ኬልቅያስ
392 subscribers
303 photos
4 videos
69 files
43 links
ኬልቅያስ የቴሌ ግራም ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የነፍስ ማዕዶችን የሕይወት ቃል ወንጌለ መንግሥት የምስል ( vidio ) ትምህርቶች ፣ ያሬዳዊ መዝሙራትን ፣ የቅዱሳን ዜና ሕይወት ፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ የአብያተ ክርስቲያናት እና የገዳማት ታሪክ ፣ የአባቶች ምክር ፣ የጠቢባን የአባቶች አባባል ፣ መንፈሳዊ ጥቅሶች እና ኪነ - ጥበባዊ ልዩ ልዩ አውዶች የሚቀርብበት ነው።
Download Telegram
ይሆናል?" አለ ንፍታሌም። "በድንገት እንኳ ፈርዶብህ ከገባህ ከሰውነት ተለውጣ የማታውቃት ሌላ አውሬ አስፈሪ ፍጥረት ነው የምትሆንብህ። የሚገርም ራሄል ቤቷ በጣም እንደሚያምር ልዩ እንደሆነ ስታወራ ሰምቼ ቤቷን ላይ በጣም ነው የምጓጓው። ግን ህልም ነው ወንድ ሆነህ ኢሄ አይሆንም" አለ ክብሮም። ንፍታሌም የበለጠ ተገረመ።

ስለ ሊቁ ልጅ የማያውቃቸውን ብዙ ምስጢሮች ሰማ ንፍታሌም። በተለይም የስዕል ሙያ እንዳላትና አዲስ አበባ ከተማ የአንድ ትልቅ ቤተክርስቲያን የውስጥ ምሥሎች ስራ መስራቷን ሲሰማ የበለጠ ተደነቀባት። ክብሮም ንፍታሌም የሚያውቀውንም የማያውቀውንም ሲነግሩት ሰሚ ስለሆነ ብዙ አወጋው። "ትዳርም ቢሆን አለ የተባለ የአዲስ አበባ ባለሀብት ስመጥር ሰው ጠይቋት እሻፈረኝ ማለቷ ይገርማል። ወንድሞቿም ውጪ ጥሩ ጥሩ ቦታ ናቸው አሉ። እርሷ እዛም መሄድ እንቢ ብላ ነው ይገርምሀል። በጣም ታስደንቅሀለች!" አለ ክብሮም በዝምታ የሚሰማውን ንፍታሌምን እርጋታውን ጥሞናውን በማስተዋል እያደነቀ። "አንተ በደንብ ታወቃታለህ? ማለቴ ትቀራረባላችሁ?" አለው። "አይ የመተዋወቅ ያክል እንጂ እምብዛም አይደል" አለ ንፍታሌም። በዚህ መሀል ራሄል ተመልሳ መጣችና "ማርታም የምትሄድ ይመስለኛል። ደውዬ ልጠይቃት ይሆን?" አለችና ስልኳን ካስቀመጠችበት ወስዳ እየነካካች ተቀመጠች። "ሄሎ ማርቲዬ!" አለች። ሲያወሩ ቆይተው "ሰላም ጋር ለቅሶ ለመድረስ ከነገወዲያ አስበን ነበር አጋጣሚ ሌላ ቤቱን የሚያውቅ ስናገኝ ወደ ነገ ቀኑን ቀየርን። የሚመችሽና የምትሄጂ ከሆነ ብዬ ነው መደወሌ" ብላት ማርታም ሳታቅማማ ተቀብላ ተሰነባበቱ። "ቆይ ግን ሰው አይበዛም ወንበር አያንስም?" አለ ክብሮም ስለሚያሽከረክራት መኪና እያሰበ። "ኤርምያስኮ አይሄድም!" አለችው። "አምስት ሰው ይችላል እንደዛ ከሆነ " አላትና "መጣው!" ብሎ ወጣ። ኢሄ ለንፍታሌም ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት። "ቆይ ቡና ላፍላ!" ብላ ስትነሳ ንፍታሌም እንደሚቸኩል ነግሯት ተቀመጠች። "ራሄል ካላስቸገርኩሽ አንድ ጊዜ አንቺ ጋር ያየኋት ልዩ ምሥል ለአንድ ጥብቅ ጉዳይ ፈልጊያት" ሳይጨርስ "ውይ ሰላም ክፍል ነች። እዚህ እያለች መች ነው ካስቀመጥኩበት አውጥቼያት የኔ ልጅ ይዞ አለቅ ብሎ እንደዚያው ወስዳው እርሷ ቤት ተኝቶ እዚያው ተረሳች። ምነው ለምን ፈልገኻት ነው?" አለችው። "አይ እኔጋ እንደምታውቂው እርሷን የምትመስል ሌላ ምሥል አለችና ከኋላ የተጻፉ ጽሑፎች ግን ልዩነት አሏቸው አንዳንድ ነገር ለማመሳሰልና ለማስተያየት ነበር" ሲላት ተጠራጥራው "ምን ከኋላ ያለው ጽሑፍ ቢመሳሰል ቢለያይ ምን ጥቅም ምን ጉዳት ሊሰጥህ?" አለችው። " እስቲ በደንብ ሌላ ጊዜ በደንብ እናወራበታለን። አንቺም ጋር እኔም ጋር የተገኘችበት መንገድ ምሥጢር ነው" ሲላት "አዎ እርሱማ ልክ ነህ" አለችው። "እና አንዳንድ መረጃ ላይ ለመድረስ...."ብሎ ሀሳቡን ገታ። ሊል የፈለገው ሳይገባት እረሰሷም ተወችውና "ለሁሉም ሰላም ቤት ነው ያለው" አለችው። "በቃ እሺ አመሰግናለው ነገ በጠዋት ብንነሳ ጥሩ ነው እንደዋወላለን" አላት ከተቀመጠበት እየተነሳ። "እሺ ደውልልሀለው ስልክህን ስጠኝ?" "09 22....." ነገራት። "ውይ ልጄ ተነሳ!" ብላ ተፈትልካ ወደ ውስጥ ገባችና ወዲያው በደረቷ አቅፋው ስትመጣ ንፍታሌም ለመውጣት መራመድ ጀመረ። "ውይ በባዶ አፍ እንዲሁ...!" ስትለው "ኧረ ምንም ችግር የለው" እያለ ከቤት እንደወጣ "ተነሳህንዴ? እኔም ጥዬህ ጠፋው!" አለ ክብሮም። "እንግዲህ ነገ እንገናኛለን!" ብሎት ጨብጦት ወደ ራሄል ሲዞር ሕጻኑን አየውና ደንግጦ ቆሞ ቀረ። ራሄልም በንፍታሌም መደናገጥ የበለጠ ደንግጣ "ምነው ምንድነው?" አለችው። ንፍታሌም ግን ሕጻኑን በዝምታ በድንጋጤ ዓይኑን ማመን አቅቶት ትክ ብሎ አየው!

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ኅዳር 15 2018 ዓ.ም ባሌ ሮቤ 💢
🌄🌅🌌 ህቡዕ ገጽ 🌌🌅🌄

     🌄🌓👤 ህቡዕ ገጽ 👤🌓🌄

   💢💠 ከክፍል 268 የቀጠለ 💠💢

አባ ትህትና ግን እዚያ እንደቆዩ ሁሉ ድካም ከፊታቸወ ሳይታይ  እንግዶቻቸውን ያስታምሙ ገቡ። አቤል ፍርሀቱ ጨመረ። የተስፋዬ እርጋታው ጸጥታው ጨመረ። የከነዓን ደስታው እጥፍ ሆነ። ሌላ ሕይወት ሊጀመር ተስፋዬና አቤል ወደ ገዳሙ ገብተው የመጀመሪያቸውን ምስጋና ሊያቀርቡ ቻሉ። የሚያውቁትን እስኪያውቁ ባወቁት ለመደነቅ ተገደዱ። ሁላቸውም ከድካማቸው ሊያርፉ ወደ ተዘገጃለቻቸው ማረፊያ ደርሰው ጎናቸውን አሳረፉ።

🌄🌓👤 ክፍል 280 👤🌓🌄

ተስፋዬ የነበረበትን ያንን ዓለም ትቶት ብቻ ሳይሆን ጥሎትም የመጣ ለመሆኑ እርጋታው የልቡ ፀጥታ የሀሳቡ መሰብሰብ ማሳያ ነው። ያ ብዙ ፍለጋ ያደከመው ያ በጉዞው ሁሉ የባከነው ብዙ የጣረው ብዙ የባከነው ብዙ የታገለው ብዙ የሳተው ያ ሌላ ፍለጋ ራሱን ያጣው አቤል ከሙሲቾ መልስ የታየበት የባሕሪ ለውጥ ማንነቱን ለሚያውቀው አስደንጋጭ ሆኗል። አቤል ተስፋ የቆረጠ ፍለጋ ያቆመ ይመስላል። ሁሉን የተወው ሁሉን የጠላ ከሁሉ የተጣላ ነው የሚመስለው። ብቻ ፀጥታ ውስጥ ሰጥሟል። አቤልና ተስፋዬ ከመጡበት አዲስ ስፍራ አዲስ ነገር ጠባቂ ናቸው። በቀጣይ ቀን ካረፉበት ሲነቁ አባ ትህትና ያሉበትን ገዳም ጠዋት ሊያስጎበኟቸው ካደሩበት ወደነርሱ መጡና "ሰላም ለናንተ ይሁን ወንድሞቼ!" አሉ እጅ በመንሳት። "አባ ሰላም አደሩ!" አለ ተስፋዬ "እንዴት አደራችሁ?" አሉ አባ "እግዚአብሔር ይመስገን" አለ አቤል። " በሉ የዛሬ ቆይታችሁ ከከነዓን ጋር ይሆናል። ገዳሙን ዘወር ዘወር ብላችሁ ትጎበኙታላችሁ። ምናልባትም ለምትሰነብቱባቸው ቀናት ከእንግዲህ በአንድ ላትሆኑ ትችላላችሁ። ከነዓንም ከነገ ጀምሮ አይገኝ ይሆናል። ዛሬን አንዳንድ ነገር እያሳያችሁ ከእናንተ ጋር ይቆይ" ሲሉ " እሺ አባ!" አለ ተስፋዬ። "ሰላም አደራችሁ!" አለ ከነዓን ቡኒ ፎጣውን አመሳቅሎ ለብሶ ከቤተክርስቲያን የጠዋት የኪዳን ጸሎት ሲመለስ ወደነርሱ ጎራ ብሎ። "መጣህ?" አሉት አባ። "በል እንግዲህ ለእንግዶቹ አንዳንድ ነገሮችን አላምዳቸው! አትለያቸው" አሉትና ተሰናብተው ወጡ። ከነዓን እንደታዘዘው ሁሉ የተጣለበትን አደራ ሊወጣ ተጋ። አቤልና ተስፋዬን ካሉበት ገዳም ማየት ያለባቸውን ማወቅ የሚገባቸውን አብሯቸው ሆኖ ሊያሳውቃቸው ተያይዘው ካሉበት በአት ወጡ። በትልልቅ እድሜ ጠገብ ዛፎች የተሞላው የገዳሙ ይዞታ አንዳች ልዩ ውበት አለው። አስቀድመው እንደወጡ ከነዓን ወደ ቤተክርስቲያኑ ወስዶ አሳይቷቸው ተሳልመው አጭር ጸሎት አድርሰው ወደ ቀጣዩ አመሩ። የገዳሙ ቅጽር ጸጥታው ከጫጫታ ከግርግር ከርሞ ለመጣ አስፈሪ ነው። "ሁሌም ጸጥታው እንዲ ነው?" አለ ተስፋዬ ጮክ ብሎ። ከነዓን ግን ምላሽ የሰጠው በምልክት ነበር። አራት ጣቱን አፉ ላይ በማድረግ ዝም እንዲል አዘዘው በሰው ቁመት ያክል አጥሯ ከፍ ያለች የተከለለች ስፋቷ መጠነኛ ከሆነ ቅጽር ጋር ሲደርሱ። ተስፋዬ በጣም ደነገጠ። አቤልም በግሉ ጥያቄ ሆነበት። "ለምንድነው ዝም ያለው?" አለ በልቡ የታጠረውን ስፍራ በዓይኖቹ ዘወር ብሎ እያየ። በተለይም ትልቅ ሰፊ ዋርካ የተንጣለለ ጥላ ያለበት ይህ ቅጽር ሳሩ ልምላሜው ዓይን ይገዛልና የሁለቱም እንግዶች ልብ በዓይናቸው ምልከታ ተገዛ። ሶስቱም ተከታትለው ቅጽሯን አልፈው እንደራቁ " ቅድም ያለፍንበት የታጠረው አካባቢ ማውራት አይቻልም" አለ ከነዓን ቆም ብሎ። " ከገዳሙ የስውራን ስፍራ አንዱ ነው" ሲላቸው ተስፋዬ ግራ ገባው። አቤል ደግሞ ደነገጠ። " ስውራን ምንድነው?" ተስፋዬ ጠየቀ። ኢሄን ለማስረዳት ከነዓን ብዙ ደከመ። አቤል ግን በዝምታ ገመድ እንደ ተሸበበ ያደምጥ ነበር። ከነዓን ለሚመልሰው ተስፋዬ ሌላ ሲጠይቅ እንዲህ እንዲህ እያሉ ተስፋዬ ስውራን ማለት ምን እንደሆነ ኋላ ሲረዳ በየእርምጃው እየተደነቀ " ይገርማል!" "እውነት ነው ግን?" "ምንድነው የምሰማው!" እያለ በአድናቆት ቅኝታቸው ቀጠለ። ከነዓን ታሪክ እያወሳ ከአንዱ ወደ አንዱ እየወሰደ እያሳያቸው የሽበት ዘውድ የደፉ አረጋዊ አባት በድንገት ሲመጡባቸው ከነዓን ከእሩቅ ተመለከታቸው። ከነጭ ጸጉር በቀር በራሳቸው ላይ ጥቁር ተፈልጎ አይገኝም። የርሱን የመሰለ ፎጣ አገልድመው ለብሰዋል አረጋዊው ሲያዩዋቸው ባሉበት ቆሙ። ከከነዓን ተከትሎ ተስፋዬ ዓይኑን ከርቀት ጣለባቸው። አቤል ግን ሲያያቸው ተሸበበው አንደበቱ በኃይል ተፈታ ባለበት ቆሞ በድንጋጤ እያያቸው "እኔ አላምንም!" አለ። ከነዓንና ተስፋዬ ግራ ገባቸው። " እዚያ ቆመው የሚታዩትን ታውቃቸዋለህ?" አለ አቤል። "አዎ በዚህ ገዳም ትልቅም የተከበሩ የተወደዱ አባት ናቸው" አለ ከነዓን። "ብዙውን ጊዜ....." ብሎ ሊናገር የነበረውን ተወው። አቤል ጓግቶ ሲጠብቅ የከነዓን ጀምሮ ማቆም ምክንያታዊ እንደሆነ ለመረዳት አልቸገረውም። ወደ እርሳቸው ትይዩ የነቀረ ጉዞአቸው በመሪው በከነዓን ምክንያት ወደ ቀኝ በመታጠፍ ሲወስዳቸው "እርሳቸው ባሉበትጋ....." አለና አቤል ነገሩን ተወው። ከዚያች እርሳቸውን ካየበት ቅጽበት ጀምሮ ኅሊናው "ክብ ሩጫ!" እያለ ያቃጭልበት ጀመረ።

ለሰዓታት ሶስቱም በከነዓን መሪነት እየተዟዟሩ ሲጎበኙ ቆይተው ተስፋዬ ደከመኝ በማለቱ ምክንያት ተመልሰው ወደ ማረፊያቸው አቀኑ። ከዚያ እንደደረሱ ከነዓን "መጣው አረፍ በሉ" ብሎ ሲወጣ አቤል "አብሬህ ልሂድ?" አለው በተማጽኖ "በዚህ ድካም ላይ ሌላ ድካም ነው የሚሆንብህ። እኔ ከገዳሙ ውጪ አንድ ቦታ ደረስ ብዬ ልመለስ ነው" አለው ለርሱ በማሰብ። "ግድ የለህም አልደከመኝም። ተስፋዬ እስከዚያው አረፍ ይበል አብረን ደርሰን ብንመጣ" አለ አቤል አንድ የፈለገው ነገር እንዳለ ሁሉ። "ለእኔ ግድ የለም እንሂድ እሺ!" አለውና አቤልና ከነዓን ተያይዘው እያወጉ ሄዱ። በወሬ መሀል "ቅድም ያየናቸውን አባት ሳያቸው በጣም ነው የደነገጥኩት። ቆመው የነበረው ለምንድነው?" አለ አቤል። "እርሳቸው ከርቀት ሰው ወደርሳቸው ሲመጣ ካዩ እንደዚያው ናቸው። ዝም ብለን ወደርሳቸው ብንሄድ እንኳ ይሸሹናል። አያወሩም ይባላል። ያወሯቸው ከምክራቸው ጠበል የጠጡ ሰዎች መድኃኒት ናቸው ይሏቸዋል። ስለ ማንነታቸው እያደነቁ ከማውራት በቀር በትክክል ምንድናቸው? ለሚል ጥያቄ እርሳቸውን በትክክል የሚያብራራ የለም። በጣም በሚደነቅ ስለርሳቸው ከሰማሁት በዚህ ገዳም ውስጥ በአታቸው የት ማደሪያቸው የቱጋ መጠጊያቸው ማንጋ እንደሆነ ማንም አያውቅም። የት እና እንዴት እንደሚኖሩ አይታወቅም አይገርምህም!" አለው። "ከረጅም ዓመታት በፊት በዚህ ምክንያት በገዳሙ ውስጥ ያለ ገዳሙ እውቅና የሚኖር ሰው አለ ተብሎ በርሳቸው ላይ ገዳሙ መክሮ ማንነታቸውን በትክክል ስላላወቀ መናንያኑ ይህን ያለ አድራሻ በዚህ ገዳም የሚኖር ሰው ፍለጋ ብዙ ደክመው በብዙ ፍለጋ ዝለው ቢያጧቸው ሲተዉአቸው ደግሞ ታዩ ተብሎ ከታዩበት አካባቢ ቢታሰስ ቢፈለግ ደግሞ ባይገኙ እንዲህ ባለ እንቆቅልሽ እያሉ አንድ ትልቅ በአታቸውን ዘግተው የሚኖሩ አባት ናቸው "ተዉአቸው!" ቢሉ ነገሩ አጀብ ተብሎ እንደታምር እየተነገረ ነገሩ የተተወው።" አለ ከነዓን በጣም በመገረም ስሜት። አቤል የሚሰማው እንደ እግር እሳት ለበለበው። " ሁሌ መገኛቸው ከዚሁ ገዳም ነው?" ጠየቀው። ሁለት አይነት ነገር ሲነገር ሰማለው። አንዱ ከዚህ እንደማይወጡ ፍጹም ባህታዌ ናቸው የሚል ነገር አለ። አንዳንዶች ግን ከብቃት የደረሱ ስለመሆናቸው የሚናገሩ ከመሆኑ በተጨማሪ
የእግዜርን መልእክት መልእክተኛ ሆነው ሊያደርሱ ወደ ከተማም ጭምር እንደሚወጡና በጎዳና ጭምር ደሀ መስለው ተቀምጠው የሚለምኑ በዚያ ውስጥ መልእክት አድራሽ መሆናቸውን የሚናገሩም አሉ" አለ አቤል የሚያውቀውን በሚገባ አብራርቶለት። "እራሳቸው ናቸው!" አለ በብስጭት አቤል። "ማን?" አለ ደንግጦ ከነዓን። በራሱ እጅግ በማዘን "እውነትም ክብ ሩጫ!" አለ። "የማላውቀው የተፈጠረ ነገር አለ? ምንም አልገባኝም" አለ ከነዓን ግራ ገብቶት። "የኔ ለኔም የሚገባኝ አልነበረም። በስልጣኔ ካብ ባይ ከፍ ብሎ ተቀምጬ ሁሉን ያወኩ ሁሉን የምረዳ ራሴን አድርጌ አስብ ነበር። ለካ የእንቧይ ክምር ኖሯል የተገበዝኩበት። ሁሉንም ራሴን የካብኩበት ሲናድና ስወድቅ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አየሁት። ሳልማር ደጋግሜ እየወደኩ ደጋግሜ እየሳትኩ ደጋግሜ በጸጸት አለንጋ እየተገረፍኩ። መነሻ እና መድረሻ የሌለው ክብ ሩጫ ስሮጥ እንዲሁ ጉም ለመዝገን ስደክም ደመና ልደገፍ ስጥር እኔ እኔን ሳልሆን ለኔ የሆነውንም ሳላውቅ ሳልረዳ እኔ ከኔ ጠፍቼ እኔን ሳላገኘሁ እኔን ሳልሆን አለሁ!" አለ ያ ሲጸጸት እንደ ዥረት የሚወርደው እንባው ምንጩ እንደ አለት ደርቆ በጋ ሆኖ። ንግግሩ አንጀት ይበላል። ከነዓን በጣም አዘነለትና ትናንቱን ተረከለት። የከነዓንን ትናንት ሲሰማ ተጽናና ዛሬውን አይቶ። "ከእንግዲህ ምንም ማወቅ ከእንግዲህ ምንም መስማት አይደለም ፍላጎቴ ከእንግዲህ የሚቀድመውን አስቀድሜ በራሴ ውስጥ የጠፋውን እኔን ፈልጎ ማግኘት ነው ፍላጎቴ። ስንቴ ወደኩ መሰለህ! እንዴት ሰው በአንድ ፈተና እርሱኑ ጥያቄ ደጋግሞ ይስታል። አሁን ቅርብ ጊዜ እንኳን ከአንድ ምሥጢራዊ ስፍራ ለማየት ለመስማት እኔን ሳልሆን እኔን ሳላገኝ ተገኝቼ ባዶዬን አጨብጭቤ ከበረቱት ጋር መንገድ ጀምሬ ደክሜ በባዶዬ ተመለስኩ። የሚገርምህ ጉዞውን አለማቆሜ ነው። ኢኸው እየሄድኩ ነው አንተም አሁን ያገኘኸኝ። "ማብቂያ የሌለው የኪሳራ ጉዞ" አለ አቤል። "ደግሞኮ ስገበዝ ስተች እንከን ሳወጣ። አይገርምህም በመንገዴ እነ ንፍታሌምን ሁሉ እኮ ነው የተቸውት" አለ በስሜት። ኋላ ከነዓን ንፍታሌምን እንዳያውቀው ገባውና እንደማፈር ብሎ "ይቅርታ አሁን ያልኩ ሰው በከተማ የሚኖር መነኩሴ ታውቃለህ? እንደዛ ነው። ምኑንም እኮ ነው የማታውቀው የማትገምተው" ሲለው "የኔንም ሕይወት ለዚ ያበቃው ምክንያቱ እርሱ ነው" ሲል ከነዓን አቤል ደነገጠና " ማን አቤል?" አለ በመደነቅ። ሁሉን ትተው ደግሞ ስለ ንፍታሌም ማውጋት ያዙ እየተጓዙ።

ከነዓን ንፍታሌምን ያወቀበትን አጋጣሚ ነገረው። ኋላ ሁሉን ትቶ ለዚህ ሕይወት የበቃበትን ጨምሮ ሲነግረው አቤል ያገኛቸውን ሁሉ ብኩን ሆኖ እንዳሳለፈ የበለጠ ወገግ ብሎ ታየው። "ና በዚያ አይደለም። በዚህ ነው የምንሄደው!" አለው ከነዓን ወደ ዋናው በር መውጫ ከሚወስደው መንገድ በስተግራ በኩል ባለው እያመለከተው። " በዚህ በኋላ ቅርብ ነው" አለውና በዚያ አቀኑ። "ንፍታሌም መድረክ ላይ ቆሞ ሲያስተምር ካገኘሁት በላይ ሕይወቴን የቀየረው እንደመድረኩ ሁሉ እንዲያውም በበለጠ በተለየ ስሜት በደስታ ተሞልቶ ብቻዬን በሚያስተምረኝ እና ሆኖ ባየሁት በተግባሩ ጭምር ነው። አንዳንዴ እየሰማውት እኔን ከኔ ለይቶ በእንባው መርከብ ጭኖኝ ከሚተርክልኝ ታሪክ ጋር ደርሶ ያወርደኛል። እርሱ ሲያስተምርህ መስማት ብቻ አይደለም ማየት ትችላለህ። ታውቃለህ ሁሌ አልረሳም "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ይለኛል....." ታላቅ እምነት። ይሄን ደግሞ በሕይወቱ በሆነው ያረጋግጥልሀል ታሪክ ተርኮ። አንድ ጊዜ የሆነውን እንዲህ ነገረኝ" አለ ከነዓን መልሶ ሊተርክለት ታሪኩን በደንብ እያስታወሰ። አቤል ለመስማት ጓጓ። ሁለቱም ሳይታወቃቸው የገዳሙን ይዞታ ጨረሱ። ከገዳሙ ይዞታ ተያይዞ ካለው ደን ውስጥ ሲደርሱ መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች "ነብር ነብር ነብር!" እያሉ እየተጯጯሁ ሲመጡባቸው አቤል የሚገባበት ጠፋው። ከነዓን ግን "መን አለኝ መሰለህ?" ብሎ ታሪኩን ሊነግረው ሲዞር የአቤል ነፍስ በጣር ውስጥ ሆና አየውና "ምነው አይዞህ ለነብሩ ከሆነ የገዳማችን ዘብ ነው አይነካንም" አለው። ያኔ እየተጯጯሁ የመጡት ልጆች አጠገባቸው ሲደርሱ ገና ከነዓንን ሲያዩት በረጅሙ እየተነፈሱ "አባ ጠባቂው መጣብን ጠባቂው መጣብን" አሉትና እየሸሹ ወደመጡበት ከሚሄዱት ከከነዓንና ከአቤል ጋር ፍርሀታቸው ሁሉ ለቋቸው ሲጓዙ አቤል ቲኒሽ ተረጋጋ። ቲኒሽ እንደተጓዙ "ያው ያው እዛጋ ዛፉ ስር" አለ አንዱ ከእረኞቹ። አቤል ወደተባለው አቅጣጫ ቢያማትር ምንም አጣ። ከነዓን ወዳሳዩት ያማትር ጀመር። እንደዋዛ ወደተባለው ዛፍ ሲቀርቡ ሰባቱም ነብሩን አዩት ነብሩም አያቸው። እየቀረቡት ሲመጡ መጠኑ እየጨመረ እያደገ እየተነፋፋ መጣ። አቤል እግሮቹ እየደከሙ ልቡ ምቷ እየጨመረ መጣና ወደ ከነዓን ሲመለከት አፉ ሲንቀሳቀስ ሲያነበንብ አየው። ወዲያው ነብሩ መጠኑ እየቀነሰ እያነሰ መጥቶ ዞሮ እንኳን ሳያያቸው ወደ አንዲት ቁጥቋጦ ሲገባ ታየ። "ይገርምሀል ተአምረኛ ፍጡር ነው። በዚህ አካባቢ ሃይማኖተኛ የሆነች ትሁት ሴት ነበረች ባለቤቷ ግን እጅ ክፉ ነው። ይቺን ሴት በብዙ ያንገላታታል። በዚህ ድርጊቱ ተማራ አንድ ቀን በሌሊት ወንድ እንኳ የማያደርገውን ከቤቷ ወጥታ በዚህ ጫካ ውስጥ አቋርጣ ለመጥፋት እየሄደች እርሷ ከወጣች ከደቂቃዎች በኋላ ባሏ ተከታትሏት ሊገድላት ከዚህ ጫካ ይደርስና በድቅድቅ ጨለማ ማንም በሌለበት ሚስቱን በጭካኔ በያዘው ስለት ወግቶ ሊገላት ደርሶባት አንቆ ሲያዛት ጉደኛው ደረሰልሀ!" አለ ከነዓን። "ማነው?" አለ አቤል። "ነብሩ ነዋ!" አለ ወደ ቁጥቋጦው እየዞረ። "ዘሎ ተከመረበት ሰውዬው ወደቀ...."

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ኅዳር 29 2018 ዓ.ም ባሌ ሮቤ 💢
🌄🌅🌌 ህቡዕ ገጽ 🌌🌅🌄

     🌄🌓👤 ህቡዕ ገጽ 👤🌓🌄

   💢💠 ከክፍል 279የቀጠለ 💠💢

"እሺ ደውልልሀለው ስልክህን ስጠኝ?" "09 22....." ነገራት። "ውይ ልጄ ተነሳ!" ብላ ተፈትልካ ወደ ውስጥ ገባችና ወዲያው በደረቷ አቅፋው ስትመጣ ንፍታሌም ለመውጣት መራመድ ጀመረ። "ውይ በባዶ አፍ እንዲሁ...!" ስትለው "ኧረ ምንም ችግር የለው" እያለ ከቤት እንደወጣ "ተነሳህንዴ? እኔም ጥዬህ ጠፋው!" አለ ክብሮም። "እንግዲህ ነገ እንገናኛለን!" ብሎት ጨብጦት ወደ ራሄል ሲዞር ሕጻኑን አየውና ደንግጦ ቆሞ ቀረ። ራሄልም በንፍታሌም መደናገጥ የበለጠ ደንግጣ "ምነው ምንድነው?" አለችው። ንፍታሌም ግን ሕጻኑን በዝምታ በድንጋጤ ዓይኑን ማመን አቅቶት ትክ ብሎ አየው!

🌄🌓👤 ክፍል 281 👤🌓🌄

ዓይኑን ተጠራጠረ ማመን አቃተው። ንፍታሌም ዓይኖቹ ንፍታሌም ላይ ተተክለው ቀሩ። "ቤቢን ወደኸዋል አይደል? ለነገሩ ሞክሼክ አይደል?" አለ ክብሮም ግራ መጋባቱን በፈገግታ ውስጥ ደብቆ። ንፍታሌም ወዲያው እንዳስደነገጣቸው ሲገባው ድንጋጤውን ዋጥ አድርጎ እጆቹን ወደ ሕጻኑ እየሰደደ " ስሙ ንፍታሌም ነው?" አለ። ራሄል አንዳች ነገር እንዳለ ገብቷታል። "ማነው ንፍታሌም ብሎ ያወጣለት?" አላት በጠቋሚ ጣቱ ያንን ድንቡሽቡሽ ሕጻን ጉንጩን ነካ ነካ አድርጎ እየፈገገ። "ሰላም ነች ከንፍታሌም በቀር ብላ...." አለች ራሄል ሳትፈልግ ተገዳ ስሙን እንደተቀበለች ሁሉ። "ሰላምን ትርጉሙን ጠይቂያት አሸናፊ ማሸነፊያ ማለት ነው ብላኛለች። በጣም ተወዳጅ ስም ነው!" አለ ክብሮም። ንፍታሌም በፈገግታ ውስጥ ድንጋጤውን ሰውሮ እያጫወተው ከዚህ ሕጻን ጋር የተገናኙበትን ያልተዘመረላት ምሥጢረኛዋ ባሌ ከምሥጢሯ እልፍኝ አገናኝታቸው ንፍታሌምን በምን ሁኔታ እንዴት እንዳየው የኋሊት በትዝታ ተስቦ ተመለከተው። በዚያ የጠቢባን መንደር በጠቢቡ የኔታ አመሀ እየተመራ በማያውቀው መንገድ ወደማያውቀው እልፍኝ የተወሰደው ንፍታሌም "ሕጻኑንስ ማነው እዚያ ያመጣው? ከማን ጋር? እንዴት?" ራሱን ጠየቀ። መልስ የለም። የውስጡን ጥያቄ ምላሽ ፍለጋ ወደ ውጪ አወጣው። ከሕጻኑ ጋር የተገናኙበትን ጊዜ አስታውሶ ወሩን ቀኑን ጠቅሶ በዚያ ጊዜ ንፍታሌም የት ነበር ብሎ ሊጠይቅ አሰበና አልመስልህ ስላለው መልሶ ተወው። "በሉ ሰላም ሁኑ!" አለ ንፍታሌም ውስጥ በጥያቄ ላይ ጥያቄ እየተጨመረበት እነርሱን እየተሰናበተ። ራሄል ባለችበት ልጇን እንደያዘች ስትቆም ንፍታሌምና ክብሮም ወደ በሩ አብረው አቀኑ። "በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው!" አለ ንፍታሌም ወደ ክብሮም ዓይኑን አንስቶ። "በጣም እንጂ! የጠፋባት ጊዜ ራሄል ያበደችው እየረሳኝም" አለ ክብሮም የነበረውን ሁኔታ እያስታወሰ። "ጊዜውን በትክክል ታስታውሰዋለህ?" ንፍታሌም ጠየቀው። ክብሮም በአርምሞ ጣቱን በጣቱ እየፈተለ ከንፈሩ ድምጽ ሳያሰማ እየተንቀሳቀሰ ጊዜውን ቆጥሮ ሰፍሮ ነገረው። ንፍታሌም ከመጀመሪያው በላይ ደነገጠና "በጣም ነው የሚገርመው! ቆይ ግን እንዴት? ለማመን የሚከብድ ነው!" አለ ንፍታሌም እውነቱን ሲያውቅ። በሕጻንነቱ ከምሥጢራዊው ደጅ ለመገኘት በታደለው ሕጻን እየተደነቀ። ክብሮምም "የልጁ ምኑ ነው የማይገርመው ብለህ ነው? ራሄል ጠፍቶ ካገኘችው በኋላ የምታይበት ልዩ በሀሪ እንዳለና አንዳንዴ ፍጹም ባልጠበቀችው ሁኔታ ድንገት ስትደነቅበት ነው የምትታየው። ብዙውን ነገር ግን ምሥጢር አድርጋ ነው የምትይዘው። ብቻ በአጠቃላይ የሕጻኑ ጉዳይ ከአዕምሮ በላይ የሆነ ምሥጢር ነው። የጠፋ ጊዜ እንኳን በዚህ ቤት የተስተናገደ የማይፈታ እንቆቅልሽ ስንት አልፏል መሰለህ" አለ ክብሮም እያወራለት ከጊቢ ወተው ደጅ ቆመው ቆይተው። "በል ሂድ አላቁምህ!" አለውና ተሰናብቶት ገባ።

ንፍታሌም በልቡ በጥያቄ ላይ ጥያቄ በመደነቅ ላይ መደነቅ ሲጨመርበት እንደ እብድ ብቻውን እያወጋ ብቻውን እያወራ መንገዱን ቀጠለ። "ቆይ ይሄ ሁሉ እንዴት?" ፈገግ ይላል። "እሺ የስሙ አጋጣሚ ነው ይባል። ሁለታችንም ጋር የምትገኘው ምሥጢራዊት ስምስልስ?" አለ። 💢"ህቡዕ ገጽ"💢 💢"ኅቡዕ ገጽ"💢 የሚለው የኋላው ቀናት መልስ ያልተገኘለት የየእለት ጥያቄው ጭራሽ አገረሸበት። "ምስሏን ከየት አንዴት ነው ያገኘው?" ጥያቄ ሆነበት። ያገኘው ግን የጥያቄውን መልስ ሳይሆን እርሱ ምሥጢራዊዋን ምስል እጁ የገባበትን አጋጣሚ የራሱን አስታወሰ። "ለርሱም ያ እብድ ነው? እንዴት ይሆናል? የት በምን አግኝቶት? ለእናትዬውስ ቢሆን እንዴት ሊሰጣት ይችላል?" ንፍታሌም መልስ ሳያገኝ ጥያቄ አበዛ። "እዚያ ምሥጢራዊ የጥበብ እልፍኝ ድረስስ ማነው ያመጣው? ከእናቱ ሰርቆ እዚያ ሊወስደው የሚችለው ማነው?" ንፍታሌም ሳይታክት ራሱን ጠየቀ። መልስ ስለሌለ ግን ቅር ተሰኝቶ ፊቱ ዳመነ። በድንገት ግን የመጨረሻውን ጥያቄ ለማግኘት ሕጻኑ ንፍታሌም በጠፋበት ጊዜ የተፈጠሩ ነገሮችን መመርመር ወደ አንድ አቅጣጫ ከአንድ ምሥጢር ጋር እንደሚያደርሰው አሰበ። ለዚህም በተለያየ መንገዱን መልስ ፍለጋ ለሚያደርገው የርቀት ጉዞ ከፊቱ ያለው ወደ አዋሽ ቆላቲ ከነራሄል ጋር ሕጻኑ ንፍታሌምም ባለበት የራሄል ወዳጇ ምሥጢረኛዋ የልብ ጓደኛዋ ማርታ ጓደኛው ዶ/ር ቢኒያም እና ክብሮም ሆነው ወደ ሰላም የሚያደርጉት ጉዞ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ተሰማውና ኅሊናው ለነገሩ ተነቃቃ። በአዋሽ ለሚኖረው ቆይታም ከማን ጋር ምን ማድረግ ማንን ምን መጠየቅ እንዳለበት እና ጊዜውን እንዴት እንዲጠቀም በአዕምሮው ያመላልስ ጀመረ። እንደገና ኢሄን እያሰበ ደግሞ ትልቁ ጥያቄ ቋጥኝ አክሎ በላዩ ወደቀበት። "ቆይ ግን ያ ለቀናት የሰነበትኩበት ያ የልሂቃን ጓዳ ያ የጠቢባን ደጅ ያ የቅዱሳን ቦታ ያ የፍልስፍና የመራቀቅ ያ ጸጥታ ስፍራ ግን የት ነው? እውነት ግን ባሌ ነው? እውነት ግን ኢትዮጵያ ነው?" አለ በጥያቄ ጀምሮ ሀገሩን ሲያስታውስ እንደ ሁል ጊዜው ውዳሴ ኢትዮጵያ ሊያደርስ። "እንዴት ያለች ምሥጢር ነች ሀገሬ?" ብሎ ጀመረ። "ደሀ ነች ስትባል ባለጠግነቷን ደብቃ ሸሽጋ የያዘች። ኋላ ቀር ነች ሲሏት መጥቃ ከስመጥሮቹ ዘመናትን ቀድማ ከማይደርሱባት ደርሳ የተሰወረች? ደስታን በልቧ ጥበብን በእልፍኟ ይዛ እውቀት ያጠፋቸውን የነጮች መሰይጠን የሚናፍቁ ልጆቿን አዝላ የያዘች። የበረከት ምንጭ ሆና የረሀብ ስም የተቀጸለላት። ምንም የላትም ስትባል ያሌላት የሌለ። መታየትን አልታይ ብላ ሳትታይ የምትታይ ኢትዮጵያዬ እንዴት ምሥጢር ነች። ልጅ አይውጣልሽ ተብላ እርግማን አለባት ሲሏት ጀግና ወልዳ ጠቢብ ወልዳ ወደዋት እርሷን ሲሉ እርሷን መስለው እንደርሷ ወላለመታየት የደረሱትን ሸሽጋ የያዘች። ለርሷ ብለው እርሷን ብለው ራሳቸውን የተዉ ያፈራች በነርሱ የተከበረች በነርሱ የተፈራች ፈረሰች ሲባል ጸንታ ያለች የማይደረስባት ሀገሬ እንዴት ነች። ወደቀች ሲባል ከልዕልናዋ ርቀት ያልተደረሰባት ጥያቄ የሆነች ሀገሬ ኢትዮጵያዬ እንዴት ልዩ ነች! ድርሳነ ኢትዮጵያ ውዳሴ ኢትዮጵያ መወድሰ ሀገር ማንም በማይሰማበት አንድ ሰው ብቻውን ለብቻው ኢትዮጵያን መስሎ እርሷን አህሎ እርሷን ብሎ እየተቀኘ በርሷ ይራመዳል ንፍታሌም መዝሙሩ መወድሱ የበለጠ ሀገሩን አስናፈቀው። "ግን መቼ ነው የማገኝሽ?" አለ ተከፍቶ ባእድ ሀገር ያለ ይመስል። "መቼ ነው የምትመጪው ጦቢያዬ?" አለ እርሷ ብቻ እንድትሰማው ለርሷ በለሆሳስ። "የማላውቅሽ ባሌስ መቼ ነው የማውቅሽ?" ጠየቀ። እያወራ እንዳወራ ቤት ደረሰ።
ንፍታሌም ስለ ደረጀ እና ከነበረችበት ሕይወት ወጥታ አዲስ ሕይወት ልትጀምር መንገድ አገናኝቷቸው በርሱ አማካኝነት ካገኘቻቸው ካህን ንሰሐዋን ተቀብላ ሌላ አዲስ መንገድ ስለጀመረችው ስለሁለቱም ሁሉ ሊያወራቸው ስለሚገባ እቤት ገብቶ ከእናቱ ጋር ተገናኝቶ በተለይም ትእግስትን እናቱን ስትረዳቸው በመመልከቱ ደስ ብሎት ጥቂት ቆይቶ ወደ ሮቤ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አቀና። ንፍታሌም ለቅዱስ ሚካኤል ልዩ ፍቅር አለው። ደርሶ ከቤተክርስቲያኑ ቅጽር ከጥላው አርፎ የቀጠራቸውን አባት ይጠብቃቸው ጀመረ። ጥቂት አረፍ እንዳለ በዚያ በመቃብር ቤት በራቸውን ዘግተው የሚኖሩ ጸሎተኛ እናት ትዝ ቢሉት ወደርሳቸው አቀና። ንፍታሌም ወደርሳቸው ማቅናቱ እንዲሁ አልነበረም። ቀኑ ሥላሴ ስለነበር እርሳቸው በየወሩ ሳያስታጉሉ ከሚዘክሩት ዝክራቸው ሊካፈል ወደርሳቸው አመራ። እኚህን እናት ብዙ አውርቷቸው ብዙ ተደንቆባቸው ብዙ አድንቆአቸው አይጠግብም። የሃይማኖታቸው ጥንካሬ የእምነታቸው ጥግ ልዩ ነው ሁሌ የደመምባቸዋል። ዝክሩን እንኳ የሚዘክሩት በደብሩ የሚያውቋቸው ዝግ በራቸውን አንኳክተው ከሚመጸውቷቸው ደረቅ ዳባ ሲሆንላቸውም ገንዘብ ካላቸው ዳቦ ልጆች ልከው ያስገዙና እርሷኑ ቆራርሰው በደከመ አቅማቸው እሳት አያይዘው ሻይ አፍልተው ድንገት የመጣውን ሁሉ "የሥላሴ እንግዳ ኖት ይዘከሩ" እያሉ ከዝክራቸው ያቀምሳሉ። ለአምላካቸው ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው። ከፍጹም ፍቅራቸው የተነሳ የሞተላቸውን በጸሎት ሊያወሩት ካላቸው ጉጉት ሁሌ የጸሎት መጽሐፍ ይዘው ማንበብ ባይችሉ እንኳ "የልቤን አይቶ..." እያሉ በመታመን ቆይተው በዚህ ትጋታቸው ማንበብን ታድለው ሳይማሩ ማንበብ ችለው የሚናፍቁትን ጸሎት ማድረስ እንደቻሉ ለንፍታሌም የነገሩት እንዲሁ እንደ ዛሬው ሁሉ በዝክራቸው ተገኝቶ ብቻቸውን ሲያወጉ ነበር ይህን የሰማው። ንፍታሌምን ስሙን መጥራት ስለሚከብዳቸው "እንግዳው!" ይሉታል። "የዛሬ ወር ምነው ቀረህ?" ይሉታል አልመጣ እንደሆነ። አንድ አዲስ ነገር ለመስማት አልያም በመምሬ አድባር ዛፍ ስር ለአብርሃም የተገለጠ ሥላሴ በዝክራቸው እንዲገኝ በማመን በረከት ናፍቆ ካለ አይቀርም። ሲደርስ እኚያ እናት እንደ ተለመደው ከጊዜ ርዝመት የጠቆረ ማንደጃቸው ላይ ስንጥርጣሪ እንጨት ደርድረው እሳት ለማያያዝ በአንድ እጃቸው ክብሪት ጭረው በአንድ እጃቸው የያዙት አሮጌ ፔስታል ላይ ለኩሰው እንጨቱ ላይ ቅላጩን ሲያንጠባጥቡ ቦግ ብሎ ነዶ እሳቱ እጃቸውና ፔስታሉ ጋር ደርሶ ቅላጩ እጃቸውን ክፉኛ አቃጥሎት የርሱን ህመም እያስታመሙ ንፍታሌም ደረሰ። ደነገጠ። ሰላም እንኳ ሳይላቸው "ምን ሆነው ነው እሳት ነው?" አላቸው። "ምን አውቄ እንግዳው ምን እንደበደልኩ። አሳቱ ተጣላኝ" አሉት። "ጂቢ ገዝቼ ልምጣ ይሆን?" ሲላቸው "አለ እዚው እኔ ቤት ዙሪያ አለ። በል ፈጥነህ የሸረሪት ድር አብዝተህ አምጣልኝ አሉትና ከቤታቸው ግድግዳ ከመቃብር ቤቱ ላይ እንዳዘዙት አመጣላቸው። ያንን የሸረሪት ድር የተቃጠለ እጃቸው ላይ ደመደሙትና ወደ ስራቸው ሲመለሱ "ይተውት እኔ ነኝ ዛሬ ሻዩን የማፈላው" አላቸው። "የዛሬው ለሁለት የምንዘክረው ይሆናል ይሁን እሺ" አሉትና ንፍታሌም ሻዩን አፍልቶ እርሳቸውም የእለቱን ጻድቅ አቅርበው ቄሱ ከእማሆይ ደጅ ላይ ጥላው ስር ንፍታሌምን ከእሩቅ ሲያዩት ወደርሱ መጡ። "በል ጣዲቁን ባርክና ቆራርሰ ስጠን" አሉት። "ቆይ የሚባርክ ሰው እየመጣ ነው" አላቸው። "የመጨረሻውን የሥላሴን ዝክር ከአንተ ለመዘከር ለዚህ ያበቃኝ የእምዬ ማርያም ልጇ የተመሰገነ ይሁን" አሉት። ንፍታሌም ባይገባው ብዙ ሳይጨነቅ ነገሩን ተወው። ቄሱ ደርሰው "ሰላም ዋላችሁ!"አሉና ቀድመው ንፍታሌም ኋላ እርሳቸውን አሳልመው ዝክሩ ተዘክሮ ንፍታሌምና ቄሱ ስለተገናኙበት ተነጋግረው እማሆይን ሲሰናበቷቸው "እንግዳው!" አሉ ንፍታሌምን ጮክ ብለው። ንፍታሌም መለስ ብሎ "ፈለጉኝ እንዴ?" አላቸው። "እንግዳው ባታውቀውም እንግዲ የሥላሴን ዘክረናል የእመቤቴንም የመጨረሻውን አብረን ስለምንዘክር እንዳትቀርብኝ!" አሉት። "የመጨረሻ?" አላቸው ግራ ገብቶት። "አዎ ሰው ሞቱን ተሸክሞ ዟሪ ነው!" አሉት። "አመሞት እንዴ?" አላቸው። "ኧረ የለም አላመመኝም!" አሉት። "ይሁን እንደዛ ከሆነ እመጣለው ሰላም ያድርሰን!" አላቸውና ተሰናብቶ ሄደ። ኋላ ዋናውን ጉዳይ ጨርሶ ወደ ቤቱ አቀና።

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ታኅሳስ 1 2018 ዓ.ም ባሌ ሮቤ 💢
🌄🌅🌌 ህቡዕ ገጽ 🌌🌅🌄

     🌄🌓👤 ህቡዕ ገጽ 👤🌓🌄

   💢💠 ከክፍል 280 የቀጠለ 💠💢

በዚህ ድርጊቱ ተማራ አንድ ቀን በሌሊት ወንድ እንኳ የማያደርገውን ከቤቷ ወጥታ በዚህ ጫካ ውስጥ አቋርጣ ለመጥፋት እየሄደች እርሷ ከወጣች ከደቂቃዎች በኋላ ባሏ ተከታትሏት ሊገድላት ከዚህ ጫካ ይደርስና በድቅድቅ ጨለማ ማንም በሌለበት ሚስቱን በጭካኔ በያዘው ስለት ወግቶ ሊገላት ደርሶባት አንቆ ሲያዛት ጉደኛው ደረሰልሀ!" አለ ከነዓን። "ማነው?" አለ አቤል። "ነብሩ ነዋ!" አለ ወደ ቁጥቋጦው እየዞረ። "ዘሎ ተከመረበት ሰውዬው ወደቀ...."

  🌄🌓👤 ክፍል 282 👤🌓🌄

"ዘሎ ተከመረበት ሰውዬው ወደቀ" አለ ከነዓን በቦታው እንደነበረ በዓይኑ በብረቱ እንዳየ ሁላ ስሜቱን ተረድቶት ወደ ሚተርክለት ሰው ስሜቱን እያስተጋባ። አቤል ቀጥሎ የሚሰማውን ለማወቅ ጓጓ። ከነዓን እርምጃውን አቁሞ ነብሩ ወደ ገባበት ቁጥቋጦ ትክ ብሎ እያየ በዝምታ ተዋጠ። አቤል መጠበቅ አልቻለም። "ከዚያስ ምን ተፈጠረ?" አለውና ተራኪውን ትቶት ከሄደበት የሃሳብ የርቀት መንገድ መለሰው። " ከዚያ በኋላ ያለውን ስሰማ ያን እለት አለቀስኩ። ሰው መሆንን አየሁበት። ራሴን መዘንኩበት" አለ ከነዓን ታሪኩን ከመቀጠል ይልቅ የታሪኩን አጓጊነት ለመስማት የባሰ ሲጨምርበት። "ልስማው?" አለ አቤል። " በወደቀው ሰው ላይ ነብሩ እንደተከመረ መልእክተኛውን ልኮ የታደጋት ኢትዮጵያዊት ሃይማኖተኛ ሴት "አምላኬ ሆይ አይሁንበት አታድርግበት። ጻድቁ አባቴ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ድረስልኝ። ልብ ስጠውና ሰው አድርገው እንጂ አይሁንበት" እያለች ፍቅርን ተርጉማ አሳየች። ያኔ ነው መልእክተኛው ከሰውዬው ላይ ወርዶ ሰውዬው በድንጋጤ በድን ሆኖ ፈዞ እንዳለ ጥሎት የሄደው። " ተመስገን የገብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክ። ተመስገን ጌታዬ። ስንተውህ ያልተውከን ስንሸሽህ የተከተልከን ከምሕረት እጆችህ ቸርነትህን ልንቀበል ያበቃኸን ተመስገን። የኔን የበደለኛዋን ልመና ቸል ያላልክ ተመስገን" ብላ ባለቤቷን ከወደቀበት አንስታው እርሷን አልማ የወጣችበትን መንገዷን እርሱም አቅዶ የወጣውን ክፋቱን ትተው በፍቅር ወደ ቤታቸው ተመለሱ። አሁን ድረስ በአካባቢው ሰው የተወደደ የገብረመንፈስ ቅዱስን ዝክር ሳያቋርጥ የሚዘክር ምሳሌ ሰው ሆኖ ከትዳር አጋሩ ጋር በፍቅር ይኖራል" አለ ከነዓን። "አቤል አየህ ሰው በሃይማኖት ተሰርቶ በፍቅር ሲኖር ነው ሰው የሚሆነው" ሲለው ቃሉ ዘልቆ የልቡን ደጅ ሲያንኳኳበት አቤል "እስቱእስቲ አሁን ያልከውን ድገመው" አለው። ከነዓን ፈገግ ብሎ ደገመለት። "ሰው የሚሰራው በሃይማኖት የሚኖረው በፍቅር መሆን አለበት" አለው። "ያቺን ሴት ተመልከት። ሊገድላት ያነቃትን ባሏን በሃይማኖት ብትሰራ ነው ይቅርታን ታጥቃ በፍቅር አሸብርቃ በዚያ ጨለማ ለአምላኳ የታየችው መልስ ያገኘችው ለባሏ የተረፈችው" አለ ከነዓን በታላቅ መደነቅ። "ከዚያ ጊዜ በፊት በዚህ ገዳም የሚታወቅ ይህ ነብር ከዚያ ጊዜ በኋላ የበለጠ ስሙ ናኘ። ሌላም ብዙ የሚነገርለት ታሪክ አለ። መልእክተኛ ጠባቂም ነው።" አለ ከነዓን። ሁለቱም እንዲህ እንዲህ እያሉ የቆዩበትን ድንቅ ተአምር አውግተው ከቆሙበት ወደ ሚሄዱበት ጉዞ ቀጠሉ።

አቤልና ከነዓን አብረው እያወጉ ከገዳሙ አቅራቢያ ወዳለው ከነዓን ለመልእክት ወደሚሄድበት ደረሱና አቤል ከደጅ ቆይቶ ከነዓን ወባሕርዛፍ ቅጠል ዙሪያው ወደተከለለው ጊቢ ገባ። አቤል አካባቢውን ተፈጥሮውን መልክአምድሩን እየተዟዟረ ሲቃኝ ሲያደንቅ ቆየ። በድንገት ግን አዕምሮው በሚያየው መልክአምድር ውስጥ ሌላ በሕይወት ዘመኑ ካያቸው ሁሉ ያን ያህል የሚያስደንቀው ልዩ ተፈጥሮ ተምሳሌተ ገነት የሆነች ምስጢራዊት ደጅ ኅናው ወደ አዋሽ ቆላቲ የሙሲቾ ተራራ ሰንሰለታማ ተራሮች ወሰደው። የነበረውን ቆይታውን ያገኘውን ያጣውን መንገዱን ያበላሸበትን ጥፋቱን የተማራቸውን ትምህርቶች በሀሳብ ማዕበል እየተማታ በትዝታ የኋሊት ቃኛቸው። በሀሳቡ ከሙሲቾ ቀጥሎ ትልቅ ተራራው ንፍታሌም ሆነበት። ገዝፎ ታየው ደምቆ ታየው። ግና እንደ ሙሲቾ ተራራ እርሱም ምስጢር ሆነበትና "የማይገመት ሰው ነው!" አለ በልቡ ለራሱ። ቀጥሎ በአዋሽ ቆይታው የሚያውቃቸውን ሁሉ አንድ በአንድ ሲያስታውስ አሁን እዛ መገኘትን አሁን አዛ መሆንን ናፈቀ። ግና ትዝታና ሀሳብ ምናብ እንጂ ወስደው አያደርሱምና አቤል አዚሁ ወደዚሁ ወደ ገሀዱ ተመለሰ። "ተመልሼ ግን ሄድ ይሆን? እርግጥ እግዚአብሔር ከፈቀደ እመለሳለሁ! ስበረታ ሰው ስሆን ያንን ቦታ ንፍታሌምንም ድጋሚ አገኛቸዋለው!" አለ ድምጹን አሰምቶ ብቻውን እያወራ። "ብዙ አቆምኩህ አይደል?" አለ ከነዓን ከኋላው ሳያየው ደርሶ። "በፍጹም አልቆየህም!" አለ አቤል። "እንመለስ እንግዲ!" አለው ከነዓን ወደ ገዳሙ ፊቱን እንዳዞረ። "ድያቆን ነህ አይደል?" አለው ከነዓን አቤልን ድንገተኛ ጥያቄ። አቤል እንደተራ ረብ የለሽ ሰው አይቶ የገመተው ስለቤተክርስቲያን እንኳ ምንም ግንዛቤ እንደሌለው እንዲሁ ብቻ የልማድ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመላለስ ተመላላሽ ቤተክርስቲያንን የማያውቃት አድርጎ የገመተውን ንፍታሌም በአዋሽ ቆላቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መንገድ ቀን አገናኝቷቸው ዲያቆን ጎድሎ ቅዳሴ ሊታጎል በነበረበት ስውር እርሱነቱን ከትህትናው መንጦላይት ውስጥ ወጥቶ ቅዳሴ አሟልቶ ሲቀድስ ባየበት በዚያን ቀን ከመደነቁ ባለፈ እንደርሱ እርሱን መስሎ መኖርን ከመመኘቱ የተነሳ ዲያቆን መሆኑን እንኳ ላይናገር የወሰነ መሆኑን ዘንግቶት "አዎ የስም ዲያቆን" አለ አቤል። "የስም ዲያቆን ማለት ምን ማለት ነው?" አለው ከነዓን። ነገሩን ሊያብራራ ሲያስብ አቤል ለራሱ አለመታመኑ ታወሰውና በራሱ እጅግ አዘነ። "እርሱ ማለት ልክ እንደኔ ለስም ብቻ የሆነበት ነዋ። ይገርምሀል ሁለተኛ ዲያቆን ነኝ እራሱ ብዬ ላልናገር ከቀናት አንድ ቀና አስተምሮኝ አልፎ እኔም ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር። አሁን ዲያቆን ነኝ ካልኩህ በኋላ ነው ያስታወስኩት። ህይወት ሲኖርህ ግን ያ እኔን እንዳስተማረኝ ሰው ተግባራዊ ትሆናለህ" አለ አቤል ንፍታሌምን እያሰበ። "የሚያስተምርማ ከሆነ ልስማው ታሪኩን ንገረኝ!" አለ ከነዓን ቀና ብሎ አቤልን አይቶት። " ምን ገጠመኝ መሰለህ? በሕይወቴ እጅግ በጣም ከደነገጥኩበት ቀን አንዱ ነው። እና አልረሳውም።" አለ አቤል በልቦናው አክናፍ ታሪኩን ለሰሚ ሊተርክ እንድ ወፍ እየበረረ ወደ አዋሽ ተወሰደ። " አሁንም ድረስ ያልገባኝን ምስጢር ሰው አዋሽ ቆላቲ የሄድኩበት አጋጣሚ ከርሱ ጋር አገናኘኝ። ኢሄ ሰው አኗኗሩ ምስጢር ነው። እንዲ ነው ብለህ ልታብራራው አትችልም ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ከሁሉም ጋር ሁሉንም ሆኖ መኖር ያውቅበታል። ይኼ ነገሩ ነው መሰለኝ በስም የምኖረውን እኔን ለርሱ ጥሩ አመለካከት አንዳይኖረኝ ያደረገው። ከርሱጋ ከዚህ ከምልህ ቀን በፊት በተገናኘንባቸው ቀናቶች ሳየው ለነገሮች የማይጨነቅ ችላ ባይ ግድ የሌለው አይነት ሰው እንደሆነ ነው የተረዳሁት። ይገርምሀል እርሱን እንዴት እንዲህ እንዳሰብኩት አላውቅም። አዋሽ ሳላገኘው በፊት ያገኘሁት ጎባ ተክለሃይማኖት ገዳም ነበር። ከአባቶች ጋር ያለው ቅርበት የመዳፈር የትዕቢት መስሎኝ ነበር። ከሌሎች ጋርም ሳየው ደግሞ ልክ እነርሱን መስሎ ስለነበር ጠላሁት። ለየብቻችንም ተገናኝተን ስለማንነቱ ጠየኩት። የነገረኝ ከስም ክርስትና ያላለፈ ሕይወት እንደሌለውና ከማልረሳው "ሰው መሆን ግን እፈልጋለው!" የሚል ንግግር ተናግሮኝ ነበር። ፌዝ
ስለመሰለኝ ጥቂት መከርኩት። ስለቤተክርስቲያን ምን ግንዛቤ እንዳለው ጠየኩት። የነገረኝ የገመትኩትን ነበር። ዲያቆን መስሎኝ ነበር። መልሼ እንዳልሆነ ምንም የቤተክርስቲያን እውቀት እንኳ እንደሌለው ከማየት ብቻ እርግጠኛ ሆንኩ። ይቅርታ አድርግልኝና ጠላውትም። ለሁለተኛ ጊዜ በአዋሽ ሕይወት አገናኘን። ይህን ሰው ቀናት አብረን አሳለፍን። መስማት ያበዛል ዝግ ያለ ነው። ኢሄን እንኳ ለማስተዋል አልቻልኩም ነበር። አንድ ቀን ልዩነቱ ምስጢራዊ ቀንና ሰዓት ደረሰች። ብርቱዎች ስንቅ ሰንቀው ከምስጢር ተካፍለው ምስጢራዊ ጉዞ ለማድረግ የሚዘጋጁባት ቀን። እኔም ያንን ጉዞ ናፋቂ ነበርኩ። ምንም በጊዜው በይሆን እንኳ" አለ ዓይኑን እንባ ሞልቶት። ከገዳሙ ቅጽር እያወሩ ሳያውቁ ስለደረሱ። "እዚች ጥላዋ ስር አርፈን እናውጋ?" አለ ከነዓን። ተስማሙ ከጥላው አርፈው ታሪኩ ቀጠለ። "በአንድ ያለነው ምልምል እጩዎች አራት ነበርን። ከአራታችን አንዱ በሀሳብ ከኔ ጋር የሚመሳሰልና ለዚ ላልኩህ ሰው ተመሳሳይ ምልከታ ነበረን። እንዲያውም እርሱ "ምስጥ ነው ኢሄ!" ይለው ነበር አስታውሳለው። እርሱም እንደኔ ምንም ሃይማኖታዊ ግንዛቤ እንደሌለው ያስብ ነበር። በዚህች እለት ታዲያ ከምስጢር ለመካፈል አራታችንም ብንታጭም ሳንችል የቀረነውም በአንድ በሌሊት ከአንድ ሰማያዊ ሰውጋ ወደ ቤተክርስቲያን አቀናን። ይህ ሰውም ነበር። ደርሰን በዚያ ያልተጠበቀ ሆነ። ዲያቆን ታጣና ቅዳሴው ሊታጎል ሆነ። ካህናቱ ተጨንቀው ከወዲያ ወዲህ ሲሉ አየው። ሰማያዊ ሰው ያልኩህ ልዩ አባት መቅደስ ነበሩ ወጡና በወንዶቹ በኩል ፈንጠር ብሎ የቆመውን አብሮን የሄደውን ቤተክርስቲያን ለመግባቱ እንኳ እኔ ፈቃዴ ያልሆነ ያንን ሰው ጠርተውት ሲያናግሩት ተመለከትኩ። እያወሩ ከዓይኔ ከእያታዬ ውጪ ሆኑ። ባለሁበት እንዳለው የቅዳሴው ስረዓት መጀመሩን ከቤተልሄም ወደመቅደስ ሲመጣ በሚሰማ የቃጭልና የደወል ድምጽ ተረዳው። ሕዝቡ ባለበት ሰገደ። እኔም እንደዚያው። ቅዳሴ ላይ ሆኜ ጎሽ ዲያቆን አገኙ እያልኩ ደስ አለኝ። አንድ ድምጽ ግን በልዩነት ወደ ጆሮዬ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቤ ገባ። ዲያቆኑ ነበር። ኋላ የሰማሁትን ላይ ሰዓቱ ደረሰ። ገባሬው ዲያቆን ከመቅደስ ወጥቶ በዓይኔ አየሁ ግን ማመን አቃተኝ። ያ ሰው እርሱ ከትህትናው መንጦላይት ውስጥ ወጥቶ ከፊቴ ትህትናን ለብሶ አየሁት። እያለቀስኩ ቅዳሴውን ፈጸምኩ" አለ ሳይታወቀው አቤል እንደ ያኔው እንባው እየወረደ። "ዲያቆን ለካ እንደዛ ነበር። እኔም አሁን ዲያቆን ነኝ አልኩ ራሴን ወቀስኩ የጠላሁት ሰው ለካ እርሱ ሰው ነበር። ዲያቆን ብቻ ሳይሆን በእውነትም እርሱ ዲያቆን ነበር። ዲያቆን ሆኖ አየሁት ዲያቆን ሆኖ አገኘሁት። በእንባ ታጠብኩ። ምንም ማለት አልቻልኩም ያልኩት "አይ ንፍታሌም!" አልኩ በመገረም" አለ አቤል። ከነዓን ደነገጠ "የነገርከኝ ታሪክ ስለ ንፍታሌም ነውንዴ? እንዴ ንፍታሌም ዲያቆን ነው?" አለ ከነዓን። አቤል በአውንታ አንገቱን ነቀነቀ።

