ጀነት እንገናኝ
893 subscribers
487 photos
51 videos
26 files
351 links
ውድ የጀነት ተሳፋሪዎች : አጭር የጀነት መግቢያ መንገዶችን ይዘን አብረን ወደ ጀነት እና በቃ ጀነት እንገናኝ ። if jannah is Ur dream hold tight 2 Ur deen. ለጀነት ሰውን እንጋብዝ #share

ለማንኛውም አስተያየት እና ሀሳብ ካላቹ
በውስጥ ጣፍ ጣፍ ያድርጉልን


@Romislamic_Bot
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እየሩሳሌም 3ኛው የሙስሊሞች ቅዱስ ስፍራ❤️

አንብበው ሲጨርሱ ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያዳርሱ!
እየሩሳሌም በሙስሊሞች ዘንድ ከመካ እና ከመዲና ቀጥላ ሶስተኛዋ ቅድስት
ስፍራ ናት፡፡ ሙስሊሞች ለእየሩሳሌም የሚሰጡት ትልቅ ቦታን ባለመረዳት
ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞች የእየሩሳሌም ጠላት እንደሆኑ አድርገው
ያስባሉ፡፡ እውነታ ግን እየሩሳሌም ለሙስሊሞች የተከበረውን መስጂደል አቅሳን
ይዛ የምትገኝ የተከበረች ስፍራ ናት፡፡
ሙስሊሞች ወደ መካ እና መዲና እንደሚጓዙት ሁሉ ወደ እየሩሳሌም በመጓዝም
መስጂደል አቅሳን ማየትን ይሻሉ፡፡በወራሪዋ እስራኤል አማካኝነት ይህ የተከበረ
ቦታ በህፃናት፣በአዛውንቶች እና በሴቶች ደም ሁሌም እንዲጨቀኝ ቢደረግም አንድ ቀን ከወራሪዋ እስራኤል ነፃ የሚወጣበት ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡ አለም ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ለእየሩሳሌም የሚሰጡትን ቦታ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ጠንቅቀው ሊረዱት ይገባል፡፡ ስለ ፍልስጤማውያን ስንጮህ
በግፍ መሬታቸውን በወራሪዋ እስራኤል ስለተነጠቁ ብቻ ሳይሆን ወይም
ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ወይንም አረብ ስለሆኑ ሳይሆን በወራሪዋ
እስራኤል በጉልበት የተያዘብን በእየሩሳሌም ምድር የሚገኘው መስጂደል አቅሳም የፍልስጤማውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ሙስሊም ቅዱስ ስፍራ በመሆኑ ነው፡፡
እያንዳንዱ ሙስሊም ስለ እየሩሳሌም ፤ስለ መስጂደል አቅሳ ዘወትር ፀሎት
ያደርጋል፡፡ ከግፈኞቹ ፂዬናውያን ነፃ ወጥታ ሁሉም ወደ እየሩሳሌም ተጉዞ
በመስጂደል አቅሳ ሰላቱን ሊሰግድ ይናፍቃል፡፡
የሙስሊሞችን እና የእየሩሳሌምን ጥብቅ ትስስር ለመረዳት የተወሰኑ ነጥቦችን በመጥቀስ እንመልከት
👍1. መስጂድ አል-አቅሷ የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ አምላካችን አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷን እና ዙሪያውን በሱ የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ መሆኑን በቁርአን ላይ ገልፆልናል፡፡
ﺳُﺒْﺤَﺎﻥَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺃَﺳْﺮَﻯٰ ﺑِﻌَﺒْﺪِﻩِ ﻟَﻴْﻠًﺎ ﻣِّﻦَ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪِ ﺍﻟْﺤَﺮَﺍﻡِ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪِ ﺍﻟْﺄَﻗْﺼَﻰ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺑَﺎﺭَﻛْﻨَﺎ
ﺣَﻮْﻟَﻪُ ﻟِﻨُﺮِﻳَﻪُ ﻣِﻦْ ﺁﻳَﺎﺗِﻨَﺎ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ ﺍﻟﺴَّﻤِﻴﻊُ ﺍﻟْﺒَﺼِﻴﺮُ ﴿١
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን
ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡((አል- ኢስራእ ፡1)
👍2. ሌላው አል-አቅሷን ከሙስሊሞች የሚያስተሳስረው የኢስራእና ሚዕራጅ
ምድር መሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰማዩ ዓለም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ
ከመካው መስጂድ ወደ እየሩሳሌም መስጂድ አልአቅሷ ተጉዘዋል፡፡ ከዚያም
በመነሳት ነበር ወደ ሰማዩ ዓለም የተጓዙት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ወደ በይት
አልመቅዲስ መጓዛቸው የቦታውን ታላቅነትና ቅድስና ያመለክታል፡፡
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ወደ እየሩሳሌም ወደሚገኘው አል-አቅሷ መስጂድ በተጓዙበትም
ወቅት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ከአላህ የተላኩትን ታላላቅ ነቢያቶችን መሪ ሆነው
አሰግደዋል፡፡ከነዚህም መካከል ከነብዩላህ አደም ጀምሮ እስከ እየሱስ ክርስቶስ
(አ.ሰ) ያሉት ነብያት ይገኙበታል፡፡
👍3. የእየሩሳሌም ምድር በርካታ ታላላቅ የአላህ ነብያት የተላኩበት ምድርም
ነው፡፡ አባታችን ኢብራሂምን (አብረሃም) (ዐ.ሰ) ጨምሮ ዳውድ
(ዳዊት)፣ሱለይማን(ሰለሞን)፣ሙሳ(ሙሴ)፣ ኢሳ( እየሱስ ክርስቶስ ) (አ.ሰ) እና
ሌሎችም ህዝቦች አላህን በብቸኝነት አንድ አድርገው እንዲገዙ ጥሪ
እንዲያደርጉ ከአላህ የተላኩበት ምድር ነው፡፡
👍4 . እንደ አብዛኞቹ ዑለማኦች(የእስልምና ሊቃውንት) ስምምነት በእየሩሳሌም
የሚገኘውን አል-አቅሷ መስጂድን ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት አባታችን አደም
(ዐ.ሰ.) ሲሆኑ ኋላ ላይ ግን ነብዩላህ ኢብራሂም (አ.ሠ) ካዕባን በድጋሚ
እንደገነቡት ይህንንም መስጂድ (የፀሎት ቦታ) አስፍተውታል፡፡ በመቀጠልም
የነብዩላህ ዳውድ(ዳዊት) ልጅ የሆኑት ነቢዩ ሱለይማን(ሰለሞን) ሙሉ
ግንባታውን በማደስ እንዳጠናከሩት እና እንደገነቡት በታሪክ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
በምድር ላይ አላህን ለማምለክ ታስቦ በነብዩላህ ኢብራሂም) (አ.ሰ)የተገነባው
የመጀመሪያው መስጂድ (የፀሎት ስፍራ) መካ የሚገኘው አልሐራም (ከዕባ)
መሆኑ ይታወቃል፡፡ አል-አቅሷ ደግሞ በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው መስጂድ
(የፀሎት ስፍራ) ሲሆን በሱ እና በከዕባ መካከል የአርባ አመት ዕድሜ ብቻ ነው
ያለው፡፡ ነብዩላህ ኢብራሂም ከልጃቸው እስማኤል ጋር በመካ ካዕባን ከገነቡ
ቡኋላ ከ 40 አመታት ቡኋላ በእየሩሳሌምም ይህን መስጂደል አቅሳን (የፀሎት
ስፍራ) አስፍተውታል፡፡ ከነብዩላህ ኢብራሂም ቀጥሎ ልጃቸው ይስሓቅ ቀጥሎም
የልጅ ልጃቸው ያቆብ (ዐ.ሰ) ወደ ግብፅ እስከሄዱበት ጊዜ ድረስ አላህን
በብቸኝነት የሚያመልኩበትቦታ ሆኖ ቆይቷል፡፡
👍5. እየሩሳሌም የሚገኘው አል-አቅሷ የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ(የሰላት
አቅጣጫ) ነው፡፡ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለአለም ህዝብ በነብይነት ሲላኩ
