ከገጠምኩ ለኢየሱስ
19.2K subscribers
5 photos
4 videos
26 files
166 links
well come ወደ ቻናላችን በደህና መጣችሁ
1000284624703 አገልግሎታችን መደገፍ ከፈለጉ።
ስራችን ሙሽራው ማላቅ ቤተክርስቲያን ማብቃት ነው Owner @ErmiyAs_kifle
Download Telegram
...…..እርሱ ግን አርጓል

ተቀምጬ ነበር ዉስጤ ሀዘን ሞልቶ
አይኔን የጣልኩበት አምላኬ ሰው ሞቶ
ሳሰላስል ብዙ ምክንያቱ ቢጠፋኝ
ልጄ ያልኩት አምላክ ከጎኔ ሲለየኝ
አላስችል አለኝ ዉስጤ ፍቅርህ እየታወሰኝ
ሩህሩህ ደግ አባት እንዳንተማ አይገኝ
ደቀመዛሙርቱም ከፍሉ ተክዞ
ገሚሶ ሲሃመነታ ሲሰናዳ ለጉዞ
የትንሳኤ ማለዳ በሌሊት ተነስቼ
አይሁድ እንዳያዩኝ ማልጄ ወጥቼ
ሽቱ ልቀባበት አስከረንህ ላይ እዛ
ጌታዬ ተኝቶ ሞቶ እንደዋዛ
ስፈራ ስቸር በሌሊቱ ዉድቅት
ድንገት ታወሰኝ ያድንጋይ የከደኑት
አይይይ መከራዬ እሱም አለ ለካ
ከኔ አቅም በላይ ነው ዲንጋዩ ቢለካ
ደግሞም ዘብ አቁመዋል እንዳወሰድ በሰው
ይሁን ግን እንዴት ነው ድንጋዩን ማነሳው
እያሉ አዝግሜ ስደርስ ከደጃፉ
ተንከባሎ አገኘሁ ያድንጋይ ግዙፉ
ሮጬ..ሮጬ ዘለቅኩ ዉስጡ ካለበት አስከረኑ
የለም አልተገኘም ባዶ ነው ኮፈኑ
እሰይ እሰይ እሰይ እእእእልልልልል
እንደተናገረው ጌታ ተነስቷል
ኧረ የምስራች ላዘናችሁ ሁሉ
መቃብር ባዶ ነው አሜን አሜን በሉ
ያኔ የተናገረው ገሊላ ሲያስተምር
በሶስተኛ ቀን እንደሚነሳ ሲናገር
አላመንንም ነበር አይተን ሰውነቱን
እርሱ ግን አርጓል አሸንፎ ሞትን

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
........አንዱን በግ ለሁሉ አበቃው
ይሄ አለም ክፉ ነው ሀጥያት በዝቶበታል
ለአንዱ ሰውቼ ሌላው ይከፈታል
የበሬ የኮርማ የበግና ጠቦት
የዋኖስ የእርግብ አላዳነኝ ከሞት
ደግሞም ብገሰግስ ወደ መዳን ስፍራ
የመማፀኛ ከተማው ሩቅ ነው ተራራ
እባብም ሰቀልኩኝ ለመዳን ከመርዙ
ያም አልኩኝ ይህም አልኩኝ በዛብኝ መዘዙ
ሀጥያቴ በዝቶ ከመስዋዕቴ አቅም
ሰውቼ ስመለስ ይከፈታል ዳግም
ግራ ግበቶኝ እኔ ሳለሁ ሳመነታ
ለኔ ምትክ አድርጎ ሚሞት በኔ ቦታ
በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ
ተላከና መጣ ልይዘኝ በእጁ
አብ ስራህ ደንቅን ነው መስዋዕትህ ልዩ
ሀጥያት የሌለበት ያልታየ በላዩ
የኔ ብቻ ሳይሁን የአለምን ሀጥያት
የሚያስወግድ መስዋዕት ፣የሚታደግ ከሞት
ብዙ ...ብዙ ታርዶበት ብዙ የሞተውን
በልጁ ሞት ዋጀ ሲኦል የያዘውን
ሳይወጣ ከከተማ ተራራማ ሀገር
የመማፀኛ ከተማ አመጣልን እግዚአብሔር
አንዱን በግ አርዶ ለሁሉ አበቃው
አለማትንና ስልጣናት ለስሙ አስገዛው
ቤዛችን ነው ጌታ የታረደው በግ
ሁሉን በስልጣን ይዞ ጻዲቃን የሚያደርግ
በደሙ ተወራርዶ ዲያብሎስን ቀጣ
ስለኛ ሞተልን ሀጥያት በፃዲቅ ተቀጣ
አሁን ነፃ ሰው ነን ኩነኔ የሌለብን
በአብ ፊት የሚቆም ሊቀ ካህን አለን

በጌታሁን አናሞ☺️☺️

https://t.me/kegetemku_leyesus
በእኔ ሰበብ

*******

የተከበርክ ሳለህ ከፍጥረቱም በፍት
ከንቱ ያልተወራልህ ስለአንተ ማንነት
ዝናህ ሁሉ መልካም በምስጋና የታጀብክ
ታዲያ በእኔ ሰበብ ዛሬ ላይ ምን ተባልክ።

አትስረቁ እያልኩ በአፌ አስተምሬ
አታድርጉ ባልኩት ስገኝበት ዞሬ
ዛሬስ በእኔ ሰበብ አባቴ ምን ተባልክ
እኔ በሰረኩት አንተ ሌባ ተባልክ።

በሕግ ስመካ ሕግን ስተላለፍ
ቤትህን እያፈረስኩ ጣዖትን ስፀየፍ
ዉዴ በእኔ ሰበብ ዛሬ ላይ ምን ተባልክ
አሕዛብ ስሳደቡህ አንገት ደፍተህ አፈርክ።

ለካስ ለካስ
እንዲህ ሆኗል ውዴ ከእኔ በተነሳ
ማይገባው መንደር በስድብ ተወሳ
እንደ ልጅነቴ ላስከብር ሲገባኝ
ያንን ክቡር ስሙን ውርደት አስለበስኩኝ።

