Information Science and Technology
18.4K subscribers
261 photos
24 videos
99 files
399 links
Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.
Download Telegram
አጭር መዝገበ ቃላት

HTTPS

በዚህ “http://www.example.com/” መልክ የተጻፈ የድር አድራሻን አይተው ከኾነ “http” የሚለውን ቅንጥብ ውሂብ ያስተውላሉ። HTTP (hypertext transfer protocol) ማለት በኮምፒውተርዎ ላይ ያለው የድር መዳሰሻ በርቀት ካለው የድር አገልጋይ ጋር የሚነጋገርበት ቋንቋ ነው። እንደ አለመታደል ኾኖ መደበኛው http በኢንተርኔት ላይ መልዕክትን የሚያስተላልፈው ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ነው። HTTPS (S የምትለዋ በእንግሊዘኛው “ሴኪዩር” የሚለውን ይወክላል ይህም ደህንነቱ የተረጋገጠ ለማለት ነው) ደግሞ ለድረ ገጾች የሚልኩትን ውሂብ እና ከእነርሱ የሚቀበሉትን መረጃ ከሰላዮች ለመከላከል ምስጠራን ይጠቀማል።

PGP ወይም እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነት

በተግባር ከዋሉት የመጀመሪያዎቹ ትግበራዎች አንዱ ነው። የPGP ፈጣሪ የኾነው ፊል ዚመርማን በ1991 ፕሮግራሙን ሲጽፈው አራማጆችን እና ሌሎች ሰዎችን ግንኙነቶቻቸውን ለማመስጠር እንዲረዳቸው በማሰብ ነው። ፕሮግራሙ ወደ ሌሎች ሀገራት ሲሰራጭ ፊል ዚመርማን በአሜሪካ መንግሥት ተመርምሯል። በወቅቱ ጠንካራ የአደባባይ ምስጠራን ጨምሮ ሌሎች መሣሪያዎችን ወደ ውጪ መላክ የአሜሪካን ሕግ የሚተላለፍ ድርጊት ነበር።
PGP እንደ የንግድ ሶፍትዌር ምርትነት በገበያ ላይ አለ። በነጻ በተግባር ላይ ለማዋል ከPGP ጋር ተመሳሳይ መርሆችን የሚጠቀመውን GnuPG (ወይም GPG) የተባለው ሶፍትዌርን ማግኘት ይቻላል። ሁለቱም ተመሳሳይ እና ተተካኪ ስነ ዘዴን ስለሚጠቀሙ ሰዎች GnuPGን እየተጠቀሙ ስያሜውን ግን የ“PGP ቁልፍ” ወይም የ“PGP መልእክት” መላክ ብለው ሲጠቅሱት ይስተዋላሉ።

SSH

SSH  (ወይም Secure SHell) በትዕዛዝ መስመር አማካኝነት በርቀት ያለን ኮምፒውተር ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው። ትእዛዞችን ከመላክ በተጨማሪ በሁለት ኮምፒውተሮች መካከል ያለን የኢንተርኔት ትራፊክ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማስተላለፍ የSSH ስነስረዓት አንዱ ገጽታ ነው። የSSH አገናኝን ለማዋቀር በርቀት ያለው ስረዓት እንደ SSH አገልጋይ መከወን እና በቅርበት ያለው መሣሪያ ደግሞ የSSH ደምበኛ ፕርግራም ሊኖረው ይገባል።

XMPP

ለፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ክፍተ ምንጨ ኮድ ስርዓት ነው። XMPPን ጎግል ለጎግል ቶክ የሚገለገልበት ሲኾን ፌስቡክ ግን ቀደሞ ይገለገልበት የነበረ ቢኾንም አሁን ግን አቁሟል። ኮርፖሬት ያልኾኑ ነጻ ፈጣን የመልዕክት መላኪያ አገልግሎቶች አብዛኛውን ጊዜ XMPPን ይጠቀማሉ። እንደ ዋትስአፕ ያሉ አገልግሎቶች የራሳቸው ዝግ እና ሚስጢራዊ ስርዓት አላቸው።

ልዕለ መረጃ

ልዕለ መረጃ (ወይም "ስለ ውሂብ  ያለ ውሂብ") ከመረጃው ባሻገር ያለ ስለመረጃው የሚናገርር ቅንብር መረጃ ነው። የመልዕክቱ ይዘት ልዕለ መረጃ አይደለም። ነገር ግን መልዕክቱን ማን ላከው፣ መቼ ተላከ፣ ከየት ተላከ እና ለማን ተላከ የሚሉት የልዕለ መረጃ ምሳሌዎች ናቸው። የሕግ ስርዓቶች ከልዕለ መረጃዎች ይልቅ የመረጃውን ይዘት ይከላከላሉ። ለምሳሌ በአሜሪካን ሀገር የሕግ አስፈጻሚ አካላት የግለሰቦችን የስልክ ውይይት ለማዳመጥ የፍርድ ቤት ማዘዣ ማግኘት አለባቸው ነገር ግን ስልክ የደወሉላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝርን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ የልዕለ መረጃ በርካታ ነገሮችን ሊገልጽ ስለሚችል እንደ መረጃው ሁሉ በጥንቃቄ መጠበቅ አለበት።

መመስጠር

እንደገና መገጣጠም እና ትክክለኛ መረጃ() በያዘ ሰው ወደ ቀድሞ ቅርጹ መመለስ በሚያስችል መልኩ መረጃን ወይም መልእክትን በሂሳባዊ ስልት በመቆራረጥ ትርጉም የሌለው እንዲመስል ማድረግ፡፡ይህ መልዕክቱን ወይም መረጃውን እነማን ማግኘት እንዳለባቸው ይገድባል፡፡፡ ምክንያቱም ያለ ትክክለኛ ቁልፍ ኦርጂናል መረጃውን ማግኘት እና ምስጠራውን ወደኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ ምስጠራ በስነ ምስጠራ መስክ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

መሰበሩን ወይም ሰብሮ ለመግባት መሞከሩን ፍንጭ የሚሰጡ ምልክቶች

የኮምፒውተርዎ ወይም የመገልገያ መሣሪያዎ ስርዓት መሰበሩን ወይም ሰብሮ ለመግባት መሞከሩን ፍንጭ የሚሰጡ ምልክቶች።

መፍታት

ምስጢራዊ መልዕክትን ወይም ውሂብን ስሜት እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው። ከምስጢራዊነት በስተጀርባ ያለውን ሃሳብ መልዕክቱን እንዲቀበሉ የታቀደላቸው ሰዎች ብቻ መፈታት እንዲችሉ ማድረግ ነው።

ሙሉ ዲስክ ምስጠራ

በኮምፒውተርዎ ላይ ያለ ውሂብን ደህንነት የመጠበቅ ዕቅድ ካለዎት ጥቂት ፋይሎችን መርጠው ማመስጠር ወይም በኮምፒውተርዎ የሚገኙትን ሁሉንም ፋይሎች ማመስጠር ይችላሉ። “የሙሉ ዲስክ ምስጠራ ” በኮምፒውተር ላይ የሚገኝ ሁሉንም ነገር በምናመስጥርበት ወቅት የምንጠቀመው ቃል ነው። አብዛኛውን ጊዜ ሙሉ ዲስክ ምስጠራን መጠቀም ጥቂት የተመሰጠሩ ፋይሎችን ከማስተዳደር ይልቅ ደህንነቱ የተጠበቀ (እና ብዙውን ጊዜ ቀላል) ነው። ነጠላ ፋይሎችን ለማመስጠር ቢሞክሩ ኮምፒውተርዎ ያለ እርስዎ ዕውቅና ጊዜያዊ ያልተመሰጠረ የፋይሎቹን ቅጂ ሊያስቀምጥ ይችላል። በተጨማሪም አንዳንድ ሶፍትዌሮች ስለ ከምፒውተር አጠቃቀምዎ ያልተመሰጠሩ መረጃዎችን ሊያስቀምጡ ይችላሉ። የአፕል OS X፣ ሊኒክስ እና የዊንዶውስ ከፍ ያሉ ሥሪቶች አብሮ ገነብ የኾነ የሙሉ ዲስክ ምስጠራ አገልግሎት ቢኖራቸውም አብዛኛውን ጊዜ ግን በነባሪ የሚሠሩ አይደሉም።

ማከያ

አነስ ያለ ሶፍትዌር ሲሆን ሌላ ሶፍትዌርን በማበጃጀት ከዚህ በፊት ስራዎችን የሚያከናውንብትን መንገድ እና ራሱ ስራውን የሚቀየር ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ማከያዎች የግላዊነት ወይም የደህንነት ተግባሮችን በድር አሳሾች ወይም በኢሜይል ሶፍትዌር ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ማከያዎች ሸረኛ ሶፍትሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ሲጭኑ እውቅና ያላቸውን እና ከዋናው ምንጮች ብቻ የሆኑትን ለመምረጥ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

ምስጠራ

አንድን መልዕክት ወደ መጀመሪያው ተነባቢ ቅርጽ "መፍታት" ከሚችለው ሰው በስተቀር መልዕክት እንዳይነበብ አድርጎ መቀየር የሚያስችል ሂደት ነው።

ምናባዊ የግል አውታረ መረብ

ምናባዊ የግል አውታረ መረብ ወይም VPN ኮምፒውተርዎን ድህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በአንድ ድርጅት ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የማገናኛ መንገድ ነው። VPNን ሲጠቀሙ ሁሉም በኮምፒውተርዎ ላይ የሚያደጉት የኢንተርኔት ግንኙነትዎ በአንድ ጥቅል ይመሰጠር እና ለሌላኛው ድርጅት ይተላለፋል። በዚህ ድርጅት ምስጠራው እና ጥቅሉ ከተፈታ በኋላ ወደ ተቀባዩ ይተላለፋል። ለእዚህ ድርጅት አውታረ መረብ ወይም በኢንተርኔት ላይ ለሚገኝ ለማንኛውም ኮምፒውተር ከእርስዎ ኮምፒውተር የመጣው ጥያቄ ከእርስዎ ሥፍራ ሳይኾን ከድርጅቱ እንደመጣ መስሎ ይታያል።
በተቋማት ውስጥ VPN ደህንነቱ የተጠበቀ የውስጥ ሀብት አገልግሎትን (ለምሳሌ እንደ የፋይል አገልጋዮች እና ፕሪንተሮች) ለማቅረብ ይውላል። በተጨማሪም በአካባቢ የሚደረግ የኢንተርኔት እገዳን ለማለፍ፣ ወይም በአካባቢ የሚደረግ ስለላን ለማሸነፍ በግለሰቦች ጥቅም ላይ ይውላል።

ረጋ-ሠራሽ አስተኔ ጥቃት

በአምራቹ ቀድሞ ያልታወቀ በሶፍትዌር ወይም በሃርድዌር ላይ ያለ ስህተት ነው። አምራቹ ስለዚህ መረጃ አግኝቶ እስኪያስተካክለው ድረስ አጥቂዎች ለራሳቸው አላማ ሊጠቀሙት ይችላሉ።

ሰነመሰውር

የማይመለከታቸው ሰዎች የመልዕክቱን ይዘት መረዳት ሳይችሉ ከተቀባይ ጋር መልዕክቶችን መላክ እና መቀበል የሚያስችል ሚስጥራዊ ኮድን ወይም መሰውርን ዲዛይን የማድረጊያ ጥበብ ነው።
ሲም ካርድ

ከአንድ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያ አገልግሎትን ለማግኘት በተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎ ውስጥ የሚወጣና የሚገባ አነስተኛ ካርድ ነው። በተጨማሪም ሲም (subscriber identity module) ካርዶች የስልክ ቁጥሮችን እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ማስቀመጥ ይችላሉ።

ስርዓተ ክወና

በኮተፒውተር ላይ የሚገኙ ሌሎች ፕሮግራሞች እንዲሰሩ የሚያስችል ፕሮግራም ነው። ዊንዶውስ፣ አንድሮይድ፣ እና አፕል OS X እና iOS የስርዓተ ክወና ምሳሌዎች ናቸው።

ስጋት

በኮምፒውተር ደህንነት ቋንቋ ማለት ውሂብዎን ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት ችግር ውስጥ ሊከት የሚችል አደገኛ ክስተት ነው። ስጋት ታቅዶ የሚፈጸም (በአጥቂዎች የታቀደ) ወይም በአጋጣሚ ሊከሰት (እርስዎ ሳያውቁ ኮምፒውተርዎን ከፍተው ያለጥበቃ በአጋጣሚ ትተውት ሄደው) የሚችል አደጋ ሊኾን ይችላል።

ሶሊድ ስቴት ድራይቭ (SSD)

ድሮ ኮምፒውተሮች ውሂብን የሚያጠራቅሙት በተሽከርካሪ ማግኔታዊ ዲስኮች ላይ ነው። አሁን አሁን ተንቀሳቃሽ ስልኮች እና አብዛኞቹ የግል ኮምፒውተሮች በማይንቀሳቀሱ የዲስክ አንጻፊዎች በዘላቂነት ውሂቦችን ያጠራቅማሉ። እነዚህ የSSD አንጻፊዎች ውድ ቢኾኑም ከማግኔታዊ ማጠራቀሚያዎች በተሻለ ፈጣን ናቸው። እንደ አለመታደል ኾኖ ከSSD አንጻፊዎች በአስተማማኝ እና በዘላቂ ኹኔታ ውሂብን ማስወገድ አስቸጋሪ ሊኾን ይችላል።

