ከገጠምኩ ለኢየሱስ
20K subscribers
7 photos
4 videos
26 files
175 links
well come ወደ ቻናላችን በደህና መጣችሁ
ስራችን ሙሽራው ማላቅ ቤተክርስቲያን ማብቃት ነው ለማንኛውም ማስታወቂያ Owner @ErmiyAs_kifle
Download Telegram
የመመለስ ውጤት
ከገጠምኩ ለኢየሱስ
ሁላችሁም ስሙት

share Join React❤️❤️
@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
.....ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ

በመቅደስ ሲያስተምር ሲገልጠው መጽሀፉን
ደዌንም ሲፈውስ ሲያስነሳ ሙታንን
ማንስ ምን አለ ያኔ መና ሲወርድ
ተገረመ ጴጥሮስ በባህር ሲራመድ
አሁን ግን ሰዓቱ ጊዜው ደረሰና
ነገረ ደጋግሞ እንዳትገቡ ወደ ፈተና
አዎን ያውቀዋል ያኔም ሲመጣ
መስዋዕት እንደሚሆን በመስቀል እንዲቀጣ
አብሮ የከረመ የተማረ ከእርሱ
የአስቆሮቱ ይሁዳ ከዳና ተለየ ከሱ
ወትሮም ሌባ ነበር ገንዘብ ወዳድ ድሮ
አይሁድ ተጠቀሙ ክፉ መንፈስ በእርሱ አድሮ
ሰጠ ሸጠ ጌታውን በሰላሳ ዲናር
በመሳም ጠቆመ አፉ ሳይናገር
ወንበዴ እንዲይዙት በሰይፍና በገመድ
እያጋፉ ወሰዱት ወደ ጎልጎታ መንገድ
ዮሴፍም ሲመለስ ከቀሬና ወደዛ
በግድ አሸከሙት መከራውም በዛ
ጌታዬን ሰቀሉት በራስ ቅል ከፍታ
ቀኑም ጨለመ ፀሀይም የለ ሆነ በቀን ማታ
ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ ፃዲቅ
ነብሱ እስክትወጣ አለም ዋጣት ድቅድቅ
በርባን ሲፈታ ሲያፌዙ መንገደኞች
አይተን እንድናምን ይውረድ አሉ ፌዘኞች
እጣ ተጣጣሉ ልብሱን ቀደዱና
አወይ መከራው አወይ የሰው ልጅ ፈተና
ሙሴ እንደሰቀለ የተረገመን እባብ በዚያ ምድረበዳ
ጌታዬ እርግማን ሆኖ ተሰቀለ ሊከፍል የሀጥያትን ዕዳ
ወደታች ወርዶ ተቀብሮ ከመሬት
ወንጌልን ሰበከ ከህያዋን አልፈው በመቃብር ላሉት
እንዲህ ያለ ፍቅር ከወዴት ይገኛል
ሞቴን በሞት ሽሮ እኔን አድኖኛል

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
የመስቀሉ ሚስጥር

ሶስት ዓመት ተኩል መሃላቸው ሆነህ
ሆሳዕና ብለው እንዳላከበሩህ
አህያ ላይ ጭነው ዘንባባ አንጥፈው
እንዳልዘመሩልህ ይገባሃል ብለው
ታዲያ ምነው ዛሬ ያንን ሁሉ ረሱ
በዘንባባ ፋንታ ድንጋዩን አነሱ.
መሲህ መሆንህን ሳያውቁ ዘንግተው
አዳኛቸውን እንደሌባ ቆጥረው
እንደ ወንጀለኛ ወደ መስቀል ነዱት
ንጉሳቸውን ሰቅለው ሊገሉት.
በመልክና አምሳሉ የፈጠራቸውን
እስትንፋስ ቀጥሎ ኑሩ ያላቸውን
ምንጭ የሆናቸውን የነፍሳቸውን ጌታ
አዋርደው ገደሉት በዚያ በጎልጎታ.
ግን የሚገርመው የሚደንቀው ነገር
ዓለም ያላየችው የእግዚአብሔር ሚስጥር
በመስቀል ላይ ታየ በናዝሬቱ ኢየሱስ
በሞቱ ሕይወት ሰቶ ኪዳኑን ሲያድስ.
ለካ የቀራንዮ የመስቀሉ ጉዳይ
በደም ተለውሶ ተንጠልጥሎ እንዲታይ
አብ በልጁ ላይ እንዲያ መጨከኑ
አባ ለምን ተውከኝ ሲል አለማዘኑ
እኛን ለማዳን ነው ከኃጢያት እርግማን
በፈሰሰው ደሙ ከኃጢያት ሊያነፃን.
ይሄ ነው እንግዲህ የመስቀሉ ሚስጥር
ለዓለምሁሉ የታየው የክርስቶስ ፍቅር
አብ ልጁ ላይ ጨክኖ ለእኛ የሰጠበት
ወልድ ስጋን ለብሶ በመስቀል የሞተበት
መንፈስ ቅዱስ እኛን መቅደሱ ያረገበት
በመንፈሱ አትሞ ወራሽ የሆንበት
ይሄ ነው እውነቱ የዳንበት ጉዳይ
ብርሃናችን በርቶ ለዓለም እንዲታይ.
ሃና መኮንን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
.......የአይሁድ ንጉስስስ??

