የተባበሩት መንግስታት እና "Amplifier" በመባል የሚጠራ የሥነጥበብ ቡድን በመጋቢት ወር ላይ ለአርቲስቶች በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሥነ ጥበብን ስራዎችን እንዲያቀርቡ ባቀረበው የገለልተኝነት ዘመቻዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስራወች ከተለያዩ አርቲስቶች የተሰበሰቡ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ቡድኖቹ እነዚህን ሥራዎች በመምረጥ ለሕዝብ እያሳዩ መሆናቸውን "goats and soda" የሚባል የዜና ድረገፅ አስታወቀ፡፡
በአለም ዙርያ በአሁኑ ጊዜ በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው ወረርሽኝ ምክንያት በየሀገሩ ያሉ የተለያዩ የጤና ሰራተኞች እየከፈሉ ላሉት መስዋዕትነት እውቅና የሚሰጡ እና ምስጋና የተሞሉ አበረታች እና ሕብረተሰብን እያዝናኑ እውቀት የሚያስጨብጡ ጠቃሚ መልክት አዘል የጥበብ ስራዎች በዓለም ዙርያ በየጎዳናው መስተዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል ባለፈዉ ሳምንትም በ"UK" ጎዳናዎች ላይ ለጤና ቢሮውና ሰራተኞች የምስጋና መልክቶችን ያዘሉ የስነጥበብ ስራዎች መታየታቸውን the guardian መፅሄት ዘግቦአል።
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በቻናላችን ላይ ለ1 ወር የተጀመረውን የስነ-ጥበብ ስልጠና የምትወስዱ ሁሉ የዛሬው የትምሕርት ክፍለጊዜ 9:00 ለይ የሚጀምር በመሆኑ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁን እናሳስባለን።
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በፕሮግራማችን መሰረት ለስነ-ጥበብ ስራ የሚረዱ ቅድመ ልምምዶች ዛሬ ይዘንላችሁ መተናል። በቪድዮው ላይ ያለውን መመሪያ በመመልከት ቢቻል በትልልቅ ወረቀቶች ላይ ለምሳሌ እንደ ጋዜጣ የመሣሠሉ የወረቀት አይነቶችን በ ምቹ ቦርድ ወይም ግድ ግዳ ላይ በመለጠፍ እጃችሁን ማፍታታት ጠቃሚ የስነጥበብ ጅማሬ ነው።
ማሳሰቢያ
የእርሳስ አያያዛችሁ ልክ በምስሉ ላእንደምትመለከቱት መሆኑ አስፈላጊ በመሆኑ ባይመቻችሁም ራሳችሁን ለማስለመድ ልትሞክሩ ይገባል።
ማሳሰቢያ
የእርሳስ አያያዛችሁ ልክ በምስሉ ላእንደምትመለከቱት መሆኑ አስፈላጊ በመሆኑ ባይመቻችሁም ራሳችሁን ለማስለመድ ልትሞክሩ ይገባል።
ውድ የጆያብ ስቱድዮ የስነጥበብ ተማሪዎች የፊታችን አርብ ወደ ዋናው ትምሕርታችን የምንገባ በመሆኑ ዛሬ በተማራችሁት መሠረት የሚገባውን የዕጅ ማፍታቻ ልምምድ እያረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባችሁዋለን።
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮቻችን ዛሬ ከታላላቅ ሰዐሊያን መካከል ብዙዎቻቹ የምታውቁትን ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ
ይዘንላቹ መተናል
ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ
የህዳሴው ዘመን ሠአሊ (The Renaissance artist) በመባል የሚጠራ አለም በብዛት በሠዓሊነቱ የሚያውቀው ድንቅ ሠዓሊ ቢሆንም ከዛ ባለፈ ድንቅ የቅርፃቅርፅ ፣ የኪነ ሕንፃ ጥበብ ፣ የፈጠራ ባለሙያ ፣ የውትድርና ስትራቴጂ ቀራጭ እና ረቂቅ የሆኑ ሳይንሳዊ እውነታዎችን የሚመረምር ከፍተኛ የማወቅ ጉጉት ያለው ታላቅ ችሎታ ያለው ሰው ነበር። ይህ ድንቅ አርቲስት የተወለደው-ኤፕሪል 15 ቀን 1452 አንችኖኖ በምትባል ቦታ ሲሆን ትልቅ ዕውቅና ካላቸው የሥነ-ጥበብ ስራዎቹ መካከል-የመጨረሻው እራት ( the last supper ) እና ሞና ሊሳ ጥቂቶቹ ናቸው።