ሁለቱም ለረጅም ደቂቃዎች በዝምታ በመደነቅ ውስጥ ቆዩ። "እውነትህን ነው ንፍታሌም ዲያቆን ነው?" አለ ከነዓን የኋሊት ንፍታሌምን የሚያውቅበት ጊዜ ጋር በሀሳብ ተወስዶ አንድ ነገር አስታውሶ ጉዳዩ ከሰማው ጋር ሲገናኝበት። "ኢሄ ስለ ንፍታሌም ቲኒሹ ነገር ነው። ኋላ ያ ምስጢራዊ ጉዞ ሲደርስም እርሱ ምስጢር ነው የሆነብኝ ኢሄንን ግን እንዴት ብዬ ምን ብዬ እንደማወራውም ስለማላውቅ በውስጤ ብቻ ተደንቄ ዝም ልበል!" አለ አቤል። "እንዴት ያለ መታደል ነው!" አለ ከነዓን። "የሚገርም ነው እርሱን ያገኘሁበታን የመጀመሪያ ቀን ክስተት አልረሳም። ከዚያ በኋላም በነበረን ግንኙነት እርሱ አስደናቂ ሰው ነበር። አሁን ከአንተ በሰማሁት ግን ማመን እንዲከብደኝ ያደረገኝ አንድ የማውቀው ነገር ነበር" አለ ከነዓን። አቤል እንባውን እየጠራረገ "ምንድነው?" አለው። "በተደጋጋሚ አገኘው ነበርና በአገልግሎቱ ዙሪያ ካሉበት ፈተናዎቹ መካከል አንደኛው እንደጉድለት የሚያነሱበት ብዙዎች አንተ አሁን አለው የምትለኝን ክህነት ነበር። አውቅ ስለነበር ጠይቄውም አውቅ ነበር። "ለምን ዲያቆን ሆነ ኋላም በቅስናው የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ ሆነ የበለጠ አገልግሎትህን አታሰፋም?" አልኩት አንድ ቀን። ስቆ ነው የመለሰልኝ "መጀመሪያ ክርስቲያን ልሁንና ነው" አለኝ። መልሱ በጊዜው ስላሳመነኝ ከዚህ አልፌ አልተናገርኩም። "እሺ ክህነት የለውም በሚል ላለብህ ፈተናስ?" አልኩት። "ትልቁ ፈተና ሰው አለመሆኔ እንጂ እርሱ አይደለም። ሰው ከሆንኩ በዚያ የሚመጣብኝን ማለፍ እችላለሁ" አለኝ። በዚህ ምክንያት የሚሰድቡትም አሉኮ። ሆኖ እንዳልሆነ ሆኖ ነበር ያ ሁሉ የሆነው?" አለ ከነዓን። "ለዚህ ነው ምስጢር ነው የምለው" አለ አቤል። "እንዳልኩህ ነው በንፍታሌም መንገድ ላይ ከነበሩ እንቅፋቶች አንዱ እኔ ነበርኩ። አልመታሁትም አላገኘሁትም አላደናቀፍኩትም እግሮቹን አንስቶ በጥበብ አለፈኝ" አለ አቤል። "ምክንያቱም እርሱ እንደሚናፍቀው ሁሉ ሰው ነው! በወጣትነት ውስጥ ያለ አረጋዊ ጠቢብ ወጣት!" አለ አቤል ንፍታሌምን በማድነቅ ራሱን በመውቀስ ውስጥ ሆኖ። " ልክ ነው ለዚህም ነው አምላኩም በብዙ ከብዙ ስለሚጠብቀው ደዊትን መስሎ "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚለው" አለ ከነዓን። "አንድ ጊዜ ሲመክረኝ የሚወደውን ከአፉ የማይነጠለውን የዳዊትን መዝሙር እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚለውን አስቀድሞ በሕይወቱ የተገለጠውን የዚህን መዝሙር ትርጉም ነገረኝ። እንዴት ያለ መጠበቅ ነው? እንዴት ያለ መወደድ ነው? አልኩ የነገረኝን ስሰማ። ለአገልግሎት ካለበት ወደ ሌላ ከተማ ሄዶ የሆነበትን ሲነግረኝ ነበር ይህን ያልኩት። በሚደንቅ ለአገልግሎት ወደ ሄደበት ከተማ ሲጠራ በዚያ አካባቢ ትልቅ የሰላም ችግር ነበር። የቅርቡ መሄዱን የሚያውቁ ሰዎች እንዳይሄድ ጭምር ነግረውት ንፍታሌም ግን እግዚአብሔር እረኛው እንደሆነ አምኖ ወጣ። ከከተማው እንደደረሰ ለቀናት የነበረው የሰላም ችግር የከተማዋን ገጽታ አደብዝዞ ነበር። ሲደርስ የተቀበሉት ሰዎች ከአንድ ሆቴል ምኝታ ከተያዘለት ክፍል አድርሰውት ምሳውን ከነርሱ ጋር ተመግቦ ቀኑ አርብ ስለ ነበር ወደ ተዘጋጀው የጉባኤ አገልግሎት አቀና። ሲጠበቁ የነበሩ ከአዲስ አበባ የተጋበዙ አገልጋዮች በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት መቅረታቸው ዘግይቶ ቢታወቅም ንፍታሌም በቦታው ተገኝቶ አገልግሎ አገልግሎቱ ሲያልቅ ከሰዎች ጋር ወደሚያርፍበት ሆቴል አቅንተው በአንድ ተሰባስበው እራት ተመግበው ተለያዩ። በጉባኤው ላይ የሚያውቀው አንድ ወዳጁ ግን በቤቱ በእንግድነት ሊቀበለው ናፍቆ ሳያናግረው ያከታተለው ነበርና አብረውት የቆዩት ሰዎች ተሰናብተውት ሲሄዱ ያ ወዳጁ ወደርሱ መጥቶ ይዤህ ወደ ቤት ካልሄድኩ ብሎ ከመሸ ተያይዘው ወደርሱ ቤት ያቀናሉ። ያቺ ምሽት ግን እንዳለፉት ቀናት ሁሉ ያለ ሰላም ከማለፏም በላይ ንፍታሌም አልጋ ለያዘባት ሆቴልና በአንዳንድ ክርስቲያኖች ቤት ሌሊቱ ከጨለማ በላይ የሕይወት ድቅድቅ ጨለማ ሆና አደረች። ሌሊቱን ኔቶርክ ጠፋ። ታላቅ የጥይት እሩምታ ሲሰማበት አደረ። የብዙ ሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ። ለአገልግሎቱ ንፍታሌም የጠሩት ሲጨነቁ አደሩ። ጠዋት መጠነኛ ሰላም ሲሆን ከተማዋ በሕግ ሰዎች እንደተጥለቀለቀች የጉባኤው አዘጋጆች ለንፍታሌም መኝታ ወደ ተያዘበት ሲደርሱ ታላቅ ድንጋጤ ወረደባቸው። የሆቴሉ መናፈሻዎች የአልጋ ክፍሎች ወድመዋል። በዚያ መኝታ ይዘው ካደሩ የተገደሉ እንዳሉም ሰሙ። ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል የተወሰዱም መኖራቸው ሲነገር ተፋጥነው ንፍታሌምን ስላላገኙት
ወደ ሆስፒታል አመሩ። ንፍታሌም ከረፈደ ካደረበት ቤት የሌሊቱን በከተማዋ የወረደባትን የመከራ ናዳ ሊያይ ከተቀበለው ሰውጋ ወጣ። ሁሉ ሲያይ ንፍታሌም እንደ ሁል ጊዜው በዚያ ሆቴል የሆነውን ሲመለከት "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው....." ዘመረ። የትራንስፖርት አገልግሎት ጭምር ተቋርጦተ በዚያ ሰንብቶ ከሞት አምልጦ የተመለሰበትን እንዲህ አውግቶኝም ነበር።" አለ ከነዓን። አቤል ሲሰማ ንፍታሌም ናፈቀው። ከተቀመጡበት ዛፍ ስር ሲጨዋወቱ ቆዩ። "ንፍታሌም የሕይወት መምህር ነው። ልንመስለው የሚገባ ምሳሌ የሆነ ሰው ነው። በል ተነስ እንሂድ!" አለ ከነዓን። ኢሄን በመሰለ ከነዓን ከአቤልና ከተስፋዬ ጋር እስከ ምሽት አብሯቸው ቆይቶ በቀጣይ ቀን እንደማይኖር ነግሯቸው ማታ ተለያዩ። በቀጣዩ ቀን እርሱ ወደ ተልዕኮ ርቆ ሲወጣ ተስፋዬም ወደ ሚሰነብትበት ስፍራ መቶ አንድ ሰው ወሰደው። አቤልም እንዲሁ በአንድ ወጣት በኩል ወደ አንድ አረጋዊ በአት አመራ።

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ታኅሳስ 3 2018 ዓ.ም ባሌ ጎባ 💢
🌄🌅🌌 ህቡዕ ገጽ 🌌🌅🌄

     🌄🌓👤 ህቡዕ ገጽ 👤🌓🌄

🌄🌓👤 ክፍል 283 👤🌓🌄

ራሄል ያለ ወትሮዋ ከፊቷ የማታውቀውን መንገድና የሰላምን ናፍቆት በልቧ ይዛ ከእንቅልፏ ተነስታ ጉድ ጉድ ትል ጀመረ። "ራሄል ለምን ባባን እማዬ ጋር ትተሽው አትሄጅም?" አለ ኤርምያስ ከተኛበት ሕጻኑን ይዛው መሄዷ አሳስቦት። ስራዋን እየሰራራች "ውይ አይሆንም እኮ አንደኛ ሊያስቸግር ይችላል። ሲቀጥል ደግሞ እናቴን ቢል ምን ሊደረግ ነው? ይዤው ብሄድ ይሻለኛል። እኔም ልቤ አያርፍም" አለችው። መልስ አልሰጣትም በዚያው ዝም አለ። ራሄል በማለዳ ተነስታ ከአንዱ ወደ አንዱ ስራ ስትል ክብሮምም እንዲሁ ከርሷ ቲኒሽ ዘግይቶ ተነሳና የመኪናውን ሞተር አስነስቶ ተመልሶ ወደ ክፍሉ ገባና መዘጋጀት ያለበትን ይዘጋጅ ጀመር። ማርታም እንዲሁ ካለችበት በማለዳ ወደ ሮቤ መጣች። እነ ራሄል ቤት ስትደርስ ራሄል የጀመረችሁን ሁሉ አጠናቃ ልጇን ታቅፋ አገኘቻት። ሰላምታ ተለዋውጠው በቀጥታ መያዝ ያለባቸውን ይዘው ወጡ። የያዙትን እቃ መኪናው ላይ እየጫኑ ክብሮምም ቦርሳውን አስቀምጦ ስልኩን አውጥቶ ደወለና "ሄሎ ንፍታሌም!" አለ እንደሚያየው ሁሉ ፈገግ ብሎ። "አልተነሳውም አትለኝም መቼም አይደል?" አለው ቀጥሎ። መልሱን ለመስማት ራሄልና ማርታም ወደ ክብሮም ትኩረታቸውን አደረጉ። "ኧአ ባክህ!" አለ ክብሮም እንደመደንገጥ ብሎ። "ምንድነው ቀረው ነው የሚለው?" አለች ራሄል ሀሳብ ገብቷት። "እሺ እሺ በቃ!" ብሎ ስልኩን ዘጋና። "ውይ ከወጣው ቆይቻለው ነው የሚለው መንገድ ላይ እየጠበቀን ነው። በቃ ግቡ እንሂድ" አለና ገቢና ከፍቶ ሲገባ ሁለቱ ከኋላ ተከታትለው ገቡ። ንፍታሌም ያለበት ሲደርሱ ቢኒያምን አብሮት አገኙትና መኪናው ሲቆም ንፍታሌምና ቢኒያም ከኋላ ሊገቡ የኋላውን በር አንዳቸው ሲከፍቱ "አንድ ሰው ኑ ገቢና ግቡ!" አለ ክብሮም ንፍታሌም እንዲገባ ፈልጎ ማለት ከብዶት። "ደቢና ይግቡ ዶክተር!" አለ ንፍታሌም። "አንተ ባለህበት ለኔ ገቢና ይግቡ የተከበሩ" አለው በአጸፋው ቢኒያም። ንፍታሌም እንደ ክብሮም ምኞት ገቢና ሲገባ ቢኒያም ከራሄል አጠገብ ተቀመጠ። "እንዴት አደራችሁ ሁላችሁም ሰላም!" አለ ቢኒያም። "ሰላም አደራችሁ!" አለ ንፍታሌምም እንዲሁ። ውስጥ የነበሩት ምላሹን ሰጧቸውና ጉዞ ተጀመረ። "ብዙ አቆምናችሁ እንዴ?" አለው ክብሮም እየነዳ ዘወር ብሎ ንፍታሌምን እያየው። "አይ ጥሩ ጊዜ ነው የወጣነው አልቆምንም" አለው ንፍታሌም በይሉኝታ። "እውነት ለመናገር ከ30 ደቂቃ በላይ ቆመናል። እንዲያውም የቀደማቹን መስሎን ነበር ስንወጣ" አለ ቢኒያም። ሶስቱም በቢኒያም ግልጸኝነት ተደናገጡም ተደነቁም። "ይቅርታ እንግዲ!" አለ ክብሮም ሳያንገራግር። " ኧረ ይቅርታ የሚያስጠይቅ አይደለም" አለ ንፍታሌም ወደ ኋላ ጓደኛውን ዞሮ እያየ እግረመንገዱን ሌሎቹንም አየት እያደረገ። "ሰው ለዓመታት ሰው ይጠብቅ የለም እንዴ?" አለ ንፍታሌም። "ለምሳሌ አንተ ማንን ለዓመታት ጠብቀህ ታውቃለህ?" አለው ቢኒያም መልስ ሊያሳጣው። "ለምሳሌ አንተን!" አለ ለማሰብ ሳይቸገር። "ያኔ ተማሪ ሆነን ዶክተር መሆን እፈልጋለው ትል ነበር። ልጅነትም ስለነበር በጫወታ መሀል እንኳ ሀኪም ነኝ እያልክ መርፌ ይመስል በሚስማር ካልወጋዋችሁ እያልክ ታስቸግር ነበርና መጨረሻህን ላይ ዓመታት ጠበኩ ይኸው..." አለ ንፍታሌም። ውስጥ ያሉት መጠነኛ ሳቅ ሳቁ። "እርግጥ እኔ ስለሆንኩ ጠብቀህ አላሳፈርኩህም ተገኝቻለው። አንተ አይነቱ አለንጂ ሲጠብቁት ውለው ቢያድሩ ዘመን ቢያስቆጥሩ ከጠበቁበት ካሰቡበት የማይገኝ። እርግጥ እናደድ ነበር አሁን መልሱን ሳገኝ ስረዳ ተውኩት" አለ ቢኒያም ፈገግ ብሎ። "ምኑ ነው የገባህ?" አለ ንፍታሌም። ቢኒያም "ለምን በልጅነትህ ትል የነበረውን ለምን እንዳልሆንክ" ሲል ይኼን ለመስማት ራሄልና ክብሮም እጅግ ጓጉ። "ምን ነበር መሆን የሚፈልገው?" ክብሮም ሲል ራሄል "ልል ስል!" አለች። ቢኒያም ስቆ "ወታደር እሆናለው ይል ነበር! ለካ ያኔ ጦርነት በቲማቲም መስሎት ነበር ሲገባው ሀሳቡን ቀየረ። ስጠብቀው ኖሬ አልመጣ ሲል ነው ነገሩ የገባኝ" ብሎ ቢኒያም ከት ብሎ ሲስቅ ሌሎቹም ተባበሩ። ንፍታሌም ግን የጫወታውን መንገድ የሚቀይርበት ክስተት ተፈጠረ። የልጅነት ምኞቱን ምክንያቱን ሲያስታውስ ያ የፍላጎቱ ምክንያት ለሀገሩ የሚዋደቅ ወታደር ጋር ወሰደውና አንድ ከአቅሙ በላይ በሆነ ስሜት ሲረታ ገጹ ሲተክዝ ታየ። ክብሮም እየሳቀ ሲዞር ደነገጠ። "ምነው ንፍታሌም ንግግራችን አስከፋህ እንዴ?" አለ ደንግጦ። "ፍርሀቱ ተቀስቅሶ ነው እንጂ!" አለ ቢኒያምም ዞሮ በፈገግታ እያየው። እርሱም የዳመነ ገጹን ቢያይ ራደ። "ወታደርን ያክል ክቡር ምን አለና ነው የሚያስከፋው!" አለች ራሄል። "ኧረ ተይ ባክሽ አንቺ ደግሞ እንደው!" አለች ማርታ ሀሳቧን ተቃውማ። ለሁሉ እርቅ የሚያወርድ ሽማግሌ ከንፍታሌም ልቦና ውስጥ ሊወጣ ያን ግዜ ይሰናዳ ጀመር። ሁሉም ንፍታሌም ምን ይል የሚሉ መሰሉ።

