የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
Channel created
​የከንቲባው ልጅ

ክፍል 1


.
.
:- እውነተኛ ታሪክ ነው!
.
.
እለተ ረቡዕ : ሚያዚያ 30, 2011 ዓ.ም ፡ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፡ 11:00 ሰዓት አካባቢ ከሶስቱ የጊቢው በሮች ታዋቂ በሆነው በቶኒ በር ስፖርት ቤት ለመሄድ እየወጣሁ ነው ። ስፖርተኛ አይደለሁም ፡ ሰሞኑን እየተሰጠኝ ባለው አስተያየት ምክንያት መከራ እያየሁ ያለሁ ሚስኪን የ #2ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ እንጂ ። ሰው እንዴት ሳይጠየቅ comment ይሰጣል ...? ስትወፍር ፡ ምን አገኘህ ደግሞ ...? እያለ ያሽሟጥጣል ። ስትከሳ ፡ ጎዶሎህን ይሞላ ይመስል ምን ጎደለህ ደግሞ ...? ይልሀል ። ምንም ነገር ብትሆን የሰው ልጅ comment ከመስጠት ወደ ዋላ አይልም ። ምን አለበት Like ብቻ አርጎ ቢቀየስ ። ሰሞኑን "ምነው ከሳክ" ብሎ ያልጠየቀኝ ሰው ካለ ለዘላለም ይኑር ፣ የተባረከም ይሁን ። በነሱ አይን ምከንያት እነደከሳሁ ማን በነገራቸው ። እኔማ የሰው አይን እና አስተያየት ሲበዛብኝ ፈርቼ ንሰሐ ገባሁ ። (አቤት ውሸት ...) አንዳንዴማ አይናቸው ተጎልጉሎ እስኪወጣ ድረስ ስለሚያዩኝ አካሄድ እራሱ ይጠፋብኛል ። (ውይ ማጋነን ስንወድ ግን ...) የሆነ ቀን ብልጭ አለብኝና ፡ ለምን ስፖርት አልጀምርም ብዬ ከራሴ ጋር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስብሰባ ተቀመጥኩ ። ውሳኔውም ፡ በርታ ፣ ጠንክር ፣ አይዞህ ፣ ከጎንህ ነን ጀምር የሚል ነበር ። ለዚህም ውሳኔ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል ። (አቤት መበጥረቅ...) ይኸው ጠንክሬ ተፍ ተፍ ማለት ከጀመርኩ ቀናቶች እየተቆጠሩ ነው ። ወደ ስፖርት ቤቱ እያቀናሁ እያለ ፡ ፊትለፊት መንገድ ላይ በኔ street በጣም የምታምር የቤት መኪና መጣች ። መንገድ ልልቀቅ ብዬ ትንሽ ወደ ጫፍ ፈቀቅ አልኩኝ ። መኪናዋ ግን እኔ ወደ ሄድኩበት ቦታ መጥታ ጭራሽ እግሬ ስር ደርሳ ቆመች ። በሁኔታው በጣም ተናድጃለው ፤ በዛላይ ተደናግጫለሁ ። የመኪናው ሞተር ሲጠፋ ይሰማኛል ። ወዲያው ከመኪናው ውስጥ በግምት በኔ እድሜ የምትገኝ በጣሙን የምታምር ልጅ ወርዳ ፊትለፊቴ ቆመች ። አይኔ ሲደነግጥ ፡ ልቤ በምት ሲያጅበው ፡ ያስታውቅብኝ ነበር ። መኪናዋን በአይኔ ቃኝቼ ብቻዋን እንደሆነች አረጋግጫለሁ ። አይን አይኔን ካየች በዋላ እስኪጨንቀኝ ጥብቅ አርጋ አቀፈችኝ ። ያልጠበኩት ስለነበር "የኔ እህት ፡ ችግር አለ ...? ሰው ተሳስተሽ እንዳይሆን" ስላት በድጋሜ አየችኝ እና ጭራሽ ጉንጬን ሳመችኝ ። በድርጊቷ ስለተገረምኩኝ ፡ ይቺ ልጅ ግን ጤነኛ ነች ...? እያልኩኝ ልብ ብዬ ማየት ጀመርኩ ። ደግሞኮ ከዛሬ ውጪ አይቻት አላውቅም ። ቀጥላ በእጆቿ እጆቼን ስትይዘኝ ፡ በቃ ይቺ ልጅ እኔን የሚመስል ፍቅረኛ አላት ብዬ አሰብኩ ። አይኖቿ ውስጥ የሚታየኝ የፍቅር ስሜት አይኔ ውስጥ ገብቶ እምባዬን አመጣው ። ሚስኪን ነገር ትመስላለች ። ቢሆንም ግን እጄን ለማላቀቅ ሞከርኩኝ ፡ እሷ ግን ይበልጥ ግጥም አርጋ ያዘችኝ ። ግራ ሲገባኝ ፡ ይሄ ነገር prank ነው እንዴ ...? ብዬ ካሜራ ለማፈላለግ በአንገቴ ዞር ዞር አልኩኝ ። ሰፈሩ ግን ያለወትሮው ጭር ብሎ ስለነበር ማንም አልነበረም ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ፡ ግን በጣም ጨንቆኛል ። እሷ እስካሁን አፍ አውጥታ አልተናገረችም ፡ ካይኔ ላይ ግን አይኗን ለሴኮንድ እንኳን አልነቀለችም ።
እጆቼ በእጆቿ እንደታሰሩ ፡ አይኖቼ ካይኖቿ እንደተፋጠጡ ፡ ስሜቶቿ ጭምር ሰውነቴን ሙሉ እንደወረሩ ፡ ሁለታችንም ግትር ብለን ከቆምን ብዙ ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። እንደ ዛሬ ሲጨንቀኝ ትዝ አይለኝም ። ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሏል ። አንደኛው ፡ 'ይሄ ነገር አላማረኝም ፡ እንደምንም ብለህ ብታመልጣት ይሻልሃል' በሚለው እና 'ግዴለህም ማውራቷ አይቀርም ፡ ትንሽ ብቻ ታገስ' በሚለው መሀከል ። ምን ቀን ይሁን በዚህ ሰፈር እንዳልፍ የፈረደብኝ ...? እጆቼን ከእጆቿ በጉልበት መንትፌ መሮጥ አልከበደኝም ። ግን ምን ሆና እነደሆነ ማወቅ ስለፈለኩ ነው ። ማንኛውም ጤነኛ ሰው መንገድ ላይ የማያውቀውን ሰው ፡ የሆነ ነገር ካልሆነ በስተቀር መቼም እንዲህ አያደርግም ። ልጅቷም የሆነ ነገር ብትሆን እንጂ ፡ ከመሬት ተነስታ ፡ በሰላም ሀገር ለምን እነዲህ ታስጨንቀኛለች ...? መፋጠጡ ሲደክመኝ ፡ 'የኔ እህት ፡ ስምሽ ማነው ...? እንተዋወቃለን ወይ ...? ከኔ ምንድነው የምትፈልጊው ...?' የሚሉትን ጥያቄዎች አከታትዬ አቀረብኩላት ። የደነገጠች ትመስላለች ፤ እንደውም ከፊቷ ላይ ያነበብኩት ነገር ቢኖር ፡ "እንዴት እንዲህ ትለኛለህ ...? ስንቱን አብረን እንዳላሳለፍን ...?" አይነት ነበር ። እስካሁን አፏ አልተከፈተም ፡ ነገረ ስራዋ ሁሉ ግን ፍቅረኛዋ እንደሆንኩ አይነት ሆነብኝ ። አንዴ ስታቅፈኝ ፣ አንዴ ስትስመኝ ፣ ከዛን ጉንጬን ስትዳብሰኝ ፣ ሌላ ጊዜ ሸሚዜን ስታስተካክልልኝ ፣ አይን አይኔን በፍቅር ስትመለከተኝ ፣ በቃ ባጠቃላይ ኤሊፍ ለኦማር የምትሆነውን እየሆነችልኝ ነው ። እኔ ደግሞ በጭንቀት ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም ። እስካሁን ስላልተነፈሰች ፡ 'ይቺ ልጅ ማውራት ስለማትችል ፡ ፍቅሯን በ acting እየገለፀችልኝ ይሁን እንዴ ...?' እያልኩ አሰብኩ ። ብቻ ምን ያላሰብኩት አለ ...? እሷ ግን እኔን በማግኘቷ ደስ ያላት ትመስላለች ። ልክ የእናቱን ጡት እንዳገኘ ጨቅላ ህፃን እያየችኝ ትቦርቃለች ። በማላውቀው ነገር ፡ ከማላውቃት ልጅ ጋር ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ #10 ደቂቃ በላይ ፡ ለዚያውም ድምጿን ሳልሰማ ቆምኩኝ ። ዝምታዋ አስፈራኝ ፡ ብታሳዝነኝም ምንም ማድረግ ስላልቻልኩኝ ፡ 'በቃ የኔ እህት ፡ ሰዓት ረፍዶብኛል ፡ መሄድ አለብኝ" አልኳት እና እጆቼን ከእጆቿ እንደምንም አላቅቄ ፡ አንድ እርምጃ ሳነሳ ፡ ይሄን ሁሉ ደቂቃ ሳታሰማኝ የቆየችውን ድምጿን እንደ ቴዲ አፍሮ አልበም ልክ በቃ ይሄ ሰውዬ ሙዚቃ አቁሞ ገዳም ገብቷል ብለን ተስፋ ስንቆርጥ እንደሚያሰማን እሷም በስተመጨረሻ ያንን ሰምቼውም ማላውቀውን ድምጿን ተስፋ ቆርጬ ስሄድ አሰማችኝ ። እውነት ለመናገር ድምጿን ስሰማ ልቤ ለሁለት ነበር የተሰነጠቀው ። በጣም በሚያሳዝን እና ልብን በሚነካ ዜማ "ጥለኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" አለችኝ ። ዞር ብዬ ሳያት እምባዋ ከነዚያ ፀሀይ ከሚመስሉ አይኖቿ ፡ እንደ ዶፍ ዝናብ እየወረዱ ነው ። አማራጭ አልነበረኝም ፡ ያነሳሁትን አንድ እርምጃ ወደ ቦታው መልሼ እቅፌ ውስጥ ሸጎጥኳት ። እንደውም ቅድም እሷ ካስጨነቀችኝ በላይ ነው እቅፍ አድርጌ ያስጨነኳት ።
ለ አስተያየት @babusem
✎ ክፍል ሁለት በኋላ ይለቀቃል....
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል................
​የከንቲባው ልጅ

ክፍል 2


.
.
.
.
እቅፌ ውስጥ ሆና ስታለቅስ ደረቴ ላይ እምባዋ እንደ ጅረት ይፈስ ነበር ። የሷ እንደዛ ማልቀስ ሲገርመኝ ፡ የኔም እምባ ከየት መጣህ ሳይባል ጀርባዋ ላይ ዱብ ዱብ እያለ አጃዒብ አስባለኝ ። ቃል ሳታወጣ ስሜት ማጋባት ትችልበታለች ። በጣም እንደተጎዳች ታስታውቃለች ። ችግሩ ግን የማይሆን ሰው ላይ መውደቋ ነው ። እኔ እንኳን የሰውን ችግር ልቀርፍ ይቅርና ፡ የራሴንም የራሱ ጉዳይ ብዬ የተውኩ ሰው ነኝ ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ፤ ብቻ እንደ ተቃቀፍን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። በኔ ፍቃድ ተላቀቅንና 'እሺ እቤት ላድርስሽ ...? የት ነው መሄድ የምትፈልጊው ...?' ስላት ፡ "ብቻዬን እዛ ቤት መሄድ አልፈልግም" አለችኝ እና ድጋሜ እቅፌ ውስጥ ገብታ ማልቀስ ጀመረች ። አሳዘነችኝ እና ድንገት ሳላስበው 'አያሳስብም ፡ አብረን እንሄዳለን' አልኳት ። "ያሉት ከሚጠፋ ..." ። መኪናዋ ውስጥ ገብተን ፡ መሪውን ወደ ዋላ አዙራ ፡ ሄጄ ወደ ማላውቅበት ሰፈር ወሰደችኝ ። ድሬዳዋ ከመጣሁ በዚህ በ2 ዓመት ውስጥ ፡ እንደዚህ አይነት ቤቶችን አይቼም አላውቅም ። ሲመስለኝ የሀብታሞች ወይንም የባለስልጣናት ሰፈር ይመስለኛል ። ይህን ሰፈር አልፈን ትንሽ ደቂቃ እንደሄድን ፡ ጭር ያለና ብዙም ሰው የሌለበት ፡ በዛላይ ምንም ሰፈር የሌለበት ቦታ ደረስን ። ግን መኪናው ውስጥ ሆኜ አንድ ቤት ይታየኛል ። መኪናውን በሩ ፊትለፊት አቁማ ፡ "ደርሰናል ፡ እንውረድ" አለችኝ ። የቤቱ አሰራር ኢትዮጵያ ውስጥ ካየዋቸው ለየት ያለና ያልተለመደ አይነት ነበር ። ጥበቃ የለውም መሰለኝ ፡ እራሷ የውጪውን በር ከፍታ ፡ መኪናዋን ጊቢ ውስጥ አቆመች ። እየመሸ ስለሆነ ብዙ ነገሩ እንደ ልብ አይታይም ። "ና ፡ አትፍራ ፡ እንደ ቤትህ እየው" ስትለኝ ፡ በልቤ ውስጥ 'አሜን' አልኩኝ ። እንደዚህ አይነት ቤት ስገባ የመጀመሪያዬ ነው ። ማን ያውቃል ምናልባትም የመጨረሻዬም ሊሆን ይችላል ። ወደ ሳሎን ቤቱ መራችኝና ሶፋ ላይ እንድቀመጥ በእጇ ጋበዘችኝ ። "ሚጠጣ ምን ላምጣልህ ...?" ብላኝ ፍሪጅ ከፈተች ። አይኔ በቅድሚያ ፍሪጁ ውስጥ ወዳለው ቢራ ላይ ቢያርፍም ፡ ጨዋ ለመሆን ያክል ፡ 'ኮካ አርጊልኝ' አልኳት ። ለኔም ለራሷም ኮካኮላ ከፍታ ፡ ፊትለፊቴ ባለው ሶፋ ላይ ተቀመጠች ። በሁኔታው ግራ እንደተጋባሁ ስለተረዳች ፡ በራሷ ተነሳሽነት ታሪኳን እና ቅድም እኔላይ ስላሳየችው ነገሮች ልትነግረኝ ተዘጋጀች ። "እየውልህ የኔ ወንድም ፡ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም ነገር በጣም ይቅርታ እሺ ፤ ስሜታዊ ሆኜ ስለነበር ነው ። በዛላይ የት መሄድ እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ በገባኝበት ሰዓት ነው አንተን በመኪናዬ ውስጥ ያየሁክ" ብላ ታሪኳን ጀመረች ። "እናቴን አይቻት አላውቅም ፡ ያኔ ገና ስወለድ ነበር ያጣዋት ። የኔ ህይወት እንዲተርፍ ፡ የሷ ማለፍ ነበረበት ። ያኔ እንዳሁኑ በየቦታው ሆስፒታሎች ከመሠራታቸው በፊት ብዙም አልነበሩም ። እኔ ስወለድ እናቴን ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር ፡ በአቅራቢያው ደግሞ ጤና ጣቢያ ስላልነበር ፡ በፈሰሳት ብዙ ደም ምክንያት አቅም አጥታ ህይወቷ አለፈ ። ብዙዎች አግኝተው ነው የሚያጡት ። እነደኔ አይነቱ እድለ ቢስ ግን ሳያገኝ ያጣል ። እናቴ ህይወቷን ሰውታ ህይወት ስለሰጠችኝ ፡ አባቴ ህይወት ብሎ ስም አወጣልኝ ። እስካሁን አልተዋወቅንም አይደል ...? ህይወት እባላለሁ" አለችኝ እና እጇን ለትውውቅ ዘረጋችልኝ ።
'ተስፋዬ እባላለሁ' አልኳት የዘረጋችልኝን እጅ እየጨበጥኩ ። ታሪኳን ቀጠለች ፡ "አባቴ ነው ያሳደገኝ ፡ የሚገርምህ እናት እንደሌለኝ ተሰምቶኝ አያውቅም ። እንደ እናትም ፣ እንደ አባትም ፣ ሆኖ ብቻውን ያሳደገኝ እሱ ነው ። አባቴ እንደ አባት ብቻ አይደለም ፡ እንደ ጓደኛም ጭምር ሆኖ ነው አብረን የኖርነው ። ከ 1 ነገር ውጪ አንድም ነገር ከልክሎኝ እና አጉድሎብኝ አያውቅም ። በነገራችን ላይ አባቴ ባለሥልጣን ነው ፡ ያውም የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ" ስትለኝ በሆዴ 'በቃ ተስፍሼ ቁርጥህን አወቅ ፡ ነገ ወይ ከርቸሌ ፡ ወይ ሲኦል ገብተሃል' አልኩኝ ። ስታወራ አይን አይኔን እያየች ስለነበር እንደፈራሁ ገብቷት ፡ "አይዞህ አትጨናነቅ ፡ አባቴ እነደምታስበው አስፈሪ እና ቁጡ ሰው አይደለም ፤ በተቃራኒው ደግ እና አዛኝ ነው ። ደግሞም ለጊዜው ሀገር ውስጥ ስለሌለ ማንም እዚህ ቤት አይመጣም ፈታ በል"። ስትለኝ ትንሽም ቢሆን ተረጋጋሁ እና ታሪኳን እንድትቀጥልልኝ በአይኔ ምልክት ሰጠዋት ። "እንዳልኩህ አባቴ የከተማችን ከንቲባ ነው ። በዚህም ምክንያት ብዙ ችግሮች እየደረሱበት ነው ። ለጊዜው የሱን እንተወውና የኔን ጥቂት ልንገርህ ። "እስካሁን ድረስ አባቴ ስልጣን ላይ ከወጣ በዋላ ያየሁት ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ጓደኛም የለም ። ከአባቴ ውጪ ቀርቤ የማውቀው ሰው የለኝም ። ብዙ ጊዜ ከቤት ስለማልወጣ ሰውን በአካል ሳይሆን በቴሌቪዥን ነው የማየው ። በአጭሩ በብቸኝነት የምሰቃይ ሴት ነኝ ። ከአባቴ ጋር ከቅዳሜ ምሽት እስከ እሁድ ሙሉ ቀን አብረን እናሳልፋለን ። ከዚያ ውጪ ግን አምስቱንም ቀናት ስራ ላይ ነው የሚያሳልፈው ። አልፎ አልፎ ደህንነቴን ለማወቅ ካልሆነ በስተቀር እዚህ አይመጣም ። በስልክ ግን በየሰዓቱ እናወራለን ማለት ይቻላል ። ቢያንስ በቀን #5 ጊዜ እንደዋወላለን ። ሰሞኑን ግን ምን እንደሆነብኝ እንጃ ከደወለልኝ ድፍን #3 ቀን ሞላው ። አሜሪካን ሀገር አስተካክዬ የምመጣው ነገር አለኝ ብሎ ነበር ከ #5 ቀን በፊት የሄደው ። የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ቀናት ደውሎልኝ በሰላም አውርተን ነበር ። ከዛ በዋላ ግን ስለሱ የማውቀው ምንም ነገር የለም ። በዚህ ጉዳይ በጣም ስለተጨነኩ እና ቤቱ ያለወትሮው ሊበላኝ ስለደረሰ ነበር ከዚህ ቤት ለመውጣት ያሰብኩት ። ግን የት መሄድና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ። በዛ መሀል ነበር አንተን በመኪናዬ ውስጥ ያየሁክ ። ሳይክ በቃ ፡ ዘመዴን ያገኘሁ ነበር የመሰለኝ ። ለዛም ነው ቅድም እንደዛ ያለቀስኩብህ ። ብቻዬን እዚህ ቤት ውስጥ ያሳለፍኩትን የብቸኝነት ስቃይ ከኔና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅም ። በቲቪ ብዙ ፊልሞችን ሳይ ነፃነታቸውን አይቼ እቀናባቸዋለው ። አባቴ በስራው ምከንያት ስለሚጠነቀቅልኝ ፡ ሰራተኛም ፣ ጥበቃም የለንም ። ከሱ ውጪ ይሄን ቤት የሚያውቀው ሰው ያለም አይመስለኝም ። በተረፈ መኪና መንዳት እና ምግብ ማብሰል አባቴ በስርዓት አስተምሮኛል ። ሲጀምር ብዙም የምግብ ፍላጎት ስለሌለኝ ያን ያክል አያስጨንቀኝም ። ስራዬ ሁሉ ቲቪ ማየት ፣ መፅሐፍ ማንበብ እና መተኛት ብቻ ነው ። ይሄ ሁሉ የሆነው እንግዲህ የዛሬ #4 ዓመት አካባቢ ልክ አባቴ ወደ ስልጣን እንደመጣ ነው ። ትምህርቴንም አቋርጫለሁ ፤ አሁን እንደምታየኝ በልጅነቴ የቤት እመቤት ሆኜ ቀርቻለሁ" ። ብላኝ በድንገት ከሶፋው ላይ ብድግ አለች ።

