ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
መሀን አራስ
ክፍል አስራ አራት
(ሚስጥረ ጀማል)

በቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ:: አማቼ እኔ ለቤተሰቧ አልበቃሁምና ሌላ ምራት አመጣች ባሌም ባላችን የሚሆንላትን ሁለተኛ ሚስት ተቀበለ :: ምናልባትም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ቴቴ ጋር መሄድ ያዘወተረው ቴቴም ግዳይ እንደጣለ ጀግና ሥትሸልልብኝ የነበረው ለዚህ ነው:: ሠሚር ሆን ብሎ ይሄንን ጉዳይ እንደማይቀበል ከእንባውም ለመረዳት ግልፅ ነው:: ነገር ግን ቴቴን የማሸንፍበት ምንም የቀረ ጉልበት የለኝም:: ሁሉ ነገር ካቅሜ በላይ ሁሉ ነገር ከመቻል ገደቤ ያለፈ ሆኖብኛል ::ደክሞኛል!!! በርግጥ ሠሚር ሁለተኛ ሚሥት ማግባት ይፈቀድለታል:: በዛ ላይ አቅሙ ኖሮት ከሁሉ በላይ ደግሞ ከኔ ከመጀመርያ ሚስቱ የአይን ማረፍያ የሚሆን ዘር ባለማግኘቱ:: "ለሠሚር የምታዝኝለት ከሆነ አይንሽ እያየ ይሄ ሁሉ ሃብትና ንብረቱ ያለወራሽ እንዲቀር አትፍረጂ እዘኝለት" የቴቴ ንግግር ነበር:: "አዲሷን ልጅ የፊታችን እሁድ እጇን ከቤተሠቧ ልንጠይቅ ነው። በርግጥ ምንም ለውጥ የለውም ግን ሠሚር ላንቺ ካላሣወቅኩኝ ሞቼ እገኛለሁ ሢል ነው ዛሬ የመጣነው:: በይ አሁን እንሂድ በደንብ ተዘጋጂበት"
አማቼና እጩ የባሌ ሚሥት በቆምኩበት ትተውኝ ሄዱ ።የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ :: በኔ ቤት ዛሬ በፋኪሃ ምክንያት አዲሥ የደሥታ ምዕራፍ ልጀምር ማሠቤ ነው ።በርግጥ በማርያና ሠበብ አዲሥ ምዕራፍ እየተከፈተ ነው ነገር ግን ከደሥታ የራቀ:: በዚህ የሃዘን ድባብ ውሥጥ ሆኜ አዲሷን የልጄን እናት የፋኪሃን ክፍል አሥተካክዬ እረፍት እንድታደርግ ብቻዋን ተውኳት:;
'ምናልባትኮ ቴቴ ልክ ናት በትእግሥት ይሄን ሁሉ አመት ቢታገሥም ልጅ ልሠጠው አልቻልኩም። በዛ ላይ ጌታዬም የፈቀደለትን እንጂ አዲሥ ነገር አይፈጠርም :: 'ሥል ለራሤ ነገርኩት አንዳንዴ እንደ ሃኪም ትእዛዝ መራራ የህይወት መጠጦችን ጉንጭ እና ጉንጫችን ተጨምቆ በሚከፈተው የአፋችን ፍልቅቅ መሃል ያን መራራ መድሀኒት እንጠጣለን ምናልባት ሊያድንም ላያድንም እንደሚችል ብናውቅም አማራጭ ባለመኖሩ።
የዛኑ ቀን ማታ ሠሚር ሣይመጣ አመሸ ልክ ከምሽቱ ስድሥት ሠአት ላይ ቴቴ ጋር ነኝ የሚል የፅሁፍ መልእክት ገባልኝ:: የኔ ምሥኪን በዚህ ጭንቅ አጣብቂኝ ውሥጥ ሆኖ እንኳ ያሥብልኛል:: ልበል??? ወይሥ እኔ እዚህ ስጨናነቅ ከአዲሢቷ ሴት ቅርብ ሆኖ ማደርን ተመኝቶ ሄደ ልበል??? እንጃ ሠሚር ግን እንዲህ ያደርጋል ብሎ ከማሠብ አለማሠቡ ይቀላልና ጉዳዬን ለማሥተካከል ግዜ ወደማይፈጅበት ጌታዬ ሙሉ የነገሬን መረጃ ለማቀበል ይረዳኝ ዘንድ ውዱዕ አድርጌ ከጌታዬ ፊት ተገተርኩ :: ሠላተል ኢስቲሃራ ሠግጄ ለባሌ የተሻለውን ይሠጠው ዘንድ ለኔም የወደደልኝን ያሥወድደኝ ዘንድ ልመናዬን አቀረብኩ::
በማግሥቱ ሰሚር አንገቱን እንደደፋ ወደ ቤት ተመለሠ እኔም ሌላ ሴት እንዲያገባ መፍቀዴንና ይሄንን የሚያደርገው ሆን ብሎ አለመሆኑን እንደምረዳው ገለፅኩለት። ከደሥታው ጋር እየታገለ አነባ :: አቀፈኝ:: ከቀናት ቡሀላ ፊቴ ቆሞ ሣቀ:: ዐለሜ ሳቀልኝ:: ከዚህ በላይ ምን አለ??? በርግጥ እኔም ይሄ እንዳይፈጠር የሠው እርጉዝ ከጣራዬ ሥር አሥቀምጫለሁ ቀን ከሌት ጌታዬን ተማፅኛለሁ ግን አልሆነም:: ምናልባትም ጥሩውን ምረጥልኝ ያልኩት ጌታዬ ለኔ መጥፎ የመሠለኝ ጥሩ ሥለሆነ መርጦልኝ ይሆናልና ተቀበልኩ:: ሠሚር ረገመኝ::እኔም አሚን አልኩት
ለዚህም ይሆናል...
ምርቃቱን ቀርቶ እርግማኑን ወደው አሚን ያሉት ወዳጅ፣
መቀበል ነው ፅድቁ ከኣማልክት ቀርቶ ከሸይጧን ቢወዳጅ::
የተባለው::
በአንድ ወር ግዜ ውሥጥ የሽምግልናው ጉዳይ አልቆ የባሌ ሰርግ አንድ ሳምንት ቀርቶታል ።የልጄ እናት ፋኪሃም አሁን የሠባት ወር እርግዝና ላይ ናት:: ሥለሆነም በትንሽ ነገር ትደክማለች ፣ ትነጫነጫለች ቢሆንም ግን በምንም ምክንያት ላለማሣዘን የቻልኩትን ያህል እንከባከባታለሁ ። ሠራተኛ የሠራውን ምግብ እንኳን እንዳትበላ በእጄ ያበሠልኩትን በእጄ እመግባታለሁ። ምክንያቱም በኔ አሥተሣሠብ የሷ ማህፀን ለልጄ ብዬ የተከራየሁለት ቤት ነው። አከራይ ደግሞ በተከራዩ ሠበብ መሠቃየት የለበትም። እናም የቻልኩትን አደርጋለሁ ።ትምህርት ቤቷ ሄዳ እሥክትመለሥ እንኳን አላምናትም በዝያው ልጄን ይዛ የምትቀር እየመሠለኝ በቀን ውሥጥ ብዙ ግዜ እደውልላታለሁ :' በሌላ ጎን የግል የምሠራውን ሥራ የምቆጣጠረው እኔ ነኝ ወዲህ ደግሞ የሠሚሬ የጋብቻ ሥነሥርአት ሥለተቃረበ ውሥጤ በሀዘን እላዬ በድካም ዝሏል:: የምግብ እና የእንቅልፍ ፍላጎቴ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል:: ከዚህ ሁሉ ጀርባ የሠሚርን ሥሜት ለማንበብ እሞክራለሁ ፍፁም ደሥተኛ ይመሥላል ይሄ ያረጋጋኛል :: እኔም እሡም ተጎድተን አይቻልም ቢያንሥ በሽንፈቶች መሃል አንድ ተጠቃሚ ሠው ሊኖር ይገባል :: እንደተመኘሁትም ያ ሠው ሠሚር ሆኖልኛል:: ሠሚር እንደነገረኝ ከሆነ ከሠርጋቸው ቡሃላ ተከራይተው የሚኖሩበት ቦት እንደሚፈልጉ ነበር ነገር ግን ቴቴ ከለከለችው"ያንን የመሠለ የተንጣለለ ቤት የማንም የመንደር እርጉዝ እንዲኖርበት ነው እንዴ ቤትህን ጥለህ ምትወጣው" በማለት ሃሣቡን አሥቀይራዋለች ፋኪሃ ይሄንን የሠማች ቀን " ከዚህ በላይ ችግር ልሆንብሽ አልፈልግም"በማለት ልትሄድ ተነሥታ ነበር በሥንት ልመና እና የገባችልኝን ቃል በማሥታወሥ ሀሣቧን አሥቀየርኳት::

