ ያለወትሮዋ ዝም ማለቷ እየገረማት አላወቅሽኝም እንዴ ፋጡማ አክስትሽ እኮ ነኝ ምንም አይነት መልስ የለም፡፡ በሁኔታው ግራ እንደተጋባች ፋጡማ ቤቷ እዛው እቅራቢያ ስለነበር ይዛት ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ ሰውነቷ ጠውልጎዋል ከንፈሯም ከሚባለው በላይ ደርቆዋል ፋጡማም ፊቷን ፣እጇን እና እግሯን አጠበቻት፡፡ሀሊማ ከቅድሙ ትንሽ እንደ መንቃት እያለች ነው ወደ ውስጥ ይዛት ገብታ የሚበላ አቅርባላት እያበለቻት ሳለች ስልኳን አንስታ ወደ አባቷ ጋር ለመደወል "ቤት ልደውልላቸው አይደል?" አለቻት አንገቷን በመነቅነቅ እንዳትደውል በምልክት ነገረቻት፡፡ "እሺ ቤት አልደውልም ግን ምን እንደሆንሽ ንገሪኝ" አለቻት ምን ብላ ትንገራት ዝም አለቻት፡፡ "እሺ በቃ ልደውል ነው"ስትላት ሀሊማ በድንገት እንባዋ እንደ ጉድ መውረድ ጀመረ መናገር ትፈልጋለች ግን አፏ ተሳስሮባታል፡፡

ፍጡማ በሁኔታዋ ትንሽ ተረበሸች፡፡ "እሺ በቃ ተይው አትነገሪኝ" ብላ ከተቀመጠችበተ ተነስታ ሀሊማ አጠገብ ሄዳ እቅፋ አባበለቻት በጣም እርቧት ስለነበር የበላችው ምግብ አደካከማት፡፡ ገና አቅፋት ጸጉሯን ማሻሸት እንደጀመረች እንቅልፍ ይዟት ሄደ ፈጡማም ሀሊማ እንደተኛች ስታይ አስተካክላ አስተኝታት የሀሊማ አባት ጋር ለመደወል ስልኳን ይዛ ወጣች::
:
:
:
ክፍል 4
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
የፈቲ ባል …….ክፍል 12 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል-1
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 12◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒
የመጨረሻ ክፍል ነገ ማታ ከ100👍 ቡሀላ ይለቀቃል
➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
"ሀሊማ"
ክፍል 4
ሂክማ ጀማል
:
:

ለመደወል ስልኳን ይዛ በሩን ጠጋ አድርጋላት ወጣች፡፡ "ልደውል ወይስ ይቅር ሀሊማ ልደውል ስላት ለምን አለቀሰች?አባቷ ጋርእንድደውል ለምን አልፈለገችም? ለነገሩ አባቷ ጋር ከመደወል ዘይነባ ጋር መደወል የተሻለ ይመስለኛል፡፡" ብላ አሰበች "ግን ደግሞ ምን ልትሰራ እዚህ ድረስ መጣች ለዛውም ብቻዋን" ብዙ ጥያቄዎች አእምሮዋ ውስጥ ተፈራረቀባት፡፡ ግን ለማንኛውም አባቷ ጋር ከመደወል ዘይነባ ጋር መደወል የተሻለ ነው ብላ አሰበች፡፡

091325...... የዘይነባን ስልክ ቁጥር ተጭና መደወል ጀመረች ይጠራል ከአሁን አሁን ስልኩ ተነሳ እያለች በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆና እየጠበቀች ነው፡፡

የዘይነባ ስልክ ቻርጀር እንደተሰካ ነው ሰሚራና ከድር ሳሎን ቤት ውስጥ ቁጭ ብለዋል፡፡ከድር ማለት የሀሊማ አባት ነው ዘይነባን ለመግደል ሲያስቡ ነገሩ እንዲህ ከባድ ይሆናል ብለው አላሰብም ነበር፡፡ እስኪመሽ ጠብቀው ሬሳውን የሆነ ቦታ ላይ ለመደበቅ ተስማምተው እስኪመሽ እየጠበቁ ነው፡፡ድንገት ግን የ ዘይነባ ስልክ ሲጠራ ሁለቱም በጣም ደነገጡ፡፡ ሰሚራ ከተቀመጠችበት ተነስታ ስልኩ ወደሚጠራበት ቦታ ሄዳ ስልኩን ከቻርጀሩ ላይ ነቀለችው የተመዘገበ ስልክ ነው ፈጡማ ይላል ብላ ልታቀብለው እጇን ስትዘረጋ "እኔ አንስቼ ምን እንድላት ነው የምትሰጭኝ እራስሽ አንሽው" በዚህ መሀል ሁለቱም እየተጨቃጨቁ ስልኩ ተዘጋ ሰሚራ ስልኩን ይዛ መጀመሪያ ወደ ተቀመጠችበት ቦታ ሄደች፡፡ ከ ጥቂት ደቂቃዎች በሀላ ድጋሚ ስልኩ ጠራ ስልኩን ደፍሮ አንስቶ የሚያናግር ጠፋ ሰሚራ አሁንም ስልኩን እንደያዘች ነው፡፡
ፋጡማ ከመጀመሪያው በላይ አሁን ይበልጥ ተጨነቀች፡፡ የሀሊማ ሁኔታ የስልኩ አለመነሳት አንድ ላይ ሲሆኑ ብዙ መጥፎ መጥፎ ሀሳቦች እንድታስብ አደረጋት፡፡ ኧረ ምን ሆነሽ ነው ፋጡማ ደግ ደጉን አስቢ እንጂ አለች ፈጡማ እራሷን ለማረጋጋት እየሞከረች ምን አልባት አላየችው ይሆናል ብላ ድጋሚ ስልኩን መደወል ጀመረች፡፡ ከድርና ሰሚራ እንደዛው እንደተፈጠጡ ናቸው፡፡ ፋጡማ ኔትዎርክ አስቸገሯት ደጋግማ እየሞከረች በመጨረሻ ተሳካላት መጥራት ጀመረ ሁለቱም በድጋሚ በጣም ደነገጡ ሰሚራ ከድርን አፍጥጣ እያየችው ነው በ አይኗ አንሳው እያለች ትእዛዝ የምትሰጥ ነው የሚመስለው፡፡ ሰሚራ በከድር ዝምታ ተናዳለች ፡፡ፋጡማ በበኩሏ ኧረ አንሽው ...አንሽው እያለች ነው ሀሊማ አሁንም እንደተኛች ናት ግን ድንገት ሰሚራ ስልኩን ብድግ አድርጋ የማንሻውን ቁልፍ ተጭና ሄለው አለች



ክፍል 5
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍2