Consulate General of Ethiopia, Jeddah
21.8K subscribers
1.77K photos
4 videos
76 files
325 links
Download Telegram
👍4429🙏20🥰13
👍6623🥰12
የጅዳ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጽ/ቤት ከSendian Al khalij ካምፓኒ ጋር ውይይት አድረገ፣
(ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ፡ጄዳ)
የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የቢዝነስ ዲፕሎማሲየሥራ ዘርፍ ከSendian Al khalij Agriculture ካምፓኒ የእርሻ መሐንዲስ ከሆኑትከአቶ Mohamed Fayez ጋር ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በጽ/ቤታቸውበመገኘት ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ ላይ ለአቶ Mohamed በአገራችን ለኢንቨስትመንትምቹ ሁኔታዎች ያሉ መሆናቸውን፣ ትኩረት የተሰጣቸውን የኢንቨስትመንት መስኮች እና ማበረታቻዎች በማስመልከት ገለጻ ተደርጎ ግንዛቤየማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል።አቶ Mo
hamed Fayez በበኩላቸው በተደረገላቸው ገለጻበኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና ማበረታቻዎች በተመለከተ ግንዛቤ በማግኘታቸው አመስግነው፤ ካምፓኒያቸው በኢንቨስትመንትመሳተፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከኢትዮጵያ ኤክስፖርት የሚደረጉ የግብርና ምርቶችን መግዛት የሚፈልጉ መሆናቸውን በማንሳት የምርቶቹን ዝርዝርማግኘት እንደሚፈልጉ አስረድተዋል። ቆንስላ ጽ/ቤ
ቱም ከአገራችን ኤክስፖርትየሚደረጉ የግብርና ምርቶችን ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን በማመስገን፣ የምርቶችን ዝርዝር ከሚመለከታቸው አካላት በማግኘት እንዲደርሳቸውየሚደረግ መሆኑን ገልጿል።. ..Telegr
am

(
የቴሌግራምቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon.Twitter (በ

ዊተርይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
30👍18
በሳዑዲ አረቢያ የተወለዱ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን እና ጀማኢየት ዩብሲሩን የአይን ህክምናማህበር መካከል የነፃ የዓይን ህክምና ስምምነት ተፈራረሙ፣

(ጥር20 ቀን 2018 ዓ.ም ፡ጄዳ)በ
ሳዑዲአረቢያ መካ የተወለዱ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን ከመካ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ጋር በመተባበር በሳዑዲ አረቢያ ህጋዊ እውቅናካለው ጀማኢየት ዩብሲሩን የአይን ህክምና የበጎ አድራጎት ማህበር በመካ ክልል ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ከኢትዮጵያ ለሀጅና ዑምራለሚመጡ ዜጎቻችን የዓይን ህክምና በነፃ ለመስጠት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ በስምም
ነቱወቅት ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ዓላማ የሚበረታታና አስፈላጊ በመሆኑ ወደ ተግባር እንዲገባ አስፈላጊውንድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ይህ ድርጅት በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ የነፃ ህክምና እንዲያደርግ እንደሚያመቻቹገልፀዋል፡፡ Mr.Jaza
a Al-Dahas የጀማኢየት ዩብሲሩን አማካሪና ዋና ኃላፊ እንደገለፁት ስምምነቱ ለአንድ ዓመት ተግባራዊ እንደሚሆን አንስተዋል፡፡ድርጅቱ በቀጣይ በኢትዮጵያ መሠል አገልግሎት ለመስጠት ይሁንታውን ገልጿል፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት በመካ ኮሚዩኒቲ ጽ/ቤት በኩልመመዝገብ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡. ..Telegr
am