ሸረኛ ሶፍትዌር

በእንግሊዝኛው አጠራር ማልዌር የሚባሉት ሸረኛ ሶፍትዌሮች ሲኾኑ በመሣሪያዎ ላይ አላስፈላጊ ተግባሮችን እንዲያከናውኑ ተደርገው የተሠሩ ፕሮግራሞች ናቸው። የኮምፒውተር ቫይረሶች ሸረኛ ሶፍትዌሮች ናቸው። በተጨማሪም የማለፊያ ቃልን የሚሰርቁ፣ እርስዎ ሳያውቁ እንቅስቃሴዎን የሚቀዱ፣ ወይም ውሂብዎን የሚያጠፉ ፕሮግራሞች ሸረኛ ሶፍትዌሮች ተብለው ይጠራሉ።

ሽሽግ ስም

በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ (ለምሳሌ የመስመር ላይ ፎርሞችን ሲሞሉ ) የሚጠቀሙበት ስም ሲሆን እና ከዚህ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ሰዎች ዘንድ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን እርስዎ በዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያውቋቸው ከእርስዎ ስሞች ጋር የተዛመደ አይደለም፡፡

ቁልፍ

በስነ መሰውር መልዕክትን ማመስጠር ወይም መፍታት የሚያስችል ቅንጥብ ውሂብ ነው።

ቁልፍ መዝጋቢ

እጅግ ሸረኛ የኾነ ፕሮግራም ወይም መሳሪያ ሲኾን በመሣሪያዎ የቁልፍ ሰሌዳ ላይ የተጫኗቸውን ቁልፎች (የማለፊያ ቃሎችን እና ሌሎች የግል መረጃዎችን ጨምሮ) በመመዝገብ በድብቅ እነኚህን መረጃዎች ለሌሎች አሳልፎ የሚሰጥ ነው። ( በሚለው ሐረግ ውስጥ "" የሚለው ቃል የሚያመለክተው በቁልፍ ሰሌዳዎ ላይ ያሉትን ቁልፎች ነው)። ቁልፍ መዝጋቢዎች አብዛኛውን ጊዜ ተጠቃሚዎች ተታለው በማውረድ በኮምፒውተራቸው ላይ የሚጭኗቸው ሸረኛ ሶፍትዌሮች ሲኾኑ አልፎ አልፎ ግን በቁልፍ ሰሌዳው ወይም መሣሪያው ላይ በምስጢር የተገጠሙ ሃርድዌር ሊኾኑ ይችላሉ።

ቁልፍ መያዣ

የአደባባይ ስነመሰውርን የሚጠቀሙ ከኾነ በርካታ ቁልፎች የት እንዳሉ ማወቅ ይኖርብዎታል። ይህም ምስጢራዊ ቁልፍዎት፣ የግል ቁልፍዎት፣ የአደባባይ ቁልፍዎት፣ እና እርስዎ የሚገናኙዋቸው ሰዎች የአደባባይ ቁልፎችን ያካትታል። የእነዚህ ቁልፎች ስብስብ አብዛኛውን ጊዜ የቁልፍ መያዣ ተብሎ ይጠራል።

ቁልፍ የጣት አሻራ

የአደባባይ ቁልፍን የሚወክሉ ፊደሎች ወይም ቁጥሮች ቅደም ተከተል ነው፡፡ አንዳንድ የግላዊነት መሣሪያዎች ሌሎች ሰዎች በመሳሪያቸው ላይ ያደረጉትን በእርስዎ መሣሪያ ትክክለኛነትነቱን እንዲያረጋግጡ ያደርጋሉ፡፡ የዚህ ዓላማ መካከለኛ የሆነ ሰው የተሳሳተ ቁለፍ በመጠቀም እንዳያታልዎ መከላከል ነው፡፡

በIP ላይ የሚደረግ የድምጽ ግንኙነት

ማንኛውም ኢንተርኔትን በመጠቀም የድምጽ ግንኙነት ለማድረግ የሚያገለግል ቴክኖሎጂ ነው። ወይም በIP ላይ የሚደረግ የድምጽ ዝውውርን ተጠቅሞ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረግ የስልክ ጥሬ አገልግሎት ነው።

በዝውውር ሂደት ድርብርብ የውሂብ ምስጠራ

ውሂብ በኔትወክ በሚተላለፍበት ወቅት ኔትወርኩ ላይ ስለላ የሚያካሂዱ አካላት ውሂቡን እንዳያነቡት ያግዳል።

ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያ

"የኾነ የሚያዉቁት እና ያለዎት ጉዳይ።" የተጠቃሚ ስምን እና የማለፊያ ቃልን ብቻ የሚጠይቁ የመግቢያ ስርዓቶች ክፍተት አላቸው። አንድ ግለሰብ እነዚህን ቅንጥብ መረጃዎች ቢያገኝ (ወይም መገመት ቢችል) መረጃዎች አደጋ ላይ ይወድቃሉ። ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያን የሚሰጡ አገልግሎቶች ትክክለኛ ማንነትዎን የሚያረጋግጡበት ተጨማሪ የተለየ ማስረጃ እንዲሰጡ ይጠይቅዎታል። ሁለተኛው ማትሪያ አንድ የሚስጥራዊ ኮድ፣ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ ባለ ፕሮግራም የመነጨ ቁጥር፣ ወይም እርስዎ የያዙት እና ማን እንደኾኑ የእርስዎን ማንነት ለማረገገጥ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ሊኾን ይችላል። እንደ ባንክ ያሉ ኩባንያዎች እና እንደ ጎግል፣ ፔይፓል እና ትዊተር ያሉ ዋና ዋና የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያ አገልግሎትን ይሰጣሉ።

ችሎታ

በዚህ መመሪያ መሰረት የአጥቂ ማለት ዓላማው ግቡን እንዲመታ የሚያስችለው አቅም ነው። ለምሳሌ የአንድ ሀገር የደህንነት መሥሪያ ቤት የስልክ ጥሪዎችን ማዳመጥ የሚያስችል ችሎታ ሊኖረው ይችላል። ጎረቤቶች ደግሞ እርስዎን በመስኮት የመከታተል ችሎታ ሊኖራቸው ይችላል። አንድ ችሎታ “አለው" ማለት ያለውን ችሎታ በተግባር ላይ ያውለዋል ማለት ላይኾን ይችላል። ነገር ግን በተግባር ላይ ሊያውለው ይችላል ብለው በማሰብ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብዎታል ማለት ነው።

ንቁ ያልኾነ አጥቂ

ማለት የመስመር ላይ ግንኙነትዎን የሚሰማ ነገር ግን በቀጥታ መልዕክቱን ይዘት መቀየር የማይችል ማለት ነው።

አብይ የማለፊያ ቃል

የማለፊያ ቃላት ካዝናን ለመክፈት የሚጠቀሙት የማለፊያ ቃል ወይም ፕሮግራሞችን ወይም መልዕክቶችን የሚከፍቱበት ዋነኛ መንገድ ነው። አብይ የማለፊያ ቃልን በተቻለ መጠን ጠንካራ ማድረግ ይኖርብዎታል።

አጥቂ

አጥቂዎ የእርስዎ የደህንነት ግቦች ላይ ጥቃት  ለመሰንዘር የሚሞክር ሰው ወይም ድርጅት ነው። ያሉትን ነባራዊ ኹኔታዎች መሠረት በማድረግ አጥቂዎች የተለያዩ ሊኾኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ወንጀለኞች በካፌ ውስጥ ያለ መረብን ሊሰልሉ እንደሚችሉ፣ ወይም ትምህርት ቤት የክፍሎ ተማሪዎች ሊሰልሉዎት ሊጠረጥሩ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ አጥቂዎች ሃሳባዊ ናቸው።

ኢንተርኔትን ማጣራት

ማጣራት ማገድ እና ቅድመ ምርመራን ለዘብ ባለ መልኩ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው ። አንዳንዴ ምናባዊ የግል አውታረ መረቦች ወይም እንደ ቶር ያሉ አገልግሎቶች ካልተጣሩ የኢንተርኔት ግንኙነት በመስጠት ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

ከመስመር ውጪ ማራጋገጫ

"ከመስመር ውጪ" ማለት እየተጠቀሙት ካለው የመገናኛ መንገድ ውጪ የኾነ የመገናኛ መንገድ ነው። ደህንነቱ ያልተጠበቀ ስርዓትን ተጠቅመው እየተነጋገሩት ያለውን ሰው ማንነት ለማረጋገጥ አብዛኛውን ጊዜ አነስተኛ ተመሳሳይ የጥቃት ተጋላጭነትባለው ሌላ የመገናኛ መንገድ አማካኝነት መገናኘትን ይጠይቃል። ለምሳሌ የአንድን ሰው ትክክለኛ የአደባባይ እንደሚጠቀሙ ለማረጋገጥ ቁልፉን ተጠቅመው ምስጢራዊ መልዕክትን ከመላክዎት በፊት በአካል ተገናኝተው ቁልፉን ማረጋገጥ ይችላሉ።

ከምዝገባ ውጪ
ፈጣን የመልዕክት ስርዓቶች አብዛኛውን ጊዜ ያልተመሰጠሩ ናቸው። OTR ወይም ከምዝገባ ውጪ በፈጣን የመልዕክት ስርዓቶች ውስጥ ምስጠራን የማበልጸጊያ መንገድ ነው። በመኾኑም እንደ ፌስቡክ ቻት፣ ወይም  ጎግል ቻት ወይም ሃንግአውት፣ ያሉ ታዋቂ የግንኙነት መረቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መጠቀም ያስችልዎታል።

ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ

ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ እንድ መልዕክት በላኪው ወደ ሚስጥራዊ መልዕክት መቀየሩን እና በተቀባዩ ብቻ መፈታት መቻሉን የሚያረጋግጥ ስርዓት ነው። ሌሎች የምስጠራ ዓይነቶች በሦስተኛ ወገን የሚደረግ ምስጠራ  ላይ የተመሰረቱ ሊኾኑ ይችላሉ። ይህ ማለት አመስጣሪዎቹ አካላት በዋናው መልዕክት መታመን አለባቸው ማለት ነው። ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ አብዛኛውን ጊዜ ደህንነቱ የተሻለ እንደኾነ ይታሰባል። ምክንያቱም ምስጠራውን መስበር ወይም ጣልቃ መግባት የሚችሉ አካላትን ቁጥር በመቀነሱ ነው።

ኩኪዎች

ኩኪዎች ድረ ገጾች የድር መዳሰሻዎን እንዲያውቁ የሚያደርጉ የድር ቴክኖሎጂ ናቸው። በዋናነት ኩኪዎች የተዘጋጁት ድረ ገጾች የመስመር ላይ ግብይቶች ማድረግ እንዲችሉ፣ ምርጫዎችን ለማስቀመጥ ወይም በድረ ገጽ ገብተው እንዲቆዩ ለማድረግ ነው። በተጨማሪም የድር ጉብኝትዎን እና የማንነትዎን መገለጫ እንዲሰበስቡ ያስችላሉ። ስለዚህም ድረ ገጾች ፤ ምንም እንኳን በዚያ ድረ ገጽ መለያ ባይኖርዎት ወይም በመለያዎ ውስጥ ያልገቡ ቢኾኑ፤ እርስዎን እንዲያውቁ እና የት እንደሚሄዱ፣ ምን አይነት መሣሪያን እንደሚጠቀሙ፣ እና ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳለዎት ሊያውቁ ይችላሉ።

ክፍት ምንጭ ሶፍትዌር

ክፍት ምንጨ ኮድ ሶፍትዌር ወይም ነጻ ሶፍትዌር ተጠቃሚዎች ኮዱን ሊያሻሽሉት እና እንደ አዲስ ደግመው ሊሰሩት በሚችል መንገድ በነጻ የሚሰራጭ ሶፍትዌር ነው። እንደ "ነጻ ሶፍትዌር" የሚታወቅ ቢኾንም ያለ ምንም ዋጋ በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው ማለት ላይኾን ይችላል። የFLOSS ፕሮግራመሮች ልገሳን፣ ወይም ለአገልግሎት ድጋፍ ወይም ለቅጂ ክፍያን ሊጠይቁ ይችላሉ። ሊኑክስ እንደ ፋየርፎክስ እና ቶር ሁሉ ነጻ እና ክፍት ምንጨ ኮድ የኾነ ፕርግራም ምሳሌ ነው።

