#ጤናረቡዕ
ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የአንጀት ቁስለት ህመምና የአመጋገብ ስርዓት እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያዎች እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።
እንደተለመደው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የአንጀት ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ እንዲሁም የስነ ምግብ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ዘላለም ደበበን ይዘን ቀርበናል።
ስለባለሙያዎቹ በዝርዝር ከላይ በፎቶ አያይዘናል።
ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!
@tikvahethmagazine @ibdeth

👏3❤2👍2
ውድ ቤተሰቦቻችን
በ #ጤናረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለ አንጀት ቁስለት እና አመጋገብ ስርዐት ከ ዶ\ር ዘላለም ደበበ እንዲሁም ዶ\ር ሀይለሚካኤል ደሳለኝ ጋር የቀጥታ ስርጭት ቆይታ ነበረን።
የድምጽ ቅጂውን በዩትዩብ ገጻችን የለቀቅን ሲሆን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን መከታተል ይችላሉ።
እናመሰግናለን!
https://youtu.be/TXT4DFTlcoU

YouTube
IBD & Diet | የአንጀት ቁስለት እና አመጋገብ ስርዐት
#Podcast
የአንጀት ቁስለት ህመምና የአመጋገብ ሥርዓትን በተመለከተ ከአንጀት ስፔሻሊስቱ ዶ\ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ እንዲሁም ከሥነ ምግብ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ\ር ዘላለም ደበበ ጋር የነበረንን ቆይታ በቀጥታ መከታተል ያልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን የድምፅ ቅጂውን ማዳመጥ ይችላሉ።
Listen to the recorded podcast where we discuss Inflammatory Bowel Disease and…

🙏7👍5👏1
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ
ውድ የጤና ረቡዕ ተከታታዮቻችን በዚህኛው የጤና ረቡዕ የዝግጅት ምዕራፍ "ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ" በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተከታታይ ሳምንታት እናቀብላችኋለን፡፡
እንደሚታወቀው በአሁኑ የክረምት ወቅት በሀገራችን በተማሪዎችም ሆነ በሰራተኞች ዘንድ የተወሰነ የስራ መቀዛቀዝ የሚስተዋልበት ጊዜ እንደመሆኑ የአዕምሮ ጭንቀትና ድባቴ በርከት ያሉ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተለያየ ስር የሰደደ ህመም ባጋጠማቸው ሰዎች ላይ በተወሰነ መልኩ ተባብሶ ይታያል፡፡
ለዚህም ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት ስለ የአዕምሮ ጤናና የሆድ እቃ፣ እንደ የአንጀት ቁስለት ያሉ ስር የሰደዱ ህመሞችና የመድሃኒቶቻችው የጎንዮሽ ጉዳት በአዕምሮ ጤና ላይና የእነዚህ ስሜቶች ተግባሪያዊ ማሳያዎችና መፍትሄዎችን እንዳስሳለን፡፡
በአራተኛውና በመጨረሻው ሳምንትም ባለሞያ ጋብዘን በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ከእናንተ የሚመጡልንን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭት የምንመልስ ይሆናል።
በዚህ ሳምንትም፦
✔️ የአዕምሮ ጤናና የሆድ እቃ ጤና እንዴት ይገናኛሉ?
✔️ የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ተፅዕኖ በአዕምሮ ጤና ላይ
✔️ ከአካባቢያዊ ሁናቴዎችና የአኗኗር ዘይቤ ተፅዕኖ በአዕምሮና በሆድ ዕቃ ጤና ላይ በሚሉት ርዕሶች ላይ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ይዘን ቀርበናል፡፡
የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://telegra.ph/Healthy-Gut-Healthy-Mind-08-17

