Jafer Books 📚
30.7K subscribers
8.06K photos
173 videos
91 files
1.06K links
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ

ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok

ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL

ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
Download Telegram
አለሁ እንዳላችሁኝ አለሁ ይበላችሁ።
እንዳደመቃችሁኝ ያድምቃችሁ።



ትላንት፣

" እኔም ጋ ና፣ እኔም ጋ ንይ" በበዛበት በዚህ የውክቢያ ዘመን፣ የክረምቱን ቁር ሳትፈሩ፣ በዝናቡ ሳትበገሩ፣ ይመሻል በሚል ስጋት ሳትያዙ አብራችሁን ለማምሸት ለመጣችሁ ሁሉ ቁና ሙሉ ምስጋና።



ሞልቶላችሁ መምጣት ላቻላችሁ፣ ርቀት ላገዳችሁ ነገር ግን በመልእክት ላጥለቀለቃችሁኝ፣ መፅሐፌን በመልእክተኛ ለገዛችሁ፣ ለእናንተም ቁና ሙሉ ምስጋና።



አንባቢዎቼ ፣

ትላንት፣ ዛሬ፣ ወደፊትም፣ የምትሰጡኝ ድጋፍ ጉልበቴ ፣ ስዶለዶም በትችት መሳላችሁ የመሻሻሌ ምክንያት ነውና አመሰግናለሁ ።



አምስቱም መፅሐፍት አሳታሚዬና አከፋፋዬ ጃዕፋር ባለበት ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ ይገኛሉ።



አለሁ እንዳላችሁኝ አለሁ ይበላችሁ።
እንዳደመቃችሁኝ ያድምቃችሁ።

አሜን አትሉም ወይ ሰው ሲመርቃችሁ?
❤47🥰8🙏2👍1
የደራሲ ሕይወት እምሻው የድርሰት ስራዎችን በድጋሚ በጥራት አሳትመን ለንባብ አብቅተናቸዋል :: መጻሕፍቱን በሁሉም መደብሮቻችን ይገኛሉ ::

ጃዕፈር መጻሕፍት !
❤21
መፅሐፍ ከ400 በላይ መቃዎሚያን የሚመለከቱ በሰበር እና በፌዴራሽን ምክር ቤት የተሰጡ ውሳኔዎች በማከተት የተዘጋጀ ሲሆን እነሆ ለቅምሻ፡-

በሰበር የተቀመሩ የፍ/ቤት ስልጣኖች ለምሳሌ መብቱ በሰበር ውሳኔ የተነካበት ሰው ጥቅሙን የሚያስከብርበት አግባብ

ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.5 ወጭ ያሉ በድጋሜ ክስ ማቅረብን የሚከለከልባቸው ሁነቶች

የዕቁብ ገንዘብ እና የንግድ ሕጎች የይርጋ ጊዜ

ለልማት መሬቱ የተወሰደበት ሰው የጉዳት ካሳ የመጠየቂያ የይርጋ ጊዜ

ተወላጅነትን ለመካድ በእናት እና በአባት በሰበር የተወሰነው የይርጋው ጊዜው ልዩነት ተተችቶ ቀርቧል

በ ADR ላይ ከፍ/ቤት ስልጣን፣ ጉዳዩ በውሳኔ ያለቀ ነው እና ከይርጋ አንጻር በሰፊው በፌዴራሽን ምክር ቤት ወሳኔ ጭምር ተደሷል

በውርስ፣ በባልና ሚስት እንዲሁም በሌሎች ውስን ጉዳዮች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.216 የማይሰራበት በ7 ሰበር ዳኞች በተሰጠው ውሳኔ ጭምር ተዳሷል፡፡
👍12❤7🔥3
በደራሲ መልካሙ ተፈራ የተዘጋጀው " የሕይወት መንገድ " የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ :: ይህ መጽሐፍ በዋናነት " አምላክ የለም " ለሚሉ ኢ-አማኞች የአምላክን መኖር እየገለጸ በተለያዩ መንገዶች በፈጣሪ አምላክ መገኘት/ በመኖሩ ጉዳይ ጥያቄዎች ሐሳቦችን ለመሞገት የቀረበ ሲሆን የሰው ልጅ የዘለዓለምን ሕይወት የሚያገኝበትንም መንገድ ለማሳየት ይሞክራል ::
👍45❤16🔥4🕊2🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንዴት ሰንብታችኋል?