✎ ለአስተያየት @babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 3

.
.
.
እንደዛ ተስፈንጥራ በቁጭት እና ንዴት ከመነሳቷ በፊት ፡ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን ኮካችንን እየተጎነጨን ፡ እሷ አይን አይኔን እያየች እያወራች ፡ እኔ ደግሞ አፌን ከፍቼ እያዳመጥኳት ነበር ። ተነስታ ቤት ውስጥ ወደዛ ወደዚህ ስትል አይኔ ፊትለፊቷ ወደተሰቀለው የግድግዳ ሰዓት ላይ አረፈ ። አናቱ ላይ በትክክል መገመት ባልችልም #02:05 አካባቢ ይላል ። እሷ ቅድም ከተስፈነጠረችው በላይ ነበር ደንግጬ ከሶፋው ላይ የተነሳሁት ። 'በቃ እኔ ልሂድ ፡ ሰዓቱ ሳላስበው በጣም ሄዷል ፡ ባይሆን ሌላ ቀን አገኝሻለው' ብያት ወደ በሩ ሳቀና ፊትለፊቴ ቀድማኝ ፡ በሩን ተደግፋ አትሂድ የሚል ፊቷን አሳየችኝ ። "ዛሬን ብቻ እዚህ ቤት ብታድር ትሞታለህ ...? ፡ እእእ ፡ ንገረኛ ...? በዛላይ መሽቷል ፡ በዚህ ሰዓት መሄድ ላንተም ጥሩ አይደለም" አለችኝ ። ብቻ ልጅቷ ሆዴን በልታዋለች ። ወድጄም ባይሆን ለማደር ወስኛለሁ ። ሲጀመር በዚህ ሰዓት ብቻዬን ወደ ግቢ ልመለስ ነው ወይንስ ልጅቷን ፡ 'እንዳመጣሽኝ ወደ ቦታው መልሺኝ' ልላት ነው ...! ሆኖም ግን ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም ። የማላውቀው ሰፈር ፣ የማላውቀው ቤት ፣ ከማላውቃት ልጅ ጋር ...! ብቻ ደስ አይልም ። "ቆንጆ እራት ሰርቼ ፡ አብረን እንበላለን እሺ...! እስከዛ እንዳይደብርህ TV እያየህ ጠብቀኝ" አለችኝና ኩሺና ገባች ። የምወደውን ebs ቲቪ እያየሁ ጠበኳት ። እራቱም ቀረበና አጭር ፀሎት ተደረገ ። ከዛን ለራሷ ሳትጎርስ ፡ እኔን ልታጎርስ ምግብ የጠቀለለ እጇን ወደ አፌ ዘረጋች ። ሁኔታው ግር ቢለኝም እያመነታሁ ጎረስኩላት ። ቀጥላ "ከአባቴ ጋር ስንበላ መጀመሪያ ተጎራርሰን ነው" ስትለኝ ፡ እኔም የቤቱን ስርዓት ለማስቀጠል ብዬ ለራሴ ያዘጋጀሁትን ጥቅልል እንጀራ ወደ አፏ ሰደድሁ ። እውነት ለመናገር የሰራችው ምግብ ከነ ጣቷ ብሉኝ ብሉኝ ይላል ። ለጨዋታ ያህል ፡ 'አንቺ ፡ እውነትም የቤት እመቤት አይደለሽ እንዴ ...?' አልኳት ። ቅር አላላትም ፡ እንደውም "ሙት እሺ" አለችኝና በግራ እጇ ፡ እንዳልጎዳ በማሰብ ትከሻዬን መታችኝ ። እራታችንን በልተን ጨርሰን ፡ ከምግብ ጠረጴዛ ወደ ሶፋው ተመለስን ። ቲቪውን ለማየት እንዲያመቸን ፡ ሁለታችንም ከቲቪው ፊትለፊት ባለው ሶፋ ላይ ተቀምጠናል ። ሀሳባችንን እርግፍ አርገን ትተናል ። ብቻ እየተጫወትን ፡ እየተሳሳቅን ነው ። የምሽቱን ፀጥታ በሳቋ አድምቃለች ። ስቃ አታውቅም መሠለኝ ፡ ስትስቅ አታባራም ። ደግሞ ስትስቅ ደረቴ ላይ ልጥፍ ትላለች ። ኮስተር ማለት አልፈለኩም ፡ ዛሬ የደስታዋ ቀን ይሁን ብዬ እራሴን ሰጥቻታለሁ ። እስካሁን ግን እየሆነ ባለው ነገር አየተገረምኩ ነው ። ህልም እንጂ እውን አይመስልም ። የጥፋተኝነት ስሜት አልተሰማኝም ። ሲጀመር ምን አጠፋሁ ...? እንደውም "ሰውን ለመርዳት ፡ ሰው መሆን በቂ ነው" የሚለውን አባባል አየተገበርኩ ያለው ነው የመሠለኝ ። በመሀል ሰዓቱ በጣም መሄዱን ስላወኩ 'ዛሬ የመተኛት እቅድ የለሽም እንዴ ...?' አልኳት ። ከዛን "ውይ ፡ በጣም ይቅርታ እሺ ፡ እኔኮ ብዙ ጊዜ ቀን ቀን ስለምተኛ ነው" አለችኝ እና እጄን ይዛ ወደ አንድ ክፍል ወሰደችኝ ። "የአባዬ መኝታ ቤት ነው ፡ ከፈለክ እዚህ ተኛ ፤ ይሄኛው ደብሮህ ሳሎን ሶፋ ላይ ማደር ከተመቸህ ግን እዛም ማደር ትችላለህ" ስትለኝ ፤ የባለስልጣን አልጋ ላለመዳፈር ብዬ 'ኧረ ፡ ሶፋው እኮ ይበቃኛል ፡ አትጨናነቂ' አልኳት ። "እንደተመቸህ" ብላኝ ፡ ብርድ ልብስ አቀበለችኝና ቲቪውን ዘግታ ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች ። በልብስ መተኛት ስለማልወድ ፡ ከላይ የለበስኩትን አውልቄ ልተኛ ስል ልጅቷ ድንገት ከተፍ አለች።

...በልብስ መተኛት አልወድም። ልተኛ ልብሴን ሳወልቅ ሳላስበው በድንገት መጥታብኝ ፡ ትንሽም ቢሆን አሳፈረችኝ ። መደንገጤን አይታ "ውይ በጣም ይቅርታ እሺ ፡ ልብስህን እንዳወለክ ስላላወኩ ነው ። ለማንኛውም ፡ ደና እደር ሳልልህ ሄድኩኝ አይደል ...? ፡ ደና እደር እሺ የኔ ጌታ" አለችኝና ወደመጣችበት ተመለሰች ። የሷን አላውቅም ፡ እኔን ግን በፍጹም እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ። እኔ እንኳን ይሁን ልመናት ፡ እሷ ግን እንዴት አመነችኝ ...? ፡ ይሄን የመሠለ ቤት ውስጥ ብቻዋን የምትኖር አንዲት ፍሬ ልጅ ፡ እንዴት እንደኔ አይነቱን ጎረምሳ አምና ታሳድራለች ...? ፡ ነው ወይስ ተደብቃ ምን እንደማደርግ እያየችኝ ይሁን ...? ፡ anyways የሶፋው ምቾት ፡ ምቾቴን ነስቶኝ እንቅልፍ ባይኔ ዝር ሳትል ፡ ከመስጂድ "Allah wakbar" የሚል ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ። በ #4 ማይክራፎን ነው ሚጠቀሙት መሠለኝ ድምፁ ከልክ በላይ ይሰማል ። ሲመስለኝ ቤታቸው ለመስጂድ ፤ ወይም ደግሞ መስጂዱ ለቤታቸው ቅርብ ነው ። ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ከልጅቷ መኝታ ቤት ድምፅ ይሰማኝ ጀመር ። ሲመስለኝ እየቃዠች ነው ፡ ድምጿ ስለረበሸኝ ወደ ክፍሏ አመራሁ ። "አባአአአ ፡ አባዬኤኤኤ ፡ አትሂድ አባ ፡ አትሙትብኝ ፡ አይሆንም" (በሃይለኛ ድምፅ) ። የኔ በር በርግዶ መግባትና የሷ ከቅዠት መባነን clash አደረገ ። በጣም አልቧታል ፤ በዛላይ ከመጠን በላይ ቁና ቁና እየተነፈሰች ነው ። ለማረጋጋት ብዬ አቀፍኳትና እንደ ልጅ እያባበልኳት "አይዞሽ እሺ ሁሉም አልፏል ፡ ደግሞም ቅዠት እንጂ እውነት አይደለም" አልኳት ። ደረቴ ውስጥ ገብታ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች "አባዬን የሆኑ ሰዎች ጫካ ውስጥ ሲገድሉት አየሁ እኮ" አለችኝ ። በጣም ፈርታለች ፡ ሁሉ ነገርዋ ይንቀጠቀጣል ። በፍርሀት ስታቅፈኝ እራሱ እንዳለቃት ነው መሠለኝ ፡ ትንፋሽ እንኳን መውሰድ እስኪያቅተኝ ድረስ ነው ። ለተወሰኑ ደቂቃዎች በእቅፌ ውስጥ ሆና አምርራ አለቀሰች ። ቀስ በቀስ ግን ድምጿ እየቀነሰ ፡ እየቀነሰ ፡ በስተመጨረሻ silent ሆነች ። ቀስ ብዬ ሳያት ፡ አሸልባለች ። እንደምንም ብዬ ሳልቀሰቅሳት አልጋዋ ላይ አስተኛዋት ። ለደቂቃዎች አልጋዋ አጠገብ ቁጭ ብዬ አየኋት ። ቅድም ያየሁት ፡ ያ እንቡጥ ፅጌሬዳን የሚመስለው ጉንጯ አሁን ላይ በእንባዋ ታጥቦ ሌላ ሰው አስመስሏታል ። ቅድም እንተኛ ስላልኳት ሊፀፅተኝ ነው መሠለኝ ። እንደዛው እንደሳቀች ባነጋነው ። ብቻ ልጅቷ ሚስኪን ከሚባሉት ጥቂት ሴቶች መሀል አንዷ ናት ። ትቻት ወደ ሳሎን ተመለስኩኝ ። ለመጀመሪያ ጊዜ ለሊቱን ሙሉ አይኔ ሳይከደን ጀምበር ወጣች ። ቢረዝምም ይነጋል ፡ ሚያልፍ ባይመስልም ሁሉም ያልፋል ። የዛሬው ቀን አያልፍም እንዴ ብዬ የሰጋሁት ትናንት ሆነልኝ ። ያልተኛሁት ያለሁበትን ቦታ ፈርቼ አልነበረም ። በቃ እንቅልፍ እምቢ ስላለኝ ነው ። ለማንኛውም ተመስገን ማለቱ ሳይሻል አይቀርም ። ተመስገን ፈጣሪዬ ።
"ነቅቻለሁ ፡ ተርፌያለሁ ፡
ራሴን ላድን ፡ ቆርጫለሁ ...!"
Le asteyayet
@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 4