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍2
የፈቲ ባል …….ክፍል 5 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
<unknown>
◉ የፈቲ ባል ክፍል 5◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
Forwarded from ሙድ እንያዝ በእኛ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሀን አራስ
ክፍል አስራ አምስት
(ሚስጥረ ጀማል)

ከሠርጉ ቀን እሥከ ሣምንት ያሉትን ቀናት ሆቴል ከርመው ወደቤት እንደሚመጡ ተሥማማን።።በዛ ላይ ለኔም ቢሆን ሠሚርን ከነ አካቴው ከቤቴ ከማጣት ቤቴ ውሥጥ ኖሮ ከክፍሌ ማጣቱ የተሻለ መሥሎ ሥለተሠማኝ እኔው ቤት መኖራቸው እረፍት ሠጥቶኛል::
የሠርጉ ቀን ወደ አራት ሠአት አካባቢ በገዛ እጄ ባሌን ሞሽሬ 'ሌላ ሚሥት ይዘህ ና!' ብዬ መርቄ ሸኘሁት። ሠርገኞቹ ሁሉ ከወጡ ቡሃላ እኔ የልጄ እናት እና ያልተወለደው ልጄ ብቻ ቀረን:: እግሬን ብርክ ያዘኝ። እኔን ለመውሠድ ሲመጣ የሚደሠተው ሠሚር ሌላ ሚሥት ለመውሠድ እየሄደ ሲደሠት ሣይ ለራሴ አዘንኩ :: ራሴን በቀጭን ገመድ ባጠፋሁ ብዬ ተመኘሁ ግን ለማን ብዬ ?? ጌታዬ በመቀሥቀሻው ሁሉም በሠራት ቅንጣት ታህል ሥራ በሚጠየቅበት ቀን ነፍሴን ያለፍቃዱ ያጠፋሁበትን ቀጭን ገመድ በእጄ እንደያዝኩ ሲቀሰቅሠኝ "ማነው ይሄን መብት የሠጠሽ?" ሲለኝ ምን ምላሽ ሊኖረኝ ነው??? "እኔ የፈቀድኩለትን ሁለተኛ ሚስት ማን ሥለሆንሽ ትከለክያለሽ?" ሲለኝ ምን እለዋለሁ? አሥታግፊሩላህ!!! ይሄን የማይረባ ሃሣቤን ትቼ የሠው ማህፀን ውሥጥ ወደተቀመጠው ልጄ በመሄድ እንዲህ አልኩ፦"'ሀ' የሚልህ ካለ በርግጥም 'ሁ'ን የሚጠራልህ ሠው ይመጣል ለሁሉም ግዜ አለው::!"
ሣምቱን ሙሉ በሠሚር ናፍቆት ሥሠቃይ አሣለፍኩት። አልፎ አልፎ ይደውልልኝ የነበር ቢሆንም በዛ ብቻ ሥቃዬን ማጥፋት አልቻልኩም:: ቀኑ ደርሶ ባሌ ሚስቱን ይዞ መጣ። ለሁለቱም ይመጥናል ያሥፈልጋል ያልኩትን ሁሉ አሟልቼ ክፍላቸውን አዘጋጀሁ :: አሁን ሁሉ ነገር ፍትሃዊ ሆኗል ሠሚር ለኔ ያደረገውን ለአዲሷ ሚስቱ ለማርያና ያደርጋል። ለማርያና የገዛውን ለኔ ሣይገዛ አይተውም :: ማርያናም ልጅ ትሠጠናለች ቤታችን ይደምቃል ብዬ ሥለማሥብ እሷን ከመንከባከብ አልቦዘንኩም :: ቀናት ከሣምንታት እየተደራረቡ እየተገፋፉ ለሁለት ወራት ያህል በአንድ ቤት አንድ አባ ወራ ሁለት እማወራ እንዲሁም አንድ የኔን ልጅ ያረገዘች ንግሥት ሆነን ኖርን :: የኔ ንግሥት :: ነገር ግን ጤናዬ ልክ ሊሆንልኝ አልቻለም። ከግዜ ወደ ግዜ የሚባባሥ ችግር ይፈጠርብኝ ጀመር ከምግብ አቅም እንኳ ማንኛውንም አይነት ምግብ የመብላት ፍላጎቴ ጠፋ በየግዜው እያዞረኝ መውደቅ ሥራዬ ሆነ ይሄንን ነገር ከሠሚርም ሆነ ከፋኪሃ ደብቄያቸው ነበር ::
ስላዘገየን ይቅርታ እንጠይቃለን
ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
የፈቲ ባል …….ክፍል 6 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
<unknown>
◉ የፈቲ ባል ክፍል 6◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
መሀን አራስ
ክፍል አስራ ስድስት
(ሚስጥረ ጀማል)

