✍ከቅዱስ አባት ረድኤት በረከት ያድለን!!!
መልካም ቀን!🙏🙏
መልካም ቀን!🙏🙏
" ራስህን ከቤተክርስቲያን ፈፅሞ አትለይ፤ ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን ደኅንነትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መጠጊያህ ናት።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
" ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና..."
ኢሳ. ፶፮፥፯ /56፥7/
ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት የጸሎት ቤት ነው። በእዚያም እርሱ አለና።

✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ✝፡፡ ✞✞✞
✞✞✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው #ቅዱስ_ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝ ✞✞✞
+"+✝ #ቅዱስ_ታዴዎስ_ሐዋርያ ✝+"+
=>#ቅዱሳን_ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ3 ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል::
¤እንደ #ዮሐንስ_ወንጌላዊ ያሉት በ20ዎቹ ውስጥ:
¤#ቅዱስ_ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ30ና በ40ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን
¤እነ #ቅዱስ_ዼጥሮስ ደግሞ በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ:: ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም: ከጐልማሶችም ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው::
+ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ #ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) #ስምዖን እና #ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል::
+ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ:
¤ከ12ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ:
¤3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ተምሮ:
¤በዕርገቱ ተባርኮ:
¤በበዓለ ሃምሳም 71 ልሳናትን ተቀብሎ:
¤#ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል::
+ቅዱስ ታዴዎስ አንድ ቀን ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር ወደ አንዲት ሃገር ይገባሉ:: ታዲያ ለቀናት ያለ ምግብ ወንጌልን ሲሰብኩ ቆይተው ነበርና ደጐቹ ሐዋርያት ራባቸው:: ወደ ከተማዋ ሳይገቡ አንድ ሽማግሌ ሲያርስ አይተው ሰላምታን ሰጡትና "እባክህ እርቦናልና አብላን" አሉት:: እርሱም ምንም ወገኑ ከአሕዛብ ቢሆነ አሳዝነውት በሬዎቹን ሳይፈታ እየሮጠ ሄደ::
+ያን ጊዜ ቅዱስ ታዴዎስ ሊቀ ሐዋርያትን "እርሱ እስኪመጣ ለምን አናርስም" አለው:: 2ቱ ተነስተው ታዴዎስ ሞፈር: ዼጥሮስ ደግሞ ስንዴውን ያዘ:: ቅዱሳኑ እየዘሩ ያረሱት ሰውየው ምግብ ይዞ እስኪመጣ አድጐ: አፍርቶ: እሸት ሆኖ ቆየው::
+ገበሬው የተደረገውን ተአምራት ባየ ጊዜ ደነገጠ:: ሊያመልካቸውም ወደደ:: እነርሱ ግን "እኛ የልዑል ባሮች ነን" ብለው በክርስቶስ ማመንን አስተማሩት:: "ልከተላችሁ" ቢላቸው "የለም! ከእሸቱ ይዘህ ወደ ከተማ ግባና ራት አዘጋጅልን:: እኛ እንመጣለን" አሉት::
+እርሱ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሕዛብ ነገሩን ተረዱ:: ተሠብሥበውም "እነዚህ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እሳትም ሰይፍም አይበግራቸውም" ብለው ወደ ከተማ እንዳይገቡ ከበሩ ላይ ራቁቷን የሆነች ዘማ አቆሙ::
+ቅዱስ ታዴዎስ ገና ከርቀት ስላያት ቀና ብሎ #ቅዱስ_ሚካኤልን "እርዳን" አለው:: ሊቀ መላእክትም ድንገት ወርዶ ዘማዋን ሴት በጸጉሯ በዓየር ላይ ሰቀላት:: በከተማዋ ያሉ አሕዛብም ይህንና ሌሎች ተአምራትን አይተው ሁሉም በጌታችን አምነው ተጠመቁ:: ለሐዋርያቱም ሰገዱላቸው::
+አንድ ቀን ግን አንድ ጐረምሳ ባለ ጠጋ ቅዱስ ታዴዎስ "ሀብት ንብረታችሁን መጽውቱ" ሲል ሰምቶት ዘሎ የሐዋርያውን ጉሮሮ አንቆ ከሞት አድርሶት ነበር:: ያን ጊዜ "ጌታየ! ለካ ሀብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ያልክ ለዚህ ነው!" ብሏል:: ባለ ጠጋው "እንዴት ይሆናል?" ቢለው መርፌ አሠርቶ ግመሉን ከነ ባለቤቱ በሰው ሁሉ ፊት 3 ጊዜ አሳልፎታል::
