ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️
11K subscribers
166 photos
9 videos
7 files
575 links
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!!
❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።

LEAVE ከማለት ይልቅ 👉 @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን።
Promotion– @kedir2

For Le ወንድም channeል
ለፈገግታ @ethio_keld
Download Telegram
መሀን አራስ
(ክፍል አምስት)
ሚስጥረ ጀማል

ለሰአታት ከመሬት ሳልነሳ ቆየሁ ::
ምን እንደማስብ እንኳን ግልፅ አልሆነልኝም:: ሰውነቴ ከዳኝ ከጉልበቴ ታግዬ ተነስቼ በሬን ቆልፌ ወደአልጋዬ አመራሁ:: እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገኝ ስልኬ ተንጨለጨለች በዳበሳ አነሳሁት አዲስ ቁጥር ነው ድምፁ ግን ፍፁም የተለመደ። ለአመታት ሲያዝናና ሲያስደስት የኖረ የሚመስል ተወዳጅ አስደማሚ ድምፅ :: የተጫጫነኝ ሁሉ ለቀቀኝ ከተንበለበልኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ለደቂቃዎች ከቁጥጥሬ ውጭ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን አደረግኩ ተቀመጥኩ ተነሳሁ ጋደም አልኩ ይህንን ነገር መግታት ግን አልቻልኩም :: በስልኩ ሽቦ የሚንቆረቆረው ድምፅ ያለምንም ቁም ነገር የማያጨናንቅ ወሬዎችን ያፈልቃል እጅግ አደምጠዋለሁ ብዙም አላወራም :: ነገ ከስራ ስወጣ እንድንገናኝ ቀጥሮኝ ስልኩ ተዘጋ:: ዳግመኛ ሰመመን ውስጥ ተዘፈቅኩ :: ስልኬን ወርውሬ በከፊል በመሰበሯ ምክንያት ተንጋዳ የቆመችው መስታወቴ ፊት ተገተርኩ::
አንድም ምን ሁኔታ ላይ እንዳለሁ ለማየት ሌላ ደግሞ ሰሚር ምን ፈልጎ ቀረበኝ ለሚለው ጥያቄዬ መልስ ፍለጋ:: መሥታወት አይቶ እንደማያውቅ ህፃን ቦረቅኩ ከውስጥ ያለች ሌላ ቆንጆ ሴት የቆመች እስከሚመስለኝ ድራስ ራሴን አስተዋልኩት:: ለካ እንደዚህ ቆንጆ ነኝ::ግማሽ ለሊቱ በመገላበጥ ነጋ ካጠገቤ አሉ የምላቸው ሁለት ወንድሞቼ እና እናቴ በመኪና አደጋ በአንድ ጀንበር እኩል ካለቁብኝ ቡሀላ የትውልድ ከተማዬን ጥዬ ከተማ ወዳለች አክስቴ ጠቅልዬ ከመጣሁ ቡሀላ ተወልጄ ያደግኩባት የሰላሌ ከተማ፣ እኔነቴም ፣መልኬም ሁሉ ነገር አስጠልቶኛል :: ስለሆነም ራሴን መልኬን ረስቻለሁ::
ራሴን ሳሽሞነሙን ስራ ረፈደብኝ ያለኝን ልብስ ሁሉ ዘርግፌ አንድ ባንድ ለካሁ ልብሶቼን ከሰውነቴ አንፃር ሳይሆን ከሰሚር ልብሶች አነፃፀርኳቸው ጭራሽ ረከሱብኝ :: ይሻላል የምለውን ለብሼ ወደ ካፌ አቀናሁ:: ገና ከመግባቴ እነሄዋን በጥያቄ ያዋክቡኝ ጀመር ከልብ ከመነጨ የደስታ ባህር ስር ተዘፍቄ እዚም እዛም እያወጣሁ አንቦራጭቅ ይዣለሁ::እነሱ ግን በማላውቀው ምክኒያት ያንጓጥጡኛል :: ንግግሬን ሳልጨርስ ጥለውኝ ሄዱ :: የራሳቸው ጉዳይ እኔ እነሱ ከሥንቱ ጋር ሲሆኑ ምን ብያለሁ ? በርግጥ ባለጌ ናቸው ብያለሁ ግን በቃ ኡፍፍፍፍፍ ውስጤ በከፊል ሲራበሽ መልሥ ለማልሠጠው ጥያቄ ሲከምር ይታወቀኛል ውስጤም የራሡ ጉዳይ ከማለት ውጭ ምርጫ አጣሁለት ቀኑ አልመሽ ስራውም አልገፋ አለኝ :: የምንጓጓላቸው ነገሮች ለምን ትዕግስታችንን እንደሚፈታተኑት ባይገባንም እንታገሳለን ለትዕግስት ከምናባክነው ግዜ በላይ ታግሰን የምናገኘው ነገር በላጭ እንደሆነ ስላመንን ይሆናል::ግን ለምን ጓጓሁ? ድጋሚ ሌላ ጥያቄ ድጋሚ መልሥ ማጣት!!
ሰአቱ ደርሶ ጋውኔን አውልቄ ወጣሁ ሰሚር ቀድሞኝ ተገኝቷል :: ዛሬም እንደ ትላንቱ ራሴን እያስረሳኝ ሌላ ሰው እያስመሰለኝ ምንም ሳያጨናንቀኝ ተለያየን ቀናት ተቆጠሩ የሰፈር ሰዎችም ለመዱት:: እኔም ካልደወለ ቅር እያለኝ ካላገኘሁት ይከፋኝ ጀመር ሁሌም እንገናኛለን እናወራለን ንግግሩ የኔን አለም አስረስቶ የሱ አለም ውስጥ ይከተኛል ;: ሰሚር ልዩ ሰው ነው ሰው ሁሉ ለሚወደው አካል ልዩ ነው ስለዚህ ያሰው እውነትም ልዩ ሆኖ ሳይሆን እኛ ውስጥ ያለውን ልዩ ፍላጎት በዚያ ሰው ላይ ስላገኘነው ይሆናል :: ከቀናት ባንዱ ግንኙነታችን ላይ የተከሠተውን ነገር ሣሥበው አሁን ድረሥ ይገርመኛል ጌታዬ ምንም ቤሆን ባርያውብ ወደራሡ የሚመልሥበት ጥበብ አለው:: በሥራ መውጫ ሠአቴ ላይ ነበር ሠሚር እንደተለመደው በር ላይ ቆሞ ሲጠብቀኝ ተገናኘን ሰሚር ፊቱ ላይ አይቼው የማላውቀውን አይነት የሃዘን ካባ ተከናንቧል ልቤ ተረበሸ ምን እንደሆነ ከመጠየቅ ይልቅ በራሡ ፍላጎት ይነግረኝ ዘንድ መጠበቅ ጀመርኩኝ አንድም ቃል አልተነፈሠም መኪናዋን አሥነሥቶ ሄደንበት በማናውቀው መንገድ እየነዳ ነው በየመሀሉ ከረዥም ትንፋሽ ጋር "ኢና ሊላህ " እኛ የአላህ ነን ሲል ይሠማኛል ልቤ በጣም ፈርቷል :: ቆይቶም ከአንድ ነጭ የድንኳን ዳሥ ከተጣለበት ትልቅ ግቢ ፊት ለፊት መንገዳችን ተገታ በሩን ከፍቶ እንድወርድ ጠየቀኝ አልተቃወምኩትም::
"ተከተይኝ" ከዚያ ሁሉ ጥበቃ ቡሀላ ይቺን ቃል ተንፍሶ በድንኳኑ መሀል ማቋረጥ ጀመረ ከግራና ቀኝ ሠዎች በሀዘን ኩርምት ብለው ተክዘዋል ምንም አላማረኝም የለቅሦ ሹክሹክታቸው ልቤን ነካኝ የራሴ ሀዘን ትዝ አለኝ እኛ ሠዎች ሥንባል ለሀዘናችንም ይሁን ለደሥታችን አሥታዋሻችን ቅርብ ነው ሆዴ ተላወሠ :: ሠሚር ከአንድ አነሥተኛ ክፍል ውሥት ይዞኝ ገባ ክፍሏ ጨለም ያለች ሆና በትንሿ መሥኮት አማካኝነት በጥቂት የብርሀን ጨረሮች ታግዛ እርሥ በርሥ ታሥተያያለች ምንጣፍ ተነጥፎበታል ከመሥኮቱ ትይዩ ተለቅ ያለ ቁርአን በእንጨት ማሥቀመጫ ላይ ተከፍቶ ተቀምጧል ::ሠሚር ከቁርአኑ ፊት ለፊት ተቀምጦ ማልቀሥ ጀመረ ከዚህበላይ መታገሥ አልቻልኩም የሆነውን እንዲነግረኝና የት እንዳለን አጥብቄ መጠየቅ ጀመርኩኝ ሠሚር ከእንባ እና ሲቃ ጋር እየተናነቀ መናገር ጀመረ...
"ሂዱ ይሄ የኛ ቤት ነው ከልጅነቴ ጀምሮ የአባቴን ቦታ ተክቶ ያሣደገኝ በዱንያም በአኼራም ጉዳይ ትልቅ ትምህርትን የሠጠኝ አያቴ ዛሬ ወደማይመለሥበት አለም ሄዷል!" አለኝ ኬት መጣ የማልለው እንባ ያጥለቀልቀኝ ጀምሯል ምን እንደምለው አላወቅኩም ንግግሩን ቀጠለ....