ፎከሩ እንደጀግና ዝም ሲልላቸው
የመዳን ዋጋ እጅጉን ቀሏቸው
አድርገውት አረመኔ ወንበዴ የተጠላ
ለመስቀል ገፋፉት ከፊትና ኋላ
😄😄😄😄😄😄😄😄
ሄሮዲስ ገረመው ዉዝምታው ብዛት
ሲመቱት ሲሰድቡት ሳይናገር ቃላት
ጠየቀ ታች ወርዶ ከመንበረ ዙፋኑ
አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን በዉኑ??
ብሎ አለና አስሮ አስገረፈ
አመረላክ የሆነ ሰው ስጋው ረገፈ
ደግሞ አጣደፉት ሳይገድሉት ላያድሩ
ይሰቀል ይሰቅል በሚል ቃል ታወከ መንደሩ
ጲላጦስም አየ መረመረ በጣም
በዚህ ሰው ላይ አንዳች አልተገኘም
ልልቀቀው ገርፌ ዳግም እንዳይረብሽ
አራባ ይሁን ግርፋቱ ይለቀቅ ሳይመሽ
ከብሎ ቢፈርድ እንኳን ከቶውን ማን ሰማ
ተገደደ ንጉስ እንዲህ ከሆነማ
ለራሱ ስቅላት እንጨት አሸክመው
ሲወድቅ ሲነሳ ጌታዬ ደከመው
ተጠማሁኝ አለ የሆነው የህይወት ምንጭ
ሆምጣጤ አጠጡት ከጥሙ የሚጋጭ
ቻለና ሄደ ተነዳ ቀራኒዮ ተገፋ ጎልጎታ
በሰው ዉርደት ምትክ ተዋረደ ጌታ
ነብሱን አሳልፎ ሰጠና ፈፀመ
የኔና ያንተ ሞት እዳ ያኔ አከተመ

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
.......የአስቆሮቱ ይሁዳ
መጠራቱ ነበር እኔን የገረመኝ
ከወንድሞቹ መሀል በምህረቱ ሲገኝ
ተመርጦ ካለበት ከነ ክፉ ምግባሩ
ይሁዳም ተቀመጠ ሆኖ ደቀ መዝሙሩ
ሌሎቹ ሲማሩ ሲሰሙ ሲጠይቁ
የአምላክን መንገድ ተግተው ሲናፍቁ
የአስቆሮቱ ሰው አስመሳይ ተግባሩ
ገንዘብ ገንዘብ ይላል ልቡ ከጅምሩ
ትዝ ይለኛ ያኔ ያች ሴት ሚስኪኗ
ቢደንቃት ቢገርማት የጌታ መሆኗ
መክፈል ቢያቅታት ብታመጣ ሽቶ
ሰባብራ ብታፈስ ልቧ ሊረካ ሽቶ
ስታጥብ በእንባዋ የጌታዋን እግር
በፀጉሯ ስታብስ ለዉለታዉ ስትጥር
ያኔ ያሰላ ነበር ይሁዳ ግምቱን
የሽቱ ዉድነት ገለጠው ስሜቱን
ተናደደ በጣም ተቆጣ በሆዱ
አጉረመረመ ብቻውን ልክ እንደ ልማዱ
ቢሸጥኮ ይሄኔ ይሄ ያልበስጥሮስ ሽቶ
ለድሃ ቢሰጥ ያኖር ነበር ተደስቶ
😃😃😃😃😃😃😃😃😃
አይ አንተ ተላላ ይሁዳ ነው ስምህ
ከስምህ ተቃራኒ ሆነህ መገኘትህ
ታማኝ ሲሆን ቅሉ የአንተ ትርጓሜ
አታላይነትህ ጨረሰብህ እድሜ
በለጠብህ ገንዘብ ሸጥከው ጌታህን
መቃብር አበጀህ ወስደህ ዲናርህን
አታመልጥም ከቶ ከሚነደው እሳት
ራስህ አጠፋህ ቀድመህ በዛ ሳት