ዌር ለቨሊንግ ወይም ንትበትን አመጣጣኝ

የፍላሽ ዲስክ፣ የሶሊድ ስቴት አንጻፊዎች (SSD) እና ሌሎች የዲጂታል ማጠራቀሚያዎች በተደጋጋሚ ቢጻፍባቸው ሊነትቡ እና ሊያልቁ ይችላሉ። ንትበትን አመጣጣኝ የሚባለው ንትብትን ለመከላከል ውሂብን በተመጣጣኝ መልኩ በሁሉም ሥፍራ ላይ እንዲሰራጭ የሚያደርግ ዘዴ ነው። ዋናው ጥቅሙ የመሣሪያዎች የአገልግሎት ዘመን እንዲራዘም ማድረግ ነው። ለድህንነታቸው የሚጠነቀቁ ሰዎች የንትበት አመጣጣኝ መሣሪያ ውሂባቸውን ለዘላለሙ ለማጥፊያነት ከሚጠቀሙበት መሣሪያ አሰራር ጋር ጣልቃ በመግባት እንዳይረብሽ ያሳስባቸዋል። በፍላሽ ዲስክ ወይም በሶሊድ ስቴት አንጻፊዎች (SSD) ላይ ያሉ ሰነዶችን ደህንነቱ የተረጋገጠ የፋይል ማጥፋት ሂደትን ከማመን ይልቅ የሙሉ ዲስክ ምስጠራን መጠቀም የተሻለ ጥበቃ ሊያደርግ ይችላል። ምስጠራ ከትክክለኛው የማለፊያ ሐረግ ውጪ በአንጻፊው ላይ ማንኛውንም ፋይል ለማገገም (መልሶ ለማምጣት) የሚከወነውን ጥረት አዳጋች በማድረግ ደህንነቱ የተረጋገጠ ስረዛን በሚያደርጉበት ወቅት የሚያጋጥሞትን ችግር ይቀርፋል።

ውሂብ

ማንኛውም ዓይነት መረጃ በአብዛኛው ጊዜ በዲጂታል መልክ ይቀመጣል፡፡ መረጃ ሰነዶችን፣ ስዕሎችን፣ ቁልፎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ መልዕክቶችን እና ሌሎች ዲጂታል መረጃዎችን ወይም ፋይሎችን ሊያካትት ይችላል፡፡

ውግድ መላሽ ሶፍትዌር

አብዛኞቹ መሣሪያዎች ውሂቦትን እንዲያስወግዱ ይፈቅዳሉ። ለምሳሌ አንድን ሰነድ ጎትተው የውግድ ቅርጫት ውስጥ መክተት ወይም በፎቶ አልበም ውስጥ ዴሊት የሚለውን መጫን ይችላሉ። ነገር ግን ፋይልን ካለበት ሥፍራ ማስወገድ የፋይሉ ዋና ቅጂ ለዘላለሙ መሰረዝ ወይም ማጥፋት ማለት አይደለም። ውግድ መላሽ ፕሮግራሞች በመሣሪያው ባለቤት ወይም መሣሪያውን የመጠቀም አቅም ባላቸው ሌሎች ግለሰቦች አንዳንድ የተወገዱ ውሂቦችን ለማገገም የሚጠቀሟቸው መተግበሪያዎች ናቸው። ውግድ መላሽ ፕሮግራሞች ሳያውቁ በስህተት የራሳቸውን ውሂብ ለሚያስወግዱ ወይም ውሂባቸው ኾን ተብሎ ለተወገደባቸው (ለምሳሌ ከካሜራው ላይ ፎቶዎቹን እንዲያስወግድ የተገደደ ፎቶ አንሺ) ጠቃሚ ናቸው። ነገር ግን እነኚሁ ፕሮግራሞች ሚስጥራዊ ውሂቦችን ለዘላለሙ ማጥፋት ለሚፈልጉ ግለሰቦች ናቸው። ውሂብን ስለመደምሰስ እንዲኹም ውግድ መላሽ ፕሮግራሞች በዘመናዊ መሣሪያዎች ላይ እንዴት እንሚሰሩ ለበለጠ መረጃ ውሂብዎን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማጥፋት የሚለውን ይመልከቱ።

ዕሴት

በስጋት ሞዴል ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ማንኛውም ቅንጥብ ውሂበ ወይም መሣሪያ ነው።

የIMAP መዋቅሮች

IMAP፤ አብዛኞቹ የኢሜል ፕሮጋራሞች ኢሜሎችን ከሚልኩ ፣ ከሚቀበሉ እና ከሚያጠራቅሙ አገልጋዮች ጋር የሚገናኙበት መንገድ ነው ። በኢሜል ፕሮጋራምዎት ላይ የIMAPን መዋቅሮች በመቀየር ኢሜልዎትን ከሌላ አገልጋይ እንዲጭን ማድረግ ይችላሉ። ወይም ኢሜልን በኢንተርኔት ላይ ወደ እርሶ የሚያስተላልፈውን የደህንነቱን እና የምስጠራውን ደረጃ ማስተካከል ይችላሉ ።

የIP አድራሻ

አንድ መኖሪያ ቤት ወይም ተቋም ድብዳቤን ለመቀበል የፓስታ አድራሻ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ያለው መሣሪያ እንዲሁ ወሂብን ለመቀበል የራሱ አድራሻ ያስፈልገዋል ። ይህ አድራሻው የIP (Internet Protocol) አድራሻ ይባላል። ከአንድ ድረገጽ ወይም ከመስመር ላይ ካለ አገልጋይ ጋር ሲገናኙ የራስዎን የIP አድራሻ ይገልጻሉ። ይህ እውነተኛ ማንነትዎን ይገልጻሉ ማለት ላይኾን ይችላል ( የIP አድራሻን ተጠቅሞ ግንኙነት እየተደረገበት ያለውን አድራሻ ወይም ኮምፒውተሩ የማን እንደኾነ ማመልከት አዳጋች ነው)። የIP አድራሻ ስለ እርስዎ አንዳንድ መረጃዎችን ለምሳሌ ግምታዊ የኾነን የመኖሪያ ክልልዎን ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎን ስም አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል። እንደ ቶር ያሉ አገልግሎቶች የIP አድራሻዎን በመደበቅ የመስመር ላይ ድብቅነትን ያጎናጽፍዎታል።

የመሻሪያ ምስክር ወረቀት

የምስጢር ቁልፍን መጠቀም ባይችሉ ወይም ሚስጥራዊነቱ ቢያበቃ ምን ሊፈጠር ይችላል? ቁልፉን ከዚህ በኋላ እንደማያምኑት ለማሳወቅ መፍጠር የሚችሉት ሰነድ ነው። ይህንን ሰነድ መፍጠር የሚችሉት ቁልፉ እስካለዎት ድረስ ሲኾን ወደፊት ሊያገጥምዎት ለሚችል አደጋ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡት።

የማለፊያ ሐረግ

የማለፊያ ሐረግ እንደ ማለፊያ ቃል የሚያገለግል ነው። "የማለፊያ ሐረግ" የሚለውን የምንጠቀመው የማለፊያ ቃል አንድ ቃልን የያዘ በመኾኑ እርስዎን ለመከላከል በጣም አጭር ስለኾነ ነው። ስለዚህም ረዥም ሐረግን መጠቀም የተሻለ ደህንነትን እንደሚሰጥ ለማስገንዘብ ነው። ለተሻለ ገለጻ የዌብኮሚክ XKCD የኾነውን ይህን ገጽ http://xkcd.com/936/ ይጎብኙ።

የማለፊያ ቃል አስተዳደር

አንድ ዋና የማለፊያ ቃልን በመጠቀም የማለፊያ ቃሎችዎን ማመስጠር እና ማጠራቀም የሚያስችል መሣሪያ ነው። ይህን መሣሪያ መጠቀም በተለያዩ ድረ ገጾች እና አገልግሎቶች ላይ የተለያዩ የማለፊያ ቃሎችን ማስታወስ ሳይጠበቅብዎት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይረዳዎታል።

የማሰሻ ጣት አሻራ
መካነ ድር በሚጎበኙበት ጊዜ መካነ ድሩ ስለ መካነ ድር ማሰሻዎ ወይም የኮምፒዩተር ባህሪያት ሊያውቅ ይችላል፡፡ ምናልባት በመካነ ድሮች እና ኮምፒዩተሮች መጠነኛ ልዩነት ቢኖርም እርስዎ ምንም ወደ መለያ ባይገቡም እንኳን ኮምፒተርዎ ኩኪዎችን እንዲያስቀምጥ ባይፈቀዱም ወይም ከተለየ አውታረ መረብ ጋር ከበይነመረቡ ጋር ቢገናኙም እንኳን እርስዎ መሆነንዎን ለመለየት የሚያስችል መንገድ ሊኖር ይችላል፡፡
ለምሳሌ እርስዎ በተለየ አንድ ቋንቋ በተሰናዳ መሣሪያ፣ በተለየ የስክሪን መጠን፣ በተወሰነ የድር ማሰሻ ስሪት የተወሰነ መካነ ድርን የሚጎበኝ ብቸኛ ሰው ሊሆኑ ይቻላሉ እንበል፡፡ ከዚያም መካነ ድሩ እርስዎ ማንነትዎን ለማሳየት ምንም ነገር ባያደርጉም እርስዎ በሚጎበኙበት ጊዜ ሁሉ እርስዎ መሆንዎን ሊገነዘቡት ይችላሉ፡፡

የምስጠራ ቁልፍ

መልዕክትን ወደ ቅርጽ አልባ መልክ በመቀየር እንዳይነበብ የሚያደርግ ቅንጥብ መረጃ ነው። በአንዳንድ ኹኔታዎች መልዕክቱን ለመፍታት ተመሳሳይ የምስጠራ ቁልፍን መጠቀም ያስፈልጋል። በሌላ ኹኔታ ደግሞ መልዕክቱን የማመስጠሪያ እና የመፍቻ ቁልፍ የተለያዩ ናቸው።

የሰርጎ ገብ ጥቃት (MITM)

የተመሰጠረ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎትን ተጠቅመው ከጓደኛዎ ተኽላይ ጋር እያወሩ ነው እንበል። እየተነጋገሩ ያሉት በትክክል ከሱ ጋር እንደኾነ ለማጣራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት የት ከተማ ላይ እንደኾነ እንዲነግርዎት ይጠይቁታል። ‘ጅማ’ ብሎ ይመልስልዎታል። ይህም ትክክል ነው። እንደ አለመታደል ኾኖ ሁለታችሁ ሳታስተውሉት ሌላ ግለሰብ የመስመር ላይ ግንኙነታችሁን ጠልፎ ይሰማል። ለመጀመሪያ ጊዜ ከተኽላይ ጋር በመስመር ላይ ሲገናኙ በትክክል ከተኽላይ ጋር ሳይኾን ከዚህ ማንንቱ ከማይታወቅ ግለሰብ ጋር ኾኖ እሱ ደግሞ ከጓደኛዎት ተኽላይ ጋር ያገናኞታል። እርስዎ ጥያቄውን ያቀረብኩት ለተኽላይ ነው ብልው ሲያስቡ ጥያቄውን በእርግጥ የጠቁት ግን በመሃከል ለገባው ግለሰብ ነው። ግለሰቡም ጥያቄዎትን ተቀብሎ ለጓደኛዎ ለተኽላይ ያስተላልፋል። መልሱንም ተቀብሎ ለእርስዎ ይሰጣል። ምንም እንኳ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ከተኽላይ ጋር እንደሚገናኙ ቢያስቡም፤ እየተገናኙ ያሉት ግን ከሰላዩ ጋር ነው። በተመሳሳይ ተኽላይም እንዲሁ ያስባል። ይህ ይባላል። በመሃል ሰርጎ በመግባት ስለላ የሚያካሂድ የእርስዎን ግንኙነቶች እንደ ፈለገ ከመሰለሉም ባሻገር በግንኙነትዎ መካከልም አሳሳች መልዕክቶችን ሊያስገባ ይችላል። ደህንነት ተኮር የኢንትርኔት ግንኙነት ሶፍትዌሮች ሁሉንም ዓይነት የኢንተርኔት ግንኙነቶች የመሰለል አቅም ካላቸው ከሰርጎ ገብ ጥቃቶች መከላከል አለባቸው።

የሰነድ ማስተላለፍ ስምምነት ደንብ (FTP አገልጋይ)

ሰነዶችን ከአንድ ኮምፒውተር ሌላ ራቅ ያለ ሥፍራ ወደሚገኝ ኮምፒውተር የማስተላለፊያ ቆየት ያለ መንገድ ነው። አብዛኞቹ የFTP ፕሮግራሞች (እና ፋይሎቹን የሚያጠራቅሙት የFTP አገልጋዮች ) ሥራ በድር መዳሰሻዎች እና በድር አገልጋዮች ወይም እንደ ድሮፕቦክስ ባሉ የፋይል ማዋደጃ ፕሮግራሞች ተተክተዋል።

የሰነድ ስርዓት

በኮምፒውተርዎ ላይ ወይም በሌላ መሣሪያዎት ላይ ውሂብዎት የሚጠራቀምበት ሥፍራ ነው። የግል ዶክመንቶችን እና ማስታወሻዎችን በቀላሉ እንዲገኟቸው የሚጠያራቅሙበት ስርዓት ነው።