መኪናው ውስጥ የነበረ ሳቅ ጨዋታ ለደቂቃዎች በዝምታ ተዋጠ። "አምስት ስራዎች ያስደንቁኛል። አምስተኛውን የሚያህል ግን የፍቅር ትርጉም የሀነ ስራ የለም ሲል በንፍታሌም ንግግር ተደናገጡ። ሁላቸውም ንግግሩን ሊሰሙ ኅሊናቸውን አሰናዱ። "ለኔ አምስተኛው ሀኪም ነው። በሕይወት ውስ የተጨነቀን የተቸገረን እንደማሳረፍ ምን እረፍት ምን ስራ አለ። የታመሙ በእግዚአብሔር ፈቃኩ በአንተ በኩል ድነው ኡፍ ሲሉ የናፈቋትን ድህነት አጊኝተው እንደማየት ምን እረፍት አለ። እርግጥ ነው ተከፍሎ በገንዘብ ይሆናል። ይሁንና እራሱ ገንዘብ ግን ሊያድን አይችልም። ስላወቀ ስለተማረ ሀኪሙ ነው ለመዳን ባለመድኃኒቱ። አራተኛው እርሱን ያስተማረው የእውቀት ፈንጣቂ የብርሀን ጮራን የሚያበራ የመምህር ስራው አጹብ ያስብለኛል። አስተማሪም እንዳልኳችሁ በገንዘብ ነው እሚያስተምረው ግን ለገንዘብ ብቻ ብሎ አይደለም። ለዚህ ምስክሩ ሀተማሪዎቹ ያለው ፍቅር ነው። ከኔ ተምረው ከኔ እንዳይበልጡ ብሎ እውቀቱን አይሰውራቸውም ይልቁኑ ተሽለው እንዲገኙ በፊደልም በግብረ ገብነትም ይቀርጻቸዋል። በልጠውት ሲያገኛቸው አያፍርም ይኮራል። ፍሬዎቼ ናቸው ይላል። አያችሁ መምህር ለፍሬ እንጂ ለደሞዝ አይሰራም።" አለ ንፍታሌም። ከዚያስ ምን ይል ይሆን እያሉ ልባቸው ተንጠለጠለ። "ቀጥሎ ግን ለሁለቱ ደረጃ መስጠት ይከብደኛል። ገበሬ እና እረኛ" አለና በኅሊናው መጻፍ ቅዱስ ቢታወሰው ለደረጃው ነገሩን አቀለለለትና ሶስተኛ ገበሬ ነው" አለ። "ገበሬ በሕይወቱ ሃይማኖቱ ግልጥ ብሎ ይታያል። ገበሬ ሀይማኖተኛ። በሃይማኖት ውስጥ ያሁትን ሶስት መሠረታዊ ነገሮች በገበሬ የሕይወት ተግባር ውስጥ ታገኙታላችሁ። ገበሬ አማኝ ነው 💢 እምነት💢 አለው። ስለሚያምን አምኖ የበለጠ ሊቀበል ያለውን ከቤቱ አውጥቶ በአፈር ላይ ይበትናል። የዚህ እምነቱ ምንጭ ላመነው ያለው 💢 ፍቅር 💢 ነው። እግዚአብሔርን ስለሚወደው ያምነዋል። ያመነውን ይዞ ያለውን ይበትናል። የያዘውን ለቆ እግዚአብሔርን ይይዛል። ሌሎች ስራዎች ላይ ይህን ማግኘት ከባድ ነው። ሰው በአንድ እጁ እግዚአብሔርን በሌላው ደግሞ ገንዘብ ወይ ስልጣኑን አልያም ዘመዱን እንዲያ እንዲያ ሊይዝ ያምረዋል። ባላገሩም ይህን አውቆ አይቶ ይተርታል። "ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም" ይለዋል። ሰው ግን እንዲሁ ሁለት እንደሆነ አንዱ እርሱ አንዱ እርሱን እንደታገለ እንዲሁ አንድ ሳይሆን ራሱን ሲታገል ራሱን ሳያሸንፍ ምዕራፉ
ይዘጋል። ገበሬ ግን ከቤት ያለውን አውጥቶ በትኖ በ💢ተስፋ💢 የሚወደውን ያመነውን አምላኩን ይጠባበቃል። የበተነውን በጊዜው ደርሶ ሲሰበስብ ለኔ ብቻ አይልም ደግሞ ለከተሜው ካለው ያካፍላል። ለገንዘቡ ትሉ ይሆናል። አይደለም። እርሱንም የሸጠውን ከተሜው ወይ ከተሜነት ያለበት እርሱን የማይመስለው ገበሬ ይገዛውና ደግሞ ጊዜው ዳግም ሲደርስ ዘር ብሎ ይሸጥለታል። እንኪያስ ለከተሜው እአእል ሰጥቶ ገንዘብ ባይቀበል ዳግም ዘሩን በምን ገዝቶ ዘርቶ ገበያው ሊጠግብ? ገበሬ ያወጣውን በአፈር በትኖ በዚያው ቢቀርበት ባይበቅል ከተሜው ለኛ ብሎ ነው ብሎ ካሳ አይከፍለውም። ሲከስር ብቻውን ሲያገኝ ለሁሉም ነው ገበሬ። ግን ብዙው ለዚህ ውለታው ስሙን ስድብ አድርጎ "ገበሬ!" ይላል። ስሙ ክብር ነው" አለ ንፍታሌም። ገጠር እንዳደገ እንደ አርሶ አደር ልጅ አርሶ እንዳለፈ ድካሙን ስራውን እንደሚያውቅ ሁሉ ከልቡ ለየት ባለ ገበሬን ሲገልጽ። "አቤት እረኛ ደግሞ...!" አለ ንፍታሌም ከብቶች ሲጠብቅ እንደኖረ መንጋውን እንደሚወድ ቲንሽ እረኛ። "እረኝነት በገጠር ላለ ልጅ ከልጅነት የሚጀምር ልዩ ስራ ነው። እረኛ ማለት መንጋውን አሰማሪ ከብቶቹን መንጋውን ጠባቂ ማለት ነው። ኢሄ ቀላል አይምሰላችሁ መንጋውን ከበረት እየነዱ አውጥቶ ሜዳ አውሎ መምጣት አይደለም። ከለመለመ መስክ ውኃ ካለበት ይወስዳቸዋል። ሲጠግቡ ደስ ይለዋል። እረኛ ፈተናው ብዙ ነው። በጥበቃው ዝንጉ ከሆነ ከብቶቹ ይጠፋሉ። ከጠፉ ደግሞ ከጌታው ቅጣት አለበት። የቤተሰቦቹም ከሆኑ ቁጣው ቀላል አይደለም። ከዚህም የባሰ ፈተና በእረኛ ስላለ ነው እረኝነት ልዩ ነው የምለው። መንጋውን የሚበላበት አውሬ ሲመጣ የመታደግ ኃላፊነት ይወድቅበታል። በዚህ ምክንያትም ስለ መንጋቸው ለሞት የተሰጡ ብዙዎች አይተናል። ይህን ስራ አምላክም ተጠርቶበታል" አለ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚለውን መዝሙር በውስጡ እየደገመ። " እሺ ላንተ አንደኛው ስራ ፍቅርን የሚተረጉመው ምንድነው?" አለች ራሄል አራቱን ከሰማች በኋላ። " አንደኛውማ ምንም ለራሱ የማይኖረው የፍቅር ተምሳሌት ወታደር ነው። ስለወታደር ምንም ማለት ይከብደኛል። እርሱን ለመግለጽ ቃላት አቅም ያጣሉ። ወታደር ለሌላው የመኖር መስዋዕት ሆኖ ድንበር ሀገርን ለማስከበር ለራስ ሳያስቡ ለሀገር መውደቅ ነው። ለሌላው ብሎ ወደ ሞት መሄድ እውነተኛ ፍቅር ነው። ወታደር የሚወዳትን እናቱን ወደ ሞት እየሄደ እንደሚመለስ ሰው ተሰናብቶ ይሄዳል። ወታደር የሚወዳትን አካሉን ሚስቱን ስሞ ወደ ሞት እያየ የሚራመድ ለሀገሩ የታመነ ጀግና ነው። ለሀገሩ ሲል ለወገኑ ሲል ይራባል ይጠማል። በበረሀ በዱር በገደሉ ይዋደቃል። ወታደር ሙሉ ሰው ነው ሰው ሰውነትን የሚያከብር። ወገኑን የሚወድ አይደለም ለጠላቱም ፍብሩን በተግባር የሚገልጽ እንጂ። ሊገድለው የሚተኩስበት ወድቆ ሞቶ ሲያገኝ በክብር ሥጋውን የሚያሳርፍ ጠላቱ ተማርኮ እጅ ሲሰጥ ምንም በርሱ ላይ የማያደርግበት የሰውነት ጥግ ነው ወታደር። ወታደር ሀገሩን ብሎ ይወጣል። ሀገሩን ብሎ ይኖራል። ሀገሩን እንዳለ ይሞታል። ሕይወቱ ነች ሀገሩ። ባንዲራው እስትንፋሱ ነች። ነገን የት እንደሆነ ሳያውቅ ሀገሩ በጠራችው የሚገኝ የራሱ ምንም የሌለው ራሱን ለወገኑ መስዋዕት ያደረገ ነው ወታደር። ወታደር የሀገር ክብር ነው" አለ ዓይኖቹ እንባ አቅረው እኝባው ታግሎ ይዞት። አራቱም ስሜታቸው ተነዋወጸ።

እንዲህ እንዲህ እያሉ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። ክብሮም ንፍታሌምን እጅግ በብዙ ወደደው። ንግግሩ ግብረ ገብነቱ ገዛው። ራሄልም "እንዴት ያለ ተሰምቶ የማይጠገብ የጥበብ ምንጭ ነው? ወጣትነትን ከብስለት ጋር እንዲ መታደል በመንፈሳዊነት ደምቆ ኃይል ያላቸውን ቃላት ከአንደበት አውጥቶ ከሰው ልብ ዘልቀው እንዲገቡ ተሰሚነትን በዚህ መጠን ማግኘት ምን መታደል ነው?" እያለች ብቻዋን በውስጧ ታደንቀው ራሷን ትጠይቅ መልስ ታጣና ማድነቅ ኋላም "እውነትም ኢሄን አለመውደድ አይቻልም። ሰላም መውደድ ያለባትን ነው የወደደችው። እንደው የንፍታሌምና የሰላም ጥምረት ግን የሚፈጥረውን ትዳር ምን ብሎ መግለጽ ያቻላል። ሰላምዬ ምኞትሽ ይሁንልሽ የኔ እንቁ" አለች ራሄል በውስጧ። የመሊዩን ከተማ አልፈው ገጠሩን አቆራርጠው እየተጨዋወቱ ከጫካው ደረሱ። ኢሄ መንገድ ከክብሮምና ንፍታሌም ውጪ ለሁሉም የመጀመሪያ ነው። ተፈጥሮው ተራራው ደኑ የመለሰክአ ምድሩ አቀማመጥ እጹብ ያሰኛል። "እንዴት የሚያምር ነው አከባቢው? ቆይ ቆላ ነው የሚባለው ገና አልደረስንበትም ማለት ነው?" አለች ማርታ። "ኢሄ የምታዩት ደን እንደ ኢትዮጵያ ካልተሳሳትኩ 2ኛ ወይ 3 ኛ ነው። ሰንሰላታማውን ተራራ ይዞ ያለ ረጃጅም ዛፎች ልዩ እጽዋቶች የሚገኙበት ትልቁ ጫካ ነው" አለ ክብሮም። መንገዱ በጨመረ ቁጥር የሚያዩት ይበልጥ መስህብነቱ እየጨመረ ልባቸውን እየገዛው መጣ። አንዱን ሲያልፉት የሚበልጠውን እያዩ በቀኝ ያለውን ሲሉን የግራው እጹብ እያሉ መንገዳቸው ቀጠለ። አንድ ለጥ ያለ ሜዳ ጋር ሲደርሱ ግን አድንቀው ማለፍ አቃታቸው። በጸኃፊ የቀንድ ቀለም የማይገለጽ ልዩ ውበት ቢያዩ " እዚህ ጋር አታሳልፈን በናትህ አቁምልንና እንየው" አለ ዶ/ር ቢኒያም። መኪናውን ጥግ ይዞ አቆመውና ሁሉም ወርደው ሰፊውን የተንጣለለ በአረጓዴ ቃለምልልስ ያሸበረቀ እንስሳት በየመልካቸው ያስጌጡት ከኋላ ከርቀት የሚታየው ተራራ ግርማ ሞገስ የሆነው ልዩ ስፍራ ዓይናቸው በስስት አልጠግብ ብሎ ከአንዱ ወደ አንዱ እያሉ ሲቃኙ ቆዩ። ለማስታወሻ ፎቶ ሲነሱ ንፍታሌም በየተራ ፎቶ አንሺ ሆኖ ተሾመ። አይተው ሳይጠግቡ ጉዞአቸው ቀጠለ። አራት ሰዓት ተኩል ሲሆን በርበሬ ከተማ ደረሱ። መኪናቸውን አቁመው የሚበላ በልተው አርፈው 5:20 ሲሆን ጉዞ ወደ አዋሽ ቆላቲ ጀመሩ። ከከተማው እንደ ወጡ ቲኒሽ ሙቀቱ አሰልችቷቸው ድካም ተጫጭኗቸው የነበረው ወደ ነፋሻማ አየር እየደረሱ ሲሄዱ ተፈጥሮ መልሶ ወደ መስህብነት እየተለወጠ ሲመጣ ተነቃቁ። ተፈጥሮውን እንዲ እያደነቁ በርበሬ ወረዳ ጎሮ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሲደርሱ ከመኪና ወርደው የሚያምረውን የቤተክርስቲያኑን ቅጽር ጥቂት ቃኝተው ጉዞ ቀጠሉ። ወደ አዋሽ ሲቃረቡ ሁሉም መደመሙ ጨመረ። አዋሽ ሲደርሱ ሁሉም እያዩ ከመደመም በቀር የሚያወራ ጠፋ። ልዩ ተፈጥሮ ልዩ ጌጥ ምድራዊ ገነት ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያስጌጣት እመቤት ኢትዮጵያ ተሸልማ አገኟት። መኪናው አንዴ ቁልቁለቱን ደግሞ አቀበቱን እየወጣ እየወረደ ከነሰላም ቤት ሲቃረብ "ኢሄ የጻድቁ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ነው" አለ ንፍታሌም። መኪኪናው ቆሞ ሊሳለሙ ገቡ። ተወደ ቤተክርስቲያኑ ቅጽር ሲገቡ አንድ ወጣት ብቻ ከአንድ ጥላ ስር ብቻውን ተቀምጦ ተንሰቅስቆ ያለቅሳል። ቢኒያም ወደርሱ ደርሶ አናገረው ሊያጽናናው የሚችለውን ሁሉ አደረገ። ወጣቱ እጅግ እንደተከፋ ቢኒያምን አመስግኖት ወደ ቤቱ ተነስቶ አመራ። እነርሱም ተሳልመው ጸልየው በቀጥታ ወደነ ሰላም ቤት አቀኑ። መኪናዋ ግን መንገዱ ስለማያስኬድ ካለችበት አቆሟት። ሲደርሱ ሰላም ጉድ ጉድ እያለች ደረሱ። " እዚህ ቤት ቤቶች!" አለች ራሄል። ሰላም ምሳ እየሰራች ስለነበር ከኩሽና ወጣ ስትል ወዳጆቿን አይታ ተከፍታ ደንግጣ ቆማ ቀረች። ማርታ እና ራሄል የሚያውቋትን ሰላም ሳይሆን ሌላ ሰላም ያዩ መሰላቸው ደንግጠው ደርቀው ቀሩ። ጠቁራለች ከስታ ፊቷ ገርጥቷል። ውበቷ ግን እንዲህም ደምቆ ፈክቶ ይታያል። ክብሮም ማመን አቃተውና ቀስ ብሎ "በስመአብ ምን ሆና ነው እንዲህ የሆነችው?" አለ። ቢኒያም ልቡናው ታወከ። ሰላም ስታያቸው
ከፋትና እንባዋ ዱብዱብ አለ። ራሄል ወደ ሰላም ፈጥና ተራምዳ "ሰላምዬ!" ስትላት ማርታ እዬዬዋን ለቀቀችው። እንደ አዲስ ለቅሶ ሰፈሩ ተረበሸ። ከልካይ ሳይኖር ተላቀሱ። ሌላው እንግዳም ጥቂት ቆይተው ደረሱ። መሪጌታ አመሀ የሚወዱትን መቅደስ ተሳልመው ለቅሶውን እየሰሙ እያነቡ ቤታቸው ደረሱ።