.
.
.
ከእንቅልፌ ሳይሆን ከሶፋው ላይ ተነሳሁ ። ደግነቱ እሷም ተነስታ ኩሺና ውስጥ ሽር ጉድ እያለች ነው ። ሲመስለኝ እንቁላል ነገር እየተሰራልኝ ነው ። አፍንጫዬ ነው ሹክ ያለኝ ። ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ድሬዳዋ ከመጣሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ልክ እናቴ ወይንም እህቴ ቤት እያለሁ እንደምትለኝ "ቁርስ ቀርቧል" የሚል የድግስ ጥሪ ከጆሮዬ ገባ ። ስላልተኛሁ ፊቴን ልታጠብ ...? አልታጠብ ...? በሚለው ሀሳብ አየተወዛገብኩ በስተመጨረሻ ታጥቤ ወደ ቁርሱ አቀናሁ ። ልክ እንደ ትናንት ማታው ተጎራርሰን ጀመርነው ። (የቤቱ ህግም አይደል ...) እውነት ለመናገር ልጅቷ ባለሞያ ናት ። የምትሰራው ምግብ ልክ እንደሷ ጣፋጭ ነገር ነው ። (እሷን ደግሞ መች ቀመስካት ...?) ምን እንደ ነካን አላውቅም ፡ ሁለታችንም ተስገብግበን ሳልፈልግ ጨረስነው ። ከቁርስ በዋላ ልክ እንደ ትናንቱ ሶፋው ላይ face to face ተቀምጠን መፋጠጥ ጀመርን ። እሷም እንደኔው ብዙም እንዳልተኛች አይኗ ይናገራል ። የግድግዳ ሰዓቱን ዞር ብላ አየችና "ዛሬ እንኳን እንደማታው አትሂድ ብዬ አላስጨንቅህም ። ማታም በዚያ ሰዓት ወተህ በኔ ምክንያት ችግር ላይ እንድትወድቅ ስላልፈለኩ ነበር ። አሁን ግን ነግቷል ፡ ከኔጋር እዚህ ብትቆይ ደስ ይለኛል ፡ መሄድ ከፈለክ ግን አላስጨንቅህም በሩ ክፍት ነው" አለችኝና ተነስታ በሩን ከፈተችው ። ቢሆንም ግን ቅር እያላት እንደሆነ ፊቷ በደምብ ያስታውቃል ። እኔም ተነሳሁና ወደ ተከፈተልኝ በር አመራሁ ። እሷ ደግሞ በሩን እንደከፈተች የበሩን መክፈቻ ሳትለቅ እዛው ቆማ ወደ መሬት አቀርቅራ ታያለች ። በሩጋ እስክደርስ ለመሄድ አስቤ ነበር ፤ ግን እሷን አልፌ የምሄድበትን ጉልበት አጣሁ ። እጇን ከበሩ መዝጊያ ላይ አንስቺ በራሴ እጅ ዘጋሁትና እጇን እንደያስኩ ወደ ሶፋው ተመለስን ። ጎበዝ ተማሪ ባለመሆኔ ዛሬ ገና ኮራሁ ። ጎበዝማ ብሆን ኖሮ ፡ "ኧረ ትምህርት ያመልጠኛል ፡ በዛላይ ብዙ assignment አስቀምጬ ነው የመጣሁት" እላት ነበር ። በዚች ምድር ላይ ካሉት ነገሮች ቁጥር #1 የምጠላው ትምህርትን ነው ። ጥናት አልተደረገም እንጂ በአለማችንም ለትምህርት ጥላቻ ካላቸው ሰዎች መካከል ቁጥር #1 እኔ ልሆን እችላለሁ ። ለትምህርት ብዙም ትኩረት አልሰጥም ። እሱ ላይ ጊዜዬን ሳጠፋ በጣም ያናድደኛል ። በተለይ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ፡ final ፈተና ወሩን ሙሉ አንብበህም የማትሰራው ጉድ የንዴቴን መጠን ከፍ ያደርገዋል ። ከተሳካ አቋራጭ መንገድ ይመቸኛል ። እንደዚህ ስላችሁ ደግሞ የምኮርጅ እንዳይመስላችሁ ። ምን በወጣኝና ፤ የሚኮርጅ ጓደኛ አለኝ ፡ ከሱላይ ነው የምሰራው ። በዚች ምድር ላይ ከሰይጣን ውጪ የምጠላው ነገር ስለሌለ ፡ የሚያስጠሉኝን ነገሮች የሰይጣን ማህበርተኛ አድርጌያቸዋለው ። ለምሣሌ በኔ አይን illuminate የሆኑ ነገሮች እነዚህ ናቸው ፦ #1-ትምህርት ፣ #2-ትምህርት ፣ #3-ትምህርት ... ትምህርትን የጠላሁበት ትክክለኛ ምክንያት አላውቅም ። ለነገሩ ስንፍናዬኮ በቂ ምክንያት ይሆናል ። anyways ለጊዜው ትምህርቱን የራስህ ጉዳይ ብዬው ፡ እልጅቷ ቤት ቀርቻለሁ ። ከጥቂት ዝምታ በዋላ "እሺ ወጣት ተስፋዬ ፡ እስኪ ስላንተ ንገረኝ ፡ በትንሹም ቢሆን ስለኔ አውቀህ የሌ ...?" አለችኝ ።

'እንዳልኩሽ ስሜ ተስፋዬ ይባላል ። እናቴ ናት ያወጣችልኝ ። የተወለድኩት ሙገር ቀበሌ ውስጥ በምትገኝ ኩባ ሰፈር በምትባል ቦታ ነው ። ምናልባት ሙገርን በሲሚንቶ ልታውቂያት ትችያለሽ ። (ሙገር ሲሚንቶ ፣ ዳንጎቴ ሲሚንቶ) የትውልድ ሰፈሬ ኩባ የተባለው ፡ ያን ጊዜ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን የሰሩት ሰዎች ኩባውያን ስለነበሩ ነው ። ኩባ ሰፈር ደግሞ በፋብሪካው አጥር አጠገብ በታችኛው በኩል የተመሠረተ ሲሆን ፡ ያን ጊዜ የኩባውያን ፡ አሁን ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች መኖሪያ ስፍራ ነው ። ሁለተኛ ክፍል እስክደርስ እዛው ነው ጥርሴን ነቅዬ ያደኩት ። #2ኛ ክፍል #2ኛ ሴሚስተር ላይ አባቴ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ የስራ እድገት አገኘና ቤታችንን ከኩባ ሰፈር ወደ ሙገር መኮዳ ቀየርን ። መኮዳ ከኩባ ሰፈር በእግር ከ #30-40 ደቂቃ የሚፈጅ መንገድ ሲሆን በመኪና ደግሞ ከ #5 ደቂቃ አያልፍም ። ሰፈሩም መኮዳ የተባለው በድሮ ጊዜ እዚህ አካባቢ የኦዳ ዛፍ እንደነበር ይነገራል ። ለዛም ነው ሰፈሩ በአፋን ኦሮሞ Muka odaa /ሙከ ኦዳ (የኦዳ ዛፍ) የተባለው ። ከዛን ቀስ በቀስ ስሙ ከልጅ ልጅ ሲያልፍና ሲቆላመጥ መኮዳ ሆኖ ቀረ ። እና እዚህ ድሬዳዋ እስክመጣ ድረስ ለ #10 አመታት እዛው ነው ከቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩት ። መኮዳም ኩባ ሰፈርም ካምፕ ናቸው ። የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች ብቻ የሚኖሩበት ሰፈር ። አብዛኛው የሙገር ሰው ግን የሚኖረው ሬጂ በሚባል የሙገር ከተማ ውስጥ ነው ። አስተዳደጌ ያንቺ ተቃራኒ ነው ። እቤት ውስጥ አባቴ ፣ እናቴ ፣ #3ቱ እህቶቼ እና አጎቴ ሆነን ነው የኖርነው ። እንዳንቺ ብቻዬን ለአመታት ይቅርና ለሰዓታትም አሳልፌ አላውቅም ። ቤተሰብ ፣ ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ጓደኛ ፣ ሁሉንም አለኝ ። ሰፈር መንደሩ ያውቁኛል ፤ እኔም እንደዛው ። ምናልባት እኔና አንቺን የሚያመሳስለን ነገር ቢኖር የሲሚንቶ ሀገር ልጆች መሆናችን ነው ። ለነገሩ ምናችንም ሲሚንቶ አይመስልም ። ከአፈር እንደተሰራን እናስፎግራለን ። ባይሆን ግን ነጮቹ ከሲሚንቶ የተሰሩ ይመስሉኛል ። anyways ብዙም ባያኮራም ፣ ደስ የሚሉ ብዙ ታሪኮችን አሳልፌ አሁን ላይ ደርሻለሁ ። እንደ ምታዪኝ አሁን የግቢ ተማሪ ነኝ ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ #2ኛ ዓመት የመካኒካል እንጂኔሪንግ ተማሪ ነኝ' አልኳት እና ብዙ እንዳወራሁ ስለተሰማኝ ዝም አልኩ ። ቀጥላም "ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በመሆንህ ደስተኛ ነህ ...?" አለችኝ ። አኔም 'መጀመሪያ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እንደደረሰን ስናውቅ በደስታ አብደን ነበር ። ከ #1 ክፍል ውስጥ #10 ተማሪ ነበር አንድላይ እዚህ የደረሰን ። እዛ ሆነን የጠበቅነው ነገርና ፡ እዚህ መጥተን ያየነው ምንም አይገናኝም ። ባጠቃላይ ስለ ድሬ ባጭሩ ሙዚቃዋ ሸወደን ማለት ይቻላል ። anyways አማራጭ ስለሌለኝና "ነገር ሁሉ ለበጎ ናቸው" በሚለው ቃል ስለማምን አሜን ብዬ ተቀብየዋለሁ' አልኳት ። መጠየቅ ትወዳለች መሠለኝ ፡ ጥያቄው ቀጥሏል ። "ይቅርታ ግን ፡ መጠየቅ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም ። እእእ ... ፍቅረኛ አለህ ...?"

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል...............
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 5

.
.
.
'የፍቅር ታሪኬን ማወቅ ከፈለግሽ ፡ ፈጣሪ ከፈቀደ አንድ ቀን በሰፊው እነግርሻለሁ ። በአሁኑ ሰዓት ግን ፍቅረኛ የለኝም ። ባይሆን እናንተ ፍቅር ላይ ብዙ ልምድ አላችሁ ይባላል ፡ እንደውም ለምን ያንቺን አትነግሪኝም...?' አልኳትና እንዲህ አለችኝ "ብታምንም ባታምንም ከማንም ጋር የፍቅር ህይወት ኖሮኝ አያውቅም ። እስር ቤት ያለ ሰው ከማን ፍቅር ይይዘዋል ...? ያውም ብቻዋን በአንድ ቤት ውስጥ የታሰረች ነፍስ ። ባይገርምህ ምኞትሽ ምንድነው ብትለኝ ከነፃነት ቀጥሎ ፍቅር እንዲይዘኝ ነው ። እዚህ ቤት ውስጥ ሆኜ ያላየሁት የህንድ ፊልም ፡ ያላነበብኩት የልቦለድ መፅሐፍ የለም ማለት ትችላለህ" ስትለኝ ቤቱን በአይኖቼ መፈተሽ ጀመርኩ ። የመፅሐፍ መደርደሪያው ውስጥ የሀገር መፅሐፍ ተከማችቷል ። TV stand ስርም ብዙ ካሴቶች ይታዩኛል ። ስታወራኝ እምባዋ ይመጣል ፡ ሆድ ይብሳታል ። በሀይልና ቁጭት ስለምታወራ አንዳንዴ ታስፈራለች ። "በዚህ ሰዓት የምፈልገው ፡ በቃ እንደ ማንኛውም ሰው ፡ በነፃነት የፈለኩበት ቦታ ሄጄ ፡ የፈለኩትን ነገር ማድረግ ነው" አለችኝና እምባዋን ዱብ ዱብ አረገች ። ጥሎብኝ እኔ ደግሞ ሴት ልጅ ስታለቅስ ካየሁ ፡ የኔም እምባ ሳይጠሩት ይመጣል ። እንደዛ ስትሆን የማየት አቅሙ ስላልነበረኝ ፡ እቅፍ አረኳትና ለማፅናናት ሞከርኩኝ ። የሀገሬ ሰው ሲተርት "ሴት ልጅ ብቻዋን ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም" ይላል ። እኔ ግን እላችኋለሁ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም'። ደረቴ ላይ ተለጥፋ ዝም አለች ። ይሄን ጊዜ ሁሉን ነገር ረስታ የሰላም እንቅልፍ የምትተኛ ይመስለኝና እፎይታ ይሰማኛል ። ጠረንዋ ፣ ልብ ትርታዋ ፣ ሀዘኗ ፣ ጭንቀቷ ፣ ሁሉ ነገሯ ወርሶኛል ። ልጅቷ ያጣችው ነገር አንድና አንድ ነው ። እሱም የሰው ፍቅር ብቻ ነው ። ይሄን ለማግኘት ደግሞ መጀመሪያ ልጅቷ ነፃነቷን ማግኘት አለባት ። ሳላስበው በድንገት እንደሚባንን ሰው ከእቅፌ ውስት ብድግ ብላ "ለምን አንጠጣም...?" አለችኝና ወደ ፍሪጁ አመራች ። ከፈተችውና #4 ቢራ ይዛ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችና ከጎኔ ተቀመጠች ። "አባዬ ቅዳሜና እሁድ እዚህ ሲያሳልፍ ፡ አንድ ሁለት የማለት ልምድ አለው ። እና እንደምታየው ፍሪጅ ውስጥ አንድ #10 የሚሆኑ አሉ ። እኔ እንኳን የሆነ ቀን የቢራን ጣዕም ለማወቅ ብዬ ጠጥቼ ፡ እየመረረኝም ቢሆን አንድ ጠርሙስ እንደምንም ጨርሼ ነበር ፡ ከዛን ቀን ውጪ ጠጥቼ አላውቅም ። ዛሬ ጠጪ ጠጪ ስላሰኘኝና የሚያጣጣኝ ሰው አንተን ስላገኘሁ ነው የጠየኩህ ። ካልደበረህ እንጠጣ ...?" አለችኝ በልመና አይነት ድምፅ ። 'እሺ ግን ሳናበዛ' አልኳትና አንድ ሁለት ማለቱን ጀመርነው ። ልምድ እንደሌላት ታስታውቃለች ። ስትጠጣ ፡ ፊቷ ጭምድድ ይላል ፤ በዛላይ በሆነው ባልሆነው ትስቃለች ። ደግሞ አስሬ "ጠጣ እንጂ" የምትለው ጉድ አለ ። ቀስ በቀስ ለሁለታችንም ሶስተኛው ቢራ ተከፈተ ። "ስማኝማ" እያለች ብዙ የማይገጥሙ ቀልዶችን እየነገረችኝ ልታስቀኝ ጥረት ታደርጋለች ። (እኔ ደግሞ ብዙ ጊዜ ጀማሪ ቀልደኞችን የማበረታታት አባዜ ስላለብኝ ፡ ባያስቅም እስቅላታው ።) አንዴ ደረቴን እየመታች "ሙት እሺ" ስትለኝ ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥምጥም ስትልብኝ ፡ አራተኛ ቢራ ላይ ደረስን ። አይኖቿ ድብዝዝ ብለዋል ፤ ድምጿም እየሳሳ ሄደ...መላ ሰውነቷ ድክምክም ብሏል ። ባጭሩ ልጅት እራሷን ለመሳት ሶስት ሴኮንድ ነው የሚቀራት ። አይፈረድባትም ፡ ያውም ልምድ የሌላት ልጅ ፡ በዛላይ በዚህ ጠራራ ፀሀይ ። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ቢራ የጠጣሁ እለት ፡ ሌሊቱ እንዴት እንደነጋልኝ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ። anyways ልጅቷ አራተኛውን ቢራ ከአንገቱ ላይ እንኳ ዝቅ ሳታደርገው እቅፌ ውስጥ አሸልባለች ። ልብስ እንኳን አልቀየረችም ነበር ፤ ልክ ማታ በሌሊት ልብስ እንደ ተኛች ነው ያለችው ። እቅፌ ውስጥ እንዳለች ተሸክሜያት ከሶፋው ላይ ተነሳሁና ወደ መኝታ ክፍሏ ጉዞ ጀመርኩኝ ። ብዙም አትከብድም ፡ አካሏ በሙሉ በጥንቃቄ የተሰሩ ይመስላሉ ። ማንኛውም ወንድ የሚመኘው አይነት የሰውነት ቅርፅ ያላት ልጅ ናት ። ቅዱሱ መፅሐፍ "ወደ ሴት አይቶ የተመኛት በልቡ አመነዘረባት" ይላል ። (ውሃ በላኝ ማለት ነው ...?) የተኛች መስሎኝ ነበር ፡ ግን ሙሉ በሙሉ እራሷን አልሳተችም ። ሲመስለኝ የሚሆነውን ነገር በቭዥታ መልክ እያየች ነው ። እንደውም ማውራት ጀመረች ። "አንተ ፡ የት አየወሰድከኝ ነው ...? ፡ እእእ ፡ ምን ልታደርገኝ ነው ...?" እያለች በልመና አይነት ድምፅ ሽቅብ ወደላይ እያየችኝ ፡ መልስ ሳልሰጣት መኝታ ክፍሏ ገብቼ አልጋዋ ላይ አስተኛዋት ። በትንሹም ቢሆን እኔም ዞሮብኛል ። እራሴን መቆጣጠር ግን ያን ያክል አይከብደኝም ። ልጅቷ አልጋዋ ላይ ሆና ወደላይ እያየችኝ በሹክሹክታ ማውራቷን አላቆመችም ። "አ ሰ ከ ር ከ ኝ ፡ አ ...? ፡ ምንድነው ሚዘጋክ ...? ፡ አንተን እኮ ነው ማወራው ...! ፡ እንደውም ና እስቲ ወደኔ ቅረብ ፡ ና...!" አለችኝ በእጆቿ ጭምር ። ምን ልትለኝ ይሁን እያልኩ ወደ አልጋው ቀርቤ ፡ ትንሽ እንደ መንበርከክም ብዬ ፡ ጆሮዬን አፏ ላይ ደቀንኩት ። ከትንፋሿ ውጪ ምንም አይነት ድምፅ አይሰማኝም ። ቀና ብዬ ሳያት ሄዳለች ። ደሀ እራሱ እንዲህ ለጥ አይልም ። ከተንበረከኩበት ተነሳሁና ፡ የክፍሏ ግድግዳ ላይ በጀርባዬ ተደግፌ ፡ ልክ እንደ ትናንት ማታው ፡ አትኩሬ እሷኑ ማየት ጀመርኩ ። የከንቲባ ቤት ነኝ ፡ ያውም የሴት ልጁ መኝታ ክፍል ። እኔና እሷ ብቻ ። ሰይጣን ይታይ ይመስል ባይኖቼ ቤቱ ውስጥ መፈለግ ጀመርኩኝ ። ሰይጣን ሆይ ፡ እንዴት እስካሁን ሁለት ሰክረው አንድ መኝታ ቤት ውስጥ ያሉ ወንድና ሴት አግኝተህ ዝም አልክ ...? ነው ወይስ በጉጉት እየጠበከን ነው ...? መኝታ ቤቷ ውስጥ ሰይጣን ሰምቶኝ መልስ ይሰጠኝ ይመስል ጆሮዎቼን አቁሜ እጠብቀዋለሁ ። እሱን ፍለጋ በአይኖቼ ሳማትር ፡ በልጅቷ ራስጌ ግድግዳ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል "የሚጠብቀኝ አይተኛም ፡ አያንቀላፋም" ከሚል ጥቅስ ጋር ተዳምሮ ፤ በተቃራኒው ደግሞ በልጅቷ ግርጌ ግድግዳ ላይ ፡ የድንግል ማሪያም ስዕል "አይዞህ ትለኛለች ፡ ድንግል ከነልጇ" ከሚል ግጥም ጋር ተዋሕዶ የተለጠፈውን አየሁ ። በዚህ መሀል ፡ ልጅቷ የማይሰሙ ቃላት እያወጣች መገላበጥ ጀመረች ። ተኝታበት ከነበረው አቅጣጫ ወደ ተቃራኒው ስትገለበጥ ፡ አልብሻት የነበረውን አልጋ ልብስ ከራሷ ላይ ጣለች ። ከወገብ በታች አብዛኛው ሰውነቷ በግልጽ ይታያል ። እግሮቼም ወደ አልጋዋ ጉዞ ጀመሩ ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 8