የስጋት ሞዴል

ለውሂብዎ ምን ዓይነት ጥበቃን ማድረግ እንደሚፈልጉ በትኩረት የሚያስቡበት ብልሃት ነው። ከሁሉም ዓይነት ማታለሎች ወይም ጥቃቶች ራስን መከላከል አዳጋች ነው። ስለዚህ ውሂብዎን ምን ዓይነት ሰዎች ሊፈልጉት እንደሚችሉ፣ ከውሂቡ ምን ሊፈልጉ እንዳሰቡ እና እንዴት ሊያገኙት እንደሚችሉ በትኩረት ማሰብ ይኖርብዎታል። ምን አይነት ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል ብሎ አስብዎ አስቅድሞ ጥቃቱን ለመከላከል ማቀድ የስጋት ሞዴል ይባላል። የስጋት ሞዴልዎን ከአወጡ በኋላ አደጋው የመድረሱን የመኾን ዕድል ትንተና ማካሄድ ይችላሉ።
 

የቁልፍ መለዋወጫ ድግስ

የአደባባይ ምሰጠራን ሲጠቀሙ መልዕክቱን ለማመስጠር የሚጠቀሙት ቁልፍ ባለቤትነቱ የመልዕክቱ ተቃባይ መኾኑን እርግጠኛ መኾን ይኖርብዎታል (የቁልፍ ማረጋገጫን ይመልከቱ)።
ለእዚህ ሂደት PGP የማቃለያ መንገድ አለው። ይህም ‘ይህ ቁልፍ ባለቤትነቱ የእዚህ ግለሰብ ነው ብዬ አምናለሁ እና እርስዎ የሚያምኑኝ ከኾነ እርስዎም ይህንኑ ይቀበሉ’። የአንድን ግለሰብ ቁልፍ ይህ ነው ብሎ በአደባባይ ማወጅ ‘ቁልፋቸውን መፈረም’ ይባላል። ይህ ማለት ማንኛውም ቁልፉን የሚጠቀም ሰው እርስዎ ስለቁልፉ ያወጁትን ይመለከታል ማለት ነው። ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ ቁልፉን እንዲያረጋግጥ ለማበረታት የ PGP ተጠቃሚዎች የቁልፍ መፈረሚያ ድግሶች ያዘጋጃሉ። ድግሶቹ ድግስ ቢኾኑም እንደ ስማቸው የሚያስደስቱ አይደሉም።

የቁልፍ ማረጋገጫ

በአደባባይ ስነመሰውር እያንዳንዱ ግለሰብ የቁልፎች ስብስብ አለው። ደህንነቱ የተጠበቀ መልዕክት ለመላክ የሚላክለትን ሰው ቁልፍ በመጠቀም መልእክቱን ያመሰጥሩታል። አጥቂዎች የእነርሱን ቁልፍ እንዲጠቀሙ ሊያታልሉዎት ይችላሉ። ይህ ማለት በታቀደለት ተቀባይ ፋንታ የላኩትን መልዕክት አጭበርባሪዎች ማንበብ ይችላሉ ማለት ነው። ይህ እንዳይከሰት የኾነ ቁልፍ በአንድ ግለሰብ ጥቅም ላይ እንደሚውል ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። አንድ ቁልፍን ከአንድ ግለሰብ ጋር የሚያዛምዱበት ማንኛውም ዓይነት መንገድ ነው።

የተጋላጭነት አዝማሚያ ትንተና

በኮምፒውተር ደህንነት ቋንቋ ለአደጋ ስጋቶች የመከሰት ዕዳላቸው ምን ያህል እንደኾነ ማስላት ሲኾን ለመከላከልም ምን ያህል ጥረት እንደሚያስፈልግ መረጃን ይሰጣሉ። በውሂብዎ ላይ ያለዎትን ቁጥጥር ወይም የመጠቀም ሊያጡ የሚችሉባቸው ብዙ የተለያዩ መንገዶች ቢኖሩም አንዱ ከሌላኛው የመከሰት ዕድሉ የተለያየ ነው። ተጋላጭነትን መገምገም ማለት የትኞቹን ስጋቶች የምር መውሰድ እንዳለብዎት እና ጊዜ ወስዶ ለማሰብ የትኖቹ ስጋቶች ብዙም ጉዳት የማያደርሱ (ወይም ለመከላከል በጣም አዳጋች እንደኾኑ) ወይም የመከሰት ዕድላቸው አናሳ እንደኾነ መወሰን ማለት ነው። የስጋት ሞዴልን ይመልከቱ።

የትዕዛዝ መስመር መሣሪያ

"የትዕዛዝ መስመር" ትንንሽ የተያያዙ እና ራሳቸውን የቻሉት ትዕዛዛትን ለኮምፒውተር ለኮምፕዩተር የሚሰጥበት መንገድ ነው። የትዕዛዝ መስመር መሣሪያን ለመጠቀም ተጠቃሚው የተለያዩ ትዕዛዛትን ተርሚናል ኢሙሌተር በሚባል መስኮት ላይ ጽፎ የኢንተር ወይም የሪተርን ቁልፍን ሲጫን በዛው መስኮት ላይ ለትዕዛዙ የጽሑፍ ምላሽ ያገኛል። አሁን ድረስ የዊንዶስ፣ የሊኒክስ እና የአፕል ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ይህንን የትእዛዝ መስመር ማስኬጃ ሶፍትዌር መጫን ይፈቅዳሉ። በተጨማሪም አንድ አንድ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ትክክለኛ መተግበሪያ ካገኙ የትዕዛዝ መስመርን ማስኬድ ይችላሉ። የትዕዛዝ መስመር ከኮምፒውተርዎት ስርዓተ ክውና ጋር አብረው ተጭነው የሚመጡ ሶፍትዌሮችን ለማሠራት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። አንዳንድ የሚወርዱ በተለይም ለቴክኒካዊ ነገሮች የሚጠቅሙ ፕሮግራሞች በልምድ በምንጠቀምባቸው አዶዎች እና ቁልፎች ምትክ የትዕዛዝ መስመርን ይጠቀማሉ። ተገቢውን ውጤት ለማግኘት ትክክለኛ የፊደሎችን እና የአሃዞችን ቅደም ተከተል በትክክል ማስገባት ግን ያስፈልጋል። አብዛኛውን ጊዜ የሚፈልጉትን ውጤት ካላገኙ ማድረግ የሚጠበቅብዎት ምን እንደኾነ ግልጽ አይደለም።

የትዕዛዝ እና ቁጥጥር ሰርቨር

(C&C or C2) በሸረኛ ሶፍትዌር ለተጠቁ መገልገያዎች ትዕዛዝ የሚያስተላለፍ እና ከእነዚህ ከተጠቁ መገልገያዎች መረጃን የሚቀበል ኮምፕዩተር ነው፡፡ አንዳንድ ሰርቨሮች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መገልገያዎች ይቆጣጠራሉ፡፡

የንግድ ቪፒኤን

የንግድ ምናባዊ የግል አውታረ መረብ የኢንተርኔት ግንኙነትዎን ደህንነቱ በተጠበቀ የግል አውታረ መረቡ የሚሰጥ የግል አገልግሎት አቅራቢ ነው፡፡ ጠቀሜታው የሚልኩትም ኾነ የሚቀበሉት ሁሉም ውሂብ ከአካባቢው ኔትወርክ የተደበቀ እንዲኾን ማድረግ ነው። በመኾኑም በአቅራቢያዎ ካሉ ወንጀለኖች፣ የማይታመኑ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ከማንኛውም የእርስዎን አከባቢ አውታረ መረብ ከሚሰልል አካል የሚጠብቅ የተሻለ አገልግሎት ያገኛሉ። የቪፒኤን አገልግሎቱ የሚከወነው ያለው በውጪ አገር ሊኾን ይችላል። ይህም ግንኙነትዎን ከመንግሥት ለመጠበቅ እና በሀገር ውስጥ የሚደረግ እገዳን ለማለፍ ይጠቅማል። የጎንዮሽ ጉዳቱ አብዛኞቹ የኢንተርኔት ግንኙነቶች በንግድ የቪፒኤን ሰጪው በኩል መታየት መቻላቸው ነው። ይህ ማለት የንግድ ቪፒኤን አቅራቢው (እና አገልግሎት ሰጪው የሚገኝበት ሀገር) የእርስዎን የኢንተርኔት ግንኙነት እንደማይሰልል ዕምነት ሊኖርዎ ይገባል።

የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃል

የማለፊያ ቃል አብዛኛውን ጊዜ በከፊል ቋሚ ነው። አንዴ ካዋቀሩት እስኪቀይሩት ወይም መልሰው እስኪያዋቅሩት ድረስ መጠቀም ይችላሉ። የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃል የሚያገለግለው ለአንዴ ብቻ ነው። አንዳንድ የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃል ስርዓቶች የሚሠሩት በርካታ የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃሎችን መፍጠር የሚችሉ መሣሪያዎችን ወይም ፕሮግራሞችን በመጠቀም ነው። እነዚህን የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃሎች ተራ በተራ መጠቀም ይችላሉ። ይህ የሚጠቅመው የማለፊያ ቃልዎን ማስገባት ባለብዎት ስርዓት ውስጥ የቁልፍ መዝጋቢ እንደተጫነ ከጠረጠሩ ነው።

የአየር ክፍተት

ኢንተርኔትን ጨምሮ ከሁሉም አውታረ መረቦች የተገለለ ኮምፒውተር ወይም ኔት ዎርክ የአየር ክፍተት የተፈጠረለት ይባላል።

የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራ

የተለምዶ የማመስጠሪያ ስርዓቶች መልዕክትን ለማመስጠር እና ለመፍታት ተመሳሳይ ምስጠራን ወይም ቁልፍን ይጠቀማሉ። ስለዚህ "bluetonicmonster" በሚል የማለፊያ ቃል ሰነድን ከተመሰጠረ እርስዎ ይህንን ለመፍታት ሰነዱን እና "bluetonicmonster" የሚለውን ምስጢር ማግኘት ይኖርብዎታል። የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራ ሁለት ቁልፎችን ይጠቀማል።አንዱ ለማመስጠር የሚያገለግል ሲኾን ሌላኛው ደግሞ ምስጢሩን ለመፍታት ነው። ይህ በርካታ ጥቅሞች አሉት። አንደኛው ጥቅም ሰዎች የሚልኩልዎትን መልዕክቶች የሚያመሰጥሩበትን መስጠት ይችላሉ (ሌላኛውን ቁልፍ በሚስጥር እስካቆዩ ድረስ)።
እናም ይህ ቁልፍ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ከእርስዎ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላል። ለሰዎች የሚሰጡት ቁልፍ "የአደባባይ ቁልፍ" ይባላል። የዚህም ዘዴ ስያሜ የመጣው ከዚህ ነው። የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራ ኢሜሎች እና ፋይሎችን ለማመስጠር እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነትን (PGP or Pretty Good Privacy)፣ ፈጣን የጽሁፍ መልዕክትን ለማመስጠር OTRን እና ለድር መዳሰሻዎች SSL/TLSን ይጠቀማል።