Telegraph
Healthy Gut, Healthy Mind
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ የሆድ እቃና አዕምሮዋችን እንዴት ይገናኛሉ? የሆድ እቃና አዕምሮ፤ የሆድ እቃ- አዕምሮ ዘንግ ( Gut- brain axis ) በሚባል የመረጃ ማስተላለፊያ አውታር ከአንጎል ወደ ታች የሆድ እቃ ድረስ፣ እንዲሁም ከሆድ እቃ ወደ ላይ አንጎል ድረስ ይገናኛሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ዋና የሚባሉ የሰውነት ክፍሎቻችን ይህን ግንኙነት የሚያስቀጥሉበት የተለያዩ መንገዶች አሏቸው፡፡ ከእነዚህም…
👏3👍2
Forwarded from Crohn's And Colitis Ethiopia
እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል አደረሳችሁ
ክሮንስ ና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
ክሮንስ ና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
👍4❤1
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ ለህክምና ተማሪዎች!
የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም
ይህ የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም በአይነቱ ለየት ያለ ለህክምና ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን፤ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት ጤና ስፔሻሊስት መሆን ለሚሹ ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት ህክምና ትምህርት ላይ ላሉ የተዘጋጀ ነው።
ይህ እድል በአለማችን ላይ ስላሉት ከአንጀት ቁስለት ህመም ህክምና ጋር የተያያዙ ጉድለቶች እንዲሁም ከዚህ ህመም ጋር ያሉ ወጣት እና ጎልማሳ ሰዎች ምን አይነት የህክምና ትኩረት ይፈልጋሉ የሚለውን ይዳስሳል።
መስፈርት
-ማንኛውም አመት ላይ ያለ የህክምና ተማሪ
-የአንጀት ጤና ስፔሻሊቲ የመማር ፍላጎት
-ከየትኛውም የአለማችን ክፍል
ፕሮግራም
- 90 በመቶ የወርሀዊ ውይይት ዝግጅት መሳተፍ
- በየወሩ ከሚደረገው ስብሰባ በኃላ ስለ ስብሰባው የሚጻፍ ጽሁፍ መሳተፍ\ማገዝ
- ከአንጀት ቁስለት ህመም ጋር የሚኖሩ ወጣቶች ጋር በቅርበት ስለሚያስፈልገው ልዩ ትኩረት መረዳት
- ከድርጅቱ የህክምና አማካሪ ቦርድ እና አመራር ጋር በቅርብ መገናኘት
- በአመት አንድ ጊዜ ለሚካሄደው የአንጀት ቁስለት ህመም ኮንፈረንስ በፈረንጆች አቆጣጠር 2023 አመተ ምህረት ላይ ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድል (የጉዞ ድጋፍ እስከ 1000 የአሜሪካ ዶላር)
ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfflOypTySxTtFYjoGKvbojfO2EV7-vKSMoyz2Kaf9OZv3srA/viewform
በ #ጤናረቡዕ ላይ ስትሳተፉ የነበራችሁ የህክምና ተማሪዎች @IBDETHIOPIA ላይ በመጻፍ የምስክር ደብዳቤ ማግኘት ትችላላችሁ።

👍6❤1
#quickfact
በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:-
✔️የወር አበባ ምንድን ነው?
✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት
✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል
በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን።
ማስፈንጠሪያውን በመጫን በሰፊው ያንብቡ ።
https://telegra.ph/IBD--Menses-08-20

IBD & Menses Part 1
የወር አበባ ዑደትና የአንጀት ቁስለት የወር አበባ ምንድነው? የወር አበባ ዑደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ (የእንቁላል አቃፊ) ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን (ውደት) በተባለ ስርዓት አንድ እንቁላል ይወጣል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የተለያዩ የሆርሞን ለውጦች ማህጸንን ለእርግዝና…
👍5❤2
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ
የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና
[ በ @ibdeth የቀረበ ]
- አካላዊ ጤና እና የአመጋገብ ስርዓት ዘርፈ ብዙ ተዛምዶ አላቸው።
- ደካማ የአመጋገብ ሥርዓት ለወረደ ስሜት አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በሌላ ጎኑ ተገቢ የአመጋገብ ሥርዓት ጉልህ በሚባል ደረጃ የአዕምሮን ጤና ያሻሽላል።
- የአመጋገብ ስርዓታችን በሆድ እቃችን ውስጥ በሚገኙ ረቂቅ ተህዋሳት ላይ በሚያመጣው ተፅዕኖ የአዕምሮን ጤና ላይ በተላያየ መንገድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል።
- የዘወትር የማዕዳችን ሥርዓት፥ እንደ ትኩራት ማጣት እና በስሜት ግፊት ነገሮችን በማድረግ የሚገለጠውን Attention Deficit Hyperactivity Disorder/ADHD/ ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ጋር ተያያዥነት አለው።
- ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ በተላዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን የተለያዩ የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ላይ እራሱን ችሎ ወይም እንደ አባሪ መድኃኒት መጠቀም ስኬታማ ውጤትን አሳይቷል።
- የአመጋገብ ሥርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በአዕምሮ ምግቦች የበለጠጉ ምግቦችን መጠቀም ስኬታማ እና በእንፃራዊ መልኩ ደግሞ ቀላል በሆነ መንገድ የአይምሮ ጤናን ለማሻሻል እንዲሁም ከአይምሮ ህመም ለማገገም አይነተኛ መንገዶች ናቸው።
🔗 ተጨማሪ በ 👉 INSTANTVIEW ያንብቡ
@tikvahethmagazine @WriteforTikvahbot