.
.
.
እጄን ይዛኝ ፡ ወደ ቤት እየወሰደችኝ "እንዴት በዚህ ሰዓት መጣህ ...? ፡ ትምህርት የለም ወይንስ #03:00 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ናፈኩህ ...?" አለችኝ እንደ መሽኮርመም ነገር ሆና ። ስለ ጊቢው ሁኔታ ጓደኛዬ የነገረኝን እንዳለ ነገርኳት ። እሷም እንደኔው በረብሻው ደስተኛ ባትሆንም ትምህርት እስከ ቀጣይ እሮብ ባለመኖሩ በውስጧ እልል እያለች እንደሆነ ያስታውቅባታል ። ለምን እንዲህ አናደርግም "ዛሬ አርብም አይደል ፡ እስከ እሮብ ድረስ #5 ቀን አለን ። እና ይሄን ሁሉ ቀን #1 ቤት ውስጥ ከምንጎለት ፡ ለምን ከዚህ ርቀን የሆነ ቦታ ሄደን ፈታ ብለን አንመለስም ...?" አለችኝ ። አሰብኩበት ፡ ጉዳቱ አልታየኝም ፤ ተስማማሁላት ። በውሳኔው ሁለታችንም ደስተኞች ነን ። "ከበቂ በላይ ገንዘብና መኪና አለን ፡ ግን የት ነው የምንሄደው ...?" የሚል ሀሳብ አነሳች ።
"ብቻ አንቺ ኑሪልኝ ኑሪልኝ
ኑሪልኝ እንጂ ፣
የትም ይመቸኛል የትም
የትም ይመቸኛል የትም" ።
አይነት መልስ ሰጠዋት ። "ለመዝናናት ደብረ ዘይት እና ሀዋሳ አሪፍ እንደሆኑ በቲቪ አይቻለሁና ከሁለቱ አንዱ ቢሆን ደስ ይለኛል" አለችኝ ። እኔም 'ሀዋሳ ሄጄ አላውቅም ፤ ቡሾፍቱ ግን #3 ጊዜ ስለሄድኩኝ እዛ ሳይሻል አይቀርም' ስላት በደስታ ተስማማች ። ነገ በጠዋት ጉዞ ወደ ውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ። ከባንክ ቤት ለጉዞው ብለን #10 ሺህ ብር አወጣች ። ATM ስላላት ተጨማሪም ካስፈለገን ፡ ባስፈለገን ሰዓት እናወጣለን ብላኛለች ። ምናልባት መንገድ ላይ ረሀብ ከለቀቀብን ብለን ለነገ ምግብ ተባብረን አዘጋጅተናል ። ነጋና ጉዞ በጠዋት ጀመርን ። ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ መካከል የ #512km ርቀት እንዳለ ታፔላ ላይ ተለጥፎ አምብቤያለሁ ፤ ሰዎች ስያወሩም ሰምቻለሁ ። Google ላይ search ሳደርግ ግን #452 km ነው የሚለው ። በዚህም በዚያም በመኪና (ኢትዮ ፣ ዘመን ፣ ገዳ ፣ ሰላም ፣ ወዘተ bus'ኦች) ከድሬ ሸገር ለመድረስ ከ #8 ሰዓት እስከ #9 ሰዓት ይፈጃል ። በባቡር እራሱ ሄደን ነበርና ከሸገር ጠዋት #02:00 ሰዓት ተነስቶ ቀን #10:00 ሰዓት ነው ድሬ የሚደርሰው ። እሱም መብራት ካልጠፋ ነው ፤ ከጠፋ ማታ #03:00 ሰዓትም ሊገባ ይችላል ። ከድሬ ደግሞ ቀን #07:00 ሰዓት ይነሳና ምሽት #03:00 ሰዓት ለቡ ፡ አዲስ አበባ ይገባል ። በፕሌን ደግሞ የ #45 ደቂቃ መንገድ ነው ። እኛ #01:00 ሰዓት ነበር በ Rava #4 መኪና ከድሬ የተነሳው ። ፈጣሪ ካለ እስከ #10:00 ሰዓት ፊንፊኔ እንገባለን ። anyways የከንቲባው ልጅ መኪናዋን አየር ላይ እያከነፈችው ነው ። ቢቻለኝና ስልጣኑ ቢኖረኝ የአምስት ዓመት ስራ ልምድ እፅፍላት ነበር ። በአነዳዷ ስገረም አየችኝ መሠለኝ "አይዞህ እሺ ፡ ከቢሾፍቱ ስንመለስ አለማምድሀለው" አለችኝ ። የድሬ ሸገር asphalt ብዙም ውጣ ውረድ የለውም ። በግራም በቀኝም አልፎ አልፎ ከሚታይ ትናንሽ ሰፈር ውጪ በረሀ ነው ማለት ይቻላል ። አብዛኛው መሬት ሰውም ፣ እንስሳም ፣ እፅዋትም የለውም ። አፈር ብቻ ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ ፡ "እስቲ ሶስቴ ደብረ ዘይት የሄድክባቸውን ጊዜያት አስታውሰኝ ...?" አለችኝ ።

'ለመጀመሪያ ጊዜ ደብረ ዘይት ከተማ የሄድኩት #6ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። በወቅቱ scout የሚባል የወጣቶች ህብረት ነበር ። scout ማለት ወጣቶች ከትምህርት ሰዓታቸው ውጪ መጥፎ ቦታዎች እንዳይውሉ ፣ የሀገር ፍቅር እንዲኖራቸው ፣ ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ፣ በትምህርታቸውም እንዲጠነክሩ የሚያደርግ ምርጥ ማህበር ነው ። ወጣቶች ላይ ትኩረት ያድርግ እንጂ ህፃናትና ጎልማሶችም የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ ። እና ያኔ ነበር ቢሾፍቱን ከጓደኞቼ ጋር ሀ ብዬ የረገጥኩኝ (ሀ እንኳን ያልኩ አይመስለኝም ...) ። እዛ የሚገኙትን አየር ሀይል ተቋምና ባቦጋያ ሀይቅን ጎብኝተን ገባን ። በዓመቱም ድጋሜ በ scout ሄደንና ሆራ አርሰዴንና የወጣቶች ማዕከልን አይተን ፡ ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን ተመለስን ። ለመጀመሪያ ጊዜ በጀልባ ሀይቅ ላይም የተንሳፈፍኩትም ያኔ ነበር ። እንዴት ደስ እንደሚል አጠይቂኝ ። በዛን ጊዜ ሙገር scout በእግረኛ ሰልፍ እንደ ኢትዮጵያ ታዋቂ ነበር ። ብዙ ፕሮግራም ላይ ተሳትፈናል ፣ ብዙ ቦታዎችን ሄደናል ። እንደውም ከአባሎቻችን መካከል አንዱ እድል አግኝቶ አሁን USA ነው ያለው ። አሁን ላይ ግን አባላቱ በትምህርት ምከንያት በየ ዩኒቨርስቲው ስለተበታተኑ ማህበሩ ፈርሷል' አልኳት ትንሽ እንደማዘን ሆኜ ። "እሺ ለሶስተኛ ጊዜስ እንዴት ሄድክ ...?" አለችኝ ። 'ለ #3ኛ ጊዜ እንኳን ደብረ ዘይት የሄድኩበት ምክንያት ለየት ይላል ። ታሪኩም ረዘም ስለሚል እንዳላሰለችሽ ሌላ ጊዜ ልንገርሽ' አልኳትና በረዥሙ ተንፍሼ አየር ወሰድኩኝ ። "የምለቅህ እንዳይመስልህ ፡ ምሳ ከበላን በዋላ ትተነፍሽያታለሽ" አለችኝ እየሳቀች ። "ስማኝማ ፡ ፊትለፊታችን ምንድነው ይሄ ሁሉ መኪናና ሰው...?" አለችኝ ትንሽ እንደ መደንገጥ ነገር ሆና ። 'አይዞሽ አትፍሪ ፡ አሁን አዋሽ ደርሰናል ። በዚህ መንገድ የሚያልፍ ማንኛውም መኪናና እቃ ሳይፈተሽ ንቅንቅ አይልም ። እንደ ኢትዮጵያ ብዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች የሚያዙት እዚህ ነው ። ምክንያቱ ደግሞ ህገ ወጥ መሣሪያዎች ፣ ጫማ ፣ ልብስ ፣ electronics ፣ ወዘተ ቁሳቁሶች በውጫሌ በኩል ወደ ድሬዳዋ ስለሚገቡ ነው' አልኳትና መኪናችንን check አርገው ምንም የተለየ ነገር ስላልያዝን ሳያቆዩን ለቀቁን ። አዋሽ የሚሰሩ ፈታሾች ግን የሚሰሩት እንደ ሙዳቸው ነው ። ደስ ሲላቸው ያለሽን controband እቃ እንዳለ ፣ ሲያሻቸው ግማሹን ይወስዱብሻል ። መፈተሽ ሲሰለቻቸው ደግሞ ምንም ነገር ሳያዩ ያሳልፋሉ ። ይሄን ደግሞ ብዙ ጊዜ በዚህ ስናልፍ ታዚቤያለሁ ። የድሬ ሸገር መንገድ ርዝመት ከሙቀቱ ጋር ተዳምሮ በጣም አሰልቺና አድካሚ ነው ። ብዙ ሰዓት ሄደናል ። መተሃራ ለምሳ ወርደን ማታ የሰራነውን take away በልተን ፣ ትንሽ አረፍ ብለን ጉዞ ቀጠልን ። ከመኪናው ቴፕ ላይ የምትከፍታቸው ሙዚቃዎች ያበዱ ናቸው ። ለነገሩ ልጅቷም እብድ ነገር ናት ። እንደኔው የአስቱካ ወዳጅ ናት ። "ጨጨሆ ፡ ጨጨሆ" እያለች ከአስቴር አወቀ በላይ እየጮኸች ሳያት እብደቷ ተጋብቶብኝ እኔም ሙድ ውስጥ ገባሁ ።እንዲህማ ከቀጠልን መኪናዋ አክሮባት መስራቷ ነው ። አሁን ተገለበጠች ፡ አሁን ተፈጠፈጠች እያልኩ ከምሰጋ ብዬ ለትንሽ ደቂቃ መኪናውን አቁመን እብደታችንን እንድንጨርስ ነገርኳት ። አቆመችና "ስማኝማ ፡ ሽንቴ መጣኮ" አለችኝ....


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 6


.
.
.
ወደ አልጋዋ ቀረብኩኝ ። ወደ ግራ ዞሬ ቀና ስል የክርስቶስ ስዕል ግድግዳ ላይ ሆኖ አካል ለብሶ ታየኝ ። "ልጄ ሆይ ፡ የሰይጣንን ሀሳብ አትስማ" የሚለኝ ይመስለኛል ። በቀኝ በኩልም እመቤቴ ስጋ ለብሳ "ልጄ ሆይ ፡ ልጄ የሚልህን አድርግ" የምትለኝ ይመስለኛል ። እውነትም የሚጠብቃት አይተኛም ። አልጋ ልብሱን መልሼ አለበስኳትና ክፍሏን ለቅቄ ወጣሁ ። ሳሎን ውስጥ ሆኜ ፡ በሁለት ሀሳብ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነው ። አንደኛው ፡ 'እዚህ ትቻት ሄጄ ወደ ጊቢ ብመለስ ምን ትሆናለች...?' የሚለው ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ 'እስክትነቃ ድረስ እዚህ ብቻዬን ብቆይ ምን ሊፈጠር ይችላል...?' የሚለው ነው ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና ልጅቷን ትቼ መሄድ ከብዶኛል ። በዛውም ልክ ደግሞ እዚህ ቤት ብቻዬን መቀመጥም አስፈርቶኛል ። ቆይ ፡ ድንገት አባቷ ቢመጡስ ...? ፡ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ለመሄድ ወሰንኩና ከቤቱ ወጣሁ ። የውጪኛው በር ጋር ስደርስ ግን 'አባቷ ውጭ ሀገር ከሆኑ ፡ ሳያሳውቃት በዚህ ጠራራ ፀሀይ ምን ያስመጣቸዋል ...? ፡ እንደውም ድፍረቱ ከየት እንደመጣ ሳላውቅ ፡ እንደውም ይምጡ ፡ በዛላይ ጥሩ ሰው እንደሆኑ እራሷ ነግራኛለች' የሚለው ሀሳብ መጣልኝና ሀሳቤን ቀይሬ ወደ ቤቱ ተመለስኩ ። እስከ ቀን #10 ሰዓት ብቻዬን ጅዝብ ብዬ ከሶፋው ላይ ሳልንቀሳቀስ ዋልኩኝ ። ደህንነቷን ለማረጋገጥ ብዬ ወደ ክፍሏ ስገባ ፡ እሷ ሌላ አለም ውስጥ ናት ። ማታ ብዙም ስላልተኛች ልቀሰቅሳት አልፈለኩም ። እንዳለችውም ቀን ቀን የመተኛት ልምድ አላት ። እኔን ደግሞ ሲፈጥረኝ ፡ በታሪክ ቀን ቀን መተኛት አልወድም ። (ለዛ ነው ብቻዋን እንድትተኛ የተውኳት ። ቆይ ቆይ ፡ ማታ ቢሆን ምን ልታደርግ ነበር ...😂) ። መንቃትዋ ስለማይቀር ብዬ ኩሺና ገባሁ ። ለሰካራም ፍትፍት መዳኒት እንደሆነ ጭምጭምታ ደርሶኛል ። እሱን ልሰራላት ሽር ጉድ እያልኩኝ ነው ። ለ emergency ተብሎ ድሮ እቤት እያለሁ በእናቴና እህቴ ፍርፍር ፣ እንቁላል ጥብስ ፣ እንቁላል ፍርፍር እና ሽሮ መስራት ስልጠና ተሰቶኝ ነበር ። አፍንጫን የምትሰነጥቅ ቆንጂዬ ሽሮ ፍትፍት ሰርቼ ጨረስኩና #11 ሰዓት አካባቢ ፡ ልጅቷ ክፍለ ገብቼ ቀሰቀስኳት ። ስትነቃ በትንሹም ቢሆን ደንግጣ ነበር ። "አይዞሽ አትፍሪ ፡ እኔ ነኝ ምንም አልተፈጠረም" አልኳትና ተነሳች ። ጭንቅላቷን በደምብ ጭምቅ አርጋ "እራሴ ሊፈነዳ ነው" አለችኝ ። እኔም "እሱን አውቃለሁ ፡ አሁን ፊትሽን ታጠቢ ፡ ከዛን መዳኒቱን እኔ እሰጥሻለሁ" አልኳት ። በራሴ እጅ የሰራዋትን ፍትፍት ሽሮ አጎረስኳትና አድናቆቱን መጠበቅ ጀመርኩ ። ፊቷ ላይ ግን የሚታየኝ የአድናቆት መንፈስ ሳይሆን ፡ የሆነ ጨው በዝቶበት አይነት ነው ። እንደውም "ምን ሆነህ ነው እንደዚህ አይነት ምግብ የምታበላኝ...? ፡ እስቲ ቀምሰህ እየው" ብላኝ አጎረሰችኝ ። እየጣፈጠኝ በልቼ ዋጥኩት ። ከዛን ከት ብላ እየሳቀችብኝ "ወጣቱ ፡ አንተ እራሱ የቤት እመቤት አይደለህ እንዴ ...! ብላኝ ቀልቤን ገፈፈችው ። ጭራሽ "በናትህ ለጊዜው የቤት ሰራተኛዬ ስለሄደችብኝ እዚሁ ቆይና አገልግለኝ" እያለች ታሾፍብኛለች ። ይበዛል ብዬ የሰራሁትን ብቻዋን ለማለት በሚስችል ሁኔታ በልታ ጨረሰችው ። እንደውም ዛሬ ተረኛ እራት የምትሰራው አንተ ነህ የሚል ስሜት ከፊቷ ላይ ይነበባል።
ፍሪጅ ውስጥ ወተት ስለነበር እሱንም ሰጠዋትና በስተመጨረሻ ወደ ቀልቧ ተመለሰች ። እንደውም "የኔ ዶከተር ፡ መዳኒቶችህ ሰርተዋል ፡ ነገር ግን በየእለቱ መቋረጥ የለባቸውም ብዬ አስባለሁ" እያለች ታሾፍብኛለች ። ሳሎን ውስጥ እንደተለመደው ፡ ብቻችን ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን መፋጠጥ ጀመርን ። ትኩር ብላ ታየኛለች ፤ እኔም እንደዛው ። ከፊቷ ላይ እንደሚታየኝ ከሆነ በጣም ደስ ብሏታል ። "ስማኝማ" ብላ መናገር ጀመረች ። "እንዴት እስካሁን ብቻህን እዚህ ልትቆይ ቻልክ ...? መሄድ ነበረብህ እያልኩ አይደለም ግን" አለችኝ ። 'ካየሁሽ ሰዓት ጀምሮ ቀልቤን ወስደሽዋል ፡ እራሴን ብቻ አይደለም ፤ ሁሉ ነገሬን አስረስተሽኛል ። ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሽ ነበር ልቤን የጣልኩልሽ ። ብቸኝነትሽ ፣ ሚስኪንነትሽ ፣ ባጠቃላይ ሁለመናሽ ፡ እንኳን ለእንደኔ ቀርቦ ላየሽ ወንድ ይቅርና ፡ በሩቁ አይንሽን ብቻ ካዩሽ ይነበባል ። ደካማ ጎኔን ነው ያገኘሽው ። ልቤን እንዳይመለስ አርገሽ ጠልፈሽዋል ። በቃ ምን እያልኩሽ እንደሆነ ገብቶሻል ፤ አታስጨንቂኝ ። እንደውም ቁርጡን ልንገርሽ ...? ፡ ከዚህ ቤት እግሬን ለሴኮንድ እንኳን የማነሳ አይመስለኝም' እንድልሽ መቼም አጠብቂም አልኳትና አስደነገጥኳት ። "ሙት እሺ ...? ፡ እኔ እኮ የምርህን መስሎኝ በደስታ ላለቅስ ነበር ። እንደውም አሎድህም እሺ ...? ፡ በቃ እንደውም ተጣልተናል አታናግረኝ" አለችኝ እንደ ማኩረፍ ነገር ሆና ። 'እሺ በቃ አንቺን የሚያስከፋ ከሆነማ ውሸቱን እውነት አረግልሻለው' አልኳትና እቅፍ አረኳት ። በጣም መሽቷል ፤ አንድ ሰዓት አልፏል ። "አልቻልኩም እማምላክ ፡ ስቃዬ በረታ ፣
የመከራዬ እለት ፡ እንደምን ሊረታ ፣
ሳለቅስ አነጋለሁ ፡ ሳነባ ውላለሁ ፣
የሚያፅናናኝ የለም ፡ ብቸኛ ሆኛለሁ" ።
መዝሙር ከፍተን አይደለም ፡ የስልኳ ጥሪ ነው ። አባቷ ነው ደዋዩና እንዴት ደስ እንዳላት idea'ው የላቹም ። እኔን እራሱ ሶስቴ ስማኛለች (ጉንጬን) ። በር ላይ እንደቆመና ብዙም እንደማይቆይ ነገራት እና እኔን በጓሮ በኩል ይዛኝ ወጥታ የሆነ ጭልምልም ያለ ቦታ አስቀምጣኝ "እራሴ መጥቼ እወስድሃለሁ ፡ እስከዚያው ግን ከዚህ ንቅንቅ እንዳትል እሺ...?" ብላኝ ከፊትለፊቴ ተሰወረች ። ያለሁበት ቦታ ጊቢ ውስጥ ባይሆን ኖሮ በፍርሀት መሞቴ ነበር ። ጨለማ ነው ፡ በዛላይ ፀጥታው ነፍስን ከስጋ ይለያል ። ስልኬን አውጥቼ ሰዓት ሳይ #01:54 ይላል ። በልቤ ምን እየተባባሉ ይሁን እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ ፡ ከ #15 ደቂቃ በዋላ መጣችና ወደ ቤቱ መለሰችኝ ። ከእስር ቤት የተፈታሁ ነበር የመሰለኝ ። 'ለምንድነው ለትንሽ ደቂቃ ብቻ የመጣው ...? ፡ የትስ ጠፍቶ ነበር ለዚህ ሁሉ ቀን ሳይደውል እንኳን ያስጨነቀሽ' አልኳት ። "እሱን የምጠይቅበት ጊዜ አላገኘሁም ። በጣም ናፍቆኝ ስለነበር መሄዱና አለመደወሉ ትዝም አላለኝም ። ባይሆን የመጣበት ጉዳይ ትንሽ አሳስቦኛል ። ምን ምን ወስዶ እንደሄደ ታውቃለህ ...? ፡ የኔን photo ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ የትምህርት ማስረጃዎች ፣ በቃ ስለኔ ነክ የሆኑ ማስረጃዎችን እንዳለ ይዟቸው ሄደ ። ለምን ስለው ለሆነ process ነው ፡ ሲያልቅ surprise አረግሻለው አለኝ" ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 7