የአደባባይ ቁልፍ አገልጋይ

እንደ PGP ያለ የአደባባይ ስነመሰውርን ለሚጠቀም ግለሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ መልዕክትን ለመላክ ቢያቅዱ፤ መልዕክቱን ለማመስጠር መጠቀም ያለብዎትን ቁልፍ ማወቅ ይኖርብዎታል። የአደባባይ ቁልፍ አገልጋይ ለእነዚህ ቁልፎች እንደ ስልክ ቁጥር መዝገብ በመኾን ያገለግላል። ይህም ሶፍትዌሩ የኢሜል አድራሻን፣ ስምን፣ ወይም ቁልፍን በመጠቀም ሙሉ ቁልፉን ፈልጎ ለማውረድ ይፈቅዳል። ብዙ የPGP የአደባባይ ቁልፍ አገልጋዮች ቢኖሩም አብዛኛውን ጊዜ የቁልፍ ስብስባቸውን የሚጋሩት ግን እርስ በእርሳቸው ነው። የቁልፍ አገልጋዮች የሚያትሟቸው ቁልፎች እውነተኛ ወይም ሀሰተኛ እንደኾኑ አያረጋግጡም ። የአደባባይ ቁልፍ አገልጋይ ላይ ማንም ሰው በሌላ ሰው ስም ቁልፍን ሊጭን ይችላል። ይህ ማለት በቁልፍ አገልጋይ ላይ ከአንድ ሰው ስም ወይም ኢሜል ጋር የተያያዘ ቁልፍ የዛ ሰው እውነተኛ ቁልፍ ላይኾን ይችላል ማለት ነው። የቁልፉን እውነተኛነት ለማጣራት ፊርማውን ማጣራት ወይም በሚታመን መንገድ የጣት አሻራውን ከዋናው ተጠቃሚ ጋር ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።
PGP የሌሎች ሰዎችን ቁልፍ እንዲፈርሙ ይፈቅዳል። ይህም የእርስዎን ቁልፍ በመጠቀም አንድ ቁልፍ የኾነን ግለሰብን ለማግኘት ትክክለኛው ቁልፍ እንደኾነ የሚያረጋግጡበት መንገድ ነው። ይህም እውነተኛውን ከሀሰተኛ ቁልፍ ለመለየት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ተጠቃሚዎች የሚያውቋቸውን እና ግንኙነት የሚያደርጓቸውን ግለስቦች ትክክለኛ ቁልፍ ከፈረሙ ሌሎች ሰዎች በእነኚህ ፊርማዎች አማካኝነት ቁልፎቹ እውነተኛ እንደኾኑ ማረጋገጥ ይችላሉ። ከቁልፍ አገልጋይ ቁልፍ ሲያወርዱ የቁልፉን እውነተኝነት የሚያረጋገጥ የሌሎች ሰዎች ፊርማን አብረው ሊያወርዱ ይችላሉ። እነዚህን ሰዎች በእርግጥም ከአወቋቸው እና የእነርሱ እውነተኛ ቁልፍ ካለዎት አዲስ በአወረዱት ቁልፍ ተጨማሪ መተማመኛ ይኖርዎታል። ይህ የማረጋገጫ ሂደት የመተማመኛ ድር ይባላል። የእዚህ የማረጋገጫ ሂደት ጥቅሙ ያልተማከለ እና በአንድ ባለ ስልጣን ቁጥጥር ስር አለመኾኑ ነው። ስለዚህ ለአዲስ አንድ ቁልፍን ተጠቅመው ለግለሰብ መልዕክት ሲጽፉ የኾነ ኩባንያን ወይም መንግሥትን ማመን አይጠበቅብዎትም። በምትኩ የራስዎን ማኅበራዊ መረብን ማመን ይችላሉ። የመተማመኛ ድር ዋነኛ የጎንዮሽ ጉዳቱ የሌሎች ሰዎችን ቁልፍ ሲፈርሙ እውቂያዎት እነማን እንደኾኑ ለመላው ዓለም ማሳበቁ ነው። ይህም በግል የሚያገኟቸው ሰዎችን ዝርዝር እና ማንነት አደባባይ ያወጣዋል። በተጨማሪም መተማመኛ ድርን በትክክል ለመጠቀም ሠፊ ጊዜ እና ትኩረት የሚፈልግ ሲኾን አንዳንድ የማኅበረሰቡ አባላት በጥቂቱ ወይም ጭራሽኑ አጠቀሙትም።

የከርሞ ምስጢራዊነት

አንዱ የግል ቁልፍዎ ቢሰረቅ እንኳን የቀድሞ ግንኙነትዎ ደህንነት እንደተጠበቀ የሚያረጋግጥ ደህንነቱ የተጠበቀ
አንዱ የግል ቁልፍዎ ቢሰረቅ እንኳን የቀድሞ ግንኙነትዎ ደኅንነት እንደተጠበቀ የሚያረጋግጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመልእክት መላኪያ ስርዓት መግለጫ ባህሪ ነው። ለHTTPS መካነ ድሮች የከርሞ ምስጢራዊነት በጣም በርካታ የትራፊክ መረጃዎችን ከሚመዘግቡ እና የተሰረቀ ቁልፍን ተጠቅመው ሚስጥራዊ መልዕክቶችን ከሚፈቱ እንደ መንግስት ካሉ የደኅንነት ኤጀንሲ አጥቂዎች ለመከላከል አስፈላጊ ጥበቃ ነው። የከርሞ ምስጢራዊነት ለፈጣን የመልዕክት አገልግሎት እና የመወያያ ስርዓቶች የተሰረዙ መልዕክቶች እስከ ወዲያኛው እንደተሰረዙ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ወደ አገልግሎቱ መግባትን ማቦዘን ወይም የቀድሞ መልዕክቶችን ደኅንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሰረዝ ይኖርብዎታል።
መላኪያ ደንብ የመግለጫ ባህሪ ነው።  ለHTTPS ድረ ገጾች የከርሞ ምስጢራዊነት በጣም በርካታ የትራፊክ መረጃዎችን ከሚመዘግቡ እና የተሰረቀ ቁልፍን ተጠቅመው ሚስጥራዊ መልዕክቶችን ከሚፈቱ እንደ መንግስት ካሉ የደህንነት ኤጀንሲ አጥቂዎች ለመከላከል አስፈላጊ ጥበቃ ነው።  የከርሞ ምስጢራዊነት ለፈጣን የመልዕክት አገልግሎት እና የመወያያ ስርዓቶች የተዘረዙ መልዕክቶች እስከ ዘላለሙ እንደተሰረዙ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ወደ አገልግሎቱ መግባትን ማቦዘን ወይም የቀድሞ መልዕክቶችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሰረዝ ይኖርብዎታል።

የኮርፖሬት የውስጥ አውታረ መረብ ወይም ኔትወርክ

አብዛኛውን ጊዜ ትላልቅ ተቋማት እና ኩባንያዎች ከራሳቸው የውስጥ አውታረ መረብ የሚገኙ አገልግሎቶችን (ለምሳሌ የኢሜል፣ የድር፣ እና የሰነዶች እና የፕሪንተር) ይሰጣሉ። ነገር ግን እነኚህ አገልግሎቶች ከውስጥ አውታር ወጪ በኢንተርኔት ላይ ማግኘት አይቻልም። አብዛኞቹ ተቋማት ይህ የውስጥ ሰነዶቻቸውን ለመከላከል በቂ እንደኾነ ያስባሉ። ነገር ግን ከውስጥ ኔትወርክ ጋር መገናኘት የሚችል ማንኘውም በአካባቢው ያሉ ሰነዶችን ማግኘት ወይም ጣልቃ በመግባት መጥለፍ ይችላል። አንድ ሰራተኛን በላፕቶፑ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌርን እንዲጭን ማታለል የእዚህ ዓይነት ጥቃት ምሳሌ ሊኾን ይችላል።
ተቋማት ሰራተኞቻቸው ኢንተርኔትን ተጠቀመው ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የውስጥ ኔትወርክ ላይ ያሉ ሰነዶችን እንዲያገኙ ሃሳባዊ የግል ኔትወርክ (VPN) አገልግሎትን ያቀርባሉ። ይህም ለመስሪያቤቱ የውስጥ ኔትወርክ ጥበቃን ይሰጣል።

የይለፍ ቃል

የሚታወስ ሚስጢር ሲሆን የሆነ ነገርን ማግኘት ላይ ገደብ ይጥላል፡፡ ስለዚህ ያንን ነገር ማግኘት የሚችለው የይለፍ ቃሉን የሚያውቀው ብቻ ነው፡፡ የመስመር ላይ መለያ፣ መሳሪያ፣ ወይም ወደ ሌላ ነገር ውስጥ ማግባትን ሊገድብ ይችላል፡፡ በበርካታ ቃላት የተመሠረተ ረጅም የይለፍ ቃል አንድ «ቃል» አለመሆኑን እንድናስታውስ «የይለፍ ሐረግ» ይባላል፡፡ የይለፍ ቃል አስተዳደር ወይም የይለፍ ቃል መተግበሪያን ለመክፈት የሚያስችለን ዋና የይለፍ ቃል በአብዛኛው "ዐብይ ይለፍ ቃል" ይባላል::

የደህንነት ጥያቄ

የማለፊያ ቃሎችን ለማጠናከር አንዳንድ ስርዓቶች "የደህንነት ጥያቄዎችን" ይጠቀማሉ። እነዚህም እርስዎ ብቻ መልሳቸውል ሊያውቋቸው የተገቡ ጥያቄዎች ናቸው። የደህንነት ጥያቄዎች ችግር በጣም ሊገመት የሚችል መልስ ያላቸው ልክ እንደ ተጨማሪ የማለፊያ ቃሎች መኾናቸው ነው። የደህንነት ጥያቄዎችን እንደ ማንኛውም የማለፊያ ቃል እንዲቆጥሯቸው እንመክራለን። ጥያቄዎቹን ለመመለስ ረዥም፣ አዲስ፣ በዘፈቀደ የተፈጠረ ሐረግን ይፍጠሩ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡት። ስለዚህ ባንክዎ የእናትዎን አባት ስም ሲጠይቅዎት ከ"ፈረስ ቤት ባትሪ ወንዝ" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ የኾነ በዘፈቀደ የፈጠሩትን መልስ ለመመለስ ይችላሉ።

የደኅንነት የምስክር ወረቀት

የሶስተኛ አካል ጥቃትን ለመከላከል የአደባባይ ትክክል(በተለየ አካል ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን) መሆኑን ወዲያውኑ ማረጋገጥ የሚቻልበት መንገድ ነው፡፡ በአብዛኛው መካነ ድሮች ከትክክለኛው መካነ ድር ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት እንዳለዎት እና ግንኙነትዎን ሌላ አካል አንዳላዛባው ለማረጋገጥ ይጠቀሙበታል፡፡

የድር መዳሰሻ

ድረ ገጾችን ለማየት የሚጠቀሙት ፕሮግራም: ፋየርፎክስ፣ ሳፋሪ፣ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር፣ እና ክሮም ሁሉም የድር መዳሰሻ ናቸው። ስማርት ስልኮች አብሮ ገነብ የኾነ ለተመሳሳይ ዓላማ ማለትም ለድር መዳሰሻ የሚውል መተግበሪያ አላቸው።

የድር ማሰሻ ማጥለያ ቅጥያ

አንድ ድረ ገጽን በሚጎበኙበት ወቅት የድር ማሰሻዎ ለድረ ገጹ አስተዳዳሪ አንዳንድ መረጃዎችን ይልካል። ለምሳሌ IP አድራሻን፣ ስለ ኮምፒውተርዎ አንዳንድ መረጃዎችን እና ይህንን የድር መዳሰሻ ተጠቅመው ያደረጓቸውን የቀድሞ ዳሰሳዎች የሚያያይዙ ኩኪዎችን ሊይዝ ይችላል። ድረ ገጹ ከሌላ የድር አገልጋይ የተወሰዱ ስእሎችን እና ይዘቶችን የሚጨምር ከኾነ ከእነዚህ ድረ ገጾች ላይ የኾነ ይዘትን እንዳወረዱ ወይም እንደጎበኙ የሚናገር ተመሳሳይ መረጃ ለእነዚህ ድረ ገጾች ይላካል። የማስታወቂያ መረቦች፣ ትንተና አቅራቢዎች እና ሌሎች ውሂብ ሰብሳቢዎች መረጃዎችን ከእርስዎ የሚሰበስቡት በዚህ መልክ ሊኾን ይችላል።
ከድር መዳሰሻዎ ጋር ጎን ለጎን የሚሠራ ተጨማሪ ሶፍትዌርን መጫን እና በዚህ መንገድ ለሶስተኛ ወገን የሚሾልከውን የመረጃ መጠን መቀነስ ይችላሉ። እጅግ በጣም ታዋቂ ምሳሌዎች ማስታወቂያን የሚያገዱ ፕሮግራሞች ናቸው። EFF ፕራይቬሲ ባጀር የተሰኘውን ሌላ የትራፊክ ማገጃ ቅጥያ መሣሪያን ይሰጣል።

የጎራ ስም

የኢንተርኔት አገልግሎት ወይም የደረ ገጽ አድራሻ በቃላት ሲገለጽ። ለምሳሌ : ssd.eff.org የሚለው።

የጣት አሻራ

ቁልፎች በጣም ረዥም ናቸው። አልፎ አልፎ በሺዎች የሚቆጠሩ ወይም የላቀ ርዝመት ያላቸው ሊኾኑ ይችላሉ። ከዚህ አንፃር አነስተኛ ወይም የተወሰኑ የቁጥሮች እና የፊደሎች ስብስብን የያዘ ሲኾን የቁልፉን አሃዞች ሳይዘረዝሩ እንደ ተለየ የቁልፍ መጠሪያነት ሊያገለግል ይችላል። ለምሳሌ እርስዎ እና ጓደኛዎ ተመሳሳይ እንዳላችሁ ለማረጋገጥ ብትፈልጉ በቁልፉ የሚገኙትን በሺዎች የሚቆጠሩ አሃዞች በማንበብ ብዙ ጊዜ ማጥፋትን ወይም በምትኩ ሁለታችሁም የቁልፉ የጣት አሻራን በማስላት የማነጻጸር ምርጫ አላችሁ። አብዛኛውን ጊዜ በስነመሰውር ሶፍትዌር የሚቀርቡ የጣት አሻራዎች ወደ 40 የሚጠጉ የፊደሎች እና የአሃዞች ስብስብን የያዘ ነው። የጣት አሻራው ተመሳሳይ እንደኾነ በጥንቃቄ ለማጣራት ከሞከሩ በመሃል ገብቶ በማስመሰል ሊያታልል ከሚሞክር አካል የተጠበቁ ኖዎት። አንዳንድ ሶፍትዌሮች የጓደኛን ቁልፍ ለማረጋገጥ እጅግ ምቹ የኾኑ አማራጮችን ሊሰጡ ይችላሉ። ነገር ግን የግንኙነት አገልግሎት አቅራቢዎች በቀላሉ ግንኙነቱን እንዳይሰሙ አንዳንድ የማረጋገጫ ዓይነቶች ይህን ስለላ መከላከል የሚችሉ መኾን ይኖርባቸዋል።
 