አዲሷ የሰሚር ሚስት ማርያና ግዜያት በቆዩ ቁጥር በምን ምክንያት እንደሆነ ባይገባኝም ፀባይዋ እየተቀያየረ መጣ:: ከሠሚር ጋርም አልፎ አልፎ በሥሡ ሢጨቃጨቁ እሠማለሁ :: እኔም ላይ ፊቷን ካጠቆረችብኝ ቀናት ተቆጠሩ በርግጥ ማርያና የምትሠራውም የምትማረውም ነገር ሥለሌላት ለግዜው ከቤት መውጫ ምክንያት የላትም:: ቢሆንም ግን ልክ የሰሚር መኪና ከሠፈሩ እንደራቀ እሷም ለባብሳ ትወጣለች። የት እንደምትሄድ ባላውቅም ለሠሚር የመናገር ድፍረቱን አጣሁ:: በዛ ላይ ጭቅጭቃቸው እየባሠ ሥለመጣ ተጨማሪ ችግር ልፈጥር ስላልፈለግኩ ዝምታም መርጫለሁ::
ዛሬ ለሊት ሠሚር ከማርያና ጋር የሚያድርበት ቀን ነበር:: እሡ መስጅድ ደርሶ እሥከሚመለሥ በግዜ ተነሥቼ ቁርሥ አዘጋጀሁና ጠበቅኳቸው ማርያና ከመኝታ ክፍል ሠሚር ከመሥጅድ ወዳዘጋጀሁት ቁርሥ ተሠበሠቡ :: ልቤ አልተረጋጋም ሁለት ሰው ይቀራል ልጄ እና የልጄ እናት:: ያለወትሮ ተኝታ ማርፈዷ ግር ቢለኝ ልጠራት ወደ ክፍሏ አመራሁ :: የማቃሠት ድምፅ ይሠማኛል በድንጋጤ በሩን ከፍቼ ገባሁ ፋኪሀ መሬት ላይ ተንበርክካ የአልጋውን ጠርዝ ይዛ ታጣጥራለች:: ደነገጥኩ ::የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ ያቺ የጨረቃ ሥባሪ የመሠለች ልጅ ሥቃይ ተጫውቶባት የህመም ጥቀርሻ ለብሳለች ላብ አሥጥሟታል ::"ሂዱዬ ልሞትልሽ ነው!" አለችኝ የሞት ሞቷን:: ማን እንደሞተ ትሞቻለሽ,?? በፍፁም!!! አንቺማ አትሞችብኝም !!!!
"ሠሚር!" ብዬ ጮህኩ ተሯሩጠን ወደ ሆሥፒታል ወሠድናት : ያ ሆስፒታል እኔም እንደሠዉ ወግ ደርሶኝ ለወራት ገብቼ በወለድኩበት ሥል የተመኘሁትን ሆሥፒታል የኔን ልጅ ለመውለድ ፋኪሃን ይዤ ገባሁበት::እድለኝነት ተሠማኝ።አዋላጅ ነርሶቹ በፍጥነት ተቀብለውን ወደ ማዋለጃ ክፍል አሥገቧት እኛ በሩ ላይ ቀረን:: ፋኪሃ ሥትጮህ ይሠማኛል የመረረ ጩኸት! አቤት የኛ መከራ !! የፈለግነውን ለማግኘትም ያለው ሥቃይ ! ጌታዬ እውነት ተናገረ በእርግጥም ከችግር ጋር ምቾት አለ!!! ከዛ በር ላይ ሣንንቀሣቀሥ ሠአታት ተቆጠሩ ምንም አይነት የናፈቀንን የልጅ ድምፅ መሥማት አልቻልንም። ፋኪሃም ድምጷ ቀሥ በቀሥ እየቀዘቀዘ መጣ :: 'የኔ ንግሥት ደከመችብኝ::'በድጋሚ አዋላጆቹ መሯሯጥ ጀመሩ :: የጊቢው ዶክተሮች በሙሉ ወደ ማዋለጃ ክፍሉ ተሠበሠቡ :: ወድያውም አንዲት ነርሥ የሆነ ወረቀት እና ብዕር ይዛ ወደኛ ቀረበች::ልቤ ቀጥ ስትል ይሠማኛል:: " አዝናለሁ ፋኪሃ ያለችበት ሁኔታ ከሷ አልፎ ልጁም እንዲታፈን እያደረገው ነው። ስለሆነም ከዚህ በላይ ችላ መግፋት ስለማትችል በኦፕራስዮን ልንገላግላት ነው :: የቅርብ ቤተሠብ ከሆናችሁ ከ ኦፕራስዮኑ ቡሃላ ለሚከሠተው ማንኛውም ነገር ሃላፊነቱን እንደምትወሥዱ ፈርሙ እና በፍጥነት ሥራችንን እንጀምር::" ይሄንን ማመን አልፋለግኩም:: ከኦፕራሲዮኑ ምንም ነገር ቢከሠት አሜን ከማለት ውጭ ምርጫ የላቹም የሚል ወረቀት ላይ ልፈርም???= በእንባ እና በጉጉት ሊፈርጡ በደረሡ አይኖቼ ካቀረረው እንባ ጋር እየታገልኩ ወደ ሠሚር ዞርኩ:: አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀልኝ :: ፈረምኩ:: ፋኪሃ ምንም ቢገጥማት እቀበላለሁ ብዬ ፈረምኩ:: ልጄ ምንም ቢገጥመው አሜን እላለሁ ብዬ ፈረምኩ:: በቃ ፈረምኩ!!! ነርሷ ወረቀቱን ተቀብላኝ በፍጥነት ወደ መጣችበት ክፍል ገባች :: መቆም አቃተኝ :: የመሬት ሥበት ከተለመደው የበዛ መሠለኝ :: እዛው ባለሁበት መላ ሠውነቴ ወደ እግሬ ሲጎተት ተሠማኝ ወደቅኩ:: 'ጌታዬ ሆይ !በርግጥ ምን አጥፍቼ ነው እንዲህ ምታሠቃየኝ አልልም ! በደሌ ቁጥር እንደማይለካው አውቃለሁ:: ነገር ግን የኔን ቅጣት በሌሎች ላይ አታድርግብኝ!::' ሥል ተማረርኩ :: ሠሚር ሊያባብለኝ ሞከረ:: አልተሣካለትም:: ከድፍን አንድ ሰአት ቀዶ ጥገና ቡሃላ የጤና ባለሙያዎቹ ከክፍሉ እየወጡ አልፈውን ሄዱ :: ፊታቸው ላይ ጥሩ ሥሜት አይነበብም:: "ተረጋጊ እኔ አጣርቼ ልምጣ " በማለት ሠሚር ወደ ክፍሉ ገብቶ የተወለደውን ልጅ ታቅፎ ወጣ::ያየሁትን ማመን አልቻልኩም ::

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
የፈቲ ባል …….ክፍል 7 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
<unknown>
◉ የፈቲ ባል ክፍል 7◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
መሀን አራስ
ክፍል አስራ ሰባት
(ሚስጥረ ጀማል)

ልጄን የመንጠቅ ያህል ተቀበልኩት ለደቂቃዎች ከቁጥጥሬ ውጪ የሆኑ ተግባራት ፈፀኩ ።ልጁን ወደ ደረቴ ለጥፌ አቀፍኩት:' አሸተትኩት ሣቅኩለት፣ አለቀሥኩለት፣ አዋራሁ፣ት ጌታዬን አመሠገንኩ!!!! አንድ ነገር ትዝ አለኝ ።ያለምንም ክፍያ ለልጄ ማህፀኗን የፈቀደች ያቺ ምሥኪን የማህፀን አከራይ ከምን ደረሠች??? ይህን ጥያቄ ያዘሉ አይኖቼን ወደሠሚር አይኖች አሻገርኳቸው::ሠሚሬ እያለቀሠ ነው':: አንገቱን በአሉታ እየነቀነቀ ምርርር ብሎ ያለቅሣል::
ምን ማለቱ ነው?? አልኩ ልጁን እንደታቀፍኩ ወደ ማወለጃ ክፍሉ የመንፏቀቅ ያህል አልነሣ ያለኝን እግሬን እየጎተትኩ ገባሁ ::' ምንም ቢፈጠር አሜን እላለሁ' አሥብላ ያሥፈረመችኝ ነርሥ ልጁን ከእጄ ላይ እየተቀበለችኝ "ሀሣባችን ሁለቱንም ማትረፍ ነበር ነገር ግን ፋኪሃ ለሊቱን ሙሉ ብቻዋን ሥታምጥ አድራ እዚህ አቅሟ ደከመብን በዛ ላይ ብዙ ደም ፈሷት ነበር የቻልነውን ሞክረናል :: እነሆ የፈጣሪ ፍላጎት ተፈፅሟል መፅናናቱን ይስጣችሁ" ይህንን ንግግር ከሠማሁ ቡሃላ የተፈጠረውን አላውቅም የልጄ እናት ሥትቀበር እንኳን ራሤን ከሣትኩበት አልነቃሁም ነበር። ከሁለት ቀን ቡሃላ ራሴን ሆሥፒታል አልጋ ላይ አገኘሁት :: ገና አይኔን ሥከፍት ሠሚር ልጄን አቅፎ ከጎኔ ተቀምጧል :: ወዲህ ደግሞ የማላውቃቸው ሸምገል ያሉ አባትነት የሚታይባቸው ትልቅ ሠው ቆመዋል:: ሰሚር መንቃቴን ሲያይ ተደሠተ ልጄን አምጥቶ አሳቀፈኝ :' እርሪታ የሌለበት ዝምምምም ያለ የእንባ ጎርፍ ማሥጋለብ ጀመርኩኝ የእንባ እርምጃዬ እየተሽቀዳደመ ይተናነቀኝ ይዟል። በመሃል አውራ ጣቱን አፉ ውሥጥ ከትቶ የተኛውን ልጄን አየሁና "አሜን" አልኩኝ :: የልጄን ሥም አሜን ብዬ ሠየምኩት በውስጠ ታዋቂነት የራሴን መሃንነት አሜን አልኩ :' የፋኪሃን በልጅነት መቀጠፍ አሚን አልኩ::ያላረገዝኩ ያላማጥኩለትን ወንድ ልጄን በክራይ ይኖርበት ከነበረው ማህፀን አሥፈልቅቄ ወደቤቴ ይዤ ገባሁ :: ፋኪሃ ለ ሶስት ወር እንድታጠባው ይረዳታል ተብሎ የተዘጋጀውን የአራሥ ቀለብ እየታረስኩ በተመረጠ የቆርቆሮ ወተት ልጄን እየመገብኩ አንድ ወር ያህል መሃን አራስ ሆኜ ተኛሁ:: ፋኪሀ ግን እንደወጣች ቀረች እነሆ ምንም ነገር ሳላደርግላት ልጅን ያህል ውለታ ውላልኝ አለፈች ይሄኔ ነበር...
ለሷ ለሷ ሳልል ለ'ኔ ለ'ኔ እያለች ከፀለየችልኝ ካለቀሰችማ፣
እባክህ ጌታ ሆይ የዚያችን ሴት ለቅሶ ቁም ፀሎቷን ስማ ::!!! ማለት
እነሆ ፀሎት ልፋቷ ተሳክቶ ልጇ ልጄ በመሆን አኸተመ!! 'ያረቢ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለሠራችው ሥህተት ሁሉ ማራት። በማለፍያዋ ሰአት በዚህ ልጅነቷ ያየችውን መከራ የሀጥያቷ ማበሻ አድርግላት አሚንንንንን !! የዘወትር ዱአዬ ነው:: ያ ..ሆሥፒታል ውሥጥ የነበረው ሸምገል ያለ ሠው ፋኪሃን "የጫንሽውን ሳታራግፊ አይንሽን እንዳላይሽ" ብሎ ያባረራት አጎቷ መሆኑን ከቀናት ቡሃላ ሠሚር ነገረኝ:: ይሄው ዛሬ የጫነችውንም አራግፋ አይኗን ማየት የማይችልበት የባሰ ግዜ ሢያጋጥመው ምን ብሎ ይሆን? አልኩ በልቤ:: አንዳንድ ግዜ ነገራቶችን ለማሥተካከል አሥበን የምንወሥነው ውሳኔ የከፋ ችግርን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል በማሠብ መጠንቀቅ ያባት ነው:: ይሄው ዛሬ ከነ አካቴው ልጅቷን አጥተዋል ምን ተሠምቷቸው ይሆን!!!
አንዳንድ ግዜ ልጄ አሚን ምርር ብሎ ሲያለቅሥ ይከፋኛል ። እናቱ አለመሆኔን ያወቀብኝ ይመሥለኝና እኔም አብሬው አለቅሣለሁ :: በዚያ ላይ አብዛኛውን ግዜ ያመኛል