ይብቃ አረ ይብቃኝ
አሁንስ ይበቃል ተልካሻ መሆኔ
እንደ ዝንብ እየሆንኩ ስሙን ማስኮነኔ
የእውነት ልጁ ሆኜ ክብሩን ላስመልሰው
ፈለጉን በመሆን አባቴን ልካሰው።

ይኸው
ይኸው አባብዬ የምትወዳት ልጅህ
በመታደስ መንፈስ ቤትህ መጣሁልህ
በአሕዛብ መካከል ልሆን መከበሪያህ
ያስወቀስኩህ እኔው በክብር ላስጠራህ፤
በዚያ መልካም እጅህ እንደገና ያዘኝ
በምህረት አይንህ በይቅርታ እየኝ
እንዳላፈገፍግ ፀጋህን ጨምርልኝ
እስከፍጻሜው ቀን እንዲመስልህ እርዳኝ
   እወድሃለሁ አባቴ🥰🥰

ከሮሜ 2:17- 24  የተፃፈ

ቤቴል

@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
ክፍል 9
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

በ7ኛ ቀን ወሰንኩኝ አልፎ አልፎ ሴተኛ አዳሪዎች የሚያወሩት ነገር እሰማ ነበረ ሴትየዋ አትሰጣቸውም እንጂ ገንዘብ እንደሚያገኙ
ከዚያ ቤት ሲወጡ ቤተሰባቸው እንደሚረዱ የሚፈልጉትን እንደሚያደረጉ ተረዳሁ

ታድያ ኢቺ ሴትዮ የማትለቀኝ ከሆነ ለምን እንደምትለኝ አላደርግም ብትለቀኝስ የትኛው ኑሮ ልኖር ነው ያው መንከራተት መንከራተት ነው ምን አታገለኝ በቃ ልወስን ከዚ ብወጣም ስንከራተት አዱ ይደፍረኛል ሲጀመር በታዓምር ከዚ መውጣት አልችልም

እንደውም ከዚ የተሻለ ስራ ለኔ አይኖርም በቃ በቃ በቃ ኢቺን ስራ መስራት አለብኝ እንዴ 🤔 ከዚ ግቢ እወጣለሁ በቀን ኢሄንን ያህል እሰራለሁ ኢሄን ያህል እሰበስባለሁ ቤተሰቦቼን እረዳለሁ እለብሳለሁ እበላለሁ ምን አታገለኝ ከዚ ኑሮ ምን አለፋኝ ብዬ ወሰንኩና

ከራሴ ጋር ተስማማሁ ማልቀስ አቆምኩ ደስተኛ ለመምሰል ጥረት አደረግሁ ሁሌም ማታ ማታ እንደምትጠይቀኝ ዛሬስ አልተስማማሽም ብላ ጠየቀችኝ

ያቺ ቀን ተስማምቻለሁ አልኳትና ጎንበስ ስል እባኤ መሬት ላይ ጠብ አለ ሀሳቤ ማልቀስ አልነበረም

ሰቲቷ በጣም ደስ አላት ጎበዝ ልጅ አየሽ አሁን ገብቶሻል በቃ ከዚ በኋላ እኔና አንቺ የሚያጨቃጭቀን ነገር የለም

ማታ ስትገቢ ኢሄንን ልበሺ ኢሄንን ጫማ አድረጊ አለችኝ እኔም የምትለኝን ሁሉ እሺ ብዬ ተስማማሁ

እሷ የምትፈልገው ሰው ያን ቀን ሳይመጣ ቀረ
እንደተደዋወሉ አቃለሁ ምን እንዳለት አላቅም
ቀኑ መሸ ሆቴሉ የሚዘጋበት ሰዓት ደረሰና ተዘጋ

ምን ውስጥ ልገባ እንደተስማማሁ እያሰብኩኝ ከልጅነቴ ጀምሮ እንደተንከራተትኩ ቤተሰቦቼም ናፍቀውኛል ወደ ፊትለፊት ተደፍቼ ሰው እንደሞተበት ሰው እያለቀስኩ አደርኩ ጠዋት አሞኝ መነሳት አቃተኝ

ጠዋት ምን ሆነሽ ነው ምን በልተሻል የሚለኝ አጣሁ ማታ10:00 ሴትየዋ መጣችና የታለች አዲሷ ልጅ ብላ ጠየቀች ገባችና አየችኝ በፍፁም አላመመሽም አታስመሲ ተነሺ ብላ አስነሳችኝ የሚበላ ሰጠችኝ ለመብላት ሞከርኩ

ይቀጥላል

@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
ክፋል10
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

በ8ኛ ቀን ግን ሴትየዋ ያሰበቹ ተሳካ የኔ
ህይወት ተበላሸ ለሶስት ወር ያህል እሷ
ልበሺ ያለችኝን እየለበስኩ አድርጊ ያለችኝን
እያደረግሁ ያለምንም ጥያቂ በዝያ ቆየሁ

በሶስተኛ ወር ግቢ ውስጥ ያሉ ሴቶች እርስ
በራሳቸው ተጣልተው የተለየ ግርግር
ተፈጠረና ወጣሁ

ከዝያ ቤት ወጣሁ እንጂ ከዝያ ህይወት አልወጣሁም ወደ ሌላ ቡና ቤት ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ

የሴተኛአዳሪዎች ህይወት ትንሽ ብፅፍ ደስ
ይለኛል ሰዎች ስለ ሴተኛአዳሪ የሚያስበው
እንዲህ ነው

ዱርዬ ጥጋበኛ ዘልዛላ ምቾት የሚያደርጋት ያሳጣት ክብረቢስ ይመስላቸዋል ግን በፍፁም አይደለም ብዙ አይነት
ሴተኛ አዳሪ አሉ ለምሳሌ

እናት አባቶቻቸው ሲሞቱ የታናናሾቻቸው አላፍትና ወስደው ህይወታቸውን ለመታደግ
የራሳቸው ህይወት ለቡናቤት አሳልፈው
ይሰጣሉ

ሌሎቹ ደግሞ እንደኔ ሳያውቁ በጓደኛ ግፊት
ወይም ባሰሪያቸው ግፊት ሌሎች ደግሞ በድህነት ምክንያት ሌሎች ደግሞ
በጥጋብ አግብተው ምቹ ኑሮ እየኖሩ ጥጋብ
የሚያደርጋቸው ሲያሳጣቸው ይገባሉ
ሌሎች ደግሞ ከኢንቨርስቲ ተጭረው

ስለ ቡናቤት ሴቶች የፃፍኩላቹ ምናልባት
በመንገድ ወይም ባጋጣሚ የቡና ቤት ሴት
ስታገኟቸው አመለካከታቹ የጥላቻ እንዳይሆን እንድትረዷቸው አሳስባቹዋለሁ!!