የፋይል ጣት አሻራ

የአደባባይ ቁልፍን የሚወክሉ ፊደሎች ወይም ቁጥሮች ቅደም ተከተል ነው፡፡ አንዳንድ የግላዊነት መሣሪያዎች ሌሎች ሰዎች በመሳሪያቸው ላይ ያደረጉትን በእርስዎ መሣሪያ ትክክለኛነትነቱን እንዲያረጋግጡ ያደርጋሉ፡፡ የዚህ ዓላማ መካከለኛ የሆነ ሰው የተሳሳተ ቁለፍ በመጠቀም እንዳያታልዎ መከላከል ነው፡፡

ያልተማከለ አገልግሎትን የሚዘጋ ጥቃት
በተቀናጁ በርካታ ኮምፒውተሮች አማካኝነት የጥቃቱ ዒላማ ለኾነ ድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት ጥያቄ እና ዳታ በአንድ ግዜ ልኮ በማጨናነቅ ድረገጹን ከመስመር ውጪ እንዲኾን ማድረግ ነው። ለእንደዚህ ዓይነት አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒወተሮች አብዛኛውን ግዜ ከርቀት በወንጀለኞች ቁጥጥር ሥር ያሉ ናቸው። ወንጀለኞቹ እነዚህን ኮምፒውተሮች በቁጥጥር ሥር የሚያውሉት ሰብሮ በመግባት ወይም በሸረኛ ሶፍትዌሮች በመበከል ነው።

ደህንነታቸው የተጠበቀ ሶኬቶች ድርብርብ (SSL)

በኮምፒተርዎ እና አንዳንድ ከሚጎበኟቸው መካነ ድሮች እና የበይነ መረብ አገልግሎቶች ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተመሰጠረ ግንንኙነትን ለመጠበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከአንድ መካነ ድር ጋር ሲገናኙ የመካነ ድሩ አድራሻ ከ HTTP ይልቅ በ HTTPS ይጀምራል፡፡ እንደ ኤ.አ.አ በ1999 ስሙ በይፋ ወደ ትራንስፖርት ሽፋን ደኅንነት (TLS) ተቀይሯል፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች አሁንም የድሮውን ስም ይጠቀማሉ፡፡

ደንብ (ፕሮቶኮል)

የግንኙነት ፕሮቶኮል በፕሮግራሞች ወይም በኮምፒውተሮች መካከል ውሂብን የማስተላለፊያ ዘዴ ነው። ተመሳሳይ ደንብ (ፕሮቶኮል) የሚጠቀሙ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች እርስ በእርሳቸው መግባባት ይችላሉ። የድር መዳሰሻዎች እና የድር አገልጋዮች በተመሳሳይ ደንብ ይግባባሉ። እርሱም "http" ይባላል። አንዳንድ ደንቦች ይዘታቸው እንዳይታይ ለመከላከል ምስጠራን ይጠቀማሉ። የhttp ደንብ ደህንነቱ የተጠበቀው ሥሪት "https" በመባል ይታወቃል። ሌላኛው በበርካታ ፕሮግራሞች ጥቅም ላይ የሚውለው የምስጠራ ደንብ ምሳሌ OTR (Off-the-Record) ነው። ይህ ለፈጣን መልዕክት የምንጠቀመው ደንብ ነው።

ዲጂታል ፊርማ

የመረጃ ምንጩ ትክክል መሆኑን እና ከተጻፈበት ጊዜ ጀምሮ እንዳልተቀየረ ለማረጋገጥ ሂሳባዊ የቴክኒክ ዘዴን የመጠቀም ስልት ነው፡፡ የዲጂታል ፊርማዎች ሶፍትዌሮችን ከኢንተርኔት አውርደን ስንጭን እየጫንን ያለነው ሶፍትዌር ከትክክለኛው ስሪት ህትመት ጋር እኩል መሆኑን እና ማንም እንዳላዛባው እርግጠኛ ለመሆን ያገለግሉናል፡፡ እንዲሁም ለተመሰጠሩ ኢሜሎች እንዳልተቀየሩ ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ መረጃ በዲጂታል ፊርማ የማይጠበቅ ከሆነ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ወይም ሌላ የመገናኛ አውታር ሰው የተጻፈውን ወይም የታተመውን ይዘት ሊቀይር ይችላል፡፡ ይህ እንደተከሰተ ለማወቅ የሚያስችል ቴክኒካዊ ዘዴ አይኖርም፡፡

ድር ላይ የተመሠረተ የእጅ አዙር አገልጋይ

የታገዱ ድረ ገጾችን ለማግኘት ያገለግላል። በአጠቃላይ የታገደውን ድረ ገጽ አድርሻ በአድራሻ (URL) አሞሌው ላይ እንዲያስገቡ ውክልናውን ይወስዳል። በመቀጠልም የድር አድራሻውን በተወካዩ ገጽ ላይ ያሳያል። ይህ ከሌሎች የመስመር ላይ እገዳን ከሚከላከሉ አገልግሎቶች በተሻለ መልኩ ቀላል ነው

ጊዜያዊ አድራሻ

ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም ደግመው የማይጠቀሙት የኢሜል አድራሻ ነው። ከማንነትዎ ጋር የተያያዘውን የኢሜል አድራሻዎን ሳይገልጡ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለመመዝገብ የሚጠቀሙት ነው።

ጊዜያዊ ወይም በርነር ስልኮች

ከማንነትዎ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌሌው፣ አንዳንድ ትናንሽ የስልክ ጥሪዎችን ወይም እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እና ክትትል እንደሚደረግበት ወይም ለአደጋ እንደተጋለጠ በሚጠረጠርበት ወቅት ሊወገድ የሚችል ስልክ ነው። ጊዜያዊ ስልኮች አብዛኛውን ጊዜ በጥሬ ገንዘብ የሚገዙ የቅድሚያ ክፍያ ስልኮች ናቸው።

ጥቃት

በኮምፒውተር ደህንነት ጥቃት ማለት ደህንነት ለአደጋ ለማጋለጥ በጥቅም ላይ የሚያውሉት፣ ወይም የሚጠቀሙት ዘዴ ነው። ደግሞ ጥቃትን የሚሰነዝር ሰው ወይም ድርጅት ነው። የጥቃት ዘዴ አንዳንድ ጊዜ "ብዝበዛ" ያባላል።

ጥንድ ቁልፍ

የአደባባይ ስነመሰውርን በመጠቀም የተመሰጠሩ መልዕክቶችን ለመቀበል (እና በአስተማማኝ ኹኔታ መልዕክቱ ከእርስዎ እንደመጣ ለሌሎች ለማሳወቅ) ሁለት ቁልፎችን መፍጠር ይጠበቅብዎታል። አንደኛው በምስጢር የሚጠብቁት የግል ቁልፍ ነው። ሌላኛው ደግሞ ሌሎች እንዲያዩት የሚፈቅዱት የአደባባይ ቁልፍ ነው። እነዚህ ሁለት ቁልፎች ቀመራዊ በኾነ መንገድ የተያያዙ ሲኾኑ በብዛት በጋራ ስማቸው "ጥንድ ቁልፍ" ይባላሉ።

ጸረ ቫይረስ

አንድ መሣሪያ በሸረኛ ሶፍትዌር (ወይም ማልዌር) ቁጥጥር ሥር እንዳይውል የሚከላከል ሶፍትዌር ነው። "ቫይረሶች" የመጀመሪያዎቹ እና በብዛት የሚገኙ የሸረኛ ሶፍትዌር ዓይነቶች ሲኾኑ ስያሜያቸው ከአንድ መሣሪያ ወደ ሌላ መሣሪያ የሚዘዋወሩበት መንገድን ያንጸባርቃል። በአሁኑ ሰዓት ያሉት ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ከሌላ ምንጭ የሚያወርዷቸውን ሰነዶች ከራሳቸው የሸረኛ ሶፍትዌር ጽንሰ ሃሳብ ጋር እያወዳደሩ እና እየገመገሙ ማስጠንቀቂያ የሚሰጡ ናቸው።
የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ሸረኛ ሶፍትዌሮችን የሚያውቁት ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሩን ያበለጸገው ግለሰብ ሲሰራቸው ሸረኛ ሶፍትዌሩን እንዲያውቁት የሚያደርግ የትንተና አቅም ሲፈጥርላቸው ነው። ይህም የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች አንድን ግለሰብ ወይም የተወሰኑ የማህበረሰብ አባላትን ለማጥቃት ኾን ተብሎ ታቅዶ የተሰራን ሸረኛ ሶፍትዌርን የመከላከል ውጤታማነታቸውን ይቀንሰዋል። አንድ አንድ በሳል ሸረኛ ሶፍትዌሮች የሚያጠቁት በንቃት ሲኾን ራሣቸውንም ከጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች መከላከል ይችላሉ።