::ሠሚርም በዚህ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜውን ከእኛ ጋር ያሣልፋል:: ከኔ እና ከልጄ::
በእሱና በማርያና መሃል ያለመግባባቶች እየሠፋ ነው :: ይሄ ጉዳይ እሥከሚፈጠርብኝ ቅርብ ግዜ ድረሥ ገበያ በወጣሁ ቁጥር ለማርያና የእርግዝና ማረጋገጫ (kit) ከፋርማሲ ሣልይዝላት አልገባም ነበር:: ምናልባት "አንድ ቀን እርጉዝ ነኝ!" ብላ ከማንም በላይ በኔ መሃንነት ልቡ የተሠበረውን ሰሚሬን አለሜን ታሥደሥትልኛለች ልቡን ትጠግንልኛለች ብዬ በማሠብ ቢሆንም ታምሜ እሥከተኛሁበት ግዜ ድረሥ እርግዝና አለመፈጠሩን ነው የምትነግረኝ ::ሥለዚህ እነሡ ሊነግሩኝ ከፈሩ በሚል ምክንያት ማርያናን ራሴ ጠርቼ ጠይቅኳት። ነገር ግን "በዚህ ሶስት ወር ውሥጥ ምንም እርግዝና የለም" ሥትል ሃዘን ባልተላበሠ የደሥታ ፊት ሆና ሥትነግረኝ ፈራሁ:: አዘንኩ;: የሆነ እኔ ሳላውቅ በጀርባ የሚካሄድ ነገር ቢኖር እንጂ ከመጋባታቸው በፊት ቴቴ የማህፀን ምርመራ እንዳሥደረገቻትና ምንም አይነት ግልፅ የሆነ ያለመውለድ ችግር እንደሌለባት ተናግራለች:: ሥለሁሉም አላህ ያውቃል::
አሁን አሁን ልጄ ጠረኔን እየለመደልኝ ነው እኔም ካጠገቡ ለደቂቃ መለየት አልፈልግም :: ልጄ ነፍሥያዬን በፍቅሩ ሞልቶልኛል :: የኔ አሜን!!! ፍቅሩ እንደ እብድም ያደርገኛል::
አንድ ቀን በባህሉ መሰረት መሃን ናት እያሉ ያነወሩብኝን የሠፈሩን ሴቶች 'አራሥ ነኝና ኑ መርቁ' በማለት ሠብሥቤ ገንፎ አብልቼ "የፈጣሪ ተዐምር!" ሲሉ ሠሚር ደርሶብኝ የሳቀብኝን ሣቅ አልረሣለትም :: በርግጥ ጉጉቴ አሣዝኖኝ እንጂ ሥራዬ እኔንም አሥፈግጎኛል :: ሣንነጋገር ተግባብተን ሥቀንበት አልፈናል::
ከእለታት አንድ የሆነ! ግን በጣም ብዙ የሚመሥል ገራሚ ቀን ላይ እንዲህ ተከሰተ...

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
የፈቲ ባል …….ክፍል 8 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
<unknown>
◉ የፈቲ ባል ክፍል 8◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
መሀን አራስ
ክፍል አስራ ስምንት
(ሚስጥረ ጀማል)

