INSA Cyber Talent Center
5.01K subscribers
150 photos
24 videos
56 files
60 links
We work to inspire, cultivat, develop and hire talents in cyber ecosystem.
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" በስልጠና ማጠናቀቂያ ወቅት ያገኙት ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ለመማር በሚወዳደሩበት ወቅት 10 በመቶ ውጤት እንዲኖረው እናደርጋለን "- የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ/ም የክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 629 ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት አስመረቋል።

ታዳጊዎቹ በክረምት መርሃ ግብር የሰለጠኑት ፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በቴክኖሎጂ ልማት፣
- በኢምቤድድ ሲስተም፣ እና በኤሮስፔስ ዘርፎች ነው።

ላለፉት ሦስት አመታት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር፤ በ2017 ዓ/ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 76 ልጆች ሰልጥነው መመረቅ መቻላቸው ተገልጿል።

ስልጠናውን የተከታተሉት ታዳጊዎች ከኢለመንተሪ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ናቸው ።

ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን ከኢንሳ በተጨማሪ  በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በማጠናቀቂያው ወቅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመከታተል በሚወዳደሩበት ወቅት የመቁረጫው ነጥብ ዝቅ እንደሚያደረግላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ግቢ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል ስልጠናውን ኮርስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በመንገር ችግሮችን መፍታት ከመቻላቸውም በላይ ፕሮዳክቶችን ይዘው መጥተዋል።

የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት እና መሸጥ የሚችሉ ፕሮዳክቶችን ይዘው ወጥተዋል።

እኛ ፈተና ፈትነን ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑ ይታወቃል ፈተና ፈትነን ስንቀበል የ 12 ውጤት እና የመግቢያ ፈተና ውጤት ነው የምናየው።

በእዚህ ስልጠና ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥተው በግቢያችን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የወሰዱት ሰርተፍኬት በግቢያችን ለመማር በሚያመለክቱበት ወቅት ቫልዩ ይኖረዋል።

ከእዚህ ቀደም ስናወዳድር 50 በመቶ 12 ክፍል ውጤት 50 በመቶ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እንመለከት ነበር አሁን 10 በመቶ በስልጠና ማጠናቀቂያው ወቅት ያገኙትን ሰርተፍኬት እንዲይዝ  እናደርጋለን።

አንድ ላይ ተደምሮ ከመቶ ሲያዝ የመቁረጫ ነጥብ ላይ ባመጡት ቁጥር ዝቅ ያደረግላቸዋል ፣ ልዩ ኮታ ይሰጣቸዋል ማለት ነው ።

ይህንን እድል አምናም ሰጥተናል ዘንድሮ ከገቡ መካከልም ይህንን እድል ያገኙ አሉ በሚቀጥለው አመትም ይህ ይቀጥላል።

ሁለተኛ እዚህ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮዳክቶችን አውጥተዋል እኛ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽን እና ኢንኩቤሽን ሃብ ሰርተናል ይህ ሃብ ወደ 189 ስታርታፖችን መቀበል ይችላል።

እነዚህ ስታርታፖች ከተለያዩ ቦታ እና ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው እና መሸጫ ቦታ ያጡ ሰዎችን የምናሰባስብበት ቦታ ነው።

ይህንን ስፔስ (ቦታ) ስልጠናውን ለተከታተሉ ሰዎች ለሰሯቸው ምርቶች (ፕሮዳክቶች) እናቀርባለን።

የምናቀርበው በሁለት አይነት መንገድ ነው አቅሙ ኖሯቸው በራሳችን እንቀጥል ካሉ የተወሰነ ኪራይ እናስከፍላለን ፣ምንም አቅም የለንም የሚሉ ካሉ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከዩኒቨርሲቲውም አንድ ላይ አድርገን ድጋፍ በማድረግ ምርታቸው ወደ ገበያ እንዲወጣ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
37👍4🤣1
INSA Cyber Talent Center pinned «https://youtu.be/M8Sr3EkprdM?si=LqeXI4D97BDgYe7H»
“ሴኒቮ”
በትምህርት፣ ደራሲያን እና አንባቢዎች መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ ዲጂታል መድረክ


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከተሳተፉና ከተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዱ አሌክሳንደር ሳሙኤል ነው፡፡ አሌክሳንደር በሰመር ካምፕ ቆይታው “ሰኒቮ” የተሰኘ የዲጂታል ፕላትፎርም አበልጽጓል፡፡

ሴኒቮ በትምህርት፣ ደራሲያን እና አንባቢዎች መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ ዲጂታል መድረክ ነው:: ከኢትዮጵያ ጀምሮ ሙሉ አፍሪካን አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ የሚችል የዲጂታል መድረክ ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም ተማሪዎችን፣ መምህራን እና አዲስ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን በቀላሉ መፅሃፍቶችን፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችን እና የኢ-መማሪያ በአንድ ቦታ በማቅረብ ትውልዱን በእውቀት የታነጸ ማድረግ ነው። ሰኒቮ ትብብርን፣ ፈጠራን እና የእውቀት መጋራትን የሚያበረታታ የዲጂታል ከባቢ ለመምህራን እና ለተማሪዎችን መፍጠር የቻለ ነው።