.
.
.
"ሁሌም እዚህ ሲመጣ ስጦታ ከእጁ አይጠፋም ። የዛሬውን ለየት የሚያደርገው ግን በፊት በፊት እሱ ፊትለፊት ነበር ከፍቼ የማየው ። ዛሬ ግን እሱ የለም ፤ እና በናትህ ስጦታውን ከፍቼ ደስ የሚለኝ ከሆነ እንደ አባቴ ሁንልኝና ጥምጥም ብዬብህ ፡ በጣም እንደ ምወደው ልንገርህ ...?" ብላኝ መልሴን እንኳን ሳታውቅ በካኪ ወረቀት የመጣላትን ስጦታ ከፈተችው ። ወረቀት እና የባንክ ደብተር ነው ። ቅድምያ ለወረቀቱ ሰጠንና ገልጠነው እኔ እንዳነበው ስልጣን ተሰጠኝ ። "የኔ ልጅ ፣ የኔ ስስት ፣ የኔ ህይወት ፡ አንቺን ያገኘሁባትን ያቺን እለት ፡ እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ድረስ መቼም አልረሳትም ። ያን ቀን የኔ ልጅ ፡ ደምና እምባ ነበር ከአይኖቼ የፈሰሰው ። ደስታና ሀዘን በተመሳሳይ ሰዓት ገጥመውኝ ፡ አንድ ጊዜ ሳለቅስ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ስስቅ ብቻዬን ስሰቃይ ነበር ። በቀኝ እጄ አዲስ ህይወት ይዛ የመጣችልኝ የፈጣሪ ስጦታ አንቺን ይዣለሁ ። በግራዬ በኩል ግን በዚች ምድር ላይ አለኝ ብዬ የምኮራባት የአይኔ ብሌን የእናትሽ አስክሬን ተቀምጧል ። አንቺን አገኘሁ ብዬ ደስታዬን እንኳን ሳልጨርስ ፡ ፍቅሬን አጥቼ ህይወት ጨለመብኝ ። እናትሽ ስትወልድሽ ገና #18 አመቷ ነበር ። በዛላይ ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር አቅም አጥታ ህይወቷ አለፈ ። የኔ ልጅ ህይወቴን እናትሽን ያቺ ቀን ብነጠቅም ፡ አንቺን እንደ ምትክ አግኝቻለሁ ። አንቺ ባትኖሪ ምን እንደምሆን አላውቅም ነበር ። ወይ በህይወት የለሁም ፤ ወይም ደግሞ ትርጉም የለሽ ኑሮ ይኖረኝ ይሆናል ። የኔ እናት ፡ በህይወቴ ብዙ አይነት ሰዎችን አይቻለሁ ። ሁሉንም ሰው መጠርጠር አለብሽ እያልኩ አይደለም ። ግን የኔ ልጅ ማንን ማመን እንዳለብሽ ጥንቃቄ አድርጊ ። እስካሁን ድረስ በኔ ምክንያት ከሰዎች ነጥዬሻለው ። በቅርቡ ግን ይሄ ሁሉ ታሪክ ይሆናል ። ትዝ ይልሻል የሆነ ቀን ፡ አንድ ቀን በጣም ደስ የሚያሰኝሽን ነገር አደርግልሻለሁ ያልኩሽን...? ፡ ከምንም በላይ ነፃነትሽን እንደምትፈልጊ አውቃለሁ ። ለእስከአሁኑ እራሱ ተፀፅቻለሁ የኔ ልጅ ። ለምን ለብቻሽ እዚህ እንዳስቀመጥኩሽም ወይ አንድ ቀን እነግርሽ ይሆናል ፤ ወይም ደግሞ ህይወት እራሷ ታስተምርሽ ይሆናል ። ለማንኛውም በቅርቡ ነፃ አወጣሻለሁ ። ይሄን ሳምንት ብቻ ስጪኝ ። ቀጣይ ሳምንት እመጣና ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል ። ውዱ አባትሽ" ። ከደስታ ብዛት የተነሳ ዘላብኝ ነበር የሳመችኝ ። እኔም ደስ ስላላት ብቻ ደስ ብሎኛል ። ሁለታችንም ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን እየተያየን እያለ ፡ ድምፅ ሳታወጣ እምባዋ መፍሰስ ጀመረ ። እንደ ጉድ ይፈሳል ። ትንሽ ቆይታ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ። ይሄኔ ነበር second እንኳን ሳላባክን እቅፌ ውስጥ ያስገባዋት ። 'እሽሽሽ ፡ በቃ ፡ በቃ' እያልኳት እንደምንም ብዬ ለቅሶዋን አስቆምኩኝ ። አንዳንዴ ለብዙ ጊዜያት በናፍቆት ስንጠብው የነበረውን ነገር ስናገኝ በደስታ እናለቅሳለን ። አኛ በነፃ ያገኘነውና ምንም የማይመስለን ነፃነት ለሷ የስንት አመት ምኞቷ ነው ። ለብዙ ደቂቃዎች እቅፌ ውስጥ እንዳለች ለኛ ለሰዎች በነፃ ተሰጥተውን ፡ እኛ ግን አጠቃቀሙን ሳናውቅበት ስላጣናቸው እንዲሁም በሰዎች ምክንያት ስለተነፈግናቸው ነገሮች እያሰብኩ አሳለፍኩ ። በጣም ስለመሸ ተነሽና ተኚ ልላት ስል ፡ እሷ ለካ በእንቅልፍ አለም ተወስዳለች ። ተሸክሜያት ወደ መኝታ ክፍሏ አመራሁ ።

ከእንቅልፌ ስነቃ #01:00 ሰዓት ሆኖ ነበር ። ሶፋ ላይ ነው ያደርኩት ። የከንቲባው ልጅ ቀድማኝ ተነስታ ቆንጆ ቁርስ ሰርታ ደስ ብሎን በላን ። በእቅዴ መሠረት ወደ ጊቢ ለመመለስ ተነሳሁ ። እስከማውቀው ሰፈር ድረስ በመኪናዋ ሸኝታኝ ፡ ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተመለሰች ። በመሄዴ እንደ ደበራት ታስታውቃለች ። እኔም ግድ ሆኖብኝ እንጂ መሄዱን አልፈለኩም ። ስለሷና ስለ አጋጣሚያችን እያሰብኩ ጉዞዬን ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አደረኩ ። በሀሳብ ርቄ መሄዴን ያወኩት ID card ሳላሳይ የጊቢውን በር ሳልፍ ጥበቃው በስድብ ሲወርድብኝ ነበር ። እንዴት እንደደነገጥኩ ። ቆሌዬን ነው የገፈፈው ። (ቆሌ ግን ምንድነው ...🤔) ፡ ይቅርታ ጠይቄ ID አሳይቼ ወደ ዶርም አቀናሁ ። የዶርም ልጆች በመርዶ ነበር የጠበቁኝ ። "ባክህ ትናንት ጊቢው war ሆኖ ነበር የዋለው ። መጀመሪያ ጠዋት አካባቢ ተማሪዎች ከቤተ ክርስቲያን ወደ ጊቢ ሲመለሱ የለበሱት t-shirt የመስቀል ስዕል ነበረው ። (ጊቢ ውስጥ ሀይማኖታዊና ፖለቲካዊ ነክ ልብሶች መልበስ ክልክል ነው) ። በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ ከፌዴራል ጋር የአትገቡም እንገባለን ፀብ ውስጥ ገቡ ። በዚህ መሀል አንዱ ተማሪ አንዱን ፌደራል በድንጋይ ግንባሩን ይለዋል ። ከዛን ፌደራሎቹ ተናደው ጊቢ ውስጥ ያገኙትን ተማሪ እያባረሩ መደብደብ ጀመሩ ። እኛን እራሱ ለምሳ ስንወጣ እግዚአብሔር አተረፈን እንጂ ረግጠውን ነበር ። ይህ የሆነው እንግዲህ ከ #04:00 - #06:00 ሰዓት አካባቢ ነው ። ከዛን #10:00 ሰዓት ላይ ደግሞ ጊቢ ውስጥ GC cup final እግር ኳስ ነበር ። እሱም ተጀምሮ ብዙም ሳይቆይ ደጋፊዎች ለ #2 ተከፍለው ድብድብ ጀመሩ ። ያንዱ ደጋፊ ከሌላኛው መስሎክ ነው ...? ፡ አይደለም ፡ የብሔር ግጭት ነው ። turk/ኦሮ vs Wolfsburg/ማራ ። የሁለቱም ብሔር ተፋላሚዎች ያገኙትን ነገር እየተወራወሩ ፡ አብዛኛው ተማሪ ደግሞ እግሬ አውጪኝ እያለን እንደምንም ዶርም ገባን" ሲለኝ ፡ በሆዴ 'አይ ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ' ብዬ ሳልጨርስ ፡ "በዚሁ ያበቃ መስሎክ ነው ...?" ብሎ የቀረውን ቀጠለልኝ ። "ማታ ላይ የስታዲየሙ ክፍል ሁለት ጦርነት ቀጠለ ። በብሔር ተከፋፍለው ጭራሽ ዶርም ለዶርም እየዞሩ መከሻከሽ ይጀምራሉ ። ብዙ ተማሪዎች ከተጎዱ በዋላ ፌደራል መጣና #5 ጊዜ ወደላይ ተኩሶ በታተናቸውና ወደ መጡበት ተመለሱ" ብሎ ትረካውን አጠቃለለልኝ ። history መፃፍ የሚያነብልኝ ነበር የመሰለኝ ። እና ቀጣይ ምን ሊሆን ነው ብዬ ስጠይቀው "ተማሪዎች ቀጣይ ሳምንት ለ #3 ተከታታይ ቀናት class አንገባም ብለዋል" አለኝ ። እንዴት ደስ እንዳለኝ ideaw የላችሁም ። ደስ ያለኝ በረብሻው ምከንያት አይደለም ፤ ትምህርት ስለሌለ እንጂ ። ቀኔ ብሩህ እንዲሆን ትምህርት ከሌለ ብቻ ይበቃኛል ። ከሱ በላይ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር ያለም አይመስለኝም ። ሻዎር ወስጄ ፣ ልብሴን ቀይሬ ፡ አዲስ ነገር ካለ ደውለው እንዲያሳውቁኝ ለዶርሜ ልጆች ነግሬያቸው ወደ ከንቲባው ልጅ ለመሄድ መንገድ ጀመርኩኝ ። መንገዱ እንዳልጠፋብኝ ያወኩት በሩ ጋር ስደርስ ነበር ። ምናልባት እቤት ከመጣህ ደውልልኝ እንጂ አታንኳኳ እሺ ፡ ብላኝ ስለነበር ፤ ደውዬ ደጃፏ ላይ እንደቆምኩ ነገርኳት ። ደቂቃ ሳታባክን በሩን ከፍታልኝ ፡ በደስታ ተጠመጠመችብኝ ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል..................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 10