ይህንን ታሪክ ስፅፍላቹ ነውርም ምስጥርም
እንደሆነ ወደ አምሮዬ ይመጣል ምናልባት
ምስጥሬን ስነግራቸው የሚወዱኝ ሰዎች
አጣቸው ይሁን የሚል ፍርሀትም ነበረኝ

ነገር ግን እኔ ስቃይ እንደ ውሀ ጭልጥ አድርጌ የጠጣሁ የሰው አፍ ያደከመኝ
በእሳት እና በመከራ የተሰራሁ በሸለቆ ውስጥ የተማርኩ ያሳለፍኩትን ላልደግመው
የተመለስኩ ሰው ነኝ እና ምንም ነገር ሊያስቆመኝ አይችልም


ቡና ቤት ቋሚ ስራዬ አድረጌው ቀጠልኩ
እኔ ገና ከክፍለሀገር የመጣሁ ምንም የማላውቅ ገጠሬ ነኝ እና ከሴቶች ጋር ለመመሳሰል የማደርገው ጥረት

ሲቅሙ እቅማለሁ ሲታጠቡ እታጠባለሁ
ሲኳኳሉ እኳኳላለሁ ከቡና ቤት ህይወት በብዛት ትዝ የሚለኝ ነገር ማታ ማታ ተውበን
እንገባና ቤቱ ሲዘጋ ወደ ስራ ያልሄዱ ሴቶች
ሰክረው ገብተው የሚያለቅሱት ለቅሶ

አንዷ የሞተችው እናቴ ትዝ አለችኝ ትላለች
ሌላኛው የቤተሰቦቼ ችግር ትላለች ሌላኛዋ
እንደዚ አይነት ህይወት ወስጥ እንዴት ገባሁ
ትላለች ሁሉም ብሶቱን እያነሳ ያለቅሳል

ከላይ መግቢያ ላይ እንደፃፍኩት የህይወቴ
ትውስታ መፃፍ የጀመርኩት የእግዚያብሄር
ምህረትና ቸርነት በተመለከተ ነው

የምፅፈው ነገር ትንሽ ትምህርት ካገኛቹበት
ወይም እንዲቀጥል የምትፈልጉ ከሆነ ላይክ አድረጉልኝ ገና ብዙ የምፅፈው ነገር አለ

ይቀጥላል

@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
...........ብዕሬ አለቀብኝ
ከጥናፍ እስከ አጥናፍ ልተርክ ስነሳ
አዕዋፍ ሳይንጫጩ ስላንተ ላወሳ
መንደርደሪ ብዬ በምስጋ ጀመርኩ
ስለ ገናናነትህ ዝናህን እያሰብኩ
እልፍ አዕላፋት የሰማይ ሰራዊት
ቅዱስ ቅዱስ ሚሉህ በቀንና ሌሊት
ግርማህ የሚያስፈራ ድምፅህ ነጎድጓድ ነው
ማደሪያህ በሰማይ መረፊያህ ምድር ነው
ይሄስ ይከብደኛል ከታሪክ በላይ ነህ
ሰግደው ሲሉ ቀና ደግሞም ቅዱስ ነህ
እጄን በአፍ ጭኜ ሳማትር ከማዶ
ከደመናት መሀል አየሁት ተራምዶ
ደግሞ መለስ ብዬ ሳስሰው ስራህን
በአለማት መሀል ድንቅ ፍጥረትህን
ተራራው ሸንተረሩ ጋራና ጅረቱ
ስላነተ ያወሳሉ ያዘማል ፍጥረቱ
የዛፎች ሽውሽውታ የነፋሳት ዜማ
የበቦች ሽታ የወፎቹ ዝማሬ ቀርቦ ለሰማ
አስተውሎ ላየ ሰው ምስባክ አያሸውም
የአምላክ ድንቅ ስራ ሰብኮ አይገልፀውም
=======//==========
በጧት ማለዳ ጮራ ስትፈነጥቅ በህብረ ቀለማት
ደግሞ አዘቅዝቃ ጀንበር ስትጠልቅ ያለው ዉበት
ከዋክብት ሲወጡ ከየጓዳቸው በሰማይ ሰሌዳ
ብርሃኗን ሰጠች ጨረቃም ወጥታ ለክብሩ ተገዳ
ክረምት ከበጋ ሚዛን ሳያዛባ ሄዶ ደግሞ ይመጣል
የዘመናት ሰሪ ቅዱስ እግዚአብሔር ስራህ ያስደንቃል
ሀፍረት ያዘኝ እኔ በዝች አይምሮዬ ማሰቤ ልገልፅህ
የዘመናት ቀመር የአመታት ቁጥር መነሻ የሌለህ
እድሜህ አይወሰን የነበርክበት የምትኖረው ከፊት
ብዕሬ አለቀብኝ ፅፌ ሳልጨርስ ስለአንተ ማንነት
በቃ ትቼዋለሁ ያየሁትን ልፅፍ ቃላት አጣሁና
አድንቄ ስመለስ ስራህ አይመዘንም ይታደሳል ገና
ቀለም ቢሆንልኝ ወንዝና ባህሩ ጅረቱ ፏፏቴ
መጻፊያ ቢሆኑም ቅጠል ዛፎች ሁሉ እያየሁ በፊቴ
ሲሶውን ላይገልጹ ለፈጠራቸው ለሰራቸው ጌታ
ትቼዋለሁ ብዬ ስሙ ይክበርልኝ ይኑር በከፍታ