አንድ የሆነ! ግን በጣም ብዙ የሚመስል ቀን! ሚገርም አጋጣሚ ተከሰተ ...
ከምሽቱ አንድ ሰአት ሆኗል። ሰሚር ወደ ቤት አልገባም። ዛሬ ማርያና ጋር ሥለሚያድር በግዜ ሠግጄ ለመተኛት ውዱዕ ማድረግ ፈልጌ ወደ መታጠብያ ክፍሉ አመራሁ:: ያየሁትን ማመን አቃተኝ!!! መታጠብያ ቤቱ በሠፊው ተከፍቷል ማርያና በተቻኮለ ሥሜት ውሥጥ ሆና የሆነ መድሃኒት ሥትውጥ አገኘኋት:: 'ማርርያና!' አልኳት በእጇ የያዘችው ብርጭቆ ወድቆ እሥከሚሠበር ድረሥ ደነገጠች። የፊቷ ቀለም ተለዋወጠ:: 'አሞሽ ነው እሥቲ የምን መድሃኒት ነው ምትውጭው ?? ' ብዬ የያዘችውን የመድሃኒት ማሸግያ ተቀብያት አየሁት:: ማመን አልቻልኩም!!! በኔ መሃንነት ሲሰቃይ የኖረው ባሌ በዋናነት ልጅ ልትወልድለት አሥቦ ያገባት ማርያና በየ ምሽቱ አንድ አንድ ፍሬ የሚወሠድ የወሊድ መቆጣጠርያ እንክብል ተጠቅማ ዘሩንም ዘሯንን ሥታጠፋ ከርማለች :: ልታሥረዳኝ መንተባተብ ጀመረች ። ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም። በጥፊ ሥመታት ከመታጠብያው ሲንክ ስር ወድቃ ራሷን ሳተች። በዛው ቅፅበት የሠሚር መኪና ወደ ግቢው ሥትገባ አየኋት። ምንም አልደነገጥኩም:: እዛው በቆምኩበት ደረሠብኝ::"አንቺ እብድ ምን አደረግሻት?" ሲል ጮኸ! ወድያውም ሊያነቃት ያደረገው ሙከራ ሰርቶለት ማርያና ራሷን አወቀች:: ' የኔ አለም ለመጀመርያ ግዜ ሠደበኝ ።ለዛውም እብድ አለኝ' ያለ ጥፋቴ! ለሡ ባሠብኩ እሡን እሡን ባልኩ:: ተሠደብኩ::ምንም የመናገር አቅም አጣሁ። እንባዬ እየተናነቀኝ ወደ ልጄ ሄጄ መነፍረቅ ጀመርኩ።
በዚህ መሃል ሠሚርና ማርያ በከፍተኛ ጩኸት ሲጨቃጨቁ ሥለተሠማኝ ለማገላገል ሄድኩ :: "ቆይ ለምን አገባሽኝ,????" እያለ ይጮሃል :: ያለቅሳል ህመሙ አመመኝ ምናልባት እኔ መድሃኒቱን ሥትወሥድ ባላያት እሡ እንዲህ አይሆንም ነበር አልኩ። በራሤ ፈረድኩ!::ወይኔ ባሌ!!!!
"እሺ ሁሉን ነገር እናገራለሁ" ማርያና ከእንባዋ እየታገለች መናገር ጀመረች:: "እኔ በዚህ ሠአት የማግባትም ሆነ የመውለድ እቅድ የለኝም ነበር:: ነገር ግን ቴቴ በየግዜው ሥላንተ በምትነግረኝ ነገር ተታለልኩ። እኔን እንዳገባኸኝ ሂዳያን የምትፈታት መሥሎኝ ነበር:: አንተን በማግባት ብቻ ሃብትህ ዝናህ ሁሉ የኔ ሊሆን የሚችል መሠለኝ ።ጓደኞቼንም አማከርኳቸው ልጅ ከወለድኩልህ በዛው አንተው ቤት እንደምቀር አሥፈራሩኝ። እኔም ከምወደው ሠው ጋር ካልሆነ በቀር ዘላለሜን ካንተ ጋር ለመኖር አሥቤም አላውቅም። በዛ ላይ ሆሆታው ቴቴ ለኔ ያላት ክብር ምናምን አታለለኝ። አገባሁህ ነገር ግን ህይወቴን በሙሉ ልጅ ወልጄ ያንተ መሆንን አልፈለግኩም። በዛ ላይ አዲሷ ሚሥትህ እኔ ብሆንም ከሂዳያ ጋር ሁሌም እንደ አዲሥ ሙሽራ ነው ሥትወዳት የማየው። ሥለዚህ እሥከግዜው እራሤንም እሥከማሣምን ድረሥ ልጅ በሚሉት ገመድ ራሤን ላሥርልህ አይገባም ብዬ አሠብኩ::" ሰሚር ከተቀመጠበት ተነሥቶ እግሬ ስር ወደቀ "ሂዱዬ አንቺ ለአመታት ደሥታዬን ለመሙላት ፍላጎቴን ለማሣካት ጤንነትሽን ያጣሽ ሴት ሆይ፣ ሃላፊነቷን ወሥደሽ ልጇን ልጃችን ለማድረግ በማሠብ የሌላውን እርጉዝ ደፋ ቀና ብለሽ ያሥተናገድሽ ሴት ሆይ፣ ከግዜ ቡሃላ በመሠላቸት ያመጣሁብሽን አዲሥ አመል እንኳን ታግሠሽ በገዛ ቤትሽ ጣውንትሽ ትኖር ዘንድ የፈቀድሽ፣ ባልወለደ አንጀትሽ የሠው ጨቅላ ታቅፈሽ የታረስሽ የኔ መሃን-አራስ ሆይ በደልን ሁሉ በሚምረው ሃያሉ ጌታ ይዤሻለሁ ማሪኝ!" የሠሚር ማዘን ልቤን ሠበረው። ከወደቀበት አንስቼ ልጄን አሥታቀፍኩት እንዲህም አልኩ 'ዓለሜ በዚህ በኔና ባንተ ታሪክ ላይ ነገሮች ሁሉ የእርግማን ያህል ቢከብዱም ልክ እንደዚህ ልጅ ምላሻ ችን ሁሉ አሜን እንጂ ሌላ መሆን የለበትም ::'
ሰሚር ወድያውኑ ቴቴ ጋር ደውሎ ያጠፋችውን ሥህተት እሥከመጨረሻው ዐውፍ እንደማይላት ነገራት::
ይሄኔ ማርያና በዝግታ ተራምዳ ክፍሉን ለቃ ወጣች:: ከደቂቃዎች ቡሃላ በሰሚር እቅፍ ውሥጥ እንዳለሁ ለቅሦውን ለማሥቆም ሥሞክር እቃዋን ሁሉ ይዛ ከደረጃው ሥትወርድ አየኋትና 'ማርያና በዚህ ሰአት..?' ብዬ ለመመለሥ ብድግ አልኩ " አይ ሂዱ ለበደለኛ ሰው ቀኑም ጨለማ ነው:: ሥለዚህ አሁንም ሄድኩ ጠዋት በብርሃንም ሄድኩ በጨለማ እኩል ነው እንቅፋት ሚመታኝ::" የሠሚር ሚሥት ቤቱት ጥላ ሄደች ::
አንዳንድ ቀኖች በእርግጥም የአንዳንድ ቀኖች ተቃራኒ ናቸው :: ምናልባትም ይሄ ቀን ባሌ ሌላ ሚስት ሊያመጣ ሞሽሬ የላኩት ቀን ራሴት ማጥፋት ሣይቀር የተመኘሁበት ቀን ተቃራኒ ነው:: ግራ ገባኝ !! ባሌ እንደ ድሮው የግሌ ሆነ ብዬ ልደሠት?? ወይሥ ሠሚሬ የአብራኩን ክፋይ ለማግኘት እንደጓጓ በመቅረቱ ልዘን???
ለሊቱን እዛው ብርድ ላይ ሥለቆየን ልጄ አሚን ሲያስለው አደረ እኔም ቢሆን ጤንነት አልተሠማኝም ሠሚርም ከባብዶታል :: ሥለዚህ ሱብሂ ሠላት እንደሠገድን ሶስታችንም ተያይዘን ወደ ሆሥፒታል አመራን '' ለልጄ ሽሮፕ ታዘዘልኝ ::ለባሌ ደግሞ ራሱን ፈታ የሚያደርግበት ረዘም ያለ የእረፍት ግዜ እንደሚያሥፈልገው ተነግሮን ወጣን እነሆ የኔ ውጤት ቀረ:: ልጄን እንደታቀፍኩ ከሠሚር አጠገብ ቁጭ ብያለሁ :: ዶክተሩ አይን ላይ ከባድ የሃዘን ድባብ ይነበባል ::ፈራሁ ሠሚር ከዶክተሩ ያሥጥለኝ ይመሥል በትከሻው ምሽግ የዶክተሩን ጮር ሸሸሁ" ምነው ዶክተር ችግር አለ?" ሠሚር የሞት ሞቱን ጠየቀው። ሁለታችንም ፈርተናል :: ዶክተሩ መናገር ጀመረ" am sorry to say this but..." ወይ መከራዬ? ምን ይሆን ቀጣዩ የሃዘኔ ምዕራፍ አልኩ በልቤ ዶክተሩ ቀጠለ.." እንዴት እንደተከሠተ አላውቅም::ግን.....

የመጨረሻ ክፍል 400👍ቡሀላ ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
የፈቲ ባል …….ክፍል 9 ተራኪ ጃዕፈር ጀማል
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 9◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒

➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
👍1
መሀን አራስ
ክፍል አስራ ዘጠኝ(የመጨረሻ)
(ሚስጥረ ጀማል)

ወይ መከራዬ? ምን ይሆን ቀጣዩ የሃዘኔ ምዕራፍ አልኩ በልቤ ዶክተሩ ቀጠለ.." እንዴት እንደተከሠተ አላውቅም::ግን ቢያንሥ መጠንቀቅ መቻል ነበረብሽ!" "ዶክተር በቃ አታጨናንቀን በጣም እየረበሽከን ነውኮ "ሠሚር መቆጣት ጀመረ" እሺ እንግዲህ በዚህ ፍጥነት አርግዘሽ እንዴት survive ልታደርጊ እንደምትችይ አላውቅም ::" ከሃውልት በላይ ደርቄ ቀረሁ!!!
ዶክተሩ ቀጥሏል" እንዴት እንደምትቋቋሙት አላውቅም ቢያንሥ ይሄ ጨቅላ እንኳ ትንሽ እሥኪጠነክር መጠበቅ ነበረባችሁ ካልሆነው መከላከያ መጠቀም ያባት ነበር anyhow ምንም ማድረግ አይቻልም ::
ደግሞኮ በሚገርም ሁኔታ ከ100 እናቶች ቢበዛ 1 እናት ላይ ብቻ የሚከሠት triple pregnancy ወይም 3 ልጆችን ነው በአንዴ ያረገዝሽው::"
ግራ ገባኝ ነፍሴ ለብቻው ሥጋዬ ለብቻው የተናጠለ መሠለኝ:; ውስጤ ለውሥጤ ያወራል::' ማለት??? ጌታዬ የአመታት ፀሎቴን ሰማኝ???? ማህፀኔ ከሞተበት ተቀሰቀሰ??? እኔም ወጉ ደረሰኝ??? አረገዝኩ ?? ሶስት ልጅ??? 'ይሄን ጉድ እንዲያሥረዳኝ ወደ ሠሚር ዞርኩ ሠሚር ካጠገቤ የለም ።እዛው መሬቱ ላይ ሱጁደ ሹክር እያደረገ ነው :: አይ በቃ ቅዠት አይደለም ማለት ነው አሜንን ወንበሩላይ አስቀወጥኩና እኔም ከ ዐለሜ ጎን ሱጁድ ወረድኩ'ሰጀደ ወጅሂየ ሊለዚ ኸለቀሁ ወሸቀ ሰምዐሁ ወበሰረሁ ፈተባረከላሁ አህሰኑል ኻሊቂን'
እኔም ሆነ ሠሚር ቃላትን አዋቅሮ ተነጋግሮ መግባባት አቃተን ። ብቻ አንድ ነገር እናውቃለን እኔ ና እሡ ለመጀመርያ ግዜ ከአመታት ሙከራ እና መከራ ቡሃላ ልጅ ሊኖረን ነው:: ለሠአታት ተቃቅፈን አነባን!! ዶክተሩ ግራ ተጋብቷል። እሡ ያሠበው አሜንን የኔ ልጅ ነው ሥላልኩት በዛ ፍጥነት ማርገዜ ይጎዳኛል ብሎ ነበር :: ይሄንን ሁሉ ውሥብሥብ ታሪክ ለሡ የምናሥረዳበት ግዜ ሥላላገኘን አሜንን ይዘን ወደቤት ሄድን መነጋገር አቃተን እየተያየን መሣቅ ሆነ ውሏችን :: ጉዳዩን እንዳረጋገጥን የእርግዝና ክትትል ለመጀመር ወድያውኑ ከኔ ሱቅ ፊት