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
እናማ የዛሬ የዘመኔ ይሁዳ
በንዋይ ተታለህ ጌታህን የከዳህ
ተመለስ ወንድሜ አሁንም ያለህ አስቆሮቱ
አንተንም ያድናል የኢየሱስ ሞቱ
ንቃ አምልጥ ተነስ ቀኑ ነው ዛሬ
ሌላ ሳይመሽብህ ልንገርህ ዞሬ
ይጠራሀል ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ
ዉርደትህን ሸፈነ ራቁት ተንጠልጥሎ
ደሙ አልደረቀም ያፈሰሰው ላንተ
ቀኑ ሳይመሽብህ ነብስህን አስመልጥ አንተ
አታስብ ብዛቱን የሀጥያትህን ክምር
የፈሰሰው ደም ሆናል ለአንተም ጭምር

በጌታሁን አናሞ


https://t.me/kegetemku_leyesus
ክፍል 8
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

አንዳንዴ በጣም እያለቀስኩ ሴተኛ አዳሪዎች ሲያዩኝ ማዘን ጀመሩ ኢቺ ሴት እርጉም ነች አትለቅሽም ከዚም በፊት ሌሎች ሴቶች እንዲህ አድርጋለች ይሉኛል

እና ምን ላድርግ ብዬ ስጠይቃቸው
ወይ እሺ ብለሽ ሳታስገድድሽ መስማማት
ወይም በሆነ አጋጣሚ ዘበኛው ዘወር ሲል
ጠፍተሽ መውጣት ብቻ ነው አማራጭ ያለሽ አሉኝ

ዘበኞቹ ሁለት ናቸው የትም አይንቀሳቀሱም
እዛ ውስጥ የሚሰሩ ሴቶች አብዛኛቸው ያለ ፍላጎታቸው ነው ስራው ይፈልጉታል እዛ ቤት ውስጥ መሆናቸው አይፈልጉትም
ምክንያቱም የሚያገኙት ገንዘብ ሴትየዋ ነች የምትጠቀምበት

የሴቶች የውበት ሳሎን ግቢ ውስጥ አለ
ለምንም አይነት ነገር ማንም መውጣት አይችልም ድንገት ዘበኛ ከሌለ ውሻ አለ

እንዲገባቹ የምፈልገው ነገር ቢኖር እዛ ቤት
ለሁሉም ሴቶች በሩ ዝግ ነው ማንም እንደፈለገ ገብቶ መውጣት አይችልም

በአራተኛ ቀን እሺ እንድላት በጥብቅ
ጠየቀችኝ እኔም በጥብቅ እያለቀስኩ እንድትተወኝ ጠየቅኋት አንድ ባለ ሀብት ሰው
አምጥታ እሺ ብትዩ ወርቅ ይገዛልሻል ልብስ ይገዛልሻል አለች እኔ ደግሞ እግሯ ስር ተንበርክኬ እባክሽን ተይኝ ብዬ ለመንኳት

በመጨርሻም አንድ አማራጭ ሰጠችኝ
የደላላና ትራንስፖርት ከፍይ እንድሄድ ወይም
የምትለኝን ተስማምቼ እንድቀጥል የጠየቀችኝ 1ሺ ብር ነው እኔ 1ሺ ቀርቶ
10ብር የለኝም ዙርያ ገደል ሆነብኝ
እናንተ ስታነቡት ላትረዱኝ ትችላላቹ
በሳቱ ከእኔ ጋር ስላልነበራቹ
ለኔ ግን ከፊልም በላይ ነው