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
........ጠረጠርኩህ መሰል
ሳትመጣ ወደኔ ወዳለሁበት ስፍራ
ቀድሜ ሳወራ መንገድህ ስጠርግ ቁጥኙን ሳጠራ
ድሮ ድሮ ያኔ ሳላውቅህ አውቄህ መንፈሴ መስክሮ
በበረሃ የሚጮህ ሰው ነኝ ዉሎዬ ነው ተናግሮ
እያልኩ እጮህ ነበር በበረሃማው ስፍራ
ለኑሮ በማይመች አቀበት ተራራ
የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውን አስወግዱ
ከሀጥያት ተመለሱ በሀሰት አትነግዱ
እያልኩ ነበር ሳጠምቅ በዮርዳኖስ ዉሃ
ለሚመጣው መንገስት እያስታጠኳቸው እንዲገቡ ንሰሃ
ታዲያ...ታዲያ ጠየቁኝ በምግባሬ ያወቁኝ
ስብከት ንንሬ ከመሬት ዘለል ሲሆን ጠረጠሩኝ

ማነህ??ማነህ ቆይ አንተ ንገርን እንወቅህ
ንግግርህ ጠጣር ሀያል ነው ቃልህ
እስቲ እንጠይቅህ አንተ መሲሁ ነህ??
ንገረን ለኛ አንተ ራስህን ማነኝ ትላለህ??
=======///==========
ሰውነቴ ራደ ልቤም ተረበሸ መንፈሴ ታወከ
ከሚመጣው መሲህ አወዳድረውኝ ህሊናዬ ታከከ
🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄
ስሙኝ ስሙኝ ልንገራችሁ፣ እንወቅህ ላላችሁ
እኔ ጠራጊ ነኝ መልክተኛ ብቻ እሱን አልምሰላችሁ
ከኔ ይበረታል ፣በፅድቅ በግርማ ስልጣኑ ይልቃል
እኔ የማጠምቅ በዉሃ ፣እሱ በእሳት ያጠምቃል
አዎ ከፀሀይ ይደምቃል አልችልም ለመቆም ከፊቱ
እጆቼም አይታዘዙ የጫማውን ክር ሊፈቱ
ይሄ ነው ጌታዬ የምሰብክለት የመጣሁ ላቀና
ተራራውን ልንድ ኮረብታውን ላደርግለት ቀና

ብዬ ያልኩህ ለታ አንተም ተገኝተሀል
በዮርዳኖስ ዉሃ ለስጋ ንሰሀ እዛው ተጠምቀሀል
እና!!እናማ ከመጣህ ካየሁክ ጀምሮ
ድንቅ ተአምራትህ አያልቅም ተነግሮ
ግና....ሀጥያትን ስገስፅ አይሆንህም ስለው
ይሄው ተጠፍሬ እየተሰቃየሁ በእስራት አለሁ😫
ንገረኝ ደግሞ አንተ እኔ ልጠይቅህ
ከመሞቴ በፊት የተነገረልህ
ያኔ የሰበኩህ ይመጣል የተባልከው
መሲሁ ክርስቶስ በእርግጥ አንተን ነው??
ካልሆንክ ንገረኝ ከነመከራዬ በእስራቴ ሳለሁ
ሌላ ክርስቶስ እንደሆነ እጠብቃለሁ
ብዬ ብጠይቅህ ጥያቅዬ ወቀሰኝ
ዝናህን ስሰማ ማዳንህ ታወሰኝ
ጠረጠርኩህ መሰል ይህ አለም ሲከብደኝ
ስለ ስምህ ስደት እስራት ሲገርፈኝ።
አሁን አውቄያለሁ በእርግጥ ያኔ ያልኩህ
የአብርሃም በግ ከላይ የመጣህ
ክርስቶስ አንተ ነህ እጠብቅሀለሁ
በእርግጥ እንድትመጣ ቃልህን አምናለሁ

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
የበዛ በደሌን ሀጥያቴን እያወክ
አትፀየፈኝም ልጄ ትለኛለህ
ደግሞም እነፃለው ያጥበኛል በደሙ
ምን ብዬ ልናገር ውዴ ይክበር ስሙ

ኤርሚያስ ክፍሌ

t.me/kegetemku_leyesus
የኢየሱስ ስም
ከገጠምኩ ለኢየሱስ
ድንቅ ትምህርት ነው ሁላቹም ስሙት የሰማቹት ላይክ እና ሼር አድርጉት

@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
.......እኔም ተጠማሁ

በዱር ከፍታዎች አድርጋ መኖሪያ
በተራሮች ራስ ግርጌ ነው መሰማሪያ
ተዘላ ትኖራለች የዱር ፍየል ዋላ
ነብሷን ለመጠበቅ አትልም የኋላ
ለዉሃ ያላት ፍቅር ዋጋው አይተመን
አሁንም አሁንም ወደ ዉሃ ምትበን
ምን ይሆን ምክንያቷ ለዉሃ መሳሳቷ
ሄደች ሲሉ ፈጥና ከምንጩ መገኘቷ
ብዬ ሳሰላስል አገኘሁ አንድ እውነት
ለዋላ ለካ ዉሃ ሰበቧ ነው ለህይወት
ስጋዋና ነው ጠላቷ ማመንጨቱ ሽታ
ስበትላ የሚወጣ ሚጠቁም ያለችበት ቦታ
ጠላቷ ገላዋና ነው የሚያጋልጥ ለክፉ
ከሩቅ ይጠራቸዋል መጥተው እንዲያጠፉ
መብላቷን አታቆም ይርባታልና
ከዉሃም አትርቅ ስጋዋ ይሸታልና
እናማ መፍቴሄ ለመጠበቅ ራሷን
ቢጠማትም ባይጠማት መጠጣት ነው ዉሃን
ያኔ ስትቀምሰው ከዉሃ ጠብታ
ድራሹ ይጠፋል ያ የስጋዋ ሽታ
አስስሰው ቢመጡ አናብስት ከዋላ
ሊያገኙአት አይችሉም ከጠጣች በኋላ
ዉሃ ህይወቷ ነው የመኖር ዋስትናዋ
ለመርካት አይደለም ለመኖር ነው ለዋላዋ
ይሄ ሚስጥር ገባኝ ለሚሸተው ስጋዬ
አፈር አፈር እያለ ላደፈው ገላዬ
ምድር ምድር ብሎ ያዋለኝ ከመሬት
ከፍፍ ብዬ እንዳልሄድ ለያዘኝ ሀጥያት
እኔም ተጠማሁኝ የመንፈስህን ዉሃ
አሳዶ እንዳይዘኝ የሀጥያት በረሃ
ልጠጣ ልረስርስ ከቅዱስ መንፈስ
ሊይዘኝ ያሻው ስጋ ባዶ ይመለስ
ልሰወር ልደበቅ ልጠጋጋ ከምንጩ
ከቅዱስ መንፈሱ ከማይደርቅ ምንጩ
ያኔ እተርፋለሁ ስጠጣ ከቅዱሱ
ተጠልዬ አልፋለሁ ስጋንና መንፈሱን
እንዳይሸት ገላዬ እንዳልገኝ ለሀጥያት
ከዘላለም ዉሃ ምንጭ ልገኝ ቀን ከሌት
ሰበቤ ነው ለኔም ለመኖሬ ዋስትና
የእግዚአብሔር መንፈስ ያሳርፋልና