ይቀጥላል
ሼር ያድርጉት!

For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
ይህ ነው እንግዲህ!!!
ነገ በጌታው የሚክደው!
ነገ የጌታውን ፀጋ የሚያስተባብለው!
ነገ በራሱ የሚኮፈሰው!
ነገ ሰዎችን የሚበድለው!
ነገ የቲምን ገፍትሮ፣ድሀን አዋርዶ የሚኖር!
"ሰው ከአሁን በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲሆን እኛ የፈጠርነው መሆኑን አያስታውስምን?" (መርየም ፡ 67)
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1
👉ምን በልተን ይሆን??????
* * *
:- ታዋቂው ሙስሊም ሳይንቲስት # ኢብኑ ኸልዱን# " አልሙቀዲማ" በተሰኘው መፅሀፉ ውስጥ እንዲህ ሲል ፅፏል
አረቦች ግመል መብላት አዘወተሩና ቅናትና ጥርጣሬን ከሷ ወረሱ
* * *
ቱርኮች ፈረስን ባህላዊ ምግባቸው አደረጉና ጥንካሬና ሀይልን ከሷ ወረሱ
* * *
አፍሪካውያን ዝንጀሮን ተመገቡና ዳንስና ጭፈራን ከሷ ወረሱ
* * *
ፈረንጆች አሳማ በሉና ስለትዳራቸው ቅናት የሚባል ነገር ከውስጣቸው ጠፋ
# ኢብንል ቀይም እንዲህ ይላሉ:-
" የሰው ልጅ ሁሉ የተኗኗረውንና የተላመደውን እንሰሳ ባህሪይ ይወርሳል።
ስጋውን የበላ እንደሆ ደግሞ ውርርሱ ያየለ ይሆናል።"

🙊 ታዲያ እኛስ ምን በልተን ይሆን ከዚህ ዲነል ኢስላም በእጅጉ ሰው በሚፈልግበት ዘመን በዚህም በዚያም በትንሽ በትልቁም የምንናቆረው ?????
የዶሮ ስጋው ይሆን?!!!

JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
Sheikh As Sudais & Ash Shuraim ::: Al-Qur'an Juz 1
Usep Kertarajasa
ረመዷን 19 ጁዝ (19)

Al'Furqan 21 – Al'Naml 55
Sheikh Shuraim & Sudais

እናስተንትን ትርጉሙን ለማወቅ እንሞክር
መልካም ግዜ ከንግግሮች ሁሉ በላጭ
ከሆነው የአላህ ቃል (ቁርኣን) ጋር💞
✿┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
❤️ ……በእርርግጠኝነት ሁላችንም በህይወታችን ውስጥ የምንወዳቸው ሰዎች አሉን። ይህ ለሰዎች ነው።❤️
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
ከመልካም ስሞቹ መካከል " #አል_ወዱድ " /ወዳድ/ አንዱ ስለሆነው #ስለ_አላህ_ሱ_ወ ምን ይሰማናል????
🌺🌺🌺 #አል_ወዱድ 🌺🌺🌺
እስቲ ይህንን,#ሀዲስ ቆም ብለን እናስታውስ :-
"የመጀመሪያው ሰማይ በሁለተኛው ሰማይ ውስጥ ሲሆን በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። ሁለተኛው ሰማይ በሶስተኛው ውስጥ በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። ሶስተኛው በአራተኛው ውስጥ በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። አራተኛው በአምስተኛው ውስጥ በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። አምስተኛው በስድስተኛው ውስጥ በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። ስድስተኛው በሰባተኛው ውስጥ በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። ሰባተኛው በዐርሽ ውስጥ በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። ዐርሽ ደግሞ በኩርሲይ/መንበር/ ውስጥ ሲሆን በበረሃ ላይ እንደተጣለች ፍሬ ነው። መንበሩ ከሰማያትና ምድር በላይ ይሰፋል።"
እስቲ እናስብ…… ከነዚህ ሁሉ ግዙፍ #የአላህ ፍጥረታት አንፃር እኛ ምን ያህል ነን?? በርግጠኝነት እዚህ ግባ የማንባል ኢምንት ነን። ነገር ግን #አላህ_ሱ_ወ ቦታ ሰጠን። መጠናችን ይህን ያህል ትንሽ ከመሆኑ ጋር ይወደናል።
🌺🌺🌺 #አል_ወዱድ 🌺🌺🌺

❤️ " #አል_ወዱድ /ወዳድ/"የሚወድ ብሎ ራሱን ሰይሟል። እስቲ አርቀንም እናስብ አብዝተንም እናስተንትት።❤️
💐💐💐 #አል_ወዱድ 💐💐💐

ይህ የምንናገረው ሁሉ #የሙስሊሞች የእምነት አመለካከ (ዐቂዳ) መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል። እንዴት???
አዎን #አላህ_ሱ_ወ ፈጣሪ መሆኑን እንዳረጋገጥነውና እንዳመንነው ሁሉ 🌺 #አል_ወዱድ 🌺 ወዳድ፣/የሚወድ/ መሆኑንም ሙሉ በሙሉ ማመን ይኖርብናል።❤️
ይህ በቀልባችን ውስጥ ቋጥረን የምንይዘው የፀና አቋማችን /ዐቂዳ/ መሆን ይኖርበታል።
🌺🌺" #አል_ወዱድ" ውደደን!!🌺🌺
Amiiin
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° ° °
💖የሰዎች ልብ ንፁህና መልካም
እንዲሆንልህ ከፈለግክ 
💖አንተም ለነሱ ልብህን ንፁህና
መልካም አድርግላቸው

(وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ)
" መልካሚቱና ክፉይቱም (ጸባይ) አይተካከሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር  ያን ጊዜ ያ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይሆናል ፡፡" [ፉሲለት 34]

☺️መልካምነት ከራስ ነው የሚጀምረው
መልካም ስትሆን በአጠገብህ የሚገኙት
መልካም ይሆኑልሃል
👿መጥፎ ስትሆንም በአጠገብህ የሚገኙት. መጥፎ ይሆኑብሃል

🌼ጥሩ ሰው ጠፋ ከማለት አንተ ጥሩ ሆነህ የመጀመሪያው ሁን

https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
••┈┈•⊰✿ 🌺 ✿⊱•┈┈••
#share #share #share
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋ ﹋ ﹋
2
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሀን አራስ
(ክፍል ስድስት)
ሚስጥረ ጀማል