ይቀጥላል

@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
አቤት ትህትና

ሕዝቡን ሊያስተምር በተቀመጠበት
እንዲህ ሲሉ ጌታን ጥያቄ ጠየቁት
በመንግስተ ሰማይ የሚበልጠው ማነው
ከሁሉ ፊት ሆኖ ቀድሞ የሚታየው
ብለው ቢጠይቁት ደቀመዛሙርቱ
ፈልገው ለማወቅ እጅጉን በብርቱ
ጌታ ግን አላቸው ለሁሉም አጥርቶ
ሃሳባቸውን አውቆና ተረድቶ.
ትልቅ ለመሆን የሚፈልግ ሰው
ራሱን ዝቅ አድርጎ ሌላውን ያገልግለው
ብሎ ሲነግራቸው የሰማዩን ሚስጥር
ትልቅ የመሆኛን ዋና ቁልፍ ነገር
ባይገባቸው እንኳን ከቶ ባይረዱት
በዚያች ሰዓት ጌታ ያላቸውን እውነት
ስለራሱ ነበር ጌታ መናገሩ
አብረው ለነበሩት እንዲያ ማስተማሩ.
አምላክ ሆኖ ሳለ የሁሉ ፈጣሪ
ጊዜ የማይዘው ለዘላለም ኗሪ
አምላክነቱ ከቶ ሳይገድበው
ከአብ ጋር መተካከልን እንደመቀማት ሳይቆጥረው
ለአባቱ ታዞ ዝቅታን መረጠ
የትህትናን ሚስጥር ለዓለም ገለጠ.
ደቀመዛሙርቱ ፉክክር ላይ ሳሉ
እኔ ነኝ የምበልጠው እየተባባሉ
እሱ ግን ዝቅ ብሎ እግራቸውን አጠበ
ከፊቱ ያለውን መስቀል እያሰበ.
አቤት የኢየሱሴ ትህትና ብዛት
ለአባቱ ታዞ ለእኛ የሞተበት
አብ እንኳን በልጁ እጅግ ተደስቶ
ራሱን በመስጠቱ መስቀል ላይ ሞቶ
እጅግ አከበረው ከፍ ከፍ አረገው
ከስም ሁሉ በላይ ስምንም ሰጠው.
ይህ ነው እንግዲህ ትህትና ማለት
ራስን ዝቅ አድርጎ ከፍ ብሎ መታየት
ትልቅ የመሆኛው ዋና ቁልፍ ጉዳይ
ሆኖ መገኘት ነው የሁሉ አገልጋይ.
ሃና መኮንን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
#የተወደዳችሁ የአባቴ ብሩካኖች እንኳን አደረሳችሁ🔥🔥

➣ድል አድራጊዉ ጌታ ተነስቷል የዚህ የምስራች ነጋሪዎች ስለሆናችሁ ደስ ይበላችሁ🙏🙏

➣የእኛ ጌታ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል የመቃብሩም ድንጋይ ተንከባሏል ሀሌሉያ🙏🙏🙏

➣ሉቃስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፥ ይዘብቱበትማል ያንገላቱትማል ይተፉበትማል፤
³³ ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።

#ለሠቀሉት ለተፉበት አጋፔ የሆነዉን ፍቅሩን ለግሷል 😥

#ለዘላለም በማይደመሠሥ ፍቅር ተወደናል

#ስለ እኛም ሞትን ድል አድርጓ ተነስቷል🙏🙏

➣ለእኛ ትንሳኤ ሆኖል🙏🙏🙏



➣በእያንዳንዳችሁ ቤት ትንሳኤ ሆኖል🙌🙌

➣እየሱስ ሲነሣ ዝም ብሎ አይደለም የተነሣዉ እነማሪያም 12ሀዋሪያት እየሱስ ስላተለያቸዉ ተስፋ ቆርጠዉ እንደነበር እናዉቃለን እየሱስ ሲነሳ ተስፋቸዉም አብሮ ተነስቷል እየሱስ ሲነሳ ታሠድሶ ሆኖል 🙌🙌


➣ሀያላን እየሱስ ሲነሳ የሞተ ነገራችንም አብሮ ተነስቷል

➣የመኖር ተሥፋችንም ጨምርዋል🔥

➣የቆመ ነገራችንም መንገዱን ቀጥሏል🙌

➣የሞተዉም ነገራችን ተነሥቷል😳

➣እርምጃችንም ፍጥኖል🥹

➣የሠማይ ናፍቆታችንም በዛዉ ልክ ጨምሯል

#ህያዉ የሆነዉ ክርስቶስ ሞት የማይችለዉ እርሱም ከሙታን መካከል ሞትን ድል አድርጓ ተነሥቷል🙏🙏

የምወዳችሁ
#ትንስኤ ሆኖልናል እንኳን ደሥ አላችሁ

በአሉ #የእየሱስ ድንቅ ስራዎች ንዲሁም በመሥቀል የተከፈለላችሁን ታላቅ ፍቅሩን እያሠባችሁ ሀሤት እያደረጋችሁ የምትዉሉበት ቀን ይሁንላችሁ🙏🙏🙏🙏😍😍😍