የሙስሊሞች ቂብላ/የሶላት መቀጣጫ/ ወደ ከዕባ/መካ/ እንዲሆን ከመደረጉ
በፊት ለአሥራ ስድስት ወይም ለአሥራ ሰባት ወራት ወደእየሩሳሌም ወደ
መስጂደል አቅሳ ዞረው ሰግደዋል፡፡ ካዕባ የሰላት አቅጣጫ ከመደረጉ በፊት
ሙስሊሞች ወደ እየሩሳሌም በመዞር ነበር ሰላታቸውን የሚሰግዱት፡፡ ዛሬ ላይ
ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞች ወደ መካ ካዕባ ዞራችሁ የምትሰግዱት
ለጥቁሩ ድንጋይ ነው ብለው ባለማወቅ ውንጀላ ሲያቀርቡ ሙስሊሞች
በመጀመሪያ ፊታቸውን ወደ እየሩሳሌም በማዞር ይሰግዱ እንደነበር ቢያውቁ ወደ
አንድ አቅጣጫ መዞር የምንሰግድለት አምላክ አንድ ቦታ በመገኘቱ ሳይሆን
የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን ይረዱ ነበር፡፡
6. ጓዝ ተጭኖና ስንቅ ተቋጥሮ ለጉብኝትም ሆነ ለሶላት ከሚኬድባቸው ሶስት
መስጂዶች ውስጥ እየሩሳሌም የሚገኘው አል-አቅሷ መስጂድ አንዱ ነው፡፡
በዚህ በእየሩሳሌም በሚገኘው በአልአቅሷ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት በሌላው
መስጂድ ውስጥ ከሚሰገደው በደረጃ በአምስት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ በአል-
አቅሷ መስጂድ ውስጥ የሚሰገደውን ሶላት ሊበልጥ የሚችለው በመካ
(መስጂድ አልሐራም) እና በመዲና የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ ውስጥ
የሚሰገደው ሶላት ብቻ ነው፡፡ለዚህም ነው ሁሉም ሙስሊም ከመሞቱ በፊት
ከመካ እና ከመዲና መስጂዶች ቀጥሎ ወደ እየሩሳሌም ተጉዞ በመስጂደል
አቅሳ ለመስገድ የሚመኘው፡፡
👍7. በርካታ የነብዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች እና ትላልቅ ደጋግ ሰዎች
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እየሩሳሌም ስለሚገኘው ስለ አል-አቅሷ ደረጃና
ቅድስና ያስተማሩትን በመከተል ወደዚያ ሄደዋል፡፡ ጎብኝተውታል፡፡ ሰግደውበታል፡፡
አል-አቅሷ በታሪክ በተለያዩ ገዥዎች ሥር በቅብብሎሽ ከቆየ በኋላ
በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር የሆነው በኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ.ዐ.)
ዘመን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ ሶሓቦች በበይት አልመቅዲስ በመገኘት
ተምረዋል፣ አስተምረዋል፡፡ እዚያው ቆይተው ከሞቱት ታላላቅ ሶሓቦች መካከል
ዑባዳ ኢብኑ አስሷሚት እና ሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረ.ዐ.) ይገኙበታል፡፡
የተቀበሩትም ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ በሚገኘው ባብ አር-ረሕመህ
በሚሰኘው ቦታ ላይ ነው፡
፡ አልአቅሷን ከጎበኙ ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ፣ አቡ
ዑበይዳ፣ የምእመናን እናት ሶፍያ ፣ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር፣
ኻሊድ ኢብኑ አልወሊድ፣ አቡ ዘር፣ አቡ ደርዳእ፣ ሰልማን አልፋሪሲይ፣ ዐምር
ኢብኑ አልዓስ፣ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ፣ አቢ ሁረይራ፣ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር እና
ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
. በርካታ ትላልቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንትም ለትምህርትና ለኑሮ ወደዚያው
ተጉዘዋል፡፡ ታዋቂው ሙፈሲር ሙቃቲል ቢን ሱለይማን፣ ኢማም አልአውዛዒ፣
ኢማም ሱፍያን አስሠውሪይ፣ ኢማም ለይሥ ኢብኑ ሰዕድ፣ ሻፊዒይና ሌሎችም
ይገኙበታል፡፡
ይህና የመሳሰለው ጉዳይ አለም ላይ ያለው ሙስሊም ማህበረሰብን
ከእየሩሳሌም ጋር ያስተሳስረዋል፡፡ያገናኘዋል፡ የፍልስጤም ምድርም ሆነ
በአጠቃለይ ሻም የሚባለው ሀገር የበርካታ የአላህ ነቢያት መፍለቂያ ነው፡፡ አል-
አቅሷ ደግሞ ሻም የሚባለው ምድር ልብ ነው፡፡ በግፈኛ ፂዬናውያን በጉልበት
የተወሰደው ይህ ቅዱስ ስፍራ ዳግም ወደ ቀድሞ የሙስሊሞች ይዞታነት በአላህ
ፈቃድ መመለሷ አይቀርም፡፡
በ 1948 የፍልስጤማውያንን መሬተ በመቀማት በፂዬናውያን የተመሰረተችው
እስራኤልም ህዝቧ በአላህ እና በነብያት አንደበት የተረገሙ ህዝቦች ናቸው፡፡
ከአላህ የተላኩ ነብያቶችን በግፍ ሲገድሉ የኖሩ፣ ኢሳን /እየሱስ ክርስቶስትን
(ዐ.ሰ) ለመግደል እና ለመስቀል ያሴሩ፣መርየምን በዝሙት የወነጀሉ፣የአላህ
እጆች የታሰረች ናት ያሉ፣ ኡዘይር (እዝራን) የአላህ ልጅ ነው ያሉ፣ ከአላህ
የተወረደውን ዘቡር(መዝሙረ ዳዊትን) እና ተውራትን(ኦሪትን) በመበረዝ የአላህን
ቃል ያዛቡ አመፀኛ ህዝቦች ናቸው፡፡ ይህ ከቀድሞ ታሪካቸው የቀጠለው
አረመኔያዊ ተግባራቸው ዛሬም ድረስ የፍልስጤማውያንን ህፃናት፣ሴቶች እና
አዛውንቶች ዘወትር ደማቸውን እያፈሰሱ እና በእሳት እያነደዱ ህይወታቸውን
እየገፉ ይገኛሉ፡፡
የነብያት ጠላት የነበሩት እነዚህ የአይሁድ ህዝቦች ፂዬናውያን በቅርቡም
በሙስሊሞች ሶስተኛ ቅዱስ ስፍራ በሆነችው እየሩሳሌም የሰላት ጥሪ
ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዳያደርጉ ህገ ደንብ አውጥተዋል፡፡ በተለያዩ
ጊዜያቶችም ወደ ተከበረው መስጂድ ለሚገቡ ሙስሊሞች የእድሜ ገደብ
በማበጀት ለወጣቱ ሙስሊም እገዳ ሲጥሉ ቆይተዋል፡፡ዘወትር አረቡ አለም ብቻ
ሳይሆን መላው ሙስሊም ማህበረሰብ የኢትዬጲያን ሙስሊሞች ጨምሮ
በፂዬናዊያን የተመሰረችውን እስራኤልን የሚቃወመው ቅዱስ ስፍራችንን
በጉልበት በመውረሯ ፣ የሙስሊሞችን ቅዱስ ስፍራ የፍልስጤማውያንን ደም
በማፍሰስ እያረከሰች በመሆኗ እና ጨካኝ እና ጨፍጫፎ በመሆኗ ነው፡፡
ኢትዬጲያ ውስጥ ሆናችሁ ስለፍልስጤም እና እስራኤል ምን ያገባቹሃል ለሚለው
ወቀሳ እየሩሳሌም ለሙስሊሞች ሶስተኛ ቅዱስ ስፍራ በመሆኗ በውስጧ ያለውን
መስጂደል አቅሳ ከእምነታችን ጋር ትልቅ ቁርኝት ያለው በመሆኑ የእየሩሳሌም
ጉዳይ የፍልስጤማውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አለም ሙስሊም ጉዳይ በመሆኑ
በቀጥታ ስለሚመለከተን መሆኑን ሁሉም ሊረዳልን ይገባል፡፡ በኢስላም ቅድስት
ከተማ ለሆኑት ለመካ እና ለመዲና ሙስሊሞች እንደሚቆረቆሩ ሁሉ ሶስተኛ
ቅዱስ ለሆነችው ለእየሩሳሌም ለመስጂደል አቅሷም ሁሉም ሙስሊም
እንደሚቆረቆር ሊታወቅ ይገባል፡፡ የእየሩሳሌም የመስጂደል አቅሷ በፂዬናውያን
ወረራ ስር ሆኖ ጥቃት ሲደርስበት የሚያመን፣የሚያስቆጣን እና የሚያስቆጨን
ስፍራው በኢስላም የተቀደሰ በመሆኑ እና ከሃይማኖታችን ጋር ትልቅ ቁርኝት
ያለው ስለሆነ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡
መስጂደል አቅሳን ከተረገሙት ፂዬናውያን እጅ አላህ ነፃ ያውጣልን!!
ከመሞታችን በፊትም ወደ እየሩሳሌም ተጉዘን በመስጂደል አቅሳ ለመስገድ
ሁላችንንም አላህ ያብቃን!!
አሚን !!