" ሂዱ ይሄ ቦታ አያቴ በከባድ በሽታ ምክንያት ለ 10 አመት ያህል የአልጋ ቁራኛ ከሆነ እና ከአለም ተሥፋ ሲቆርጥ ቀንከሌት በአምልኮ ደፋ ቀና ያለበት ቦታ ነው ሁሌም ሥመጣ በኢባዳ ላይ ነበር የማገኘው ትንሽ እንዲያርፍ ሥጠይቀው 'ልጄ ይሄ አለም የሥራ እንጂ የእረፍት አይደለም የኛ እረፍት ሰማይ ቤት ነው ደግሞሥ ለጌታዬ ያልሠገድኩ ለማን ልሠግድ ነው?' ይሉኝ ነበር ሂዱ ይሄው ወደ ዘላለም እረፍቱ ሄደ አላህ የጀነት ያድርገው" ሰሚርን በዚህ ሁኔታ በማየቴ ልቤ ተሠበረ ነገር ግን ይሄን ሁሉ ለኔ ለምን እንደሚነግረኝ ተገልፆልኛል ከዚህ በላይ መቆየት አልፈለግኩም ሠሚርን ማፅናናት ከማልችልበት ከባድ ሃዘን መሃል ትቼው ከገባሁበት ፍጥነት በቀዘቀዘ እርምጃ ወደቤቴ አዘገምኩ የኔ ጌታ እና የሠሚር አያት ጌታ አንድ መሆኑን እያወቅኩ እሣቸው ከህመም ጋር እየታገሉ ጌታቸውን የፈሩትን ያህል እኔ ባለመፍራቴ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ሥጋት ገባኝ ቤተሠቦቼ በህይወት እያሉ የነበረኝ ጥቂት ትዝታ ውሥጥ እንጂ ከዛ ውጪ ጌታዬን ትዕዛዛቱን ክልክላቱን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቼ እንደኖርኩ ተገለጠልኝ ሠሚርም ይሄን ተረድቶ ሊያሥረዳኝ መሞከሩ ገባኝ አንዳች የጌታዬ ፍቅር እንደ ዝናብ ልቃቂቅ ከልቤ መሀል ላይ ጠብ ሲል ተሠማኝ
ቀናት ቀናትን ወለዱ ሠሚርም ቀሥ በቀሥ ከሃዘን ሥሜቱ ተላቀቀ ከለቅሦ ቡሃላ በተግፕናኘን የመጀመርያው ቀን እንደተለመደው ብቻውን ለመሥገድ ሲመቻች እኔም ከኋላው ለመሥገድ መቆሜን ያየ ቅፅበት ላይ ፊቱ ላይ የነበረውን የደሥታ ወጋገን ያየ ፀሃይን ይንቃል በሚፍለቀለቅ ፈገግታ ውስጥ ሆኖ" ሂዱ ከተገናኘን ከ አራት ወር ቡሀላ ሰላት ኖረሽ???" በማለት በሳቁ አሳቀኝ
የአንዱ ሞት እንኳን ለአንዱ ከተኛበት ለመንቃት ሰበብ እንደሚሆን በራሤ ደርሶ አየሁት አልሃምዱሊላህ
ዛሬም እንደተለመደው የሠሚር መኪና እኛ በር ላይ ቆማለች እኔም በሩን ከፍቼ ወረድኩ ሠሚር ከኋለኛው የመኪናዋ ወንበር ላይ አንድ የታሸገ ካርቶን እያቀበለኝ ቤት ግቢና ከፍተሽ እይው ደህና እደሪልኝ ብሎኝ ሄደ :: ተጣደፍኩ የዛች መከረኛ ጎጆዬ ቁልፍ አታገለኝ ምን አሥቸኮለኝ የሚነጥቀኝ

የለ ብዬ ብፈ

ላሠፍም ልቤ ልታፀድቅልኝ አልቻለችም ቤት ገብቼ በሩን ከውሥጥ ቆለፍኩትና የእሽጉን ቁልፍ በተራው መታገል ጀመርኩ ውበቱ የሚያስደነግጥ ሙሉ ቀሚስ ከነ ሻርፑ አገኘሁ ከዚያ ሥር ደግሞ የተፈጥሮ ያልሆነ አርቴፊሻል ቀይ አበባ:: አበባው ላይ የማውቀው ሽቶ ተነሥንሷል የሠሚር ሽቶ ደሥ አለኝ ደነገጥኩ::ፈራሁ ::ለምን አርቴፊሻል ሆነ??? ምን ማለቱ ነው??? ከልቤ አደለም ማለቱ ነው??? ድሮም ምኑም አላማረኝም እኔም ራሴ ሞኝ ነኝ ይህን የመሠለ ባለፀጋ ከእንደኔ አይነት ከርታታ ጋር ምን ይሁን ብሎ ይኖራል??? ተነጫነጭኩ ለደቂቃዎች አኮረፍኩ ቆይ ግን ምኑ ነው ከልቡ ያልሆነው??? ፍቅሩ??? መውደዱ??? ሲጀመር መች እወድሻለሁ አለኝና ነው ጥራቱን የምመዝነው??? የማልረባ! ከራሤ ተባላሁ ሥልኬ ጮኸች:'
አነሣሁት ሠሚር ነው በተደበላለቀ ሥሜት ውሥጥ ያልተጣሩ ቃላት አወራሁት "ልብሡን ወደድሽው?"
"የቱን? እ አዎ እንዴታ"
"ልክሽን በግምት ነው እንግዲህ ሆነሽ? ለካሽው?"
ወይኔ ጉዴ ሥለ አበባው ሥፈላሠፍ ዋናውን ጉዳይ ረሥቼው ነበር
"ቆይማ እንዳትዘጋው ልለካው "
ሥልኩን አሥቀምጬ ልብሥ መቀየር ጀመርኩ እንዴ ምን ሆኜ ነው??? ምን አርበተበተኝ ??? "ሥልኩን አነሣሁት ልኬ ነው ሠሚር በጣም አመሠግናለሁ "
ግን....አ.አ.አበባው...??? አላሥጨረሠኝም እንደመሣቅ እያለ
"በቃ ነገ እሡን ልብሥ እንደለበሥሽ ላገኝሽ እፈልጋለሁ በዛውም የአበባውን ትርጉም አሥረዳሻለሁ ደህናደሪልኝ"
ወይ መከራዬ ጭራሽ ይስቅብኛል??? በሱ ቤት መቀለዱ ነው:: በሠው የተፈጥሮ ኦርጅናል ስሜት ላይ ሠው ሰራሽ ቀልድ እንዴት ይከብዳል??? እሥከዛሬ የነበረን ሁሉ እንደዚህ አበባ አርቴፊሻል ነው ቢለኝሥ??? የሀብታሞች ቀልድ እንዲህ ይሆን እንዴ???

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
💚 የሰው ልጅ ሲወድህ
ውብ እንደሆንክ እና ዱንያ ሰፊ
እንደሆነች ይሰማሃል...
๏ የውበት እና የዱንያ ጌታ
የሆነው አላህ ሲወድህስ...?

  » @ketibeb ⚘ღ
የረመዳንን የመጨረሻ አስር ቀናቶችን በቤት ውስጥ እንዲት እንጠቀምባቸው??

