የCTF ውድድር ጥሪ!
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)
6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የCapture The Flag (CTF) ውድድር!!
የሳይበር ደህንነት ክህሎትዎን የሚፈትሹበት እና ከሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የሚወዳደሩበት መድረክ !!
ይወዳደሩ! ይሸለሙ!
ለመመዝገብ፡- ከታች ያለውን QR ኮድ ስካን ያድርጉ
ቦታ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በአካል
ቀን ጥቅምት 1/2018ዓ.ም
ከ ጠዋቱ 2፡ 30 በአካል

🫡16❤12💩9🥰3🔥1😢1🤪1
Forwarded from INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የሳይበር ደህንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል
አዲስ አበባ፡ መስከረም 29/2018 ዓ.ም፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከጥቅምት 1-30/2018 ዓ.ም ድረስ የሚከበረውን 6ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው 6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የሳይበር ደህንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡
በሀገራችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከማደጉ ጋር ተያይዞ በዜጎች፣ በተቋማት እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመው፣ የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡና እራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ የሚያግዙ የተለያዩ መርሐግብሮች የሚካሄዱበት ወር እንደሆነ ገልጸዋል።
6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በሁለት ዋና ዋና ጭብጦች እንደሚከበር የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ የመጀመሪያው የሃሰተኛ መረጃ ዝግጅትና ስርጭት መከላከል ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ዲጂታላይዜሽን እና የሳይበር ደህንነት ጋር የሚያተኩር ነው፡፡
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA

❤24💩6🔥2
የኢመደአ የሳይበር ታለንት ሰልጣኞች በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ አሸናፊ ሆነዋል
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የሳይበር ታለንት ልማት ሰልጣኝ የነበሩት ቶማስ ብርቅነህ እና አለሙ ተስፋ በቻይና ጉዋንዡ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት የክህሎት ውድድር ላይ የብርና የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት አሸንፈዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለሁለቱም አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፤ የአስተዳደሩ የክህሎት ልማት ውጤት በመሆናቸው የተሰማውን ደስታ ይገልጻል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት የክረምት መርሃ ግብር ሰልጣኝ የነበረው ቶማስ ብርቅነህ በውድድሩ ላይ ባቀረበው ፕሮጀክት፤ በ Artificial Intelligence ዘርፍ በ “LUCY: Advanced AI Robotics and IoT Integration” የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል፡፡
በተመሳሳይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት የክረምት መርሃ ግብር ሰልጣኝ የነበረው አለሙ ተስፋ በ Future Technology ዘርፍ በ “Digital Business Card” ፕሮጀክት ላይ የነሃስ ሜዳልያ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ላለፊት ተከታታይ አራት አመታት ባካሄደው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም የተሳተፉና የተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች በተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደሩ ሲሆን፤ የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት አቅም በማሳደግ ባማቀጣጠል ረገድ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
https://www.facebook.com/100064697533028/posts/pfbid02GBtKmfcpwVvjn4GZ79PiuxvbiknDaYzWGiDgpEJGZUS28WKusL46G32qyvb8b1sDl/

Facebook
INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
የኢመደአ የሳይበር ታለንት ሰልጣኞች በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ አሸናፊ ሆነዋል
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የሳይበር ታለንት ልማት ሰልጣኝ የነበሩት ቶማስ ብርቅነህ እና አለሙ ተስፋ በቻይና ጉዋንዡ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት የክህሎት ውድድር ላይ የብርና የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት...

🔥25❤14💩4👍2👏2
👏94🎉39❤12🔥10⚡4😢3🤣1🆒1