.
.
.
የሆነ ነገር ወዳልሆነ ነገር ሊመራክ ከሆነ ፡ ማድረግ ያለብህ ከሆነ ነገር መራቅ ነው ። አልጋ ልብሱን አልብሻት ወደ አልጋዬ ተመልሼ ተኛሁ ። ጠዋት ነግቶ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፡ #03 ሰዓት አልፎ ነበር ። እዛው ካለንበት ሆቴል ቆንጆ ቁርስ በልተን ፡ ያለብንን የ #1 ለሊት የቤት ኪራይ ከፍለን ወደ ቡቲክ አመራን ። ውቢቷ ቢሾፍቱ ላይ ፈክተን የምናበራበትን ልብስ ገዝተን #05:30 ላይ ጉዞአችንን ወደዛው አደረግን ። ለሸገር ቅርብ ስለሆነች ብዙም ደቂቃ አልፈጀብንም ። ኩሪፍቱ ሪዞርት ከበር ላይ በክብር ተቀበሉን ። የምንቆይበት ክፍል ይዘን ፈታ ለማለት ትጥቃችንን አሟልተን ወደ መዋኛ ገንዳ አመራን ። ዋና እንደማትችል ጠጋ ብላ በጆሮዬ ነገረችኝ ። እኔም ልክ እሷ እንደነገረችኝ ፈራ ተባ እያልኩ በጆሮዋ እንደማልችል ነገርኳት ። በድንጋጤ አየችኝና "እና ምን ልናደርግ ነው የመጣነው ...? ፡ እኔ ደግሞ ምትችል መስሎኝ አንተን ተስፋ ማድረጌ" አለችኝ አኩርፋ ። ከዛን ሳኩባትና 'ስቀልድ ነው ባክሽ ፡ ዶልፊን እራሱ ጉልበቴ ስር ቁጭ ብሎ ነው የተማረው' አልኳት ። (ዶልፊን ግን ቁጭ ማለት ይችላል እንዴ ...) ። "ሂድ ፡ ጉረኛ" አለችኝና ትከሻዬን በፍቅር መታችኝ ። እኔ ለክባድ ብዬ ተከርብቼ ውሃው ውስጥ ገባሁ ። እሷ ግን ውሃ ነክታ አታውቅም መሠለኝ በስንት ልመና በዳዴ ገባች ። ለመዋኘት ገብቼ አሰልጣኝ ሆኜ አረፍኩ ። ያን ያክል እንኳን አላስቸገረችኝም ። ነገሮችን በቀላሉ የመያዝ ልዩ ችሎታ አላት ። ዋና የለመድኩት እንዲህ ባማረ ገንዳ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንዝ ውስጥ ነበር ። እየዋኘሁ ፣ እያለማመድኳት ፣ እያረፍን ፣ በድጋሜ ያሁኑን step እየደገምን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። አይን አይኔን እያየች "አስቸገርኩህ አይደል ...? ፡ በቃ የመጨረሻ አንድ ዙር አለማምደኝና ይብቃን" አለችኝ ። ሁለቱ እጆቼን ውሃው ውስጥ እንደ ምንጣፍ ዘረጋሁላት ። በሆዷና ታፋዋ እጆቼ ላይ ተኝታ በእጆቿ ደግሞ ውሃውን ወደ ዋላዋ እየገፋች ወደ ፊት ትመነጠቃለች ። እኔም ከጎኗ ሆኜ እከተላታለሁ ። እንደዛ እያደረገን የገንዳው ጫፍ ላይ ደረስን ። ከእጆቼ ላይ ወርዳ እዛው ውሃው ውስጥ በኔ ፊትለፊት ቆመችና አይን ለአይን ተጋጨን ። ውበቷ እንዴት እንደ ሚያስደነግጥ ideaw የላቹም ። አላወቁም እንጂ ሴቶቻችን የሚያምሩት በሜካፕ ሳይሆን በተፈጥሮአቸው ነው ። በዋናው ውሃ ታጥባ ኩልል ብላ ቆማ ስታየኝ ፈዘዝኩኝ ። በጣም ተቀራርበናል ። እንደውም ንፋስ በመሃላችን ለማለፍ ፈልጎ ሲታገለን ይሰማኛል ። አይኖቼ ከንፈሯ ላይ ደርቀው ቀሩ ። እሷም እንደኔው በአይኖቿ ከንፈሬ አካባቢ እየሾፈችኝ ነው ። ወደ ከንፈሬ በጣም ቀረበች ። ከንፈሯ እንኳን እሁድ ተገኝቶ ፡ እሮብንና አርብን እራሱ ያስገድፋሉ ። የሁለታችንም ስሜት እናታችን ላይ ሲወጣ ተጎራረስን ። ከንፈሯ ከከንፈሬ ፣ ትንፋሿ ከትንፋሼ ተዳመረ ። የኔን ትንፋሽ ወስዳ የሷን ለገሰችኝ ። ትንፋሿ ይሞቃል ፤ ከንፈሯ ይጣፍጣል ። ለብዙ ሴኮንዶች ከንፈር ለከንፈር ተገጣጥመን ፡ የአለምን አየር ንቀን ውስጣችን ያለውን ተለጋግሰን ዋና ገንዳው ውስጥ ከቆየን በዋላ ከንፈራችን ተላቀቀ ፡ አይናችንም ተከፈተ ። ትንሽ እንደ መተፋፈር ሆነን ከውሃው ውስጥ ወጣን ። በርዷት ነው መሠለኝ መንሰፍሰፍ ጀመረች ። አሳዘነችኝና ፎጣ አልብሻት ተሸከምኳትና ወደ ክፍላችን ጉዞ ጀመርኩኝ ።
እሷን መሸከም ለኔ ብርቄም ድንቄም አይደለም ። ሶፋ ላይ በተኛችና በሰከረች ቁጥር እስከ መኝታ ክፍሏ የማድረስ የሁለት ቀን ስራ ልምድ አለኝ ። የዛሬው ግን ለየት ይላል ። አልሰከረችም ፣ አልተኛችም ፣ እራሷን አልሳተችም ፣ አይኖቿ አልተከደኑም ፣ ወዘተ ። ክፍላችንን እንደምንም በአንድ እጄ ከፍቼ ገባንና መልሼ በእግሬ ዘግቼው አልጋው ላይ ቀስ ብዬ አስተኛዋት ። አይኗን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ወደላይ በስስት ታየኛለች ። እኔም ወደታች እንደዛው ። አንዲት ቃል ሳናወጣ በአይኖቻችን ብቻ እናወራለን ። ከዛን እጆቿን አንገቴ ላይ ጠምጥማ ወደራሷ ጎተተችኝና ድጋሜ ከንፈሮቻችን ህብረት ፈጠሩ ። ፎጣውን ከላዩዋ ላይ ወርውራ አልጋው ላይ ጣለችኝ ። ሁለታችንም ከዋና ገንዳው እንደ ወጣን ፡ እኔ ከላይ ራቁቴን ፡ ከስር ደግሞ በዋናው ቁምጣ ፤ እሷ ደግሞ ከላይ ጡት ማስያዣና ከስር በዋናው ፓንት ነው ያለነው ። ቅድም ከውሃው ስንወጣ በርዷት እንደዛ እንዳል ተንዘፈዘፈች ፡ አሁን ላይ ግን ገላዋ በሙሉ እንደ እሳት እየፈጀኝ ይገኛል ። አንገቷ ስር ገብቼ ስስማት ፡ አይኖቿን ጨፍና ፣ ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፣ መልሳ ደግሞ በሀይል ትተነፍሳለች ። (አንገቷ ስር ከገባህ ፡ አይኗን ስትጨፍን እንዴት አየህ ...) ። ዛሬም እንደ በፊቱ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም' አልኩ ለራሴ ። ምን እያደረግን ነው ...? ፡ እዚህ ድረስ ለምን መጣን ...? ፡ ፈታ ማለት ምን ማለት ነው ...? ፡ አልኩኝ ለራሴ ። ከሀሳቤ ነቃሁ ፡ ከአንገቷ ምሽግ ወጣሁ ፡ ከአልጋዋ ላይ ተነሳሁ ፡ ወደ ራሴ አልጋ ሄድኩ ፡ ወደ ራሴም ተመለስኩ ። እሷም ግራ በመጋባትና በመናደድ አይነት ስሜት ከተኛችበት ቀና ብላ ታየኛለች ። የሆነ ነገር ልትለኝ ስትል በራችን ተንኳኳ ። እኔ እከፍታለሁ አልኳትና ከላይ ሸሚዝ ለብሼ ከፈትኩኝ ። አስተናጋጅ ነበር እና "የምትፈልጉት ነገር ካለ ማዘዝ ይቻላል" አለኝ በክብር እጅ እየነሳኝ ። እኔም 'ትንሽ ርቦናልና ምግብ ብናገኝ ደስ ይለናል' አልኩት ። እሱም "ከፈለጋችሁ እዚህ ፡ ፍቃዳችሁ ከሆነም ደስ የሚል ቦታ እወስዳችሁና እዛ ትበላላችሁ" አለኝ ። 'አይ ፡ ላሁኑ እዚህ እንበላለን ፤ ባይሆን ደስ የሚለውን ቦታ ማታ ትወስደናለህ' አልኩትና ሄደ ። #08 ሰዓት አልፏል ። አኩርፋኝ ቢሆንም አስተናጋጁ ያመጣልንን ምግብ እንደ ተለመደው ለራሷ ሳትበላ መጀመሪያ አጎረሰችኝ ። እኔም አጎረስኳትና ትንሽ በልተን ተውነው ። ከበላን በዋላም ሁለታችንም በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን ሳናወራ ጀምበር እየታዘበችን ወደ ቤቷ ገባች ። ላወራት ብዬ ስነሳ በራችን ድጋሜ ተንኳኳ ። ስከፍት የቅድሙ አስተናጋጅ ነበርና ቅድም ወዳለኝ ቦታ ሊወስደን እንደ መጣ ነገረኝ ። #10 ደቂቃ ስጠን ብዬው ፡ ተመልሼ ፈራ ተባ እያልኩ ልጅቷን ቀሰቀስኳት ። 'ተነሽና ልብስሽን ቀይሪ ፡ ወደ ሆነ ቦታ እንሄዳለን' አልኳት ። አልተቃወመችኝም ፡ ልትቀይር ወደ ውስጥ ገባች ። ከሸገር የገዛነውን ልብስ አውጥቼ ለበስኩትና እሷ እስክትጨርስ መጠበቅ ጀመርኩኝ ። በዛ ውበቷ ላይ ቅድም የገዛነውን ልብስ እሷ ላይ ስስለው ፡ በቃ ጨረቃ እራሷ በአካል መጥታ የምታገኘኝ መሠለኝ ። ልጅቷ ከገባችበት ቀይራ ወጣች ።
"ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ደምቀሽ ስትወጪ ፣
ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ጨረቃ አፈረች" ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 9


.
.
.
ስትሸና ያው እኔን ማፈሯ አይቀርም ብዬ እንድትከለል ፡ ጫካ እንደሌለ እያወኩ ለወጉ በአይኔ መፈለግ ጀመርኩኝ ። የድሬ ሸገር መንገድ ዳር ላይ መደበቅያ ጫካ ከመፈልግ ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኝነትን ማስቆም ይቀላል ። ለነገሩ ሽንት ለመሽናት ጫካው አስፈላጊ አይመስለኝም ። ብዙ ጊዜ መንገድ ስንሄድ ሽንት ሲመጣብን ለዛፎቹ አስበን ይመስል ወደ ጫካ እንሮጣለን ። ከሰው ለመደበቅ ነው እኮ ... ። በነ ጦጢት እየተሾፈን እንደሆነ ማን በነገረን ። anyways ጫካ ስላጣን በመኪናው ተከልላ ሸንታለች ። እኔኮ ግርም የሚለኝ ሰው ሲሸና ጠብቆ ሽንቴ የሚመጣው ጉድ ነው ። ውሃ ስለማልጠጣ ሽንት አዘውትሮ የመሽናት ልምድ የለኝም ። (መሽናቴ ካልቀረ ምን አስጠጣኝ ...) ። #08:00 ሰዓት አልፏል ። አዲስ አበባ ለመግባት በግምት #2 ሰዓት ይቀረናል ። ሸገር ለ #1 ቀን ማደር ስለፈለግን እንጂ ቀጥታ ቢሾፍቱ መሄድ አላቃተንም ። ከስንት ድካም በዋላ ልክ #09:42 ደቂቃ ላይ በአቂቃ ቃሊቲ በኩል አዲስ አበባ ገባን ። መንገዶች ሁሉ በመኪናና ሰዎች ተሸፍኗል ። እንደምንም ክፍት መንገድ ባየን ቁጥር እየሾለክን ቦሌ ካንዱ ሆቴል ጎራ ብለን #1 ክፍል ያዝን ። በጣም ደክሞን ስለነበር ሁለታችንም ሻዎር ገባን (አንድላይ አይደለም ፡ ብቻ ለብቻ ነው ደግሞ...) ። እንግዲህ ዛሬን ሸገር ላይ ፍልስስ ልንል ነው ። አዲስ አበባ እንደ ድሬ አይደለችም ። የሰው ብዛት ፣ የመኪናው ጋጋታ ፣ የህንፃዎቹ ብዛትና ውበት ፣ የከተማው ስፋት ፣ ባጠቃላይ ሸገር እንደ ድሬ ቶሎ ምትለመድ አይነት አይደለችም ። እዛው ከያዝነው ሆቴል እራት በልተን ፡ ወይን እየጠጣን ስሟን ለመምሰል ሌት ተቀን ደፋ ቀና የምትለዋን ከተማ ከላይኛው ፎቅ ቁልቁል ወደታች እያየናት ነው ። ሆቴሉ ግሩም ነው ፤ ከላይ በሁሉም አቅጣጫ ከተማዋን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ። ምሽት ላይ ከላይ ስትታይ ስሟን ትመሰላለች ። የከንቲባው ልጅ "ወይ አዲስ አበባ" እያለች ትገረማለች ። ከዛን ወደኔ ዙራ "ስማኝማ ፡ ፈታ ልንል ነው አይደል ይሄን ሁሉ ርቀት አቋርጠን የመጣነው ...?" አለችኝ ። አዎ ስላት "እንደዛ ከሆነ ፡ በናትህ ፡ ስወድህ ፡ night club ውሰደኝ" አለችኝ ። "ጀማሪ እረኛ ፡ ከብት አያስተኛ" ይለዋል የሀገሬ ሰው ። ልጅቷ እቤት ሆና በፊልም ያየችውን ነገር ባካል ማየትና ማድረግ ትፈልጋለች ። ደግነቱ ከያዝነው ሆቴል አጠገብ club ይታየኛል ። እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደዛው አመራን ። entrance / መግቢያ ከፍለን ፡ ተፈትሸን ገባን ። ጎበዝ ፡ ወጣቱ እዚህ አ እንዴ ያለው ። ለካ ኢትዮጵያ ወደ ዋላ የቀረችው ወዳ አይደለም ። መደማመጥ የለም ፡ ጭፈራ ብቻ ነው ። የእስፒከሩ ጩኸት ፣ የሰው ጫጫታና ዳንስ ቦታውን ሶሪያ አስመስሎታል ። "እንቅስቃሴዎች ሁሉ dance ናቸው" የሚለውን ዘፈን teddy yo እዚህ ቤት ቁጭ ብሎ የፃፈ ይመስላል ። እኔ እንኳን club ስገባ የመጀመሪያዬ ስለሆነ ስራቴን ይዤ ቁጭ ብያለሁ ። ባይሆን መጠጧን አንድ ሁለት እያልኩኝ ፡ ትርዒቱን እያየሁ ልምድ እየቀሰምኩ ነው ። ልጅት ደግሞ በስሜት አሸሸ ገዳሜውን ለመቀላቀል #1mm ነው የቀራት።

"ሂድልኝ ሀዘን ጭንቀቴ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ ፣
ጥፋልኝ ሀዘን ህመሜ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ" ።
ብቻችሁን መምጣት ክልክል ነው የተባለ ይመስል ፡ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የመጡት (ልክ እንደኛው ...) ። የፈራሁት አልቀረም ፡ የከንቲባው ልጅ እጄን ይዛ አስነስታኝ ትርዒቱ መሃል ቁጭ (ይቅርታ ቁም ለማለት ነው ...) ። እንቅስቃሴ ጀምረናል ፡ ለነገሩ dance ላይ ብዙም የስራ ልምድ ስለሌለኝ እየጨፈርኩ ሳይሆን እየተወላገድኩ ነው ብል ይቀለኛል ። በመሀል በመሀል አንድ ሁለቱን ፡ ሶስት አራት እያልነው ነው ። ፊልም ላይ አረቄ /Jin ባንድ ትንፋሽ እንደዛ ሲጨልጡት በውሃ የሚያታልሉን ይመስለኝ ነበር ። ዛሬ ግን በአይኔ በብረቱ አይቼ አምኛለሁ (አይን ብረት ነው እንዴ ...) ። ኧረ ሴቶቻችን ተበላሽተዋል ጎበዝ ። ከወንዶቹ ይልቅ እነሱ ባሱኮ ። የሌሎቹ ሲገርመኝ የኔዋ ጉድ ብሳ ተገኘች ። እየጠጣን ፣ እየጨፈርን ፣ እያረፍን ፣ በድጋሚ የአሁኑን step እየደገምን በስተመጨረሻ ልጅቷ ውሃ ሆና እላዬ ላይ ተዘረገፈች ። እንዴት ተሸክሜያት ከክለቡ እስከ ያዝንበት ሆቴል እንዳደረስኳት ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው (እኔም ግን አውቃለሁ ...) ። በስንት ድካም የያዝነው ክፍል ደረስንና አልጋው ላይ ዘረገፍኳት ። ንሰሐ ገብቼ ሀጥያቴን የተናዘዝኩ ያክል ነው ቅልል ያለኝ ። የለበሰችው አጭር ቀሚስ ገላዋን ሙሉ በሙሉ የመሸፈን አቅም አልነበረውም ። በቀላል maths ከወገብ በታች አካሏ #80% ይታያል ። አልተን ገዳገድኩም እንጂ መጠጡ አናቴ ላይ ወጥቷል ። እሷ ግን የት እንዳለች እራሱ የምታውቅ አይመስለኝም ። የያዝነው #1 ክፍል ቢሆንም #2 አልጋ አለው ። እኔ አልጋዬ ላይ ሆኜ በእውን እያየዃት ፤ እሷ ደግሞ በስካር አለም ተወስዳ ተኝታለች ። የሰው ልጅ ከእንስሳ የሚለየው እራሱን መግዛት በመቻሉ ነው ። እንስሳት እራሳቸውን መግዛት ስለማይችሉ ያገኙትን በልተው ፣ ካገኙት ጋር ወስበው ፣ ሂድ ወደ ተባሉበት ሄደው ይኖራሉ እንጂ እንደ ሰው በእቅድና አላማ አይንቀሳቀሱም ። የሰው አፈጣጠር ግን ይለያል ። ህሊና ከሚባል ዳኛ ጋር ስለተፈጠረ በጎ ሲያደርግ በርታ ፣ መጥፎውን ነገር ሊሰራ ሲል ደግሞ እረፍ ፣ ከሰራም በዋላ ደግሞ በድለሀል ይቅር በል የሚል ከሳሽ አይምሮው ውስጥ ተቀምጧል ። የሰው ልጅ በሁለት መንገድ ይበድላል ። አውቆና ሳያውቅ ። ሳያውቁ ያደረጉት ይሁን ፤ ነገር ግን እያወቁ ማጥፋት የጥፋት ሁሉ ጥፋት ነው ። ብዙ ጊዜ ስካርን ተገን በማድረግ ብዙ ስተት ይፈፀማል ። በዚች ሰዓት እኔ እራሴን አልሳትኩም ። ስለዚህ እራሴን መግዛት እችላለሁ ማለት ነው ። መጥፎ ነገርን አለማድረግ እየተቻለ ማድረግ ሰይጣንነት ነው ። ይቺ ልጅ እዚህ ድረስ አብራኝ የመጣችው ስላመነችኝ ነው ። በዚህ ዘመን ደግሞ የሰውን እምነት ማግኘት የማይገኝ ትልቁ ፀጋ ነው ። ወደሷ ጠጋ ብዬ ጫማዋን አወለኩላት ። ወደ ከንፈሯ ተጠጋሁና ጆሮዬን አፏ ላይ ደቀንኩት ። ትንፋሿ ሰውነቴን ውርር ስያደርገኝ በህይወት እንዳለች አረጋገጥኩኝ ። አይኖቼ ከእግር እስከ እራስ ፀጉሯ ድረስ scan አረጓት ። ይሄ ነገር ወንድነቴን እየተፈታተነው ነው መሰለኝ ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 11


