የ6ኛ ፣ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ምዴል ፈተና መስጫ የጊዜ ሴሌዳ
(መጋቢት 30/2017 ዓ.ም)
(መጋቢት 30/2017 ዓ.ም)
❤1
እንቅልፍ ነው እሚያስወስድህ/ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
---------------------------------------------------------------
"ዝም አልኳቸው ዝም ይበሉኝ
ትቻቸዋለሁ ይተዉኝ
አልነካቸውም አይንኩኝ"
ብለህ ፥ ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተዉኛል ብለህ
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?!....
ተስፋ አርገህስ ምን ልትሆን ፥ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ?
እንቅልፍ እንጂ እሚያስወስድህ ።
"አልጠራቸውም አይጥሩኝ
አይንኩኝ ስሜን አያንሱኝ"
ብለህ እንዴት ትመኛለህ ፥ እንደማይተዉህ ስታውቀው
የተወጋ በቅቶት ቢኛ ፥ የወጋ መች እንቅልፍ አለው
የጅምሩን ካልጨረሰው ?
የተበደለ ቢችልም
ቢሸሽግም ቢደበቅም
የበደለ ዝም አይልም ።
እንዴት አስችሎት ዝም ይበል? ለፍልፎ ከማስለፍለፉ
አደል እንዴ የሱ ቤዛ ፥ የበደሉ ጥቅም የግፉ
ሰላም መንሳት አደል ትርፉ? . . . .
ዝምማ ካለ ጉድ ፈላ
ነገር በጤና ሲብላላ
እያደር ሲጣራ ኋላ
ግፉ ይፋ ይሆናላ! . . . .
ሰላምማ ከለገሠህ
ሕመምህ እየታወሰህ
ትዝታ እየቀሰቀሰህ
የሕሊናም ሚዛን ረግቶ ፥ ጉዱ ሁሉ ኩልል ሲል
ያደፈረሰው ሲያጠልል
እግዜር ያሳያችሁ ብለህ ፥ ፍረዱኝ ዳኙኝ እንዳትል
ከነአካቴው ሳይጨርስህ
ምን ቢሆን ሰላም አይሰጥ ።
እሱስ ቢሆን ያለትክሉ ፥ ያላጥንቱ የሰላም ውርስ
ከቶ የማያውቀውን ቅርስ
ይስጠኝ ብትል የት ይሆናል
ያልተዘራ መች ይበቅላል? . . . .
የጓሮ ጐመን ሲያጠላ
አጥፊ ትሉን እንዲያፈላ
እንዲያው በነገር ቀደም ፥ እንደሱስ ስሙን ቢለፍፍ
ሰላምን የሰጠህ መስሎህ ፥ በጉጉት ስታሰፈስፍ
ተለሳልሰህ እንደቃተትክ ፥ ተስፋ አርገህ እንዳትል እርፍ ።
እና ዘበት ነው ጥረትህ
በከንቱ ተስፋ ማድረግህ
ላያዋጣ መመኘትህ
የሰላም ቅዠት ማየትህ
ምን ልትሆን? ምን ሊሆንህ? . . . .
ይቅርብህ ። በኔ ይሁንብህ
እንቅልፍ ነው እሚያስወስድህ ።
---------------------------------------------
ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን

👍4
የፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚፈጠር ስርቆት አይኖርም
ሚያዚያ 04/2017 ዓ.ም
ባለ 12 አሀዝ የፋይዳ ልዩ ቁጥር በህይወት ዘመን አብሮ የሚቆይ የማይቀየር ቁጥር ሲሆን የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሀዝ) ቁጥር የሚባለው ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የሚቀየር ቁጥር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር አንድ ግለሰብ ትክክለኛት ለማረጋገጥ አገልግሎት የሚያገለግል ነው፡፡
ነገር ግን ይህ ቁጥር በባዮሜትሪክ መረጃ የተደገፈ ልዮነትን የሚገልፅ በመሆኑ የአንድን ሰው ፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚመጣ ምንም አይነት የማንነት ስርቆት ወይም ሌላ አገልግሎት ተመሳስሎ የሚገለገልበት አግባብ አለመኖሩን ከብሄራዊ መታወቀያ ፕሮግራም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @Taye.B

ጥንቃቄ - ሸር
ብዙ ሰው የቴሌግራም አካውንቱ እየተጠለፈጠት ይገኛል። ይህም የሚሆነው ከታች ባያያዝኩት Screenshot አይነት link በመላክ የርስዎ ፎቶ ከታች አለልዎት በማለት ይልኩላችኋል።
ይህን link አንድ ጊዜ ከተጫናችሁት ቴሌግራም እና የWhatsApp አካውንታችሁ ሙሉ በሙሉ ይመሰዳል።
በዚህ ሂደት
1- በአካውንታችሁ ከምታውቁት ጓደኛ ዘመድ ብድር ላኩልኝ አስቸኳይ ፈልጌው ነው በማለት ያጭበረብሩበታል።
2- የወንጀል ስራ ይሰሩበታል
3- መረጃችሁን ታጡበታላችሁ።
ስለዚህ ይህን መረጃ ለ3ኛ ጊዜ እያጋራሁት ቢሆንም ትኩረት ባለመሰጠቱ ብዙዎች እየተሸወዱ ይገኛሉ።
ስለሆነም የዚህ አይነት መልዕክቶችን የምታውቁት ሰው ቢሆንም ባይሆንም ለምን አለቃችሁም ቢሆን አትክፈቱት
መረጃውን አጋሩት
https://t.me/karapschool

👍2❤1👻1
ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ♥️ ♥️ ♥️
Happy Easter! Wishing you a joyful and blessed holiday filled with peace, love, and hope. 🎄🎄🎄
Ayyaana Du'aa ka'uu Gooftaa keenya iyyesuus kiristoosiin(fayyisaa dhala namaatiin) baga isin gahe. Ayyaana gaarii። ♥️ ♥️ ♥️
አቶ ታዬ ቢሻው።

👍4❤1
Follow the Kara Kore Pschool 2017 channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb5zaIK6mYPRVRZHSI0e
WhatsApp.com
Kara Kore Pschool 2017 | WhatsApp Channel
Kara Kore Pschool 2017 WhatsApp Channel. Kara kore primary school information desk! 0 followers
❤1
#Reminder
የፋይዳ መታወቂያ አውጥተዋል?
በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ተፈታኞች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ሊያወጡ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።
የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባውን በጊዜ በማድረግ የፋይዳ መታወቂያዎን ይያዙ።

❤1👍1
12ቱ ተቋማት በአንድ ጣሪያ ሥር
*
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
የአሰራር ስረአቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያሰቀር ነው፡፡
አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት አስራ ሁለት የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን አርባ አንድ የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችንም አቅርበዋል፡፡
አገልግሎቶቹም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ፋይዳ ድጅታል የመታወቂያ ምዝገባ እና ሌሎችንም አካትተዋል። በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም በአንድ ስፍራ የ12 ተቋማት 41 አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህም ፡
1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም
ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡም ይገኛሉ።

❤3