@jenet8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ⓵①⑨②]👌


#ቁርኣን
Night Reminder Read the supplications according to your country timings 💜

🔖 Before sleeping 🔖


🎈Intend to wake up for Fajr.

🎊 Recite Surah Mulk

🙏Cup your palms together, blow gently into them and then recite
💕Surah Ikhaas
💕Surah falaq
💕Surah naas
Then pass your hands over as much of your body as you can reach, beginning with the head and the face, then the entire front of your body. Do this three times

🎈Recite Ayatalkursi
(Those who recites ayatalkursi before sleeping he will safe from the whispers of shaytan till the morning)

📓Recite Last two verses of Surah Baqarah

(Those who recite 2 verses of surah baqra it's enough for him)

*"آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْ رُسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ ۞ لَا يُكَلِّفُ اللهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِنْ نَسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ*
----------------------------

بِاسْمِكَ رَبِّي وَضَعْتُ جَنْبِي، وَبِكَ أَرْفَعُهُ، فَإِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا، بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِينَ (1)

----------------------------
📌 اللَّهُمَّ إِنَّكَ خَلَقْتَ نَفْسِي وَأَنْتَ تَوَفَّاهَا، لَكَ مَمَاتُهَا وَمَحْيَاهَا، إِنْ أَحْيَيْتَهَا فَاحْفَظْهَا، وَإِنْ أَمَتَّهَا فَاغْفِرْ لَهَا. اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَافِيَةَ( 1)

----------------------------
📌 اللَّهُمَّ قِنِي عَذَابَكَ يَوْمَ تَبْعَثُ عِبَادَكَ   ( 3 )
"O Allah, protect me from Your punishment on the day Your servants are resurrected. [three times]"
----------------------------

📌 سُبْحَانَ اللَّهِ (33)
How Perfect Allah is
----------------------------
📌  الْحَمْدُ لِلَّهِ (33)
All praise is for Allah

----------------------------
📌   اللَّهُ أَكْبَرُ (34)
Allah is the greatest. [thirty-four times]"