ጽኑ ኬላ

ኮምፒውተርን ካልተፈለገ ግንኙነት ወይም የአካባቢ ኢንተርኔት ንክኪ የሚከላከል መሣሪያ ነው ። ጽኑ ኬላ (Firewall) የሚላኩ ኢሜሎችን ወይም ከድረ ገጽ ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን የሚከለክል ሕግ ሊኖረው ይችላል። ጽኑ ኬላ የመጀመሪያው ግንብ በመኾን ኮምፒውተርን ካልታሰበ ጥቃት ወይም ሊከላከል ይችላል። ወይም ተጠቃሚዎች ኢንተርኔትን በተወሰኑ መንገዶች እንዳይጠቀሙ ይከላከላል።
ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል
Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡
Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ
1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡
2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.
3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡
4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜየተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Uninstall Updates”
5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡
6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ
7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡
8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡
በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡
ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ
$$$$$$$$$$$$$$$$$%%$%%$$$
በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት #YouTube ቻናል ከፍተን የናንተን መምጣት እየተጠባበቅን ነው።
#Subscribe ላደረጋችሁ ያለው ጥቅም ⬇️⬇️⬇️
1. እዚ ለመፃፍ የማይመቹ #ጥያቄዎቻችሁን በቪድዩ📹 እንመልስላችኋለን።
2. አዳዲስ #የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይቀርቡበታል። 👍
3. በሀገራችን አሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ሰዎች ልምዳቸውን ለናንተ ያካፍላሉ። 👨‍💻👩‍💻
4. Wifi hacking, Facebook hacking, ROOT አልሆኑም ያሉ ስልኮችን እንዴት #ሩት እንደምታደርጉ እናሳያለን።
⚠️Subscribe ስታደርጉ የምንለቃቸው ፕሮግራሞች ወዲያው ይደርሷችኋል።
⚠️ ቴክኖሎጂን ከ"ሀ" ለምትጀምሩ ሰዎች በቀላሉ ብዙ ነገር አውቃችሁ ከሌላው በላይ ትሆናላችሁ።
⚠️መሰረታዊ ነገር ለምታውቁም በደንብ ይረዳችኋል።
⚠️በተጨማሪም ይበልጥ እንድንሰራ ድጋፍ ትሆኑናላችሁ።
⚠️⚠️ሌላው እንድታውቁልን የምንፈልገው ነገር #YouTube እንደምንፈራው ብዙ ብር አይበላም ካላመናችሁን ትንሽ የገንዘብ መጠን ስልካችሁ📱 ውስጥ ባለበት ሰአት ከፍታችሁ ሞክሩት።👍👍
ሊንካችን 👇👇👇
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች
==================
የተወሰኑ በሽታዎች በዘር ወደ ልጅ ወይም ወደ የልጅ ልጅ እየተላለፉ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ በሽታዎች በተፈጥሮ የሰውነት አወቃቀር ምክንያት የሚመጡ፤
አንዳንዶች ደግሞ ተመሳሳይ የመኖሪያ ቦታን በመጋራት፣ ተመሳሳይ ምግብ ሁሌ በመመገብ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ሊይዝዎት ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ በዘር ከሚተላለፉ በሽታዎች ውስጥ የተወሰኑትን ከዚህ ቀጥሎ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
1. የስኳር በሽታ
ሁለቱም ዓይነት 1 አይነት እና 2 የሚባሉት የስኳር በሽታ አይነቶች በዘር ይተላለፋሉ፡፡ በየትኛውም ዓይነት የስኳር በሽታ ተጠቂ የሆነ የቤተሰብ አባል ካሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የደሞን የስኳር መጠን እየተመረመሩ ይከታተሉት፡፡
ምንም እንኳን ዓይነት 1 የስኳር በሽታን እንዳይዘን ማስቀረት ባይቻልም፤ ዓይነት 2 ግን እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው በጤናማ አመጋገብና ስፖርትን በመሥራት ነው፡፡
2. የጡት ነቀርሳ (ካንሰር)
የጡት ካንሰር ጂን 1 እና የጡት ካንሰር ጂን 2 በመባል የሚታወቁ በዘር የሚተላለፉ የሰውነት መዋቅሮች (ጂኖች) አሉ፡፡ የቤተሰብዎ አባላት በተለይም እናትዎ፣ እህትዎ ወይም ሴት ልጅዎ የጡት ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ በቶሎ እርስዎም መመርመር ይኖርብዎታል፡፡
3. የማህፀን ካንሰር (ነቀርሳ)
ይህን ዓይነት ካንሰር የጡት ካንሰር ጂኖች እራሳቸውን በመለወጥ ሊያመጡት ይችላሉ፡፡ እናቶ፣ የሴት ልጅዎ ወይም እህትዎ የማህፀን ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ
እርስዎም በህይወትዎ የ 5 በመቶ በዚህ በሽታ የመያዝ ዕድል አለዎት፡፡ በሽታው ሳይባባስ በጊዜ ለማወቅ መመርመር ይበጃል፡፡
4. ከፍተኛ የደም ግፊት
ከፍተኛ የደም ግፊትን ተመርምሮ የታዘዘን መድኃኒት በተገቢው መልክ በመከታተል፣ ጤናማ አመጋገብ በመመገብና የሰውነት እንቅስቃሴ (ስፖርትን)
በመሥራት ልንቆጣጠረው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች በሽታው በጣም እስኪባባስ ድረስ እንዳለባቸው አያውቁትም፡፡ ከወላጆች አንዳቸው የደም ብዛት ተጠቂ ከሆኑ፤ በየጊዜው በመመርመር ጤናዎን መከታተል ይኖርብዎታል፡፡
5. ከፍተኛ ኮሌስትሮል!
ኮሌስትሮል የምንለው በቀይ የደም ሴሎች (በደምዎ) ውስጥ የስብ ብዛትን ነው፡፡ በበዛ ቁጥር ለጤና በጣም አደገኛ ነው፡፡ የኮሌስትሮል መጠንዎን ጤናማ
አመጋገብን በመከተልና ስፖርት በመስራት ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የኮሌስትሮል መጠንዎን የማይቆጣጠሩት ከሆነና ወላጅዎ ወይም ልጅዎ ከ55 ዓመታቸው በፊት ለልብ ህመም የተጋለጡ ከሆነ አደጋ ላይ እንደሆኑ ይወቁ፡፡
የኮሌስትሮል መጠነንዎን በየጊዜው ይከታተሉ፡፡
6. ግላውኮማ
ግላውኮማ በዘር የሚተላለፍ የዓይን በሽታ ነው፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ የግላውኮማ ችግር ካለ ጨርሶ እንዳይዝዎት ማድረግ ባይቻልም በህክምና ማዳን ግን ይቻላል፡፡
7. ድብርት
በድብርት ምክንያት የመጣ የአእምሮ ህመም በቤተሰብዎ ውስጥ ካለ ያ የታመመ ሰው በዘር ተላልፎበት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ነገር ግን ልብ ይበሉ፡፡ ይህ በሽታ ሁሌ በዘር ብቻ ተላልፎ አይዝም፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ ይህ በሽታ ባይኖርም እርስዎ በራሶ ሊይዝዎት ይችላል፡፡
8. አለርጂ እና አስም!
አለርጂ የምንለው ለምሳሌ የአበባ የወንዴ አባላዘር ብናኝ ሲሸተን ዓይናችንን የመቆጥቆጥ እና የመቅላት፣ የመተንፈሻ አካሎቻችን ማሳከክ እና ለመተንፈስ
መቸገር ዓይነት ምልክት ካሳየን አለርጂ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህም አለርጂ በዘር ይተላለፋል፡፡
ከወላጅዎ አንዳቸው በአለርጂ ከተጠቁ እርስዎም 50 በመቶ የመያዝ ዕድል አሎት፡፡ ሁለቱም ወላጆቾ ደግሞ ካለባቸው የ75 በመቶ የመያዝ ዕድል አለዎት ማለት ነው፡፡ አስምም ብዙ ጊዜ ከአለርጂ ጋር በአብዛኛው ዝምድና አለው ተብሎ ይታመናል፡፡
╚═════📌Share📌════╝
subscribe to our loved ones and respected followers on Youtube, because we open new youtube channel.
የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe አድርጉ።
🔸Subscribe ያላደረገ video ሊደርሰው ወይም መከታተል አይችልም። click z link below to subscribe
👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
ምግብ ከተመገቡ በኋላ በፍጽም ሊያደርጓቸው የማይገቡ ተግባሮች
1. ትኩስ ሻይ መውሰድ/ መጠጣት!
ሻይ ምግብ ከተመገብን በኋላ ወዲያው መጠጣት የበላነው ምግብ እንዳይዋሀድ ያደርጋል። ሻይ ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር የተመገብነው ምግብ ውስጥ የሚገኘውን ብረት(iron) ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድ ለብረት እጥረት እና ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል። በተጨማሪም ሻይ (Tannin) የተሰኝውን ንጥረ ነገር በመያዙ ሰውነታችን ፕሮቲን እንዳይመጥ ያደርገዋል። ስለዚህ ሻይን ምግብ ከተመገቡ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በኃላ መውሰድ ለጤናዎ እጅግ አስፈላጊ ነው።
2. አትክልቶችን (ፍራፍሬዎችን) መመገብ!
ፍራፍሬዎችን ከምግብ በኋላ መመገብ ከተመገብነው ምግብ ጋር በማጋጨት ወደ ጨጓራችን እንዳይደርስና ብሎም ከርሳችን እንዲነፋ ያደርጋሉ። በመሆኑም ፍራፍሬዎችን ከምግብ በኃላ ከመመገብ ይልቅ በጠዋት መመገብ ንጥረ ነገራቸውን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረድናል።
3. ሲጋራ ማጨስ!
ትንባሆ ከምግብ በፊትም ሆነ በኋላ ማጨስ ጤናማ አይደለም። ትምባሆ በውስጡ እስከ 60 የሚደርሱ ካርሲኖጅን(Carcinog
en) የተሰኝ ካንሰርን የሚያስከትሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል። በተጨማሪም ትንባሆ ኒኮቲንና ታር የተሰኙ ጤናን የሚጎድ ነገሮችን ይዟል። ከምግብ በኃላ ትምባሆ ማጨስ ማለት 10 ሲጋራዎችን ከምግብ ሰዓት ውጪ በማጨስ ከሚከሰተው ካንሰርን እና የመተንፈስ ስርዓትን ለሚያውክና ለመሳሰሉ በሽታዎች የማጋለጥ አቅም ይኖረዋል።
4. ቀዝቃዛ ውሀ መጠጣት!
ቀዝቃዛ ውሀ ከምግብ በኋላ መውሰድ ምግብን አንድ ላይ በማሰባሰብ የምግብ እንሽርሽሪት ጤናማ እንዳይሆን ያደርገዋል። ቀዝቃዛ ውሀ ከመጠቀም ይልቅ ሞቅ ያለ ውሀ ያለ ውሀ መጠቀም ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን እንዲመጥ ያግዘዋል። ከዚህ በተጨማሪም ውሀን ከምግብ በፊት መውሰድ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮች እንዲዘገዩ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራሉ።
5. እንቅልፍ መተኛት!
ምግብ ከተመገብን በኋላ ወዲያው መተኛት የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ያደርጋል። በሌላ በኩልም ስርዓተ እንሽርሽሪትን በማስተጔጎል የከርስና የሆድ ችግር ያስከትላል።
6. ሰውነትን መታጠብ/ ሻወር መውሰድ!
ሰውነትን መታጠብ የደም ዝውውር በተለይ በእጅ እና እግር አካባቢ እንዲፋጠን ያደርገዋል። ይህም በሆድ አካባቢ የሚገኝን የደም ክምችት እንዲቀንስ እና የምግብ እንሽርሽሪት እንዲዳከም ያደርጋል ከዚህ ባሻገር የልብ ችግር ሊያስከትል ይችላል።
7. ውዝዋዜ!
የሰውነት እንቅስቃሴና ውዝዋዜ ማድረግ ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን በአግባቡ እንዳይመጥ(እንዳይዝ) ያደርገዋል።
8. የእግር ጉዞ!
ከምግብ በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ ተገቢ አይደለም። እንሽርሽሪት ስርዓት እንዳይኖረውና ያልተለመደ የአሲድ ኡደት በብዙዎች ዘንድ እንዲፈጠር ያደርጋል። ስለሆነም የእግር ጉዞን ከ 20 ደቂቃ የምግብ ሂደት በኃላ ቢደረግ ይመከራል።
9. ቀበቶ መፍታት/ማላላት!
ምግብ ሳይመገቡ ቆይታ ማድረግ ጤናማ ያልሆነና ልማዳዊ ድርጊት መሆኑ ይታወቃል ይህም ለምግብ አመጋገብ ጥሩ የማይባል ስርዓት ነው።ስለዚህ ምግብን በመጠኑና በአግባቡ ቀበቶዎትን ሳያላሉና ሳይፈቱ መመገብ ከአቅም በላይ በመመገብ የሚከሰትን ችግር መከላከል ይቻላል።
መልካም ጤንነት!!!
ምንጭ፦ webmd.com
╚═════📌Share📌════╝
subscribe to our loved ones and respected followers on Youtube, because we open new youtube channel.
የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe አድርጉ።
🔸Subscribe ያላደረገ video ሊደርሰው ወይም መከታተል አይችልም። click z link below to subscribe
👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
#በኢ_ሜይል አካውንቶች ላይ የሚቃጡ የመረጃ ጥቃቶች ምን ዓይነት ናቸው?
#እንዴትስ_መከላከል_እንችላለን ?
✏️ፊሺንግ #Phishing አንዱ የሳይበር ጥቃት ዓይነት ሲሆን የኢ-ሜይል አድራሻችንን መሠረት በማድረግ ለሚፈፀም የጥቃት ዓይነት የተሰጠ ሙያዊ ቃል ነው፡፡
የፊሺንግ ጥቃት ወንጀለኞች ግላዊ የሆኑ መረጃዎቻችንን ለመስረቅ ወይም ላልተገባ ዓላማ ለማዋል የሚጠቀሙበት የማጭበርበሪያ መንገድ ነው፡፡
ለምሣሌ የባንክ የሒሳብ ቁጥራችንን ወይም የይለፍ-ቃሎቻችንን ለመመንተፍ በኢ-ሜይል አድራሻችን የሚላኩ የማደናገሪያ መልዕክቶች ናቸው፡፡
✏️በኢ-ሜይል አድራሻ የሚላኩ የፊሺንግ መልዕክቶች ለተጠቃሚዎች እውነተኛ የሚመስሉ፤ ተጠቃሚውን ከተለያየ ዓይነት የጥቃት ሥጋት ለመጠበቅ ወይም ለመርዳት እንደሆነ የሚገልፁ እና አንዳንድ ጊዜም ተጠቃሚዎች ሎተሪ ወይም ነጻ የትምህርት ዕድል አሸናፊ እንደሆኑ የሚያበስሩ በመምሰል የማታለል ዓላማ ያላቸው ይዘቶች ናቸው
✏️የመረጃ መንታፊዎቹ ያዘጋጁትን አገናኝ #Link ተጠቃሚዎች እንዲከፍቱ በማግባባት እውነተኛ የዕድሉ አሸናፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በሚመስል አግባብ አካውንታቸውን እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃል እንዲያስገቡ በመጠየቅ ጥቃት ለማድረስ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡
የፊሺንግ ጥቃት ፈጻሚዎች ዋና ዓላማ የግለሰቦችን የባንክ ቁጥር ለመመንተፍ ወይም ግላዊ መረጃዎችን ለሌሎች አሳልፎ ለመሸጥ በማቀድ የሚፈጸም ህገ-ወጥ ተግባር ነው፡፡
✏️የፊሺንግ ጥቃትን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
የርዕሰ ጉዳዩ ትክክለኛነት መረጋገጥ /Subject Line and Tone/
#አብዛኛውን ጊዜ ከምንጠቀምባቸው ባንኮች ወይም የፋይናንስ ተቋማት የተላኩ የሚመስሉ የፊሺንግ መዝባሪዎች መልዕክቶች በኢ-ሜይል አድራሻዎቻችን ተልከው እናገኛለን፡፡
በዚህ ወቅት መልዕክቶቹን ከመክፈታችን በፊት ትክክለኛ አድራሻ መሆኑን ወደ ባንኮቹ ወይም ፋይናንስ ተቋማቱ በመደወል ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ አንዳንድ የመልዕክት አድራሻዎች የትክክለኞቹን የፋይናንስ ተቋማት ስያሜ በተወሰነ ፊደል ለውጥ በማድረግ በቀላሉ ለማታለል የሚሞክሩ ናቸው፡፡
አባሪ /Attachments/
#የፊሺንግ ጥቃት ፈጻሚዎች ኢ-ሜይል አካውንታችንን ለመስረቅ የኛን ትኩረት የሚስቡ አባሪ ፋይሎችን የሚልኩልን ሲሆን ፋይሎቹን በምንከፍታቸው ጊዜ የተላኩልን መልዕክቶች ለህገወጥ ተግባር ሆን ተብለው የተሰሩ ማጥመጃዎች በመሆናቸው ኮምፒውተራችንን ለጉዳት ያጋልጣሉ፡፡ በመሆኑም ሁሉም አባሪዎች ጠቃሚ መረጃዎች ናቸው ብሎ ማሰብ ተገቢ አለመሆኑንና የሚላክልንን መልዕክት ከምናውቀው ትክክለኛ አካል የተላከ መሆኑን መረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
አገናኝ /Link/
#ሁልጊዜም በኢ-ሜይል ለሚላኩ አገናኞችን በምንከፍትበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ የተላኩልን ሊንኮች ትክክለኝነታቸውን ለማረጋገጥ ሊንኩን በቀጥታ በድረ-ገጽ ላይ በመተየብ እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ አንዳንድ የፊሺንግ ሊንኮች “Click here”፣ “Preview document” ወይም “Sign In” የሚሉ እንድንከፍት የሚጋብዙ ቃላትን ይጠቀማሉ፡፡
ስልክ ቁጥሮች /Phone Numbers/
#በኢ_ሜይል የሚላኩ የማረጋገጫ ስልክ ቁጥሮችን መጠራጠር ተገቢ ነው፡፡ የተላከልን ስልክ ቁጥሩ ትክክለኛነቱን ከባንክ ደብተር ላይ ከሚገኝ አድራሻ በመውሰድ ደውለን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ አለ በለዚያ በኢ-ሜይል የቀረበልንን መልዕክት በኢ-ሜይል አድራሻችን በተላከ ስልክ ቁጥር ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ከደወልን አጥፊዎች አስቀድመው ያዘጋጁት ቁጥር ከሆነ በሚፈልጉት መንገድ መረጃ በመስጠት ለጥቃት ልንጋለጥ ስለምንችል ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡
═══════════════
╚═════📌Share📌════╝
subscribe to our loved ones and respected followers on Youtube, because we open new youtube channel.
የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe አድርጉ።
🔸Subscribe ያላደረገ video ሊደርሰው ወይም መከታተል አይችልም። click z link below to subscribe
👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
Asra Aratu Qedassie ze Debre Abay Geez
የአስራ አራቱ ቅዳስያት ዘ ደብረ ዓባይ በ ግዕዝ
፩--ግዕዝ ሠራዊት ዘ ቅዳሴ ቅዱስ ሓዋርያት
፪-- ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ እግዚእ
፫--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም
፬--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ወልደ ነጐድጓድ
፭--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ፫፻ (ሥስት ምዕት)
፮-- ግዕዝ ሠራዊት ዘ ቅዳሴ አትናትዎስ
፯--ግዕዝ ሠራዊት ዘ ቅዳሴ ባስልዮስ
፰--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፱--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ኤጲፋንዮስ
፲--ግዕዝ ሠራዊት ዘ ቅዳሴ ዮሀንስ ኣፈ ወርቅ
፲፩--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ቄርሎስ
፲፪--ግዕዝ ሠራዊት ዘ ያዕቆብ ዘሥሩግ
፲፫--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
፲፬--ግዕዝ ሠራዊት ዘ ካልዕ ጎርጎርዮስ
https://youtu.be/a96Oas_BqB0
የአስራ አራቱ ቅዳስያት ዘ ደብረ ዓባይ በ ዕዝል
፩--ዕዝል ሠራዊት ዘ ቅዳሴ ቅዱስ ሓዋርያት
፪-- ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ እግዚእ
፫--ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም
፬--ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ ወልደ ነጐድጓድ
፭--ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ ፫፻ (ሥስት ምዕት)
፮-- ዕዝል ሠራዊት ዘ ቅዳሴ አትናትዎስ
፯--ዕዝል ሠራዊት ዘ ቅዳሴ ባስልዮስ
፰--ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፱--ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ ኤጲፋንዮስ
፲--ዕዝል ሠራዊት ዘ ቅዳሴ ዮሀንስ ኣፈ ወርቅ
፲፩--ግዕዝ ሠራዊት ዘቅዳሴ ቄርሎስ
፲፪--ዕዝል ሠራዊት ዘ ያዕቆብ ዘሥሩግ
፲፫--ዕዝል ሠራዊት ዘቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
፲፬--ዕዝል ሠራዊት ዘ ካልዕ ጎርጎርዮስ
https://youtu.be/7O72WVv0UIA
በኤስዲ ካርዶች ላይ የጽሑፍ ጥበቃን/write protected ለማስወገድ 3 መንገዶች
##############$$$#$######
በዊንዶውስ ውስጥ በኤስዲ ካርድዎ ላይ የመፃፍ ጥበቃ ስህተቶችን ለማስወገድ? ችግሩን ለመፍታት ሶስት ፈጣን መንገዶች እንድምከተው እናያለን።

