INSA Cyber Talent Center
9.84K subscribers
216 photos
28 videos
60 files
108 links
We work to inspire, cultivat, develop and hire talents in cyber ecosystem.
Download Telegram
INSA Cyber Talent Center
Malware Mastery session screen record @insactc @cteinsa
How was our Malware Mastery class?

🔥 React if you want to have another session.

@insactc
@cteinsa
22🔥11😁4🌚1
🚀 2018 INSA Cyber Talent Summer Camp Challenge is coming soon!

💎If you are passionate about cybersecurity and related technology fields, this is a great opportunity for you.

Please invite and add your friends, classmates, and anyone who has interest, passion and talent in cyber and related technology streams.

📢 Join our Telegram communities for updates and information:
@insactc
@cteinsa
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥4121🏆4👨‍💻4
MARCH 14, DID YOU KNOW?

March 14 is called Pi Day (π) because the date 3/14 matches the famous number 3.14. Have a great weekend! insactc
23😁207🤓5🤨3👍1
How Programming Language Start
In 1946, the first electronic computer changed the course of technology.

Six women—Kathleen McNulty, Jean Jennings Bartik, Betty Snyder, Marlyn Wescoff, Frances Bilas, and Ruth Lichterman—designed the programming methods that allowed ENIAC to execute complex calculations. At the time, there were no programming languages, no compilers, and no established field of software engineering.

They worked directly with the machine’s architecture: configuring switches, cables, and logic flows to translate mathematical problems into operational instructions.

Many of the concepts they developed, structured problem decomposition, execution sequencing, and logical debugging, became foundational practices in modern software development.
insactc
🔥2612
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከፍተኛ መኮንኖች በኢመደአ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሥር የሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከፍተኛ መኮንኖችና አመራሮች በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና መሥሪያ ቤት ትምህርታዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ።

ጉብኝቱ በዋናነት ከፍተኛ መኮንኖቹ በኮሌጅ ቆይታቸው በክፍል ውስጥ የተማሩትን የደህንነትና የጦርነት ንደፈ-ሃሳብ (Theory) በትግባር ላይ ካለው የቴክኖሎጂ አቅም ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው። በተለይም በዘመናዊው ዓለም የጦርነት አውድ ውስጥ አንዱና ዋነኛው እየሆነ የመጣውን የሳይበር የጦር አውድ (Cyber Warfare) በትክክል ለመገንዘብና የሀገሪቱን የሳይበር መከላከያ ዝግጁነት ለመመልከት ጉብኝቱ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ለኮሌጁ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፤ ኢመደአ የሀገሪቱን ቁልፍ የመረጃ መሠረተ-ልማቶች ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችንና የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት አስረድተዋል።

ከፍተኛ መኮንኖቹ በጉኝታቸው ወቅት በሰጡት አስተያየት፤ የወደፊቱ ጦርነት ከምድር፣ ከባህርና ከአየር ባለፈ በሳይበር ምህዳር ላይ የሚወሰን በመሆኑ፣ እንዲህ አይነት የልምድ ልውውጦች ለሀገራዊ ደህንነት ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
🔥1510💩2❤‍🔥1
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የ"INSA ሳይበር ታለንት ሴንተርን" በማንቀሳቀስ የኢትዮጵያን የዲጂታል ፈጠራ ባለሙያዎችን በማፍራት እና ብሄራዊ የሳይበር ደህንነትን በማጠናከር ላይ ይገኛል። ይህ ማዕከል በሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ፕሮግራሞቹ በርካታ ወጣት ተሰጥኦዎችን በዘመናዊ የሳይበር እና ዲጂታል ክህሎቶች እያሰለጠነ ይገኛል።
ከ4ኛው ዙር የINSA ሳይበር ታለንት ሴንተር ፕሮግራም ከወጡ ውጤቶች መካከል አንዱ ሰኒቮ (Senivo) እውቀትን እና ዲጂታል አገልግሎቶችን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የቴክኖሎጂ startup ሲሆን፣ የINSA ሳይበር ታለንት ሴንተር ብሄራዊ መድረክ በመሆን ብቅ የሚሉ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦዎችን በማበረታታት እና በማፍራት እንደ ሰኒቮ ያሉ ስኬታማ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን በመፍጠር ለበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በፈጠራ የተሞላች ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመፋጠር እንዲሁም ለዲጂታል 2030 (Digital 2030) ስትራቴጂ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል።
#digitalethiopia2030 #incubation #startup #insa #talent
https://www.linkedin.com/posts/bishaw-beyene-3458b816b_digitalethiopia2030-incubation-startup-ugcPost-7440295756814761984-7g5B?utm_source=share&utm_medium=member_android&rcm=ACoAACkq86sBpR5w30BlAuQ2aOSHxe-xQypSyUg
7
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም፦ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፣ 1447ኛውን የዒድ አል-ፈጥር በዓል በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እና ለአስተዳደሩ ሰራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ዋና ዳይሬክተሯ በመልዕክታቸው፤ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት የሚከበረው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት ያሳየውን የመረዳዳት፣ የመተዛዘንና የአብሮነት ድንቅ ኢትዮጵያዊ እሴት በማስቀጠል፣ አቅመ ደካማ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ በዓሉን በኅብረትና በደስታ ሊያከብር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት አያይዘውም፣ አስተዳደሩ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እና ለ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ ስኬት ግንባር ቀደም ሚናውን በቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ምህዳር መገንባት ለሀገራዊ ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ኢመደአ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን ለመጠበቅ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በበዓላት ወቅት የሚከሰቱ የሳይበር ጥቃቶችን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በተለይም በእንዲህ ዓይነት ወቅት ሃሰተኛ ማስታወቂያዎች፣ ሽልማቶችና አሳሳች የሊንክ ማጭበርበሮች (Phishing) የሚፈጸሙ የሳይበር...

ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
13🔥4🤨2🥱1
የኢድ እንግዳ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፤ የ2018 ዓ/ም የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በቆይታቸው የሥራና የአመራር ሕወታቸውን፤ አጠቃላይ ከሕይወት ጉዟቸው ጋር በማዋዛት ጥሩ ቆይታ አድርገዋል፡፡
ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ ያደረጉትን ቆይታ የኢድ አልፈጥር ዕለት ዓርብ መጋቢት 11/2018 ዓ/ም በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ከቀኑ 5:00 ላይ እንዲከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
https://www.facebook.com/share/p/16ym2hr6Km/
11🔥3