----------------------------
📌 اللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ، رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ، فَالِقَ الْحَبِّ وَالنَّوَى، وَمُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَالْإِنجِيلِ، وَالْفُرْقَانِ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أّنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتهِ. اللَّهُمَّ أَنْتَ الأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الْآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الْبَاطِنُ فَلَيْسَ دُونَكَ شَيْءٌ، اقْضِ عَنَّا الدَّيْنَ وَأَغْنِنَا مِنَ الْفَقْرِ (1)

----------------------------

📌 الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَطْعَمَنَا وَسَقَانَا، وَكَفَانَا، وَآوَانَا، فَكَمْ مِمَّنْ لاَ كَافِيَ لَهُ وَلاَ مُؤْوِيَ(1)

----------------------------
📌 اللَّهُمَّ عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضِ، رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيكَهُ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي، وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ وَشِرْكِهِ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِي سُوءاً، أَوْ أَجُرَّهُ إِلَى مُسْلِمٍ(1)

----------------------------

🍬Sleep in a state of wudu
 
🛏 Clean the bed

💌 Sleep on right side keeping right  hand below the cheek.

🎀Sleep with a clean heart.

🔮 Then recite dua

*بِاسْمِكَ اللَّهُمَّ أَمُوتُ وَأَحْيَا* ( 1)


Bismikallahumma 'amootu wa 'ahyaa

"In Your name O Allah, I live and die."

Narrated Hudhaifa:
When the Prophet (ﷺ) went to bed, he would say: "Bismika amutu wa ahya." and when he got up he would say:" Al-hamdu li l-lahil-ladhi ahyana ba'da ma amatana wa ilaihin nushur


In sha Allah

#night_reminder
@Gemsofjannah98
ምእራባዊያኑን ያሸበረችው፣  አውሮፕላን ጠላፊ ደፋር የሴት ጀግና፣ ፍልስጤማዊቷ አቢዎተኛ የነፃነት ታጋይ #ለይላ ኻሊድ ማናት ⁉️  
እነሆ በሰላም፣ በእኩልነት እና በሰው ልጆች ነፃነት የሚያምነው የዓለም ህዝብ በሙሉ ስለሚያደንቃት ፍልስጥኤማዊት ልናወጋ ነው። ይህቺ የነፃነት ታጋይ በእስራኤልና በአሜሪካ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ "አሸባሪ" ተብላ ተፈርጃለች። የአውሮጳ ህብረትን ጨምሮ አብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ግን "የነፃነት ታጋይ" በማለት ነው የሚገልጿት። በዚህም የተነሳ በአውሮጳ ፓርላማ ተጋብዛ ንግግር ለማድረግ ችላለች።

እኛም በታጋይነቷ ነው የምናውቃት። ይህቺ ሴት ማን ነበረች? እስቲ በአጭሩ እንተዋወቃት።
ምእራባዊያኑን ያሸበረችው፣  አውሮፕላን ጠላፊ ደፋር የሴት ጀግና፣ ፍልስጤማዊቷ አቢዎተኛ የነፃነት ታጋይ #ለይላ ኻሊድ ማናት ⁉️  
እነሆ በሰላም፣ በእኩልነት እና በሰው ልጆች ነፃነት የሚያምነው የዓለም ህዝብ በሙሉ ስለሚያደንቃት ፍልስጥኤማዊት ልናወጋ ነው። ይህቺ የነፃነት ታጋይ በእስራኤልና በአሜሪካ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ "አሸባሪ" ተብላ ተፈርጃለች። የአውሮጳ ህብረትን ጨምሮ አብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ግን "የነፃነት ታጋይ" በማለት ነው የሚገልጿት። በዚህም የተነሳ በአውሮጳ ፓርላማ ተጋብዛ ንግግር ለማድረግ ችላለች።

እኛም በታጋይነቷ ነው የምናውቃት። ይህቺ ሴት ማን ነበረች? እስቲ በአጭሩ እንተዋወቃት።
----
የፍልስጥኤም የነፃነት ትግልን ከጀመሩት አንጋፋ ድርጅቶች መካከል አንዱ Pupolar Front for the Liberation of Palestine (PFLP) ይባላል። ይህንን ድርጅት የመሠረቱት ዶክተር ጆርጅ ሀበሽ እና ዶክተር ዋዲ ሃዳድ ነበሩ። ጆርጅ ሀበሽ የግንባሩ ዋና ጸሐፊ ሲሆን ዋዲ ሀዳድ ደግሞ የግንባሩ ወታደራዊ እና የደህንነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ነበር።

የPFLP አመራር በተመሠረተበት ጊዜ ትኩረት ካደረገባቸው ነገሮች አንዱ ትግሉን ለዓለም ህዝብ ማስተዋወቅ ነው። በዚህም መሠረት ታጋዮቹ በ1968 ባካሄዱት የአውሮፕላን ጠለፋ የፍልስጥኤማዊያንን ትግል ለማስተዋወቅ እንደረዳ ተገንዝቧል፡፡

የግንባሩ አመራር በቀጣዩ ዓመት (1969) ከመጀመሪያው ጠለፋ በበለጠ ሁኔታ ብዙዎችን ሊያነጋግር የሚችል ኦፕሬሽን እንዲካሄድ ወሰነ፡፡ የግንባሩ የወታደራዊ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበረው ዶ/ር ዋዲ ሀዳድም እንዲያ ዓይነቱን ኦፕሬሽን እንዲያስፈጽም በግንባሩ የፖለቲካ ቢሮ መመሪያ ተሰጠው፡፡ ለኦፕሬሽኑ የሚያስፈልገው የፋይናንስ፣ የማቴሪያል እና የሰው ኃይል ግብአቶችም ተመደቡለት፡፡
 
ዶ/ር ዋዲ ሀዳድ ከፖሊት ቢሮው የተሰጠውን ትእዛዝ በሚያስፈጽምበት መንገድ ዙሪያ የተለያዩ አማራጮችን ሲያጠና ቆየ፡፡ በሀሳቡ የመጡትን ርእዮች ሁሉ ከገመገማቸው በኋላ አንድ ብልሃት የተሻለ ሆኖ ታየው፡፡ ይህም ጠለፋው በሴት ታጋይ እንዲመራ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት ከቀዳሚ የግንባሩ አባላት አንዷ የነበረችውን የሃያ አምስት ዓመት ወጣት ኦፕሬሽኑን በኃላፊነት እንድታካሄድ መረጣት፡፡ ሌሎች ሶስት ታጋዮችንም በረዳትነት መደበላት፡፡