በዳዒ አህመዲን ሁሴን
መሀን አራስ
ክፍል ሰባት
(ሚስጥረ ጀማል)

ልብሱን እንደለበሥኩኝ የሃሣብ ባህር አናወዘኝ አይደለም እንዲህ ያማረውን ቀርቶ ማንኛውንም አዲሥ ልብሥ የበሥኩበት ግዜ በቅጡ እንኳ ትዝ አይለኝም እጅግ ከመቆየቱ የተነሣ ለብሼ አላውቅም ማለት ይቀላል :: ዛሬም ድረሥ የሠሚር ፍላጎት ግልፅ ባይሆንልኝም እኔ ግን ከእሱ ሌላ ሠው አለ ቢሉኝም የማላምንበት ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ሠው ማለት ለችግር ደራሽ ሢፈልጉት አለሁ የሚል ነው የሚል ያልታወቀ ፍልሥፍና ከልቤ ታትሟል ሠሚር ደግሞ ሳልጠራው አቤት የሚል ፃድቅ ነው ሥለዚህ ለኔ ሠሚር ማለት ሰው:: ሰው ማለትም ሰሚር ነው:: ለዛውም ሰሚር ብቻ::
ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር አደረ ለበአል ልብሥ ተገዝቶለት ከመጓጓቱ የተነሣ ልብሡን ለብሦ እንደሚያድረው ህፃን አይነት ስሜት ተሠምቶኝ ይሁን....ልብሱን ሣወልቀው ሰሚርን የማራገፍ ሥሜት ተሠምቶኝ ይሁን ባይገባኝም ቀሚሱን እንደለበሥኩት ነጋ እኔ የሠሚር ፈሪ:: እኔ የሠሚር ህፃን::
ጠዋቱን ተጣጠብኩና ወደ ስራ ወጣሁ እንደዛው እንደለበሥኩኝ እንደዛው እንዳማረብኝ:: ሰፈርተኛው መንገደኛው ቀርቶ ግድግዳና መሬቱ ሁሉ እኔን ብቻ የሚያይ ሥለኔ ብቻ የሚያስብ ሥለኔ ብቻ የሚያወራ መሰለኝ ማማር ግን እንዴት ደሥሥሥሥሥ ይላል::!!!
ካፌ እንደደረስኩ ሄዋንና መዲና ቀድመውኝ ሥራ ጀምረዋል ገና በሩን ከፍቼ ሥገባ ሁለቱም የባንዲራ ሰቀላ ላይ እንደቆመ ሰው ተገትረው ቀሩ ይሄ ሁሉ ለውጥ በሠሚር ምክንያት እንደተፈጠረ ሥለሚገባቸው "ሠውን ማመን ቀብሮ ነው" የሚሉ ይመሥለኛል ልክ ባንዲራ ሲሰቀል "እኛም ባንቺ እንኩራ " እንደሚባለው መፈክር "እኛስ ባንቺ አፈርን" ብለው ትንግርታቸውን ሲያገባድዱ ይታየኛል አንገቴን ደፋሁ :: ወደኔ ተጣደፉ ወንበር ላይ አሥቀመጡኝና እንደመልዐክት ክንፍ ሄዋን ከግራ መዲና ከቀኝ ቆሙ ወድያውም በየተራ ምክር መሣይ ዱላቸውን አወረዱብኝ ወገሩኝ::
ከግራ በኩል " ሂዱ አረ ባክሽ አይንሽን ግለጪ እንዴት ይሄንን ጉድ መለየት ተሣነሽ???"
ከቀኝ"ቆይ ግን አንቺ ያቺ ለኛ ለባልደረቦቿ እንኳን ፊት የማትሠጠው ሂዳያ ነሽ ወይስ ሌላ ነሽ??"
ከግራ" ሂዱ እኛ የሃብታም ሠዎችን ባህሪ እናውቃለን እንደማሥቲካ መጠው ለመትፋት እንደ እቃቃ ጥሩ ቀልድ የበዛበት ጨዋታ ለመጫወት እንደ ደሃ ሴት ነፍስ የሚመቻቸው የለም".....
ተዘባበቱብኝ አስፈራሩኝ ፈራሁላቸው ሰሚር እየቀለደብኝ መሥሎ ተሠማኝ የለበሥኩትም ቀሚስ ሠሚር ለሚጫወትባት አሻንጉሊቱ ብሎ የገዛው ቅያሪ መሠለኝ እኔ የሰሚር አሻንጉሊት::! " አረ ሰሚር እንደዛ አይነት ሠው አደለም" ለማለት ሲቃጣኝ " እኛም ስንቱን ሠይጣን በመልዐክ ሥንመሥል ኖረን ከረፈደ ነቅተናል ሞኝ አትሁኚ " አሉኝ ሠሚር የኔ ሸይጣን???
አለቃችን መምጣቱን ሲያዩ መዲና እና ሄዋን ባለሙያ ሴት እፍፍፍ እንዳለችው ብጣሪ ገለባ ካጠገቤ ተበተኑ እኔን ግን መንቀሣቀሥ እንዳልችል አድርገው አሳስረውኛልና ከነበርኩበት ሣልነቃነቅ አለቃዬ ካጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ
"ፓ ፓ ፓ ልዕልት መሥለሽ የለም እንዴ ሠሚርን እይታውን እንዳደነቅኩለት ንገሪው " አለ የሚያሾፍብኝ መሠለኝ ወድያውም ለመጀመርያ ግዜ ከሠሚር ጋር አብሬ የሄድኩበትን ቀን ለመርገም ሥቃጣ አለቃዬ ባይፈቅድለት ኖሮ እንደማልከተለው ትዝ አለኝና
" ግን የዛን ቀን ሠሚር ምን ብሎህ ነው ይዞኝ እንዲሄድ የፈቀድክለት?" እየተቅለሠለሥኩ ከቁጭት ጋር እየታገልኩ ጠየቅኩት
"የምርሽን ነው??? ሰሚር ሥለኔ ምንምአልነገረሽም???"
አረ በፍፁም ደነገጥኩ
" ሠሚርኮ ከልጅነት ጀምሮ አብሮ አደጌ ከድህነት ሠበዞች መሀል ጎትቶ አውጥቶ እዚህ እንድደርሥ የረዳኝ የህይወት ዘመን ከባድ ባለውለታዬ ነው እናማ አይደለም አንቺን ብቻ ያሉኝን ሠራተኞች በሙሉ ከኔው ከራሴ ጭምር ባሻው ሰአት ይዤህ ልሂድ ቢለኝ አይኔን አላሽም ምክንያቱም እንደማይጎዳሽ እርግጠኛ ነበርኩ"
ታድያ ይሄን ሁሉ ደግነት ከልቡ ፈልቅቆ አራግፎ እኔን እንዴት ሊጎዳ ይፈልጋል?? ፍላጎቱ እንደዛ ቢሆን ቢያንሥ በዚህ ሁሉ አብሮነታችን አንዲት ምልክት እንኳን ማየቴ ተገቢ ነበር::ሥለዚህ ሠሚር ልቡ ማንኛውም አካል ሲቸግረው እጁን ሠንዝሮ የሚፈልገውን ያህል የሚቆነጥርበት የደግነት ካዝና እንጂ የክፋት ማዘጋጃ አይደለም ። ሠሚር የኔ ደግ:: የልቤ ተሥፈኝነት ፊቴ ላይ አበራ ከዚህ ቡሃላ ሥለ ሠሚር ከራሡ ውጭ ማንንም አልሰማም አልኩ::
እንዳይደርሥ የለምና ሠአቱ ደረሠ ሠሚር እንደተለመደው ከካፌያችን በር ላይ መቆም አላረካውም ዛሬ ወደ ካፌያችን ገባ ከቁመናው ጋር ቀልብን የሚሠልብ ጥቁር ሙሉ ልብሥ ለብሷል ለመውጣት መዘጋጀቴንና ከቀሚሱ ጋር የሠጠኝን አርቴፊሻል አበባ መያዜን ሲያይ ፈገግ አለ:: አማረኝ::
"እጅግ አምሮብሻል"እኔ በምሠማበት ድምፅ ያህል ተናገረ።
"ያንተን ማን በነገረህ!" እሡ በማይሰማበት ድምፅ ያህል ተናገርኩ ::በሆዴ::
ሠሚር የመኪናውን በር ከፍቶ አሥገባኝ ወድያውም
"ወዴት እንደምንሄድ እንድታዪ አልፈልግም ሥለዚህ ቅር ካላለሽ አይንሽን ልሸፍንሽ ነው"
እሺታዬ ን ገለፅኩለትና በሠጠኝ ጨርቅ በገዛ እጆቼ እይታዬን ለመሸፈን አይኔን አሠርኩኝ::
አይኔ እንጂ አዕምሮዬ አልታሠረም ነበርና በአንድ በኩል የነ ሄዋንን በአንድ በኩል የአለቃዬን ንግግር እየከለሥኩ አሥባለሁ መሃል ላይ ደግሞ ሠሚር እሥከዛሬ ምንም አይነት የነሄዋን ሃሣብ አይነት ነገር አለማሣየቱ እረፍት ይሠጠኛል ቢሆንም ግን እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም:: መኪናዋ መቆሟን ተረዳሁ" አሁን አይንሽን መግለጥ ትችያለሽ" አለኝ በህይወቴ ለመጀመርያ ግዜ አይኔ የሚበራልኝና "እሥቲ እውነትም አይንሽ እንደበራ አረጋግጪ "የተባልኩ ይመሥል ተጣደፍኩና ማሠርያውን ፈታሁት ::