ከትምህርት ባሻገር፣ በአህጉሪቱ ያሉ የደራሲ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል የሚያስችል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የዲጂታል መድረክ በማቅረብ የአፍሪካ ደራሲያንን ለመደገፍ የሚያስችል ነው። በሰኒቮ በኩል፣ ተማሪዎች የሚፈልጉትን ማድረግ፣ መፍጠር ይችላሉ፡፡ የተለያዩ የአካዳሚክ እና ትምህርታዊ ያልሆኑ መጽሃፍቶችን ማግኘት፤ በኦንላይን ላይ የመማሪያ ክፍለ ጊዜዎች እና ኮርሶች ለተማሪዎች ብቁ ከሆኑ አስተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች ጋር ይገናኛሉ። ፕላትፎርሙን በመጠቀም ደራሲዎች እና መምህራን ስራቸውን በቀላሉ ማተም፣ መሸጥ እና ማጋራት
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
👏569🔥5👍1
ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን መቆጣጠሪ ሲስተም (Anti-Money Laundry - AML)

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከተሳተፉና ከተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዷ ናኦሚ ጎዝጉዜ ናት፡፡ ናኦሚ በሰመር ካምፕ ቆይታዋ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ሲስተም (Anti-Money Laundry - AML) አበልጽጋለች፡፡

ይህ ፕሮጀክት የገንዘብ ማጠብን (Money laundry) በህገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብን ለመከላከል ታስቦ የተሰራ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ ስርዓት አጠራጣሪ ወይም ሕገ-ወጥ ወይም ያልተለመዱ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን ወይም ግብይቶችን ይከታተላል፤ ይለያል።  ከዚህም ባሻገር ለህግ አስከባሪዎች ምርመራን በማቅለል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 629 ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች የተመረቁ ሲሆን፤ ተመራቂዎቹ በግልና በቡድን በመሆን ሰላሳ አንድ (31) ችግር ፈቺ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ሰርተዋል፡፡
በተመራቂዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
🔥6017👏16🤬8💩6👍5💔5🙉1
ንስርኮፕ - ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት የሚያስችል ሲስተም

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከተሳተፉና ከተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዱ ስለሺ አብርሃም ነው፡፡ ስለሺ በሰመር ካምፕ ቆይታው ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት የሚያስችል ንስርኮፕ (NISIRCOP) የተሰኘ ሲስተም አበልጽጓል፡፡

ይህ ሲስተም በተለያየ ጊዜና ቦታ የተከሰቱ የወንጀል ድርጊቶችን ከተፈጸሙበት ቦታ፣ ጊዜና የወንጀል ዓይነት ጋር በማስተባበር የወንጀል ትንተና እና ስታትስቲክስ ሰርቶ ለወንጀል ክትትልና ምርመራ አካላት ያቀርባል፡፡ በቀረበው ስታትስቲካዊ መረጃ በመመስረት ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራን አስቀድሞ ለመስራት አስፈላጊውን የሰው ኃይል በተገቢው ቦታና ሰዓት ለመመደብ ያስችላል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 629 ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች የተመረቁ ሲሆን፤ ተመራቂዎቹ በግልና በቡድን በመሆን ሰላሳ አንድ (31) ችግር ፈቺ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ሰርተዋል፡፡
በተመራቂዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
👍32👏1512🤡3💩2🤬1🍾1
Dear INSA Talent Center Community,

We’re excited to announce that INSA’s official LinkedIn page is now active and engaging! 🎉
Follow us and be part of a growing professional network where you can:

Stay updated on INSA’s latest programs, projects, and national cyber initiatives
Gain insights and tips on cybersecurity, digital innovation, and technology trends
Explore opportunities for collaboration, learning, and professional growth
We kindly encourage you to follow, engage, and share the page with your network — your support helps us expand Ethiopia’s digital security community and reach more talents like you.
🔗 Visit and follow us now: https://www.linkedin.com/company/information-network-security-agency/
 
Together, let’s #SecureEthiopiasDigitalFuture!
Warm regards,
9🙏4🤝2🫡2😁1
INSA Cyber Talent Center pinned «Dear INSA Talent Center Community, We’re excited to announce that INSA’s official LinkedIn page is now active and engaging! 🎉 Follow us and be part of a growing professional network where you can: Stay updated on INSA’s latest programs, projects, and national…»
Care.et (National health record management system)

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከተሳተፉና ከተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዷ ኢናስ ወንድም ፍስሃ ናት፡፡ ኢናስ በሰመር ካምፕ ቆይታው የሀገራችንን የጤና እንክብካቤን ለማዘመን የሚያስችል Care.et (National health record management system) ፕላትፎርም አበልጽጋለች፡፡