.
.
.
ይሄን የመሠለ ውበትማ ለትውልድ እንደ ቅርስ መተላለፍ አለበት ብዬ ስላሰብኩኝ አስተናጋጁን ፎቶ አንሳን ብዬው ተነሳን ። እኔ በሱፍ ነኝ ፤ እሷ ቬሎ ነገር ጣል ብታደርግ ኖሮ የሰርግ ፎቶ ነው የሚመስለው ። እጅ ለእጅ ተያይዘን አስተናጋጁ ወደ ሚወስደን ቦታ ደረስን ። በአበባ የተሽቆጠቆጠ መሬት ፣ እጅግ ውብ በሆኑ ምግብና ወይን የተሞላ ጠረጴዛ ፣ ለስለስ ብሎ ከተለቀቀ ሙዚቃ ጋር ተፋጠጥን ። የከንቲባው ልጅ ቅድም ተኮራርፈን ስትተኛ ከአስተናጋጁ ጋር በመተባበር

‍ ነበር እንዲህ ያስዋብነው ። ለቦታው ደግሞ ይበልጥ ውበት የሰጠው ፡ አጠገቡ ሀይቅ መኖሩ ነው ። አስተናጋጁ "መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ፡ የምትፈልጉት ነገር ካለ ይችን ደወል መጫን ብቻ ነው" ብሎን ጠረጴዛ ላይ ወዳለው ነገር ጠቁሞን ሄደ ። ጨረቃዋ ቁልቁል በቅናት እያየችን ደስ የሚል እራት በልተን ወይን እየጠጣን ነው ። "ጨረቃዋ አታምርም የኔ ጌታ ...?" አለችኝ ። ትኩር ብዬ አይኖቿን እያየሁ 'ካንቺ ባትበልጥም ቆንጅዬ ናት' አልኳት ። እንደተለመደው በፍቅር ትከሻዬን እየመታች "ሙት እሺ" ትለኛለች ። ለጨዋታው ድምቀት 'አንቺ እንዳታለቅሺ አስቤ እንጂ እኔኮ መሞት አላቃተኝም' ስላት ፡ ባንዴ ፊቷ ተቀያይሮ ብርሃን ይመስሉ የነበሩ አይኖቿ ወደ ደመናነት ተቀይረው በእንባ ተሞሉ ። 'አንቺ አመረርሽው እንዴ ፡ እኔኮ እየቀለድኩ ነው' ስላት ፡ "ካሁን በዋላ ግን ለቀልድም ይሁን አይሁን ፡ እሞታለሁ እንዳትለኝ እሺ ...?" አለችኝ እንባ እየተናነቃት ። አንጀቴን ስትበላኝ ቁጭ ብዬ ማየት ከበደኝ ። ከወንበሬ ላይ ተነሳሁና ተንበርክኬ 'እሺ በቃ አይለምደኝም' አልኳትና እንባዋን ጠራርጌ ከተቀመጠችበት እጇን ይዤ ተነሳን ። ወደ ጆሮዋ በአፌ ተጠግቼ በለሆሳስ 'ከኔጋር መደነስ አትፈልጊም...?' አልኳት ። "አሎድህም እሺ ...!" አለችኝና በፈገግታ ለዳንሱ እጇን ዘረጋችልኝ ። ያው የተከፈተው ሙዚቃ ለስለስ ያለ ስለሆነ የኛም ውዝዋዜ ጠንከር ያለ አይደለም ። ግራ እጄን እንደ እናቶቻችን መቀነት ወገቧ ላይ ጠምጥሜ ፣ የቀኝ እጄን ጣቶች የግራ እጇን ጣቶች ክፍተት ሞልቼበት ፣ እሷም ቀኝ እጇን ትከሻዬ ላይ አሳርፋ ፣ በእግሮቻችን አንዴ ወደፊት ፡ አንዴ ወደዋላ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ጎን እያልን በመሀል በመሀል ደግሞ እያወራን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። ከደሬቴ ላይ ተነስታ ቀና ብላ አይን አይኔን ታያለች ። እንዲህ ስታየኝ ደግሞ ልቤን ታቆመዋለች ፤ ምድር ላይ መኖሬን ታስረሳኛለች ። አይኖቿ ውስጥ እስከ ዳግም ምፅአት ድረስ የሚበቃ የብርሃን ሀይል ይታየኛል ። ወረድ ብዬ ከንፈሯን ሳይ ደግሞ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ትዝ ይለኛል ።
"ሳማት ሳማት አለኝና ፡
ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣
ሳሙኝ ፡ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ፡
ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር" ።
ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል የሚያደርገኝ ። እነዚያ የህይወትን ነዳጅ የሚያመነጩ ከንፈሮቿን ስጎርስ እስከ እለተ ሞቴ ድረስ ምግብ ባልበላ እንኳ የሚያኖሩኝ ይመስሉኛል ። ስስማት አይኖቿን ጭፍን አርጋ ትቀልጥብኝ ነበር ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ "ውጪው ይበርዳል አይደል የኔ ጌታ ፡ ወደ ውስጥ እንግባ ...?" አለችኝ ።
እንዳለችውም ውጪው ያን ያክል ባይበርድም ፡ ሃሳቧን ላለመቃወም ብዬ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ክፍላችን አመራን ። ወደ ክፍላችን የሚወስደን ደረጃ ጋ ስንደርስ "እንደ ቅድሙ ተሸክመኸኝ አትገባም የኔ ጌታ" አለችኝ ። ልክ ሙሽሮች የሰርጋቸው ለት ማታ እንግዳውን "በሉ እናንተ ብሉ ፣ ጠጡ ፣ ጨፍሩ ፡ እኛ ልንተኛ ነው" ብለው ወደ መኝታቸው እንደ ሚሄዱ ፤ እኔም ልጅቷን እንደ ሙሽራ ተሸክሜያት ፡ እሷ ደግሞ በተዘረጉላት እጆቼ ላይ ፍልስስ ብላ ወደላይ እያየችኝ አልጋው ጋር ደረስን ። ዛሬ ፈርቻለሁ ፤ የፈሩት ደግሞ ይደርሳል ተብሎ ተፅፏል ። ከጠጣነው ወይን ይልቅ ትንፋሿ አሰከረኝ ። ከተቀባነው ሽቶ ይበልጥ የገላዋ መዐዛ ማረከኝ ። ልብሶቻችንን ማወላለቅ ጀመርን ። ኮቴ ፣ ሸሚዜ ፣ የሷም ልብስ እንደዛው ። እኔ ከላይ ፤ እሷ ከታች ። በዚህ መሀል ነበር የአንገት መስቀሌ ከአንገቴ ላይ በመሀላችን ሲንጠለጠል በድንጋጤ የተነሳሁት ። እንደ ቅድሙ ዝም አላለችኝም ። "የሆንከው ነገር ካለ ለምን አትነግረኝም ፡ እእእ ...?" አለችኝ በልመና አይነት ድምፅ ። አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ልነግራት ተዘጋጀሁ ። 'እየውልሽ ህይወት ፡ የፍቅር ታሪኬን አንድ ቀን እነግርሻለሁ ብዬሽ ነበር ። እና እሱን ዛሬ ብነግርሽ ነው የሚሻለው ብዬ ታሪኩን ጀመርኩላት ። #2007 ዓ.ም ክረምት ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ከዱከም / ደብረ ዘይት ከተማ ዘመድ ጥየቃ ወደ ሙገር ትመጣለች ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየዋት በካምፓችን ውስጥ በሚገኘው ሆቴል ቁጭ ብላ መፅሐፍ ስታነብ ነበር ። ብዙ የሰፈራችን ልጆችም በስፍራው ላይ ነበሩ ። አዲስ ሴት በሰፈራችን ከታየች ደግሞ አብዛኛው ወንድ ይጋደልባታል ። እዛ የነበሩት ወንዶች ተራ በተራ ወደሷ እየሄዱ አፍረው ተመለሱ ። ልጅቷ መስሚያዋ ጥጥ ነበር ። እኔ ደግሞ በዚያን ጊዜ ሴት ልጅን እንኳን ቀርቤ ላናግራት ይቅርና አይኔን ብቻ ካዩኝ በፍርሃት እምባዬ ይመጣል ። ያቺን ቀን ያቺን ልጅ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኜ በማየት ብቻ ቀኑ አለፈ ። ከዛን ቀን በዋላ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ ነበርኩና ፕሮግራም አዘጋጅተን ነበር ። እና ያቺን ልጅ ድጋሜ እዛ አየዋት ። ያን ምሽት ተዋውቀን ከቤተ ክርስቲያን አብረን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ መንገድ ላይ ዝናብ መጣብን ። ፀጉሯ ቱክስ ስለነበር እንዳይበላሽባት እንሩጥ አልኳት ። እሷ ግን "ዝናብ በጣም ስለምወድ እንደውም ቀስ ብለን እንሂድ" አለችኝ ። ሁሉም ሰው ከዝናቡ ሸሽቶ ወደቤት ገብቷል ። እኔና እሷ ብቻ በእግዚአብሔር ፀበል እየተጠመቅን በኩራት ዝናብ ውስጥ እየሄድን ፡ እሷ ስለምትወድ ብቻ ብርዱን እየጠጣሁ እስከ ዘመዷ ቤት አደረስኳት ። ብዙም አልተግባባንም ፤ ልጅቷ ብዙም አታወራም ነበር ። ግን በጣም ሳቂታ እንደ ነበረች አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል ። ብዙም ሳላውቃት መሄጃዋ እንደ ደረሰ ነገረችኝ ። የተገናኘነው ከሶስት ቀን አያልፍም ፤ እሱንም ለትንሽ ደቂቃ ፡ ያውም ብዙም ሳናወራ ። ስልክ ቁጥሬን የ #2008 የእንቁጣጣሽ ፖስት ካርድ ላይ ፅፌ ሰጥቻት ተሰነባበትን ። ከዛን ቀን በዋላ ያቺን ልጅ ሳላያት አንዱ ክረምት አልቆ ሌላኛው ተተካ ። ከሁለት ዓመት በዋላ #2009 ዓ.ም ክረምት ላይ ድጋሜ ወደ ሙገር መጣች ። ስለሷ ከስሟና ከመጣችበት ዘመድ ቤት ውጪ ምንም ነገር አላውቅም ነበር ። እሷ ደግሞ ከመጣች በዋላ ስሜ ጠፍቶባት ታሪኩ በሚል ስም እኔን ፍለጋ ጀመረች ።...