በአራቱ ፍልስጥኤማዊያን እንዲጠለፍ የታዘዘው ነሐሴ 28/1969 ከሮም ተነስቶ በአቴንስ በኩል ትራንዚት አድርጎ ወደ ቴል አቪቭ የሚበር አንድ የእስራኤል አየር መንገድ አውሮፕላን ነበር፡፡ ወጣቶቹ ሮማ ደርሰው ለኦፕሬሽኑ መዘጋጀት ሲጀምሩ ግን የPFLP የደህንነት ኮሚቴ ያልተጠበቀ መረጃ ደረሰው፡፡ ይህም መረጃ “በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ይስሐቅ ራቢን የበረራ ቁጥሩ 840 በሆነ የአሜሪካው TWA አየር መንገድ አውሮፕላን ነሐሴ 28/1969 ከኒውዮርክ ተነስተው ሮም ይገባሉ፣ በማግስቱ ደግሞ በተመሳሳይ አውሮፕላን ወደ ቴል አቪቭ ይበራሉ” የሚል ነበር፡፡

ሚስተር ይስሐቅ ራቢንን ብዙዎች የሚያስታውሱት በ1993 ከያሲር አረፋት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙ በመሆናቸው ነው፡፡ በቀደመው ዘመን ግን ሰውዬው እንዲያ አልነበሩም፡፡ ፍልስጥኤማዊያን የተጨፈጨፉባቸውንና ከሀገራቸው የተባረሩባቸውን ዘመቻዎች ከመሩት የእስራኤል የፖለቲካ እና ወታደራዊ ባለስልጣናት አንዱ ነበሩ፡፡ በ1948 እስራኤል ምዕራብ እየሩሳሌምን ከፍልስጥኤሞች የነጠቀችበትን ዘመቻ የመሩት እርሳቸው ነበሩ፡፡ በ1967 በተካሄደው የዐረብ-እስራኤል ጦርነት ፍልስጥኤም በእስራኤል ሙሉ በሙሉ በተወሰደችበት ወቅት ደግሞ የእስራኤል የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ነበሩ፡፡ የጦር ኃይሉ በፍልስጥኤማዊያን ላይ ልዩ ልዩ ግፎችን እየፈጸመ ከሀገራቸው እንዲያባርራቸው የተሰጠውን ትእዛዝ በበላይነት ያስፈጸሙት እርሳቸው ነበሩ፡፡ ስለዚህም ነበር የPFLP አመራር መረጃው ሲደርሰው እርሳቸውን አፍኖ ለመውሰድ የወሰነው፡፡
---- 
ዶ/ር ዋዲ ሀዳድ ከላይ የጠቀስኩት መረጃ ሲደርሰው ቀደም ብሎ ባወጣው ፕሮግራም ላይ ለውጥ ለማድረግ ወሰነ፡፡ ወደ ወጣቶቹ ደውሎም የመጀመሪያው እቅድ መሰረዙን ነገራቸው፡፡ ለትራንዚት በሮማ ከተማ በሚያርፈው የTWA አውሮፕላን ወደ ቴል አቪቭ ለመጓዝ የሚያስችላቸውን ቲኬት እንዲገዙና አውፕላኑን ጠልፈው ወደ ደማስቆ እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡

ወጣቶቹም ትእዛዙን በመቀበል በTWA አውሮፕላን ለመብረር የሚያስችላቸውን ቲኬት ገዙ፡፡ ነሐሴ 29 ቀን 1969 ጓዛቸውን ይዘው በሮማው የሊኦናርዶ ዳቪንቺ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኙ፡፡ ወደ TWA አውሮፕላን ከገቡ በኋላም ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ለአርባ ደቂቃዎችም በዝምታ ተጓዙ፡፡ አውሮፕላኑ ወደ አድሪያሪቲክ ባሕር ሲጠጋ ግን በጉያዎቻቸው የያዟቸውን ሽጉጦች በማውጣት የጠለፋ ኦፕሬሽኑን ጀመሩ፡፡

ወጣቷ ፍልስጥኤማዊት አንድ ጓዷን አስከትላ በፍጥነት ወደ አብራሪዎች ክፍል ገባችና ፓይለቱ አውሮፕላኑን ወደ ደማስቆ እንዲያበርረው አዘዘችው፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ደግሞ የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ባሉበት ሆነው ጉዞአቸውን እንዲቀጥሉ ነገሯቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም አንዲት ሴት በአውሮፕላኑ የድምጽ ማጉያ መሳሪያ እንዲህ ስትል ተደመጠች፡፡

“ጤና ይስጥልን መንገደኞች! ይህ አውሮፕላን ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ በፍልስጥኤም ህዝባዊ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የፍልስጥኤም ህዝባዊ ነፃነት ግንባር በፅዮናዊያንና በኢምፔሪያሊስቶች ሴራ ሉዓላዊነቷ የተገፈፈውንና ህዝቡ የተበተነባትን ፍልስጥኤምን ነፃ ለማውጣት የሚታገል ድርጅት ነው፡፡ ግንባራችን ከፍልስጥኤም ህዝብ ጠላቶች በስተቀር ሰላማዊ ሰዎችን የማጥቃት ዓላማና ፍላጎት የለውም፡፡ ይህ አውሮፕላን የተጠለፈው የኢምፔሪያሊስት ጠላቶቻችን ንብረት ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ በወዳጅ ሀገር ካረፈ በኋላ በነፃ ትለቀቃላችሁ፡፡ እስከዚያው ግን ከወንበሮቻችሁ ሳንትንቀሳቀሱ ጉዞአችሁን እንድትቀጥሉ በጥብቅ እናስታውቃለን”

ወጣቷ ይህንን የተናገረችው በእንግሊዝኛ እና በዐረብኛ ቋንቋዎች ነው፡፡ ይህች ወጣት ትግሉን የተቀላቀለችው በአስራ አምስት ዓመቷ ነው፡፡ ከላይ የተገለጸውን ጠለፋ እስፈጸመችበት ጊዜ ድረስም የትግሉ ንቁ ተሳታፊ ነበረች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ የPFLP አባል ሆና ዘልቃለች፡፡ ፍልስጥኤማዊያን ሴቶች በትግሉ ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎ በሚወሳበት ጊዜም በቅድሚያ የምትጠቀስ የትግል አርአያ ለመሆን በቅታለች፡፡