+ያም ማለት ጌታችን እንዳለው "በሰው ዘንድ የማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል::" (ማር. 10:23) በዚህ ምክንያትም ያ ክፉ ባለ ጸጋ ወደ ልቡናው ተመልሶ ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ሥር ወደቀ:: ሐዋርያውም አለው "ሀብትህን ለነዳያን ስጥ:: ይህንንም በትር እንካና እየዞርክ ወንጌለ መንግስትን ስበክ::" ባለ ጸጋውም የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ በክብር ዐርፏል::
+ቅዱሳኑ ታዴዎስና ዼጥሮስ ግን በሃገሪቱ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው: ካህናትን ሹመው: ያቺን በዓየር ላይ የሰቀሏትን ዘማም የተባረከች መበለት አድርገው: በሌሎች አሕጉራት ወንጌልን ለማዳረስ ወጥተዋል::
+ቅዱስ ታዴዎስም እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም በዚህች ቀን ዐርፏል::
=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ ሐዋርያ በረከት ይክፈለን::
=>ሐምሌ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
=>+"+ ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን "ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል!" አላቸው:: ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ:: ጌታ ኢየሱስም ደግሞ መልሶ "ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ #እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው! ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አላቸው:: +"+ (ማር. 10:23-28)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"ነገር ኹሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ! !!
አንድ አንዴ በሕይወታችን ምንም የማይጠቅሙ ነገሮችን ልንመርጥ እንችላለን ።የሚያስፈልገንና የማይጠቅመን ግን መንፈስ ቅዱስ ሲመርጥልን ነው።"
አደጋና ስጋት ፡በሽታና ስቃይ ፡እጦትና ችግር ፡ራብና ጥማት ፡ኅዘንና ትካዜ ፡የሌለው ሕይወት እጅግ ጠቃሜ እንደ ኮነ አድርገን እናስባለን ነገር ግን ይህን የሌለው ሕይወት ኹሉ ጠቃሜ ላይኾን ይችላል ።
እንደ ራሳችን ሓሳብ ሳይኾን እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ ስንጓዝ ግን ነገር ኹሉ ለበጎ ነው ። ነገር ኹሉ ሲባልም በእኛ እይታ በጎ ነው የምንለው ብቻ አይደለም ፡ ክፉ ነው የምንለውም ጭምር እንጂ።እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ ስሆን ማግኘትም ማጣትም ፡ጤንነትም በሽታም ለበጎ ነው።
እግዚአብሔር ለእኛ መልካም የሚያደርግልን በጎ ነው ብለን በምናስበው ነገር ብቻ አይደለም። እጅግም ክፉና አስቸጋሪ መስለው ከሚታዩን ኹኔታዎችም ለእኛ ለልጆቹ እጅግ የሚደንቅና በጎ ነገርን ማድረግ ይችልበታል።
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በልቤ ደስታን ጨመርኽ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።
በሰላም እተኛለኹ አንቀላፋለኹም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻኽን በእምነት አሳድረኸኛልና።
መዝ4:7-8

✝✝††† እንኳን ለዓምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† ✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝✝†††
††† ✝✝ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ✝✝ †††
††† ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " #ዓምደ_ሃይማኖት- የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ (ግብጽ) በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ #አባ_ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: #መንፈስ_ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::
ከዚያም በ412 ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም 24ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ #ቤተ_ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::
በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው #እመቤታችንንየአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት!)
