INSA Cyber Talent Center
4.96K subscribers
150 photos
24 videos
56 files
60 links
We work to inspire, cultivat, develop and hire talents in cyber ecosystem.
Download Telegram
4ኛ ዙር ሰመር ካምፕ ምርቃት በፎቶ
🔥14👏21
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" በስልጠና ማጠናቀቂያ ወቅት ያገኙት ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ለመማር በሚወዳደሩበት ወቅት 10 በመቶ ውጤት እንዲኖረው እናደርጋለን "- የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ/ም የክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 629 ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት አስመረቋል።

ታዳጊዎቹ በክረምት መርሃ ግብር የሰለጠኑት ፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በቴክኖሎጂ ልማት፣
- በኢምቤድድ ሲስተም፣ እና በኤሮስፔስ ዘርፎች ነው።

ላለፉት ሦስት አመታት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር፤ በ2017 ዓ/ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 76 ልጆች ሰልጥነው መመረቅ መቻላቸው ተገልጿል።

ስልጠናውን የተከታተሉት ታዳጊዎች ከኢለመንተሪ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ናቸው ።

ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን ከኢንሳ በተጨማሪ  በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በማጠናቀቂያው ወቅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመከታተል በሚወዳደሩበት ወቅት የመቁረጫው ነጥብ ዝቅ እንደሚያደረግላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ግቢ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል ስልጠናውን ኮርስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በመንገር ችግሮችን መፍታት ከመቻላቸውም በላይ ፕሮዳክቶችን ይዘው መጥተዋል።

የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት እና መሸጥ የሚችሉ ፕሮዳክቶችን ይዘው ወጥተዋል።

እኛ ፈተና ፈትነን ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑ ይታወቃል ፈተና ፈትነን ስንቀበል የ 12 ውጤት እና የመግቢያ ፈተና ውጤት ነው የምናየው።

በእዚህ ስልጠና ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥተው በግቢያችን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የወሰዱት ሰርተፍኬት በግቢያችን ለመማር በሚያመለክቱበት ወቅት ቫልዩ ይኖረዋል።

ከእዚህ ቀደም ስናወዳድር 50 በመቶ 12 ክፍል ውጤት 50 በመቶ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እንመለከት ነበር አሁን 10 በመቶ በስልጠና ማጠናቀቂያው ወቅት ያገኙትን ሰርተፍኬት እንዲይዝ  እናደርጋለን።

አንድ ላይ ተደምሮ ከመቶ ሲያዝ የመቁረጫ ነጥብ ላይ ባመጡት ቁጥር ዝቅ ያደረግላቸዋል ፣ ልዩ ኮታ ይሰጣቸዋል ማለት ነው ።

ይህንን እድል አምናም ሰጥተናል ዘንድሮ ከገቡ መካከልም ይህንን እድል ያገኙ አሉ በሚቀጥለው አመትም ይህ ይቀጥላል።

ሁለተኛ እዚህ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮዳክቶችን አውጥተዋል እኛ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽን እና ኢንኩቤሽን ሃብ ሰርተናል ይህ ሃብ ወደ 189 ስታርታፖችን መቀበል ይችላል።

እነዚህ ስታርታፖች ከተለያዩ ቦታ እና ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው እና መሸጫ ቦታ ያጡ ሰዎችን የምናሰባስብበት ቦታ ነው።

ይህንን ስፔስ (ቦታ) ስልጠናውን ለተከታተሉ ሰዎች ለሰሯቸው ምርቶች (ፕሮዳክቶች) እናቀርባለን።

የምናቀርበው በሁለት አይነት መንገድ ነው አቅሙ ኖሯቸው በራሳችን እንቀጥል ካሉ የተወሰነ ኪራይ እናስከፍላለን ፣ምንም አቅም የለንም የሚሉ ካሉ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከዩኒቨርሲቲውም አንድ ላይ አድርገን ድጋፍ በማድረግ ምርታቸው ወደ ገበያ እንዲወጣ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
37👍4🤣1
INSA Cyber Talent Center pinned «https://youtu.be/M8Sr3EkprdM?si=LqeXI4D97BDgYe7H»