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
1👍1
"የመጨረሻው ቀን ―ሲቀርብ!
•┈┈•⊰✿✿⊱•┈┈•

⇨ነብያችን ﷺ የመጨረሻው ቀን ሲቃረብ ያለዉን ሁኔታ ሲገልፁ እንዲህ አሉ፦

⇨ጊዜ ይቀራረባል እውቀት ይነሳል ፈተና ግልፅ ይወጣል ፣ ስግብግብነት 【ስስት】 ይስፋፋል ፣ "(ሀረጅ"ም )ይበዛል አሉ:: "
·
⇨ ሀረጅ" ደግሞ ምንድን ነው ሲባሉ? ነብያችን ﷺ "ግድያ ነው" አሉ፡

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል···

ኢስላማዊ ትምህርት ይቀላቀሉ
↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯↯ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
••┈┈•⊰✿ 🌺 ✿⊱•┈┈••
መሀን አራስ
ክፍል ስምንት
(ሚስጥረ ጀማል)

ዙርያውን ሠው ረግጦት የማያቅ የመሠለ የደረቁ የጠወለጉ ዕፅዋት የከበበው አቧራ የለበሠ የድንጋይ ጉልላት ነገር ይታየኛል :: ግራ መጋባቴን የፃፍኩበትን አይኔን ያነብልኝ ዘንድ ወደ ሠሚር ዞርኩ እሡም ወርጄ እንድመለከት በሚያዝ መልኩ ምልክት ሠጠኝ:: ከመኪናዋ ወርጄ ወደቤቱ ተጠጋሁ ያየሁት ነገር የመሥጂጅ ቁባ ነበር ከማርጀቱ የተነሣ ቀለሙ ከላዩ ላይ ገፏል አይደለም ወደ መስጂዱ ወደዚያ ሠፈርም ሠው ዝርብሎ የሚያውቅ አይመሥልም አሣዘነኝ!!! ሠዎች ለመኖርያ ቤታቸውን ግፋ ቢል በየአመቱ አጠቃላይ እድሣት ያደርጋሉ እንደዚህ ያለ የሃያሉ ጌታዬ ቤት ግን በየቦታው አቧራ ለብሶ አለሁ ባይ ያጣል::
"ሂዱ አያሣዝንም?"አለኝ ሠሚር። ማዘኔንማ ከአይኔ ተረድቷል ምን መናገር እንዳለብኝ ሥላላወቅኩ ዝም አልኩት
"በርግጥ ግራ ሊገባሽ ይችላል ዛሬ እዚህ ያመጣሁሽ ግን በመብራቶች ከተንቆጠቆጡ በምንጣፎች ካጌጡ በሠጋጅ ምዕመናን በቁርአን ድምፆች ካሸበረቁት መሥጂዶች እኩል እንደዚህ በእርጅና ሠዎች የረሷቸው በአቧራ የተወረሡ መስጂዶችንም አላህ እንደሚመለከት እና በዚህ ከግንባታው አንፃር እዚህ ግባ የማይባል ካገልግሎቱ አንፃር ግን በተከበረው በአላህ ቤት ፊት ሆኜ እንደማልዋሽ እንደምታምኚ እርግጠኛ ሥለምሆን..."
ሠሚር ንግግሩ ሢረዝም ግራ ተጋባሁ ዞር ብዬ አይን አይኑን ማየት ጀመርኩ ሲርበተበት ደረሥኩበት
"ሂዱ በጌታዬ ቤት ፊት ቆሜ በጌታዬ ሥም ምዬ ነው የምነግርሽ እድሜዬን በሙሉ ካንቺ ጋር ማሣለፍ እፈልጋለሁ ::"
እርርርርርፍፍፍፍፍ
እሡ ተነፈሠ እኔ በተራዬ ትንፋሽ አጠረኝ::የምናገረው እንደጠፋኝ ሢገባው በእጄ ላይ የያዝኩትን አርቴፊሻል ቀይ አበባ ተቀበለኝ ዝም ብዬ ከማየት ውጭ አማራጭ አጣሁ
" ሂዱ ለምን አርቴፊሻል አበባ እንደሠጠሁሽ ታውቂያለሽ??? ኦርጅናሉን ብሠጥሽ ይሄኔ ጠውልጎ

ነበር የኔ ላንቺ ያለኝ ሥሜት ግን ለመጀመርያ ግዜ ከአለቃሽ ጋር ወደ ካፌ ሥንመጣ ካየሁሽ ጀምሮ እሥከዛሬ ድረሥ እየፋፋ እንጂ እየጠወለገ አልሄደም እሥቲ አንቺው ንገሪኝ እንዴት ብዬ የማይጠወልግ ፍቅሬን በሚጠወልግ አበባ ልግለፅልሽ??? እንዴት ብዬ ህያዉን ፍቅሬን ከቀናት ቡሃላ በሚሞት አበባ ልግለፅልሽ???
ሂዱ አፈቅርሻለሁ!!! ፍቅሬ ተፈጥሯዊ ነው ግን የማይጠወልግ የማይሞት ፍቅር:: ሂዱዬ ታገቢኛለሽ ኣ?" ነፍሴ ጮቤ ረገጠች።
ሠሚር የኔ ጨዋ ነበር።
ሠሚር የኔ ቆንጆ ነበር።
ሠሚር የኔ ደግ ነበር ።
ዛሬ ደግሞ ሠሚር የኔ ፍቅር
ሰሚር የኔ ባል ሊሆን ነው ።
ንግግር ሲቸግር እንባ ይቀላል ፈገግታ ሣቅ እንባና ለቅሦ የተደበላለቁበት ሥሜት አሣየሁት። ደሥ አለው:: ደሥ ሲለው ደስ አለኝ:: ደሥ አለን::
"ሂዱ ሽማግሌ ልላክ?" አሥደነገጠኝ እኔ ዘመደቢሥ እኔ ዘረቢሥ እኔ ብቸኛ ነኝ ሽማግሌዎቹ ማንን ሊጠይቁ ነው ??
"ማንም እንደሌለሽ አውቃለሁ ግንኮ አላህ አለሽ እሡም እኔን ሠጥቶሻል ሥለዚህ መላ አለን አክስቴ እቴቴ ትንሽ ወግ ሥለምታከር እኔ ሽማግሌዎቹን አሥረዳቸዋለሁ ከዛም አንቺ ቤት መጥተው እንደተፈቀደልኝ ለቴቴ ይነግሯታል" አለኝ እኔ ግን ፈርቻለሁ " ከዛሥ ከሠርጉ ቡሃላ ቤተሠቦችሽ ቢሉኝሥ?"
" ለሡ ችግር የለውም የቅርብ ዘመዶችሽ እንዳልሆኑና ወደሀገራቸው መመለሣቸውን እንናገራለን " አለኝ እናቴ መሞቷ ለሁለተኛ ግዜ አዲሥ ሀዘን መሥሎ ተሠማኝ ይሄንን እንደማልሥማማበትና ቤተሠቦቹ ከተቀበሉኝ ካሁኑ ማንነቴን አውቀው መሆን እንዳለበት ነገርኩት። ሀሣቤን ተቀብሎ ለቤተሠቡ ሲናገር ሁሉም እሺ ብለው እናቱ የኔን ብቸኝነት ተቃወሙ እኔ እድሜ ልኬን የኖርኩበት ብቸኝነት ለጆሯቸው አሥጠላቸው አታገባትም ብለውት እንደነበርም ሠምቻለሁ:: ነገር ግን በሠሚር እልህና ድርቀት ምክንያት ጋብቻው ተወሠነ::ሠሚር ማታ ማታ ካደረሠኝ ትንሿ ጎጆዬ ውሥጥ ተሞሽሬ በድጋሚ ላልመለሥባት ትቻት ወጣሁ መዲና እና ሄዋን የሚዜውን ቦታ ሸፈኑልኝ ከሰርጉ ቀን ጀምሮ የአክሥቱ አይን እንደእሣት እየፈጀኝ የብቸኝነት ውርጭ እየተፈራረቀብኝ ሥኖር ከሠሚር ፍቅር ውጪ የሚያባብል የሚያፅናና አንዳችም ወገን አልነበረኝም ::
ይሄ የአምሥት አመት ታሪኬ ነው::
እነሆ ዛሬ የሠሚር አክሥት እቴቴ እኔና ሠሚር ለአራት አመታት ያህል በፍቅር የኖርንባት የግል ቤታችን ሊመጡ ነው። ይሄን ሁሉ አመት ልጅ መውለድ ባለመቻሌ ይረግሙኛል
"ከሷም ብሦ ደግሞ ዘርህን ሣትቀጥል ተንጠልጥለህ መቅረትህ ነው???" ሲሉት ብዙ ግዜ በጆሮዬ ሠምቻለሁ:: ሠሚር ግን "አላህ ይሠጠናል" ከማለት ውጭ አንድም ቀን ተማሮብኝ አያውቅም :: ዛሬም ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥቼ ሥነፈርቅ ያደርኩበት ትልቁ ምክንያት ይሄው ነው::ይሄው ዛሬም መኝታ ክፍላችን ውስጥ ካለው ቁም ሣጥን ላይ በክብር ለአመታት ያሥቀመጥኳት ያቺ አርቴፊሻል ቀይ አበባ ድሮዬን ታሥታውሠኛለች ይሄንን የአመታት ታሪክ ሣብሠለሥል የሠሚርን መኪና ክላክሥ ከገባሁበት ሠመመን አባነነኝ በሩን ከፈትኩት ከሠሚር አጠገብ አክሥቱ እቴቴ አሉ
" ወይ መከራዬ" አልኩ በልቤ ለአይኗ ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ የልቤን ሥቃይ የዛሬዋን እንግዳዬን ለመቀበል ከሳቅ ይልቅ እንባ እንደሚቀለኝ ማን በነገራት እያልኩ::