ታዲያ ወጣቷ የምትወሳው በታጋይነቷ ብቻ አይደለም፡፡ በታሪክ ምዕራፍ የመጀመሪያዋ ሴት የአውሮፕላን ጠላፊ ሆና የተመዘገበች በመሆኗም ሚሊዮኖች ያውቋታል፡፡ በዘመኑም ጉድ ተብላ ወሬዋ በብዙዎች ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡ ገድሏን የሚዘክሩ ብዙ ጽሑፎችና መጻሕፍት ተጽፈዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም ታሪኳን የሚዘክሩ ፊልሞች ተሰርተዋል፡፡ በእርሷ የተነሳም በርካታ የዓለም ህዝብ ስለፍጥኤማዊያን ትግል ሊያውቅ ችሏል።
----
ያቺ ፍልስጥኤማዊት ወጣት በተጸውኦ ስሟ “ለይላ ኻሊድ” በመባል ትታወቃለች፡፡ ከፍልስጥኤም ክርስቲያን ቤተሰቦች የተወለደች ናት። በፖለቲካ አቋሟ ማርክሲስት ናት። ለይላ አሁንም በሕይወት አለች።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል ብዙዎቹ ስለአውሮፕላን ጠለፋ ሰምተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጠላፊዋ ሴት ስትሆንባቸው በጣም ነበር የተደናገሩት፡፡ ይህም የሆነው በዘመኑ ወንዶች እንጂ ሴቶች በአውሮፕላን ጠለፋ ሲሳተፉ ስላልታየ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ተሳፋሪዎቹ ከመደናገጥ ይልቅ ወደ አግራሞት ነበር ያደሉት፡፡ ጠላፊዋ የድርጅቷን የፖለቲካ ዓላማዋ እያብራራች ስትገልጽላቸው ደግሞ ያደንቋት ጀመር፡፡
 
ለይላ ኻሊድ የአውሮፕላኑን አብራሪ እየመራች ጉዞዋን ቀጠለች፡፡ አውሮፕላኑ የሜዲትሪያኒያንን ባሕር ሲያቋርጥ ግን የትውልድ ከተማዋ ናፍቆት ተቀሰቀሰባት፡፡ በመሆኑም አብራሪውን “የተወለድኩት በሐይፋ ከተማ ነው፡፡ ሆኖም ለረጅም ጊዜ አላየኋትም። ስለዚህ ከተማዬን ማየት እንድችል አውሮፕላኑን በዚያ በኩል አሳልፈው” በማለት አዘዘችው፡፡ አብራሪውም እንደተባለው አደረገ፡፡ ለይላም የሐይፋ ከተማን ከሀያ ዓመታት በኋላ ከሰማይ ወደታች ቁልቁል አየቻት፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎችም በኃላፊነት የምትመራውን አደገኛ ኦፕሬሽን ዘንግታ ከተማዋን እያየች አነባች፡፡

ከሽርፍራፊ ሰከንዶች በኋላ ግን ደነገጠችና ከትካዜዋ ነቃች፡፡ አትኩሮቷንም ሰብስባ ወደ ኦፕሬሽኑ ተመለሰች፡፡ ታዲያ አብራሪው የለይላን ሁኔታ ሲያይ ከልቡ ነበር ያዘነላት፡፡ በመሆኑም  ትእዛዞቿን በምንም መልኩ ለመጣስ አልደፈረም፡፡ ከአንድ ሰዓት ተኩል በኋላም አውሮፕላኑን በደማስቆው የሐፊዝ አል አሳድ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ አሳረፈው፡፡
-----
አውሮፕላኑ ወደ ደማስቆ እንደሚመጣ ለሶሪያ ባለስልጣናት ተነግሮ ስለነበረ ብዙ መደናገጥ አልተፈጠረም፡፡ አውሮፕላኑ ሲያርፍ ደግሞ PFLP ያሰማራቸው ተጨማሪ ኮማንዶዎች ለይላንና ጓደኞቿን ለመርዳት ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ ለለይላም ዛሬ በብዙ ፎቶግራፎች ላይ ታጥቃ የምትታየውን AK-47 (ክላሽኒኮቭ) ጠመንጃ አመጡላት፡፡

  በአውሮፕላኑ ይጓዙ የነበሩ ተሳፋሪዎችን ማንነት ለማጣራት ፍተሻ ሲደረግ ግን አምባሳደር ይስሐቅ ራቢን በአውሮፕላኑ ውስጥ እንደሌሉ ታወቀ፡፡ በዚህም የPFLP አመራሮች የተሳሳተ መረጃ እንደደረሳቸው ተረዱ፡፡ ለወደፊቱ ጥንቃቄ ለመውሰድ ወሰኑ፡፡ ቢሆንም አውሮፕላኑ በለይላ ኻሊድ መሪነት መጠለፉ ታላቅ ዜና በመሆኑ የPFLP መሪዎች በአፈጻጸሙ በጣም ነበር የተደሰቱት፡፡

ከግማሽ ሰዓት በኋላ የተጠለፈው አውሮፕላን በደማስቆ ስለማረፉ በሶሪያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ተነገረ፡፡ በርካታ ጋዜጠኞችና ወሬ አነፍናፊዎችም ወደ አየር ማረፊያው መጡ፡፡ ለይላ ኻሊድ ከአውሮፕላኑ ሳትወርድ ከጋዜጠኞቹ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አደረገች፡፡ የዓለም ማህበረሰብ የፍልስጥኤምን ህዝብ ስቃይ እንዲመለከትና ለህዝቡ የነፃነት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ማሳሰቢያ ሰጠች፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የታገቱት ተሳፋሪዎች በነፃ እንደሚለቀቁም አስታወቀች፡፡ “አውሮፕላኑ ግን የእስራኤል አውራ ረዳትና የፍልስጥኤም ህዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነችው የአሜሪካ ኢምፔሪያሊስቶች ንብረት ነው፣ ስለዚህ በዚሁ ሜዳ ላይ እያለ ይቃጠላል” በማለትም አከለች፡፡

ለይላ ኻሊድ ከPFLP አመራር በተሰጣት ትእዛዝ መሠረት በተከታዮቹ ቀናትም ወደ አየር ማረፊያው ከመጡ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጋለች፡፡ ታዲያ ለይላ ከጋዜጠኞቹ ጋር ስትነጋገር ስለትግሉ እንጂ ስለራሷ ግድ አልነበራትም፡፡ ወደ ጠለፋው የገባችውም በግንባሩ ስለታዘዘች እንጂ ራሷን ለማስተዋወቅ አልነበረም፡፡ ይሁን አንጂ ለጋዜጠኞች መግለጫ በምትሰጥበት ወቅት ብዙዎች ፎቶ ሊያነሷት ተረባረቡባት፡፡ ከነዚያ ፎቶዎች ሁሉ እጅግ ታሪካዊና ዝነኛ ለመሆን የቻለው አንድ ታዋቂ ጋዜጠኛ በካሜራው ያስቀረው ምስል ነው፡፡