መዝሙር 42
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?



https://t.me/kegetemku_leyesus

በጌታሁን አናሞ
.......ዕድል
ስጦታ ነው ዕድል ሳይታሰብ ድንገት
ለተገባ ሳይሆን ላልተገባ ባለበት
ማንም ሳያውቀው ሰጪው ብቻ አውቆ
ግን ለማን እንደሆነ እድልን ጠብቆ
ድንገት ካለበት ከማይታሰብ ቦታ
ላንተ ነው ላንቺ ነው የእድል ስጦታ
ብዙዎች እያሉ የተገባቸው ድሮ
ሊታደሉ ሳይሆን ሊሆናቸው ተቆጥሮ
ግና እድል መጣ ለኔ ለሀጠረያተኛ
በነፃ ተሰጠኝ አረንዲሆን መዳኛ
በበደሌ ምክንያት የቁጣ ልጅ ሳለሁ
ሞት የተገባኝ ከአብ የተጣላሁ
በምህረቱ እጅግ ባለጠጋ የሆነ
በፅድቅ ሀጥያቴን በፀጋ ከደነ
መፃተኛ ሳለሁ በባርነት ቀንበር
የልጁን ደም አድሎ ሰበረ የዕዳዬን ቀንበር
እድል ነው ይህ ለኔ የዳንኩበት መንገድ
በኔ አባት ተብሎ ሊጠራ ሲወደድ
አዎን እድል ነው ይሄ ብርሃን ዛሬ
እስሬን በጠሰው እንዳል ቀር ታስሬ
ዛሬ ታድያለሁ ሞቴ ተሽሮልኛል
በክርስቶስ በኩል ሰማይ ተፈቅዶልኛል
በመጋረጃ በማይከደን ብርሃን
እዛ ታድያለሆ ልቀመጥ ከፃድቃን
ከዚህ በላይ ደስታ ከዚህ በላይ እድል
የትም አይገኝም ከዚህ የላቀ ድል
ለዘላም ኪዳን በደሙ ዋጅቶኛል
በክርስቶስ ስራ ሰማይ ተገብቶኛል

በጌታሁን አናሞ


Like Share Comment
👇👇👇

https://t.me/kegetemku_leyesus
.........ከሌለህ የለንም

በሚነደው እሳት በቍጥቋጦው መሀል
ፊትህ ሳይታየኝ ስሜን ጠርተሀል
ከዘመድ ርቄ ተሰድጄ ሳለሁ በባይተዋርነት
አይዞህ በርታ ብለህ ያኔ አሳየኸኝ አብሮነት
ተስፋ ሰንቄ ሆኜ መልዕከተኛ በጠላቴ ምድር
ያለህ የምትኖር ስምህ ነው እግዚአብሔር
ሳትንቄኝ እኔን ኮልታፋ ምላሴን
አንደበት ሆነህልኝ ሰተኸኝ ሞገስን
ስምህን እንድሸከም ገድልህን ላወራራ
ሰተኸኝ ምልክት በትርን ተመርኩዤ
የጠላትን ዳርድንበር በስምህ አዝዤ
ምርኮን በዝብዘን ወጣን እየመራኸን
የባርነት ቀንበር ወደቀ ጠላት እያየን
ቀን በደመና ሌሊት በእሳት አምድ
እየመራህ መተን በራሀውን መንገድ
በስንፍናችን አስከፋንህ መሰል
ብዙ ሰነበትክ ያድምፅህ የታል
መመሪያችን ነው እሱ የመንገድ አቅጣጫ
እኛ አናውቀውም መግቢያና መውጫ
ደመናህ ይመለስ ይቅደም እንከተል
የእሳት አምድህ ይምጣ ከኋላ እንዲከልል
ብለን ስንጣራ ፊትህ ተቆጥቶ ተሰማ ድምፅህ
መሬት ተናወጠች ተራራሮች ዘለሉ ያስፈራል ግርማህ
ተራራውም ጤሰ ዘለለ እንደ ጠቦት
ዘለት ተናወጠ ስምህ ተቀምጦበት
የብርሃንህ ፀዳል ከፀሀይ ይበልጣል
በዚህ አምላክ ፊት ማን ችሎ ይቆማል
ስትጣራ ከዚያ ከሚያስፈራ ግርማ
እንደ ብዙ ዉሆች ደምፅህ ተሰማ

ሂዱ ዉጡ ከዚህ አሁን ይበቃችኋል
በኮሬብ ተራራ ብዙ ቀን ዞራችኋል
በሉ ተራመዱ ወዳልኳችሁ ምድር
መኖሪያ እያለ መቆያ ላይታደር
ክፉ እንዳይነካ መላዕክት እልካለሁ
ማንም እንዳይዳፈር ከፊት እሰዳለሁ
ትወርሳላችሁ ያኔ ተድላ ይሆናችሁ
እኔ ግን አልወጣም አልገኝ መሀላችሁ
😥😥😥😥😥😥😥😥😥😥
አባ !በቃ ይቅርብን ከሌለህ የለንም
ባልተገኘህበት እኛም አንገኝም
እልፍ አዕላፍ መላእክት ቢወጡ ከፊት
መናፍስት ናቸው ባንዴ ሚያጠፉት
ደግሞ ስምህ እንዳይሆን ለአህዛብ መሳለቂያ
መምራት ቢያቅተው ብለው መሳቂያ
አንወጣም እኛም አንተ ካልወጣህ
መላዕክት ሳይሆን ራስህ ካልመጣህ
አቅም ማን ይሁነን የመኖር ዋሳችን
ብንበድልህ ቅጣን አትራቀን አባታችን


በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
........አንድ አለ በሰማይ..