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍2
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
🔊ፈዲለቱ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ፦
┄─═✧═✧═✧═✧ ═✧═✧═✧═✧═─
« ዘወትር ነፍስህ ወደ ወንጀል፥ ወደ ብልግና፥ ወደ ዝሙት እየመራችህ ካገኘሃት ይህ ከሸይጧን ነውና ወደ አላህ (عز وجل) ጥበቃን ልትፈልግ ይገባል። አላህም በዚሁ አዞሃል። እንዲህ ሲል . .

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
{{ከሸይጧን ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ። እርሱ ሰሚውና አዋቂው ነውና።}} [ሱረቱልአዕራፍ 200]

በርሱ ስትጠበቅ ይሰማሃል። ያለህበትን ሁኔታም ያውቃል። እንዴትም ሸይጧንን ካንተ ማራቅ እንዳለበትም ያውቃል። »
[ተፍሲር ሱረቱል ኒሳእ 1/325]

https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
👍1
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢብኑ ዓጣ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“የሴት ልጅ ውበቷ “ሐያዋ” ሲሆን የጥበበኛ ሰው ውበቱ ደግሞ “ዝምታ” ነው።”
["አሰምት ሊኢብኒ አቢ አድዱንያ" (ገጽ፡ 263)]


🥀እሕቴ ሆይ! እራስሽን ከዚህ አንቀፅ አንፃር ፈትሺ!

አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላሉ፦

﴿وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ﴾
☞"በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡"
[ ሱረቱ አል- አሕዛብ - 33 ]

☞ዐዒሻ ረዲየላሁ አንሃ ይህን የአላህ ቃል፦وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ
በቀራች ግዜ ሂጃቧ እስኪርስ ድረስ ታለቅስ ነበር።
📗[ተፍሲሩ አል ቁርጥቢ]

ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

“አላህ እኛንም እናንተንም ባወቅናት ነገር ተግባርን እንዲወፍቀን እጠይቀዋለሁ። እኛ ብዙ ነገር እናውቃለን፤ ነገር ግን ጥቂትን እንጂ አልሰራንበትም።”

📙 [ኪታቡ አል-ኢልም 86]
https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
Forwarded from ፈገግታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሀን አራስ
ክፍል ዘጠኝ
(ሚስጥረ ጀማል)