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ታኅሳስ 6 2018 ዓ.ም ባሌ ጎባ 💢
🌄🌅🌌 ህቡዕ ገጽ 🌌🌅🌄

     🌄🌓👤 ህቡዕ ገጽ 👤🌓🌄

     💢💠 ከክፍል 283 የቀጠለ 💠💢

ማርታ እና ራሄል የሚያውቋትን ሰላም ሳይሆን ሌላ ሰላም ያዩ መሰላቸው ደንግጠው ደርቀው ቀሩ። ጠቁራለች ከስታ ፊቷ ገርጥቷል። ውበቷ ግን እንዲህም ደምቆ ፈክቶ ይታያል። ክብሮም ማመን አቃተውና ቀስ ብሎ  "በስመአብ ምን ሆና ነው እንዲህ የሆነችው?" አለ። ቢኒያም ልቡናው ታወከ። ሰላም ስታያቸው ከፋትና እንባዋ ዱብዱብ አለ። ራሄል ወደ ሰላም ፈጥና ተራምዳ "ሰላምዬ!" ስትላት ማርታ እዬዬዋን ለቀቀችው። እንደ አዲስ ለቅሶ ሰፈሩ ተረበሸ። ከልካይ ሳይኖር ተላቀሱ። ሌላው እንግዳም ጥቂት ቆይተው ደረሱ። መሪጌታ አመሀ የሚወዱትን መቅደስ ተሳልመው ለቅሶውን እየሰሙ እያነቡ ቤታቸው ደረሱ።

🌄🌓👤 ክፍል 284 👤🌓🌄

ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት በነሰላም ጊቢ ተስተናገደ። ራሄል ልጇን ከግንባር ገብቶ እንዳገኘች እናት አንጀቷ ስፍስፍ ብሎ ሰላም በእቅፏ አስገብታ አባብላ ናፍቆቷን ትታው ጉዳቷን ለመካፈል አቅም ያጡት እግሮቿ ወደ ችግሯ ጊዜ ረዳት ወደ ውቧ ሰላም እየተጠላለፉ አቀኑ። ከሰላም በፊት የረጅም ጊዜ ጓደኛዋ ግን እንደ ራሄል ጊዜ ለመስጠት ጊዜ አጣችና ጩኸቷን ለቅሶዋን ለቀቀችው። ሰላም ስታያቸው ብትከፋም ሁሉንም እያፈራረቀች ሲያዝኑላት ነፍሳቸውን በእይታ አነበበችና ዓይኖቿ ግን ያለ ይሉንታ ከአንድ ሰው ላይ መነቀል ተሳናቸው። ወደርሷ የምትራመደውን ራሄልን ሳይሆን እንባዋ ኩልል ብሎ ከዓይኖቿ በጉንጯ ሲወርድ ንፍታሌምን በስስት ዓይኖቿን ሳትነቅል ትመለከተው ነበር። ንፍታሌም እንደሌሎቹ ባይደነግጥም እርሱ ከነበረበት ጊዜ በላይ በአጭር ጊዜ ሰላም ላይ ያየው ለውጥ እርሱንም ሳይረብሸው አልቀረም። በስስት ስታየው አያትና ዓይኖቹን ሰበር አደርጎ አቀረቀረ። ንፍታሌም ቆይቶ ከአጠገቡ ወዳለ ሰው ቀና ሲል ዶ/ር ቢኒያም ስብስቅ ብሎ እያለቀሰ ነው። የማርታን ድንገተኛ ጩኸት የሰማው ያፌት በርግጎ ከቤት ሲወጣ የማያውቃቸው ናቸው። አለቃቀሳቸውና ሁኔታቸው ግን እርሱንም ከማኅበራቸው ደመረው። ቢኒያም እያለቀሰ ቀና ሲል ከቤተክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ እያለቀሰ ያገኘው ሰው መሆኑን አወቀና የቀደመ ምክንያቱን ስለተረዳ ዘመዳቸው ሳይሆን እንዳልቀረ አሰበ። "ሰላምዬ የኔ ቆንጆ ምን ነካቸው እማዬን?" አለች ራሄል ሰላምን አቅፋት እየተንሰቀሰቀች። "እማዬ ድንገት ሄደች። ሳላገኘች መሰናበቷን ሰማው። እማዬ ሳልሰናበታት ድንገት እርቃ ሄደች" አለች ሰላም በዛል ተስፋ የቆረጠ በሚመስል ዝግ ባለ ንግግር። ማርታ ግን "ወይኔ እናቴን እኔ አላምንም እናቴን እናቴን እማዬን" እያለች ጩኸቷን አቀለጠችው። ያፌት የሚያለቅስ በማግኘቱ እርሙን ከልቡ ለማውጣት በጎ እድል መስሎ ስለተሰማው "እናቴን የኔ ብቸኛ ተበትነን አጠገብሽ እንኳ ሳንገኝ ዓይኖችሽ እንደተራቡን ሳታገኝን እንዴት አስቻለሽ? መጣለሁ ብዬሽ ምን አስጨከነሽ? እማ አልቻልኩም እናቴ አላመንኩም!" እያለ ሲያለቅስ ሁሉም የመጡት የሰላም ወንድም መሆኑን ያለ ነጋሪ ተረዱ። ቢኒያም እያለቀሰ የለቅሶውን ምክንያት በየመሀሉ በዓይኑ ይቃኝና እየተከፋ እንደ አዲስ እዬዬ ይላል። ሰላም እንዲ መጎዳቷ እንዲ መጎሳቆሏ አላስቻለውም። ክብሮም ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ባለበት ሰላምን ካየበት ጀምሮ ዓይኖቹ ደግመው ሰላምን ማየት ፈርተው በድንጋጤ ይመስል እንባው ደርቆ እንዳቀረቀረ "ያቺን የመሰለች ፀሐይ ምን ሆና ነው እንዲ የደበዘዘችው። ያቺ ታይታ የማትጠገብ አበባ እንዴት እንዲ ጠወለገች?" እያለ በውስጡ ሙሾ ያወርዳል። ራሄል ልጇን እንዳዘለች ከሰላም ተቃቅፈው ከተላቀቁ በኋላ እርሷም ያደረገችላትን ውለታዋን በችግሯ በሀዘኗ ጊዜ ቁርጥ ወዳጇ ሰላምን እያሰበች ግና እናቷን እየጠራች እዬዬዋን አወረደችው። ከሁሉም ልዩ ስሜት የነበረው ደግሞ ንፍታሌም ነበር። ወትሮ እንባው ቅርብ የነበረ ንፍታሌም የሰላም ትልቅ ጉዳት አስደነገጠው። ለዊህ ደግሞ የእናቷ እረፍት ብቻ ሳይሆን አንዱ ምክንያት እርሱ እንደ ሆነ ተሰማው። ለሰላም አዘነላት ራራላት እንዳቀረቀረ ምን ሊያደርግ እንዲገባ ያስብ ጀመር። ከእያንዳንዳቸው የሚሰማው የለቅሶአቸው ሙሾ ግን ኅሊናውን ከወዲያ ወዲህ ያወዛውዘው ያዘ። በመሀል ቀና ብሎ ሁሉንም አያቸውና ከሰላም ጋር ዓይን ለዓይን ተገጣጠሙ። ሰላም በዚያች ቅጽበት ከንፍታሌም ዓይኖች የሚያጽናኑ ቃላትን የሰማች መሰላት። ሲያዝንላት አይዞሽ ሲላት ከዓይኖቹ አነበበች። ንፍታሌም ብዙ ሊያያት አልቻለም ዓይኖቹን አንስቶ ወደ ውጪው በር ሲጥል አንድ ሰው ቆመው አየ። ንፍታሌም ያን ጊዜ ነው እንባው በድንገት ሿ ብሎ የዘነበው። መሪጌታ አመሀ ገና ከጊቢያቸው የነበረውን ለቅሶ ከሰሙበት በያንዳንዱ እርምጃቸው ውስጥ ስለ ሚወዷት ስለ ልጃቸው ሰላም እያሰቡ ጉዳቷ እያሳሰባቸው የምጥ እርምጃዎችን ቆጥረው ከበር ሲደርሱ ፍራታቸው ሥጋ ለብሶ በግዙፍ አካል ታያቸው። ሰላም ከስታለች። ልጃቸው ጠቁራለች። ጊቢያቸው የሞት ሀገር መሰላቸውና ተጠየፉት። እንደቆሙ ሰላምን እያዩ "ልጅሽ በሀዘን ጠቁራ ምን እንደመሰለች ብታይ አመሀን ይቅር ትይው ይሆን?" አሉና በቁማቸው ያለ ድምጽ ያለ እንጉርጉሮ ያለ ሙሾ ሊቁ ስለ ውድ ልጃቸው ጉዳት ደግሞም ስለ ሟች ሚስታቸው አነቡ። ንፍታሌም ስብር ብለው እንባቸው በጉንጫቸው ሲወርድ ቢያይ አንደበቱ ተሳስሮ አካሉ በድን ሆኖ ዓይኑ ብቻ እንባ አዘነበ። ክብሮም የንፍታሌም ቀድሞ እንደርሱ ሁሉ እንባ አለመታደል ደንቆት ካቀረቀረበት ቀና ሲል ንፍታሌም መንታ መንታ እንባው በዝምታ ወርዶ እያበሰበሰው ነው። እይታውን ተከትሎ ንፍታሌም ወደ ሚያይበት ሲያይ ያያቸው ሰው ማን እንደ ሆኑ ባያውቅም አቋቋማቸው ሁኔታቸው ሳይናገሩ ይሰማል። ክብሮምም ያለ ድምጽ ለቅሶአቸውን ሰማ ልቡ ታወከና ኬት መጣ ያለለው እንባ በዓይኑ መላ።

ቀጥሎ ሊቁ ያያቸው ልጃቸው ነበር ያፌት። የ አባቱ ነገር አልሆነለትም እየሮጠ ሄዶ ተጠመጠመባቸው። ክብሮም አዲስ ለቀስተኛ መሰሉት። የያፌት መሮጥ ተከትሎ ሁሉም መሪጌታ ባለ ቅኔውን ሊቅ ትሁቱን ሰው ቆመው አሻግረው አዩአቸው። ልጃቸው ወደርሳቸው ሲፋጠን እርምጃ ጀመሩ። ያኔ ለቅሶው የሁሉም ጋብ አለ። ያላወቋቸው ለማወቅ ያወቋቸው ለሰላምታ በሀዘን ቆሙ። መሪጌታ እንባቸውን እየጠራረጉ ልጃቸውን እያጽናኑት አቅፈውት ሰላም ተባብለው ወደ ሌሎቹ አመሩ። ንፍታሌም ዓይኑ አልተነቀለም። እንባውም አላባራም። ክብሮም የንፍታሌም እይታ ግራ አጋባው። መሪጌታ አጠገባቸው ደረሱ። ሰላምም ስታያቸው ወደርሳቸው እየተራመደች ቀጣይ ከፊታቸው ቆማ ለሰላምታ ተሰናዳች። ከምንም የማታወዳድረው የሰላሟ ወደብ እረፍት ከሚሆናት የአባቷ እቅፍ ገባች። ቀጥሎ ሁሉንም በየተራ ሰላም ብለው ኋላ ንፍታሌምን አቀፉት። ከእቅፋቸው ቶሎ አላወጡትም። እርሱም በእቅፋቸው ሆኖ የቅኔውን ጌታ ነቢይ አልያም ባለ ራዕይ እንደ ሆኑ ተሰናብቷቸው ሊሄድ በማለዳ ተነስቶ ሰርግ አለብኝ ውለህ ትሄዳለህ ብለውት የባለቤታቸውን ቀብር ውሎ እንደሄደ አስታውሶ ተደነቀ። "እንዴት ቢወዱት ነው?" እያሉ ሁሉም በንፍታሌም ተደነቁ። " እንግዲህ ሞት ጽዋችን ነች። ሁሉም የሚጎነጫት ሁሉም በጀርባው አዝሏት የሚኖር ምዕራፉ ሲዘጋ ወደ መጣበት ሊመለስ ይገባዋል። ይህን ማንም በምንም ሊለውጠው ሊያስቀረው አይችልም። ስለዚህ እግዚአብሔር ያደረገውን መቃወም ስለማይቻል ተመስገን ነው። ከጁ መልካሙን ተቀብለን ስለ መከራ አናማውም። በደስታችን እግዚአብሔርን ማመስገን። በመከራችን እግዚአብሔርን መፈለግ።
በሁሉም ጊዜ ደግሞ እርሱን ማመን። ያመነ ደግሞ አያጉረመርምም ለምን አይልምና ለቅሶው ይበቃል። እኛም ነገ ወደዚያው ነን። ልጆቼ እናንተም ከሚያዝን ጋር የሚያዝን ዋጋው ብዙ ነውና ከሀዘናችን ተካፋይ ሆናችኋልና ዋጋችሁን እግዚአብሔር ይክፈላችሁ። ኑ ወደ ቤት ግቡ እንግባ" አሉ ልብን በሚያሳርፍ ንግግራቸው። ሁሉም በየተራ ወደ ቤት ገቡና ተቀመጡ። መሪጌታ ገና እንደተቀመጡ ከፊታቸው እረፍታቸውን አጧትና "ተጫወቱ መጣው!" ብለው ወጡ። ሰላም በድንገት ለመጡት እንግዶቿ ስትደክም አባቷ ወደ ልጃቸው ኩሽና ደርሰው "ሰላምዬ!" አሏት ቀና ብላ አየቻቸው። "ወዬ አባዬ!" አለቻቸው በስስት። "እንደው አንቺ ብታርፊና የሚሰራውን ብሰራስ?" አሏት። አሳዘኗት "የኔ ውድ አባት አባይዬ!" ብላ ሄዳ ጥምጥም አለችባቸው። "እውነቴን እኮ ነው!" አሏት ከቅፋቸው እንዳለች። "በል አንተ ሂድ እንግዶቹ ጋር ሁን ምሳ አቅርቤ በጋራ በልተን አርፋለው" አለቻቸውና በስስት እያዩአት "ሰሞኑን አሞሽ ነበርንዴ?" አሏት ከእቅፋቸው እየወጣች ወደ ስራ መለስ ብላ " ኧረ አላመመኝም። ምነው?" አለች ሰላም። "ሞት ለሁሉም የማይቀር ነው ልጄ ጠንከር ልትይ ይገባል። ከእንግዲህ እኛ ወደ እናትሽ እንሄዳለን እንጂ እርሷ ወደ እኛ አትመለስም። ራስሽን አትጉጂ!" ብለዋት ወደ ቤት ተመለሱ። እርሳቸው ሲገቡ ከራሄል ውጪ የነበሩት ሁሉም ከተቀመጡበት ተነስተው ተቀበሏቸው። ራሄል ልጇን ንፍታሌምን ሄዳ ከሰላም መኝታ እያስተኛችው ነበር። አስተኝታው ተመለሰች።