ሰው ሞልቶ ባለም ወዳጅም እያለ
ለነብሴ ረሀብ ሚሞላ የታለ
ባሳርፋት ብዬ በርትቶ ጩኸቷ
ብዙ ደከምኩ ያውነው መሻቷ
የዚህ አለም ዝና ክብርና ደስታ
ሊሞላ አልቻለም የነብሴን እርካታ
ሁሉም አላፊ ነው ጉም ነው ማይጨበጥ
የንፋስ ሽታ ነው አርፎ አይቀመጥ
እጅ መንሻ ይሻል የዚህ ምድር ሰላም
ስለት ሲጎድል ባለበት የለም
አይኔን አሻቅቤ ከሩቅ ወዲያ ማዶ
አንድ አለ በሰማይ የመጣ ተዋርዶ
መድሃኒተ አለም እርካታ አለ እሱ ጋ
የህይወት ዉሃ ነው ከሱ ለተጠጋ
በቁስ ማይተመን የማይነጥፍ ሰላም
ጌታ ኢየሱስ ነው ለስጋና ነብስም
አሁን እረካሁኝ ጥሜም ተቋረጠ
የሰላም አለቃ በልቤ ተቀመጠ
ረሰረሰች ነብሴ ጎስቋላ የሆነች
የዘላለም እረፍት ጌታን ስላገኘች

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
ክፍል11
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

ሁለተኛ ጊዜ የነበርኩበት ቤት ቅውጥ ያለ ጭፈራ ቤት ነበረ ያካባቢው ነዋሪ ብዙም የሰነጠለ አልነበረም ሁለት ወር ያክል ከቆየሁ በኋላ አንድ ሰው ማታ ሙባኤል ጠፋብኝ ብሎ መጣ ሁላችንም ተጠየቅን ሁላችንም አላየንም አላየንም ተባባልን ሰውየው ሄደና ተመልሶ መጣ አንቺ ነሽ ያነሳሹ ስጭኝ አለኝ

ኸረ በፍፁም እዛ ቦታ እኮ እኔ አላስተናገድኩም አልኩት አይ በጣም እርግጠኛ ነኝ አንቺ ነሽ ያነሳሹ ሲጭኝ አለኝ ኸረ በናትህ እኔ አላየሁትም ስለው ሄጄ እስከምመጣ ካስገባሽበት ቦታ አውጥተሽ ጠብቂኝ ተመልሼ እመጣለሁ አለ

እኔ ደግሞ አላየሁት ነገር ግራ ግብት ብሎኝ እራሴን መጠራጠር ጀመርኩ ተመልሶ መጥቶ የታለ ሙባኤሌ አሁን ስደውል እየጠራ ነበረ ብሎ በጁ የብረት ከዘራ አይነት ነገር ይዞ ነበረ ወገቤ እየመታኝ ስጭኝ አለ ኸረ በናትህ እኔ አላየሁትም ብዬ እያለቀስኩ የሆቴሉ ባለቤት ከቤቷ ወጣችና ምንድነው አለቹ እሷ እራሷ ማታ እየጨፈርኩ ሙባኤል ባስቀመጥኩበት ቦታ ሰርቃኛለች አለ

እሷ መሆኗን እንዴት አወቅህ በቦታው እሷ አላስተናገደችም አለቹ ስናስተናግድ ቦታ ቦታ ይሰጠን ነበርና በርግጠኝነት እሷ እራሷ ነች ሙባኤሌን የወሰደቹ አለ አይተሀታል ወይ ስትለው በፍፁም አላየኋትም ግን እሷ ነች የወሰደቹ ብሎ ግግም አለ

ታድያ እኔ ምን ልርዳህ አላየሁትም ብላ እያለቀሰች ነው ስትለው እንዳሳምናት ለብቻዬ እድል ስጭኝ አላት እሷም አንተ እንዳልክ
ብላ ትታኝ ዘወር አለች እያነሳ በርግጫ እያነሳ በጥፊ እያነሳ በዱላ ቅጥቅጥ እያደረገኝ ስጭኝ ሙባኤሌ ማለቱን ቀጠለ
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

እኔ ደግሞ ከየት ላምጣ ለራሴ እንኳን ሙባኤል የለኝም እሪሪሪሪሪሪ እያልኩ እያለቀስኩ እየጮሁኩ ሰው ቀርቦ ምን አድረጋ ነው ብሎ ሲጠይቀው ሰርቃኝ ነው እያለ ይመልሳል ያካባቢው ሰው ደግሞ በቋንቋ ያምናሉ ማለቴ ዘረኝነት አለባቸው ያሁኑ ባላውቅም
🤔🤔🤔🤔🤔😏😏😏😏😏😏
በነገራችን ላይ ኢሄ ሁሉ ሲሆንብኝ 14አመት አካባቢ ነበረኩ ለሚያየኝ ግን በፍፁም ትልቅ እመስላለሁ

በስተ መጨረሻ እንዴት አወቀህ ነው እሷ እንደወሰደችብህ ሲባል ጠንቋይ ነግራኝ ነው አለ እንዴት ምን ነገረችህ ሲባል በቃ እንዲህ አይነት ልጅ ብላ ሙሉ ምልክት ነገራኛለች እራሷ ነች ብሎ ግግም አለ እስቲ ይዘሀት ሂድ ተባለ
ወደ ጠንቋይ ቤት ይዞኝ ሄደ ገባን አጠገቧ ጀበና አለ ቡና እየተፈላ ይመስለኛል ገና ሳልቀመጥ እኔ ነኝ የሱን ሙባኤል የውሰድኩት ወይስ ተሳስቶ ከሆነ ብዬ ነው አልኳት አዎ አንቺ ነሽ የወሰድሹ መልሺለት እኔ የማየው አንቺ እንደወሰድሽ ነው አለችኝ ምንድነው እያወሩ ያሉት ግራ ገባኝ እኔኮ ምናይነቴ ሙባኤል እንደሆነ እራሱ አላወቀሁትም ወይይይ ስቃይ