ለፊት ወዳለው የእናቶች እና የህፃናት ሆስፒታል አመራን::መኪናዋን በሩ ላይ አቆምንና ወረድን በሩ አካባቢ ያለውን ክፍት ቦታ አየሁት::
ፋኪሀን ለመጀመርያ ግዜ ያገኘኋትእዛ ነበር ቦታ ጭር ብሏል።ሁሉ ነገር በነበር ቀረ::
' አላህ ሆይ ቀብሯን አስፋላት ከመላኢኮች የሆኑ አጫዋቾች መድብላት አሚንንንን' አልኩ:: ከመግባታችን በፊት ሻርፔን በተን አድርጌ ሆዴን ሸፈንኩት:: አሜንን ዐለሜ ያዘልኝ:: በአንድ እጄ ወገቤን ይዤ በትንሹ 15 ዲግሪ ከወገቤ ወደ ኋላ ዘንበል አልኩኝ:: በአንድ እጄ ሠሚርን ያዝኩት::
ሠሚር በድርጊቴ ተገርሞ ፈገግ እያለ ያየኛል ::ከመግባታችን በፊት ወደ ሡቄ መሥኮት ዞር ብዬ አየሁ:: ሱብሀለናህ! ያቺ የዚህን ሆሥፒታል ደንበኛ የሆኑ እርጉዞችን በቅናቻ የምታየው መሃኗ ሂዳያ ዛሬ መስኮቱ ጋር የለችም። ምክንያቱም እሷ ዛሬ አንድ ልጅ አሣቅፋ፣ ከመቶ ሴቶች መሃል ተመርጣ ሦስት ልጅ በሆዷ ያረገዘች እድለኛ ሆናለች:: በዚያው ቀን የእርግዝና ክትትሌን ጀመርኩ::
ቴቴ ድል ያለ ድግሥ ደግሳ በሙሉ ቤተሰባቸው ፊት ቆማ ሰሚርን ዐውፍ በለኝ ብላ ተማፀነችው:: ሰሚርም"ለሁሉም ነገር ሃቅ ሃቁን መሥጠት ግዴታችን ነው ይሄ ያንቺ ይቅርታ ሃቅነቱ ለኔ ሳይሆን ለውዷ ባለቤቴ ለሂዱ ነው :: ያለ ጥፋቷ ለአመታት አሠቃይተሻታልና እንዲሁ እንደቀልድ በደልሽን ልትረሳልሽ ባይቻላትም ቢያንስ ለወጉ ያህል ይቅርታን መጠየቅ አለብሽ" አላት በዛ በተከበረ ቤተሠብ ፊት የኔ አለም እኔን አከበረኝ :: እኔም ይቅርታዋን ተቀብዬ አባሸርኳት ነገር ግን ከዚያን ግዜቡሃላ በእኛም ሆነ በማንኛውም ሠው የትዳር ህይወት ሙሉ ሃላፊነቱን መውሠድ ያለባቸው የጉዳዩ ባለቤቶች ባልና ሚስቱ እንጂ አማች አይደለም :: እንደሷ ባሉ አማቾች ስንት ትዳር እንደፈረሠ አሥጠንቅቄያት ተለያየን::
ሳምንቱን ሙሉ ለመዝናት በማሠብ ከሠሚር ጋር አሜንን ይዘን ከከተማ ራቅ ብለን ለመሄድ መንገድ ጀምረናል:: በዚህ ጉዞ የኔም የእርግዝና የተለያዩ አምሮቶች ይወጡልኝ ዘንድ፣ ለሠሚርም ዶክተሩ እንዳለው ረዥም እረፍትን ያገኝ ዘንድ መድሃኒት እንደሚሆነን እያወራን ነው :: ከመኪናው ኋላ ወንበር የሚያስል ህፃን ልጅ ድምፅ ተሠማን :: ሁለታችንም ደንግጠን ተያየን። የየራሣችንን መድሃኒት ሥናመቻች ለካስ ለአሚን የታዘዘለትን መድሃኒት ረስተናል :: መዘንጋታችን እያሥገረመን ከከተማ ከመውጣታችን ብፊት ከአንድ ፋርማሲ ገዛንለት ::አሚንዬ የኔ ገዳም:: እነሆ ዘንድሮ ሙሉ ቤተሰቤ ከህመሙ ይሽር ዘንድ የለማኝን ዱዐ የማይዘነጋው ፍትሃዊው ጌታ በመሃከላችን መዳንን፣ ደስታን፣ ፀጋን ሁሉ በኛ ላይ "ሁን"ሲል አሠፈነ:: እሥከ ጀነት ያዘልቀን ዘንድ የዘወትር ዱዐዬ ነው ::ለሁሉም ግዜ አለው!!!
ተፈጠመ!!!
ከ 500 👍 ቡሀላ አዲስ ምርጥ ታሪክ እንጀምራለን
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍3
#የደሴቷ_ብቸኛ_ነዋሪ....ደስ የሚል ታሪክ

በርካታ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አንዲት መርከብ በድንገት በተከሰተ ከባድ ማዕበል ምክንያት ባህሩ ውስጥ ትሰጥማለች። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታድያ በአላህ ተአምር አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል። ይህም ሰው በውሃው እየተገፋ አንዲት ደሴት ላይ ራሱን ያገኘዋል።

እርዳታ ለመጠየቅ በደሴቷ እየተዘዋወረ ሰው ለማፈላለግ ቢሞክርም ምንም ዓይነት የሰው ዘር ማግኘት አልቻለም። በአካባቢው ማዕብሉ ከሚያናውጠው ባህርና ከወፎች ድምፅ በስተቀር የሚሰማ ነገርም የለም። በዚህን ግዜ በትንሽየዋ #ደሴት ውስጥ የሚኖረው ብቸኛው ሰው እርሱ ብቻ መሆኑን ሲያረጋግጥ በጣም ተጨነቀ። ፍርሃትም አደረበት። ከዚህ አስፈሪ ችግር ያወጣውም ዘንድ አላህን ለመነ።

አንዳች የአላህ ተዓምር መጥቶ ወደ ቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ እስኪፈጠር ግን በደሴቷ ውስጥ መቆየቱ እንደማይቀር በማሰብም የሚጠለልበት ትንሽ ግዜያዊ ጎጆ ቤት ሰራ። አንገቱ ላይ ባንጠለጠለው ቦርሳ መሰል ይዞት የነበረውንም እቃ ጎጆዋ ቤት ውስጥ አስቀመጠ።

ወደ ጫካው በመግባትም የተለያዩ የሚበሉ ፍራፍሬዎችንና ቅጠላ ቅጠሎችን ማግኘት ቻለ። በዚሁ ሁኔታ በደሴቷ መኖር ጀመረ.....