የእናንተዉ 😁ፅናት🔥🔥
........ፍቅርህን ነገረኝ
ሰዎች ያወራሉ ስላንተ መከራ
የከፈልከውን ዋጋ ሁሉም በየተራ
ደራሲውም ጻፈ ቃላትን ቀምሮ
እጅግ በዉብ ሆሄ ፊደላት መርምሮ
ዘማሪውም ተቀኘ በሚያባብል ዜማ
አለም አጀብ አለ ከሩቁ ሲሰማ
ሰበከ ስለፍቅርህ ወንጌል አብሳሪው
የመከራህን ዋጋ ተመን ተናጋሪው
በዚህ ሁሉ መሀል ልቤ ግን ሸፈተ
ከግጥሙ ከዜማው አይኔ ተከፈተ
አየሁ ያን መከራ የጀርባህን ግርፋት
ደምህ ሲነጠባጠብ ከአለንጋው ብዛት
አየሁ አየሁ እኔ ከዚያ ሲቃ ጣርህ
ነብስህ ስትጨነቅ አባትህን መጥራትህ
ልቤን አላወሰው የከፈልከው ዋጋ
መሰቀልህ ሳያንስ በጦር ስትወጋ
ለጥማትህ ሲሆን መራራ ሆምጣጤ
ሰማይ ታዞ ሲጨልም ሲሆን ድንጋጤ
አየሁት ሁሉንም የመስቀልህን ስራ
በግዞት ያሉትን ወዳንተ ስትጣራ
በደምህ ሰማይ ገብተህ ከአብ ያስታረቀኝ
የጎልጎታው መከራ ፍቅርህን ነገረኝ
ለፃዲቅ የሚሞት ቢገኝ እንኳን በጭንቅ
ለበደለኛው መሞትህ ነው እጅግ የሚደንቅ

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
እንዴ እንዴ እንዴ🤭

ትዝ አለኝ ማዳኑ በሱ መወደዴ
ምህረት ባይበዛልኝ የት ነበርኩኝ እንዴ
ጠፍቼ ነበረ ያኔ ድሮ ድሮ
ላንድ አላማው አስቦኝ ቆምያለሁ ዘንድሮ

ወዶኝ አድኖኛል በማያልቀው ፍቅር
በሱ ከተወደድኩ ማነው የሚለው ቅር

አወይ የማዳኑ የምህረቱ ብዛት
ላወራው ሞክሬ አይበቃኝም ወራት

ሰዎቹ ይላሉ ከዚ አውጥቶኛል
አዳንዶቹም ይላሉ እንዲህ አድኖኛል
እኔ ግን ስጀምር እባ ይቀድመኛል

አንዳንዶች ሳያውቁኝ ሲነግሩኝ ፍቅራቸው
ምን እንደነበረኩኝ ማን በነገራቸው

የምህረትህ ብዛት እንዲህ አስደነቀኝ
ክበር ክበር ልበልህ የምከፍልህ የለኝ

እየቆየ ገባኝ ባንተ መወደዴ
አንተ ሰው ስትወድ ለካ እንዲ ነው እንዴ

ከከበረው ስፍራ ከሰማያት ወርደህ
እኔ ለማስለቀቅ እራስህ ተይዘህ

ልጁ ናት ተባልኩኝ በስምህ ተጠራሁ
በመሞቴ ቦታ ስትሞትልኝ ኮራሁ

የፀቡ ግድግዳ በፍቅር ፈረሰ
ጥቁር መጋረጃ ያኔ ተቀደደ

በመስቀሉ ስራ ተፈፀመ ብሏል
ወርጄ ሳልወጣ ከአብ አስታርቆኛል

ሰላማዊት ነክር

share Like Join
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
አፍቅሬ ያበድኩኝ

የፍጥረት ጀማሪ ሁሉ ቦታ ሚገኝ
ለመኮት ምላሽ ሳልሰጥ ሙት ሆኜ ስገኝ
የእውነትም አፍቅሮኝ አፈቀርኩ አለኝ

አንተ ቃል ሆይ አንተ ክቡር ከማን ጋ ነው
እስቲ አጫውተኝ እንዲ አይነቱ እወዳለው
ኢኸውና ከአንተ ብሎ አሳበደኝ

ለፍቅሬ መግለጫ ቃላት ሳልደረድር
በቀን በአደባባይ ላሳይህ በግብር

ክብሬን ሁሉ ጥዬ ስላንተ ልዋረድ
ከመለኮት ወር እንደ ሰው ስወለድ

በእልፍ አምልኮ መሀል በአላፋት ክብር
እንድያ ስቆላመጥ በሰማይ ከምኖር
ያንት መዳን ይሻል ብዬ በትህትና ስቆጥር
የእውነት ወድጄህ ነው ካንተ ይዞኝ ፍቅር