Diet & Mental Health
የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና አካላዊ ጤና እና ምግብ ያላቸውን ተዛምዶ በተመለከተ ለረጅም ጊዜ የጥናት እና ምርምር ዋና ርዕሰ ጉዳይ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን፣ የአመጋገብ ሥርዓት እና የአይምሮ ጤና ስላላቸው ግንኙነት ማወቅ ልዩ ትኩረትን አግኝቷል። ✔️አንጎላችን የገንቢ ምግቦች እንዲሁም ንጥረ ምግቦች አቅርቦትን በከፍተኛ መጠን ይፈልጋል። አንጎላችን በቀን ውስጥ ከምንጠቀመው ምግብ የምናገኘውን…
👍4
Crohn's & Colitis Ethiopia
#quickfact በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:- ✔️የወር አበባ ምንድን ነው? ✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት ✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን። ማስፈንጠሪያውን በመጫን…
Telegraph
IBD & Menses
#quickfact የወር አበባ ዑደትና የአንጀት ቁስለት መፍትሔዎች 🟣 ህመሙ ከፍተኛ ከሆነ፣ ሀኪምን አማክሮ የህመም ማስታገሻን መውሰድ፤ 🟣 የእርግዝና መከላከያዎች ፡- እርግዝናን ከመከላከል ባሻገር ከሰውነታችን ሆርሞኖች ጋር መስተጋብር ስላላቸው የወር አበባ ዑደትን መዛባት የማተካከልና በዑደቱ ወቅት የሚከሰተውን ከፍተኛ የሆነን ቁርጥትና ህመም የመቀነስ ባህሪይ አላቸው፡፡…
❤3
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ
- ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና
✔️ የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴን በመፍጠር በአንድ ሰው ህይወት ላይ እክልን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
✔️በሌላ በኩል ፣ የአእምሮ ጭንቀት ሁኔታ ሲከሰት የተለያዩ የስር የሰደዱ ህመሞች ምልክቶች እና የህመሞቹን መልሶ መቀስቀስ ሊያስከትል ይችላል፡፡
👉ከሁለቱ የቱም ይቅደም የቱ፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በቀጥታ ስር የሰደዱ ህመሞችን ላያስከትሉ ቢችሉም ቀድሞ ለተፈጠረው ህመም አፀፋዊ ምላሽ ናቸው፡፡
👉ከጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በተጨማሪ ስር የሰደዱ ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ተጨማሪ የስሜት ለውጦችን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፡፡
ሆኖም ያጋጠመንን ህመም መቀበል የለት ተዕለት ኑሯችንን በተገቢው ሁኔታ ለማስኬድ፣ የሀኪማችንን ምክር በአግባቡ ተቀብሎ ለመፈፀም እና ጤናማ ህይወት ለመኖር ይረዳናል፡፡
🔗 ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/NCDs--Mental-Health-08-31
#በቀጣይሳምንት
በቀጣይ ሳምንት እስካሁን ስንወያይበት በቆየንበት ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ በሚለው ዙሪያ ባለሙያ ጋብዘን፤ ከእናንተ የሚደርሱንንም ጥያቄዎች አካተን ሰፊ ማብራሪያን በቀጥታ ስርጭት ይዘን እንቀርባለን፡፡
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያሎትን ጥያቄ በ @IBDETHIOPIA ያድርሱን!