ይቀጥላል

@kegetemku_leyesus
@Kegetemku_leyesus
እንፀልይ
ከገጠምኩ ለኢየሱስ
እስኪ ላይክ ሼር በማድረግ አበረታቱን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
ክፍል12
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

አዎ አንቺ ነሽ የወሰድሹ መልሺ እኔ የማየው አንቺ እንደወሰድሽ ነው ስትለኝ ተነስቼ ወጣሁ እንዳበደ ሰው ብቻዬ እያወራሁ ስሄድ ባለ ሙባኤሉ መጣና ደረሰብኝ አመንሽ ታድያ አሁን አረጋገጥሽ እያለ አንገቴን ያዘኝ እና ትመልሻለሽ ወይስ አሁንም አታምኚም አለኝ 😭😭😭

እሺ ልመን እና ሰርቼ ልክፈል ስለው በፍፁም እኔ ከቀፎ ይበልጥ ሲም ካርዱን እፈልገዋለሁ አለ ለማውጣት ሼም ይዞሽ ከሆነ ለኔ ለብቻዬ ሲጭኝ ለማንም አልናገርም እያለ እያመረረው ሄዷል በየ ዕለቱ እየመጣ እየቀጠቀጠኝ ሰውነት ጠባሳ በጠባሳ አደረገኝ ለሱ ብዬ ቤት ብቀይርም ያለሁበት እየመጣ ይመታኛል ይመታኛል ሲባልኮ አይነት አለው ቆሜ በጠረባ ነው የሚጥለኝ በከዘራ ነው የሚመታኝ

እንዴት ለፖሊስ አትናገሪም ካላቹኝ ያካባቢው ፖሊሶች በቋንቋቸው ለሚናገር ሰው ብቻ ነው የሚሰሙት የሚያምኑት ከምሽቱ 4:00መጥተው አስፓልት ላይ አውጥተው ነው የሚመቱኝ ደግሞ ለብቻው አይደለም እኮ ተመሳሳይ ጓደኛ አለው ቢያንስ አምስት ይሆናሉ

ለመጨረሻ ጊዜ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ መጥተው እንዳልሞት እንዳልድን ሽባ አድርገውኝ ሄዱ እኔም እንደ እባብ አፈር ልሼ ተነሳሁ

የህይወቴ መከራ በዚ አላበቃም ገና መቼ ተነካና በመሀል መፃፍ የነበረብኝ የረሳሁት አንድ ነገር አለ የልጅነቴ ጠባሳ አስታወሳቹት በእሳት ተቃጥዬ ነበረ

ያቺ ጠባሳ ሰው እንዳያይብኝ ታሳቅቀኛለች ሴቶች ሁሉ ቀን ቀን ሲቅሙ እቅማለሁ ሲበሉ እበላለሁ ሲጠጡ እጠጣለሁ ማታ 12:00 ሲሆን ሁሉም ተነስቶ ወደ ሻወር ለመሄድ መተፋፈር የሚባል ነገር አይታወቅም ሁሉም ሻውሩን ይወስዳል የሰውነት ክሬም እራቆታቸው ቆመው ይቀባሉ እኔ ግን አውቄ ወደ ኋላ እቀራለሁ ሁሉም ወደ ቡና ቤት ከገቡ በኋላ እኔ ደግሞ ለመታጠብ እነሳለሁ የቡናቤቱ ማናጀር ለምን ታረፍጃለሽ እያለ ጭቅጭቅ😏😏🤔
በነገራችን ላይ ማንም አይወደኝም ማንም አያቀርበኝም ማንም አይረዳኝም ደም ግባት የሚባል ነገር አልነበረኝም ሴቶች ሲያዩኝ ፍራዋ መጣች ነበረ የሚሉኝ 🙄🙄🙄ደግም የመጨረሻ ፋራ ነበርኩኝ ከሴቶች ጋር በጭራሽ አልመሳሰልም ነበረ

ከዚያማ ጠባሳዬ እያሳቀቀኝ ቀጥሏል አጫጭር ልብስ ለመልበስ አልሞክረውም ብቻ ምን አለፋቹ እኔ ለቡናቤት እንዳልተፈጠርኩ ሁኔታው ያስታውቃል ከወንድ ጋር ሳልሄድ ብዙ ቀን ይሆነኛል ወንድ እንዳይጠይቀኝ ተደብቄ አመሻለሁ ሲነጋ የምበላው አጣለሁ ሴቶቹ እርስ በራሳቸው ፍቅር ናቸው እኔ ግን ሲያመኝ እንኳን ምን ሆነሽ ነው አይሉኝም

ከእኔም ብሶ ፍቅር ያዘኝ እ🤣? ማለቴ አንዱ ወደድኩሽ አለኝ ልጁ ቆንጆ ወንዳወንድ ፈገግታው የሚያምር ነበረ ታድያ እኔ የወደድኩት ቆንጆ ስለነበረ ሳይሆን ፋራ ሆኜ አለባበስ ሳልችል እንደውም ከእናቴ ማዕፀን ከወጣሁ ለመጀመርያ ጊዜ ሰው ወደድኩሽ ሲለኝ ከመውደድ ውጪ ምን አማራጭ አለኝ

ካአንድ ቀን እይታ በኋላ ነጋዴ ስለነበረ ወደ ንግድ ሄዶ ቆየ በሰው ስልክ እየደወለ ያወራኝ ነበር ልክ እረጅም ጊዜ እንደማውቀው ሰው ናፈቀኝ እሰከ ማገኘው ቸኮልኩ ከስራ ቦታ ተመልሶ መጣ በምሰራበት ቤት ምሳ ጋብዞኝ አይን አይኔ እያየ እጄን ይዞኝ ቁጭ ብለን ለረጅም ሳዓት እያወራን ቆየን ለካስ እሱ ከዚ በፊት ሌላ ፍቅረኛ ነበረቹ እሷም የሀገሩ ልጅ ነች ማለቴ የሆለታ ልጅ ነች በአካባቢው ታዋቂ ሴተኛ አዳሪ ነች ሌላ መዘዝ ጉዴ ፈላ!!