እንደ ባረያ ኖሬ ልጅ ልትሆን ለአባቴ
ርስትህ እንድሆን ልትሆን ርስቴ

ሸክምህን ልሸከም ልወስድ ግርፋትህ
ጥምህን ልጠማ ብዙ ልናቅልህ

ብዙ የሆንኩልህ እይ የመስቀል ፍቅሬ
አፈቀርኩህ ያልኩህ አይደለም በወሬ
አለኝ ኢየሱሴ አለኝ ቁም ነገሬ

ስፋትና ወርዱ ጥልቀት ርዝመቱ
ሳየው ውዴ ፍቅሩ ማያረጅ በጊዜያቱ

ወደደኩህ እንዳለኝ ወደድኩህ ማለት ከብዶኝ
ላልጠየቁኝ ሁሉ ኢየሲስ እላለው ፍቅሩ አሳብዶኝ

ጫወታ አምጣ ሲሉኝ ካልሆነ ቁም ነገር
እስቲ ገጠመኝህ የሆነብህ ነገር

ትውስታም ከሆነ የልጅነት ታሪክ
ሲሉኝ የሚያውቁኝ ተናገር ከወደድክ
አንተን ነው ማወሳው ሌላ የለኝ ሚተረክ

ቀን በትውስታዬ ወይም በሰመመን
ማታ በመኝታ በህልምእንኳን ቢሆን

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ የምለው
ኢየሱስ ማለት እኮ ያበድኩበት ስም ነው
የሚገርምህኮ አፍቅሬ አበድኩ ምለው
ስለወደድኩ ሳይሆን ስለወደድከኝ ነው

ኢየሱስ የእግዜር ማረግ የእግዜር ክብር
የእኔ መውደድ የእኔ ፍቅር

የእግዜር ብቃት የእግዚአብሔር ሀይል
መደነቄ ማይገልጥህ ቃል

ስለ አንተማ በዘመኔ ልኑር
ግጥሜ ብቻ ሳይሆን ህይወቴ ይመስክር

ዘወትር ዘላለም ርዕሴ ኢየሱስ ነው
ዕብደቴ አልቀይርም በጣም ነው ምወደው

ኤርሚያስ ክፍሌ

Share💯ንኩት💯👇👇
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
👆👆🀄️🀄️ሉን👆👆
💐ደምህ
ሳቄ ነው ፈገግታዬ
ሰላሜ ነው እፎይታዬ
ከጠላቴ ማመልጥበት
ተሸሽጌ የምኖርበት
አድራሻዬ ነው መዋያዬ
ሀጥያቴን ማስተሰርያዬ
ሞት ቤቴ እንዳይገባ
የፈረሰው ልቤን ሚገነባ
አለኝ ብዬ የማወራው
ለሰው ሁሉ ምናገረው
መመኪያዬ መከታዬ
ከአጥፊ ሁሉ ማምለጫዬ
የፈረሰው ህይወቴን ማድስበት
ተደላድዬ የምኖርበት
ስናገረው ማላፍርበት
ትምህርቴ ነው የእኔ እውቀት
ድፍረቴ ነው ጉልበቴ
እንዳልፈራ ብርታቴ
ያገኘሁት ጌታ በሞትህ
ሁሉዬ ነው ለኔ ደምህ
Fasika Dereje

በውስጥ ከተላከልኝ በጣም ቆንጆ ግጥም ነው
👇
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
#join&share
ፍቅርህ ቅኔ ነው
****
አብ
*-**
ወደድኩህ ለማለት፣ፍቅርህ ልታስረዳ
ዙርያ ጥምጥም ሄደህ፣ዘመድ ልሆን ባዕዳ
በቀኝህ ያለው፣የገዛ ክንድህ
ሀይልህ የሆነው፣ክብር ጥበብህ
ለእርሱ ፊት ነስተህ፣ለእኔ ልትፈካ
እኔ ወክሎ ልጅህ አርደኸው፣ጥምህ ሊረካ
ቅኔ ነውና፣ የአብ እኔን መውደድ
ልጁ ባርያ አ'ርጎ፣ እኔን ግን ዘመድ
*
ወልድ
*-*
ስጋዬን ለብሰክ፣ምድር የመጣህለታ
እኔ መውደድህ፣ቅኔው ተፈታ
መልኬን ወስደኸው፣መልክህ ሰጠኸኝ
የእኔን ሞተኸው፣የአንተው አኖርከኝ
ጠላት የሆንኩት፣ብለህ ወዳጄ
ህይወትህ ሰጠኸኝ፣ሳትፈልግ ከእጄ
ተገርፈህ ቆስለህ፣እኔ ተፈወስኩ
እርግማን ሆነህ፣እኔ የው ፀደኩ
ልትሞት ስትወጣ፣ያንን ጎልጎታ
እኔን መውደድህ፣ቅኔው ተፈታ
****
መንፈስ ቅዱስ
*-*
በእኔ የምትኖር፣በአንተ የምኖር
ቀርበህ ምትረዳኝ፣ለኢየሱስ እንድኖር
ማትርቀኝ ማተወኝ፣ጥለኸኝ የማትሄድ
የምታፀናናኝ ውዴእስኪመጣልኝ፣ወይ ደግሞ እስክሄድ
በውስጤ ያለኸው፣ሀይልና ብርታቴ
ፍቅርህ ቅኔ ነው፣እግዚአብሔር አባቴ