አንዳንዴ.....
' አብዛኛው ሠው የሌለው የአለም ህዝብ የሚቸገርበት የጋራ እጦት አልነካንም ሁሉ ነገር በእጃችን ሆኗል ::'ብለን ሥናሥብ ህዝበ አዳም በሙሉ በአንድ የእድል ለሊት ያለ ሽሚያ በገፍ የተቸረው ሥጦታ ደግሞ ሲያጥረን ይታያል:: በዚህ እጦት ምክንያት ደግሞ በእጃችን ያሉ ከባባድ ንብረቶች እንደ ኢምንት ያህል ይቀሉብናል::
እኔ ላይም የሆነው ይሄው ነው:: እድሜ ልኬን ያጓጓኝ የነበረ መኪና እንኳን ወደዛች መከረኛ የስራ ቦታዬ ለመሄድ የታክሲ ብር ያጥረኝ እንዳልነበር አሁን መኪና በከለር ማማረጥ ጀምርያለሁ:: የዙርያዬ ጭርታ እንዳላሣመመኝ ብቸኝነት ሲያሰቃየኝ እንዳልኖርኩኝ ዛሬ የሰሚር እቅፍ የአለምን ህዝብ ፍቅር ተክቶልኛል::
የጎጆዬ ጥበትና አሥቀያሚነት ከሥራ መመለሤን እንዳላማረረኝ የቤተመንግሥት ያህል ሥፋትና ውበት ያለው አዳራሹ ቤቴ ውስጥ መኖር ጀምርያለሁ::
ሊያውም ከአለሜ ጋር
ከሰሚር ጋር ከተጋባን ቡሀላ እናት አባቱ ካወጡለት የቀበሌ ስሙ ይልቅ ዓለሜ ሥለው ልቤ በሀሴት ትዘላለች:: ምን ታድርግ? አለም ማለት ህዝባዊ ትርጉሙ ባይገባኝም በኔነት ስሌት ከኔ አካል ውጪ ያለ ጠቃሚ ነገር ነው ብዬ ነው ማሥበው ከኔ አካል ውጪ ያለው ብቸኛው ህያው እና ብቸኛው ጠቃሚ ነገር ደግሞ ሰሚር ነው ::ሥለዚህ በኔ ፍቺ አለም ማለት ሰሚር ሰሚር ማለት ደግሞ አለም ። የኔ አለም:: የኔ ብቻ::
በዚያ የችግሬ ዘመን ሠው የሚባል ፍጥረት መቅረብም መውደድም በማልፈልግበት ግዜ ብዙ አካላት ካጠግቤ ነበሩ ዛሬ ግን ለአለም ልቤን ሥከፍት ከጎኔ ያለው እሱ ብቻ ነው :: እነሆ ሙሉ ለሊቱን ያለ እንቅልፍ በድብልቅልቅ ሥሜት በእንባ ጎርፍ ሥጥለቀለቅ ያደረኩበት ጉዳይ አንድና አንድ ነው :: ከጋብቻችን ጀምሮ እኔን የሠሚር ሚስት አድርጋ ማሠብ የሚያማት አማቼ ጭራሽ ልጅ መውለድ አለመቻሌ ተጨምሮ ለአይኗ ጠልታኛለች
" ጥንዶች መሃን ናቸው ብሎ ለመወሠን በተከታታይ የሚደረግ ግንኙነት ባለበት ለአንድ አመት ያህል ጠብቀው ምንም አይነት እርግዝና ባለማግኘታቸው ነው ::" ተብሎ በተነገረን መሠረት ጠበቅን:: እናም ይሄ ታሪክ በኔና በአለሜ መሀል ተከሥቷል :: ከሁለት አመት የትዳር ቆይታ ቡሃላ ምንም አይነት የእርግዝና ምልክት ሥላላገኘን ከዐለም ጋር በመነጋገር የማህፀን ስፔሻሊስት ለማናገር ወሠንን ::
በተደረገልን ምርመራም ችግሩ ከኔ መሆኑንና በማህፀን ተፈጥሯዊ ችግር ምክንያት ልጅ የሚባል ፀጋ እኔ ውስጥ መፈጠር እንደማይችል በነገረን ግዜ የመርዶ ያህል ልባችን ተሠበረ :: የኔ ሃዘን ግን ከማንም በላይ የገዘፈ ነበር ሠሚር በኔ ምክንያት ልጅ ማጣቱ ህመሜን አበረታው :: ልጅ ማግኘት አልቻልንም:: እንዳሠብኩትም አለሜን ከሠሚር በላይ በልጅ ድንበር ማሥፋት አልችልም:: ነገር ግን ዶክተሩ ተመላልሠን ቼክ እንድናደርግና ማንኛውም ለዚህ ችግር መፍትሄ ይሆናል ተብሎ የሚገኝ ነገር የሚኖር ከሆነ እንደሚጠቁመን ነግሮ ከነሃዘናችን አሠናበተን::
ሠሚር እንደሚለው ከሆነ "አንቺን ልጅ እንድትወልጂልኝ ብቻ አደለም ያገባሁሽ:: የኔ መሆን ሥላለብሽ አላህ ሥለፈቀደው ነው :: ከልጅም ከምንም ውጪ ብቻሽን ሆነሽ እንዳገኘሁሽ ለብቻችን መደሠት እንችላለን :: አላህ ለኛ ያለውን ለማንም አይሠጥም ልጅ መውለድ በእድላችን ላይ ተፅፎ ከሆነ እንኳን እንዲህ እየጓጓን ባንፈልገው እንኳን ታረግዢልኛለሽ ልጅ ይኖረናል:: እመኚኝ::" ባላምነውም የምፈጥረው አዲሥ ነገር እንደሌለ ሥለገባኝ ተቀበልኩት::
በግዚያት ቆይታ መሃል ያለዘር እንዳሥቀረሁት እያሠብኩ በማዝን ግዜም " እኔ ብቻዬን አደለም ልጅ ያጣሁት አንቺም ጭምር እንጂ ፈልገሽ ሆን ብለሽ መሀን አልሆንሽም እኔ በጌታዬ ተአምራት አልማረርም ተሥፋ አልቆርጥምም"በሚል ማፅናኛ የልቤን ምት ይቀጥልልኛል :: እስትንፋሴት ፀጥ ካለበት እድሜዬን ከቆመበት ይቀጥልልኛል:: በንደዚህ አይነት ሁኔታ ሁለት አመታት አለፉ እኔና ሠሚር አሁን የአራት አመት ባለትዳሮች ነን:: ባለፉት አመታት ሁለታችንም ለይል ተነሥተን ጌታችንን እንማፀናለን :: በየ ግዜው ልጅ በማግኘት ኒያ ሠደቃ እናወጣለን :: እሥካሁን ግን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም::
የኔ አማች የሰሚር አክስት የሆነችው ቴቴ እኔና ሰሚር ከተጋባንበት ቅፅበት ጀምሮ ባገኘችው አጋጣሚ ሠዎች በተሠበሠቡበት ቦታ ሁሉ ሣይቀር እኔን ከማነወር ወደኋላ ብላ አታውቅም :: እኔ ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር ::ሠሚር የፈለግኩትን እንድገዛበት የሠጠኝን ገንዘብ ይዤ ልብስ ለመግዛት በወጣሁበት ተከትላኝ በሠፈራችን ገበያ ግርግር መሃል የሷን ቤተሠብ ገንዘብ የምመነዝር መድረሻ ቢስ መሆኔን ለአላፊ አግዳሚው ሥትሣለቅብኝ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር::
የሰርጋችን እለት እንደ አማችነቷ እጇን ለመሳም ሳጎነብስ እጇን እንዳልነካት ያሸሸችብኝ ግዜ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር::
ከተጋባን ቡሃላም እያንዳንዱን ቤተሰባቸውን ከነ ባለቤቶቻቸው ቤቷ ሥትጋብዝ እኔን ይዞ እንዳይሄድባት በማሥጠንቀቋ ሠሚርም አልሄድም ብሎ ከኔው ጋር ተሸማቆ ቤት ውሥጥ ሢውል ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር ::

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
የፍቅር ተምሳሌት ታጅ ማሃል
———
የሙግሃል ንጉሥ የነበረው ሼህ ጃሃን ለሶስተኛው ሚስቱ ለነበረችው ለልዕልት ሙምታዝ ማሃል ማስታወሻና የመቃብር ስፍራዋም መታሰቢያ እንዲሆናት በማሰብ በህንዷ ከተማ አግራ ውስጥ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን በወቅቱ 32 ሚሊዮን ሩፒ የፈጀ ሲሆን አሁን ባለንበት ዘመን ሲሰላ 70 ቢሊዮን ሩፒ የሚያወጣ ቤተ መንግስት እንደሆነ ይገመታል:: በዓለም አቀፍ ደረጃ አስገራሚና ማራኪ የሆነ ህንፃ ለፍቅሩ መገለጫነት አሰርቶላታል፡፡

ቤተ መንግሥቱም እጅግ በጣም ያማረና አስደናቂ ቅርስ ስለሆነ በዓለም መንግሥታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ማእከል (UNESCO) ተመዝግቧል፡፡ ታጂ መሃል የልዕልት ሙምታዝ ማሃል የአፅሟ ማረፊያ የሆነው ቤተ መንግሥት የንጉሱም አፅም ያረፈው በዚህው ህንፃ ነው::

በየጊዜው በብዙ መቶ ሺህ በሚቆጠሩ የዓለም ጉብኝዎች ይጎበኛል፡፡ ታጂ የሚለው ቃል የሙምታዝን ስም አሳጥሮ በመጥራት የሚጠቀሙበት ሲሆን ማሃል ደግሞ የአባቷ ስም ነው፡፡

ንጉሥ ሼህ ጃሃን ለዘለዓለማዊት የፍቅር አጋሩ ለልዕልት ሙምታዝ ማሃል ማስታወሻ እንዲሆነው በህንድ ከተማ የሠራው ታጂ መሃል የፍቅር ተምሳሌት ህንፃ፡፡
መሀን አራስ
ክፍል አስር
(ሚስጥረ ጀማል)

