Injibara University
15.5K subscribers
4.15K photos
18 videos
597 files
246 links
Download Telegram
በምህንድስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሁለተኛ ድግሪን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ግምገማ (External Workshop) ተካሄደ::
---------------------
በግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር እሱባለው ስንቴ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪን ለመጀመር የሚያስችሉ ካሪኩለምን ጨምሮ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ጠቅሰው ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማግኘት የውጭ ግምገማ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ሥራ ለተሳተፉ ገምጋሚዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የግምገማ መድረኩን መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የድኅረ ምረቃ፣ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት ይርጋ ያየህ(ዶ/ር) ሲሆኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሁለተኛ ዲግሪ መሰጠቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እድገት በተለያዩ ዘርፎች (በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና እና ህክምና፣ በንግድ ዘርፍ፣ በስራ ፈጠራ በመገናኛ ብዙኃን እና የቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም በሌሎች አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች) ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ከሌሎች ሴክተሮች ጋር በማጣመር የተለያዩ ሴክተሮችን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል አንድ ግብዓት መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከወሎ ዩኒቨርሲቲ አለሙ ጆርጊ (ዶ/ር) እና ክባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አብዱከሪም መሀመድ (ዶ/ር) በቨርቹዋል ገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን በተነሱት ሃሳብ እና አስተያየቶች ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግምገማው ወርክሾፕ ተጠናቋል፡፡
የካቲት 7/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ክለብ (Environmental Protection Club) አቋቋሙ።

ክለቡ መቋቋሙ ዩኒቨርሲቲው የሚታወቅበት ጽዱ እና አረንጓዴነቱን ለመጠበቅ የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ እና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ኃላፊ አበበ አናጋው (ዶ/ር) እንደገለጹት ትምህርት ክፍሉ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በግቢው ውስጥ የችግኝ የማፍላት ስራ የጀመረ እና ትልቅ እገዛ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው ዕለት ደግሞ የUrban and Regional Development Planning የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ጋር በመሆን የአካባቢ ጥበቃ ከለብ በይፋ መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid06HDeYUR5tMiK9v8UcUtyexjh3YhW8s931De5UmZNMArt84vf4RPsN8Ds8cEJYbx4l/?app=fbl
በማህበራዊ እና ሰብዓዊ ሳይንስ ኮሌጅ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ (validation workshop) አካሄደ፡፡

ኮሌጁ (PhD in TEFL) እና በሁለተኛ ዲግሪ (MA in Comparative Literature and Cultural Studies) ለማስጀመር የሥርዓተ-ትምህርት ቅኝት አካሂዷል፡፡

በሥርዓተ ትምህርት ግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነባር በሆኑት ደብረ ማርቆስና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚገኝ በመሆኑ ለእነዚህና ለሌሎችም በቀጣይ ለሚከፈቱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ተጨማሪና አስፈላጊ የሆነውን የሰው ኃይል ግብዓት ከእነዚህ ዓይነት ነባር ተቋማት በመጠቀም ለተሻለ የትምህርት ጥራት መረጋገጥ ብሎም ተቋሙን በተማሪዎች ዘንድ ይበልጥ ተመራጭ ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በቀጣይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውን ምሁራንን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመሳብ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid04rYnwEHCJhUXhbij47YzknCKMfdWC1ibJuoYrD2pphSPYtpkVtgG7We3XgMby7QJl/?app=fbl
የጥሪ ማስታወቂያ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች፦

በ2015 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ቀን ከታች በተገለጸው መሰረት የካቲት 27 እና 28 መሆኑን እናሳውቃለን!
ማስታወቂያ
ለተከታታይ ትምህርት ለፈላጊዎች በሙሉ፦