ነገሩን #ቅዱስ_ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም #በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 #ቅዱሳን_ሊቃውንት ተገኙ::
የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር (ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት #ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: #ድንግል_ማርያምም #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::
የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::
††† ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም " #ታኦዶኮስ(የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን:-
¤የአምላክ እናት:
¤ዘላለማዊት ድንግል:
¤ፍጽምት:
¤ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::
እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::
ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ32 ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ444 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::
††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::
††† ሐምሌ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)
2.ቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ (ታላቅ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)
3.አባ ሉቅያስ ኤዺስ ቆዾስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
††† "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና::" †††
(ዕብ. 13:7)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

ለአንድ ሠው የምትሠጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን፣ ፍቅርህንና አትኩሮትህን ነው፡፡ ››
ለአንድ ወዳጅህ ልትሠጠው የምትችለው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን ፣ ፍቅርህንና አትኩሮትህን ከሆነ ለዚህ ሠው ያለህ አመለካከት መልካምና ቅንነት የተሞላው እንደሆነ ማወቅ ይቻላል ፡፡
ምክንያቱም በዚህ ዘመን ጊዜ ወርቅ ነው ፡፡ ለማታውቀው ወይም ጥሩ አመለካከት ለሌለው ሠው ውዱን ጊዜህን አታካፍለውም ፡፡ ፍቅር ወረት በሆነበት ጊዜ ፍቅርህን የምትቸረው ሠው በአንተ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ላለው ሠው ነው ፡፡
አትኩሮትህንም ቢሆን እንደው ለማንም ዝም ብለህ የምትለግሠው አይደለም ፡፡ አትኩሮት አጥተው የተለያዩ ባልና ሚስቶች ቤት ይቁጠራቸው ፡፡ እሷ ለእኔ ግድ የላትም ፡፡ እሱ ለእኔ ግድ የለውም እየተባባሉ ለዘመናት የገነቡትን ጓደኝነታቸውን ፣ ጉርብትናቸውን ወይም ዝምድናቸውን የተዉ እልፍ ሠዎች ናቸው ፡፡
አትኩሮት መስጠት ማለት ለወዳጃችን ወይም ለቤተሠባችን ሃሳባችን ከሃሳቡ አስማምቶ መኖር ማለት ነው ፡፡
ወዳጆች ሆይ በወዳጅነት ስንኖር እነዚህን ሶስት ነገሮች ለወዳጃችን እንሠጠው ዘንድ ግድ ይለናል አልያ የወዳጅነት ልኩ ሚዛን አይደፋም ፡፡
ወዳጅ ላልነው ሠው ወዳጅነቱን ልናስመሠክር የምንችለው ጊዜአችንን ፣ ፍቅራችንን እና አትኩሮታችንን ሳንቆራርጥ ስንሠጠው ነው ፡፡
መልካም ቀን
ለአንድ ወዳጅህ ልትሠጠው የምትችለው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን ፣ ፍቅርህንና አትኩሮትህን ከሆነ ለዚህ ሠው ያለህ አመለካከት መልካምና ቅንነት የተሞላው እንደሆነ ማወቅ ይቻላል ፡፡
ምክንያቱም በዚህ ዘመን ጊዜ ወርቅ ነው ፡፡ ለማታውቀው ወይም ጥሩ አመለካከት ለሌለው ሠው ውዱን ጊዜህን አታካፍለውም ፡፡ ፍቅር ወረት በሆነበት ጊዜ ፍቅርህን የምትቸረው ሠው በአንተ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ላለው ሠው ነው ፡፡
አትኩሮትህንም ቢሆን እንደው ለማንም ዝም ብለህ የምትለግሠው አይደለም ፡፡ አትኩሮት አጥተው የተለያዩ ባልና ሚስቶች ቤት ይቁጠራቸው ፡፡ እሷ ለእኔ ግድ የላትም ፡፡ እሱ ለእኔ ግድ የለውም እየተባባሉ ለዘመናት የገነቡትን ጓደኝነታቸውን ፣ ጉርብትናቸውን ወይም ዝምድናቸውን የተዉ እልፍ ሠዎች ናቸው ፡፡