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 12
.
.
.
.
'በኛ ካምፕ ውስጥ ደግሞ አንድ ታሪኩ ብቻ ነበር ያለው ፤ እሱም ምርጥ ጓደኛዬ ነበር ። ከዛን ልጆች እሱን ጠቁመዋት አገኘችው ። ስታየው እኔ እንዳልሆንኩ አወቀች ። ታሪኩ ደግሞ ከኔጋር ሲገናኝ ስሟንና ከየት እንደመጣች እየጠቆመ የተፈጠረውን ነገረኝ ። ያኔ ነበር እኔን እየፈለገች እንደሆነ የተረዳሁት ። ቀኑን አላውቅም እንጂ እንደ ማገኛት አውቅ ነበር ። ከሁለት ዓመት በዋላ ያቺን ልጅ ድጋሜ አየዋት ። ቆንጅናዋ እንዳለ ነው ፤ ኧረ እንደውም ይበልጥ ተውባ ነበር ። ተገናኘን ፣ ተቃቀፍን ፣ ለብዙ ሰዓት ቁጭ ብለን አወራን ። ሲመሽብን ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተለያየን ። ከዛን ቀን አንስቶ ወደ ዱከም እስክትመለስ ድረስ በየቀኑ እንገናኝ ነበር ። ሁለታችንም እንደ በፊቱ ዝምተኛ አልነበርንም ። ስለ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተጫወትን ፣ ብዙ ቦታ አብረን ዞርን ። በቃ ባጠቃላይ ፊልም ላይ ወይንም ልቦለድ ላይ የምታውቂውን የፍቅር ህይወት አብረን አሳለፍን ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሷን ከንፈር ነበር የሳምኩት ። ወክቱ ክረምት ነበር ፤ የቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ" አልበም ደግሞ በብዛት ይደመጥ ነበር ። ከሱ አልበም ውስጥ ሁለታችንም "ማራኪዬ" የሚለውን ዘፈን ከቴዲ አፍሮ በላይ ወደድነው ። ልምድ ሆኖብን ሁለታችንም ከዛን በዋላ #ማራኪዬ እያልን መጠራራት ጀመርን ። ማንም ወንድ ቢቀርባት በፍቅር የሚወድቅላት ልጅ ነበረች ። እኔም ወደኩላት ። በጣም ነበር የምንዋደደው ፤ ከምነግርሽ በላይ ። የሚገርምሽ ቀኑን ሙሉ አብረን ውለን ሰለ ማንጠጋገብ ማታ ማታ ደግሞ በስልክ txt እንፃፃፍ ነበር ። እንደውም የሆነ ቀን የተፃፃፍነውን የመልዕክት ብዛት ሳይ #5000 አልፎ ነበር ። እና ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። የኔ አሳቢ ፣ የኔ እናት ፣ የኔ ፍቅር ፣ የኔ ረቡኒ ፣ በቃ ምን ልበልሽ ፡ እሷን ምድር ላይ ያሉ ቃላት አይገልጿትም ። በዚች ምድር ላይ እንደሷ የሚወደኝ ፤ እኔም እንደሷ የምወደው አልነበረኝም ። ፍቅርን ምድር ላይ ባሉት ነገሮች ግለፅልኝ ቢሉኝ #ማራኪዬን ነበር የምጠቁመው ። ያን ጊዜ እሷ የ #10ኛ ክፍል matric ፡ እኔ ደግሞ የ #12ኛ ክፍል entrance ፈተና ወስደን ውጤት የምንጠብቅበት ነበር ። ክረምቱን አብረን በፍቅር ዘመትን ። የመጣችሁ ክረምቱን ዘመድ ጋር ለማሳለፍ ነበርና ክረምቱ ሲገባደድ መሄጃዋ ደርሶ በእምባ ተለያየን ። ውጤት ተለቀቀ ፡ ሁለታችንም አለፍን ፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ ። በስልክ ብቻ በየቀኑ txt እየተፃፃፍን ፡ በሳምንት እየተደዋወልን #8 ወር አለፈ ። ናፍቆታችን ገደቡን ሲያልፍ ቢሾፍቱ መጥቼ እንደማገኛት ቃል ገባሁላት ። በቃሌ መሠረትም ለፋሲካ በዓል ወደ ቤት ስመለስ አንድ ቀን ቀደም ብዬ ከድሬዳዋ ፡ ሸገር ፡ ከዛም ደብረ ዘይት እሷን ላገኛት ሄድኩኝ ። ለሶስተኛ ጊዜ ቢሾፍቱ የሄድኩት ያኔ ነበር ። #27-08-2010 ዓ.ም ። ተገናኘን ፣ በፍቅር ተቃቀፍን ። ስንተያይ እንዴት ደስ እንዳለን ideaw የለሽም ። የሆሳዕና ሳምንት ነበርና የሰራሁላትን የዘንባባ ቀለበት አደረኩላት ። ደብረ ዘይት ላይ አብረን ለ #3 ሰዓታት በፍቅር ሰከርን ። የመጀመሪያው ምሳችንን አብረን በላን ፣ ቢሾፍቱ ሀይቅ ሄደን juice እየጠጣን ተዝናናን ፣ photo ተነሳን ፣ ስለኛ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተሳሳምን ፣ ተቃቀፍን ፣ ብቻ ያቺን ቀን በህይወቴ መቼም አልረሳትም ። ስጦታ የአንገት መስቀል አስራልኝ ልባችን እያለቀሰ ተለያየን ። እና አሁን አንገቴ ላይ የምታዪው ይህ መስቀል ማራኪዬ ያን ቀን ያደረገችልኝ ነው' አልኳትና በረጅሙ ተነፈስኩ.....
ምንም ሳትለኝ አልጋው ውስጥ ገብታ ተኛች ። እኔም ከዛን በዋላ አልተናገርኳትም ። እንደ መሸ አልቀረም ፡ ነጋና በጠዋት ተነሳን ። ቁርስ ከበላን በዋላ "እና ደብረ ዘይትን አታስጎበኘኝም ...?" አለችኝ ። 'እሺ' አልኳትና ባቦጋያ ፣ ምሳ ሰዓት ሆራ አርሰዴ ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ቢሾፍቱ ሀይቅ ወስጃት ደስ የሚል ቀን አሳለፍን ። ትናንት ማታ በነገርኳት ታሪክ ምክንያት እንደ ከዚህ በፊቱ አትስመኝም ፣ አታቅፈኝም ፣ ሌላው ቢቀር ድንገት አይን ለአይን ስንጋጭ እራሱ አንገቷን ትደፋለች ። ወደ ኩሪፍቱ ተመልሰን እራት ከበላን በዋላ "ማታ ምንም ሳልልህ በመተኛቴ ይቅርታ ። ግን ታሪኩን እንድትጨርስልኝ እፈልጋለሁ" አለችኝ ። እኔም ካቆምኩበት ቀጠልኩላት ። 'እንዳልኩሽ ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። ይሄን ደግሞ የፍቅር ታሪኬን ለሚጠይቀኝ ሁሉ አወራ ነበር ። የሆነ ቀን ግን ታሪኬን ከነገርኳቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ስለሷ ስታወራ ከልክ በላይ እርግጠኛ የሆንክ ይመስለኛል ። ግን ተስፍሽ አንድ ነገር ልንገርህ ። ከራስህ ውጪ በማንም እርግጠኛ አትሁን ። ሁሉም ሰው አንተ እንደ ምታስባቸው ላይሆኑ ይችላሉ ። እንደዚህ የምልህ ክፉ ነገር አስቤ አይደለም ። ስለ ልጅቷ ከልክ በላይ የተማመንክባት ስለመሰለኝና አንድ ቀን እንዳትጎዳ ስለፈለኩኝ ነው" አለኝ ። በሱ አስተያየት ምንም አልተሸበርኩም ነበር ። እንደውም 'አንተ ማራኪዬን ስለማታውቃት ነው' አልኩት ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ጨዋታው የተጀመረው ። "ስማ ተስፍሽ ፡ እንደ ነገርከኝ ከሆነ ማራኪዬ የምትላት ልጅ ፡ አንተ ምንም ብትሆን ፣ የትም ብትሄድ ፣ ሌላው ይቅርና አንተ ብትተዋት እንኳን የማትተውክ ፣ እስከ እለተ ሞቷ ድረስ የምታፈቅርክ የተለየች ሴት ናት ። ይሄን ያክል ደግሞ በሷ እርግጠኛ ከሆንክ ለምን እኔ የምነግርህን ፈተና አታቀርብላትም ...?" አለኝና ፈተናው ምን እንደሆነ ጠየኩት ። ቀጠለና "ምን መሰለህ ፡ #3 ነገሮችን እንድታደርግ እፈልጋለሁ ። #1ኛው ፡ የልደት ቀኗ ሲደርስ ምንም አይነት txt እንዳትልክላት ፣ እንዳት ደውልላትም ። በዚህም ከሁሉ በላይ አንተን ስለ ምትጠብቅህ በጣም ታዝንብሀለች ። #2ኛው ፡ ያንተ የልደት ቀንም ሲደርስ ፡ ከሷ ለሚመጡልህ የመልካም ምኞት መግለጫ መልስ አትስጥ ። ይሄ ነገርም የንዴት መጠኗን ከፍ ያደርጋል ። #3ኛውና ወሳኙ ደግሞ ፡ ክረምት ክረምት እናንተ ጋር ሙገር እንደ ምትመጣ ነግረኸኛል ። እናም ባሁኑም ክረምት መምጣቷ ስለማይቀር ፡ ያኔ ስትገናኙ ፊት ንሳት ፣ እንደ ማትወዳት act አርግ ፣ ከሷ ጋር በመሆንህም ደስተኛ እንዳልሆንክ አስመስል ። አንተን ብላ መጥታ እንደዛ ስትሆንባት መቼም ምን እንደሚሰማት መገመት አይከብድም ። እውነት እልሀለሁ ተስፍሽ እነዚህን ሶስቱን ነገሮች ተግብረህ ፡ ማራኪክ 'እኔ አልተውህም ፣ እንደዚህ ብትሆንብኝም እወድሃለሁ' የምትልህ ከሆነ she is the best girl in the world" አለኝ ። ሶስቱን ፈተና ብሎ የነገረኝን ስሰማ መጀመሪያ ስቄበት ነበር ። እንደ ቀላል አይቼው ፣ እንደ ምታልፈውም በሙሉ ልቤ ስለተማመንኩኝ ልፈትናት ወሰንኩኝ ። ስለዚህ ጉዳይ ከኔና ከልጁ ውጪ ማንም ሰው አያውቀውም ። ደስ የሚለው ነገር የልደቷ ቀን ያኔ የነበርንበት ወር ውስጥ ነበር ። የመጀመሪያው የፈተና ቀን ደረሰ ፡ የልደቷ ቀን....


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 15


.
.
.
"ከአራት ዓመት በፊት #9ኛ ክፍል እንደጀመርኩ ነበር ። የከዚራ ልጅ ብሆንም Elementery እያለን በጣም የምወደውና የምቀርበው ብቸኛው ልጅ አቤል የሳቢያን ሰፈር ልጅ ስለነበር አንድላይ ለመሆን ሳብያን high school ተመዘገብኩኝ ። ከእለታት በአንዱ ቀን በትምህርት ቤታችን ጊቢ ውስጥ crazy day የሚባለውን የፈረንጆች የዕብደት ቀን ለማክበርና ለየት ብሎ የሚመጣ ሰውም እንደ ሚሸለም ጭምር ከተማሪዎች ጋር ወስነን የሚከበርበት ቀን ደረሰ ። አብዛኛው ተማሪ የተቀዳደደ ልብስ ለብሰው እንደ ሚመጡ ግልፅ ነውና እኛ ግን ከነሱ ለየት ብለን ለመቅረብ የግድ አዲስ ፈጠራ መጠቀም ነበረብን ። በደምብ አስበንበትና ተዘጋጅተንበት ሁለታችንም የዕብደቱን ቀን ለማክበር ተያይዘን ወደ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አቀናን ። እንዳሰብነውም አብዛኞቹ የተቀዳደደና የቆሸሸ ልብስ ለብሰው ፣ ፊታቸውን ደግሞ ከሰል ተቀብተው ነበር የመጡት ። ትኩረት መሳብ የቻልነው ግን እኛ ነበርን ። ያን ዕለት እኔን አይቶ ይቺማ ሴት ናት የሚል ፤ ልክ እንደኔው አቤልንም አይተው ወንድ መሆኑን የሚያውቅ ከሁለታችን በስተቀር አንድም አልነበረም ። ከፆታችን ውጪ ሁሉንም ነገር ተቀያይረናል ። እሱ የኔን ቀሚስ ፣ ጡት ማስያዣ ፣ ሹራብ ፣ ሂል/ታኮ ጫማ ፣ human hair ጭምር ገዝተን አድርጎ ፣ ሁሌም ከኔላይ የማጠፋዋን pink ሻርፕ በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥሞ ፣ ቦርሳዬንም በጀርባው ተሸክሞ ፣ ከንፈሩንም Lip stick ተቀብቶ ምን የመሰለች ቆንጆ ኮረዳ መስሏል ። እኔ ደግሞ የሱን ሰፊ ጂንስ ሱሪ ፣ ሸሚዝ ፣ Adidas ጫማ ፣ ፀጉሬ እንዳይታይ ደግሞ ከላይ በሱ ኮፊያ ሸፍኜ ፣ እሱ ፂም ባይኖረውም ጉንጮቼ ላይ ፀጉር ለጣጥፌ ምን የመሠለ ሸበላ ወንድ ሆኛለሁ ። ለኛ ዕብደት ልብስ መቅደድ ፣ የቆሸሸ መልበስ ፣ ፊትን በቀለም ማጥቆር ሳይሆን ፈጣሪ ወንድ አድርጎ ፈጥሮት እንደ ሴት የሚሆን ፤ ሄዋን አድርጎ ፈጥሯት እንደ ወንድ የሚያረጋት ፣ ባጠቃላይ ወንድና ሴት ቦታቸውን ተቀያይረው ተፈጥሮን ሲቃወሙ ማየት ነው ዕብደት ። ይህ ነገር ደግሞ ከነጮቹ ከነ ሰልባጃቸው ወደ ሀገራችን እየገባና እየተስፋፋ ያለው ጉዳይ ነው ። ወንዱ ሴት ይመስል ከንፈሩን ደም የጠጣች ድመት አስመስሎ ፣ ፀጉሩን አሳድጎ እንደ ጭላዳ ዝንጀሮ ነስንሶ ፣ ከሰውነቱ ጋር የተጣበቀ ሱሪ ለብሶ ፣ ጆሮውን ተበስቶ ፤ ሴቷም ፀጉሯን ተቆርጣ ፣ ሱሪ ለብሳ ፣ ጡንቻ እያሳየች የወንድ አካሄድ እየሄደች ማየት ቀስ በቀስ በሀገራችን እየተለመደ መቷል ። አላማችንም ይህን ነገር መፀየፍና መከላከል ስለነበር ይህ አይነቱ ድርጊት ዕብደት መሆኑን ማሳወቅ እንጂ ፆታ ተቀያየሩ የሚል አልነበረም ። በዚህም ሁሉም ተስማምተውበት ሽልማቱን ወስደን ዝግጅቱም አለቀ ። ከት/ቤት ጊቢ ወተን አቤል ሊሸኘኝ ወደኛ ሰፈር አቀናን ። በሰዓቱ በጣም ጠምቶኝ ስለነበር እዚው ጠብቀኝ መጣው ብዬው በቀኝ በኩል ወደሚታየው ሱቅ ሄድኩኝ ። ባለሱቁን #2 ጁስ ስጠኝ ብዬው መቶ ብር ሰጠውት ። ወንድ መስዬው ስለነበር ድምፄን ሲሰማ ደንግጦ ነበር ። መልሱን እስኪፈልግ ድረሰ ዞር ብዬ አቤልን እያየሁት ፤ እሱም ወደኔ ዞሮ በአይኑ እየቃየኝ ነበር ። እውነት ለመናገር ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ እንዳለ የኔን ልብሶች ስለተጠቀመ ላየው ሰው እሱ አቤል ሳይሆን ህይወት ናት ። ባለሱቁ 'ይኸው የኔ ወንድም ይቅርታ እህት ለማለት ነው' ብሎኝ መልሱን ሲሰጠኝ ከዋላዬ የተኩስ ድምፅ ሰማሁ" ።
"ስዞር ፡ አቤል እዚው ጠብቀኝ ባልኩበት ቦታ ላይ ተዘርሮ ወድቆ አየሁት ። መኪና ውስጥ ሆነው ነበር የተኮሱትና መኪናዋ ሳትቆም በዛው ሄዳ ተሰወረች ። በቃ በዛች ሰዓት የማስታውሰው ነገር ቢኖር ለአባቴ ደውዬ ያለንበትን ቦታ ነግሬው ፤ እስኪመጣ ድረስ ሰው ተሰብቦ እንዳይበዛ ባለሱቁን ለምኜው አቤልን ተሸክመን ወደ ቤቱ ውስጥ እንዳስገባን ነው ። አቤል በጣም ተዳክሞ ነበር ፤ ብዙ ደምም ከተተኮሰበት የዋላው ጭንቅላት ፈሶታል ። ሆስፒታል መውሰዱ አማራጭ አልነበረም ፤ መጀመሪያውኑ ወደሱ ሮጬ ስደርስ ህይወቱ አልፏል ። አባዬም በፍጥነት መጥቶ ሁለታችንንም ወሰደን ። ቦታው በከዚራ እና በሳቢያን መካከል ስለነበር ባለሱቁ ሁለታችንንም አያውቀንም ነበር ። ሳስበው አባቴ መጥቶ እስኪወስደን ድረስ ተጠምጥሜበት እያለቀስኩ ስለነበር ከአለባበሱ አንፃር አቤል ሴት እንደሆነ ነው የሚያምነው ። ከዛን አባቴ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ ...? ገዳዮቹ ማንም ይሁኑ ማንም እኔን እንደገደሉ አድርገው ስለሚያምኑ በአቤል መቃብር ላይ የኔን ስም አፃፈበት ። ከኔና ከአባቴ ውጪ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሶስተኛ ሰው አንተ ብቻ ነህ ። አቤል ዘመድና ቤተሰብ አልነበረውም ። በቃ ብቻውን በራሱ ለራሱ ሰርቶ የሚማር ልጅ ነበር ። እኔ እሱን እሱም እኔን ብቻ ነው የሚቀርበው ። የዋህ ፣ ለሰው አሳቢ ፣ መልከ መልካም እና ጠንካራ ልጅ ነበር ። ልባቸውን አቆሽሸው ልብሳቸውን ከሚያሳምሩት ወገን አልነበረም ። ባለው አቅም ያለውን ፅድት ያለች ዩኒፎርም ከንፁህ ልቡ ጋር ያዋሀደ ምርጥ ልጅ እንጂ ። ለዛም ነበር እሱ የሚማርበት ት/ቤት የተመዘገብኩት ። አባቴ የኔን ምርጫ ስለሚያከብር ብቻ ሳያቅማማ ነበር እዛ ያስመዘገበኝ ። ምን ዋጋ አለው ፡ አሁን ላይ ስሙ እንጂ እሱ የለ ። ለኔ የታሰበውን አፈር እሱ ቀመሰልኝ ። እሱንና እናቴን ለይቼ እላያቸውም ። እናቴ ህይወት ልትሰጠኝ ህይወቷን አጣች ። አቤል ደግሞ ህይወቴን ሊያስቀጥል ህይወቱ ተቋረጠ ። ሁለቱም አስበውበትና አቅደውበት ባያድኑኝም ለዛሬው ህይወቴ ምክንያቶች ናቸው ። ከአቤል ቀብር በዋላ አባቴ እንኖርበት ከነበረው ከዚራ ከሚገኘው ቤት ሌላ አዲስ ቤት ገዛና በድብቅ እዛ አስቀመጠኝ ። ቤቱ ላይም ከላይ 'የሚከራይ' ብሎ ለጠፈበት ። ሰዎች ሊከራዩ ሲደውሉ ብዙ ብር ስለሚጠራባቸው ማንም አይከራየውም ። ከኔና ከአባቴ ውጪ እዛ ቤት ውስጥ እኔ እንዳለሁ የሚያውቅም አልነበረም ። በዛ ቤት ውስጥ ለ #4 ተከታታይ ዓመታት አብዛኛውን ጊዜ ብቻዬን ፤ ጥቂቱን ደግሞ ከአባቴ ጋር አሳለፍኩኝ ። አንተን እስካወኩበት እለት ድረስ ከቤት መውጣት ፣ መልበስ ፣ መብላት ፣ መጫወት ፣ ምንም ነገር አያምረኝም ነበር ። የሁሉም ቀናት ውሎዬ ተመሳሳይ ናቸው ። መተኛት ፣ ማንበብ ፣ ፊልም ማየት ፣ ትንሽ መብላት ፣ በጊታሬ መዝፈን ፣ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከአባቴ ጋር መሆን ነው ። ይሄንንም ለማድረግ አንድ ዓመት ፈጅቶብኛል ። ከአቤል ሞት በዋላ ለአንድ ዓመት በአንድ መኝታ ቤት ውስጥ የሱ ደም የለበሰ አካል በህሊናዬ ውስጥ እየተመላለሰ እየወቀሰኝ ደንዝዤ አሳለፍኩኝ ። ከዛን በዋላ ነው ቀስ በቀስ ወደ ቀልቤ የተመለስኩት ። ከነዚህ ሁሉ ጊዜያት በዋላ አንተን ሳገኝ ለምን በአንዴ እንደ ተለወጥኩ ታውቃለህ ...?" አለችኝና ከቦርሳዋ ውስጥ የሆነ ፎቶ አውጥታ ሰጠችኝ ። ፎቶው ላይ ያለውን ልጅ ሳይ ለማመን ነበር የከበደኝ ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል..........