ቅኔው ግን ገብቶኛል፣ግልፅ ሆኖልኛል
በቃላቶች ሳይሆን፣በኑሮህ ታይቶኛል

ኤርሚያስ ክፍሌ

join👇
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
ዉረድ አሉት

*

አይይይ አለማወቅ አይሁድ ፈሪሳዊያን
ባለሰቀሉት ነበር የአለምን ብርሃን
ቢረዱማ እርሱን የመምጣቱን ሚስጥር
አምላክ ሆኖ ሳለ ሰው የመሆኑ ነገር
መደነቅ ሳይዛቸው ሰው ሲሆን አምላክ
ከጥንት የነበረው በአባቱ አብራክ
ቢገደው ቢመጣ ክቡር ቦታ ለቆ
እኩል ስልጣን ሳለው ከአብ በሰው ተንቆ
አይተን እንዳንወደው ደምግባቱን ሲያጣ
በደዌ ተመቶ በእንጨት ሲቀጣ
ልባቸው ደንድኖ አዳኙን ገደሉ
ራሳቸው ሰቅለው ደግሞ ዉረድ አሉ
አየየየ መታገሱ ሲመታ ሲገረፍ
አፉን ሳይከፍት ሲለጉት በጅራፍ
ለአለም ድነት እንጂ መች ሆኖ ሀሳባቸው
ታዞ ባይሰቅል ማን ነበር አዳኛቸው
እየወጉት እንኳን ምህረትን ለምኖ
ሆምጣጤ ሲያጠጡት ለድነት ተማፅኖ
የታረደው በግ በአብ ቀኝ ያለው
ዉረድ እያሉት ወጥቶ አለምን አዳነው
ሞተ ሲሉት እርሱ ህያው ሆኖ ያለ
ታላቅ ሊቀካህን በሰማያት አለ
ለአለም ኃጢአት ዘውትር ሚማልደው
ሞትን ድል የነሳው ጌታ ኢየሱስ ነው
በትንቢት የተነገረለት የናዝሬቱ ጌታ
መጥቶ ሞቶ ያዳነን በራስ ቅል ጎልጎታ
ተቀብሮ ያልቀረው ሞትን ድል የነሳ
በክብር ያረገው የይሁዳ አንበሳ
ቢሆንማ ኖሮ ቢወርድ እንዳሉቱ
ጨክኖ ባይሞትልን ታግሶ በትግስቱ
ሞተው በገደሉን ነበር ቢሆን ሀሳባቸው
ተረት ሆነን በቀረን ነበረ ታሪካቸው
ግና የኔ ብርቱ አለው ሌላም ተስፋ
የአለምን ክፋት እርኩሰት ሊያጠፋ
እመለሳለሁ አለን ወደርሱ ሊወስደን
ቤትን አዘጋጅቶ ይመጣል ሊነጥቀን
በክብር ደመና በመላዕክት ታጅቦ
በአምባው ፈረስ ላይ በግርማ ተከቦ
በቅን ሊፈርድ ለፃዲቅ ለሀጥዩ
ዳግም ይመለሳል የወጉት እያዩ

