Jafer Books 📚
30.7K subscribers
8.07K photos
173 videos
91 files
1.06K links
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ

ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok

ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL

ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
Download Telegram
Forwarded from Natishu
ምናልባት… መንገድ የሕይወት ምሳሌ፣ የ“ትናንት” አስረጂ ማሟሻ እና የ“ዛሬ” ድንበር ጠባቂ እንዲሁም የ“ነገ” ተስፋ ሥሪት ውጤት ይሆን ይሆናል፡፡

ለዚያም ይሆናል… ከ”ትናንት” “ዛሬ” እና ነገ ቅንብብ ያመልጥ በሚሳነው ሕይወታችን… ታመልጥ በማትፈልግ ነፍሳችን… የሥሪቱ አካል ይሆን በወደደ ጠጠር እና አቧሯ አልባ የሀሳብ መንገድ ይገለጥልን የወደድነው ይፈጸም የምንጠብቀው፡፡

ለዚያም ይሆናል… “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” ብዬ ቀን እክድ እወድ የምሆነው… ወይም “ትናንት እመጣለሁ” ስል የዙረት አቅጣጫዬን ከተፈጥሮ የማጣርሰው፡፡

ምናልባት… ተፈጥሮ የእኔ፣ የአንቺ እና የአንተ ስምምነት ይሆን ይሆናልና!
13
በእስጢፋኖስ ኃይለማርያም የተዘጋጀው " የአፋር ምርኮኞች " መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::
12🥰1
#ዞር ብዬ ሳየው

በንጉሤ ተፈራ እምሩ ( ዶክተር
16
" የአዳም ቁጥር " የተሰኘው የምሕረት መስፍን የግጥም መድብል ለንባብ በቃ :: መጽሐፉን በመደብሮቻችን ሁሉ ያገኙታል ::
👍235
በዶክተር አለማየሁ እሸት የተዘጋጀውና ታሪካዊ ልቦለድ ይዘት ያለው " ባህራን " የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::
👍187👎32
" Innovation Media and Communication Strategy for Development " By Neguse Tefera .
4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ አዲስአበባ ኤግዚቢሽን መአከል የሚዘጋጀዉ የንባብ ለሂወት ኤግዚብሽን ደረሰ

ከሀምሌ 24 ጀምሮ በኤግዚቢሽን ማዕከል አይቀርም
🔥1611👍8💯1
New arrivals 🔥🔥

0911932088
0911125324
Call us
Jafer books
5
🥰4
ቅንጫቢ ከ"ሰኞ ማክሰኞ"




... ቤቱን ጥሎ የሚሄደው ለሚስቱ እንዳላት፣ ቢራ ለመቀማመስ አልነበረም፡፡  ሰው የማይበዛበት ካፌ ሄዶ ማሕሌትን ለማግኘት ነው፡፡ ማሕሌትና ሚስቱ ይተዋወቃሉ፡፡ ሚስቱ ግን፣ ከማሕሌት ጋር በሌላ ነገር አትጠረጥረውም፡፡ ካፌ ካገኛት በኋላ ጎተራ የሚገኘው ኮንዶሚኒየሟ ይሄዳሉ፡፡ ሚስቱ ስለዚህ ቤት ማለትም የቤቱ ቁልፍ እንዳለው፣ ከውዱ የቤት ኪራይ ግማሹን መክፈሉን ጨምሮ ምንም አታውቅም፡፡

በሉ ቻው አለ፡፡
ቻው ሚስቱም ልጁም ባንድነት ከዝላያቸው ሳያርፉ እየሣቁ መለሱለት፡፡

የሚስቱ ሁኔታ ከዚህ ቀድሞ የማያውቀው እንግዳ ስሜት አሳደረበት፡፡
የሰው ልጅ አርሶ መብላት ሳይጀምር አንስቶ የነበረው፣ ወንዶች በትዳራቸው ላይ የመወስለት ረጅም ታሪክ ውስጥ፣ እንዲህ ባለ ደስታና ጨዋታ ላይ ያለች ሚስቱን ጥሎ  ከሌላ ሴት ጋር ሊማግጥ የሚወጣ እንደ እኔ ያለ ባል ይኖር ይሆን? ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡


ሌላ ጊዜ፣ ግማሽ ጸጉሯ ከተያያዘበት ላስቲክ አምልጦና ተንጨብሮ፣ ያደፈ ሺቲ ለብሳ ስታጠባ፣ ወይ የእሱን ቱታና ዘልዛላ ቲሸርት ለብሳ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ቆሻሻ ልብስ ስትጎሰጉስ፣ ወይ ወጥ ወጥ እየሸተተች ስትቀቅል፣ ወይ በልጆቹ ልብስ መበከት መነጫነጭ ስትጀምር ነው ጥሏት የሚወጣው፡፡

እንደዚህ በኮረዳነት ዘመኗ ከነበረ ውበቷ ጋር በሚስተካከል ሁኔታ አምራ፣ ሰውነቷ በሰኞ ማክሰኞ ጨዋታ እንደ ልጃገረድ ገላ ያለ ክልካይ እየነጠረ ወጥቶ የሄደበት ጊዜ ትዝ አይለውም፡፡

ባዶ እግሯን ናት፡፡
ቆንጆ ረጅም ሽፎን ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ለጨዋታው እንዲመቻት፣ ከጉልበቷ በላይ ግማሽ ጭኗን እስኪያጋልጠው ጎትታ ይዛው ትጫወታለች፡፡ ቀይና ፈርጣማ ባቷ፣ ቀይ ለስላሳ ጭኗ ከእዚህ በፊት ዐይቶት፣ ከዚህ ቀደም ነክቶት እንደማያውቅ ቀሚሷን በእጇ ንቅናቄ ሽፍን ግልጥ ስታደርገው ያማልላል፡፡  ሦስት ልጆቹን አጥግበው ያጠቡ ጡቶችዋ ገና እንደደረሰች፣ ገና እንደታየች፣ ገና እንደጎመራች ጮርቃ ልጅ አብረዋት ሲዘሉ ስሜት ያባብላሉ፡፡

ሚስቱ በጡት፣ ባትና ጭን ንቅናቄ፣ አማላይና አፍዝ አደንግዝ ፈገግታዋ ሳትፈልግ እየጠራችው መሰለው፡፡
ዛሬ ምን ሆና ነው እንዲህ የምትሆነው?

የእሱ እንዳልሆነች ሁሉ ሰረቅ እያደረገ ደጋግሞ ዐያት፡፡
በኋላ፣ የተከፋፈለ ሐሳቡን ከቀጠሮው ጋር አስታርቆ ከግቢው ሲወጣ ዝላይዋን አላቆመችም ነበር፡፡
የዛሬውን ቀጠሮ ለመያዝ ያሳለፈውን ድብብቆሽ አሰበ፡፡

በመጀመሪያ ከሚስቱ ተደብቆ ተከታታይ ቴክስቶችን  ላከ፡፡ የተላከው ቴክስት መድረስና አለመድረሱን ሳያረጋግጥ ልጆቹ፣ ጌም እንጫወት ብለው ወስደው ስልኩ እጇ ቢገባና የላኩትን ቴክስት ብታነበውስ? የሚል ሐሳብ ድቅን አለበት፡፡ የተላከውን ቴክስት ወዲያው አጠፋ፡፡

አሁንም ስልኩ እጁ በሌለበት (አሁንም ልጆቹ ጌም እንጫወት ብለው ወስደው)፣ ስልኩን መነጣጠቅ፣ መጣላትና ማልቀስ ቢጀምሩ ከሚነጣጠቁት ልጆቿ ቀምታ (ብዙ ጊዜ የሚሆን ነገር ነው) ለእሱ ልትመልስለት ስትል፣ ለተላከው ቴክስት የማሕሌት ምላሽ ቢገባና ብታየውስ? የሚል ሥጋት ሽው ሲለው፣ አይ ብደውልላት ይሻላል ብሎ ተነሳ፡፡  ወሬው እንዳይሰማ በረንዳ ላይ ወጥቶ በተደጋጋሚ ለማሕሌት ደወለ፣