ከዕለታት አንድ ቀን ምግብ ፍለጋ ወደ #ጫካው ሄዶ ሲመለስ ትንሿ ጎጆ ቤቱ በእሳት እየተቀጣጠለች ደረሰ። በተመለከተው አጋጣሚ በጣም አዘነ። የበለጠ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም አደረበት።

"አላህ ሆይ! ለምንድን ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የምትፈፅምብኝ!?" በማለትም በጣም አለቀሰ።

በተከታዬ ቀን የሆነ ድምፅ ከእንቅልፋ ቀሰቀሰው። ወደ ደሴቷ እየቀረበች የነበረች አንዲት መርከብ ናት ከእንቅልፋ የቀሰቀሰችው። መርከቧ እሱን ለመውሰድ ነበር ወደ ደሴቱ የመጣችው።

ሁኔታውን ማመን ያቃተው ሰውዬው "በዚህ አካባቢ እኔ መኖሬን ማን ነገራችሁ?" በማለት መርከቧ ላይ የነበሩትን ሰዎች ጠየቀ። እነርሱም "ትናንት ከዚህ አካባቢ የሚወጣ #ጭስ አይተን ነው የመጣነው" ሲሉ መለሱለት።


#አስተምህሮት.....
እኛ ሰዎች አጋጣሚዎች ሁሉ መጥፎ ሲሆኑብን በቀላሉ ተስፋ እንቆርጣለን። እንዲህ በቀላሉ መሸነፍ የለብንም። ምክንያቱም አልህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኛን በተመለከተ ሁል ጊዜ ስራ ላይ መሆኑን መዝምንጋት የለብንም። በመከራችንና በህመማችን ወቅትም እንኳ ቢሆን እርሱ አይረሳንም።

JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1
#ሀሊማ የተሰኘ ምርጥ ተከታታይ ታሪክ ከነገ ማታ ጀምሮ ልናቀርብ ወደናል ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ👍
ሁለቱ ባል እና ሚስቶች የተጋቡት ዛሬ ነው። በጣም ይዋደዳሉ። የተጋቡት እርስ በእርስ በሸሪዓ ህግ መሰረት ሽማግሌ ልከው ሳይሆን በሶሻል ሚዲያ ትውውቅ ነው። ሆኖም ግን ፍቅራቸው ከዚያ የላቀና የሚያስቀና ነበር። በፍቅር እና በደስታ ሁለት አመታትን በጋራ አሳለፋ። ከሁለት ዓመት በኋላ...

አሁን አሁን ባል በንዴት መበሳጨት ጀምሯል። እሷም ብትሆን ይህ ባህሪው ስላላማራት ነገር ብቻ መፈልፈል ሆኗል ስራዋ። ከእለታት አንድ ቀን ከስራ ተመልሶ መጣ። ያኔ የተጋቡ ሰሞን በፈገግታ እና በደስታ ተቀብላ የምታበላው ሚስቱ፣ ምሳ ሳትሰራ ሞባይሏ ላይ ተጥዳ ይመለከታታል። በንዴት "ለምንድነው ምሳዬን ያልሰራሽው!?" ሲል አንባረቀባት። እሷም በንቀት አይን ሰራተኛህ እየሰራችልህ ነው ስትል መለሰች...

ይሄኔ የንዴት ጣርያ ላይ ደርሶ የነበረው ባል ሞባይሏን ከእጇ መንጭቆ በመወርወር ከቤቱ ግርግዳ ላይ ከሰከሰው። በዚህም አልተብቃቃም የሚስቱን ፊት ባለ በሌለ ሀይሉ በጥፊ አጮላት። እሷም ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች። በዚህ ህመሟ ላይ ሌላ ህመም እንዲህ ሲል ጨመረላት "አንቺን ከማገባ የኛን ቤት ሰራተኛ ባገባ ኖሮ እንዲህ አይልሆንም ነበር። እሷ ካንቺ 100እጅ ትበልጣለች" ሲል የቅናት ቃጠሎ ውስጥ እንድትገባ አደረጋት።

ሰራተኛዋ ለንግግሩ ማፅደቅያ ላይ ይሁን ባይታወቅም ምሳውን ቆንጆ አድርጋ ይዛ መጣች።... ለነገሩ ሰራተኛዋ በፍቅራቸው እጅግ በጣም ትቀና ነበር። ተንኮለኛ መሆኗንም ፊቷን የተመለከተ ማንኛውም ሰው መገመት አያቅተውም። የሆነው ሆኖ አባ ወራው ሚስቱን የበለጠ ጠልቶ ለሰራተኛዋ እንዲያደላ የሚያደርግ ስራ ሰራች።

ይህንን የተመለከትችው ሚስት ስራዋ ሌተ ቀን ባልን ለማስደሰት መጣር ሆነ (ለነገሩ የሚስት ስራ ባልን አስደስቶ ጥሩ ማህበረሰብን መፍጠር አይደል!!)። ነገር ግን ከባሏ የምታገኘው ምላሽ እሷን የሚያስከፋ ብቻ ነው። ጨው በዛ፣ በርበሬው ያቃጥላል፣ ሽንኩርቱ አልበሰለም፣.......ውሃው ቀጠነ የእለት ተዕለት ጭቅጭቁ ሆነ። ሚስት ይህን ሁሉ በሰብር ታሳልፋለች። ጥፋቷ ምንም የማታውቀውን ሰው ከሶሻል ሚዲያ ብቻ ተዋውቃ ማግባቷ እንደሆነ ይሰማታል።

ሆኖም ግን ተስፋ አልቆረጠችም። የሰራተኛዋ ተግባር ደግሞ ልክ እንደሚስቱ ባልን ወደ ራሷ ለመሳብ እና ሚስት ላይ ውሽማ ሆና አረፈችው። ባል ከሰራተኛዋ ጋር ዝሙት ባይፈፅምም ሁል ጊዜ ለርሷ ያደላ ነበር። አንድ ቀን ይህች ሰራተኛ የሚስት ምግብ ውስጥ መርዝ በመክተት ልትገድላት ታስባለች። ባልየውን ማንም እንደማይቀማት በማመን ይህንን ስራ ለመከውን ዝግጅቷን አጠናቃ እነሆ ለሚስት የመጨረሻ እራት የሚመስለው ቀን ደረሰ። ተሳክቶላት መርዙን የሚስት ምግብ ውስጥ ጨመረችው። ሚስት የጎረሰችው 5 ጉርሻ ብቻ ሲሆን ወዲያውኑ ሆዷን ራሷን ሁሉ ነገሯን ያማት ጀመረ። እዚያው የእራት ገበታ ላይ በፊቷ ተደፋች። ይሄኔ ይጠላት የመሰለው ባል ተንደርድሮ አቀፋት። ሚስት አረፋ ከአፏ ውስጥ ይፈሳል። በፍቅር አይን ትመለክተዋለች። ባል በጣም አለቀሰ። ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብሎ በፍጥነት ወደ አቅራቢያው ጤና ተቋም ይዟት በረረ። ከብዙ ርብርብ እና የቀዶ ጥገና ህክምና በኃላ ሚስት.....





በአላህ ፍቃድ ዳነች። ባልየውም በደስታ እቅፍ አድርጎ ሳማት። እጅጉንም እንደሚወዳት ከድሮው በበለጠ ይገልፅላት፣ ያሸታት፣ ይስማት፣ ገባ። በጣም ደስ አላት። እንደ አዲስ የተጋቡ ይመስል አላህን አመሰገነች።

ያቺን መርዝ ሰራተኛ ባል እየጠፈጠፈ ለህግ አሳልፎ ሰጣት። በሰው መክደል ወንጀል ሙከራም 15ዓመት ዘብጥያ ወረደች። ባልና ሚስትም ከዚያ ግዜ በኃላ በሰላምና በፍቅር ይኖሩ ጀመር።

#አስተምህሮት.......
አላህ መጥፎ ነው ብለህ ምታስበውን ነገር ላንተ ኸይር ሊያደርግልህ ይችላል። ስለዚህ ሁሌም #አልሃምዱሊላህ በል!!

JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
2
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀሊማ
ክፍል ①
በሂክማ ጀማል


"ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠችው ነው የምንኖረው"
.
ዛሬም እንደ ወትሮዋ ከእኩዮቿ ጋር ለመጫወት ከ ቤት ወጥታ ወደ ጓደኞቿ ጋር ሄደች፡፡ ሀሊማ በጣም ተጫዋች ደስተኛ እና ሁሉም ሰው የሚወዳት አይነት ልጅ ናት የተወሰነ ሰአት ከተጫወተች ወዲህ እረሀብ ቢጤ ተሰማት ያው የልጅ ነገር እረሀቡን ለማስታገስ ያህል ብቻ ነው እነደነገሩ ምግቡን ቀመስ ቀመስ የሚያደርጉት፡፡ ከዛ ወደ ጨዋታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ሰአቱ ከ ጠዋቱ 5፡30 ይላል ሀሊማ ጓደኞቿን ተሰናብታ ወደ ቤቷ ሄደች ፡፡ ነገር ግን እቤቷ ስትደርስ ያልጠበቀችውን ነገር ያጋጥማታል ያ ክስተት ህይወቷ አንዲከብድ ያ ያሰለፈችው ጨዋታ እንዳይደገም የደረገውን ደስታዋ ሁሉ ጠፍቶ ቀሪ ጊዜዋን በ ሀዘን እንድታሳልፍ ያደረገ ክስተት ነው ሀሊማ በራፍ ላይ ስተደርስ ያልጠበቀችው ነገር ያጋጥማታል ያለ ወትሮ የግቢቸው በር ተከፍቶ ታገኘዋለች ትንሽ ግራ ገባት ምን አልባት ኡሚ እደከፈተችው ረስታው ይሆናል ብላ አሰበች በሩን ድምፅ ሳታሰማ ቀስ አድርጋ ዘጋችው ፡፡