(
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon.Twitter (

ትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
56👍32👌3
የጄዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ዲፕሎማቶችና ሠራተኞችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በጂዛንግዛት በመጓዝ ታስረው የሚገኙ ዜጎቻችንን በመጎብኘት የሊሴ ፓሴ (የይለፍ ሰነድ) የመስጠት ሥራ አከናወነ። (ጥር 24፣ 2018 ዓ.ም) የጄዳቆንስላ ጽ/ቤት ልዑካን ቡድን ወደ ጂዛን ግዛት በማቅናት ከጂዛን ግዛት ኢሚግሬሽን (ጀዋዛት) የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገሲሆን፣ በውይይቱ የግዛቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ፈይሰል አልሽህሪ በጉብኝቱ መደሰታቸውንና አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። አክለውም መሰል ውይይቶች መቀጠላቸው ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስምረውበታል። የልዑካን ቡድኑ መሪ ቆንስልጀማል ገዳ በበኩላቸው፤ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለጻ ምስጋና አቅርበው፣ ከጂዛን በቀጥታ የዲፖርቴሽን በረራ መጀመሩ ያለውን ዘርፈ-ብዙጥቅም ጠቁመዋል።ልዑካን ቡ
ድኑ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ተደራሽ ለመሆን በጂዛን ዲፖርቴሽን ማዕከልበመገኘት የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የድንበር ደኅንነት ሕግ ተላልፈው በማዕከሉ ታስረው የሚገኙ ዜጎችን በቀጥታ በረራወደ አገር ቤት ለመመለስ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሂደት በማጠናቀቅ፣ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የይለፍ ሰነድ ማዘጋጀት ችሏል።በተጨማሪም ከማቆያ ማዕከሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቀጣይ ሥራዎች ላይ ምክክር የተደረገ ሲሆን፣ በሕክምና ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ዜጎችያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውሮ ለመመልከት ተችሏል። ልዑካን ቡድኑ ላከናወናቸው ስኬታማ ስራ የጂዛን ኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ከፍተኛ አስተዋጽኦአድርጓል።. ..Telegram (የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon.Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
👍3331🙏3
የ2018 ዓ.ም የዳራሮ በዓል በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽከጅዳ እና አካባቢው የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በድምቀት ተከበረ፣

(ጅዳ፣ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም) የ2018 ዓ.ም የዳራሮ በዓል በጅዳ እና አካባቢው በሚኖሩ ከ200 በላይየሚሆኑ የጌዴኦ ተወላጆችና በጅዳ እና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊን ጋር ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ምበጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ በድምቀት ተከበረ። በስነስርዓቱ ላይ በጅዳ የኢፌዲሪ ቆንሱል ጀኔራል ተወካይ አቶ ሙሉጌታ አበበ ባደረጉት ንግግር ዳራሮ በመሠረቱ የምስጋናና የእርቅ በዓል እንደሆነ እና ዋና ዓላማዎቹም ለአምላክ ምስጋና ማቅረብ፣ በተለይም የአዝመራ መሰብሰብን አስመልክቶ ምስጋና ማቅረብ፣ ለሚመጣው ዓመት ደግሞ ሠላም፣ ዕድገት እና ብልጽግና እንዲኖር መጸለይ፤ በማህበረሰቡ ውስጥ፣በቤተሰብ መካከል እና በጎሳዎች መካከል ግጭቶችን ማስታረቅ፤ ማህበራዊ ቁስሎችን ለማጽዳትና ስምምነትን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው የሚል መልዕክት ስላለው ሁላችንም የዳራሮን ትክክለኛ ትርጉም ተረድተን ምስጋና ማቅረብን፣ እርቅ ማድረግን፣ ባህላችንንበአግባቡ መጠበቅን እና ኢትዮጵያዊ የሚያደርገንን አንድነት እንድናጠናክር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ በዲጄ የተቀናበሩ የብሄር ብሄረሰቦች ሙዚቃዎች ቀርበው ታዳሚው አዝናንቷል። በመጨረሻ ላይ የቆንስላ ጽ/ቤቱ ተወካዮች እና የተለያዩየዳያስፖራ አደረጃጀቶች ተወካዮች ለ2018 የዳራሮ ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል የተዘጋጀው ኬክ በጋራ ቆርሰው፣ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
31🥰3