Consulate General of Ethiopia, Jeddah
21.8K subscribers
1.77K photos
4 videos
76 files
323 links
Download Telegram
👍19❤7🥰6
በጅዳ የኢፌዲሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት የኅብር ቀን እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት የዋዜማ ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ፣

(ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ/ም)
የህብር ቀን - "ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ቃል እሁድ ጳጉሜ 02 ቀን 2017 ዓ.ም በጅዳ እና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ ለህብር ቀን እና ለ2018 የኢትዮጵያ አዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በፕሮግራሙ ላይ በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር (ዶ/ር) ሙክታር ከድር ባስተላለፉት መልእክትን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለፍጻሜ የበቃው በኢትዮጵያውያን ህብር መሆኑን ጠቅሰው፣ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በስነ ስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ እቤ ሳኖ የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት ተገኝተዋል። ክቡር አቶ እቤ ሳኖ ባስተላለፉት መልዕክት በሬሚታንስ አላላክ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና ከዳያስፖራው ጋር ውይይት ለማድረግ ጅዳ መምጣታቸውን ገልጸው፣ በቆይታቸውም ከሳዑዲ የሰራተኛ ቅጥር ኤጀንሲ ባለቤቶች፣ በሳዑዲ በተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ ከተሰማሩ ኢትዮጵያውያን፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውን አብራርተዋል። በውይይቱ ላይ ባንኩ ለዳያስፖራው ባዘጋጃቸው እማራጮች እንዲሁም ቴክኖሎጂዎች ላይ በባንኩ ከፍተኛ ሃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል።
በስነስርዓቱ ላይ በጅዳ የኢፌዲሪ ቆንሱል ጀኔራል ተወካይ አቶ ለዓለም ጥላሁን ባደረጉት ንግግር የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ማብሰሪያ ለሆነው የህብር ቀን እንዲሁም ለ2018 አዲስ አመት እንኳን እደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው፣ ዳያስፖራው ህጋዊ የገንዘብ መላኪያ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ራሱና ሀገሩን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በስነስርዓቱ ላይ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ጀማል ዳዲ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ማህበሩ በቀጣይ ከባንኩ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ከባንኩ ፕሬዚዳንት ጋር የመግቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በክብረ በዓሉ ላይ የተለያዩ የብሄር-ብሄረሰቦች ጣዕመ ዜማዎች በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ት/ቤት ተማሪዎች ቀርቦ ታዳሚውን እዝናንቷል። በመጨረሻ ላይ ለህብር ቀን የተዘጋጀው ኬክ በክቡር አምባሳደር (ዶ/ር) ሙክታር ከድር፣ ክቡር አቤ ሳኖ፣ የቆንስላ ጽ/ቤት፣ የኮሙኒቲ እና የተለያዩ አደረጃጀቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ ተቆርሶ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል።
❤26👍10👏5
👍35❤22👌9👏8
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምስራቅ ዲስትሪክት ም/ ፕሬዚዳንት በጄዳ ከሚገኙ የተለያዩ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ተወያዩ፣

(ጳጉሜን 3 ቀን 201 7 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምስራቅ ዲስትሪክት ም/ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ መሀመድ ከድሮ በጄዳ ከሚገኙ የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የተለያዩ የልማት ማህበራት እና በጅዳ ከኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበራት አመራሮች ጋር ተገናኝተው ተወያዩ። በውይይቱ ላይ በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዲሪ መንግስት ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር (ዶ/ር) ሙክታር ከድር፣ በጄዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንሱል ጀኔራል ተወካይ፣ በሪያድ የኢፌዲሪ ሚሲዮን የዳያስፖራ ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የጅዳ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች በተገኙበት ባንኩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች፣ የገንዘብ ማስተላለፊያ አማራጮች እና ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮረ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በዕለቱ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር ባስተላለፉት መልዕክት ዳያስፖራው ባንኩ ይዞ የመጣውን ዕድል ሊጠቀም እንደሚገባ፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የሀገራችንን ኢኮኖሚ የሚጎዳ በመሆኑ፣ በህጋዊ ሁኔታ ገንዘቡን ወደ ሀገር በመላክ ራሱንም ጠቅሞ በሀገሩ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት አስገንዝበዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በክቡር የባንኩ ም/ፕሬዚደንት እና በክቡር አምባሳደሩ ምላሽ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።
.
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
.
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
❤15