NCDs & Mental Health
ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴን በመፍጠር በአንድ ሰው ህይወት ላይ እክልን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የእነዚህ የህመም ስሜቶች በስራ፣ በትምህርት፣በግንኙነት፣በመጓጓዝ እና በአካላዊ እና ስሜታዊ ጤንነት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ፣ የአእምሮ ጭንቀት ሁኔታ ሲከሰት የተለያዩ የስር የሰደዱ ህመሞች ምልክቶች እና የህመሞቹን መልሶ…
👍6❤1
#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ
ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር
በጤና ረቡዑ ‹‹ ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አእምሮ›› በሚል ርዕስ ላለፉት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡
በቀጣይ ሳምንት በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር በቀጥታ ስርጭት ውይይት እናደርጋለን።
ከምንዳስሳቸው ርዕሶች ውስጥ:-
✔️ስር የሰደደ ህመም ከአእምሮ ጤና ጋር ያለውን ግንኙነት እንቃኛለን።
✔️የአንጀት ቁስለት ህመም እና ተመሳሳይ ህመሞች ያለበት ሰው እንዴት የስነ ልቦና ጤናውን መጠበቅ እንደሚችል እንወያያለን።
✔️የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ ቀን በቀን መተግበር ያለብንን የተለያዩ ተግባሪያዊ የስነልቦና የጤና ስልቶች በዝርዝር እናያለን።
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲብራራሎት የሚፈልጉት ጥያቄ አሎት?
በ @IBDETHIOPIA መልዕክቶን ይላኩልን፡፡ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ተገቢውን ማብራሪያ እና ምላሽ በባለሙያ እንዲሰጦ እናደርጋለን፡፡
👉 ከዚህ በተጨማሪም ከእንግዳችን ከስነ-አዕምሮ ባለሙያው ናትናኤል ጋር የአንድ ለአንድ የስነ-ልቦና ድጋፍና ምክክር ለሚፈልጉ የትና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ከቀጥታ ስርጭቱ በሗላ የምናሳውቅ ይሆናል።
ይከታተሉን!

🙏4
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ
🟣ማስታወሻ
ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የሆድ እቃ ጤናና የአእምሮ ጤና እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያ እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።
ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆነውን ናትናኤል ሰይፉን ይዘን እንቀርባለን።
ይከታተሉን!
በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

👍8
ውድ ቤተሰቦቻችን
በዚህ ሳምንት #ጤናረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለ የሆድ እቃ ጤናና የአእምሮ ጤና የስነ-ልቦና ባለሙያ ከሆነውን ናትናኤል ሰይፉ ጋር የቀጥታ ስርጭት ቆይታ ነበረን።
የድምጽ ቅጂውን በዩትዩብ ገጻችን የለቀቅን ሲሆን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን መከታተል ይችላሉ።
https://youtu.be/z6OK9ZCerfY
እናመሰግናለን!
@ibdeth

#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር በጤና ረቡዑ ‹‹ ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አእምሮ››
#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ
ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር
በጤና ረቡዑ ‹‹ ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አእምሮ›› በሚል ርዕስ ላለፉት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡
በቀጣይ ሳምንት በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር በቀጥታ ስርጭት ውይይት አድርገናል።
ከዳሰስናቸው ርዕሶች ውስጥ:-
✔️ስር የሰደደ ህመም ከአእምሮ ጤና ጋር ያለውን ግንኙነት
✔️የአንጀት ቁስለት ህመም እና ተመሳሳይ…