ጋዜጠኛው ኤዲ አዳምስ ይባላል፡፡ ኤዲ ለአሜሪካው አሶሼትድ ፕሬስ ተቀጥሮ የሚሰራ “ፎቶ-ጆርናሊስት” ነበር፡፡ ኤዲ “አንዲት ፍልስጥኤማዊት ወጣት አውሮፕላን ጠለፈች” በሚለው ዜና ተገርሞ ነበር ወደ አየር ማረፊያው በፍጥነት የመጣው፡፡ ለይላን ፊት ለፊት ሲያገኛት ደግሞ ልበ ሙሉነቷ እና ዓላማዋን የገለጸበችበት መንገድ በጣም አስደንቆታል፡፡ በመሆኑም በካሜራ እይታ ውስጥ ስትገባለት በጋዜጠኝነት ዓለም ታዋቂ ከሆኑት ፎቶግራፎች መካከል አንዱን አንስቶ ለአሶሼትድ ፕሬስ ላከው፡፡ በማግስቱም ፎቶዋ በበርካታ የአውሮጳ እና የአሜሪካ ጋዜጦች ላይ ወጣ፡፡ የግራ ኃይሎች ፎቶውን እያባዙ በዓለም ዙሪያ በስፋት አሰራጩት፡፡ በዚህም ሁኔታ ያ ታሪካዊ ፎቶ እንደ ቼ-ጉቬራ ፎቶግራፍ ታዋቂ ለመሆን በቃ፡፡

አሜሪካ እና የተለያዩ የዐረብ ሀገራት አውሮፕላኑን ከቃጠሎ ለማትረፍ ሞክረው ነበር፡፡ ነገር ግን ለይላ እና የPFLP መሪዎች ከቃላቸው ፍንክች የማይሉ ሆነው ነው የተገኙት፡፡ በማሳሰቢያቸው መሠረትም በአውሮፕላኑ ይጓዙ የነበሩትን ተሳፋሪዎችና ሰራተኞችን በሰላም ከለቀቁ በኋላ አውሮፕላኑን አቃጠሉት፡፡ ትዕይንቱም የወቅቱ ግንባር ቀደም ዜና ሆኖ በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተላለፈ፡፡
-----
ለይላ ኻሊድ ጠለፋውን ከካሄደች ከሰላሳ አንድ ዓመታት በኋላ (በነሐሴ ወር 2000) “Aviation Security” ከተባለ መጽሔት ጋር ቃል-ምልልስ ስታካሄድ ትዝታዋን እንዲህ በማለት ገልጻለች፡፡

“ከአውሮፕላኑ ውስጥ ስገባ አንዲት ህፃን አየሁ፡፡ ህፃኗ ቆንጅዬ እና ደስተኛ ናት፡፡ ከእናቷ ጎን ቁጭ ብላ ትስቃለች፡፡ በለበሰችው ቲ-ሸርት ላይ “Let us be friends” የሚል ጽሑፍ ተጽፏል፡፡ የርሷን ደስተኛነት ሳይ የልጅነት ዘመኔ ትዝ አለኝ፡፡ በልጅነቴ ምንም ሳላጠፋ ወራሪዎች ከተማችንን ይዘው ቁም ስቅላችንን ሲያሳዩን ትዝ አለኝ፡፡ ንፁሐን ጎረቤቶቻችን ፍልስጥኤማዊ በመሆናቸው ብቻ የተገደሉበት ትዕይንት ትዝ አለኝ፡፡ ከቤተሰቦቼ ጋር እየደበደቡ ከቤታችን ካስወጡን በኋላ ከከተማችን ሲያባርሩን ያደረብኝ ስሜት ትዝ አለኝ፡፡ ልጅነቴን እንደዚያች ህፃን በደስታ ለማሳለፍ አልቻልኩም፡፡ በወራሪዎች ደባ በልጅነቴ ወደ ስደተኛ ካምፕ ገብቼ አራት ዓመታትን በሰቀቀንና በችግር አሳልፌአለሁ፡፡ አስር ዓመት ከሆነኝ በኋላ ነው ታላቅ እህቴ መጥታ ከካምፑ ያስወጣችኝ፡፡ ታዲያ በአውሮፕላኑ ውስጥ ያገኘኋትን ደስተኛ ልጅ እያየሁ በውስጤ እንዲህ አልኩ፡፡

“ሚሚዬ! ፈጣሪ በሰጠሽ ፀጋ መደሰትሽ ያኮራል፡፡ እኔም በዛሬው ዕለት ከባድ ኃላፊነት ተሸክሜ ከአጠገብሽ የተገኘሁት ፍልስጥኤማዊያን ህፃናት እንዳንቺ ደስተኛ ሆነው እንዲያድጉ ስለምፈልግ ነው”

ጸሐፊ አፈንዲ ሙተቂ

ታሪኩ ከተመቻችሁ #share  አድርጉት !!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍚የነጭ ሽንኩርት የጤና ጥቅሞች🍚

👉በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች መድኃኒትነት አለው፡፡
👉በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት
ብቃት ያለው የምግብ ዓይነት ነው፡፡
👉ነጭ ሽንኩርት በውስጡ የደም መርጋትን የሚከላከል ንጥረ ነገርን ይይዛል፡፡ የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል፡፡
👉ከዕድሜ መጨመር የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ጥበትን የመከላከል ጥቅም ያለው ነጭ ሽንኩርት ይህንን በማድረግ በደም ቧንቧ ጥበት ምክንያት የሚከሰት የልብ ሕመምን ይከላከላል፡፡
በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧ ላይ የሚገኘውን የስብ መጠን
እንዲቀንስ ያድርጋል፡፡ ሰውነታችን በአለርጂ እንዳይጠቃ የማድረግ አቅምም አለው፡፡
በሰውነት ላይ ለሚወጣ ሽፍታና በአንዳንድ ነፍሳት ምክንያት የሚወጣንን ሽፍታም ይከላከላል፡፡
ነጭ ሽንኩርት በጉንፋን የመያዝ ሁኔታን በከፍተኛ ደረጃም ይቀንሳል፡፡ከተያዝንም በኋላ እንዳይበረታብን
ቶሎም እንድንድን ይረዳል፡፡
ነጭ ሽንኩርት በሰውነታችን የሚመነጨውን የኢንሱሊን መጠን መጨመርና በደም ውስጥ የሚገኙትን
የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለስኳር ሕመም ጠቀሜታነት ይሰጣል፡፡
የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ጥርሳችንን በሚያመን ቦታ ላይ በማድረግ ባክቴሪያዎችን ማጥፋትና ሕመምን የመቀነስ ጥቀም አለው፡፡
እባክዎ ሼር ያድርጉት sharing is happiness

@jenet8
Forwarded from ❀ እውቀትን ፍለጋ ❀ (Ebnu Turab R®) via @like
🏆ሙኡሚን ከዚክር ቦዝኖ አያውቅም 🏆
🌈የማታ አዝካር🌈

‘አልሏሁምመ ቢከ አሰበሕና ወቢከ አምሳይና፤ ወቢከ ነሕያ ወቢክ ነሙውት፤ ወኢለይከኑሹወር 

👉አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡ /ቲርሙዝይ/ .’ 