አትኩሮት መስጠት ማለት ለወዳጃችን ወይም ለቤተሠባችን ሃሳባችን ከሃሳቡ አስማምቶ መኖር ማለት ነው ፡፡
ወዳጆች ሆይ በወዳጅነት ስንኖር እነዚህን ሶስት ነገሮች ለወዳጃችን እንሠጠው ዘንድ ግድ ይለናል አልያ የወዳጅነት ልኩ ሚዛን አይደፋም ፡፡
ወዳጅ ላልነው ሠው ወዳጅነቱን ልናስመሠክር የምንችለው ጊዜአችንን ፣ ፍቅራችንን እና አትኩሮታችንን ሳንቆራርጥ ስንሠጠው ነው ፡፡
መልካም ቀን
በልቤ ደስታን ጨመርኽ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።
በሰላም እተኛለኹ አንቀላፋለኹም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻኽን በእምነት አሳድረኸኛልና።
'የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን!!!'

Forwarded from ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል (kal)
✍ሐመር መጽሔት የግንቦት እና የሰኔ
'ቅዱስ አባት ሆይ ÷እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስምህ ጠብቃቸው፤' [ዮሐ ፲፯÷፲፩]
-እግዚአብሔር አይዘገይም በሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ የተዘጋጀ ድንቅ ት/ት ነው። በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ሁሉን በምክንያት የሚያከናውን መዘግየት ለባሕሪው የማይስማማ ሁሉን ቻይ መሆኑን እንረዳበታለን።
-ከዚህ በተጨማሪ የጥያቄዎ መልስ በሚል ርዕስ የቀረበው ዘመናዊነትና ክርስትና ፤ሴኩላሪዝም ወዘተ የሚያብራራ ነው።
ሌላው በሰኔ ወር መጽሔት ላይ 'የቤተክርስቲያን ተልዕኮ እንዴት እንፈፅም'. በሚል ርዕሰ ጉዳይ የቀረበ ንባብ ነው። በዚህ ክፍል የነገዋ ቤተ ክርስቲያን በሚል እንደ እባብ ልባም እንደ ርግብ የዋህ ትውልድ ያስፈልጋል ይለናል።
እንዲሁም ሌሎች አስተማሪ ጉዳይ የያዘ ነዉ ።መጽሔቷን ለማግኘት(ለማንበብ)
በሰ/ት/ቤታችን መካነ ሕይወት ቤተ መፅሐፍ ክፍል
ዘወትር ከሰኞ-እሁድ ከሐሙስ በቀር ከምሸቱ 12:00-2:00 በመምጣት መጠቀም ይችላሉ።

ቅዱስ ጴጥሮስ ወይም ስምዖን ጴጥሮስ (አራማይስጥ፦ ሸማዮን ከፓ፤ ዕብራይስጥ፦ שמעון בר יונה ፦ ሽምዖን ባር ዮና፤ ግሪክኛ፦ ፔትሮስ፤ 8 ዓክልበ. ግ. - 56 ዓም) የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ እና መጀመርያው የሮሜ ጳጳስ (ፓፓ) ነበሩ።
የተወለደው በ ፩ኛው ክፍለ ዘመን በገሊላ ስም መጀመሪያ ስምኦን በኋላ ጴጥሮስ የአባት ስም ዮሐንስ ወይም ዮና ዓመታዊ በዓላት ሐምሌ ፭ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የሚታወቀው በሊቀ ሐዋርያነቱ፣ የገነትን ቊልፍ ከክርስቶስ በመቀበሉ፣ በሰማዕትነቱ ፣ ተዘቅዝቆ በመሰቀሉ ያረፈበት በ፷፬-፷፰ ዓ.ም.በቯቲካን ሂል፣ ክሌመንታይል ቻፕል፣ ሮም፣ ጣሊያን፣ በሮሜ መንግሥት በራሱ ምርጫ ተዘቅዝቆ በመሰቀል የሚከበረው በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ ሥራው መጀመሪያ ዐሣ አጥማጅ በኋላ ወንጌል ጸሐፊ ሰባኪም
ሳውል በብሉይ የወጣለት ዕብራዊ ስሙ ሲሆን፣ ጳውሎስ በሐዲስ የወጣለት ነው ትርጉሙም ብርሃን ማለት ነው። በተርሴስ (ዛሬ በቱርክ ውስጥ) ከሚቀመጥ ከአንድ ሸማኔ ተወልዶ ካደገ በኋላ በኢየሩሳሌም ኦሪትን ከገማልኤል ተማረ። ስለኦሪትና ስለሙሴ ከፍ ያለ ቅናት፤ በዘመኑ ስለተፈጠረው የክርስትና ሃይማኖት የበዛ ጥላቻ ነበረው። ስለዚህ ክርስቲያኖችን ማባረር፤ ማሰር፤ ማጉላላት ሥራዬ ብሎ ይዞት ነበር።
ስም መጀመሪያ ሳውል በኋላ ጳውሎስ የተወለደው ቦታ ተርሴስ በሮሜ መንግሥት የተወለደበት ዘመን በ፩ኛው ክፍለዘመን ፭ኛው ዓመት የሚታወቀው በመልክቱ፣ ከይሁድነት ወደ ክርስቲያንነት በመቀየሩ ፣በሰይፍ ተሰይፎ በሰማዕትነቱ ያረፈበት ፩ኛው ክፍለ ዘመን ፷፬፣፷፭፣ ፷፯ ዓ.ም.
ሥራው ፀሐፊ፣ ሰባኪ፣ የክርስትና ሃይማኖት ፈላስፋ
የሚከበረው በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ ንግሥ ሐምሌ ፭ ነው።

Wikipedia
አረማይክ
አረማይክ ወይም አራማይስጥ፣ የሶርያ ቋንቋ ወዘተ. ( ܐܪܡܝܐ /አራማያ/) ከሴማዊ ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን በመካከለኛ ምሥራቅ ከጥንት ጀምሮ ታውቋል።
ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል pinned «✍ሐመር መጽሔት የግንቦት እና የሰኔ 'ቅዱስ አባት ሆይ ÷እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስምህ ጠብቃቸው፤' [ዮሐ ፲፯÷፲፩] -እግዚአብሔር አይዘገይም በሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ የተዘጋጀ ድንቅ ት/ት ነው። በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ሁሉን በምክንያት የሚያከናውን መዘግየት ለባሕሪው የማይስማማ ሁሉን ቻይ መሆኑን እንረዳበታለን። -ከዚህ በተጨማሪ የጥያቄዎ መልስ…»
ቅዱሳን አባቶቻችን "ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው" ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፎአል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡
(አረጋዊ ታዴዎስ)
(አረጋዊ ታዴዎስ)
=>+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን
አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+
=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ
በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና
በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ
ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::
+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!)
ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው
ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት
የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ"
ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::
+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+
=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::
+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::
+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )
+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው
#አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው
አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::
+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA )
+"+
=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር
ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ
#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና
ይማጸናት ገባ::
+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው::
"ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው
ተሠወረችው::
+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ
ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው:
መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና
ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ
ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ
መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)
+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/
ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2. #በላዔ_መጻሕፍት
3. #ዓምደ_ሃይማኖት
4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ
5. #ጠቢብ_ወማዕምር
+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን
ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን
ነው::
=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:-
'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ'
ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::
እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.