ዓርብ ዕለት ስንሰበሰብ የነበረው ድባብ በደምሳሳው ይህንን ይመስል ነበር፡፡
መፅሐፍቱ በሁሉም የጃፋር መደብሮች በመሸጥ ላይ ናቸው፡፡
🥰9👍4❤3
" የፍልስፍና መንገድ " የተሰኘው የአስራት አብርሃም መጽሐፍ ለሶስተኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ ቀርቧል :: መጽሐፉ በሁሉም መደብሮቻችን ይገኛል ::
❤12👍7
“የዩቲዩብ ሚስጥሮች “የተሰኘዉ የአቤል ብርሀኑ መጸሐፍ በመደብራችን ያገኙታል
😍13👎7❤3
በአለም አቀፍ ደረጃ ዝናን ያተረፉ እነዚህን መጻሕፍት ለሀገር ውስጥ ንባብ በጥራት ታትመው ለንናብ ቀርበዋል :: ሁሉንም መጻሕፍት በሁሉም መደብሮቻዥን ያገኙታል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት !
❤12👍8
የደጃዝማች ከበደ ተሰማ " ነበር እንዳይረሳ ከታሪክ ማስታወሻ ባሻገር "

ይህ መጽሐፍ፣ ደጃዝማች ከበደ ተሰማ እጅግ ጥሩ ተቀባይነት ያገኘውን የታሪክ ማስታወሻ የተሰኘውን መጽሐፋቸውን 1962 ዓ.ም  ካሳተሙ በኋላ በተለያየ ጎዜ በታሪክ ጉዳይ ላይ የጻፏቸውን ማስታወሻዎች አንድ ጋር አሰባስቦ ያቀርባል ::

እነዚህን ጽሑፎች ደራሲው አንድ ጋር ጠርዘው አስቀምጠዋቸው ሰለነበር ፣ ካለፉ በኋላ ልጆቻቸው ጥራዙን ሲያገኙት ዋጋ ያለው ሥራ መሆኑን በመረዳት ተገቢው አርትኦት ከተደረገበት በኋላ እንዲታተም ይወስናሉ።

    áŠ¨áŒ˝áˆ‘áŽá‰š መረዳት እንደሚቻለው ፣የደራሲው ዓላማ በታሪክ ማስታወሻ ውስጥ ሊካተቱ ሲገባቸው የልተካተቱ ሁነቶችን ለትውልድ ለማቅረብ ሲሆን ፣በተጨማሪም 1953 ዓ.ም ያልተሳካ  መፈንቅለ-መንግስት ( "የታኅሣሥ ግርግር " የሚባለው-)ሲካሄድ በመንግስት ወገን ንቁ ተዋናይ ሰለነበሩ ፣ ያዩትን ፣የሰሙትን እና የታዘቡትን ጽፎ ለታሪክ ለማስቀረት ነው ።
ስለዚህ ይህ አዲሱ መጽሐፋቸው ልክ እንደቀድሞው ሥራቸው ፣ቀዳማይ ምንጭ ተደርጎ የሚወሰድ በጣም ጠቃሚ  ሰነድ ነው ። እያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ እስካሁን የማናውቃቸው አዳዲስ መረጃዎች የተካተቱ ሲሆን ፣እነዚህም መረጃዎች ደራሲው በቀጥታ ከተካፈሉባቸው  ሁነቶች የተወሰዱ ፣ወይም ከተካፈሉ ሰዎች የሰሟቸው መሆኑን ፣በተደጋጋሚ ይገልጻሉ ።
 
    ከሁሉም በላይ የሚገርመው ፣በዘመኑ ሰለ"ታሪክ"ሲታሰብ ፣ሲወራ ፣ሲጻፍ "ታሪክ " ተብለው የማይገመቱ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ማካተታቸውን ነው።

ለምሳሌ ፣የአዲስ አበባ አሰፋፈር ፣የሴትኛ አዳሪዎችን ሁኔታ ፣የጠላ ሻጮችን አሰራር (አዝማሪ ጻዲቄ ሳትቀር ) የሌባ ሻይን አሰራር  ዘርዘር አድርጎ በመተረክ ፣ ከዚህ በፊት አንበነው የማናውቀውን የአዲስ አበቤዋች ን ኑሮ አሰነብበውናል ።

ከመጽሐፉ ጀርባ የሚነበብ ።
❤10👍9