"የዲጂታል ሽግግር ምርጫ ሳይሆን የልማታችን ዋና ማዕከል ነው!" - የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ
ጳጉሜን 5/2018 ዓ/ም፤ አዲስ አበባ:- "ነገን ዛሬ መገንባት፣ ዲጂታል ሽግግር፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የምግብ ሉዓላዊነትና ሀገራዊ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ መሪ ሃሳብ "የነገ ቀን" (ጳጉሜን 5) በሳይንስ ሙዚየም በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የዕለቱ ዋና ዓላማ የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዛሬ ላይ ጽኑ መሠረት መጣልን ማሳሰብ ሲሆን፣ በዚህም የዲጂታል ሽግግር እና የሳይበር ደህንነት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በስፋት ተመላክቷል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግሯን በብቃት ለመምራት የሚያስችላትን ግልጽ ስትራቴጂ ነድፋ ወደ ተግባር መግባቷን ገልጸዋል። ይህንኑ ስትራቴጂ ስኬታማ ለማድረግ የሰው ሃይል ልማት፣ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና የሳይበር ደህንነት በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራባቸው መሆኑን አብራርተዋል።
ተጨማሪተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA

❤4🥰1
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የ2019 አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንዲሁም ለተቋሙ አመራሮችና አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና ፣ ሀገራዊ አንድነታችን የሚጠናከርበት፣ የተጀመሩት የልማትና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎቻችን ወደ ላቀ ደረጃ የሚሸጋገሩበት የስኬት ዓመት እንዲሆን ዋና ዳይሬክተሯ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ወ/ሮ ትዕግስት በመልዕክታቸው ፣ ባሳለፍነው የበጀት ዓመት የተቋሙ አመራር እና አባላት ሌት ተቀን ሳይታክቱ የሀገራችንን የሳይበር ምህዳር ደህንነቱን በመጠበቅና ሀገራዊ የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ለተመዘገበዉ ስኬት እና ውጤት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በ2019 አዲስ ዓመትም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዕድሎችን በመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ስጋቶችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የተጀመሩትን ሀገራዊ የሳይበር አቅም ግንባታዎች አስተዳደሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ወቅቱ የበዓል ወቅት እንደመሆኑ በኦንላይን ገበያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ እና በዲጂታል የክፍያ ስርዓቶች ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ማጭበርበሮችና የመረጃ ስርቆቶች የመጨመር ዝንባሌ ያላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡና ተቋማት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በተለይም በኤስኤምኤስ (SMS)፣ በዋትስ አፕ፣ በቴሌግራም እና በኢሜይል የሚላኩ ያልተረጋገጡና አጠራጣሪ ሊንኮችን (Phishing links) ከመክፈት ሊቆጠብ እንደሚገባ አደራ ብለዋል።

❤17🙏5👍3👏1🤔1
ከ3,000 በላይ ድሮኖች፣ አንድ ደማቅ ሰማይ!
የ2019 አዲስ ዓመት አቀባበል በታሪካዊ የድሮን ሾው ደምቆ አምሽቷል። በቴክኖሎጂ እና በብርሃን የተሸለመው ሰማያችን የአዲሱ ዘመን ተስፋችን ማብሪያ ሆኗል።
#droneshow
#INSA
#Newyear
#2019E.C

❤12👍7🎉2
በአዲስ መንፈስ ወደ ትምህርት ቤት፡ የዲጂታል ዘመን ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸው 5 የሳይበር ጥንቃቄዎች
ለውድ የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣት ተማሪዎች፤ እንኳን ለ2019 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!
አዲሱ ዓመት አዲስ እቅድ የምናወጣበት፣ አሮጌ ልማዶቻችንን ትተን በታደሰ መንፈስ ወደ ትምህርታችን የምንመለስበት ውብ ወቅት ነው። ዛሬ ትምህርታችን ከቴክኖሎጂ እና ከኢንተርኔት ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው። የትምህርት መረጃዎችን ለማግኘት፣ የምርምር ስራዎችን ለመስራት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ለመቅሰም ኢንተርኔት የማይተካ ሚና አለው። ይሁን እንጂ የዲጂታል ዓለም ከጥቅሙ ጎን ለጎን የተለያዩ የሳይበር አደጋዎችን ይዞ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል።
በሀገራችን የኢንተርኔት ተደራሽነት እየሰፋ በሄደ ቁጥር፣ ህጻናት እና ወጣቶች (ተማሪዎች) የሳይበር አጥቂዎች ቀዳሚ ዒላማ እየሆኑ መጥተዋል። ስለዚህ የ2019 የትምህርት ዓመት ስንጀምር የሚከተሉትን የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ንቃት እቅዶች በማውጣት ራሳችንን እንጠብቅ፡
ኢንተርኔትን ለዕውቀት ብቻ ተጠቀሙ: አዲሱን ዓመት ዲጂታል አሻራችንን ለትምህርት ብቻ እንድናውለው እናቅድ። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለጥናት እና ለአእምሮ ማበልጸጊያ እንጂ ትምህርታችንን እንዲያዘናጋን አንፍቀድ።

❤13🤔1
አሁን ያለው ዝግጅታችን በቂ አይደለም! — ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለአስቸኳይ የሳይበር መከላከል ጥሪ አቀረቡ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የሆኑ የቴክኖሎጂ ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን፤ በተለይም ደግሞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት የተቀናጀና የጋራ የሳይበር መከላከል እርምጃ (Defensive Surge) መወሰድ እንዳለበት አሳሰቡ።
ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ ኦፕንኤአይ (OpenAI)፣ አልፋቤት (Alphabet)፣ አንትሮፒክ (Anthropic) እና አማዞን (Amazon) ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፈጸሙ የሚገኙ የሳይበር ጥቃቶች ስፋትና ረቂቅነት እየጨመረ እንደሚሄድ በማስጠንቀቅ ጥቃቶቹን በጋራ ለመመከት የሚያስችሉ ሦስት ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል፦
አሁን ያለው አደረጃጀትና ዝግጅት በቂ አለመሆኑን መገንዘብ፦ ነባሩ የደህንነት አሰራር እየተወሳሰቡ የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት በቂ አለመሆኑን አምኖ መቀበል።
የመከላከል አቅምን በ-AI ቴክኖሎጂ ማብቃት፦ የሳይበር ደህንነት ጠባቂዎችንና ተቋማትን በዘመናዊ የ-AI የመከላከል አቅም ማስታጠቅ።
የተቀናጀና የጋራ ምላሽ መስጠት፦ በሁሉም እርከኖች የተቀናጀ የመከላከል ምላሽ መፍጠር።
ኩባንያዎቹ ወደፊት ሊወሰዱ ይገባል ያሏቸውን 4 ዋና ዋና እርምጃዎችም ጠቁመዋል፦
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA

❤1🤩1