6:13)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር:
የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:14)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

†††✝ እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝ቅዱስ ናትናኤል✝ †††
††† በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው::
ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር::
ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::
ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው::
ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል::
ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል::
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ: ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::
የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በመቶ ሃምሳ ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::
†††✝ አባ ብስንዳ ✝†††
††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ አባ ብስንዳ ይታሠባል::
አባ ብስንዳ በዘመነ ጻድቃን ምድረ ግብጽ ውስጥ ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱን ከገድሉ ጽናት የተነሳ መላእክት በእጅጉ ይወዱት ነበር:: "እኔ ልሸከምህ - እኔ ልሸከምህ" እያሉ ይሻሙበት: በተራ በተራም ተሸክመውት ይውሉ ነበር:: እርሱም ለበርካታ ዓመታት ውኃ የሞላበት ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ይጸልይ ነበር::
እንደ እሳት በሚባላው በረዶ ውስጥ ገብቶ መጸለዩ የፈጣሪውን ሕማማት ለመሳተፍ እና ለኃጥአን ምሕረትን ይለምን ዘንድ ነው:: ሁሌም በዘጠኝ ሰዓት መላእክት ተሠብስበው ይመጡና በብርሃን ሠረገላ ይሸከሙታል:: ከመሬትም ዘጠኝ ክንድ ከፍ ያደርጉት ነበር::
ከብዙ ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሒዷል::
††† እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከሐዋርያው እና ከጻድቁ አባ ብስንዳ በረከትም አይለየን::
††† ሐምሌ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ታላቁ አባ ብስንዳ ጻድቅ
3.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
††† "ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእሥራኤል ንጉሥ ነህ' አለው::" †††
(ዮሐ. ፩፥፵፰-፶፩)

†††✝ እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።✝ †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
†††✝ ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ወሰማዕት ✝†††
††† ቅዱስ ዮሐንስ በቀደመው ዘመን ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ መርባስ ትባላለች:: ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚወዱ: ምጽዋትን የሚያዘወትሩና በበጐው ጐዳና የሚኖሩ ነበሩ:: ነገር ግን ልጅ በማጣታቸው ምክንያት ፈጽመው ያዝኑ: ይጸልዩም ነበር:: በተለይ ለመጥምቁ ዮሐንስ ልዩ ፍቅር ስለ ነበራቸው ዝክሩን ይዘክሩ: በስሙም ይማጸኑ ነበርና መጥምቁ ሰማቸው::
ወደ ፈጣሪውም ልመናቸውን በማድረሱ መልክ ከደም ግባት የተባበረለት ደግ ልጅን ወለዱ:: እጅጉን ደስ ስላላቸው በአካባቢያቸው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስን ቤተ ክርስቲያን በገንዘባቸው አነጹ:: ሕፃኑንም በመጥምቁ ስም "ዮሐንስ" አሉት:: ጻድቁ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር አድሮበታልና ሕይወቱ ግሩም ነበር::
በሕፃን ገላው ይጾምና ይሰግድ: በልጅ አንደበቱም ተግቶ ይጸልይ ነበር:: ወላጆቹ ወደ እረኝነት ባሰማሩት ጊዜም መፍቀሬ ነዳያን ነውና ቁርስና ምሳውን ለነዳያን እያበላ እርሱ ጾሙን ይውል ነበር:: አባቱ የሚያደርገውን ሰምቶ ለማረጋገጥ ተከተለው:: እንዳሉትም እናቱ ጋግራ የሰጠችውን ትኩስ ዳቦ ለነዳያን ሲሰጥ አየው::
ሊቆጣው ፈልጐ "ዳቦህ የታለ?" ቢለው ሕፃኑ ቅዱስ ዮሐንስ "በአገልግሉ ውስጥ አለ" ሲል መለሰለት:: አባት ለመቆጣት እንዲመቸው አገልግሉን ሲከፍተው ግን ያየውን ማመን አልቻለም:: በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ዳቦዎቹ ትኩስ እንደሆኑ ተገኙ::
አባትም ወደ ቤቱ ወስዶ "ልጄ! አንተ የእግዚአብሔር ሰው ስለሆንክ እኛን ሳይሆን እርሱን አገልግል" ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ላከው::