ውድ የጤና ረቡዕ ተከታታዮቻችን በዚህኛው የጤና ረቡዕ የዝግጅት ምዕራፍ "ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ" በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተከታታይ ሳምንታት እናቀብላችኋለን፡፡
ከምንዳስሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ
👉 የጤናማ ስነ-ተዋልዶ ምንነትና የጤናማ ስነ-ተዋልዶና የሆድ እቃ ጤና ግንኙነት፤የስነ- ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን፤ ስር የሰደዱ ህመሞችና የስነ-ተዋልዶ ጤና (በወንዶችና በሴቶች ላይ)፤ የጤናማ የሆድ እቃና የወር አበባ ዑደት፣እርግዝና፣የእርግዝና መከላከያዎች፣ ጡት ማጥባትና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት ይገኙበታል።
በመጨረሻው ሳምንትም ባለሞያ ጋብዘን በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ከእናንተ የሚመጡልንን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭት የምንመልስ ይሆናል።
በዚህ ሳምንት፦
👉ጤናማ ስነ-ተዋልዶ ምን ማለት ነው?
☑️ የስነ- ተዋልዶ ጤና
የስነ- ተዋልዶ ጤና ማለት ከተዋልዶ ጤና ጋር ተያይዞ የተሟላ የአካል፣ የስሜት፣የአዕምሮ፣ እንዲሁም የማህበራዊ ጤንነት ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የበሽታ አለመኖር ወይም የመራቢያ አካላት ተገቢውን የተግባር ሂደት መተግበር መቻልን ያካትታል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ሁኔታ የሚገኙ ነገሮች የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮች ናቸው፡፡
☑️ የጤናማ ስነ-ተዋልዶና የሆድ እቃ ጤና ግንኙነት
🔘ጤናማ የሆድ እቃ ፤ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያንና በሽታ ተከላካይ ጥቃቅን ህዋሳትን ስለሚይዝ ሰውነታችንን እንደ ባክቴሪያ ፣ቫይረስና ፈንገስ ካሉ በሽታን ከሚያስከትሉብን ነገሮች ይከላከልልናል።
🔘ከዚያ በተጨማሪም ጤናማ የሆድ እቃ በነርቭና ሆርሞኖች አማካኝነት ከጭንቅላት ጋር ስለሚገናኝ አጠቃላይ የሰውነት ጤናችንን ለመጠበቅም ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡ ከዚህም ውስጥ የሰውነት ሆርሞኖች የማመንጨት፣ ማዋሃድና ማሰራጨት ሂደት ላይ ያለው አስተዋጾ ይጠቀሳል፡፡ በዚህም ምክንያት የሆድ እቃ ጤናችን ከስነ- ተዋልዶና መራባት ሂደትን ጋር በቀጥታ ይገናኛል ማለት ይቻላል፡፡
የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
https://telegra.ph/Gut-Health--Reproductive-Health-09-14

Gut Health & Reproductive Health
ጤናማ ስነ-ተዋልዶ ምን ማለት ነው? የስነ- ተዋልዶ ጤና የስነ- ተዋልዶ ጤና ማለት ከተዋልዶ ጤና ጋር ተያይዞ የተሟላ የአካል፣ የስሜት፣የአዕምሮ፣ እንዲሁም የማህበራዊ ጤንነት ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የበሽታ አለመኖር ወይም የመራቢያ አካላት ተገቢውን የተግባር ሂደት መተግበር መቻልን ያካትታል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ሁኔታ የሚገኙ ነገሮች የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮች ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ሲሰራ…
👍4
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ - 2
👉የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን
- የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖች፤ በወንዶችና በሴቶች አጠቃላይ የስነ-ተዋልዶ ጤና፣የጉርምስና የሰውነት ለውጦች ላይ እንዲሁም በሰውነት እድገት፣ ፆታዊ ጠባይና መገለጫዎች ላይ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡
- የስነ- ተዋልዶ ሆርሞኖች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ፤ ኤስትሮጅን/ፕሮጀስትሮን እና ቴስተስትሮን ናቸው፡፡
👉የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ግንኙነት
- የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን በአንጀትና በሆድ እቃ መዋቅር ላይ ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ እነዚህ ተህዋሲያን የሆድ እቃን ጤናማነት ከመጠበቅ ባሻገር በርከት ባሉ የሰውነታችን ሂደቶች ውስጥም ይሳተፋሉ፡፡
- የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን መጠን መዛባት ሲከሰትና እነዚህ ረቂቅ ተህዋሲያን ከምንመገበው ምግብ ውስጥ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ወደ ሰውነት እንዲመጠጥ ማድረግ ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰተው የአልሚ ምግቦች እጥረትም ለሆርሞኖች መጠን መዛባት እንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የሆርሞኖች መዛባቱ ደግሞ በስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችም ላይ ይታያል፡፡
👉ስር የሰደዱ ህመሞችና የስነ-ተዋልዶ ጤና
- ስር የሰደዱ ህመሞች የሚባሉት ለረጅም ጊዜ የቆዩ ህመሞች ሆነው የእለት ተዕለት ኑሮዋችንን በአግባቡ ለመምራት እንቅፋት የሚሆኑብንና ቀጣይነት ያለው የህክምና ክትትል የሚፈልጉ ናቸው፡፡
- ስር በሰደዱ ህመሞች በተጠቁ ታካሚዎች ዘንድ የስነ-ተዋልዶ ጤናቸው ከህመሞቹ ባህሪ፣ሰውነታችን ለህመሞቹ ከሚሰጠው ምላሽና ህመሞቹን ለመቆጣጠር ከሚታዘዙ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ በተለያየ መንገድ ይጠቃል፡፡
የበለጠ ለማንበብ ሊንኩ ይጫኑ።
https://telegra.ph/Gut-Health-Reproductive-Health-09-21