ይሄን ያህል ምን እንደበደልኳት ባይገለፅልኝም ሌላው ቢቀር ዘሯን ሥተካ ልጅ ሥወልድ ማየት የጠላችውን አይኔን በልጄ አይን ውጥ ማየቱን ትለማመድልኛለች ብዬ አሥብ ነበር ፣ እኔ እንድሥመው ባልፈቀደችልኝ እጇ ልጄን አቅፋ ታጫውትና ትክሥልኛለች ብዬ አሥብ ነበር
በገባያ መሀል ያዋረደችኝን ያህል ልጄን በክብር አቅፋ በሠው መሀል የኔ እና የሠሚር ልጅ መሆኑን በማሥተዋወቅ ትክሠኛለች ብዬ አሥብ ነበር
ነገር ግን ጌታዬ ይሄን እድል አልሠጠኝም አራት አመታት ያህል አንድም ልጅ ለመውለድ እድሉን አላገኘሁም ጠዋት በለቅሶዋ በጫጫታዋ ከእንቅልፌ እንድትቀሠቅሠኝ የምመኛትን ልጅ ጌታዬ አልሠጠኝም:: ቤቱ በዝምታ በጭንቀት ሲዋጥ በጨዋታዋ የምታደምቅልን ልጅ አልወለድኩለትም ::
ይሄን ሁሉ በመሀላችን ያለውን ያለመቻቻል ችግር ሥላየ ሰሚር የእኔና የሡን መኖርያ ከከተማ ወጣ እንዲል አድርጎታል:: ቴቴ አይደለም እንዲህ በአካል ተገናኝተን ይቅርና በሥልክ እንኳን ልቤን የሚያደማ ቃል ሣትጥልብኝ አትዘጋም ታድያ ትመጣለች ሲባል እንዴት አላልቅሥ?? እንዴት እንቅልፍ አልጣ???
ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል እንዲገቡ መራኋቸውና
ከማብሠያ ክፍሉ ወደ መመገቢያ ሱፍራ ምግብ ማቀራረብ ስጀምር ሰሚር እንደተለመደው እኔን ለማገዝ ብድግ ሢል አየሁት
"ተወው አለሜ እኔ እበቃለሁ ቴቴ እንዳይደብራት አጫውታት" አልኩ ፈገግ ያለፊት ለማሣየት እየሞከርኩ::
"እሺ በቃ እኔ ዝሁር ሠግጄ ልምጣ " ብሎ ከቤት ወጣ ፈራሁ:: የጠላት ወረዳ መሃል ያለምንም ትጥቅድንገት በታወጀ ጦርነት ላይ ብቻዬን ጥሎኝ የሄደ መሠለኝ:: ቴቴ ምን ትናገረኛለች ብሎ መገመት ? እንጂ ትናገረኛለች ወይ ? ብሎ መጠራጠር ዘበት ነው:: ምክንያቱም እንዲህ በግላጭ አግኝታኝ እድሏን ማክሸፍ እንደማትፈልግ አውቃለሁ
"እውነትም አለም! ወግ ወጉን ይዘሽዋል " አለች ቴቴ
"ምን ታደርጊ ያንቺ አለምማ አሸበረቀ ሞላልሽ የሡን አለም በልጅ ማጣት አጨለምሽው እንጂ እንደው አያሣዝንሽም??? ምናድርጎሽ ነው ይህን መአት የፈረድሽበት ምንበደለሽ???"
"ምን ላድርግ ቴቴ እኔምኮ ወድጄ አደለም አላህ ነው ሚሰጠው" እንደተለመደው የእንባዬ ወፋፍራም ዘለላዎች መሽቀዳደም ጀመሩ ::
" አላህማ መች ከለከለው አንቺ መሃል ተደነቀርሽ እንጂ እውነት እንደምትይው ከወደድሽው አንቺ ማትችዩ ከሆነ የምትችለዋን ዘሩን የምርቀጥልለትን አግብቶ ወልዶ ይሣምበ

ት"
ቴቴ ባገኘችኝ ቁጥር ይህን የቃል ፈንጂ ትጥልብኛለች ወድያውም ሠሚር ባንዳች ምትሃት ፈንጂውን አምክኖ ከፍንዳታ ይታደገኛል :: የኔ እንባ ጠባቂ:: አሁን አሁን ግን እራሥ ወዳድነቴ እና ሠሚርን የግሌ ለማድረግ ያለኝ ፍላጎት ቴቴ እንዳለችው ሠሚርን ብቻውን እንደማሥቀረት ያለተቀጥያ ዘር እንደማንጠልጠል እየተሠማኝ ነው:: ቴቴ ሳምንቱን ሙሉ በተለያዩ ቃላት በተመሣሣይና አንዳይነት የሃሣብ ጅራፍ ጀርባዬን ሥትገርፈኝ ከረመች አልቻልኩም :: በታላቅ የራሥ ወዳድነት ሃጥያት ምክንያት የሀገሪቷ ንጉሥ በበደልኩት ህዝብ ፊት ትቀጣ ብሎ የፈረደብኝ ይመሥለኛል በድላሃለች የተባለው ህዝብ ግን በድላሃለችና ትሰቀል ሲባል አንገቱን በአወንታ የማይነቀንቅ አዛኝ ህዝብ ከፍላጎትህ ፍላጎቷን አሥበልጣለችና በፊትህ ትገረፍ ሲባል ለኔ ጠባሳ እሡ የሚሣቀቅ ምሥኪን ህዝብ ፊት ሥገረፍ ከረምኩ አንድ ግዜ እየወረድኩ አሥር ግዜ ሥሠቀል ከረምኩ ንጉሱ ቴቴ ናት :: ህዝቡ ደግሞ ሠሚር:: ሰሚር የኔ አዛኝ ህዝብ::ምክንያቱም
እሡ ፊት ሆኜ ሥታበሻቅጠኝ ከኔ በላይ ሲሳቀቅ አይቻለሁና ::
ምንም እንኳን ፍቅርና እንክብካቤው ባይቀንሥብኝም አሁን አሁን ሰሚር እየደከመው ያለ ይመሥለኛል ተሥፋ የመቁረጥ አይነት ሥሜት ይታይበታል :: ከእሡ ቡሀላ ያገቡ እህት ወንድሞቹ ሁሉ ከአንድም ሁለት ልጅ ወልደው ቤታቸውን ማድመቃቸውን እያየ ቅናት ሣይሠማው አልቀረም አልፈርድበትም :: ምክንያቱም ሠሚር ሠው ነው የሠው ልጅ ደግሞ ዘሩን እንደመቀጠል በሥሙ የሚጠራ ልጅ እንደመውለድ በምን ይደሠታል??? በምንም:: ለነገሩ እኛ ሠዎች ሥንባል ካገኘናቸው አያሌ ውድ ነገሮች በሙሉ ያጣናቸው ጥቂት ርካሽ ነገሮች ዋጋቸው ይገዝፍብናል:: ሥለዚህ እኔ አሁንም ተሥፋ አልቆረጥኩም ተስፋ የምቆርጥበት አማራጭም የለኝም::
እነሆ ከዛ ሁሉ የአመታት ያህል ከረዘሙብኝ ቀናት ቡሃላ ዛሬ ቴቴ ወደቤቷ ለመሄድ ተነሥታለች በር ላይ ቆሜ መከራዬን በአይኔ እየሸኘኋት ነው:: አንዳች እቃ እንደረሣች አሥመሥላ ወደቆምኩበት በር ተጠጋች:: ወደጆሮዬ ተጠግታም
" ስለጉልበትሽ አምላክ ልጁን አትግደይው!!"
ብላኝ ቤቱን ለቃ ወጣች :: ከውሥጤ ግን ልትወጣ አልቻለችም::: እውነትም እኔ ሠሚርን እየገደልኩት ይሆን እንዴ?? ሥል አሠብኩ ሠሚርኮ ለኔ ህይወትን ያሣየኝ መኖር ያሥለመደኝ ከጨለማ መሃል የጎተተኝ ልዑክ ነው :: ታድያ እንዴት እገድለዋለሁ,?? እኔ ጨካኝ ነኝ??ራስወዳድ ነኝ???
"ዛሬ ቴቴን መሥማት አለብኝ ሠሚር ዘሩ መቀጠል አለበት በራሥ ወዳድነት ሠሚርን ለብቻዬ ለማድረግ በማሠቤ እየጎዳሁት ነው ከባሠም ቴቴ ባለችው ቃል እየገደልኩት? አዳኜን አልገድልም ።ሰሚር ሁለተኛ ሚስት ማግባት ፍላጎት እንደሌለው ባውቅም እንደምንም ማሣመን ይኖርብኛል :: ሠሚር ማግባት አለበት!!! ውሥጤን አፍኜ ውስጡን ግልፅ ላውጣ :: ባሌን መዳር አለብኝ :: ሥል ወሠንኩ

ይቀጥላል
For comment @ketibebot
JOIN ⇒ https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fdgq4y96u_wIQ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
👍1🔥1
💬Du’a for:
🔆Ability to do Good Deeds
📍Leaving Bad Deeds
🔆Loving the Needy
📍Forgiveness
🔆Mercy
📍Safety from Trials
🔆Love of Allah ﷻ

Ameen
@ketibeb
◇∙∙∙∙∙∙∙∙⊙⊙∙∙∙∙∙∙∙∙◇