ጌታሁን አናሞ

t.me/kegetemku_leyesus
የትንሳኤው ጀግና

አምላክ ሆነህ ሳለህ የፍጥረታት ጌታ
ዘላለም የምትኖር ሁሉን የምትረታ
ነገር ግን ስለኔ ከዙፋንህ ወረድክ
ክብር ሲገባህ ውርደትን ተዋረድክ
ሀጥያት የማያቀው ገና ከጅምሩ
ሀጥያት ሆነልኝ ስለኔ መምህሩ.
ምራቅ ሲተፋበት በፈጠረው ፍጥረት
ራሱ ባበጀው ውርደት ሲደርስበት
ዝም አላቸው ጌታ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ
እኔ ን ከአባቱ ጋር በሞቱ ሊያስማማ.
ስለኔ ቆሰለ ተሰቃየ ጌታ
ለኔ ሂዎት ሊሰጥ ሞተልኝ ጎልጎታ
በሞቱ ሞቴን ከኔ አስወግዶ
ልጅነትን ሰጠኝ በሞቱ እኔን ወልዶ.
ገደልኩት እያለ ሰይጣን ሲያወራ
ጥቂት ቀንም ቢሆን በደስታ ሲኩራራ
ሰይጣን ተሸነፈ ሲኦል ድል ተነሳ
በትንሳኤው ንጉሥ በይሁዳ አንበሳ.
ታዲያ ለዚህ ጌታ ለውዱ ወዳጄ
እኖርለታለሁ ከልቤ ወድጄ
ምንም ለሱ ውለታ ባይኖረኝ የምሰጠው
ያለኝን በሙሉ ራሴንም ጨምሬ እሰዋለታለው.
ሃና መኮንን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተፈጸሙ ትንቢቶች በብሉይ ኪዳን የቱጋር እንዳሉ የምናይበት የጥያቄና መልስ ዝግጅት ነው


1. ለጽዮን ልጅ እነሆ ንጉስሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነብይ የተነገረው የፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።(ማቴ 21:- 4-5)
ሀ ኢሳ 25:-3 ለ ሚል 2:-3
ሐ ዘካ 9:-9 መ መዝ 109:-7
2.ነገር ግን በህጋቸው በከንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።(ዮሐ15:-25)
ሀ መዝ 109:3 ለ መዝ 69:4
ሐመዝ 35:7 መ ሁሉም
3.እላችኋለሁና ይህ ከአመጸኞች ጋር ተቆጠረ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ሊፈጸም ግድ ነው አዎን ስለ እኔ የሚሆነው አሁን ይፈጸማል አላቸው። ሉቃ 22:37
ሀ ኢሳ 53:12 ለ ኢሳ 53:9
ሐ ኢሳ 53:6 መ ኢሳ 53:10
4.መጽሀፍ እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሳብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።(ዮሐ 13:18)
ሀ ኢዮኤል 1:3 ለ መዝ 41:9
ሐ ሆሴዕ 2:5 መ ኢሳ 40:3
5.ይህም ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። (ዮሐ 19:24)
ሀ መዝ 2:7 ለ መዝ 25:4
ሐ መዝ 69:1 መ መዝ 22:18

አዘጋጅ፡ ኤልሳ ክፍሌ
ከገጠምኩ ለኢየሱስ የቀረበ

@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
6.ይህ የሆነ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።(ዮሐ 19:36)
ሀ ኢሳ53:2 ለ ዘጻ 12:46
ዘኁ 9:12 መ ለ&ሐ
7ኢየሱስ ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኃላ ተፈጸመ አለ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።(ዮሐ 19:30)
ሀ መዝ 69:21 ለ ሚክ 4:6
ሐ አሞ 2:5 መ ሀጌ 1:6
8.አህዛብ በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ። (ማቴ 12:21)
ሀ ኢሳ 41:6 ለ ኢሳ 46:3
ሐ ኢሳ 42:4 መኢሳ 43:10
9.ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ የገመቱትን የተገመተዉን ዋጋ ሰላሳ ብር ያዙ።(ማቴ 27:9)
ሀ ኤር 5:3 ለ ሕዝ 3:8
ሐ ዳን 7:8 መ ዘካ 11:12
10.ደግሞም ሌላው መጽሐፍ የወጉትን ያዩታል ይላል (ዮሐ 19:37)
ሀ ዘካ 12:10 ለ ዕን 3:8
ሐ አብድዩ 1:2 መ ሶፎንያስ 4:5

አዘጋጅ፡ ኤልሳ ክፍሌ
ከገጠምኩ ለኢየሱስ የቀረበ

@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
1ሐ
2መ
3ሀ
4ለ
5መ
6መ
7ሀ
8ሐ
9መ
10ሀ

መልስ ነው
Forwarded from ኢየሱስ ይወድሀል
1 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከህግ እርግማን ዋጀን ገላ 3:13
ሀ ዘጻ 21:20 ለ ዘዳ 20:21
ሐ ዘዳ 21:23 መ ዘሌ 25:5
2 አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ።2ተኛ ቆሮ 11:24
ሀ ዘዳ20:5 ለ ዘዳ 21:9
ሐ ዘዳ 27:8 መ ዘዳ 25:3