========================

اَللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّيْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ، خَلَقْتَنِيْ وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوْءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوْءُ بِذَنْبِيْ فَاغْفِرْ لِيْ فَإِنَّهُ لاَ يَغْفِرُ الذُّنُوْبَ إِلاَّ أَنْتَ.

‘አልሏሁምመ አንተ ረብቢ ላኢላህ ኢልላ አንተ፤ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ ወአነ ዐለ ዐሕዲከ ወወዐዲከ መስተጠዕቱ አዑዙ ቢከሚን ሸርሪ ማስነዐቱ አቡዑ ለከ ቢኒዐመቲክ ዐለይየ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፈርሊ ፈኢንነሁ ላየግፈሩዝኩኑ ውብ ኢልላ አንተ 

👉አላህ ሆይ አንተ አምላኬ ነህ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ፈጥረህኛል፡፡ እኔ ባሪያህ ነኝ፡፡ እኔ የቻልኩትን ያክል ያንተን ቃልዳኪን ለመሙላት እሞክራለሁ፡፡ ከስራሀው ነገር ከክፉው በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ በኔ ላይ ለዋልከው ጸጋህ እውቅና እሰጣለሁ፡፡ ሐጢአቴም እናዘዛለሁ፡፡ ማረኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሐጢአትን የሚምር የለም፡፡’

=========================

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَصْبَحْتُ أُشْهِدُ وَأُشْهِدُ حَمَلَةَ عَرْشِكَ، وَمَلاَئِكَتَكَ وَجَمِيْعَ خَلْقِكَ، أَنَّكَ أَنْتَ اللهُ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ وَحْدَكَ لاَ شَرِيْكَ لَكَ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُكَ وَرَسُوْلُكَ. (4×)

አልሏሁምመ ኢንኒ አሰበሕቱ ኡሽሒዱከ ወኡሸሒዱ ሐመለተ ዐርሺክ፤ ወመላኢከተከ ወጀሚዓ ኀልቂከ፤ አንከ አንተአሏህ ላኢላሃ ኢለላ አንተ ወሕደክ ላሸሪከ ለከ፤ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱከ ወረሱሉከ]

☞አንተነህና ዙፋንህን የተሸከሙ /መላዕክትን/ ስመሰክር አንግቻለሁ፡፡አንተ አላህ መሆንህንና ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ እንደሌለ አንድነትህ አጋር እንደሌለህም፤ ሙሐመድም ባሪያህና መልዕክተኛህ መሆናቸውንም፡፡
አራት ጊዜ፡፡ /አቡዳውና ቡኻሪ/
========================

اَللَّهُمَّ مَا أَصْبَحَ بِيْ مِنْ نِعْمَةٍ أَوْ بِأَحَدٍ مِنْ خَلْقِكَ فَمِنْكَ وَحْدَكَ لاَ شَرِيْكَ لَكَ، فَلَكَ الْحَمْدُ وَلَكَ الشُّكْرُ.

‘አልሏሁምመ ማ አሰበሃ ቢሚንኒዕመቲን አው ቢ አሃዲን ሚን ኸልቂከ ፊሚንከ ወሕደከ ላሸሪከ ለከ፤ ፊለከል ሐምዱ ወለከሹክር

☞አላህ ሆይ በኔ ወይም በፍጡራንህ በአንድ ለይ ያነጋው፤ ፀጋ ከአንተና ከአንተ ብቻ የመነጨ ነው፡፡ አጋር የለህም፡፡ ምስጋናና ውዳሴ ይገባሃል፡፡
=========================

حَسْبِيَ اللهُ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيْمِ. (7×)

‘ሐሥቢየልላሁ ላኢላህ ኢላሁ ዐለይሒ ተወክከልቱ ወሁወ ረብቡል ዐርሺል ዐዚም 

☞አላህ በቂዬ ነው፡፡ ከርሱ ሌላ ሊመለክ የሚገባው ሀይል የለም፡፡ በርሱ ተመካሁ፡፡ እርሱ የታላቅ ዐርሽ ጌታ ነው፡፡ ሰባት ጊዜ፡፡
======================
@truth_coll
@truth_coll
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም ስራ መልካም ስነምግባር ነው።
ሀጥያት ማለት ስትሰራው የምተጠራጠርበትና
ሰዎች ያውቁብኛል ብለህ የምትፈራው ነው።
(ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ)

Share & join
👇👇👇👇👇👇
@jenet8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💧የአላህን ትእዛዛት በመፈፀም ላይ ሰብር አድርግ
💧ከከለከለህ ነገር በመራቅ ላይ ሰብር አድርግ
💧በሚያሳምሙ ቀደሮችም ላይሰብር አድርግ
🌴ከዚያ ጀነት ውስጥ ይህን ትሰማለህ
¤ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን(ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው¤       [አራዕድ 24 ]
@jenet8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💧የአላህን ትእዛዛት በመፈፀም ላይ ሰብር አድርግ
💧ከከለከለህ ነገር በመራቅ ላይ ሰብር አድርግ
💧በሚያሳምሙ ቀደሮችም ላይሰብር አድርግ
🌴ከዚያ ጀነት ውስጥ ይህን ትሰማለህ
¤ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን(ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው¤       [አራዕድ 24 ]
@jenet8
💧የአላህን ትእዛዛት በመፈፀም ላይ ሰብር አድርግ
💧ከከለከለህ ነገር በመራቅ ላይ ሰብር አድርግ
💧በሚያሳምሙ ቀደሮችም ላይሰብር አድርግ
🌴ከዚያ ጀነት ውስጥ ይህን ትሰማለህ
¤ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን(ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው¤       [አራዕድ 24 ]
@jenet8