ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
1.03K subscribers
2.92K photos
44 videos
102 files
787 links
ይኽ በፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች የሚለቀቁበት ሚዲያ ነው።
https://linktr.ee/kaletsidkizm
Download Telegram
🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑
<< በዘጠኝ ሰዓት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ራሱን ዘንበል አድርጎ ሁሉ ተፈጸመ አለ >>


📜 - ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት  ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ ።

📜 - ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት  ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ ።

📜 - ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት  ከልሃ ኢየሱስ ቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ ።

📜 - ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት  አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ ።

🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑🌑

በዘጠኝ ሰዓትም አሞትና ከርቤ አጠጡት በአፉ ውስጥም ጋቱት ሰይጣንና ሞትን ይጠብባቸዋል ዘንድ በቃሉ ጮሆ ወደ አባቱ አመለከተ
....መዝገበ ሃይማኖት....
*_ኪርያላይሶን_*
*_ኪርያላይሶን_*
*_ኪርያላይሶን_*
"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !!
አምንስቲቲ :ሙክርያ :ኣንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ :ሙክርያ :ኣንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ :ሙክርያ :ኣንቲ ፋሲልያሱ
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ
ተዘከረነ እግዚኦ ሊቅነ
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ
ወወደዮ ሓሞተ ውስተ መብልዕየ
ወአስተዩኒ ብሒአ ለጽምዕየ
ወወደዮ ሓሞተ ውስተ መብልዕየ
   ዐርብ ሠርክ፤ በዐሥራ አንድ ሰዓት
💫💫💫💫💫
አቡን ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሀተ ዘእንበለ ዐቅም ዬ ዬ ዬ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ ወኸእንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ፡፡
በዚህ ሰዓት የለከ ኃይል፣ የኪርያላይሶን ስግደት፣ የሠርክና የንዋም መልክአ ሕማማት የለም፤ የሰዓቱን ምንባባትም በቅዳሜ ሌሊት ማንበብ ይቻላል፡፡
ዐርብ ጠዋት ወጥተው የነበሩት ንዋያተ ቅድሳት ኹሉ ወደ ቦታቸው ከተመለሱ በኋላ ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዐተ ግንዘትን ይሥሩ፤ ፫ ካህናትም ሥርዐተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት፣ አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል፣ አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት ይዞ ፊት ለፊት ይምራ፤ በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ፤ ከዚህ በኋላ በ፬ቱም ማዕዘናት እየዞሩ ፬፻ እግዚኦታ ያድርሱ አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም፤
በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ (4x5=20)፣
በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ (4x5x9=180)፣
እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ (4x5=20)፣
በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ (4x5x9=180)
ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ አቡነ ዘበሰማያት ይስጥ፤ እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርያላይሶን ይበል፤ ሕዝቡም እንደርሱ ይጸልዩ፡፡
ከዚህ በኋላ በቅኔ ማሕሌት ኹሉም ይሰብሰብ፣ መቋሚያ ይዘው፣ በመካከላቸው መብራት (ጧፍ) አብርተው ይያዙ፣ የዳዊትንና የነቢያትን ጸሎት ከሕዝቡ ጋር እየተቀባበሉ ያንብቡ፤ እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፤
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ንኡስ አነ እምአኃውየ፤መዝ.፻፶(፻፶፩)፥፩-፰
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ እግዚኦ ኢትጸመመኒ፤መዝ.፻፰፥፩
ይ.ሕ.፤ ለይሁዳ ወልዱ ወለውሉደ ውሉዱ ይደምሰስ፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር፤መዝ.፻፴፭፥፩
ይ.ሕ.፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ይባርክዎ ኵሉ ግብረ እግዚእ፤መዝ.ሠለ.ደቂቅ ፩
ይ.ሕ.፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር፤ጸሎተ ሙሴ ፩
ይ.ሕ.፤ ስቡሐ ዘተሰብሐ፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአን፤መዝ.፩፥፩ ይ.ሕ.፤ ከአንባቢው ጋር ያስተዛዝሉ
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድን አንብበው መጨረሻው ላይ ‹‹ወፍኖቶሙሰ ለኃጥአን ትጠፍእ›› ሲባል፤ በመካከላቸው የየዙትን መብራት (ጧፍ) በመቋሚያ መትተው ያጥፉት፡፡ ከዚህ በኋላ መዘምራኑ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር እንደ ሥርዐቱ ይዘምሩ፡፡
ካህናቱ ሕዝቡን በወይራ ቅጠል እየጠበጠቡና ስግደት እያዘዙ ወደቤታቸው ይሸኟቸው፡፡

     💫💫💫💫💫
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !!!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለጥምና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !!!
አቤቱ ማረን ይቅር በለን፤ 🤲🤲🤲🤲🤲
#የስቅለት በዓል በቀበና መካነ ህይወት አቡነገብረመንፈስቅዱስ ቤ/ክ #አክፍሎት ማለት

በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡

ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡

ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡

ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት
#ቀዳም_ሥዑር

የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም «ስዑር /የተሻረች/» ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም፡፡ ቀዳም ሥዑር በጾም ምክንያት የተሻረችው ቀዳሚት ሰንበት ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ፣ እየተመለጠነ፣ እየተ ዘመመ እየተመረገደ እየተጸፉ ያድራል ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡

ገብረ ሰላመ በመስቀሉ እየተባለ እየተ ዘመረ ቀጤማውም ቤተ መቅደሱን ዞሮ በካህኑ ተባርኮ ለምእመናን ይታደላል፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡

ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርሰቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ትንሳዔ

“እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤”
 
             መዝሙር 78፥65

“.... ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።”
                 ሉቃስ 24፥5

ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን !
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን !
አሠሮ ለሰይጣን !
አግዐዞ ለአዳም !
ሰላም !
እምይእዜሰ!
ኮነ!
ፍሥሐ ወሰላም !


#እንኳን_አደረሳችሁ
​​👉 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ሰኞ

👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ

👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ

👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ

👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

ዓርብ

👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ

👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ

👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
ሰኞ ማዕዶት
ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል::
+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ
*ከባርነት ወደ ነጻነት
*ከጨለማ ወደ ብርሃን
*ከሞት ወደ ሕይወት
*ከኃጢአት ወደ ጽድቅ
*ከሲዖል ወደ ገነት
*ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት
አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል::
+አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች::
+ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና::
=>አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን::
=>+"+ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ::
በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ጴጥ. 3:18)