በዚህ ምክንያት ቅዱስ ዮሐንስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ ትምህርት ገባ:: በስድስት ዓመታትም ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አሥራ ስምንት ዓመት ሲሞላው ደግነቱን ወደዋልና በግድ ቅስና ሾሙት:: እርሱ ግን ለተወሰነ ጊዜ አስተምሮ ዘመዱ የሆነውንና ዲያቆኑን ቅዱስ ስምዖንን አስከትሎ መነነ::
በዚያም በፍጹም ገድል ሲኖር ብዙ ተአምራትን ሰርቷል::
¤አንድ ወታደር (አንድ ዐይና ነው) ሊባረክ ብሎ ሲጐነበስ የታወረች ዐይኑን የቅዱስ ዮሐንስ ልብስ ቢነካት በርታለታለች:: ከዚህ አልፎም ቅዱሱ ብዙ ድውያንን ፈውሷል: ለምጻሞችን አድኗል: አጋንንትን ከማደሪያቸው (ከሰው ላይ) አሳድዷል::
ታዲያ አንድ ቀን የወቅቱ የአንጾኪያ ንጉሥ የቅዱስ ዮሐንስን ዜና ይሰማል:: የእርሱ ልጅ ደግሞ አጋንንት አድረውባት ስቃይ ላይ ነበረችና የሚያድናት አልተገኘም:: ንጉሡ "ጻድቁን አምጡልኝ" ብሎ መልዕክተኛ ሲልክ ቅዱስ ዮሐንስ ደመና ጠቅሶ: በዚያውም ላይ ተጭኖ ከተፍ አለ:: ንጉሡ አይቶት ደነገጠ:: አባ ዮሐንስ ግን "እኔ ኃጢአተኛ የሆንኩ ሰው ለምን እንዲህ ትፈልገኛለህ?" ብሎ ታማሚዋን አስጠራ::
ጻድቁ እጆቹን አንስቶ ወደ ፈጣሪው ሲጸልይ በወጣቷ ላይ ያደረው ሰይጣን ሕዝቡ እያዩት ከሆዷ በዘንዶ አምሳል ወጥቶ ሔደ:: ንጉሡ ስለተደረገለት ውለታ ለቅዱስ ዮሐንስ ወርቅና ብር ብዙ ሽልማትም አቀረበ:: አባቶቻችን እንዲህ ዓይነት ነገር አይወዱምና ቅዱሱ "እንቢ አልወስድም" አለ::
ቅዱስ ዮሐንስ "ልሒድ" ብሎ ሲነሳ ንጉሡ "አባቴ ወድጄሃለሁና አትሒድ" ብሎ የልብሱን ዘርፍ (ጫፍ) ያዘው:: በቅጽበት ግን ደመና መጥታ ነጥቃ ወሰደችው:: የቀሚሱ ቁራጭም በንጉሡ እጅ ላይ ቀረች:: እርሱም ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ ያችን የተባረከች ጨርቅ በክብር አኑሯታል::
ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ) ግን ከብዙ የተጋድሎ ዓመታት በኋላ ሌላ ክብር መጣላቸው:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" የሚል ንጉሥ በመነሳቱም ሒደው በጌታችን ስም መሰከሩ:: በገድል በተቀጠቀጠ ገላቸው ላይ ግርፋትን: እሳትን ታገሱ:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተቆርጠው በሰማዕትነት ዐርፈዋል::
††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታችቸውም ያድለን::
††† ሐምሌ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ)
3.አባ ኢሳይያስ ዘገዳመ አስቄጥስ
4.አባ ገብርኤል ሊቀ ጳጳሳት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
††† "ሒዳችሁም መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ:: ድውዮችን ፈውሱ: ሙታንን አንሱ: ለምጻሞችን አንጹ: አጋንንትን አውጡ:: በከንቱ ተቀብላችሁ በከንቱ ስጡ:: ወርቅ: ወይም ብር: ወይም ናስ በመቀነታችሁ: ወይም ለመንገድ ከረጢት: ወይም ሁለት እጀ ጠባብ: ወይም ጫማ: ወይም በትር: አታግኙ:: ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና::" †††
(ማቴ. ፲፥፯)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://t.me/kaletsidkzm

✞✞✞✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ✝️ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ✝️ሐምሌ ፲፪✝️ ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ሚካኤል ሊቀ መላእክት"
የተአምር በዓልና ለሰማዕቱ "አባ ሖር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ተአምረ ቅዱስ ሚካኤል "*+
=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን በዚህች ዕለት የመላእክት
ሁሉ አለቃቸው: የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ
መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም
በሆነ ተአምር ከከተማው #ኢየሩሳሌም ጋር ታድጐታል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ከመድኃኒታችን #ክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት በፊት
#ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር::
ደጋጉ #ዳዊትና #ሰሎሞን ካረፉ በሁዋላ የሕዝቅያስን
ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ
አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ
ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም
ነበር::
+ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት
የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት::
ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም
በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ
ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ
እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::
+"እገብርልሃለሁ:: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ሃገሬን
ግን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል:: ሕዝቤንም
አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም
ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት::
+ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን
ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ : ቅዱስ
ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ
ማነው? ሕዝቡንም #እግዚአብሔር ያድናል ብለህ
አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ
የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::
+መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ #ቅዱስ_ኢሳይያስ ልኮ እርሱ
ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን
ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ
አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን
መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ
አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ #ዳዊት
ከተማዋን አድናታለሁ::"
+በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል
ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር
ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው
ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ::
በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ
ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል::
+በድንጋጤ ወደ #ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ
ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው
ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ
ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ
የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13, 19:1)
+*" ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት "*+
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን #አባ_ሖር ሰማዕቱ ይታሠባል::
+ቅዱሱ:-
¤ስርያቆስ በምትባል የግብጽ አውራጃ ተወልዶ ያደገ:
¤ገና በልጅነቱ መንኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ:
¤ዘመነ ሰማዕታት በመጣ ጊዜም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመነ:
¤ከመኮንኑም ብዙ ስቃይ የደረሰበት:
¤ብዙ ተአምራትን በመስራቱ ያሰቃየው የነበረውን መኮንን
ወደ ክርስትና መልሶ ለሰማዕትነት ያበቃ አባት ነው::
+እርሱም የሰማዕትነትን ክብር በእጅጉ ሽቷታልና ወደ ሌላ
ሃገር ሒዶ በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል
ተቀዳጅቷል:: በሐዋርያዊ አገልግሎቱ ያሳመናቸው 127
ወንዶችና 20 ሴቶችም አብረውት ተሰይፈዋል::
=>እግዚአብሔር በሊቀ መላእክት ክንፍ ሃገራችንን
ከአሕዛብ ስውር ጦር ይጠብቅልን:: ከሰማዕቱም በረከት
ያሳትፈን::
=>ሐምሌ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሕዝቅያስ ንጉሥ
2.ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
3.ቅዱስ አባ ሖር ሰማዕት
4."147" ሰማዕታት (የአባ ሖር ማሕበር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
=>+"+ እግዚአብሔር ይላል:- ስለ እኔም ስለ ባሪያየም
#ስለ_ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ::
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ::
ከአሦራውያንም ሠፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ::
ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ:: +"+
(1ነገ. 19:34)