Care.et የጤና እንክብካቤን ለማዘመን፣ የጤና አስተዳዳሪዎች፣ የሆስፒታሎችን፣ የክሊኒኮችን፣ የላብራቶሪ እና የፋርማሲዎችን ሥራ ከአንድ ቦታ ሆነው እንዲቆጣጠሩ ለመርዳት የተነደፈ ዲጂታል ፕላትፎርም ነው። የጤና ባለሙያዎች በብቃት ሥራቸውን እንዲተገብሩ የሚያስችሏቸውን ዳሽቦርዶች በማቅረብና የታካሚ መዝገቦችን በመያዝ፣ ቀጠሮዎችን፣ የላብራቶሪ ውጤቶችን እና የመድሃኒት ማዘዣዎችን ያዘጋጃል። ይህ ፕላትፎርም ለዶክተሮች፣ ላብራቶሪ ቴክኒሻኖች፣ ለፋርማሲስቶች፣ ክሊኒክ አስተዳዳሪዎች ሥራን ያቀላል፤ እንዲሁም ለታካሚው ወጥ የሆነ የህክምና ታሪኩን እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 629 ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች የተመረቁ ሲሆን፤ ተመራቂዎቹ በግልና በቡድን በመሆን ሰላሳ አንድ (31) ችግር ፈቺ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ሰርተዋል፡፡
በተመራቂዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
29👏6🙏1
Get ready to:
⚡️ Explore the world of cyber threats and online safety
🧠 Learn ethical hacking basics and real-life protection tips
🎯 Discover career opportunities in cybersecurity
🎁 Win special gifts and giveaways for top participants and quiz champions!

This is your chance to learn, compete, and win while helping make AASTU a more Cyber-Aware Campus! 💪

📢 Event details coming soon — stay tuned right here! 👀

https://t.me/AASTU_CyberClub

#CyberSecureAASTU #AASTUCyberClub
#INSA #AAST #CyberAwareness
#DigitalSafety #StayTuned #GiveawayAlert
22🔥9💩3💔2🤬1
Forwarded from Tech excellence Center
ከ0 እስከ 6 ዓመት ባለው ጊዜ የምናሳልፋቸው ልምዶችና ከወላጆቻችን ጋር ያለን ግንኙነት የቀሪ ህይወታችንን ስብዕና ይቀርፃሉ።በልጅነትታችን ፍላጎታችን ካልተሟላ፤ወይም ከተጨቆንን ወይ ደግሞ ከሰዎች ከተገለልን ትልቅ ስንሆን ወደ ጭንቀት፤ድብርት እና ሌሎች ህመሞች ውስጥ እንገባለን።ፍሮይድ እንደሚለው በልጅነታችን የምናሳልፈው ህይወት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ወሳኝ ነው።

@studtsup
29👍145🔥2
አፋልጉኝ!
ነፃ ማንነት ነጻ መንገድ
ወደ ራ'ስ መጥፋት ወደ ውስጥ መመልከት
ነፃነቱን በእጁ ያደረገ ትውልድ
ጥልቁን ማንነቱን የተረዳ ያወቀ የተጠቀመ
ራሱን ሆኖ ራሱን ነጻ ያወጣ
ውድ ስጦታውን/talent የተቀበለ የተጠቀመ...
እሱን/ሷን አምጡልኝ አፋልጉኝ ሀገሬን ልስጠው ።
@Amhabook
@studtsup
🥰19👏119😁6🥱4😐4🤗32
INSA Cyber Talent Center pinned «https://youtu.be/ui_UjYBbsKg?si=lwjD8CKQlm-bEx5s»
We ill start 2018/2026 INSA cyber talent summer camp registration and recruitment soon ... Please add or share our official telegram channel for those want to join our program.
👉👉 @insactc
🔥4712💩11👍9🥱7😢2🤡1💔1
We will start live streaming soon on this platform ...
👇👇👇
@insactc
👍56💩76🫡6🙏3🤡3😁1💔1
INSA Cyber Talent Center pinned «We will start live streaming soon on this platform ... 👇👇👇 @insactc»
Forwarded from Tech excellence Center
Ethical Vs Blackhat.pdf
17.9 MB
Ethical Vs Blackhat 📚 Book volunteer ነን👨‍🎓📚
Tech and related purchased book and articles - @techexecl
Amharic book - @AmhaBook
4🔥4😁3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚንስተር ዶር አብይ አህመድ ስለ INSA & AI ታለንት ማእከል ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎችን ሲያሰለጥኑ የተናገሩት @insactc
35💩10👍6🔥6🤣4🤪4🥰1
What programming languages do you know?
Python
C
C++
Java
C#
JavaScript,
Go,
SQL,
R,
Rust,
PHP,
Assembly,
Ruby,
Swift,
Kotlin,
TypeScript,
Lua,
MATLAB,
Delphi / Object Pascal,
Perl,
Ada,
Fortran... @insactc
33🔥11🤪3😴1👾1