Consulate General of Ethiopia, Jeddah
21.8K subscribers
1.77K photos
4 videos
76 files
323 links
Download Telegram
የጄዳ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጽ/ቤት ከባለሀብት ጋር የተደረገ ውይይት፣

(ጄዳ፡ ሐምሌ 14 2017 ዓ.ም) ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ ከቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ሥራ ዘርፍ ጋር በመሆን ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም Sadan Al Jazeera ሃላፊ ከሆኑት Waleed Aljohani ጋር ተገናኝተው ውይይት አካሂዷል። በውይይቱም አገራችን በእርሻ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሸን ቴክኖሎጂ እና በቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስተሮች ለመሳተፍ እንዲችሉ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉንና ተቀብሎ ለማስተናገድ፣ መረጃ በመስጠት እና ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ መሆኑን እና ለሥራውም የተለያዩ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች የተዘጋጁ መሆናቸውን ማስረዳት ተችሏል።
አቶ Waleed Aljohani በበኩላቸው ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት እንደሚመላለሱ እና በደንብ እንደሚያውቋት፣ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ለመሳተፍ እንቅስቃሴ የጀመሩ መሆናቸውን፣ የኢትዮጵያ ሻይ ቅጠል፣ የፍየል እና የበግ ሥጋም ወደ ሳዑዲ አረቢያ ገበያ ለማምጣት እንደሚፈልጉ አስረድተዋል።
በመጨረሻም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ኢንቨስትመንት ላይ ለመሳተፍ እና ምርቶቻችንን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለማምጣት ያሳዩትን ፍላጎት በማድነቅ በቀጣይ ሥራውን ስኬታማ ለማድረግ ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ በዲኘሎማሲያዊ መንገድ ገለፃ አድርገዋል።
.
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
.
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
2
በጅዳ የስልጤ ልማት ማህበር ቢሮ ተመረቀ

(ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም) በጅዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት በጅዳና አካባቢዋ የሚገኙ የልማት ማህበራት ተልዕኮአቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ የመገልገያ ቢሮ እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በጅዳ የስልጤ ልማት ማህበር የተሰጠውን የመገልገያ ቢሮ በማደስና በቁሳቁስ በማደራጀት አስመርቋል። በምረቃው ላይ በጅዳ የኢፌዲሪ ቆንሱል ጄነራል ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ፣ ዲፕሎማቶች፣ በጅዳ የስልጤ ልማት ማህበር አመራርና አባላት፣ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር ሰብሳቢ፣ በጅዳ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ተወካይ፣ በጅዳ የጉራጌ ልማት ማህበር ተወካይ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል። በስነስርዓቱ ላይ ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ ባደረጉት ንግግር ቆንስላ ጽ/ቤቱ የልማት ማህበራትና የኮሙኒቲ አደረጃጀቶች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል ቆንስላ ጽ/ቤቱ የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው፣ በጅዳ የስልጤ ልማት ማህበር ቢሮውን በተረከበ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማደስና በቁሳቁስ በማደራጀት የሰራው ስራ የሚደነቅና ለሌሎች ማህበራትም ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው፣ የልማት ማህበሩን አባላትና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በስነስርዓቱ ላይ የቢሮ ምረቃ ፕሮግራሙን በማስመልከት የተዘጋጀው ኬክ በክቡር አምባሳደር፣ ዲፕሎማቶች እና የልማት ማህበሩ አመራሮች ተቆርሷል።
በመጨረሻ ላይ በጅዳ የስልጤ ልማት ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሙሳ ሀሰን ባስተላለፉት መልዕክት ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ በጅዳ ለስልጤ ልማት ማህበር ብቻ ሳይሆን በጅዳና አካባቢዋ የሚገኙ የልማት ማህበራትና አደረጃጀቶች ለማጠናከር እየሰሩ ያለው መልካም ስራ የሚያስመሰግንና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸው፣ ለተሰጣቸው የመገልገያ ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል።

Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon

Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20
. 📌ማስታወቂያ📌
. *********************
ለህፃናት ሊሴ ፓሴ አመልካቾች በሙሉ:-

Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
.
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20