ይቀጥላል

@Kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
......መሀሪ ነው
መግቢያ ግራ ገብቶህ የባዘንክ ወንድሜ
የመኖርህ ዋጋ የጠፋብህ እድሜ
ደስታን ፍለጋ ብትቀላውጥ ካለም
እረፍትን ፍለጋ ላይ ታች ብትልም
ባለህበት ሆኖ የህይወት መንገዱ
ዞሮ ዞሮ እዛው ያው እንደ ልማዱ
............👂👂ስማኝማ
አንድ አለ በሰማይ ልብን የሚያሳርፍ
ከፍለህ ያጣሄው ሰላም አለ ከሱ እቅፍ
አባት ነው ለሁሉ ሚወድ ሀጥያተኛ
ደሙን አፍሶልህ የሆነ መዳኛ
ይጠራሀል ዛሬም አንተ ልጄ ብሎ
ላንተም ጭምር ነው የዋለ ተንጠልጥሎ
የሚከስህ በደል ሀጥያት ስንፍና
አሸንፈህ ዉጣ ወደ አዳኝህ ቤት ና
ደጅ አያስጠና ይቀበልሀል ደግሶ
ዉጪ አይወጣም የመጣ ተመልሶ
ፍቅሩ ማራኪ በመስቀል የታየው
እርቃኑን ተሰቅሎ በእንጨት የዋለው
ዋጋ አያስከፍልህ ከፍሎልሀል ጭራሹን
በነፃ እንድትድን ተወግቶልሀል እጁን
ና ወደ እልፍኙ ግባ ወደ አብ ጉያ
የሰላም አምላክ ነው የሌለው አምሳያ
መሀሪ ነው በደልን ይቅር የሚል ጌታ
እንደሱ ፍቅር የለ ከቶ የትም ቦታ
የሰላም አባት የእረፍቱ ባለቤት
መኖሪያን የሰራልህ መንፈሱ ባለበት
ተመልሶ ይመጣል ሊወስደን ከሱ ጋ
እዛ ሀዘን የለ   ክርምትና በጋ
በጉ ነው ብርሃን ፍቅር ነው ቀለቡ
እቅፉ ይደላል ከጉያው ለገቡ
አንተም ወንድሜ የባከንከው በአለም
ወደዚህ ድግስ ና እረፍት ይሁን ዘላለም

በጌታሁን አናሞ

https://t.me/kegetemku_leyesus
Forwarded from ኢየሱስ ይወድሀል
1ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።ማቴ 4:4
ሀ ዘዳ 8:3 ሐ ዘዳ 20:3
ለ ዘዳ 9:2 መ ዘዳ 3:8
2 ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል።ማቴ 21:13
ሀ ኢሳ 50:6 ሐ ኢሳ 56:7
ለ ሙዝ 95:1 መ ሙዝ 110:3
3 የሰውም ስርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ። ማር 7:7
ሀ ሕዝ 19:5 ሐ ኤር 9:12
ለ ኢሳ 29:13 መ ሚክ 7:9
4 እነርሱም አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺሞ ህዝቤን እስራኤል የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና.. ማቴ 2:5-6
ሀ ሚል 3:1 ሐ ኢሳ 6:1
ለ መዝ 88:6 መ ሚክ 5:2
5 ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴ 4:7
ሀ ዘጻ 20:12 ሐ ዘዳ 16:6
ለ ዘዳ 6:16 መ ዘጻ 30:5
Forwarded from ኢየሱስ ይወድሀል
1ሀ 2ሐ 3ለ 4መ 5ለ
በኢየሱስ ስም እንዲህ ባረኳችሁ መሻታችሁ ሰማይ ይሁን ሃሳብ ፈቃዳችሁ በሰማዩ ሃሳብ ይወሰድ ኢየሱሴ ይኑርባችሁ ፈቃዳችሁን ወስዶ ፈቃዱን ይክተትባችሁ እናንተ ደብዝዛችሁ ኢየሱሴ ይታይባችሁ እናንተ ሞታችሁ ኢየሱሴ ይኑርባችሁ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና ሃሳብ ኖራችሁ ማለፍ ይሁንላችሁ ለታይታ ከሚኖር ክርስትና ይሰውራችሁ ከኖራችሁ አይቀር ከልባችሁ ለኢየሱስ ኖራችሁ ማለፍ ይሁንላችሁ ለእናንተ ምንም ሳታስቀሩ ያላችሁን ለጌታ መስጠት ይሁንላችሁ የናንተ የሆነው ሁሉ አንጠፍጥፎ ይውሰድባችሁ ሰዎች እናንተን ሲያዩ ኢየሱስን ይመልከቱ የኔ ጌታ ብቻውን ይግዛችሁ ብቻውን ይኑርባችሁ በትውልድ መሃል ልዩነታችሁ ይሁን ስትጠሩት ይስማችሁ ስትፈልጉት ይገኝላችሁ ፀሎታችሁን ይመልስላችሁ እንደሃያል እንደ ጨካኝ ከፍታችሁ ይውጣ በከበዳችሁ ባስጨነቃችሁ ነገር ላይ ይቁምላችሁ ማዳኑን ያሳያችሁ ተራራ ሆኖ አላሳልፍ ያላችሁን ይንቀልላችሁ አንተ ተራራ በልጄ ዘሩባቤል ፊት ምንድነህ ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ ብሎ እንዳለው እንደዛ ከፊታችሁ እንዳትራመዱ የከለከላችሁ ነገር ደልዳላ ሜዳ ይሁንላችሁ ሰው ወዳላችሁ ሳይሆን ጌታ ወደነገራችሁ ወዳሳያችሁ ወደዛ መድረስ ይሁንላችሁ ኢየሱሴ ከፊት እየወጣ መንገዳችሁን ይጥረግላችሁ ወጥመዱን ሰብሮ ያሻግራችሁ ከምታዩትም ከማታዩትም ስውር የጠላት ቀስት ይሰውራችሁ ተባርካችሁ ለበረከት ሁኑ ዘመናችሁ የስኬት የልምላሜ ጌታ ካየላችሁ ነገር ጋር የምትገናኙበት የክብር ዘመን ይሁንላችሁ እወዳችዋለው