የኤስዲ ካርድ የመፃፍ ስህተቶች ህመም ናቸው። ትክክለኛውን ኤስዲ ካርድ ሲመርጡ እና በድንገት አዲስ ፋይሎችን በእሱ ላይ እንዲያክሉ ወይም ማንኛውንም ነገር እንዲሰርዙ የማይፈቅድልዎ ከሆነ እንዴት እንደሚጠግኑት ያስቡ ይሆናል።

ደስ የሚለው ነገር እነዚህ በኤስዲ ካርዶች ላይ ያሉ የጥበቃ ችግሮች ለማስተካከል ቀላል ናቸው። በካርድዎ ላይ ያሉትን ማናቸውንም ፋይሎች መቀየር/ራይት ፕሮቴክቲድ በማይችሉበት ጊዜ ለመሞከር ሶስት ፈጣን ዘዴዎች እናያለን።
1. አካላዊ መቀየሪያውን ቀያይር/1. Toggle the Physical Switch

ሁሉም ማለት ይቻላል የኤስዲ ካርዶች በጎን በኩል እንደ መቆለፍ ዘዴ የሚያገለግል ተንሸራታች ያካትታሉ። ከታች ቦታ ላይ ሲሆን ካርዱን ይቆልፋል እና ምንም ነገር እንዳይቀይሩት ይከለክላል. ኤስዲ ካርዱን ከመሣሪያዎ ያስወጡትና ተንሸራታቹ ከመቆለፊያ ቦታው ርቆ ከላይ እንዳለ ያረጋግጡ።
2. የካርዱን ባህሪያት እና ቦታ ይፈትሹ/ Check the Card's Properties and Space

ተንቀሳቃሽ መሣሪያን ወደ ዊንዶውስ ሲያክሉ ወደ እሱ መፃፍ የሚከለክል ቅንብር መቀያየር ይችላሉ። የኤስዲ ካርዱን ይዘት እንዳይቀይሩ በመከልከል ይህን ቅንብር ባለማወቅ ተቀይሮብን ይሆናል።
እሱን ለመፈተሽ ይህን ፒሲ ይክፈቱ እና የእርስዎን ኤስዲ ካርድ በመሳሪያዎች እና አሽከርካሪዎች ስር ይፈልጉ።
√√በቀኝ ጠቅ ያድርጉት እና Right click Properties የሚለውን ይምረጡ። አንዳንድ መሣሪያዎች፣ ነገር ግን ሁሉም አይደሉም፣ እዚህ መቀየር የሚችሉት የጻፍ ጥበቃ መግቢያ አላቸው። በዚህ ቦታ ውስጥ እያሉ የኤስዲ ካርድዎ ሙሉ በሙሉ እንዳልሞላ ያረጋግጡ። የነፃ ቦታ እጥረት የአጻጻፍ ጥበቃ/Right protected ስህተቶችን ሊያስከትል ይችላል.
3. Reset the Card's Attributes የካርዱን ባህሪያት ዳግም ያስጀምሩ

ከላይ ከተጠቀሱት መፍትሔዎች ውስጥ አንዳቸውም ቢሆኑ መፍትሔ ካልሆኑ፣ command prompt/ የትእዛዝ መስመሩን በመጠቀም የካርድዎን የመፃፍ የተጠበቀ ሁኔታ ለማጽዳት መሞከር ይችላሉ።

√√Right-click the Start Button and select Command Prompt (Admin) from the list. √√Type diskpart enter
√√then type list disk enter
√√ select disk
√√ attributes disk clear readonly

የጀምር አዝራሩን በቀኝ ጠቅ ያድርጉ እና ከዝርዝሩ ውስጥ Command Prompt (አስተዳዳሪ)ን ይምረጡ። የምንፈልገውን መሳሪያ ለመክፈት ዲስክን ይተይቡ እና ከዚያ ከማሽንዎ ጋር የተገናኙትን ሁሉንም ድራይቮች ለማሳየት ሊስት ዲስክ ይበሉ።

የ SD ካርድዎ የትኛው እንደሆነ ይወቁ (ከዝርዝሩ ግርጌ አጠገብ ሊሆን ይችላል፣ እና ከሌሎቹ አሽከርካሪዎች ያነሰ ሊሆን ይችላል) እና ቁጥሩን ያስታውሱ።
ከዚያም የሚከተለውን ትዕዛዝ ይተይቡ:
ዲስክ ይምረጡ ...በተሻለ ቪድዮውን በማየት ኤስዲ ካርድ error fix ያደርጋሉ 100% ይሰራል።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
የኮምፑውተር እውቀትዎን ያሳድጉ ግዜዎን ይቆጥቡ
▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️
Button Function on keyboard
👉Ctrl + A : Select All
👉Ctrl + B: bold
👉Ctrl + C: copy
👉Ctrl + D: font
👉Ctrl + E : Center Alignment
👉Ctrl + F : Find
👉Ctrl + G: go to
👉Ctrl + H : Replace
👉Ctrl + I : Italic
👉Ctrl + J : Justify Alignment
👉Ctrl + K: insert hyperlinks
👉Ctrl + L : Left Alignment
👉Ctrl + M: Incrase indent
👉Ctrl + n: new
👉Ctrl + O: open
👉Ctrl + P: Print
👉Ctrl + Q: normal style
👉Ctrl + R : Right Alignment
👉Ctrl + S : Save / Save As
👉Ctrl + T : Hanging Indent
👉Ctrl + U : Underline
👉Ctrl + V: Paste
👉Ctrl + w: close
👉Ctrl + x: cut
👉Ctrl + Y: redo
👉Ctrl + Z: undo
👉Ctrl + 1 : Single Spacing
👉Ctrl + 2 : Double Spacing
👉Ctrl + 5 : 1,5 lines
👉Ctrl + ESC: start menu
👉F1: running the help function provided on word
👉F2: altering name a file / folder
👉F3: running orders command
👉F4: repeating previous orders
Ann: running search and replace command or goto
👉F6.: running other command pane
👉F7: memeriksaan typos and text spelling (spelling)
👉F8: the beginning of the highlight / selection of text or object
👉F9 : Mengupdate Field (Mail Merge)
👉F10: enable menu
👉F11: entering the next field (mail merge)
👉F12: activating the us save dialog
👉ESC: cancel dialogue / command
👉Enter: perform an option or end a paragraph
👉Tab: move text according to the existing tab tags on horizontal ruler
👉Windows: Mengktifkan start menu
👉Shortcut: activating shortcut at cursor position
👉Delete: Remove 1 characters on the right of the cursor
👉Backspace: Removing 1 characters on the left of the cursor
👉Insert: Menyisip character in cursor position
👉Home: move cursor position to the beginning of the line
👉End: move cursor position to end of line
👉Page Up: Roll the screen up
👉Page Down: Roll the screen down
👉Up: MOVE CURSOR 1 line up
👉Down: MOVE CURSOR 1 line down
👉Left: MOVING CURSOR 1 characters to left
👉Right: MOVE THE CURSOR 1 characters to the right
👉Num Lock on: function typing numbers and active math operators
👉NUM LOCK OFF: Active Navigation button function
👉Shift + F10: open the shortcut, just like clicking right
👉Alt: button emphasis that is not combined with other buttons only
Work to enable or start using bar menu
👉Shift + Delete: delete selected items permanently without placing items
In Recycle bin
👉Ctrl + Right Arrow: move the insertion point to the beginning of the next word
👉Ctrl + Left Arrow: move the insertion point to the beginning of the previous word
👉👉Ctrl + Down Arrow: move the insertion point to the beginning of the next paragraph
👉Ctrl + Up Arrow: move the insertion point to the beginning of the previous paragraph
👉Alt + F4: close active items, or log out of active programs
👉Alt + Enter: displaying properties from selected objects
👉Alt + Spacebar: open the shortcut menu for active windows
👉Ctrl + F4: close active documents in programs that allow you To have some open documents simultaneously
👉Alt + Tab: switch between open items
👉Alt + ESC: cycle through items in an open order
👉Ctrl + shift + Tab: move backwards through tabs
👉Shift + Tab: move backwards through options
Version 2:
👉Ctrl + C (copy)
👉Ctrl+X (cut)
👉Ctrl+V (Paste)
👉Ctrl+Z (undo)
👉Delete (delete)
👉Shift+Delete (delete selected items permanently without putting items in recycle bin)
👉Ctrl while dragging (Men-drag) an item (copying selected items)
👉Ctrl + shift while dragging items (make shortcuts to selected items)
👉F2 Button (change the name of the selected item)
👉Ctrl + Right Arrow (move the insertion point (Cursor) to the beginning of the next word)
👉Ctrl + Left Arrow (move the insertion point (Cursor) to the beginning of the previous word)
👉Ctrl + Down Arrow (move the insertion point (Cursor) to the beginning of the next paragraph)