ሌላ ግዜ እንደምታደርገው እናቷን ጋር ሰትደርስ በቀስታ ኮቴ ሳተሰማ ትሄድና ታስደነግጣት ነበር ዛሬም እንደ ወትሮዋ እናቷን ለማስደንገጥ እናቷን ሁሌ ወደ ምታገኝበት ቦታ ኩሽና ሄደች ግን እንደጠበቀችው አልሆነም እናቷን ኩሽናው ውስጥ ልታገኛት አልቻለችም ምን አልባት ሳሎን ትሆናለች ብላ ወደ ሳሎን ቤት በተመሳሳይ መልኩ እየተራመደች ሄደች ግን እዛም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ነው ያጋጠማት ሀሊማ እናቷ ያለወትሮዋ ሁሌ ከምታገኛት ቦታ በማጣቷ ትንሽ ግራ ተጋብታ ቁጭ ብላ መጠበቅ ጀመረች ኡሚ ...ኡሚ... ብላ ልትጠራት አስባ ግን ድንገት አንድ ሀሳብ መጣላተ መኝታ ቤት ለምን አላያትም የሚል አሁንም እዛም ቢሆን ካገኘቻት ከሃላዋ ሆና ለማስደንገጥ እንዲያመቻት ቀስ አያለች ወደ መኝታ ቤቱ አመራች ነገር ግን የሆን ድምጽ ሰማች የ እናቷ ድምጽ አይደለም ማን ይሆናል ያለው እያለች እየፈራች ወደ ክፍሉ ተጠጋች በሩ አልጠበቀም ነበርና ቀስ ብላ ጠጋ አደረገችው የ አባቷ ድመጽ ሰማች በዚህ ሰአት እቤት ምን ይሰራል ብላ አሰበች ጠዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ ስራ እንደሄደ አስታወሰች ታዲያ እንዴት መጣ ብላ እያሰበች በሩን ከመጀመሪያው ትንሽ ጠጋ አድርጋ አንገቷን ወደ ውስጥ አስገባች ግን ምንም ያልጠበቀችው ነገር ነበረ የተመለከተችው ሁለት አንድ አመት ያልሆናቸው ታናናሽ መንታ እህትና ወንድሟ አልጋው ላይ እንደተኙ ናቸው
:
አልጋው ግርጌ ጋር በጀርባዋ ተንጋላ ወድቃለች ከ አንገቷ አካባቢ ደም እየፈሰሰ ነው፡፡ አባቷ ደንግጦ ባለበት ደርቆ ቆሞዋል ከአልጋው ጎን ሰሚራ የሆነ ብረት የሚመስል ነገር ይዛ ቆማለች ሰሚራ ማለት ጓረቤታችን እና የ እናቴ የቅርብ ጓደኛ ነች እኔ ሳልወለድ ጀምረው ጓደኛ ናቸው አሁን እኔ ሰባት አመቴ ነው እነሱ ከዛም በፊት ጀምሮ ጓደኛ ናቸው ነገር ግን ዛሬ ያየሁትን ነገር ማመን አልቻልኩም ብረቱን ለምንድነው የያዘችው ምን ልታደርግበት ነው ብዬ አሰብኩ......
አባቴ ራሱን ከመሳት በማይተናነስ መልኩ ነበር ደንግጦ የቆመው፡፡ አባቴ ትንሽ ወደ እራሱ እንደመመለስ ሲል ወደ እናቴ ተጠግቶ ለማንሳት ሲሞክር በድንገት ሰሚራ ፊቷን አጨማዳ
.
"ምን ለማድረግ እየሞከርክ ነው" ብላ ጮኧችበት
.......ወደ ሀኪም ቤት ልወስዳት ነው አላት እየተርበተበተ በምላሹም ሰሚራ ......."ከዛስ ባክህ ምን ሆና ነው ሲሉህ ምን ልትላቸው ነወ እኔ እና የባለቤቴ ጓደኛ በጣም ስለተዋደድን እሷን ደግሞ መፍታት ስለማልችል እኔ እና ሰሚራ ተመካክረን ልንገድላት አስበን ሰሚራ በብረት ጭንቅላቷን መታት ነው ብለህ ልትነግራቸው ነው " ብላ አፈጠጠችበት ይሄን ስሰማ በዛ በጨቅላ አቅሜ መሸከም ከምችለው በላይ ነበር ሰሚራ ብረቱን ለምን እንደያዘችው ያኔ ነበር የገባኝ መቋቋም አቃተኝ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም አንድ ሰው ከሞተ ድጋሚ ከሰዎች ጋር መገናኘት እንደማይችል ነበር እናቴ የነገረችኝ ታድያ እናቴንም ድጋሚ ላገኛት አልችልም ማለት ነው .......ስለ ሞት እንኳ በቅጡ አላውቅም ነበር አይሆንም አባቴ እንዲህ አያደርግም አባቴ እናቴን በጣም ነወ የሚወዳት እያለኩ ከ እራሴ ጋር አወራለሁ፡፡ አባቴም መናገር ጀመረ ይበልጥ ተጠግቼ ማዳመጥ ጀመርኩ እሱ ይሄን እንደማያደርግ እንዲያረጋግጥልኝ በማሰብ ግን



ክፍል 2
ይቀጥላል

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
Audio
MAREN tube
◉ የፈቲ ባል ክፍል 10◉
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒
ስለዘገየን በጣም በጣም ይቅርታ🙏🙏🙏
➫ ደራሲ - ኑዕማን ኢድሪስ
➫ ተራኪ - ጃዕፈር ጀማል
➫ ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ ተከታታይ መሳጭ ታሪክ
━━━━━━✦✗✦━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @ketibeb
@ketibeb
─── ── ✦ ── ───
❤️❤️❤️❤️❤️❤️ጀሊሉ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አንተ ነህ ጀሊሉ የልቤ መድመቂያ፤
ቦታ የሰጠኸኝ እስከ እድሜዬ ማብቂያ፤

ከሁሉም አልቀህ እኔን የፈጠርከኝ፤
በኢስላም መንገድ ላይ እንድኖር ያረግከኝ፤

ይህ ብቻ በቂ ነው ማስተዋል ቢኖረኝ፤
ሌላ ምንም ባይኖር ዲኔን ከሰጠኸኝ፤

ስጦታህን ሁሉ ዘወትር አስታውሰኝ፤
በሰጠኸኝ ፀጋ ማመሰግን አርገኝ!!!
🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲
🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲 🤲

#Siham S
LuK 01

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
አልቅሳ አታቅም

አልቅሳ አታቅም ነፍሴ እሳት ፈርታ
ቺኳ ከተቆጣች ያቀልጣል ኡኡታ
ዱንያ ወዶ ልቤ ቀን ማታ ይሰራል
ፊርዶስ ከተባለ ፍራሽ ይፈልጋል
ልቤ ምን ወደደ ለየትኛው ስራ
መልስልኝ ልቤን የአላሁ አደራ
ኸይሩን ምረጥላት ወዳንተ ትመራ
ጠብቀኝ ያረቢ ከመጪው ኪሳራ

#መሀመድ አሚን ይማም
Luk 17

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
👍1
አይረሳኝም ብለሽ!

"ከሠጠሁት ፍቅር፣ካሳየሁት አሳር፣
ከቶ አይረሳኝም፣ካሳለፍነው አንፃር!
"ልርሳት" ቢል እንኳ በሒደት ያረጃል
የመርሳት መንገዱ ዕድሜውን ይፈጃል!"
እያልሽ ታስቢያለሽ...
እያልሽ ታደቢያለሽ...
ከንቱ ነው ሐሳብሽ፣ከንቱ ነው ድካምሽ
እንደውም ...እንደውም. .
ማን ነበረ ሥምሽ?

#ፈይሠል_አሚን
Luk 27

ውድድሩን ለመቀላቀል @ketibeb
ስፖንሰር ነጃህ ሚድያ የዩትዩብ ቻናል
👍1