የደውሉላቸው ደንበኛ መሥመሩን እየተነጋገሩበት ስለሆነ በመሥመር ላይ ይጠብቁ

ይሄ መልእክት ለደቂቃዎች ተደጋገመ (ከማን አባቷ ጋር እያወራች ነው? ብሎ ሲያስብ፣ ቅናት ቢጤ ሽው አለው)፡፡ ቆየት ብሎ ደወለ፣
የደወሉላቸው ደንበኛ መሥመር ስለተያዘ
እሷም ለመደወል እየሞከረች ነው ብሎ አሰበና ትንሽ ጠብቆ ድጋሚ ደወለ፤ አነሳች፡፡
ማሕሌት፣ ሃይ ማሬ ከማለቷ፣
የበረንዳው በር ተከፍቶ ሚስቱ፣ በዚህ ሰዐት እዚህ  በረንዳ ላይ ምን ታደርጋለህ? ግባ እንጂ? ብርድ እኮ ነው አለችው፡፡

ስልኩን የማሕሌት ጆሮ ላይ ዘጋና፣ ለሚስቱ፣ እሺ ብሎ ቀጥታ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባና በሩን ቆለፈ፡፡   የመቀመጫውን ክዳን ዘግቶ እንደ ወንበር ሽንት ቤቱ መቀመጫ ላይ ዐረፍ አለ፡፡
ደወለ፣

የደወሉላቸው ደንበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ስለሆኑ ትንሽ ቆይተው ይደውሉ

ደሙ ፈላ፡፡ እንደገና ደወለ፡፡ ይጠራል ግን አታነሳም፡፡
እንደገና ደወለ፣
የደወሉላቸው ደንበኛ መሥመር ስለተያዘ…
እሷም ለመደወል እየሞከረች ነው ብሎ አሰበ፡፡ ደወለች፡፡

ሊያነሳ ሲል፣ አሞሃል እንዴ? በሰላም ነው ይህን ያህል ሰዐት ሚስቱ ነበረች፡፡
ደህና ነኝ ደህና ነኝ አላት፡፡ ተመልሳ መሄዷን ለማረጋገጥ ኮቴዋ ከበሩ እስኪረቅ ጠበቀና ስልኩን አነሳ፡፡ ለሹክሹታ በቀረበ ድምፅ ማሕሌትን አዋራና ስልኩን ዘጋው፡፡ እንዲህ መከራውን ዐይቶ ነው እንግዲህ ቀጠሮውን የያዘው፡፡

0
የተቀጣጠሩበት ካፌ ደርሶ ማሕሌትን ለመጠበቅ ቁጭ አለ፡፡ ብዙ ግዜ፣ እሷ ስለምታረፍድ፣ እንደተቀመጠ የሚያደርገው ነገር፣
ደርሻለሁ የት ነሽ? የሚል ቴክስት መላክ ነው፡፡ ሁሌ፣ እስክትመጣ፤ መጥታ ተያይዘው እስኪሄዱ፤ ሄደው ለብቻቸው እስኪሆኑ ድረስ፣ ይጓጓል፡፡
ስለዚህ፣   ደርሻለሁ የት ነሽ? ከሚለው ቴክስት በኋላ፣ ይደውላል፤ ከዛ በተከታታይ ቴክስት ያጣድፋታል፡፡
ዛሬ ግን፣ ባትመጣ ሲል ተመኘ፡፡ ገረመው፡፡ እስከዛሬ እንዲህ ያለ ስሜት ተሰምቶት አያውቅም፡፡
12👍2
Forwarded from Jafer Books 📚
New arrivals 🔥🔥

0911932088
0911125324
Call us
Jafer books
5