መሪጌታ ስለ ሰላም የነበረ ጭንቀታቸው ለቀናትም ቢሆን በመጡት ሰዎች ምክንያት እንደሚቀንስ ታሰባቸው። "እንደው ልጅ ይዞ ኢኼን ያህል መንገድ መድከማችሁ..." አሉ መሪጌታ። ራሄል "መኪና ስለያዝን ብዙም አይከብድ" ስትላቸው "መኪናዋንም ስመጣ ከመንገድ አየኋት። የናንተው ነች?" አሉ መልሰው። "አዎ የኛው ነች። መንገድ እዚህ ድረስ ስለማያመጣ ነው እዚያ ያቆምናት። እንዲያው ማቆምያ ብናገኝ..." አለ ክብሮም። " እዚያው ትቁም እዚ እንደ ከተማው አይደለም። የኛ አካባቢ ደግሞ በተለይ ልዩ ነው። ምንም አትሆንም። የቆመችበት ጥሩ ቦታ ነው ትሁን!" አሉት። ይህንን አካባቢው ልዩ ነው የሚለውን ከንፍታሌም በተደጋጋሚ ሲሰማው መቶ ተደገመበት። ራሄልም እርሳቸውን ተከትላ "ትቁም እዛው ምንም አትሆንም!" ስትለው ክብሮም በእሺታ አንገቱን ነቀነቀ። "ተኛልሽ አስተኛሽው?" አለች ሰላም ይዛ የገባችውን አስቀምጣ። "አዎ ተኝቷል!" አለች ራሄል። የሁሉም ጆሮ ወደ መሪጌታ አንዳች ልዩ ደስታ ወደ ሚሰጥ ንግግራቸው ነው ጥቂት ሲናገሩ። እርሳቸው ከንፍታሌም ጋር በምስጢራዊው የጥበብ ደጅ በተገኙበት ጊዜ የራሄልን ልጅ ከዚያ አጊኝተውት ስለነበረ ያንን ጊዜ አስታውሰው "ልጅሽ አያስቸግርም መሰል?"አሏት። "አዎ አያስቸግርም!" አለች ራሄል። "አይ ንፍታሌም ተአምረኛ ልጅ ነው ያለሽ!" ሲሏት ከያፌት ውጪ ሁሉም ደነገጡ። በተለይም ራሄል። "ስሙን በምን አወቁት?" አለች በልቧ። ንፍታሌምም "በምን አወቁት?" አለ በውስጡ። ሰንቆ ከመጣው ውስብስብ ነገር ጋር ስለተገናኘበት "ሰላም ነግራቸው ይሆን እንዴ?" እንደዚያ ካልሆነ ግን አንድ ነገር አለ ማለት ነው። ስለዚህ ይኼ የሆነ ፍንጭ ሊያስገኝ ይችላል። ሰላም እጠይቃታለው።" እያለ "በምን አወቁት?" አለችና ያስጨነቀውን ራሄል ተነፈሰችለት። "እረስተሽኝ ኖሯል ሰላም ጋር የመጣሁ ጊዜ ተገናኝተን ነበርኮ" አሏት አውቅሻለው ለማለት ያክል። ለሌሎቹ የት አወቁ ለሚለው ሙሉ መልስ ሲያገኙ ሰላም ግን "ታዲያ ያኔ ስሙ ንፍታሌም አይደል በቃ ሰላም ነግራቸው ነው" አለችና ተወችው። ንፍታሌም ግን እንደዋዛ እንዳይተወው የዚህ ሕጻን አስቀድሞ ምስጢር የሆነበት ነገር ላይ ሌላ ጥያቄ ፈጠረበት "ሳያዩት በምን አወቁት?" ኢሄንን እና ሌላውንም ስለ 💢ህቡዕ ገጽም💢 በአዋሽ ቆይታው የተቻለውን ሁሉ አድርጎ ለማወቅ በውስጡ እቅድ ያቅድ ጀመር። ከመሪጌታ ምን በምን በኩል እንደሚያገኝ። ያ የጥበብ ደጅ ከሕጻኑ ጋር የተገናኙበት ምሥጢራዊ ምስጢር ስፍራ የት ነው? የሚለውን ለብዙ ጥያቄዎቹ መልስ ሲፈልግ እንደሚከርም የልዩዋን ምስል ምስጢር እና ሁሉንም ፍለጋ ራሱን አሰናዳ።

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ታኅሳስ 8 2018 ዓ.ም ባሌ ጎባ 💢
🌄🌅🌌 ህቡዕ ገጽ 🌌🌅🌄

     🌄🌓👤 ህቡዕ ገጽ 👤🌓🌄

  🌄🌓👤 ክፍል 285 👤🌓🌄

የኢትዮጵያዊው ጻድቅ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የደብረ ሊባኖስ ታላቅ ገዳም በኢትዮጵያ ብቻ ያይደለ በልዩ ልዩ አህጉራተ ዓለም የታወቀ የበረከት ቦታ ነው። ጻድቁም እንዲሁ ናቸው ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ሁሉ የሚታወቁ የክርስቶስ ወታደር የወንጌል ገበሬ ናቸው። በኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ወንጌልን ያስተማሩ ናቸው። ገዳማቸው በተለያየ ስፍራ የሚገኝ ሲሆን በኩሩ ግን ደብረ ሊባኖስ ነው። ኢሄ ገዳም የበረከት ስፍራ ነው። የቃልኪዳን ስፍራ። ከቃልኪዳኑም ኢሄ ብዙዎችን የሚያስደንቅ ነው። "እንኳን ሰው መሬቱ ፆም አያድርም" ተብሎ ለገዳሙ ልዩ ቃል ኪዳን ስላለው እንኳን ሰው መሬቱ እንኳ ጦሙን አያድርም። ሰው ሳይቀበርበት እንደማያድር ሲነገር ማመን ይቸግራል። ግን እውነቱ ይህ ነው። በደብረ ሊባኖስ ደምቃ የዋለችው ፀሐይ ከቀኑ ጋር ተደምራ በዚያ ገዳም ለነበሩት ሁሉ ልዩ ቀን ነበረች። ምክንያቱም ዛሬ ማርያም ነች። በደብረ ሊባኖስ የእመቤታችን የወራዊ በዓልም ቢሆን ድምቀቱ ልዩ ነው። በዚያ ያለ ሁሉ ከዚህ ልምድ የተነሳ "ዛሬ እመቤቴ ነች ልዩ ቀን" ማለት የተለመደ ነውና የዛሬዋ 21 እንደ ወትሮው ሁሉ ተወዳጅ እና ለሁሉም ልዩ ቀን ሆና ደምቃ ዋለች። ቀኗን ልዩ የሚያደርግ አንድ ነገር ግን ታየ። የቦታው ቃል ኪዳን ሲጠበቅ ፀሐይ አዘቀዘቀች። "እንዴ ዛሬ ምንም ለቅሶ አልሰማውም ነው ሳላውቅ የተቀበረ ኖሯል?" የሚል "አባ አገሌ ለቀስተኞች ዛሬ ነበሩ?" ይላል ሌላው " እማሆይ ዛሬ ምንም የለቅሶ ድምጽ አልሰማው። ለቅሶ ሰምተዋል?" ደግሞ ሌላ ጥያቄ። "አባ ቀብር ነበር እንዴ ዛሬ?" ደግሞ ሌላው። "እንዴ ዛሬ መሬቷ ጦሟን ልታድር ነው እንዴ?" ይባባላሉ ቆሎ ተማሪዎች። ቀኑ እየመሻሸ ነው። ብዙ ሰው ጋር ብዙ ጥያቄ። ሁሉም የሆነ ነገር የጎደለ ያክል ቅርቅር እያለው "ምንድነው ዛሬ?" ይባባል ጀምሯል። መቃብሩ አካባቢ ያሉት "እንዴ!" እያሉ አስሬ ሰዓታቸውን የሚያዩም ነበሩ። ተጨንቀው አስሬ ሰዓታቸውን ሲያዩ ሙሽራ የሚጠብቅ ሰርገኛ ነው የሚመስሉት። "በቃ ዛሬማ ጉድ ልንል ነው!" ይባባላሉ። "እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑ አይታጠፍም" ይላል መላሽ። "እንዴ ከእንግዲህ? መሸኮ። እንዲህ ሆኖም አያውቅ" ይላል ጠያቂ። ሰዓቱ ለ 12 ሃያ ጉዳይ ሲሆን የለቅሶ ድምጽ በገዳሙ ከአንዱ አቅጣጫ ተሰማ። " ምንድነው? ምን ተፈጠረ?" ሩጫ ጥያቄ በረከተ። ቤዛ ከነበረችበት ገዳም አምላኳን ፍለጋ የአባቶቿን መንገድ ይዛ ስትወጣ ስትጓዝ እርሷን መስለው የወጡት እናቷ ደግሞ በሚወዷት ቀን አሰቀድሰው ከምስጢር ተካፍለው ያለ ህመም ያለ ጣር ካረፉበት ስፍራ ጋደም እንዳሉ እረፍታቸው ሆነ። እርቀው ወደ ሚናፍቁት ተጓዙ። እናቴን አልለይም ብሎ ተከትሏቸው የመጣው ልጃቸው ነበር እናቴን እያለ ሲያለቅስ የሚያውቋቸው ተጨምረው ለቅሶ ሲሰማ የነበረው። የቤዛ እናት ከገዳሙ የነበራቸው ቆይታ በመልካም ጉዞ እነሆ ተቋጨ። ካረፋበት "ምናልባትም ስሞት ዘመድ ጥበቃ ምን ሳይባል እለቱኑ ሸኙኝ" ብለው በተናዘዙት መሰረት በሚገባው ስርዓት የቤዛ እናት እኚያ ስመ ጥር እንግዳ ተቀባይ የተራበ የሚያበሉ ለሁሉ እናት የተባሉ ሰው አንድም ዘመድ በሌለበት በዚያች ቀን ስረዓተ ቀብራቸው ወንድ ልጃቸው ከዘመድ ዘመድ ተክቶ ባለበት ተፈጸመ። "ለካ ከቅርቡ የሚሸኝ ኖሮ ነው ቀኑ የገፋው እንጂ የእግዚአብሔር ቃሉ አይታጠፍም። እውነትም ጦም አታድርም የደብረ ሊባኖስ መሬት" አሉ አንዳንዶች። "እምብዛም አልቆዩም ያላቸውን ሸጠው ለምናኔ ወደ ገዳሙ ከወንድ ልጃቸው ጋር ነው የመጡት አሉ" ተባለ። ሌሎችም በዝና የሚያውቋቸው "ኧረ እርሳቸው ቀድመውም መንነዋል። በቤታቸው የማይስተናገድ ደሀ የለም ነው የሚባለው። ሕይወታቸው አብረሃማዊ ነው አሉ" ይላሉ። ያቲ ደምቃ የዋለች ፀሐይ ለቤዛ ወንድም ስትጠልቅ ለጨለማ ተወችው።

ሀዘኑን መቋቋም እጅግ ከበደው በአጭር ጊዜ ካረፈበት ስፍራ እንዳለ አስደንጋጭ የአካል ለውጥ ታየበት በጣም ከሳ። መታመም ጀመረ። በገዳሙ ያውቁት የነበሩ እናቱን የሚያውቋቸው ሊያጽናኑት ሲመጡ አብዝተው ያዝኑ ነበር። የሰሙ ዘመዶች ከሩቅም ከቅርብም እየመጡ መጠየቅ ጀመሩ። ሲመጡ ከስቶ ጠቁሮ ሲያዩት በመደናገጥ ወስደውት ከራሳቸው ጋር አኑረው ሊያስታምሙት ጥያቄ ቢያቀርቡም ፈቃደኛ ሊሆን ባለመቻሉ የሁሉም ተግባራቸው አዝነው አልቅሰው ጠይቀው መመለስ ብቻ ሆነ። የብሌን እናትም የእታቸውን ሞት የሰሙት በሳምንቱ ነበር እህታቸውን ያለ መቅበራቸው የእግር እሳት እንደሆነባቸው ውለው ሳያድሩ ብሌንን አስከትለው ወ/ሮ ፈትለወርቅ ወደ ደብረ ሊባኖስ ከነፉ። ደርሰው አጠያይቀው ከመቃብራቸው "ወየው እታለም ወየው እቴትዬ!" እያሉ እርማቸውን ከልጃቸው ጋር አውጥተው ቀጥሎ የእህታቸው ልጅ ያለበትን ሰው አጠያይቀው ካለበት ሄዱ። ከእህታቸው መቃብር ላይ እዬዬ ካሉት በላይ በዚያ እንባቸውን ካፈሰሱት በላይ ታሞ የተኛ መልኩ የጠቆረ ፊቱ ሌላ መልኩ ሌላ የመሰለውን የእህታቸውን ልጅ አይተው ምርር ብለው አለቀሱ። የነበሩ ሊጠይቁ የመጡ ሰዎች አጽናንተዋቸው በብዙ ድካም ማልቀስ አቆሙ። ብሌንም የአክስቷን ልጅ መታመም አይታ አዝና አለቀሰች። "ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሲሆን አትደውልም ነበር?" አሉት ፈትለወርቅ "ያረፈችው ከመሻሸ ነበር አታሳድሩኝ ዘመድ አትጠብቁ ብላ ተናዛ ስለነበር ቢደወልም አይደረስም" አለ ድምጹ እየተቆራረጠ። ከዚያ ሲያወራ ጋብ ያለለት ሳል ተቀሰቀሰ። ሳሉ የከበደ ስለነበር ።ም ሲተፋ ሲያዩት ፈትለወርቅና ልጃቸው ብሌን እንደገና እንባቸው ይወርድ ጀመር። ወ/ሮ ፈትለወርቅ "በጣም ነው የተጎዳኸው እዚህ ለህክምናም አዳጋች ነው። አሁን ነገ አብረን ወደ አዲስ አበባ ሄደን እዚያ ወንድም ጥላ ጋር ሆነህ ህክምና መከታተል አለብህ" አሉ እንባቸውን እየዘሩ። እርሱ ግን አሻፈረኝ አለ። ወ/ሮ ፈትለወርቅና ልጃቸው ሁለት ቀን ቆይተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው እግረ መንገዳቸውን ዘመድ ጥየቃ ሰነበቱ። በየሄዱበት የብሌን ቀበጥነት ተስተካክሎ የሚያስደንቅ ግብረ ገብነት ተላብሳ መታየቷ የሚደነቅ ሆነ። የርሷ ሲነሳጰወሬው ሁሉ ዞሮ ዞሮ ቤዛን የሚያነሳ የቤዛን እናት ድንገተኛ ምናኔና ሞት የልጃቸውን በከባድ ህመም ውስጥ መገኘት የሚያወሳ ሆኖ ሰነበተ። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ለጥየቃ በየዘመዳቸው ሲዞሩ ይኼ የወሬ ዑደት እንዲህ ቀናትን አስቆጠረ። ሲወራ ሰንብቶ ከሚወራበት አንዱ ተወናይ ታማሚው በአልጋ የሰነበተው ሕመም የረታው ወጣት እናቱ በአረፉ በአስራ አምስተኛው ቀን አረፈ። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠይቀውት ሲመለሱ አንድ የቆሎ ተማሪ ተዋውቀው "እንደው የከፋ ነገር ቢፈጠር እንኳን....መቼም ሰው ካልታከመ ሞት ነው። ቢብስበት እንኳ ደውለ ንገረኝ አደራ" ብለው ስልክ የተለዋወጡት ተማሪ ደውሎላቸው ቤተዘመድ ተሰባስቦ ከቀብር ደረሰና በቲኒሽ ቀናት ልዩነት በብዙ ለቅሶ የርሱም ስረዓተ ቀብር ተፈጸመ። ያን እለት ቤተዘመዱ ሟችን ቀብረው ስለ እናቱ አንብተው ስለ ቤዛም እንቆቅልሽ የማይፈታ ሕይወቷን ተንብየው እያዘኑ ሁሉም ወደ መጡበት ተበተነ። ከቤዛ በቀር እናትና ወንድሟ ከእንግዲህ ላይገኙ ከማንም ላይገናኙ ምዕራፋቸው በሞት ተዘጋ።

🌓 ይቀጥላል 🌓
💢ታኅሳስ 10 2018 ዓ.ም ባሌ ሮቤ 💢