Gut Health, Reproductive Health
የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ☞ የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖች የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖች፤ በወንዶችና በሴቶች አጠቃላይ የስነ-ተዋልዶ ጤና፣የጉርምስና የሰውነት ለውጦች ላይ እንዲሁም በሰውነት እድገት፣ ፆታዊ ጠባይና መገለጫዎች ላይ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የሆርሞኖቹ ውቅርና ውህደት መነሻ ከተመሳሳይ ህዋስ ቢሆንም በሰውነታችን ውስጥ የሚገለጹበት መንገድና የስርጭት ሂደታቸው በስነ-…
#ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-3
የወር አበባ ዑደት፣ ጤናማ የሆድ እቃና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት
✔️ የስነ- ተዋልዶ ጤና፤ ከተዋልዶ ጤና ጋር ተያይዞ የተሟላ የአካል፣ የስሜት፣የአዕምሮ፣ እንዲሁም የማህበራዊ ጤንነት ማለት እንደመሆኑና ከዚህም በተጨማሪ የበሽታ አለመኖር ወይም የመራቢያ አካላት ተገቢውን የተግባር ሂደት መተግበር መቻልን ያካተተ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ደግሞ የተስተካከለና ጤናማ የወር አበባ ዑደት አንዱ ነው።
👉የወር አበባ ዑደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡
👉ይህ የወር አበባ ዑደት ከሆድ እቃ ጤና ጋር በእጅጉ ይቆረኛል።ጤናማ የሆድ እቃ በነርቭና ሆርሞኖች አማካኝነት ከጭንቅላት ጋር ስለሚገናኝ አጠቃላይ የሰውነት ጤናችንን ለመጠበቅም ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡ከዚህም ውስጥ የሰውነት ሆርሞኖች የማመንጨት፣ ማዋሃድና ማሰራጨት ሂደት ላይ ያለው አስተዋጾ ይጠቀሳል፡፡ የወር አበባ ዑደት ደግሞ የተለያዩ የሆርሞን ለውጦች ዉጤት እንደመሆኑ በሆድ እቃና በሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያኖች ጤና መዛባት ምክንያት የሚከሰት የሆርሞኖች መዛባት ጤናማ የወር አበባ ዑደትን ሊያዛባው ይችላል።
👉 ስር በሰደዱ ህመሞች፣ ማለትም፤ ለረጅም ጊዜ የቆዩና ቀጣይነት ያለው የህክምና ክትትል በሚፈልጉ ህመሞች ውስጥ የሚያልፉ ሴቶች የወር አበባ ዑደት እንደህመሙ ደረጃና እንደ ሰው የሰውነት ሁኔታ ይለያያል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ከሚጠቀሱት ውስጥ፤ ስር በሰደዱት ህመሞች ንቁ ደረጃ ላይ የሚከሰተው የሰውነት መቆጣት ፤የሰውነታችን መደበኛ የሆርሞን ስራ እንዲዛባ ምክንያት ስለሚሆን የወር አበባ ዑደትም በዚሁ ምክንያት ሊዛባ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል የተደረጉ ቀዶ ህክምናዎች፣ የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶችና ሲጋራን ማጨስም እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
https://telegra.ph/Gut-Health-Reproductive-Health-09-28-2

✔️ የወር አበባ ዑደት፣ ጤናማ የሆድ እቃና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት ☞ የወር አበባ ዑደት ምንድነው? የወር አበባ ዑደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ (የእንቁላል አቃፊ) ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን (ዑደት) በተባለ ስርዓት አንድ እንቁላል ይወጣል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ…
❤3👍1